Telegram Web Link
⚜️የምኒልክ ተስፋው እግዚአብሔር ነው⚜️

የምኒልክ ተስፋው፥ የካቲት 22 ሌሊት በስግደትና በምህላ ሲማፀነው የሰማው #እግዚአብሔር ነው።

የምኒልክ ተስፋው፥ እቴጌ ጣይቱ በሥዕሏ ፊት ስትሰግድ ያደረችላት የእመቤታችን አምላክ፣ የአርበኞችን ጾምና የሀገር ቅንዓት የተመለከተላቸው #እግዚአብሔር ነው።

የኢትዮጵያን ሃይማኖት ያስጠበቀው፣ ሕዝብ ከባርነት ያተረፈው፣ የሕዝቡን ነጻነትና ሉዓላዊነት ያስጠበቀው የምኒልክ ሰይፍ ይህ ነው።

#ቅዱስ_ጊዮርጊስ
#ምኒልክ
#ዓድዋ

T.me/Ewnet1Nat
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
#የካቲት_23
🟢 🟡 🔴
የካቲት 23 | በዚህች ቀን #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት አባቶቻችንን አድዋ ላይ የረዳበት ነው።

በ1854 ዓ.ም ጀግናው ገበየሁ ጣልያንን ካሸነፉ በኋላ እንደገና ቅኝ ለመግዛት፣ ሃይማኖት ለማጥፋት የጣልያን ሰዎች መጡ።

በ1888 ዓ.ም መስከረም 7 ቀን፥ ሣህለ ማርያም (አጤ ምኒልክ) አዋጅ አስነገሩ። በኋላም ወደ አድዋ ተጓዙ።

በዚያም የሣህለ ማርያም ሚስት ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱ) በንጉሥ ትእዛዝ ታቦተ #ቅዱስ_ጊዮርጊስን አስይዘው ከካህናቱ ጋር ሔዱ።

በዚያም ጊዜ የአክሱም ጽዮን መነኰሳትና ካህናት የእመቤታችንን ሥዕል ይዘው ወደ ንጉሡ ወደ ምኒልክ መጥተው ከሊቀ ጳጳሱ ከነአቡነ ማቴዎስ ጋር ተቀላቀሉ ከዚያም ሌሊቱን ሙሉ ጸሎት ምሕላ ሲያደርሱ አደሩ።

ቅዳሜ ማታ ለእሑድ አጥቢያ የካቲት 22 ቀን፥ ንጉሡ ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) የጦር ልብሱን ለብሰው ከሠራዊቱ ጋር ወደ ጦር ግንባር ሄዱ። ከዚያም ከሮማውያን የጠላት ጦር ጋር ተገናኝቶ ከሌሊቱ ዐሥራ አንድ ሰዓት ጦርነቱን ጀመረ።

በዚያም ጊዜ ንጉሡ ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) በጦርነቱ መካከል ሳለ ሊቀ ጳጳሱ አባ ማቴዎስ እንዲሁም የአክሱም መነኰሳትና ሌሎቹ ካህናት በሙሉ ታቦተ ጊዮርጊስንና ሥዕለ ማርያምን ይዘው ከንጉሡ በስተኋላ በደጀንነት ቆመው ጸሎተ ምህላ ያደርሱ ነበር።

ንግሥቲቱ ወለተ ሚካኤል (እቴጌ ጣይቱም) በጸሎት ጊዜ በመዓልትም በሌሊትም ከእነርሱ አትለይም ነበር። የጽዮን አገልጋዮችም በእግዚአብሔር የሕጉ ታቦት ፊት መለከት ይነፉ ነበር።

በየካቲት 23 ቀን በሮማውያንና በኢትዮጵያውያን መካከል ከፍተኛ ጦርነት ሆነ። በዚህም ጊዜ በሰማይ ታላቅ ተአምር ተደረገ። የቀስተ ደመና ምልክት ታየ። ከዚያም ከቀስተ ደመናው ውስጥ መልኩ አረንጓዴ የመሰለ ጢስ ይወጣ ነበር። ከዚህም ጢስ ውስጥ እንደ ክረምት ነጎድጓድ ያለ ድምጽ ተሰማ።

ከዚህም የነጎድጓድ ድምጽ የተነሣ በሮማውያን ወታደሮች ዘንድ ከፍተኛ ድንጋጤና ሽብር ሆነ ለመዋጋት አልቻሉም። ይልቁኑ ኃያሉ ገባሬ ተአምር ማር ቅዱስ ጊዮርጊስ በአምባ ላይ ፈረሱ ተቀምጦ ከነፋስ ሩጫ ይልቅ እየተፋጠነ በአየር ላይ በተገለጸ ጊዜ በግንባራቸው ፍግም እያሉ ወደቁ።

"የኢትዮጵያ ሕዝብ አምላካቸው ሊረዳቸው መጣ እንግዲህ ማን ያድኅነናል" አሉ፤ ምድርም ጠበበቻቸው።

በዚህን ጊዜ የኢትዮጵያ ሠራዊት የሮምን የጦር ሠራዊት ፈጁዋቸው የተረፉትንም ማረኳቸው ፈጽመውም እስኪያጠፏቸው ድረስ በሮማውያን ላይ በእግዚአብሔር ሥልጣን የኢትዮጵያውያን እጅ እየበረታ ሄደ።

ከዚህም በኋላ የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት ሣህለ ማርያም (ምኒልክ) በእግዚአብሔር ኃይልና በተአምራት አድራጊው በቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳኢነት የሮማውያንን የጦር ሠራዊት ድል አድርገው የድል አክሊል ተቀዳጅተው ተመለሱ።

ምንጭ፦ ተአምረ ቅዱስ ጊዮርጊስ
T.me/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
⚜️
ኃይል የእግዚአብሔር ነው፤ መዘጋጀት ግን የሰው ድርሻ ነው።
⚜️
የንግሥት ጣይቱ ብጡል ጀግነት


በዐድዋ ዘመቻ ወቅት የእቴጌ ጣይቱ ዋና የሥራ ድርሻ የሠራዊቱን ስንቅ ማሰናዳት ነበር።

ወቅቱ በአብዛኛው የሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ርሃብና ድርቅ የነበረበት በመሆኑ እንዲሁም የአባ ደስታ በሽታ የቀንድ ከብቱን ስለፈጀው ለሚዘምተው ሠራዊት ስንቅ ማደራጀት ከባድ ነበር።

እቴጌ ጣይቱ በየአካባቢው ያሉ የሥጋ ዘመዶቻቸውን በመጠቀም ለሠራዊቱ ስንቅ የሚሆን እህል መጀመሪያ ወረኢሉ እንዲከማች አደረጉ። ቀጥሎም ይህ ስንቅ የሚጓጓዝበትን መንገድ አመቻችተው እስከ አድዋ ድረስ በልክና በሚበቃ መልኩ ለሠራዊቱ እንዲዳረስ ያደርጉ ነበር።


የመቀሌው ከበባ በድል እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉትም እቴጌ ጣይቱ ናቸው፡፡ የጣሊያን ወታደሮች አሁን መቀሌ እንዳየሱስ ላይ ፎርቶ ዲ. ጋሊያኖ የሚባለው ቦታ መሽገው ለሁለት ሳምንት የኢትዮጵያን ጦር አላስጠጉም ነበር፡፡ እቴጌ ጣይቱ ባመጡት ብልሐትና በራሳቸው ከሚመራው እና ከሚታዘዘው ጦር ምርጥ ተዋጊዎችን በሌሊት ልከው ጣሊያኖች የሚጠቀሙበትን ከምሽጋቸው በስተ ደቡብ ያለውን ማይንሽቲ የተባለውን ምንጭ በኢትዮጵያውያን እጅ እንዲገባ አድርገዋል።

ይህ ወታደራዊ እርምጃ በጣሊያኖች ዘንድ ከፍተኛ የውኃ ችግር በመፍጠሩ ጣሊያኖች ምሽጋቸውን ለቅቀው እንዲሄዱ አስገድዷቸዋል።

በዋናው የዐድዋ ጦርነት ቀን እቴጌ ጣይቱ የሚመሩት ጦር በውጊያ ከመሳተፉ ባሻገር የሚቆጣጠሯቸው የሥራ ቤት ሴቶች ውኃ በማቅረብ ቁስለኛ በማንሣትና በማከም ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገዋል። ጦርነቱ በብዙ ቦታዎች በመደረጉ አንዱን ክፍል የጣሊያን ጦር አሸንፎ የሚመጣውን ጦር እንዲሁም የደከመውን “አይዞህ በርታ ውጊያው አላለቀም ንጉሡም አልተመለሱም” እያሉ ሲያበረታቱ ውለዋል።
🇨🇬 👑 🇨🇬
T.me/Ewnet1Nat
በባህርዳር ከተማ አገልጋይ ካህን በአደባባይ በግፍ ተረሸኑ።
***********
በባህርዳር ከተማ በተለምዶ ዲያስፖራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የምትገኘው የቅድስት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክስርቲያን አገልጋይና የደብሩ ፀሐፊ የነበሩትን ቀሲስ ያሬድ የተባሉ አባትን የመከላከያ ሰራዊት ዛሬ የካቲት 22 ቀን ከመኖሪያ ቤታቸው በማውጣት በግፍ ረሽነዋቸዋል። በመላው ሃገሪቱ የኦርቶዶክሳውያን አገልጋዮች ግድያ በአደባባይና በጠራራ ፀሃይ እየተፈጸመ ባለበት ሁኔታ ስላገልጋዮቹ ከማንኛውም አካል በፊት ቀድሞ የሚመለከታቸው የቤተ ክህነቱ ባለስልጣናት ለጉዳዩ ምንም አይነት ትኩረት ሲሰጡት አይታይም። በትናንትናው እለትም በሜጫ ወረዳ የጋሲት ገብርኤል ጉባኤ ቤት 11 የቅኔ ተማሪዎች በመከላከያው መረሸናቸው መዘገባችን ይታወቃል።

ስምዓ ተዋሕዶ
የጋሲት ገብርኤል ጉባኤ ቤት 11 የቅኔ ተማሪዎች በመከላከያ በግፍ ተረሸኑ
***

በም
እራብ ጎጃም ዞን ሜጫ ወረዳ ብራቃት ቀበሌ ላይ ከሚገኘው የጋሲት ገብርኤል ጉባኤ ቤት 11 የቅኔ ተማሪዎች ዛሬ የካቲት 21 ሌሊቱን በመከላከያ ሰራዊት ተወስደው በግፍ ተረሽነዎል።
በአማራ ክልል እየተካሔደ ባለው ጦርነት በተለያዮ አካባቢዎች ንጹሃን ነዋሪዎች በግፍ እየተገደሉ ሲሆን በተለየ መልኩ አገልጋይ ካህናትን እና የአብነት ተማሪዎችን ማእከል አድርጎ ግድያ እንደሚፈጸም መዘገባችን ይታወሳል።

ስምዓ ተዋሕዶ
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

በ 23/6/2016 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት ይለቀቃል 👇👇👇
Audio
የእህታችን እፁብ የልዑል እግዚአብሔር ተዐምር
የተገለፀበት አፅናኝ አስተማሪ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ
21/6/2016

👉 ስለዚህ መርከብህ ማለት የተዋሕዶ እምነትህ ናት። ቤትህና ቤተሰብህ 
በዚችው እንቁ እምነትህ በእሳት ስለታጠረች፤ በእምነትህ ፀንተህ ቁም። የቁጣው እሳት እስከሚያልፍ በቤትህ 
ተወሰን። ለተገባቸው ነጩን ለለበሱት በተዋሕዶ እምነታቸው ለፀኑት ምልክቱንም ለጨበጡት ባሉበት ስፍራ 
በመርከቢቱ ተሳፍረዋል። አንዳችም ይነካቸው ዘንድ ፍጹም አይቻልም።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አምስት የተወሰደ
የእህታችን ወለተ ሥላሴ እፁብ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ =ባህርዳር
21/6/2016

👉 ዓመፃንና ግፍን በማድረግ ምድሪቱን ያከረፉ የሀገራችንም ሆነ የመላው ዓለም ሕዝብ ዛሬ በመጨረሻው 
ልትደመደሙ ሆነ። ምልክት ማግኘት የቻሉ ጎበዞች በእንባና በለቅሶ ዘሩ ዛሬ በደስታ ያጭዳሉ። ቅን የልዑል 
ፍርድ ምንግዜም አይዛነፍም። ዳኝነቱም ፍጹም ነው። ማንም በመሸምገል ወይም ሕፃን በመሆን ከፍርድ 
ማምለጥ አይቻልም ከቤቱም እንደሚጀምር በቃሉ አረጋግጧል።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ስድስት የተወሰደ
የወንድማችን ገብረመድህን እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = ም/ጉጂ
23/6/2016

👉 ከላይ የተጠቀሱትን የፈጣሪ አምላካችንን ትእዛዝ፣ ናቃችሁ፣ ምንዝርናን እንደ ትክክል ሥራ አጸናችሁ
ፈቀዳችሁ፣ ተገበራችሁ፡ አልፋችሁ ተርፋችሁ ግብረ ሶዶምነትን አጸናችሁ። በቤተ ክርስቲያን ውስጥ
አጋባችሁ፣ ተገበራችሁ

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አንድ የተወሰደ
28. Jan., 12.47​.m4a
10.6 MB
የእህታችን ስርጉተ ገብርኤል እጹብ ድንቅ ምስክርነት
ሲዊዘርላንድ
23/6/2016

👉 ይህ እውን እስከሚሆን የእሳት ጠረጋው እጅግ ከብዶ ይቀጥላል ፡፡ የሰው ትእቢት መፍጨርጨር በቀጠለ
መጠን እርምጃው እጅግ የከፋ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ ያልተሰማ ያልታየ ሆኖ ይቀጥላል ፡፡ ለኢትዮጵያ የአለም ብርሃናዊ
መንግሥት እንቅፋት የሚሆን የማይገዛ የማይታዘዝ ሁሉ አለምንም ርህራሄ ከምድረ ገፅ ይወገዳል ፡፡ ጠማማ ወልጋዳ
ዲያብሎስ በጥመት በክፉነት የቀረፀው ትውልድ ሁሉ የትም ይሁን የት ይወገዳል ፡፡ ምድር ብርሃንን ሰላምን በረከትን ሁሉ
የምታየው ሙሉ በሙሉ የኢትዮጵያ የአለም ብርሃናዊ መንግሥት አገዛዝ በምድሪቱ ሁሉ ላይ ተፈፃሚ ሲሆን ብቻ ነው ፡፡

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አስር የተወሰደ
Voice 006.amr
376.2 KB
የወንድማችን ገብረመድህን እጅግ አሳዛኝ ምስክርነት ፩
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ =ባህርዳር
21/6/2016

👉 በየትኛውም የዓለም አገሮች ባለ የሰው ዘር በሙሉ በሁሉም ቤት ሞት ይነግሣል ይቆርጣል ይፈልጣል 
ማንም ከልካይ የለውም።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ዘጠኝ የተወሰደ


ተጻፈ ታህሳስ 21 ቀን 2013 ዓ.ም
Audio
የወንድማችን ገብረመድህን እጅግ ድንቅ ምስክርነት  ፪
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ =ባህርዳር
21/6/2016

👉 ቤተክርስቲያን የንግድ ማዕከል፤ ፎቅ ሰሪ አከራይ ነጋዴ ሆናለች። አገልጋዮቿ በአብዛኛው እንደ አፍኒንና 
ፊንሀስ ያሉ በመሆናቸው እርኩሰትን አንግሰዋል። የወፈረውን በግ አርደው በሊታ ሆነዋል የከሳውን ደግሞ 
የሚወረውሩም ናቸው። ወገኖቼ በተጉ አባቶች ሰማዕትነት ተጋድሎ የጸናችው ቤተ ክርስቲያናችን የፖለቲካ 
ሹመኛ መጫወቻ ሆናለች።

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ስምንት የተወሰደ

ተጻፈ ታህሳስ 21 2011
2024/09/27 23:23:16
Back to Top
HTML Embed Code: