Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇪🇨 አስደንጋጭ የጦር አውሮፕላን መከስከስ ኢኳዶርን አንቀጠቀጣት

በአደጋው ፓይለቶቹ ሲሞቱ መኪና ውስጥ የነበሩት ሁለት ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇬🇷 ቦራ የተሰኘ አውሎ ንፋስ በግሪክ ሮድ ደሴት ከፍተኛ ጎርፍ አደረሰ
🟢🟡🔴
ኅዳር 26 | ዕረፍታቸው የሆነ እጅግ የከበሩ አባቶቻችን፦

ደሴ ሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳምን የመሠረቱት የአባታችን #የአቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ በዓላቸው ነው፡፡

በጎንደር ክፍለ ሀገር ስማዳ ወረዳ ከአባታቸው ዘክርስቶስና ከእናታቸው እግዚእ ክብራ በ1210 ዓ.ም ተወለዱ።

የአቡነ አረጋዊ 5ኛ የቆብ ልጅ ከሆኑት ዮሐኒ 2ኛ በፈተና ታግሠው በደብረ ዳሞ መነኰሱ።

አባታችን #አቡነ_ኢየሱስ_ሞዐ የአባቶቻችን፦
የተክለ ሃይማኖት (ደብረ ሊባኖስ) 
የኂሩተ አምላክ (ዳጋ እስጢፋኖስ)
የአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ (ቦረና)
የአቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ (ዳውንት) 
የአቡነ አሮን(መቄት)
የአቡነ ዮሴፍ (ላስታ) ... የመንፈስ/የቆብ አባት ናቸው። ምንኛ ድንቅ አባት ናቸው!

ለዚህም ወላዴ አእላፍ - አእላፍን ቅዱሳንን የወለዱ ተብለው ይጠራሉ።
🍀

#_አቡነ_ሃብተ_ማርያም ጻድቅ የሃገራችን ኮከበ ገዳም ናቸው። "ጽድቅና ትሩፋት እንደ ሃብተ ማርያም" እንዲሉ አበው።

ጻድቁ መካነ ሙላዳቸው ሽዋ (የራውዕይ) ውስጥ ሲሆን አባታቸው ፍሬ ቡሩክ፣ እናታቸው ደግሞ ቅድስት ዮስቴና ትባላለች።

ገና በ5 ዓመት ዕድሜያቸው ሌሊት ሌሊት እየተነሡ "ማረን እባክህን" እያሉ ይሰግዱ ነበር።

➻ ባሕር ውስጥ ሰጥመው 500 ጊዜ ይሰግዳሉ
➻በየቀኑ 4ቱን ወንጌልና 150 መዝሙረ ዳዊትን ይጸልያሉ
➻ በ40/በ80 ቀን አንዴ ብቻ ሣርና ቅጠል ይመገባሉ
➻ በየዕለቱ ያለ ማስታጎል ማዕጠንት ያሳርጋሉ
➻ በፍጹም ቂምን መከፋትን አያውቁም

በዚህች ቀን ሲያርፉም መድኃኔዓለም፦
"በሰማይም ከመጥምቁ ዮሐንስ ጎን 500 የእንቁ ምሰሶዎች ያሉበትን አዳራሽ ሰጥቼሃለሁ። በስምህ የሚለምኑ፣ በቃል ኪዳንህ የሚማጸኑትንም ሁሉ እንድምርልህ 'አማንየ! በርእስየ!' ብዬሃለሁ" አላቸው።

በረከታቸው በዝታ ትድረሰን፨
T.me/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ዋኖቻችንን እንወቅ ❗️)
🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አምስት (5)

(📌 ክፍል 1ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማንበብ 👈)
(📌 ክፍል 4ን ለማንበብ 👈)

📌 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሰላማ ማን ናቸው?

🍀 ኅዳር 26 - የልደታቸው በዓል
🌼 ታኅሣሥ 18 - ለኢትዮጵያ ጳጳስ ሊሆኑ
                            የተሾሙበት በዓል
🌺 ሐምሌ 26 - የዕረፍታቸው በዓል

እንደ ተሰጣቸው ክብር ያላከበርናቸው፣ የዘነጋናቸው ባለውለታና ብርሃናችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፦
🍀 ሕይወትና ተጋድሎ
🌼 ልዩ ቃልኪዳን
🌺 ህያው ትሩፋት

ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወታቸውን እና ትሩፋታቸውን ያንብቡ👇

📌 https://telegra.ph/ብፁዕ-ወቅዱስ-አቡነ-ሰላማ-ከሳቴ-ብርሃን-11-14-2
Audio
🟢🟡🔴
ዋኖቻችንን እንወቅ - ክፍል አምስት (5)

በድምፅ ንባብ (ትረካ)
(📌 ክፍል 1ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 2ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 3ን ለማዳመጥ 👈)
(📌 ክፍል 4ን ለማዳመጥ 👈)


📌 ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሰላማ ማን ናቸው?

🍀 ኅዳር 26 - የልደታቸው በዓል
🌼 ታኅሣሥ 18 - ለኢትዮጵያ ጳጳስ ሊሆኑ
                            የተሾሙበት በዓል
🌺 ሐምሌ 26 - የዕረፍታቸው በዓል

እንደ ተሰጣቸው ክብር ያላከበርናቸው፣ የዘነጋናቸው ባለውለታና ብርሃናችን የአቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን፦
🍀 ሕይወትና ተጋድሎ
🌼 ልዩ ቃልኪዳን
🌺 ህያው ትሩፋት

ከዚህ ሥር አጭር ዜና ሕይወታቸውን እና ትሩፋታቸውን ያንብቡ👇

📌 https://telegra.ph/ብፁዕ-ወቅዱስ-አቡነ-ሰላማ-ከሳቴ-ብርሃን-11-14-2
ከስምንቱ የመንግሥት ስኳር ፋብሪካዎች መካከል ባኹኑ ወቅት በምርት ሥራ ላይ ያለው ወንጂ ስኳር ፋብሪካ ብቻ መኾኑን ዋዜማ ካሰባሰበቻቸው መረጃዎች ተረድታለች። መተሐራ፣ ፊንጫ፣ አርጆ ዲዴሳ፣ ከሰም፣ ጣና በለስ ቁጥር አንድ፣ ኦሞ ኩራዝ ቁጥር አንድ እና ኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሁለት ፋብሪካዎች ግን በተለያዩ ጊዜያት ምርት ካቆሙ መቆየታቸውን ዋዜማ አረጋግጣለች። አብዛኞቹ ፋብሪካዎች የስኳር ምርት ያቆሙት፣ ከማሽን ጥገና፣ ከኤሌክትሪክ አቅርቦትና ከጸጥታ ጋር በተያያዘ እንደሆነም ታውቋል

በሌላ በኩል ደግሞ

በኦሮሚያ ክልል፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን፣ ሱሉለ ፊንጫ ወረዳ ውስጥ በሚገኘው መንግሥታዊው የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ሸንኮራ አገዳ ተክል ላይ ትናንት ሌላ የእሳት ቃጠሎ አደጋ መድረሱን ዋዜማ ከፋብሪካው ሠራተኞች ሰምታለች፡፡ ትናንት ከቀትር በኋላ ጀምሮ እስከ ምሽት 2 ሰዓት ድረስ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ፣ በኸለት ማሳዎች ላይ የለማ ከ200 ሔክታር በላይ የኾነ የሸንኮራ አገዳ ተክል ሙሉ ለሙሉ መውደሙን ሠራተኞቹ ተናግረዋል፡፡ ከጥቂት ቀናት በፊትም፣ የፋበሪካ ንብረት የኾነ ሰፊ የሸንኮራ አገዳ ተክልና እስከ 40 ሚሊዮን ብር የሚገመት ማሽን በእሳት አደጋ መውደሙን ዋዜማ መዘገቧ አይዘነጋም።
]
ማናቸውም ማምረቻዎች፤ፋብሪካዎች አገልግሎት ሰጪዎች የጤና ተቋሞች የግልም የመንግሥትም ድርጅቶች መስሪያ ቤቶች አለም አቀፍ ተቋሞች ፤ድርጅቶች በሙሉ ይከረቸማሉ።
⚡️ ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መንግሥት መልእክት 9 አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ገጽ 61 ላይ የተወሰደ።
🟢🟡🔴
ኅዳር 28 | ከ9ኙ ቅዱሳን አንዱ #አቡነ_ሊቃኖስ ተሰወሩ።

እኚህ ቅዱስ እንደ 8ቱ ጓደኞቻቸው ከነገሥታት ቤተሰብ የተገኙ እና ምንኩስናን መርጠው ወደ ኢትዮጵያ የመጡ ናቸው።

"አባ ሊቃኖስ" የመጀመሪያ ስማቸው ሳይሆን በእውቀታቸው የተደመመ የአክሱም ሕዝብ ያወጣላቸው ስም ነው። ሊቃኖስን 'ሊቁ አባት' ማለት ነው ብለው የተረጎሙልን አበው አሉና።

አቡነ ሊቃኖስ ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አቡነ ሊቃኖስ ለየት የሚሉበት ነገር ቢኖር ዓሥሩም የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው ጣቶች እንደፋና ያበሩ ነበር፡፡

ሁልጊዜም ለአገልግሎት ሲወጡ በትረ ሙሴአቸውን አይለዩም ነበር። ሲሰብኩም፣ ሲጸልዩም ተደግፈውባት ነበር። ታዲያ ከዘመን ብዛት የሚደገፉባት የእጃቸው መዳፍ መነደሉን አበው፦ "ወበእሒዘ በትር ዘተሰቁረ ዕዱ" ሲሉ ይናገራሉ።

የአቡነ ሊቃኖስ ገዳማቸው በደብረ ቁናጽል (የቀበሮዎች ተራራ) አክሱም ከጓደኛቸው ከአባ ጰንጠሌዎን ገዳም አቅራቢያ ይገኛል፡፡ ጻድቁ ብዙ ድንቅ ድንቅ ተአምራትን ያደረጉ ነበር፡፡ መላእክትም ዘወትር ባለመለየት ይጎበኙዋቸው ነበር፡፡

ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስም ዘወትር እየተገለጠላቸው ይባርካቸውና ቃልኪዳን ይሰጣቸው ነበር፡፡ በገዳማቸውም ልክ በደብረ ታቦር እንደተገለጠ በግርማው ታይቷቸዋል።

በጸሎታቸውም አጋንንትን አውጥተዋል፣ ድውያንን ፈውሰዋል፣ ዕውራንን አብርተዋል፣ ሙታንን አንሥተዋል፡፡

ከተስዓቱ ቅዱሳን ውስጥ አራቱ ሞትን ሳያዩ ተሰውረዋል፡፡ አቡነ አረጋዊ ጥቅምት 14 ቀን ተሰወሩ፡፡ አቡነ ገሪማ ሰኔ 17 ቀን፣ አቡነ አፍጼ ግንቦት 29 ቀን፣ አቡነ ሊቃኖስ ኅዳር 28 ቀን ተሰወሩ፡፡
🍀

በአርያኖስ እጅ ሰማዕት የሆኑት ኤጲስቆጶስ #ቅዱስ_ሰረባሞን በዓላቸው ነው።

T.me/Ewnet1Nat
                ◦🍀🍀🍀
🍀🍀
ወር በገባ በ29 ቀን ከበዓላት ሁሉ በላይ የሆነ የአምላካችን የእግዚአብሔር ወልድ በዓል ነው።

ይቺን ቀን በዓለ ወልድ (የእግዚአብሔር ወልድ በዓል) ስንል በዚህች ቀን #ዓለምን_ስለፈጠረባት
#ስለተጸነሰባት
#ስለተወለደባት
#ከሙታን_በመለኮቱ_ኃይል_ስለተነሣባት፣ እናም ዳግም ለፍርድ ስለሚመጣባት እናከብራታለን። የወልድ በዓሉ እንላታለን።

🟢🟡🔴
ኅዳር 29 | ልናከብራቸው የሚገቡ እነዚህ ቅዱሳን፦

ከ81ዱ መጽሐፍት መካከል 8ቱን የሥርዐት መጽሐፍ ከቅዱሳን ሐዋርያት ተቀብሎ፣ ጽፎ ያቆየልን፣ የቅዱስ ጴጥሮስ ሐዋርያ ደቀ መዝሙር #ቅዱስ_ቀሌምንጦስ_ዘሮሜ ሰማዕት የሆነበት፣

በቅዱስ እስጢፋኖስ የተጀመረ ዘመነ ሰማዕትነት በእርሱ የተፈጸመ፣ አርዮስን ያወገዘ ሊቅ
#ቅዱስ_ጴጥሮስ_ተፍጻሜተ_ሰማዕት ያረፈበት፣

በከሃዲው ዲዮቅልጥያኖስ ዘመን ሰማዕት የሆኑ
#47_ሚሊየን_ቅዱሳን የሚታሰቡበት፣

በ18 ዓመቷ የመክስምያኖስን ጣዖት አምላኪ ጠቢባን በመንፈሳዊ እውቀቷ አፍ ያዘጋችና ወደ ሰማዕትነት የመለሰች
#ቅድስት_ካትሪና ሰማዕት የሆነችበት፣

500 ዓመት በተጋድሎ ኖረው፣ 50 ዓመት በፀሐይ ላይ፣ 50 ዓመት በጨረቃ ላይ በክንፋቸው የዞሩት
#አቡነ_ዮሐንስ_ዘጠገሮ የተወለዱበት፣ ➻ www.tg-me.com/Ewnet1Nat/10587

ከአጋንንት ልጅነት ወደ ሥላሴ ልጅነትና ቅድስና በአቡነ ተክለ ሃይማኖትና አቡነ ዜና ማርቆስ ጸሎት የመጡት
#አቡነ_ጼዋ_ለጽድቅ ያረፉበት፣

ተከዜን ለሁለት የከፈሉ
#አቡነ_ገብረ_መስቀል ዘለጋሶ የሚታሰቡበት በዓል ነው።

የቅዱሳንን ገድል ማንበብ ለእውቀት ሳይሆን በነፍስ ዋጋ ለማግኘት ነውና በስማቸው በመማፀን፣ በመዘከር፣ በቃልኪዳናቸው በመታመን በነፍሳችን እንጠቀም።

#እንኳን_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
📌 በመላው ኢትዮጵያ መብራት ከቁጥጥር ውጭ በሆነ ምክንያት ጠፍቶ ነበር።
2025/01/08 04:07:48
Back to Top
HTML Embed Code: