Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ግብጽ በህዝባዊ አመጽ በመናጥ ላይ ናት!

የግብጽ ዜጎች የአልሲሲን መንግስት "በቃህ" በማለት ላይ ይገኛሉ።

የኛ ህዝብ በተለይ አዲስ አበባ ቤቱን በላዩ ላይ እያፈረሱበት ዝም ጭጭ ብሏል


17/04/2017 ዓ.ም
በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ አንድ የአብነት መምህርን ጨምሮ ከ 599 በላይ ኦርቶዶክሳውያን እንደተገደሉ እና ከ 780 በላይ የአብነት ደቀ መዛሙርት መበተናቸው ሀገረ ስብከቱ የ 43ኛው መደበኛ ሰበካ ጉባኤ ባካሄደበት ዕለት በገለጸው ሪፖርት አሳውቋል።

በዕለቱ በእነማይ ወረዳ ከ 103 በላይ ምእመናን ሞት እና በጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርት ከፍተኛ የሆነ መቀዛቀዝ መፈጠሩና በደባይ ጥላት ወረዳ በ 7 አጥቢያ የሚማሩ ከ 300 በላይ ደቀ መዛሙርት መበተናቸውንና በተጨማሪም በባሶ ሊበን ወረዳ አንድ የአብነት መምህርና 395 ምእመናን ሲገደሉ በአነደድ ወረዳ ከ 250 በላይ ደቀ መዛሙርት ከጉባኤ ቤት ውጭ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
በደብረ ኤልያስ የቅኔና የመጻሕፍት ትምህርት ቤት ከ 230 በላይ ደቀ መዛሙርት ሲበተኑ በሸበል ወረዳ ከ 100 በላይ ምእመናን መሞታቸው በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የተገለጸ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ ጠቅላላ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሀገረ ስብከቱ ፈተና ስለሆነው የዶግማና የቀኖና ጥሰት ጉዳይ ፣ ውይይት ተደርጓል ።(🤔)......
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ዋኖቻችንን እንወቅ ❗️)
🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አምስት (5)

(📌 ክፍል 1ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 4ን ለማንበብ 👈)

📌 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሰላማ ማን ናቸው?

🍀 ኅዳር 26 - የልደታቸው በዓል
🌼 ታኅሣሥ 18 - ለኢትዮጵያ ጳጳስ ሊሆኑ
                            የተሾሙበት በዓል
🌺 ሐምሌ 26 - የዕረፍታቸው በዓል

እንደ ተሰጣቸው ክብር ያላከበርናቸው፣ የዘነጋናቸው ባለውለታና ብርሃናችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፦
🍀 ሕይወትና ተጋድሎ
🌼 ልዩ ቃልኪዳን
🌺 ህያው ትሩፋት

ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወታቸውን እና ትሩፋታቸውን ያንብቡ👇

📌 https://telegra.ph/ብፁዕ-ወቅዱስ-አቡነ-ሰላማ-ከሳቴ-ብርሃን-11-14-2
🔔 🔔 🔔 🔔 🔔 ዛሬም ቀጥሏል....
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
🟢🟡🔴
ታኅሣሥ 19 | በዚህች ቀን፦

#ቅዱስ_ገብርኤል_ሊቀ_መላእክት ሠለስቱ ደቂቅን ያዳነበት በዓል ነው።

በቤተ ክርስቲያን ክቡር ከሆኑ ሊቃነ መላእክት አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብርኤል ብዙ የክብር ስሞች አሉት። በተለይ ግን፦
🍀 ሊቀ አርባብ፣
🍀 መጋቤ ሐዲስ፣
🍀 መልአከ ሰላም፣
🍀 ብሥራታዊ፣
🍀 ዖፍ አርያማዊ (የአርያም ወፍ)፣
🍀 ፍሡሐ ገጽ (ደስተኛ ፊት ያለው)፣
🍀 ቤዛዊ መልአክ (አዳኝ መልአክ)፣
🍀 ዘአልቦ ሙስና... እየተባለ ይጠራል።



#_ቅዱስ_ዮሐንስ_ዘቡርልስ ዕረፍቱ ነው።
በሚቀድስበት ጊዜ ፊቱ እሳት ሆኖ ይታይ የነበረውና በጸሎቱ እሳት ከሰማይ አውርዶ መና- ፍቃንን ያቃጥል የነበረ አባት ነው።


መጽሐፈ ስንክሳርን፣ ግጻዌን እና ሃይማኖተ አበውን ለመጀመሪያ ጊዜ ያዘጋጀ፣ ቀድሶ ቅዱስ ቍርባን ሲያቀብል ፊቱ የሚያበራ ቅዱስ አባት ነው።
🍀

#ቅዱስ_አባ_አካለ_ክርስቶስ
እንደ ፋኑኤል መልአክና እንደ አምላኩ መድኀኔዓለም ክርስቶስ የሕሙማን መድኀኒት ይሆናል›› የተባለላቸው ጻድቅ ናቸው።


አባታቸው ቅዱስ አቃርዮስ እናታቸው ቅድስት ታውክልያ የተባሉ እግዚአብሔርን የሚፈሩ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡ የካቲት 19ም ተወለዱ።

ሲወለዱ ብፁዕ አባታችን አባለ ክርስቶስ ከሰውነታቸው ኅቡዕ የሆኑ የእግዚአብሔር የምሥጢር ስሞች በእብራይስጥ ቋንቋ ‹‹ዲካባ፣ ማርትያስ፣ ክስብኤል›› የተባሉ ኅቡዓን የምሥጢር ስሞችን በሰውነታቸው ላይ ይዘው (ተጽፎውባቸው) ነበር።

በ322 ዓመታቸው በፈለፈሉት ዋሻ ዐርፈዋል።
🍀

#አቡነ_ዳንኤል_ዘተንቤን ዕረፍታቸው ነው፡፡

በሌላኛው ስማቸው ዳንኤል ሐዲስ በሚል ስያሜም ይታወቃሉ፡፡ ቆላ ተንቤን የሚገኘውን አስደናቂውን ውቅየን ገብርኤል ፍልፍል ዋሻ ገዳምን በ1435 ዓ.ም ከዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ጋር ሆነው የገደሙ ናቸው፡፡

በ14ኛ መ/ክ/ዘ የነበሩ ታላቅ ጻድቅ ሲሆኑ ትውልዳቸው ሸዋ ነው፡፡

ጻድቁ እህል ሳይበሉ ውኃም ሳይጠጡ 40 መዓልትና 40 ሌሊት ይጾሙ የነበሩ መናኝ ባሕታዊ ናቸው፡፡ እንደ ነቢዩ ኤልያስም ኹለት ሙት አስነሥተዋል፡፡

አቡነ ዳንኤል ፍትሕ እንዳይጓደል ድኃ እንዳይበደል ይከራከሩ ይመክሩ የሚበድሉትንም ይገስጹ ስለነበር ‹‹የድኃ ዕንባ ጠባቂ›› የሚል ስያሜ ተሰጥቷቸው ነበር፡፡

🍀

#አቡነ_ስነ_ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው።

መልአከ ሞት መስከረም 19 ቀን መጥቶ "ጊዜ ዕረፍትህ ደርሷል" ቢላቸው "የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ሳላከብር አይሆንም" ብለው መልአከ ሞትን ለ3 ወራት ገዝተው አቁመውታል።

ታኅሣሥ 19 የቅዱስ ገብርኤልን ዝክር ዘክረው እንደፈጸሙ ለስም አጠራሩ ክብር ምስጋና ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ፥ ከድንግል እናቱ፣ እልፍ አእላፍ መላእክትን፣ ሐዋርያትን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትን፣ የከበሩ መነኮሳትን አስከትሎ እንዲህ የሚል ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል

ቦታህን ሊሳለም የመጣውን ወደ ኢየሩሳሌም እንደሄደ እቆጥርለታለሁ፤

▸ በቦታህ ከወደቀው ፍርፋሪ እንኳን በስምህ ቢመገብ አማናዊውን ሥጋዬን ደሜን እንዲቀበል አደርገዋለሁ፤

▸ ኃጢአቱን ለካህን ለመናገር አሳፍሮት 3 ጊዜ "አባታችን አቡነ ስነ ኢየሱስ ይቅር በለኝ" ቢል የበዛ ኃጢአቱን እደመስስለታለሁ።

🍀

#_እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
2024/12/28 03:27:21
Back to Top
HTML Embed Code: