Telegram Web Link
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 19 | በዚህች ቀን፦

#ቅዱስ_ገብርኤል_ሊቀ_መላእክት ሠለስቱ ደቂቅን ያዳነበት በዓል ነው።

በቤተ ክርስቲያን ክቡር ከሆኑ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ብዙ የክብር ስሞች አሉት። በተለይ ግን፦
🍀 ሊቀ አርባብ፣
🍀 መጋቤ ሐዲስ፣
🍀 መልአከ ሰላም፣
🍀 ብሥራታዊ፣
🍀 ዖፍ አርያማዊ (የአርያም ወፍ)፣
🍀 ፍሡሐ ገጽ (ደስተኛ ፊት ያለው)፣
🍀 ቤዛዊ መልአክ (አዳኝ መልአክ)፣
🍀 ዘአልቦ ሙስና... እየተባለ ይጠራል።



#_ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘቡርልስ ዕረፍቱ ነው።
በሚቀድስበት ጊዜ ፊቱ እሳት ሆኖ ይታይ የነበረውና በጸሎቱ እሳት ከሰማይ አውርዶ መና- ፍቃንን ያቃጥል የነበረ አባት ነው።


መጽሐፈ ስንክሳርን፣ ግጻዌን እና ሃይማኖተ አበውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀ፣ ቀድሶ ቅዱስ ቍርባን ሲያቀብል ፊቱ የሚያበራ ቅዱስ አባት ነው።
🍀

#ቅዱስ_አባ_አካለ_ክርስቶስ
እንደ ፋኑኤል መልአክና እንደ አምላኩ መድኀኔዓለም ክርስቶስ የሕሙማን መድኀኒት ይሆናል›› የተባለላቸው ጻድቅ ናቸው።


አባታቸው ቅዱስ አቃርዮስ እናታቸው ቅድስት ታውክልያ የተባሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ የካቲት 19ም ተወለዱ።

ሲወለዱ ብፁዕ አባታችን አባለ ክርስቶስ ከሰውነታቸው ኅቡዕ የሆኑ የእግዚአብሔር የምሥጢር ስሞች በእብራይስጥ ቋንቋ ‹‹ዲካባ፣ ማርትያስ፣ ክስብኤል›› የተባሉ ኅቡዓን የምሥጢር ስሞችን በሰውነታቸው ላይ ይዘው (ተጽፎውባቸው) ነበር።

በ322 ዓመታቸው በፈለፈሉት ዋሻ ዐርፈዋል።
🍀

#አቡነ_ዳንኤል_ዘተንቤን ዕረፍታቸው ነው፡፡

በሌላኛው ስማቸው ዳንኤል ሐዲስ በሚል ስያሜም ይታወቃሉ፡፡ ቆላ ተንቤን የሚገኘውን አስደናቂውን ውቅየን ገብርኤል ፍልፍል ዋሻ ገዳምን በ1435 ዓ.ም ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጋር ሆነው የገደሙ ናቸው፡፡

በ14ኛ መ/ክ/ዘ የነበሩ ታላቅ ጻድቅ ሲሆኑ ትውልዳቸው ሸዋ ነው፡፡

ጻድቁ እህል ሳይበሉ ውኃም ሳይጠጡ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ይጾሙ የነበሩ መናኝ ባሕታዊ ናቸው፡፡ እንደ ነቢዩ ኤልያስም ኹለት ሙት አስነሥተዋል፡፡

አቡነ ዳንኤል ፍትሕ እንዳይጓደል ድኃ እንዳይበደል ይከራከሩ ይመክሩ የሚበድሉትንም ይገስጹ ስለነበር ‹‹የድኃ ዕንባ ጠባቂ›› የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

🍀

#አቡነ_ስነ_ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው።

መልአከ ሞት መስከረም 19 ቀን መጥቶ "ጊዜ ዕረፍትህ ደርሷል" ቢላቸው "የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብር አይሆንም" ብለው መልአከ ሞትን ለ3 ወራት ገዝተው አቁመውታል።

ታኅሣሥ 19 የቅዱስ ገብርኤልን ዝክር ዘክረው እንደፈጸሙ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ከድንግል እናቱ፣ እልፍ አእላፍ መላእክትን፣ ሐዋርያትን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ የከበሩ መነኮሳትን አስከትሎ እንዲህ የሚል ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል

ቦታህን ሊሳለም የመጣውን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሄደ እቆጥርለታለሁ፤

▸ በቦታህ ከወደቀው ፍርፋሪ እንኳን በስምህ ቢመገብ አማናዊውን ሥጋዬን ደሜን እንዲቀበል አደርገዋለሁ፤

▸ ኃጢአቱን ለካህን ለመናገር አሳፍሮት 3 ጊዜ "አባታችን አቡነ ስነ ኢየሱስ ይቅር በለኝ" ቢል የበዛ ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ።

🍀

#_እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
Audio
ድርሳነ ቅዱስ ገብርኤል የታህሳስ ወር.mp3
ሹመት‼️

የኦነግ ሸኔ ሰራዊት ምክትል አዛዥ የነበሩት እና በቅርቡ ከክልሉ መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት የፈፀሙት አቶ ጃል ሰኚ ነጋሳ የኦሮሚያ ክልል ሚሊሻ ቢሮ ሐላፊ በመሆን በዛሬው መሾሙ ተዘግቧል።
ያዝ እንግዲህ!!
በዛሬዉ ዕለት በአፋር ገቢ ረሱ ዞን አዋሽ ፈንቲዐሌ ወረዳ ጉርሙዳሌ ጤና መዐከል ላይ የመሬት መንቀጥቀጥ ያስከተለዉ አደጋ ነዉ።
📌ኦነግ ከአዲስ አበባ #በ60 ኪ.ሜ ርቀት በምትገኘው #በርጋ በምትባል የኦሮሚያ ከተማ አካባቢ ከ250 በላይ መከላከያ ደመስሻለሁ ብሏል።
የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የገባ ታጣቂ ቡድን  ከ83  በላይ ሰዎችን ገደለ!

ሪፖርተር እንግሊዘኛው በዛሬው እትሙ ከሶማሌላንድ በመነሳት የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ የገባ ታጣቂ ኃይል የበርካቶችን ህይወት መቅጠፉን አስነብቧል፡፡

ጋዜጣው የክልሉን መንግስት እና ገለልተኛ ወገኖችን አነጋግሮ ባወጣው ሰፊ ዘገባ ታጣቂ ቡድኑ ከባድ መሳሪያዎችን ታጥቆ የኢትዮጵያን ድንበር ጥሶ በመግባት አደገኛ ጥቃት መፈጸሙን ነው የገለጸው፡፡

ከ30 ያላነሱ የሶማሌ ክልል ፖሊስ አባላት እና 53 ንፁሀን ዜጎች ከሶማሌላንድ ወደ ኢትዮጵያ ግዛት ሀርሺን ወረዳ  በገቡ ታጣቂዎች መገደላቸውን የሶማሌ ክልል አመራሮች አረጋግጠዋል ያለው ዘሪፖርተር ሌሎች ምንጮች ግን በጥቃቱ ከ200 በላይ ሰዎች መሞታቸውን መግለፃቸውን ነው የዘገበው።

የክልሉ ፖሊስ 6 የታጣቂ ቡድኑን አባላት የማረከ ሲሆን ምርኮኞቹ የሲቪል ልብስ የለበሱ የሶማሊላንድ ጦር አባላት መሆናቸው መረጋገጡንም ነው ያስነበበው፡፡ መረጃው የዘ-ሪፖርተር ነው!

እያመመው መጣ‼️
በደቡብ ኮሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ

በአደጋው ቢያንስ 42 ተሳፋሪዎች ህይወታቸው አልፏል ተብሏል

የጀጁ አየር መንገድ ንብረት ነው የተባለው አውሮፕላኑ ቦይንግ ስሪት ሲሆን 175 መንገደኞችን ጭኖ ከታይላንድ ወደ በመጓዝ ላይ ነበር

👇👇👇👆
«ትራንስፖርት ፍጹም ይበላሻል በየትኛውም አለም መኪና ፣ ባቡር፣ አውሮፕላን፣ መርከብ ሁሉም ለመገልገል ያስቸግራል አደጋቸውም የበዛ ይሆናል፡፡ ለምህረት ያልታደሉትን ለማጥፋት ሞት ሁሉንም መገልገያዎች ወደ መግደያነት ይለውጣቸዋል፡፡ »

► ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 3 ተፃፈ 19/07/2001 ዓ፡ም
በተደጋጋሚ እየተከሰተ ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ‼️

ዛሬ ታህሣስ 20/2017 ዓ.ም ከደቂቃዎች በፊት ረዘም ላሉ ሰከንዶች የቆየውና አዲስ አበባ ድረስ የተሰማው የመሬት መንቀጥቀጥ ንዝረት  አዋሽ ፈንታሌ ከማለዳው 12:58 ላይ የተከሰተ ሲሆን በሬክተር ስኬል 4.8 ሆኖ የተመዘገበ ሲሆን 10km ጥልቀት አለው።

ሰሞኑን ተከታታይ ቀናት እየተከሰተ እንደሚገኝ ይታወቃል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አሳዛኝ ክስተት!

በደቡብ ኮሪያ የመንገደኞች አውሮፕላን ተከስክሶ የ179 ሰዎች ህይወት አለፈ።

አውሮፕላኑ የተከሰከሰው ከታይላንድ ወደ ደቡብ ኮሪያ እየበረረ እያለ #ሙዓን ተብሎ በሚጠራ ቦታ ላይ ነው የተከሰከሰው። በአውሮፕላኑ ውስጥ ከነበሩ 181 ሰዎች ውስጥ ሁለት ተሳፋሪዎች ብቻ በህይወት ተርፈዋል።

ከሁለት ቀን በፊት የአዘርባጃን አውሮፕላን በሩሲያ ሚሳኤል ተመትቶ 38 ሰዎች መገደላቸው ይታወቃል።
Update‼️

በሲዳማ ክልል በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ 71 ሰዎች ህይወት አለፈ።

👇👇👇👆
«ትራንስፖርት ፍጹም ይበላሻል በየትኛውም አለም መኪና ፣ ባቡር፣ አውሮፕላን፣ መርከብ ሁሉም ለመገልገል ያስቸግራል አደጋቸውም የበዛ ይሆናል፡፡ ለምህረት ያልታደሉትን ለማጥፋት ሞት ሁሉንም መገልገያዎች ወደ መግደያነት ይለውጣቸዋል፡፡ »

► ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 3 ተፃፈ 19/07/2001 ዓ፡ም
ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ በፈንታሌ ተከሰተ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 20፣ 2017 (ኤፍ  ኤም ሲ) በአዋሽ ፈንታሌ  ዛሬ ምሽት  ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል።

በዩኒቨርሲቲው የጂኦ ፊዚክስ ሕዋ ሣይንስና አስትሮኖሚ ተቋም የሴስሞሎጂ ትምህርት ክፍል ሃላፊ አታላይ አየለ (ፕ/ር) እንዳሉት፥ በአዋሽ ፈንታሌ ወረዳና በመተሃራ አካባቢ የተለያየ መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ እየተከሰተ ነው፡፡

ዛሬ ከምሽቱ 2 ሰዓት ከ10 አካባቢ በፈንታሌ አቅራቢያ በሬክተር ስኬል 5 የሆነ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሰቱን ለፋና ዲጂታል ተናግረዋል።

ይህም ሰሞኑን ከተከሰቱት ከፍተኛው አንዱ  መሆኑን ጠቅሰው ፥ንዝረቱ አዲስ አበባ ድረስ መሰማቱን አስረድተዋል።
2024/12/30 20:27:59
Back to Top
HTML Embed Code: