Telegram Web Link
Audio
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ
08-01-2017ዓ.ም

ክፍል ሀ
Audio
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ
08-01-2017 ዓ.ም

ክፍል ለ
🟢 🟡 🔴
መስከረም 9 | #ቅዱስ_ሚካኤል ሊቀ መላእክት የተአምር በዓሉ ነው።

ይህም እንዲህ ነው፦

የሰማይ ሠራዊት አለቃ በሆነ በከበረ መልአክ በሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚታዩ ድንቆችና ተአምራቶች ምክንያት ዮናናውያን ሰዎች ሰይጣናዊ ቅናትን ቀኑ።

ከመቅናታቸውም ብዛት የተነሣ በዚያ አካባቢ የሚወርደውን የወንዝ ውኃ በዚያች ቤተ ክርስቲያን ላይ ሊመልሱትና ከሚጠብቃት መጋቢዋ ጋር በውኃ ስጥመት ሊአጠፏት ፈልገው መለሱት።

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ለቤተ ክርስቲያኑ መጋቢ ለናርጢኖስ ተገለጠለት። ወደርሱም ቀርቦ "ጽና አትፍራ" አለው።

ይህንን ብሎ በእጁ ውስጥ ባለ በትር ዐለቱን መታው። ዐለቱም ተሰንጥቆ እንደ በር ሆነ። የዚያ ወንዝ ውኃም በውስጡ አልፎ ሔደ።

ይህንንም ያዩ ምስጉን እግዚአብሔርን አመሰገኑት። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አከበሩት።

ከዚያች ቀን እስከ ዛሬ የወንዙን ውኃ በዚያች በተሠነጠቀች ዐለት ውስጥ አልፎ ሲሔድ ያዩታል። ወደ መላእክት አለቃ ሚካኤል ቤተክርስቲያን ከቶ አይቀርብም።

አምላከ ቅዱስ ሚካኤል የሀገራችንን እና የቤ/ክን ጠላቶችን ፈጥኖ ያርቅልን። ከመዓቱም ይሰውረን።

                   ◦🍀🌼🍀
T.me/Ewnet1Nat
ቱርክ የሶማሊያን የባህር ክልል ለመጠበቅ በቀጣዩ ወር የጦር መርከቦቿን ልትልክ ነው‼️

ቱርክ በመዲናዋ አንካራ በ6 ሚሊየን ዶላር ለሶማሊያ ኤምባሲ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗ ተገልጿል

ቱርክ የሶማሊያን የባህር ክልል ከውጭ ከሚሰነዘር ስጋት ለመከላከል በመጪው ወር የጦር መርከቦቿን በአካባቢው ልታሰማራ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ 

በተያዘው የፈረንጆቹ አመት መጀመርያ የመከላከያ ስምምነትን የተፈራረሙት ሞቃዲሾ እና አንካራ በሁለትዮሽ እና የደህንነት ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት ውሳኔ ላይ ደርሰዋል፡፡

 ቱርክ በቀጣዩ ወር በሶማሊያ የባህር ክልል ታሰማረዋለች የተባለው የባህር ሀይልም የዚህ የመከላከያ ስምምነት አንድ አካል ነው፡፡

ወደ ቀጠናው የሚመጡት ሁለት አይነት መርከቦች ሲሆኑ አንድኛው አንካራ በአካባቢው ለምታደርገው የነዳጅ ማውጣት እንቅስቃሴ የሚያግዝ ሲሆን ሌሎቹ ድግሞ የሶማሊያን የባህር ክልል እና የነዳጅ አውጭ ቡድኑን የሚጠብቁ ናቸው ተብሏል፡፡

ቱርክ በሶማሊያ የሚሳኤል እና የጠፈር ሮኬት መሞከርያ ጣቢያ ልትገነባ ነው

የቱርክ የኢነርጂ ሚንስትር አልፓረሰላን ቤራክታር ባሳለፍነው ሳምንት ለሀገሪቱ መገናኛ ብዙሀን እንደተናገሩት ተርኪሽ ፔትሮሊየም የተባለው ኩባንያ እያንዳንዳቸው 5 ሺህ ኪሎሜተር ስኩየር በሚሸፍኑ ሶስት አካባቢዎች ላይ የነዳጅ ፍለጋ እንዲያደርግ ከሶማሊያ ፈቃድ ተሰጥቶታል፡፡
 
ሀገራቱ በገቡት ስምምነት መሰረትም እንደሚገኘው የነዳጅ መጠን ለመከፋፈል እና ላስፈለጋቸው አካል መሸጥ እንደሚችሉ ተጠቅሷል፡፡

 ይህን ተከትሎም ሁለት መካከለኛ የውግያ መርከቦች እና ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ አጋዥ መርከቦች አካባቢውን ለመቃኘት ወደ ስፍራው እንደሚያቀኑ ሚድልኢስት አይ ዘግቧል፡፡

ከጥቅምት ወር ጀምሮ እንደሚሰማሩ የተነገረላቸው እነዚህ መርከቦች ከባህር ላይ ሽፍቶች እንዲሁም ከምድር ሊሰነዘር የሚችል የትኛውንም ጥቃት የመመከት እና የቅኝት አገልግሎት በበቂ ሁኔታ መፈጸም የሚያስችል አቅም ያላቸው ስለመሆኑ ተነግሯል፡፡

ከሶማሊያ ጋር ትብብሯን እያጠናከረች የምትገኘው ቱርክ በመዲናዋ አንካራ በ6 ሚሊየን ዶላር ለሶማሊያ ኤምባሲ ለመገንባት በእንቅስቃሴ ላይ መሆኗም ተዘግቧል።

ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር በወደብ ጉዳይ የተፈራረመችውን የመግባብያ ስምምነት ተከትሎ ሞቃዲሾ እና አንካራ የመከላከያ እና ኢኮኖሚያዊ ትብብር ስምምነት ፈጽመዋል፡፡
  
አንካራ በሶማሊላንዱ ወደብ ምክንያት ቅራኔ ውስጥ የሚገኙትን አዲስአበባ እና ሞቃዲሾ ለማሸማገል ሁለት ያልተሳኩ ጥረቶችን ማድረጓ የሚታወስ ነው።
በሶማሌ ክልል ዋርዴር መስጂድ ውስጥ በተፈጸመ ጥቃት ስድስት ሰዎች መደላቸው ተነገረ

በምሥራቅ ኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ዶሎ ዞን ዋርዴር ከተማ በአንድ መስጂድ ውስጥ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የአገር ሽማግሌ እና ነዋሪዎች ለቢቢሲ ሶማሊ ተናገሩ።

ማክሰኞ መስከረም 7/2017 ዓ.ም. በምሥራቃዊ የክልሉ ክፍል ውስጥ በሚገኘው ዶሎ ዞን ውስጥ የተፈጸመው ጥቃት ምክንያቱ፤ በአካባቢው ባሉ ጎሳዎች መካከል ከዚህ ቀደም ተከስቶ ከነበረ ግጭት ጋር ሳይያያዝ እንደማይቀር ተነግሯል።
አቂል ሞሐመድ ሞሐሙድ የተባሉት የአካባቢው የአገር ሽማግሌ ጥቃቱ መፈጸሙን እና ወጣቶቹ መገደላቸውን ለቢቢሲ አረጋግጠዋል።

የተገደሉት ወጣቶች የሃይማኖት ተማሪዎች መሆናቸው የተገለጸ ሲሆን፣ የአገር ሽማግሌው “በስድስቱ ወጣቶች ላይ የተፈጸመው ድርጊት እጅግ ዘግናኝ ነው” በማለት ሐዘናቸውን ገልጸዋል።

ወጣቶቹ የተገደሉት ኩጂር በተባለው መስጂድ ውስጥ ለሶላት እየተዘጋጁ ሳለ መሆኑን የገለጹት የአገር ሽማግሌው፤ “ታጣቂዎቹ በአነስ ባለ መኪና ወደ መስጂዱ መጥተው በልጆቹ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል” ብለዋል።

በጥቃቱ መስጂድ ውስጥ የተገደሉት ስድስቱ ወጣቶች ወንዶች የቀብር ሥነ ሥርዓት ረቡዕ ዕለት እዚያው ዋርዴር ከተማ ውስጥ መፈጸሙን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
❗️ሊባኖሳውያን ​​በሞተር ሳይክሎች፣ መኪናዎች እና በተለያዩ መሳሪያዎች ላይ ፍንዳታ እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል
«ትራንስፖርት ፍጹም ይበላሻል በየትኛውም አለም መኪና ፣ ባቡር፣ አውሮፕላን፣ መርከብ ሁሉም ለመገልገል ያስቸግራል አደጋቸውም የበዛ ይሆናል፡፡ ለምህረት ያልታደሉትን ለማጥፋት ሞት ሁሉንም መገልገያዎች ወደ መግደያነት ይለውጣቸዋል፡፡ »

► ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 3 ተፃፈ 19/07/2001 ዓ፡ም
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
❗️ሊባኖሳውያን ​​በሞተር ሳይክሎች፣ መኪናዎች እና በተለያዩ መሳሪያዎች ላይ ፍንዳታ እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል።
❗️ባለፉት 2 ቀናት በሊባኖስ ውስጥ በደረሰው የመገናኛ መሳሪያዎች ፍንዳታ የ37 ሰዎች ህይወት እንዳለፈ እና በመጀመሪያው ማዕበል 12 ሰዎች እንዲሁም በሁለተኛው ማእበል ተጨማሪ 25 ሰዎች መገደላቸውን የሊባኖስ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር አስታውቀዋል

በጉዳዩ ዙርያ ባለስልጣኑ የሰጡት ተጨማሪ መግለጫዎች፦

🟠 በመጀመሪያው ቀን ወደ ሆስፒታል የተወሰዱት ተጎጂዎች ቁጥር 2,323 ደርሷል።
🟠 608 ሰዎች እሮብ እለት ቆስለዋል።
🟠 1,343 የሚሆኑት ተጎጂዎች በመካከለኛ ወይም ከባድ ሁኔታ ላይ ናቸው።
🟠 በሁለተኛው የጥቃት ማዕበል የገመድ አልባ መሳሪያዎች ፍንዳታ ሃይል ጠንከር ያለ በመሆኑ የከፋ ጉዳት ተመዝግቧል።
🟢🟡🔴
መስከረም 10 |
#ጼዴንያ በምትባል አገር ሥጋ የለበሰች ከምትመስል ሥዕል ከሠሌዳዋ ቅባት እየተንጠፈጠፈ አምላክን የወለደች የእመቤታችን የድንግል ማርያም ተአምር ተገለጠ

ዳግመኛም በዚህ ቀን፦

🌼 የቅዱሳት ሥዕላት ሁሉ በዓል ነው።

🌼 #ተቀጸል_ጽጌ #ዓፄ_መስቀል ይከበራል። የጌታችን ቅዱስ መስቀል አገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ የገባበት ቀን ነው፡፡

● ከከሃዲው ከሆሎፎርኒስ እጅ በጥበቧ እስራኤልን ያዳነቻቸው የሜራሪ ልጅ #ጥበበኛዋ_ዮዲት (የጳጒሜን ጾም ላይ የምናስባት ቅድስት) ዐረፈች

🌼 #ንግሥተ_ሳባ (ንግሥት ማክዳ) ዕረፍቷ ነው።

🌼 ቅድስት መጥሮንያ ሰማዕት፦ በእምነት ከማትመስላት አይሁዳዊት ቤት አገልጋይ ሆና ብትኖር እምነቷን ልታስቀይራት ብዙ ሞክራ አልሳካ ሲላት የገደለቻት፣ በሃይማኖቷ ጸንታ እምነቷን ጠብቃ ሰማዕትነትን የተቀበለች ቀን ነው።

ከእመቤታችን፣ ከቅዱስ መስቀሉ፣ ከቅዱሳኑ ሁሉ ረድኤት በረከትን አይንሣን።

🍀🌼🍀
T.me/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (♝ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን♝ 🇨🇬🇨🇬)
"ይሁ ሁሉ የእግዚአብሔርን ስራ ማደናቀፍ ያለ ዋጋ ክፍያ ይታለፋል ማለት ስህተት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ስራ ማንም በስጋ ጥበብና ጉልበት ሊያደናቅፈው የሚቻል አይደለም፡፡ ሲሞክርም ቅጣቱ ይሰነዘራል፡፡"

📎 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ቁጥር 5 ፡ ገፅ 38 * ተጻፈ መስከረም 21/2004 ዓ.ም
2024/11/15 16:59:48
Back to Top
HTML Embed Code: