Telegram Web Link
ሶማሊያ

የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዛሬ ወደ ግብፅ ካይሮ አቅንተው ከግብፅ አቻቸው ጋር ውይይት አድርገዋል!

ውይይቱ ምን ላይ ያተኮረ ነው የሚለው በግልፅ ባይታወቅም በሁለቱ ሀገራት የደህንነት ጉዳዮች ላይ እንደተወያዩ የሀገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ግብጽ ከቀናት በፊት የጦር መሳሪያ ወደ ሶማሊያ ማጓጓዛ የሚታወስ ነው።

በተመሳሳይ ዜና የሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ ከሀገሪቱ የጦር መሪ ጋር ውይይት ሲያደርጉ ውለዋል ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Audio
ገድለ አቡነ ኢየሱስ ሞዓ
Audio
መልክአ ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
🟢🟡🔴
ነሐሴ 27 | ከ7ቱ የመላእክት አለቃ አራተኛ የሆነ #የቅዱስ_ሱርያል የበዓሉ መታሰቢያ ነው።

የመላእክት መዓርግ ሲነገር ቅ/ሚካኤል፣ ቅ/ገብርኤል፣ ቅ/ሩፋኤል ብሎ ቀጥሎ የሚመጣው ሱርያል ነው።

🍀 በሊቀ ካህናት ኤሊ ዘመን፥ #ነቢዩ_ሳሙኤል በቤተ መቅደስ ሳለ የተጠራበት የመታሰቢያው ዕለት ነው።

አባቱ ሕልቃና፣ እናቱ ሐና ይባላሉ። እነርሱም ከሌዊ ነገድ ከካህኑ አሮን ወገን ናቸው። ሐናም መካን ነበረች። ክብር ይግባውና ወደ እግዚአብሔር እያለቀሰች አዘውትራ ስለ ማለደች ይህን የተባረከ ልጅ ሰጣት።

ከዚህም በኋላ ገና ስትፀንሰው እንደተሳለች ወደ እግዚአብሔር መቅደስ አቀረበችው። ካህኑ ኤሊንም በመላላክ የሚያገለግለው ሆነ።

የካህኑ የኤሊ ልጆች ግን ክፉዎች ነበሩ። እግዚአብሔርንም አይፈሩም ነበር፤ በቅዱስ መሥዋዕቱም ላይ በደሉ። ይህ ሕፃን ሳሙኤል ግን በኤሊ ፊት ለእግዚአብሔር ሲያገለግል ኖረ። በነዚያ ወራቶችም ቃለ እግዚአብሔር ውድ ነበር፤ የሚታይ ራእይም አልነበረም።

ይህም ነቢይ ሳሙኤል በሕይወት በኖረበት ዘመን ሁሉ እስራኤልን አስተዳደራቸው። ከዚህም በኋላ ሰኔ ዘጠኝ በሰላም አርፏል።

🍀 ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_ዘርዐ_ቡሩክ ልደታቸው ነው።

በትንቢት የተወለዱት እኚህ ጻድቅ አባታቸው ደመ ክርስቶስ ዐይነ ሥውር የነበረ ሲሆን አቡነ ዘርዐ ቡሩክ በተወለዱ ጊዜ ግን የአባታቸውን ዐይን አብርተውለታል።

በሰባት ዓመታቸውም «ይህን ዓለም ክፋቱን እንዳላይ ዐይኖቼን አሳውርልኝ» በማለት ዐይናቸውን እንዲያጠፋላቸው አምላካቸውን ለምነው እንደፈቃዳቸው ዐይነ ሥውር ሆነዋል።

ነገር ግን ከሰባት ዓመት በኋላ በ14 ዓመታቸው ጌታችን "ለዓለም የምታበራ ብርሃን አደርግሃለሁና ዐይንህም ይብራ" በማለት ዐይነ ብርሃናቸውን መልሶላቸው እንዲያዩ አድርጓቸዋል።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
«...ይሁንና ይሁንና እኔ ተስፋ አልቆርጥም። እኔ ተስፋ አልቆርጥም። ኢትዮጵያ እንደገና ትነሳለች። ኢትዮጵያ ትታደሳለች። ኢትዮጵያ ትመለሳለች። እንደነበረም ትሆናለች። እንደነበረም ትሆናለች።

ሥጋውያን አስተዳዳሪዎችና ሥጋውያን መሪዎችም እነሱ ባሉት አገር አትቀናም፤ አገር አትጠፋም። እሺ ቢሉ፤ እግዚአብሔርን ቢቀበሉ፤ ይኖሩባታል ይኖሩላታል። እምቢ ቢሉ ግን ይወገዳሉ እንጂ እግዚአብሔር ከመንግሥቱ አይሻርም፥ አገርም አትጠፋም።

እና ስለዚህ ከደርግ ዘመን ጀምሮ ከደርግ ዘመን ጀምሮ በእግዚአብሔር ላይ የሸፈተው ልብ የሚመለስበት ቀን በቅርብ ቀን ይመጣል። በቅርብ ቀን ይመጣል።

ዛሬ ኢትዮጵያን "እንውጣለን" ብለው ያሰፈሰፉ፤ አፋቸውን የከፈቱ፤ ጉሮሯቸውን ያላቀቁ ሁሉ ነገ ይህ ሁሉ ይዘጋል። ሁሉም ነገር ይቀራል። እግዚአብሔር አንድ ኃይል ያስነሳል ! አንድ ኃይል ያስነሳል !

አሁን እውነተኛው ነገር ከሆነ በውስጥም ያለነው በስደትም ያሉት ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አንድ ልብ አንድ ዐሳብ ሆነው ወደአገራቸው፤ ወደሃይማኖታቸው ማተኮር አለባቸው። ደሞ እምቢ ካልን እኛ እንጠፋለን እንጂ ኢትዮጵያን እግዚአብሔር ያድናታል። ኢትዮጵያም ኢትዮጵያ ትሆናለች፥ እጆቿን ወደእግዚአብሔር ትዘረጋለች፥ እግዚአብሔርም እጇን ጨብጦ ይመራታል።»


📌 ታላቁ ሊቀ ሊቃውንት አለቃ አያሌው ታምሩ በአንድ ወቅት ከአሜሪካ ሬድዮ ጣብያ ጋር አድርገውት ከነበረ ቃለ ምልልስ ስለኢትዮጵያ ትንሣኤ የተናገሩት!
🇨🇬 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
📎 www.tg-me.com/AlphaOmega930
Audio
🔊 የእግዚአብሔር ሰይፍ ተመዟል ! እንዲያው አይመለስም !
አለቃ አያሌው ታምሩ
https://www.tg-me.com/christian930/3764
📌 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክታትን ሳይሰሙ 24ሰዓት በሃሰት የሚነቅፉ ሰዎች እነማን ናቸው ብዬ 81ዱ መጽሐፍ ቅዱስን ስጠይቅ ስለማንነታቸው የተሰጠኝ መልስ ይሄ ነው።
የሱማሊያዉ ፕሬዝዳንት ክተት አወጁ‼️

የሱማሊያዉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሀመድ ሁሉም የሶማሊያ ዜጋ እና አመራር ለወታደራዊ ግዳጁ ይዘጋጂ ሲሉ ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፈዋል ፡፡
2024/09/29 22:29:06
Back to Top
HTML Embed Code: