This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM

🌪 የቻይና ሁለት ግዛቶች በታይፎን ያጊ አርብ አመሻሽ ላይ ይመታሉ ተብሎ የተተነበየ ሲሆን በሃይናን እና ጓንግዶንግ ሪዞርቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ያሳድራል።
በሃይናን ደሴት ወደ 420,000 የሚጠጉ ሰዎች አካባቢው እንዲለቁ የተደረገ ሲሆን፤ ትምህርት ቤቶች ተዘግተዋል፤ በተጨማሪም የአየር በረራ እንዲቋረጥ ተደርጓል።

Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ንዋይ)
. ጳጕሜን 3
🌈 ርኅወተ ሰማይ 🌈
💚💛❤️
ይህች ዕለት የሰዎች ሁሉ ጸሎት የሚያርግባት፣ አራተኛው መጋቢ ኮከብ የሚያልፍባት፣ ለሰው ልጆች ከፈጣሪያቸው ጸጋ በረከት የሚሰጥባት ዕለት ስለሆነች "ርኅወተ ሰማይ – ሰማይ የሚከፈትባት ቀን" ትባላለች።
[አሁን] በሰማይ መዘጋት መከፈት ኑሮበት አይደለም። የሰው ልጆችን ልመና ቅዱሳን መላእክት ያለ ከልካይ የሚያሳርጉበት፣
[አንድም] ቅዱስ ሩፋኤል የዓመቱን የጸሎት መዝገብ የሚከፍትበት ቀን ስለሆነ እንዲህ ተባለ እንጂ።
እመቤታችን ድንግል ማርያም ለዓፄ ናዖድ እንደ ነገረቻቸው፥ በዚህች ዕለት ሁሉም ቅዱሳን ስለሚታሰቡ የእግዚአብሔር የምሕረት መዝገቡ ስለሚከፈት ዕለቷን ክብርት ያሰኛታል።
#በቅዱስ_ሩፋኤል አበጋዝነት (መሪነት) በዚህች ዕለት ለዓመት የሚበቃ ምሕረት ይገኛል።
ስለዚህም አባቶቻችን በዚህች ሌሊት፥ ሦስት መቶ ስልሳ አምስት አቡነ ዘበሰማያትን ሲጸልዩ ያድራሉ። በሌላ ወገን ደግሞ የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መታሰቢያ እንደ መሆኗ ትልቅ ትኩረትም ይሰጣታል።
«☘️ ቸሩ ጌታችን ከተከፈተች ገነት ከተነጠፈች ዕረፍት ሁላችንንም ያድርሰን ☘️»
💚 www.tg-me.com/christian930
💛 www.tg-me.com/AlphaOmega930
❤️ www.tg-me.com/Ewnet1Nat

🟢🟡🔴
ጳጒሜን 3 |
የመላእክት አለቃ የከበረ #ቅዱስ_ሩፋኤል በዓሉ ነው።
እርሱም ከመላእክት አለቆች ሦስተኛ የሆነ ነው። ደግሞም ከእስክንድርያ ውጭ በደሴት የታነፀች ቤተ ክርስቲያኑ በከበረ ሊቀ ጳጳሳት ቴዎፍሎስ ዘመን በውስጧ ተአምር የተገለጸባት የከበረችበት ነው።
ያቺ ደሴት በታላቅ አንበሪ ጀርባ ላይ የቆመች ናትና የሰዎች ብዛትም በከበደው ጊዜ ቤተ ክርስቲያኒቱን ያፈርሳት ዘንድ ሰይጣን አነሣሣው። ወደ ክብር ባለቤት እግዚአብሔርም በከበረ መልአክ ሩፋኤል ስም ጮኹ።
ያን ጊዜ ይህ የከበረ ሩፋኤል ያንን አንበሪ በጦሩ ወግቶ እንዲህ አለው፦ እግዚአብሔር አዞሃልና ከቦታህ ሳትናወጽ ጸጥ ብለህ ቁም። አንበሪውም ጸጥ ብሎ ቆመ አልታወከም። በውስጧም ድንቆች ተአምራቶች ተገለጡ። ለሕሙማንም ፈውስ ሆነ።
🍀 ለእግዚአብሔር ልጅ ምሳሌው የሆነ #የመልከጼዴቅ መታሰቢያው ነው።
አብርሃምም ከጦርነት ነገሥታትን ድል አድርጎ በተመለሰ ጊዜ ኅብስትንና ወይንን አቀረበለት። አብርሃምም ከገንዘቡ ሁሉ ከዐሥር አንድ ሰጠው እርሱ ካህንም ንጉሥም ሁኖ ተሹሟልና።
🍀 መልካም ስም አጠራር ያላቸው #ዓፄ_ዘርዐ_ያዕቆብ ዐረፉ።
ተአምረ ማርያምን ጨምሮ ከ11 ያላነሱ መጻሕፍትን በመንፈስ ቅዱስ አጋዥነት ደርሰዋል። ብዙ መጻሕፍትን ከውጪ አስመጥተው አስተርጉመዋል፡፡ ሰው ሁሉ ለእመ ብርሃንና ለቅዱስ መስቀሉ ፍቅር እንዲገዛ ጥረት አድርገዋል፡፡
እመቤታችንን በፍጹም ልባቸው ከመውደዳቸው የተነሣ ዛሬም ድረስ በሃገራችን ድንግል ማርያም "የዘርዓ ያዕቆብ እመቤት" እየተባለች ትጠራለች፡፡
🍀 #ቅዱስ_ሰራጵዮን ዐረፈ።
ይህም ቅዱስ ራሱን ባርያ አድርጎ እየሸጠ አሕዛብን ወደ ክርስቶስ የሚመልስ ነው።
🍀 ባለ ስድስት ክንፉ፣ በቃልኪዳናቸው መልአከ ሞትን የማያሳዩት #አቡነ_ቀፀላ_ጊዮርጊስ ዐረፉ።
T.me/Ewnet1Nat