Telegram Web Link
ቅዱስ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ እንዳረፉ
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
ቅዱስ አቡነ ገብረ መንፈስቅዱስ እንዳረፉ
🍀🍀🍀
❮ ነፍስሽን በሰማይ አድናታለሁ ❯
🍀🍀🍀

#አቡነ_ገብረ_መንፈስቅዱስ በበዓላቸው ወቅት ያደረጉት ተአምር ይህ ነው።

በአንዲት አገር ውስጥ የአቡነ #ገብረ_መንፈስቅዱስን ዝክር የምታዘክር አንዲት ሴት ነበረች፡፡ ዝክራቸውንም እንድትዘክር አንድ ጻድቅ አባት ነግረዋታልና፡፡

ከዕለታትም በአንደኛው ቀን የአገሩ ልጆች በአንድ ትልቅ ገደል ሥር ተሰብስበው እየተጫወቱ ትልቁ ገደል በላያቸው ላይ ወደቀባቸውና ሁሉም ልጆች ወዲያው ሞቱ፡፡ አንድ ስንኳ የተረፈ የለም፡፡

የእነዚያም ልጆች ወላጆቻቸውና ዘመዶቻቸው ታላቅ ልቅሶን አለቀሱላቸው፡፡ ይህም የሆነው በመጋቢት ሦስት ቀን ነው፡፡

ልጆቹም ከሞቱ በኋላ ሦስት ሰዓት በሆነ ጊዜ የዚያች የአባታችንን ዝክር የምታዘክረው ሴት ልጅ ከሞተ በኋላ ተነሣ፤ ከተቀበረበትም ወጣ፡፡ ፀሐይም ከመጥለቋ አስቀድሞ ወደ ቤቱ ሄዶ ከእናቱ ዘንድ ደረሰ፡፡

እናቱም ስታየው በደስታ ጮኸች፡፡ የሀገሪቱም ሰዎች ሁሉ ተሰብስበው ወደ እርሷ መጡና ሞቶና ተቀብሮ የነበረውን የሴቲቱን ልጅ አሁን በሕይወት ሲያገኙት እጅግ አደነቁ፡፡

ልጁንም ‹‹ከሞት እንዴት ተነሣህ?›› አሉት፡፡ ልጁም እንዲህ አላቸው፦ ‹‹የሞትነውን ልጆች ሁላችንንም የእሳት ነበልባል የሚመስሉ መላእክት ወደ ሰማይ ወሰዱን፡፡ ከዚያም በኋላ በመንገድ ከአንድ ትልቅ ሰው ጋር ተገናኘን። የራስ ጠጉሩ እንደበረዶ ነጭ ነው። እንደተፈተለም ነጭ ሐር ነው፡፡

   እንደ መብረቅ ያለ ልብሱንም ባየን ጊዜ ልጆች ሁላችን ደንግጠን ወደቅን፡፡ እርሱንም የሚከተሉት እንደ ሰማይ ከዋክብት ነበሩ፡፡ ከልጆቹም ሁሉ እኔን ለይቶ ብቻዬን እጄን ያዘኝ፡፡

  መላእክትንም ‹ይህንን መታሰቢያዬን የምታደርግልኝ የዚያችን ሴት ልጅ ለምን አመጣችሁት? አሁንም እኔ ወደ እናቱ መልሼ እወስደዋለሁ› አላቸው፡፡

  ያንጊዜ በገደል ተቀብሬ ወደነበርኩበት ወደ በድኔ መለሰኝ፤ በሥላሴም በመስቀል ምልክት ሦስት ጊዜ ባረከ፤ ገደሊቱም ቀጥ ብላ ቆመች። በድናችንንም ተቀጥቅጦ እንደ አመድ ሆኖ አገኘነው፡፡

  ያን ጊዜም እጄን ይዞ አስነሣኝና ‹አንቺ ነፍስ ወደ ሥጋሽ ተመለሺ ብሏል እግዚአብሔር› አለ፡፡ ያንጊዜም ነፍሴ ወደሥጋዬ ተመለሰች፤ እንደቀድሞውም ሆንኩ፡፡

ገደሊቱንም ‹በሦስተኛው ቀን እስክመለስ ድረስ ተደፊ› አላት፤ ገደሊቱም ወደ መሬት ተደፋች፡፡ ያንጊዜም ‹ሂድ ወደ እናትህ ተመለስና እናትህን ‹እነሆ ልጅሽን ላኩልሽ እንዲሁም ነፍስሽን በሰማይ አድናታለሁ ብለህ ንገራት› አለኝ፡፡ ከዚህም በኋላ ከሩቅ ጠራኝና ‹እናትህ ስሙ ማነው ብላ ብትጠይቅህ ያ የታመንሽበት #ገብረ_መንፈስቅዱስ ነው› ብለህ ንገራት› ብሎኝ ከእኔ ተሰወረ፡፡ እኔም ወደ እናንተ መጣሁ›› አላቸው፡፡

ከዚያ የነበሩና የልጁንም ምስክርነት የሰሙና አባታችን ልጁን ከሞት እንዳስነሡት ያዩ የሀገሩ ሰዎች ሁሉ በመደነቅ ‹‹የአባታችንን መታሰቢያ ለማድረግ ነፍሳችንንም ሥጋችንንም ሥዕለት አድርገን ለመስጠት ወስነናል፡፡ ገንዘባችንን ከብቶቻችንን ሁሉ ሰጥተናል›› እያሉ ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

በሦስተኛውም ቀን መንፈቀ ሌሊት በሆነ ጊዜ ማለትም በዕረፍታቸው ዕለት መጋቢት 5 ቀን በሆነ ጊዜ የሀገሪቱ ሰዎች ወንዶችም ሴቶችም ቀሳውስት ዲያቆናት ሁሉ ተሰብስበው ዕጣን መብራት ይዘው ወደ ቤተ ክርስቲያን ገቡ፡፡

ያን ጊዜም ገደል ተጭኗቸው ሞተው የነበሩ እነዚያ ልጆች ሁሉም በአቡነ #ገብረ_መንፈስቅዱስ ጸሎት ከሞት ተነሥተው በእጃቸው መብራት ይዘው ‹‹ይህ አባታችን #ገብረ_መንፈስቅዱስ ሙታንን ከመቃብር የሚያስነሣ ተአምረኛ ነው፤ እግዚአብሔር በቅዱሳኑ ላይ የሚደነቅ ነው›› እያሉ በመዘመር ከመቅደስ ወጡ፡፡

እንዲህም እያሉ ከእናቶቻቸውና ከአባቶቻቸው ከዘመዶቻቸውም ጋር ተገናኙ፡፡ በደስታና በእልልታም ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡

የአባታችን የአቡነ #ገብረ_መንፈስቅዱስ ልመናቸው በተዋሕዶ ልጆች በሁላችን ላይ ይደረግልን በረከታቸው ይደርብን።

የዓሥራት ሀገራቸውን ቅድስት ኢትዮጵያን ከታዘዘ መቅሰፍት ይጠብቁልን ለዘለዓለሙ አሜን፡፡

(ምንጭ፦ አለቃ አያሌው ታምሩ የተረጎሙት ገድለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘአኅተሞ ተስፋ ገብረ ሥላሴ፣ 1992 ዓ.ም)
Audio
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት 7 ዓይነት ደብዳቤዎች
ለመላው የአዳም ዘር በሙሉ በድምፅ የቀረበ

ክፍል
3
🟢 🟡 🔴
መጋቢት 7 | #_ጻድቁ_ንጉሥ_ቴዎድሮስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ነው፨

በሃገራችን ታሪክ በጣም ተወዳጅ ከነበሩ ነገሥታት ጻድቁ ቴዎድሮስ ቅድሚያውን ይወስዳል። በርግጥ በርካቶቻችን የምናውቀው ስለ ሃገሩ ፍቅር ራሱን የሰዋውን ዳግማዊ (ሁለተኛውን) ዐፄ ቴዎድሮስን (1845-1860) ነው።

በበጎ ሥራውና በቅድስና ሕይወቱ የተመሠከረለት ግን ዛሬ የምናስበው ቀዳማዊው ሲባል፣ መይሳው ካሳ ዳግማዊ ቴዎድሮስ፣ በኢትዮጵያ ትንሣኤ ዘመን ዓለምን የሚመራው ደሞ ሣልሳዊ ቴዎድሮስ እንላቸዋለን።

ቀዳማዊ ዐፄ ቴዎድሮስ የደጉ ዐፄ ዳዊት (ጒንደ መስቀሉን ያመጡት) እና የተባረከችው ሚስታቸው የፅዮን ሞገሳ ልጅና የጻድቁ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድም ነው።

በኢትዮጵያ ለ3 ዓመታት (ከ1396-1399) ብቻ ነግሦ እያለ እንደ ንጉሥ ሳይሆን፦

● ከጠዋት እስከ ማታ ድሃ እንዳይበደል ፍርድ እንዳይጓደል ይታትር የነበር፣

● ጾምና ጸሎትን የሚያዘወትር፣

● ወገገቡን ታጥቆ ነዳያንን የሚያበላ፣

● ለአብያተ ክርስቲያናትም የሚጨነቅ ደግ ሰው ነበር።

ስለዚህም በሕዝቡ እጅግ ተወዳጅ ነበር። በነገሠ በ3 ዓመቱ ዐርፎ በዝማሬና በለቅሦ ሥጋውን ተሸክመው ሲሔዱ ወንዝ ተከፍሎላቸዋል። ከመቃብሩም ላይ ጸበል ፈልቋል::

🍀 👑 🍀 👑 🍀
#ዘለዓለም_ሥላሴ ደጉን መሪና ሰላማዊውን ዘመን ያቅርቡልን። የታደልን ያድርጉን። አሜን።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930
#መጋቢት_7
#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

ምንም ትምህርት አልሆንልህ ብሏቸው የሰው መሳለቂያ የሆኑትን አባ ጊዮርጊስ ከዕለታት አንድ ቀን እመቤታችን ተገልጻ፦

‹‹አይዞህ አታልቅስ፤  ትምህርት ተከልክሎብህ ሳይሆን የምትጠቀምበት  ጊዜው እስኪ ደርስ ነው፤ አሁን ጊዜዉ ደርሷል›› አለቻቸው። ‹‹እስከ ፯ ቀን በዚሁ እንዳለህ ጠብቀኝ›› ብለውም ተሠወረች።

እርሳቸውም ተስፋውን ተቀብለው በሱባዔ እንዳሉ እንደተለመደው በሥዕለ ማርያም ሥር ተደፍተው ሲያለቅሱ እመቤታችን ቅድስት #ድንግል_ማርያም የመላአክት አለቃ #ቅዱስ_ዑራኤልን አስከትላ ጽዋ እሳት (ጽዋ ልቦና እንዳጠጣው ዕዝራ ሱቱኤልን) የሕይወት ጽዋ አጠጣችው።

አባ ጊዮርጊስ የሕይወት ጽዋ ከተጎነጩ በኋላ የሰማይና የምድር ምሥጢር ተገለጸላቸው።

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የደረሱት መጽሐፍት ከሃምሳ በላይ ይሆናሉ፡፡ በስም የሚታወቁት ግን 

📚 ሰዓታት ዘመዓልት ወዘሌሊት፣

📚 ኖኅተ ብርሃን ከመጽሐፈ አርጋኖን ጋር አብሮ ታትሟል፣

📚 ውዳሴ መስቀል፣
📚 መዓዛ ቅዳሴ፣

📚 ውዳሴ ሐዋርያት፣
📚 አርጋኖነ ውዳሴ፣
📚 ፍካሬ ሃይማኖት፣
📚 መጽሐፈ ምሥጢር፣
📚 ውዳሴ ስብሐት፣
📚 እንዚራ ስብሐት፣
📚 ሕይወተ ማርያም፣
📚 ተአምኖ ቅዱሳን፣
📚 መጽሐፈ ብርሃን እንዲሁም ጸሎት ዘቤት ናቸው፡፡

አባ ጊዮርጊስ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ የተሞሉ አባት ናቸው፡፡

አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ
‹‹ኮከበ ክብር፣ ጽዱል፣ ፀሐዬ አግዓዚ፣ ብሩህ፣ አቡነ ጊዮርጊስ ጥዑመ ስመ ወሠናየ ግዕዝ፣ መጋቤ  ሃይማኖት ወመሠረተ ቤተ ክርስቲያን — አባታችን ጊዮርጊስ ዘጋስጫ የሚያበራ የክብር ኮከብ፣ የኢትዮጵያ ብሩህ ፀሐይ፣ ስሙ የሚጣፍጥ፣ ምግባሩ የቀና ነው።››

(ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)
🟢 🟡 🔴
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፨

~ መጋቢት 8 | #_ቅዱስ_ማትያስ_ሐዋርያ የዕረፍቱ በዓል ነው፨

🌿 ቅዱስ ማትያስ ሐዋርያ 🌿

~ በቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ከእመቤታችን በቀር ከቅዱሳን ሐዋርያት የሚበልጥ አልተነሣም።

ከእነዚህም ሐዋርያ አባቶቻችን፥ ስም አጠራሩ ይክበርና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቤተሰቦቼ ብሎ ከመረጣቸው 120 ቅዱሳን አንዱ፣ 3 ዓመት ከ3 ወር ከጌታችን እግር ቁጭ ብሎ የተማረ፣ በይሁዳ ፈንታ ከ12ቱ ሐዋርያት ይቆጠር ዘንድ መንፈስ ቅዱስ የመረጠው ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስ ነው።

እርሱም፦

◆ ሰው የሚበሉ አረማውያን ጋር ሄዶ ዓይኑን ያወለቁት፣ ሳር እየመገቡ ያቆዩት ነው፤

◆ እነዚህ አረማውያንን በጸሎቱ ልቦናቸውን መልሶ የዋህ፣ ቅን ያደረጋቸው የልጅነት ጥምቀትንም ያጠመቃቸው ነው።

◆ በሌላ ሀገረ ስብከቱ ለብዙ ቀናት በብረት አልጋ ላይ በእሳት ያቃጠሉት፣ ነገር ግን ምንም ጉዳት ያላገኘው ነው።

ይህ ቅዱስ አባታችን ለሐዋርያት የሚለየው ሌላው ነገር ደም ሳይፈሰው በመልካም እርጅና ማረፉ ነው።

~ መጋቢት 8 የዕረፍቱ በዓል ነው፨

አምላከ ቅዱስ ማትያስ ከበጎ ዕድል ላይ ይጻፈን፤ ሀገራችንን ከአረማዊ ሀሳቦች ፈጥኖ ያጽዳልን።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930
🍀🍀
ረድኤት በረከቱ ይደርብንና መጋቢት 8 ቀን በዓመታዊ የዕረፍት በዓሉ ታስቦ የሚውለው #ሐዋርያው_ቅዱስ_ማትያስ በሚነድ እሳት ውስጥ ተጥሎ ሣለ ያደረገው ታላቅ ተአምር ይህ ነው።

ማትያስ ወደ ደማስቆ ገብቶ ወንጌልን በመስበክ ብዙዎችን አሳመነ፡፡ ያላመኑ ክፉዎች የደማስቆ ሰዎችም ይህንን በተመለከቱ ጊዜ ..."ከ12ቱ መሰሪያን አንዱ ነው" ብለው ይዘው አሠቃዩት፡፡ አሥረው በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከሥሩ 6 ቀን ሙሉ እሳት አንድደው አቃጠሉት፡፡

ከ6 ቀንም በኋላ የሞተውን የተቃጠለ አካሉን ለመጣል ተመልሰው በመጡ ጊዜ በረድኤተ እግዚአብሔር እሳቱ ምንም ሳይነካው አገኙት፡፡ እንዲያውም ሰውነቱ እንደፀሐይ እያበራ አገኙት፡፡

በዚህም ገቢረ ተአምራት ብዙዎች በጌታችን አመኑ፡፡
ያላመኑ ክፉዎች አረማውያን ግን ዳግመኛ በብረት አልጋ ላይ አስተኝተው ከሥሩ 24 ቀን ሙሉ እሳት አንድደው አቃጠሉት፡፡

ጌታችንም በቸርነቱ ማትያስን ይጠብቀው ስለነበር ነበልባለ እሳቱ ሥጋውንም ሆነ ልብሱን የራሱንም ፀጉር ምንም አልነካውም ነበር፡፡ ያለምንም ጉዳት ፍጹም ጤነኛ ሆኖ ቢያገኙት እጅግ ተደንቀው ‹‹በማትያስ አምላክ እናምናለን›› ብለው በጌታችን የባሕርይ አምላክነት አምነዋል፡፡

ሐዋርያው ቅዱስ ማትያስም የጣዖታት ምኩራቦቻቸውን እንዲያፈራርሱና ጣዖታቱንም አፈራርሰው ወደ ባሕር እንዲጥሉ አዘዛቸው፡፡ እነርሱም እንዳዘዛቸው እንዲሁ አደረጉ፡፡ በምትካቸውም ቤተ ክርስቲያንን ሠራላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አስተምሮ በስመ ሥላሴ ካጠመቃቸው በኋላ አገልጋዮችን ሾመላቸው፡፡

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
❗️በአንድ ራስ ሁለት ምላስ ❗️

" ኢትዮጵያ ሀገር ሳይፈጠር የኖረች ናት ... ሰንደቅ ዓላዋን የመረጠላት እግዚአብሔር ነው ... ሰንደቅ ዓላማዋ ራሱ ይጠብቃታል ... " ያለ ምላስ መልሶ...

የሰንደቅ ዓላማዋን ቀለም ለመጥራት በመጸየፍ ዘቅዝቆ "ቀይ ቢጫ አረንጓዴ...*ርቅ " የሚል ምላስ... የ'አባት' ሊሆን ይችላል?

❗️.... የቅዱሳንን ስም እየጠራ "ቅዱሳን ይሄን ሰንደቅ በቤ/ክ አያውቁትም" ያለ ምላስ... ነገስ..

>> 14ቱን ቅዳሴያችንን የግብጽና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት አያውቁትምና እንተወው.. ይለን ይሆን?

>> ነገስ ታቦት "በኢትዮጵያ ብቻ የሚገኝ" ያለ ምላስ ሌላው ታቦት ስለማይጠቀም እናስወግደው ይለን ይሆን?

❗️የኢትዮጵያ ሰንደቅ የመጣው በፖለቲካዊ ድንበር ክለላ ከሌላ ሀገር ለመለየት ተብሎ ሳይሆን ከእግዚአብሔር በኖኅ በኩል እንደሆነ የተናገረ ምላስ ... አሁን እያሳሳቀ "ተሳዳቢ ..እና . ፖለቲከኛ..." መሆኑን እየተናገረ ይሆን?

ክርስቲያኖች፥ "ሊቅ ሊቅ" ማለቱ እና መባባሉ ይቆይና ባለቅኔው እንዳለው፦
በከንቱ ከምትጠፉ
"እየተማራችሁ" እለፉ!

🟩 አረንጓዴ
🟨 ቢጫ
🟥 ቀይ
#ፍረጅ !!
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
መጋቢት 10 | #_ቅዱስ_ዕፀ_መስቀል የተገለጠበት በዓል ነው፨

የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የከበረ ዕፀ መስቀል መገለጡና መገኘቱ ሁለት ጊዜ #_በመጋቢት_10 ሆኗል።

#_የመጀመሪያው
የጻድቁ ንጉሥ የቆስጠንጢኖስ እናት በሆነች በንግስት እሌኒ እጅ ነው። እርሷም ልጇ ክርስቲያን እንዲሆንላት ተስላ ነበርና ስእለቷ ቢደርስ ወደ ኢየሩሳሌም ሔደች።

በዚያም የመስቀሉን ታሪክ መርምራ አስቆፍራ አስወጣችው። ዕፀ መስቀሉን እና ቅንዋቱን (ሚስማሮቹን) ለልጇ ላከለት። በቦታውም ታላቅ ቤ/ክ አሳነፀችበት

#_ሁለተኛው
በሮሙ ንጉሥ በህርቃል ዘመን የሆነው ሲሆን የፋርስ የጦር መኰንን ተነጥሎ ወደ ኢየሩሳሌም ወደ ከበረ መስቀል ቤተ ክርስቲያንም ገባ።

መስቀሉም በላዩ በተተከለበት ግንድ ፊት ታላቅ ብርሀን ሲበራ አይቶ ሊያነሣው እጁን ዘረጋ። እሳትም ወጥታ እጁን አቃጠለችው። ሁለት ዲያቆናትንም ይዞ የከበረ መስቀልን ማርኮ ወደ አገሩ ተመለሰ።

ያ ዲያቆናቱና መስቀሉን የወሰደ መኰንን ከቦታዎች በቤቱ አንፃር ባለ በአንድ ቦታ ላይ ወስዷቸው ጥልቅ ጉድጓድ እንዲቆፍሩ አዝዞ በዚያ የከበረ መስቀልን አስቀበረ። እነዚያንም ዲያቆናት ገደላቸው።

ንጉሥ ህርቃልም ይህን በሰማ ጊዜ አዘነ። ከሠራዊቱም ጋር ዘመተ። መስቀሉን ግን ሊያገኝ ባልቻለ ጊዜ በምርኮ የመጣች አንዲት ብላቴና የተጣለበትን ነገረችው።

ቆፍረውም የከበረ ዕፀ መስቀልን አገኙት። ከአዘቅቱም አወጡት። ንጉሡና ሠራዊቱም ሰገዱለት።
ወደ ቁስጥንጥንያም ወሰደው።


#አቡነ_ተከስተ_ብርሃን ዘደብረ ድማኅ የዕረፍታቸው በዓል ነው፡፡

ደብረ ዲማን የመሠረቱ እና በጸበላቸው ልዩ ቃልኪዳን ያላቸው ናቸው። ወንጌልንም እየተዘዋወሩ የሰበኩ ናቸው።

በ1 ቀን 9999 ሰዎችን ሲያጠምቁ ቢመሽባቸው ብርሃን ከሰማይ ወርዶላቸዋል። በዚህም ተከስተ ብርሃን ተብለዋል
👆👆🏾👆🏽
የመስቀለ ኢየሱስ ቃልኪዳን በጥቂቱ
~ [ ድርሳነ መስቀል ]
       
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat
2024/09/27 17:17:03
Back to Top
HTML Embed Code: