Telegram Web Link
4_5874954449868297479.aac
4.4 MB
የእህታችን ወለተ ብርሃን እጹብ ድንቅ ምስክርነት  ፩
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ =አዲስ አበባ
23/6/2016

👉 ፡፡የሚያሳዝነውም ያፈረሱትን እንደ
እውነተኛ አገልጋዮች ቆጥሮ አብሮ መጥፋቱ ነው ፡፡ በደብዳቤያችን በሁሉም መልእክቶች ስለ ኢትዮጵያ ተዋህዶ ቤተ
ክርስቲያን ስለ ኢትዮጵያ ጉዳት በዝርዝር ገልፀናል ፡፡ ማንም አልሰማም ፡፡ አገልጋዮች የተባሉ ሁሉ እግዚአብሔርን
በተግባራቸው ክደውታል ፤ ንቀውታል ፤ አቃለውታል ፡፡ ፍፁም ደፍረውታል አስቀንተውታል ፡፡ ቁጣው እንዲነድ
አድርገዋል ፡፡

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አስር የተወሰደ
4_5874954449868297481.aac
5.9 MB
የእህታችን ወለተ ብርሃን እጹብ ድንቅ ምስክርነት ፪
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ =አዲስ አበባ
23/6/2016

👉 በአብነት 
ት/ቤቶች፤ ቁልፍ ቁልፍ ቦታ ላይ ሰላይ የሥርዓቱ አገልጋዮችን ሰግስጎአል። በስብከተ ወንጌሉ ከአናቱ እሰከ 
ሥሩ ድረስ ስውር መናፈቃንን አሰማርቷል። ተሐድሶ፣ ቅባት፣ የሆኑ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናት በሁሉም 
ስፍራ የበላይነቱን ይዘው በማጥፋት ላይ ይገኛሉ።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አምስት የተወሰደ
REC_0000018.wav
1.7 MB
እህታችን ወለተ ጻዲቅ
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ =ጅማ
23/6/2016
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
˙         ✥ ◦ ✥ ◦ ✥
‹‹#ክርስቶስን እክደዋለሁ!››
 
በእስክንድርያ አገር ስሙ ፈለስኪኖስ የሚባል አይሁዳዊ ባለጸጋ ሰው ነበር፡፡ እርሱም እንደ አባቶቹ የኦሪትን ሕግ ብቻ የሚጠብቅ ሰው ነው፡፡

እንዲሁም ድሀ የሆኑ ሁለት ክርስቲኖች ነበሩ፡፡በአንደኛው ላይ ሰይጣን የስድብ መንፈስ አሳድሮበት ጓደኛውን ‹‹ወንድሜ ሆይ ክርስቶስን ለምን እናመልከዋለን? እኛ ድኆች ነን፡፡ ይህ ክርስቶስን የማያመልክ አይሁዳዊ ፈለስኪኖስ ግን እጅግ ባለጸጋ ነው›› አለው፡፡

ጓደኛውም ‹‹ዕወቅ አስተውል፣ የዚህ ዓለም ገንዘብ ከእግዚአብሔር የሆነ አይደለም፤ ምንም አይጠቅምም። ጥቅም ቢኖረው ጣዖትን ለሚያመልኩ፣ ለአመነዝራዎች፣ ለነፍሰ ገዳዮችና ለአመፀኞች ሁሉ ባልሰጣቸውም ነበር፡፡ አስተውል ነቢያትም ሆኑ ሐዋርያት ድኆች ነበሩ። ነገር ግን ጌታችን ‹ወንድሞቼ› ይላቸው እንደነበር አስተውል…›› እያለ መከረው፡፡

ነገር ግን ጓደኛውን ሰይጣን አድሮበታልና ምክሩን ሊሰማው አልቻለም፡፡ ከዚህም በኋላ ይህ ክፉ ሰው ወደ ባለጸጋው አይሁዳዊ ወደ ፈለስኪኖስ ዘንድ ሄዶ ‹‹አንተን እንዳገለግል ተቀበለኝ›› አለው፡፡ ባለጸጋውም አይሁዳዊ ‹‹በሃይማኖቴ የማታምን አንተ ልታገለግለኝ አይገባህም›› አለው፡፡

ዳግመኛም ያ ጎስቋላ ‹‹ተቀበለኝ እንጂ ወደ ሃይማኖትህ እገባለሁ፣ ያዘዝከኝንም ሁሉ እፈጽማለሁ›› አለው፡፡ አይሁዳዊውም ‹‹ቆየኝ ከመምሀሬ ጋር ልማከር›› አለው፡፡

መምህሩም ‹‹ክርስቶስን የሚክድ ከሆነ ግረዘውና ተቀበለው›› አለው፡፡አይዳዊውም ተመልሶ መጥቶ መምህሩ እንደነገረው አድርጎ ተቀበለው፡፡ ከዚህም በኋላ ወደ ምኩራባቸው ወሰደው፡፡ የምኩራባቸውም አለቃ ‹‹ክርስቶስን
ክደህ አይሁዳዊ ትሆናለህን?›› አለው፡፡ እርሱም ‹‹አዎን እክደዋለሁ›› አለው፡፡

የምኩራባቸውም አለቃ መስቀል ሰርተው በላዩ የክርስቶስን ሥዕል እንዲያደርጉ፣ መጻጻንም የተመላች ሰፍነግ በዘንግ ላይ አሥረው ከጦር ጋር እንዲሰጡት አዘዘ፡፡ ከዚያም ‹‹ከተሰቀለው ሥዕል ላይ ምራቅህን ትፋ፣ መጻጻውንም ወደ አፉ አቅርብለት፣ ክርስቶስ ሆይ ወጋሁህ እያልክ በጦሩ ውጋው›› አሉት፡፡

እርሱም እንዳዘዙት አድርጎ ሥዕሉን በጦር ወጋው፡፡ ወዲያውም የዕውነት ሆኖ በተደጋጋሚ ውኃና ደም ከሥዕሉ ፈሰሰ፡፡ ለረጅም ጊዜም በምድር ላይ እየፈሰሰ ታየ፡፡ በዚያም ጊዜ ያ ከ'ሃ'ዲ ደርቆ እንደ ድንጋይ ሆነ፡፡ በአይሁድም ላይ ሁሉ ታላቅ ፍርሃት ወደቀባቸው፡፡

‹‹እውነትም የአብርሃም ፈጣሪ ስለእኛ ተሰቅሏል፤ እኛም ዓለምን ለማዳን የመጣ የሕያው የእግዚአብሔር ልጅ እርሱ እንደሆነ አመንበት›› እያሉ ጮኹ፡፡

ከዚህም በኋለ አለቃቸው ከዚያ ከደሙ ወስዶ የአንዱን ዐይነ ሥውር ዐይኖቹን አስነካው፡፡ ወዲያውም ዐይነ ሥውሩ ማየት ቻለና ሁሉም አመኑ፡፡ ወደ ሊቀ ጳጳሳት አቡነ ቴዎፍሎስ ሄደው የሆነውን ሁሉ ነገሩት፡፡

አቡነ ቴዎፍሎስም ከካህናቱ ሁሉ ጋር ወደ አይሁድ ምኩራብ ሄዶ ውኃና ደም ከእርሱ ሲፈስ መስቀሉን አገኘው፡፡ከደሙም ወስዶ የራሱንና በዚያ ያሉትንም ሁሉ ግንባራቸውን በመቀባት በረከትን ተቀበሉ፡፡ መስቀሉንም በክብር ወስደው በቤተ ክርስያን ውስጥ አስቀመጡት፡፡ ደሙ የፈሰሰበትንም ምድር አፈሩን አስጠርጎ ለበረከትና ለሕሙማን ፈውስ ሊሆን በሸክላ ዕቃ ውስጥ አኖረው፡፡

ከዚህም በኋላ አይዳዊው ፈለስኪኖስ ከነቤተሰቡ አቡነ ቴዎፍሎስን ተከተለው፡፡ ከአይሁድም ብዙዎቹ የቀደሙ አባቶቻቸው በሰቀሉት የክብር ባለቤት በሆነ በመድኃኔዓለም ክርስቶስ አመኑ፡፡ አቡነ ቴዎፍሎስም በስመ ሥላሴ አጥምቆ ሥጋ ወደሙን አቀበላቸው፡፡ እነርሱም ጌታችንን እያመሰገኑና ክብሩን እየመሰከሩ ኖሩ፡፡

ቸሩ አምላካችን መድኀኔ ዓለም ክርስቶስ በእስክንድርያ አገር ድንቅ ይኽን ድንቅ ተአምር በማድረግ አይሁዶችን በተአምራቱ በስሙ አሳምኖ በአባ ቴዎፍሎስ እጅ እንዲጠመቁ ያደረገው ነሐሴ 14 ቀን ነው። ቸሩ መድኀኔ ዓለም ለኹላችንን ምሕረቱን ይላክልን።

               ✥ ◦ ✥ ◦ ✥
የዲያብሎሳዊያን 👿 ጉባኤ...

ከ81ዱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ መጽሐፍ ቅዱስ ውጭ የሆነ ሌላ መጽሐፍ ቅዱስ የሚባል ተረት ተረት የለም!!
ይሄንን መረጃ ከማህበራዊ ሚድያ ልናጋራ የቻልንበት ዋናው ምክንያት "ሲኖዶስ" የምትሉትን የተወገዙ "ጳጳሳት" ስብስብ ማን እየመራው እንደሆነና አሰላለፉን ላልተረዳችሁ ዘገምተኛ ወገኖች ትረዱ ዘንድ ነው።

#ማስታወሻ
👇👇👇
"እንግዲህ ወገኖቼ! ዛሬ ቤተክርስቲያን ስንት ሲኖዶስ እንዳላት የምታውቁት አለ ወይ!? ላታውቁ ትችላላችሁ! ሲኖዶስ በእግዚአብሔር አይን፡ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በትክክለኞች ወገኖች ሲፈተሽ ሁለት(2) ነው።

#አንደኛው - ሁላችንም የምናውቀው፤ መግለጫም የሚሰጠው፤ ያለምንም ሃፍረት ከክፉው መንግሥት ጋር አብሮ የሚሰራው ለፖለቲካው ስርዓት ተገዢ ትውልድን ለመፍጠር የሚደክመው፤ ሃብቱ፡ ንብረቱ፡ ክብሩ እንዳይነካበት የሚደክመው ሲሆን፥

#ሁለተኛው - ደግሞ በጨለማው ወይም ደግሞ የጨለማው፤ የማይታየው ሲኖዶስ ይባላል። ይህ ደግሞ ሙሉ በሙሉ የፖለቲካው ሃይል ሲሆን በዘበኝነት፡ በጸሃፊነት፡ በአስተዳደር፡ በመምሪያ በመመሳሰሉ በቤተክርስቲያን የተቀጠሩ ያሉበት ሲሆን ስራው የዋናውን ሲኖዶስ ውሳኔ እሱ እንደሚፈልገው እንዲሆን የሚያደርግ ነው። ቀን ሲኖዶሱ ሲወስን ካልጣመው ከፖለቲካው በተለየ ከሰሜነኞቹ ሲታዘዝ በማታ በየጳጳሳቱ ቤት እየዞረ ውሳኔውን እንዲቀይሩ የሚያደርግና የሚያስፈርም ሃይል ነው፥ በወያኔዎቹ የተመለመለ  ሃይል ማለት ነው።  እምቢ ቢሉ በእጁ የእነሱን ጉድ የያዘ የወንጀል ሰነድ ስላለ የግድ ይታዘዙታል ማለት ነው።

እንግዲህ ወገኖቼ! “አውቆ የተኛን ቢቀሰቅሱት አይሰማም!” እንዲባል  ስለ ሲኖዶስም ስለ ቤተክህነትም አሰራር የማታውቁ ይመስል ስለ እነርሱ የምትጠይቁ እኛን አትጠይቁን፥ ከእነርሱ ጋር አይደላችሁም እንዴ!? በዚያው ቀጥሉ! ይታደጓችሁ።......"

ከመግለጫ 3 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የተወሰደ!
ሚያዝያ 11/2012ዓ.ም ዕለተ ትንሣኤ በድምፅ የተላለፈ
ከኢትዮጵያ 3 ክልሎች በአንድ ጊዜ መብራት መቋረጥ ወዴት የሚያመራ ይመስላችኋል ???

#ዝግጅት የመዘጋጀት ጥቅምና ጉዳቱ እጅግ በቅርቡ ሊለይ ይመስላል !!...
#ቸር ያሰማን !

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
📗📙📕 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ፥ የኢትዮጵያንና የተዋሕዶን ትንሣኤ እንመሰክራለን !

👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾👇🏾
🟩
www.tg-me.com/AlphaOmega930 (👨‍👧‍👦ግሩፕ)
🟨
www.tg-me.com/christian930 (👩‍👧‍👦ቻናል)
🟥
www.tg-me.com/Ewnet1Nat (🗣ንጽጽር)
🟢
www.tg-me.com/ethioBirhan (በልዩ ልዩ ቋንቋዎች)
🟡
www.tg-me.com/Amharic_messages (🔑በአማርኛ ብቻ)
🔴
www.tg-me.com/EthioLightContents (🗞ማውጫ)
💚
www.tg-me.com/aleqayalew (አለቃ አያሌው ታምሩ)
💛
https://www.facebook.com/joseph.ethiopia1 (📲በፌስቡክ)
❤️
https://youtube.com/channel/UCfoPIJgkHyihgUwMhvOzWXw (📡በዩቱብ)

💡 እነዚህን አማራጮች ማግኘት ያልቻላችሁ ወገኖቼ በማስፈንጠሪያቸው (Link) በመቀላቀል (Join) በማድረግ አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ ድኅረ ገጽን መከታተል፤ ከልዑል እግዚአብሔር በቀጥታ ለመላው የአዳም ዘር የሚተላለፉ የቅዱሳን አባቶችን መልዕክታት ማግኘትና የዓለምን መጻኢ እጣፈንታና የፍርድ አፈጻጸም ሒደት መከታተል ትችላላችሁ ።

🔐 ድኅረ ገጾችን በመከታተል፦
#Like #Share #Add_Member #Subscribe #Comment ማድረግ ይቻላል ።
🟢 🟡 🔴
የካቲት 28 | #አቡነ_እጨጌ_ዮሐንስ ዘጠገሮ የጽንሰታቸው በዓል ነው።

ጻድቁ አባታችን የተወለዱት በኢየሩሳሌም አውራጃ ልዩ ስሙ ሳሬራ በሚባል ቦታ ነው፡፡ የካቲት 28 ቀን ተፀንሰው ኅዳር 29 ተወለዱ፡፡

አባታቸው ድላሶር እናታቸው እምነ ጽዮን ይባላሉ፡፡ ሲወለዱ በወላጆቻቸው ቤት ውስጥ ብርሃን ወርዷል፡፡ ወላጆቻቸውም እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ክርስቲያኖች ናቸው፡፡

አባታችን ገና በተወለዱ በ5 ዓመታቸው ወላጆቻቸው ወደ እግዚአብሔር ቤት ይዘዋቸው የእመቤታችንን ሥዕል ተመልክተው በደስታ ተመልተው ሳቁ፡፡

አምላክን የወለደች የብርሃን እናቱ እመቤታችንም ከምሥሉ ወጥታ ‹‹በምን አውቀኸኝ ነው?›› ብላ አቅፋ ሳመችውና ‹‹ከእንግዲ ወዲህ የልጄ አገልጋይ ትሆናለህ ኑሮህም እንደ መላእክት ይሆናል በአንተ ምክንያት ብዙ ሰዎች ይድናሉ በምድር ላይም 500 ዓመት ትኖራለህ" ብላ ባርካው ተሰወረች፡፡

ከዚያችም ቀን ጀምሮ አባ ዮሐንስ ለክርስቶስ ተላልፎ ተሰጠ፡፡ 50 ዓመትም በበረሃ ሲጋደል ኖሮ ከ50 ዓመት በኃላ በደመና ተጭኖ በመልአኩ በቅዱስ ገብርኤል መሪነት ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ መጡ፡፡

ጻድቁ አባታችን በአቡነ ተክለሃይማኖት ዘመን መጨረሻ የመጡ ሲሆን ምንኩስና ከደብረ ሊባኖስ ገዳም ከአቡነ ተክለ ሃይማኖት ተቀብለው በዚያው በደብረ ሊባኖስ ገዳም ለ50 ዓመት በጾምና በጸሎት በተጋድሎ ኖረዋል፡፡

ከዚኽም በኋላ አባ ዮሐንስ ወደ ተዘጋጀላቸው ምድር በቅዱስ ገብርኤል አሳሳቢነት ወደ ጠገሮ መጡ፡፡

(ቃልኪዳናቸው በጥቂቱ 👇)
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/10587
🍀🍀🍀
🟢 🟡 🔴
የካቲት 29 | #ቅድስት_ፍቅርተ_ክርስቶስ (እም ምዑዝ) ዐረፈች።

ይህችም ጻድቅ ወሰማዕት እናታችን፦

๏ በ80 ቀኗ ተጠምቃ ስትቆርብ አምላክን አመስግናለች፤

๏ በትዳር ውስጥ ከቅዱስ ዘርዓ ክርስቶስ ጋር ለ40 ዓመት በድንግልና እና በንጽሕና ተወስና ኖራ በኋላ ወልዳለች፤

๏ የካቲት 15 ከባሏ ጋር ተሰይፋ እሷ ዳግም ከገነት ተመልሳለች፣

๏ በአንዲት ቀን ዘርታ፣ አብቅላ፣ አሳጭዳ ሰውን ለሚመገቡ ሕዝቦች ምግብን አሳይታለች፤

๏ በአንዲት ቀን (አርብ ታኅሣሥ 14) ቤተ ክርስቲያን ማነጽ ጀምራ ጨርሳለች፤ ይህም ቤተ ክርስቲያን ራሱ ለጌታችን ልክ እንደ ሰው ሰግዷል።

๏ እስከ ናግራን (የመን) ድረስ በመሄድ አስተምራለች፤

๏ በዓፄ ሱስንዮስ ጊዜ ሰማዕትነት ተቀብላ ደግማ ተነሥታለች።

            ◦◦ | ቃል ኪዳን | ◦◦

ጌታችንም ‹‹ሁሉም እንደ ቃልሽ ይሁንልሽ። በስምሽ ስሜ ተጨምሯልና ለቤተ ክርስቲያንሽ መባ የሰጠ፣ የተላከ፣ የተቀበረ፣ ቤተ መቅደስሽ መጥቶ የተሳለመ፣ እስከ 12 ትውልድ የምሕረት ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ። በረከቴም በቤቱና በልጆቹ በገንዘቡም ላይ ይደር።

๏ የገድልሽ መጽሐፍ ባለበት አጋንንት (ሰይጣናት) አይቀርቡም። በአዝመራ ስምሽን በጠሩት ጊዜ የለመለመ ይሁን። በጸሎትሽ የተማጸነ ሁሉ ባለጤና ይሁን።

๏ ስምሽን በእውነት የሚጠራ የከበረ ነው፡፡ ያለመጠራጠር በቀናች ሃይማኖት የገድልሽን መጽሐፍ የጻፈ፣ ያጻፈ፣ ያነበበ፣ የተረጎመ በሃይማኖት የሰማ፣ እስከ ቀዝቃዛ ውሃ ድረስ የሰጠ ኃጢአቱ ይሠረይለታል።

๏ ስለ ድካምሽ ስለ ትሩፋትሽ 7 አክሊሎችን እና ይህን ሁሉ ቃል ኪዳን ሰጠሁሽ፡፡ ላልምረው ቦታሽን አላስረግጠውም›› ብሏት ወደ ሰማይ አረገ፡፡
✧◦✧◦✧

www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
''ንስሐ ገብተን ወደ እግዚአብሔር መመለስ አለመቻላችን ፈተናችንን ከቀን ወደቀን እያባሰው ይገኛል::

ቀን አልፎ ቀን ሲተካ ደግሞ ዛሬ ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ? ብለው የሚጠይቁ ሰዎች እየበዙ ይገኛሉ:: የእኛም ጆሮዎች መልካም ያልሆኑ ነገሮችን መስማትን ተለማምደዋል::''

ታላቁ ሊቅ አለቃ አያሌው ታምሩ
ከ 22 ዓመት በፊት የተናገሩት::

#አለቃ_አያሌው_ታምሩ ‼️
#ያልተፈታው_ውግዘት ‼️
www.tg-me.com/aleqayalew
2024/09/27 21:25:55
Back to Top
HTML Embed Code: