Telegram Web Link
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📌 እምንመክርህ እንድትድን ነው።

ኢትዮጵያዊነትን እመንበት

ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነትህን ጨብጥ !

ሰንደቋን አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ባንዲራ ውደድ !

እሰረው በልብህም፣ በክንድህም፣ በአንገትህም አርገው ።

ከዚህ ውጪ ወደእኛ ና አላልልንም።

ባለህበት ግን የእግዚአብሔር ወገን ሁን።

ለእውነተኛይቱ  ቤተክርስቲያን እውነተኛ ልጇ ሁናት ።

ከሚመስሉህ ጋር  የጽዋ ማህበር አቋቁም ።
እጣ አውጥተህ ዘክር ።

ፈጣሪህን፣ እናትህን ድንግልን  አመስግን።
ይበልጥም ለቤተክርስቲያን በጸሎትም በጾምም ዘብ ሁን። ለቤተ ክርስቲያን ዘብ ሁን።

በኢትዮጵያ ትንሣኤ የጸና ተስፋ ይኑርህ።

በቃ!! የምንመክርህ ይኸንን ነው። እኛ ያልነው ይኸንን ነው። ሌላ 'ምንለው ነገር የለንም።

በውኑ እኛ መልእክታቱ የተናገሩት የሰማችሁት ሰምታችኋል ያልሰማችሁት ባትሰሙትም  ይሄው እንደ ቃሉ እየመጣ አይደለም ወይ ?

ብዙ አባቶች ተናግረዋል። የሚሰማ ግን የለም።
...

🟢🟡🔴 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን 
መግለጫ እና የሉቃስ ወንጌለ ትምህርት ክፍል 13(ሀ) ላይ የተወሰደ። አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
ሸዋ ደብረሲና!

በሸዋ ደርበሲና የመሬት መሸራተት ተከሰተ የመሬት መንሸራተቱ የተከሰተዉም ልዩ ስሙ እንዶዴ አካባቢ ሲሆን አደጋው በመኖሪያ ቤቶች እና በእርሻ መሬት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል።አሁንም ቢሆ ን የአካባቢዉ ማህበረሰብ ከፍተኛ ትኩረት ያሻዋል!
🇳🇬 በናይጄሪያ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ባለፉት ሳምንታት 170 ሰዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ዘገባዎች አመለከቱ

በሰሜናዊ ናይጄሪያ በሚገኙ አስር ግዛቶች በተከታታይ ቀናት በጣለ ዝናብ ሳቢያ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በእርሻ መሬቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱንና የሀገሪቱን የምግብ እጥረት እንዳያባብስ ስጋት መፈጠሩን የምዕራቡ ዓለም ጋዜጣ ሰኞ እለት ዘግቧል።

በተፈጥሮ አደጋው ከ200,000 በላይ ሰዎች ከመኖሪያ ቀያቸው እንደተፈናቀሉ የገለጸው ዘገባው ሰሜን ናይጄሪያ በጎርፉ በክፉኛው እንደተጎዳች አክሏል።

ጋዜጣው የናይጄሪያ ብሔራዊ የአደጋ ጊዜ አስተዳደር ባለስልጣን ቃል አቀባይ ማንዞ ኢዝኪዬል "በሚቀጥሉት ቀናት ማእከላዊ ክፍሎች እንዲሁም ወደታች ወረድ ብሎ ደቡባዊ ክፍሎችም ተመሳሳይ ጎርፍ ይገጥማቸዋል" ማለታቸውን ጠቅሶ አስነብቧል።

በናይጄሪያ በቅርቡ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ 2,000 ሰዎች እንደተጎዱ እና ከ100,000 ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት መውደሙን ዘገባው አክሎ ገልጿል።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
አይ አንች ከንቱ ዓለም
የሰው ልጅ አስገኝው ዝንጀሮ ነው ብለሽ
በዝንጀሮ ህመም ትተራመሻለሽ።
📌 "ጥበብ ፤ እውቀት ፤ ሀብት ፤ ወርቅ ፤ እንቁ ፤ ሥልጣኔ ፤ ኢንዱስትሪ ፤ ጀቱ  ታንኩ ፤ ኒኩለሩ  እነዚህ ሁሉ ከምንም ከምንም  አያድኑም ፡፡ በምንም መንገድ  አያድኑም፡፡

ትላንት በአንድ በሽታ በአንድ ይህ ኮቪድ በሚባል የታመሰውና ግራ የገባው ዓለም ኢኮኖሚውም በዚህ ምክንያት ደቆ ባዶ የሆነበት ዓለም ትርምስምሳቸውን ያወጣቸው አንድ በሽታ አንድ  የአንድ   በሽታ ገጽታ  ነበር ፡፡

አሁን ደሞ ከበፊቱም የከፋ እጅግ የከፋ የበሽታዎች አይነት የተፈጥሮ አደጋዎች እጅግ በዝተው ከሰባት እጥፍ በላይም እየጨመሩ እንደሚመጡ ዛሬም ለሁሉም ሰሚና ጠፊ ሁሉ ትውልድ ግልፅ ሊሆንለት ይገባል፡፡

እግዚአብሔር ያለውን ሳይፈጽም የሚቆም ነገር የለም፡፡ የተናገረው ሳይፈጸም ሳይከናወን የሚቀር ነገር የለም ፡፡ ወረፋውን ነው የሚጠብቀው ወገኖቼ ምንም የሚቀር ነገር የለም፡፡"

🇨🇬  በቀን 9 /12/2014 ዓ፡ም ከተለቀቀው፡፡
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የሉቃስ ወንጌል ትምህርት ክፍል ሁለት ላይ ለግንዛቤ ያህል ተቀንጭቦ የተወሰደ፡፡
📌 ጌታ ሆይ ዛሬም እንድንበት ዘንድ በመረጥኻቸው ባሮችህ በኩል የተናገርከውን ቃልህን፣ መልዕክትህን አልሰማንኽም። መልዕክታትህ ሁሉ ለስድብ ፣ ለነቀፌታ፣ ለትችት ሆኖብናል። ደስም አላሰኘንም። እነሆ በነቢዩ ኤርምያስ አንደበት የተናገርኸን ተፈጽሞብናል።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📹 🇮🇳 በህንድ ጉጃራት ክልል በጣለ ከባድ ዝናብ ምክንያት ድልድይ ተደረመሰ ‼️
አሁን..!

አሁን በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ እና ቱሉ ሚልኪ መሀከል አንድ የህዝብ አውቶብስ ሙሉ ተሳፋሪ ከሾፌር ረዳት ጋር በታጠቁ ሀይሎች ታፍነው ተወስደዋል!
» መሪዎች ይጮሃሉ የሚሰማቸውም ያጣሉ ያደራጁት የጸጥታና የጦር ኃይል አይታዘዝም የመዳከም የመበተንም እጣ ይገጥማቸዋል። ሕዝቦች ለማንኛውም የመንግሥት ኃይል አይታዘዙም አይፈሩምም ሕግ የተባለ ሁሉ የሚያከብረው ያጣል።

» ሰላም ስሙ እንጂ ምግባሩና ምልክቱ ፈጽሞ ይጠፋል።

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት 3 ገጽ 58 (የፖለቲካ ቀውስ) ተጻፈ መጋቢት 19/2001 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
2024/09/25 00:26:00
Back to Top
HTML Embed Code: