Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🇵🇭 🚒 በፊሊፒንስ በተጨናነቀ ሰፈር በደረሰ ከባድ የእሳት አደጋ  1,000 መኖሪያ ቤቶችን አወደመ

የአካባቢው ባለሥልጣናት እንዳሉት ከ3,000 በላይ ሰዎች በአቅራቢያው ወደሚገኝ የመጠለያ ማዕከል ተወስደዋል፣ ነገር ግን በሚያስደንቅ ሁኔታ የአንድም ሰው ህይወት አላልፈም።
«ኢትዮጵያ ከፍ ከፍ እያለች ነው!» ሚኒስትሩ🤔

ልብ በሉ የብር የመግዛት አቅሙ 60 በመቶ በወረደበት በዚህ ሰዓት ነው እንግዲህ!

#ፍርዳችሁ_ይቀድማችኋል!
"ከፈጣሪዬም የተማርኩት ትምክህትን አርቆ ትሕትናን መልበስን መልካም ስለሆነ ነው እንጂ ሊነገርም ሊታሰብ የማይችል ስጦታውን ጌታ ለእኔ ለትንሹ ባርያው ሰጥቷአል። ትምክህት ከጨለማ ስለሆነ በመመካት አልናገርም መግለጽ ግድ ካልሆነብኝ በቀር። የሰው ዘር አድምጥ መሪዎችህ ገዥዎችህ በከፍታ ላይ አቁመህ የምታያቸው የምትንቀጠቀጥላቸው ጣዖቶችህ ክቡር እከሌ፣ አዋቂው፣ ባለሙያው፣ ሊቃውንቱ፣ የጦር ባለሙያው፣ ኢኮኖሚስቱ፣ ባለሃብቱ፣ ቢሊኒየሩ፣ ኢንደስትርያሊስቱ፣ የህክምና ጠበብቱ፣ መሃንዲሱ፣ የአየር ንብረት አዋቂው፣ የጦር አለቃው፣ ተመራማሪው፣ የፖለቲካ ሳይንቲስቱ፣ ኧረ ምኑ ተቆጥሮ የሊቁ፣ የአዋቂው፣ የአባይ ጠንቋዩ፣ የጦር ኤክስፐርቱ ወዘተ እኚህ ሁሉ ምን ፈየዱ? ምንስ ለወጡ? ምንስ አመጡልህ? በየአገሩ ሕዝባቸውን በመግዛት፣ በማስጨነቅ፣ ወደ ጥፋት በመንዳት ላይ ያሉ ከመንደር እስከ አገር፣ ክፍለ አሕጉር የተኮለኮሉ ገዥዎች መቼ ጊዜ ለፈጣሪ ትእዛዝ ጆሮ ሲሰጡ ታየ? የእነሱ ጥፋት ምድርን ሸፍኖ ሰማይን አዳርሷል። የዘመኑን ፊደል ቆጠሩ ሁሉን አዋቂ ሆኑ። ሰርቆ፣ ነጥቆ፣ ገሎ፣ አመንዝሮ፣ ዋሽቶ፣ አታሎ በየትኛውም ቀን ተሰማርቶ ገንዘብን ሰብስቦ ሕዝብን አስጨንቆ መኖሩ ሕልማቸውና ደስታቸው ከሆነ ዘመናት አለፈም ተቆጠረም።"

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ሦስት ገጽ 5 የተወሰደ ተጻፈ መጋቢት 19 2001 ዓ.ም
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
👑 “አመድ ፡ ከዘነመ ፡ ከአራት ፡ ዓመት ፡ በኋላ ፡ የጌታችን ፡ የኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሰማዕት ፡ የሆነ ፡ በፊቅጦር ፡ በገድሉ ፡ መጽሐፍ ፡ እንደተነገረው፡ የስሙ ፡ ምልክት ፡ <ቴ> ተብሎ ፡ የተመለከተው ፡ ይነግሳል ፡፡”
👉🏿ድርሳነ ዑራኤል ዘጥቅምት ምእራፍ 2፥44

👑“...፲፤ በዚያን ጊዜ ወገኖቼ ምዕመናንን የሚጠላ ከዚህ ትውልድ ወገን ንጉሥ ይነሣል ፤ በሱ ዘመን ሃዘንና ትካዜ ይበዛባቸዋል፤ ልዩ ልዩ ችግር ያደርስባቸዋልና ልብሱንና ባሕሉን ይለውጣል ። ባሕላቸውን ለውጠው የአሕዛብን ባሕል እንዲይዙ ያስገድዷቸዋል ሕዝቦቼም
ልክ እንደ ምድረ በዳ አህያ (እርኩም) ይሆናሉ።

፲፩ ዕወቁ ተጠንቀቁ በዚህ ትውልድ የመጨረሻ ጊዜ መከራ በመከራ ላይ ይደራረብባችኋል። ከምድረ ገጽ ነቅለው ጠራርገው ሊያጠፏችሁ ይፈልጋሉና ።

፲፪ ፤ ከዚያን በኋላ ግን ጽኑዕ መንፈሴን እልክና ከወገኖቼ መካከል መርጬ ንጉሥ አነግሣለሁ ፤ ከሱ በፊት ማንም ያልተቀመጠውን ፈረስ ይቀመጣል ፤ የፈረሱም ልጓም ከአዳም በለበስኩት ሥጋ የተቸነከርኩበት የብረት ችንካር ነው ።

፲፫ ይህም ንጉሥ የወገኖቼን በቀል ይወጣል፤ አሕዛብንም ሁሉ ተዋግቶ ያሸንፋቸዋል፤ እናንተም እነሱ ያለዋጋ እንደገዟችሁ፥ እንዲሁ ዓሥር እጅ ያለዋጋ ትገዟቸዋላችሁ ፤ እንደባሪያም ትሸጧቸዋላችሁ።

፲፬ ፤ በዚያም ጊዜ የሚነግሠው ንጉሥ ሃይማኖቱ የቀና በሥራው ሁሉ ዕውነተኛ የሆነ ነው ፤ ከዚህም በኋላ በምሥራቅ በኩል ያለውን ሀገር በር እከፍትና በዚያ የታሠሩትን እሥረኞች እፈታቸዋለሁ ። ከዚያም በከሐዲዎቹ ሰዎች ላይ ይፈርዱና እኔ ከአነገሥሁት ንጉሥ በስተቀር ያጠፏቸዋል ።

፲፭፤ ጥፋታቸውም በባሕርና በየተራራው ይሆናል ። ክብር ምስጋና ለሱ ይሁንና ጌታ ለደቀ መዛሙርቱ ይህን ተናገረ።”
🫴🏿ተአምረ እየሱስ፡ 65ኛ ተአምር ።

#ቴ!
#ኢትዮጵያ_የዓለም_ብርሃን!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🔥🔥🔥

እሳት

አዲስ አበባ ስሞኑን እሳት
እያስቸግራት ነው

በቀን አንድ ቦታ ሳይቃጠል ውሏ
እያቅም

አሁን ከመሸ ጎሮ መድሀኒአለም

🔥🔥🔥
ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በ500 ሄክታር ላይ የተዘራ የደረሰ ሰብልን አወደመ

በአማራ ክልል ደባርቅ ከተማ አሥተዳደር የገጠር ቀበሌዎች በጣለው ከባድ በረዶ ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ ለከፋ ችግር መጋለጣቸውን አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

ኅዳር 14/2017 ዓ.ም ከቀኑ ስምንት ሰዓት ጀምሮ ለ30 ደቂቃ የጣለው ከባድ በረዶ የቀላቀለ ዝናብ በሶስት ቀበሌዎች ከ500 ሄክታር መሬት በላይ የደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

ጉዳቱ በተለያዩ የሰብል አይነቶች ላይ የደረሰ ሲሆን ስንዴ፣ ገብስ፣ ጤፍና ጥራጥሬ ሰብሎች ይገኙበታል።

አርሶ አደሮቹም በአካባቢው ባሕል መሰረት ሰብላቸውን በደቦ ለመሰብሰብ ነገ ዛሬ በሚሉበት ወቅት ድንገት የጣለው በረዶ ሰብላቸውን ሙሉ በሙሉ እንዳወደመባቸው ተናግረዋል።

አቶ ራራ ደሴ የተባሉ የጉዳቱ ሰለባ የሆኑ አርሶ አደር በደረሰው ጉዳት በማዘንና በመደናገጥ በርካታ አርሶ አደሮች ለከፋ የጤና ቀውስ መዳረጋቸውን አንስተዋል።

"ጉዳቱ ያልተጠበቀ ነው፤ እንኳን እኛ እንስሳቱ ራሱ የሚበሉት ድርቆሽ ሳር አልተረፈም" ሲሉ አርሶ አደሩ ማሬ ታረቀኝ ለአሚኮ ተናግረዋል።

የሰሜን ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የሰብል ልማት ባለሙያው ጥላሁን ዓለም ለአሚኮ እንደገለጹት ከ600 በላይ አርሶ አደሮች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
እንደ እባብ ጠቢብ ኹን

እንደ እባብ ጠቢብ ኹን ሲል ምን ማለት ነው? እባብ ጭንቅላቱን (ራሱን) ለማዳን ሲል ሌላው ሰውነቱ እጅግ በጣም ብዙ ጉዳት ቢደርስበት ይመርጣል፡፡ ስለዚህ እንደ እባብ ጠቢብ ኹን ሲልህ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል ሀብትህን፣ ዝናህን፣ ጓደኞችህን፣ ወይም ይህን የመሰለ ሌላ ነገር ማጣት ካለብህ እንኳን በዚህ ማዘን መቆርቆር የለበህም ሲል ነው፡፡ ሃይማኖትህ ራስህ ነውና - እውነትን የምታውቅበት! እውነት ደግሞ አርነት ያወጣሃል፡፡

ኾኖም እንደ እባብ ጠቢብ መኾን ብቻውን ለእኛ በቂያችን አይደለም፤ እንደ ርግብ ሐቀኞችና የዋሆች መኾንም ያስፈልገናል፡፡ በጎ ምግባር የሚኖረው ጥበብንም የዋህነትንም አስተባብሮ መያዝ ሲቻል ነውና፡፡ ለምን ቢሉ እንደ እባብ ጠቢብ የኾነ ሰው ስለ ሃይማኖቱ ሲል ብዙ መከራዎችን ሊቀበል ይችላል፡፡ መከራ በሚያደርሱበት ላይ ክፉን በክፉ አለመመለስ የሚችለው ግን እንደ ርግብ የዋህ መኾን ሲችል ነው፤ እንደ ርግብ የዋህ መኾን ማለት መከራ በሚያደርሱብን ላይ በበቀል አለመነሣሣት መቻል ማለት ነውና፡፡ የዋህነት በጥበብ ሚዛን ካልተመጣጠነ አንድ ሰው መከራ ሲቀበል መከራ በሚያደርስበት ላይ በበቀል እንዲነሣ ያደርጓልና፡፡ ጥበብ በየዋህነት ሚዛን ካልተመጣጠነም እንደዚሁ አላስፈላጊ ሰማዕትነትን እንዲቀበሉ ያደርጋልና፡፡
ስለዚህ ሃይማኖትህን ለመጠበቅ ስትል እንደ እባብ ጠቢብ ኹን፡፡ አብረህም መከራ በሚያደርስብህ ላይ ላለመበቀል ስትል እንደ ርግብ የዋህ ኹን፡፡ ኹለቱንም አዋሕደህ አስተባብረህ ያዝ!

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
🟢🟡🔴
ኅዳር 19 | በዚህች ቀን፦

#ጌቶቻችን ከሆኑ ከ12ቱ ሐዋርያት የአንዱ #ቅዱስ_በርተሎሜዎስ የልደቱ በዓል ነው።

ደግሞም እልዋህ በሚባል አገር አስተምሮ ብዙዎችን እግዚአብሔርን ወደማወቅ ለመለሰበት መታሰቢያው ነው።

ለዚህም ሐዋርያ ሒዶ ያስተምር ዘንድ እልዋህ በሚባል አገር ዕጣው ወጣ። እርሱም ከጴጥሮስ ጋር በአንድነት ሔደ። የክብር ባለቤት በሆነ በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አስተማሩ። ልባቸውንም የሚያስደነግጥ ድንቆች ተአምራትን በፊታቸው ከአደረጉ በኋላ እግዚአብሔርን ወደ ማወቅ መለሷቸው።

ከዚህም በኋላ ወደ ከተማው ውስጥ ገብቶ ያስተምር ዘንድ ምክንያት አደረገ። ቅዱስ ጴጥሮስም እንደ ባሪያ ሸጠው። ባለ ጸጋ ለሆነ መኰንንም በወይን አትክልት ውስጥ የሚያገለግል ሆነ።

ድንቅ ተአምርን በማድረግ የተቆረጡ የወይን ቅርንጫፎች በሠራተኞች እጅ ላይ ሳሉ አፈሩ። የአገረ ገዥውም ልጅ በሞተ ጊዜ ከሞት አስነሣው። የሀገር ሰዎችም ሁሉ አመኑ። እግዚአብሔርንም ወደ ማወቅ ተመለሱ።

ምስክርነቱንና ተጋድሎውንም መስከረም 1 ቀን ፈጸመ።
🌿

#አቡነ_ዮሴፍ_ዘእንጂፋት

አባታቸው ንጉሡ ዐፄ ዳዊት እናታቸው ደግሞ ጽዮን ሞገሳ ይባላሉ፡፡ ደገኛው ንጉሥ ዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ታላቅ ወንድማቸው ነው፡፡ ልደታቸው ኅዳር 19፥ ዕረፍታቸው ደግሞ ግንቦት 19 ነው፡፡ አቡነ ዮሴፍ የተወለዱት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ገብርኤል ብሥራት ነው፡፡

እኚህም ጻድቅ በተጋድሎ እጅግ የታወቁ ናቸው።

➻ ተአምረ ማርያምን ወደ ኢትዮጵያ ያስመጡ፣

➻ ከእመቤታችን በገነት እንጨት ያለ ምንም ማያያዣ የተሠራ ወንበር የተሸለሙ አባት፣

➻ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ለዓለም ብርሃን የሆኑት እመቤታችን ዕጣን የሰጠቻቸው፣

➻ ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑ አባት ናቸው።
🍀
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
መረጃ‼️

የሶማሊያ መንግሥት የጁባላንዱ ፕሬዝደንት ማዶቤ በአገር ክህደት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ አዘዘ

በሶማሊያ የፌዴራል መንግሥት እና በክልላዊው ጁባላንድ መሪዎች መካከል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መጥቷል።
የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት የጁባላንዱ ፕሬዝደንት በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ የእስር ትዕዛዝ ያወጣ ሲሆን፣ በተመሳሳይ የጁባላንድ መንግሥት የሶማሊያው ፕሬዝደንት ላይ የእስር ማዘዣ አውጥቷል።

በዋና ከተማዋ የሞቃዲሾው የሚገኘው ባናዲር ክልላዊ ፍርድ ቤት የጁባላንዱ ፕሬዝደንት አሕመድ ማዶቤን በሀገር ክህደት ከሷቸዋል።

የጁባላንድ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ደግሞ የሶማሊያው ፕሬዝደንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ሕገ-መንግሥቱን በመጣስ እና አመፅ እንዲቀሰቀስ ምክንያት ሆነዋል ሲል ክስ አቅርቧል።
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

🥢 ዓለሙን ስለ ክፋታቸው ክፉዎቹንም ስለ በደላቸው እቀጣለሁ የትዕቢተኛዎችንም ኵራት አዋርዳለሁ።
ትንቢተ ኢሳያስ 13፡11

በ 21/3/2017 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት ይለቀቃል 👇👇👇
ፅዮንን ባሰብናት ጊዜ
@ney_ney_emye_maryam
✝️ ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን✝️

ሶበ ተዘከርናሃ ለጽዮን 
ሶበ ተዘከርናሃ ለፅዮን
ውስተ አፍላገ ባቢሎን
ህየ ነበርነ ወበከይነ
እንዚራቲነ ሰቀልነ ውስተ ጒዓቲሃ

ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
ባሰብናት ጊዜ ጽዮንን
በባቢሎን ወንዞች አጠገብ
ተቀምጠን አለቀስን
መሰንቋችን ሰቀልን በዛፎቿ ላይ
አዝ======

ፅኑ መከራን ተቀበልን  ተጨነቅን በፈተና
የደዌ ሞት በላያችን እንደዝናብ ወርዶዋልና
አህዛብም ዘበቱብን እንዲ ብለው በየተራ
ዘምሩለት ላምላካቹ ቢያድናቹ ከመከራ

እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታልና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ ======

የማረኩን በጦራቸውበኃይላቸው የተመኩ
በጽዮን ደጅ ያለፍርሃት  የጽዮንን ክብሯን ነኩ
ይህን ያየ ከላይ ሆኖ በደመና ተሸፍኖ
ባቢሎንን አሻገረ የማረኩንን በትኖ

እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታልና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን
አዝ======

ስጋችንን ይገል ዘንድ የሞት ጥላ ቢያጠላም
እናልፋለን ሁሉን ባንቺ
የአምላክ እናት ድንግል ማርያም
ቅድስት ሆይ ከባረክሽን
እንድናለን ከደወዌያችን
ለስጋና ለነብሳችን መድኃኒት ነሽ እናታችን
እግዚአብሔር ፅዮንን በመንግስቱ መርጧታልና
ማደሪያው ትሆነው ዘንድ ወዷታልና
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ድንግል ማርያም
ፅዮን ሆይ እናታችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን
አንቺን ብንረሳ ቀኛችን ትርሳን ።
Audio
አባ አምሃ ኢየሱስ ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲየን ከኢሳት ሬድዮ ጋር ከአመታት በፊት አድርገውት የነበር ታሪካዊ ቃለ ምልልስ ቁጥር 2 .m4a
www.tg-me.com/AlphaOmega930
🟢🟡🔴
ኅዳር 21 #ጽዮን_ማርያም

በዚህች ቀን የእመቤታችን ድንግል ማርያም በዓሏ ነው። ዳግመኛም ታቦተ ጽዮን ከነበረችበት ድንኳን ወጥታ ማንም ካህን ሳይሸከማት በተአምራት አብርሃና አጽብሓ ወዳሠሩላት ቤተ መቅደስ ራሷ በመንፈስ ቅዱስ ገብታ ተገኝታለች።

"ጽዮን" ማለት "ጸወን - አምባ - መጠጊያ" ማለት ነው። አንድም በምሥጢሩ "ማኅደረ አምላክ" ማለት ነው። ጽዮን የሚለው ስም በቁሙ ለቅዱስ ዳዊት ተራራና ለኪዳኑ ጽላት ሲያገለግል በትንቢታዊ ምሥጢሩ ግን ለድንግል ማርያም፣ ለቤተ ክርስቲያንና ለዘለዓለማዊት ርስት ያገለግላል።

በዚህች ቀን በዓል ከምናደርግበትም ምክንያት በጥቂቱ፦

🌹 ታቦተ ጽዮን (ጽላተ ኪዳን) ለሊቀ ነቢያት ቅዱስ ሙሴ መሰጠቷን እናስባለን፣

🍀 ታቦተ ጽዮን በምርኮ በሄደችበት በሀገረ ፍልስጤም ዳጎን የተባለ የአህዛብን ጣኦት አድቅቃ በድል የተመለሰችበትን ቀን በማሰብ፣

🌹 ቀዳማዊ ምኒሊክ ከዐሥራ ሁለቱ ነገድ እስራኤል የበኩር ልጅ ጋር ሊቀ ካህናቱን አዛሪያስንና ታቦተ ጽዮንን ይዞ አክሱም የደረሰበትን ቀን በማሰብ፤

🍀 በዘመነ አፄ ባዜን (በ4 ዓ/ም አካባቢ) አማናዊት ጽዮን ድንግል ማርያም ወደ አክሱም ጽዮን በስደት መጥታ ገብታለች። በዚህ ጊዜም 2ቱ ጽዮኖች ሲገናኙ ታላቅ ብርሃን አክሱምን ውጧታልና ይህንንም በማሰብ፤

🌹 አብርሃ ወአጽብሃ በወርቅና በዕንቁ ያሠሩት ባለ አሥራ ሁለት ክፍል ቤተ መቅደስ ለመጀመሪያ ጊዜ ቅዳሴ ቤቱ የተከበረበት ዕለት በመሆኑ፤

🍀 በዘጠነኛው መቶ ክፍለ ዘመን ዮዲት ጉዲት አብያተ ክርስቲያንን ስታቃጥል ታቦተ ጽዮንን ይዘው ወደ ዝዋይ ሀይቅ ከተሰደዱ በኋላ ዘመነ ሰላም ሲጀመር አክሱም በነበሩ ካህናት አስታዋሽነት ከዝዋይ ወደ አክሱም የገባችበት ቀን መሆኑን በማሰብ ነው።

  🌹🌹
እንኳን አደረሳችሁ።
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
2024/12/26 06:35:56
Back to Top
HTML Embed Code: