Telegram Web Link
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🍀🌼🌺
«ዐሥር ሰዎች ሞተው ተቀበሩ ዛሬ፤
ድጓ ጾመ ድጓ፥
ብሉይና ሐዲስ፥
ቅኔና አቋቋም፥ መጻሕፍተ ሊቃውንት
እንዲሁም ቅዳሴ፥ መዋሥዕት ዝማሬ።»


[ባሕታዊ አምኃ ኢየሱስ ገብረ ዮሐንስ ስለ አለቃ አያሌው ታምሩ ዕረፍት የተናገሩት]

"ቤተ ክርስቲያን በሯን ዘግታባቸው የአለቃ አያሌው ታምሩ ቀብር ተፈጸመ"
፨ነሐሴ 17 | 1999 ዓ.ም፨

#ዝክረ_አለቃ_አያሌው
▮በረከታቸው ይደርብን።
▯www.tg-me.com/AlphaOmega930
ኦርቶዶክሳዊውን እምነት፣ እውነቱን መስክር፣ የኢትዮጵያ ፍቅር፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን ክብር፣ የአምላኳን ገናናነት፣ ኃያልነት፣ ቸርነት ተናገር! ተናገር! ዝም አትበል እያለች ትቀሰቅሰኛለች። ይህ ደግሞ የግቢውንም የውጪውንም ጋኔን ያስጮኸዋል። ያስለፈልፈዋል። እኔ ግን ደንታ የለኝም ። ወንጌልን በማስተማር አላፍርበትም። ለሆዴ ብዬም ክብሬን፣ ኦርቶዶክሳዊ፣ ኢትዮጵያዊ መብቴንም አላስረግጥም ። ይህንንም ሀብቴን ፈቃደኛ ለሆነ ሁሉ ለመንፈሳዊውም ለሥጋዊ ልጆቼም አወርሳለሁ ። ይህ ነው እውነተኛው መንገድ ።

📌 ክቡር አለቃ አያሌው ታምሩ
ከ“ምልጃ፣ ዕርቅና ሰላም” መጽሐፋቸው የተወሰደ
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
«ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክታት ለ15 ዓመታት በአጠገብህ ሲፈሱ መች ሰማሃቸው ፡፡ በየፌስቡኩ በቴሌግራሙ በዩቲዩቡ ጧት ማታ ተጥደህ የምትውል ትውልድ ፤ በቢሊዮኖች የምትቆጠረው መልእክታቶቹ ሁሉ በፊትህ አልነበሩም እንዴ ስቀህና ንቀህ እያፌዝክ አልተውካቸውም ፡፤ በታላላቅ ቋንቋዎች በሙሉ ተጽፈው በድምፅም ተዘጋጅተው ደርሰውሃል ። ለምነውሃል ያለመታከት ጮኸዋል ስለዚህ ዛሬ በፍርድ ስትያዝ ማን ያስጥልሃል ማንም አያስጥልህም የተጣላኸው ከሥላሴ ነውና፡፡»

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት 9ኛ መልዕክት ገጽ 36 * ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2013 ዓ.ም !
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍀 እግዚአብሔር አንድ ኃይል ያስነሣል!

“እኔ ተስፋ አልቆርጥም።
#ኢትዮጵያ እንደገና ትነሣለች።
#ኢትዮጵያ ትታደሳለች።
#ኢትዮጵያ ትመለሳለች።
እንደነበረም ትሆናለች
።”

#_ዝክረ_አለቃ_አያሌው_ታምሩ
            
#የአለቃ_ሳምንት

💚 አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
💛
www.tg-me.com/AlphaOmega930
❤️
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA)
"በፓትርያርክ አቡነ ማትያስ የምትመራው ቤተክርስትያናችን፤ ሲኖዶስ፤ የዋናውም የየክልሉም የጠቅላይ ቤተክህነቱ መዋቅር ከፓትርያርኩ ጀምሮ እስከ አጥቢያ ያሉ አገልጋዮች፤ ካህናት ዲያቆናት ጳጳሳት ሰባኪዎች መምህራን ዘማሪዎች ሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች አስተማሪዎች ወዘተ በተመዘናችሁበት መሰረት የተወሰነላችሁን እጣችሁን ታገኛላችሁ። ይህ ደብዳቤ እናንተ ጋ ከደረሰ ጀምሮ በተከታታይ እርምጃው ይቀጥላል። መድኃኔዓለም አባታችን መድኃኒታችን ከእናታችን ከእናቱ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ጋር ጎብኝተዋችኋል። ሥራችሁም መዝነው በጣት ከሚቆጠሩ በስተቀር ቀላችኋል። ፍርዳችሁን የታዘዘውን ሁሉ ለመተግበር ሊቀ-መላእክት ቅዱስ ሚካኤል፤ ሊቀ-መላእክት ቅዱስ ገብርኤል፤ ሊቀ-መላእክት ቅዱስ እሩፋኤል፤ ሊቀ-መላእክት ፋኑኤል በማይቆጠረው ሃይላቸውና ክብራቸው ውሳኔውን ለመተግበር ተነቃንቀዋል። ራሳችሁን አዘጋጁ የሚሰጥ ምንም ጊዜ የለም።"

ኢትዮጵያ የአለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ ገጽ 5*
📌ተፃፈ ጥር7/2012ዓ.ም
    «ደግሞም ኢየሱስ፦ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ ፤ የሚከተለኝ የሕይወት ብርሃን ይኾንለታል እንጂ በጨለማ አይመላለስም ብሎ ተናገራቸው።»
  የዮሐንስ ወንጌል ፰ ፥ ፲፪

  «እናንተ የዓለም ብርሃን ናችኹ።»
   የማቴዎስ ወንጌል ፭ ፥ ፲፬
ሰሜን ጎንደር : በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ
የ10 ሰዎች ሕይዎት አልፏል!

ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ሕይዎት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው የ10 ሰዎች ሕይዎት አልፏል ያሉት የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ናቸው።

ኀላፊው ከአሚኮ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ የአራት ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ብለዋል። የቀሪ ስድስት ሰዎች አስከሬን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሊገኝ አልቻለም ነው ያሉት።

በጉዳቱ በስምንት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ያሉት ኀላፊው በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

በመሬት መንሸራተት አደጋው ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት ሞተዋል። ከ30 ሄክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

እንደ አቶ ተስፋየ መረጃ በደረሰው አደጋ 480 አባውራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። በቀበሌው ማዕከል ወደሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማት በጊዜያዊ እንዲጠለሉ መደረጉንም ኀላፊው ጠቁመዋል።

ኀላፊው አያይዘውም በቀጣይም የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ በተባሉ የኖላ፣ ላጌ፣ ውፋ፣ ኩዳድ እና ጅብ ዋሻ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

አሁን ካለው ከባድ የዝናብ ስርጭት አንጻር ማኅበረሰቡ ከጎርፍ እና መሰል አደጋዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ያሳሰቡት ኀላፊው ለተፈናቃዮች አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA)
« ከዘረኛ በላይ ክፉና ወንድሙን እጅግ የሚጠላ የዲያብሎስ ፈረስ የለም ። ዘረኛ በነገሰበት በየትኛውም የአገራችንም ሆነ የዓለም ሥፍራ ፍቅር ሰላም የተዋህዶ እምነት ምልክታቸውም አይኖርም ።»

🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን፥ ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ መልእክት 8 ገጽ 45 — ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2011ዓ.ም
Forwarded from ቅድስት በርባራ ዘኒቆመዲያ Saint BarBara Αγία Βαρβάρα (ገድላት እና ስንክሳር)
ሰላም ለትንሣኤኪ ዘተበጽአ ዝክሩ፤
እስመ ሰበከ ብርሃነ ለእለ በጽልመት ነበሩ፤
ማርያም አንቲ ለብርሃነ አዜብ መንበሩ፤
ሰላማ ወደሰኪ ዘምስለ ጳጳሳት ማኅበሩ፤
ወደቂቅ ሰብአቱ ሥነ ዚአኪ አፍቀሩ!


🌷አርኬ (ዝክረ ቅዱሳን ርቱዐነ ሃይማኖት)
በአደባባይ ወጥተው ለተቹ ለነቀፉ እንጠይቃለን

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ምስጢረ ክህነት ክቡር ነው። የሰጠው መድኃኒዓለም ነው ብሎ ተቀብሎ የአለቃ አያሌውን ውግዘቱን እውነተኛነት መስክሮ ውግዘቱ ቤተክርስቲያን እንድታከብር ሲተጋ
----------------------------------------------- ሊቅነታቸውን ተቀብሎ ክህነታቸው አይሰራም ብሎ ክህነትን እያራከሰ ያለው ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
መንገስተ ሰማይ በደጅ ናትና ንስሀ ግቡ ብሎ ሲሰብክ
---------------------------------------------------የጌታ መምጫ ገና ነው ብሎ ህዝብን ያዘናጋው ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
መቅሰፍታት ይመጣሉና አትታወኩ በእምነት ካምላካችሁ ይበልጥ ተጣበቁ አትፍሩ አትደንግጡ ተብሎ ሲሰበክ
---------------- ወረርሽኝ ስለገባ ቤተክርስቲያን እንዳትደርሱ፣ እጃችሁን ታጠቡ መርፌ ተወጉ፣በቴክኖሎጂ በቴሌቪዥን ውስጥ አምልኩ ያለው ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
የቤተክርስቲያን ሀብቷ ተዘረፈ፣ ፍርድ ተጓደለ፣ ምእመናን እረኛ አተዋልና ህዝብ ሆይ በቤተክርስቲያንህ በእምነትህ ፅና ሰውን አትመልከት በደልን የሚያይ አምላክ አለ ብሎ ሲያፅናና
----------------------------------------------- ለህዝቡ እኛ ምናደርገውን ተቀበሉ፣ ስራችን ፍፁም ነው። ህዝቡ ቢሰቃይም እግዚአብሔር ያፅናህ ብለናል ለማዳነረ ሞክረን አልተሳካልንም። እያለ መግለጫ ሚያወጣበት ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ቤተክርስቲያን የእግዚአብሔርን ትእዛዛት ባለማክበሯ ጥፋቱ ለሀገር ብሎም ለዓለም ተረፈ እናንተ ግን ፅኑ የእግዚአብሔር የሚከበርበት ቀን ቤተክርስቲያን የምትነሳበት የምትሰማበት ቀን ይመጣል ብሎ ሲያፅናና-
--------------------------------- ቤተክርስቲያን እንድትነሳ አንፈልግም እሷ ብቻ እዚህ አለም ላይ እንድትሆን አንፈልግም ሌሎች ሀይማኖቶችም ይኑሩ ፣ የክርስቶስ ስጋ ወደሙን ህዝብ እንዲቀበል መንግስትን አስፈቅጄ አልተሳካልኝም ብሎ ቤተከክርስቲያንን ያዋረደ ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
አባቶቻችን በመንፈስ ተረድተው እንዳስቀመጡልን፣ የድንግል አስራት ሀገር ናትና የእግዚአብሔርን ህግ የሚያስከብር ንጉሥ ያስነሳል ብሎ በእምነት ሲመሰክር-
----------------------------------------------- ሳልሳዊ ቴዎድሮስ ይነግሳል የሚባል በትውፊት ሰምተናል እኛ ቢነግስ፣ ባይነግስ አይገደንም ዋናው የክርስቶስ መምጣት ነው ብሎ የቤተክርስቲያኗን ትውፊት፣ መፀሐፍ ያቃለለ ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
እውቀት ያለ እምነት ከንቱ ነው የተፃፈልንን በህይወት መተርጎም የምንችለው እርምጃችን ትክክል መሆኑን ምናረጋግጠው፣ እግዚአብሔርን ደስ የምናሰኘው በእምነት ነው ብሎ ሲሰብክ
---------------------------------- እኛን ብቻ ስሙ፣ የምታዩትን ብቻ እመኑ፣ እግዚአብሔርን አትጠይቁ፣ነብያት አያስፈልጉንም የተፃፈው ብቻ በቂያችን ነው የሚለው ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ታቦት የተቀደሰ ነው ቤተክርስቲያን ተሳለሙ፣ ፅዋዕ የአባቶቻችን ነው ከተጣለበት አንሱ ክርስቶስን ልበሱ እየተባለ ሲሰበክ
---------------------------------------------------ፅዋዕ ጣኦት ነው የአይሁድ እምነት ለማራመድም የሚጥሩ አሉ እያለ የሚያጥላላ ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ምስጢረ ሥላሴን ተንትኖ፣ ምስጢረ ሥጋዌን በተዋህዶ የከበረ ብሎ እያስተማረና ከዚህ የወጣውን እያወገዘ ሲሰብክ----------------
ቅባትና ፀጋ ጳጳሳትን በቤተክርስቲያን አክብሮ ያስቀመጠ ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
ቤተክህነት፣ቤተመንግስት፣ቤተህዝብ ዓለም ሁሉ ንስሀ ግቡ ተመለሱ እግዚአብሔርን ስላሳዘንን በቁጣ እንጎበኛለን ብሎ ህዝብን ሲያነቃ-
------------------------------------------
ያሉት ሁሉ እየሆነ ነው ይህ ደሞ የሚሆነው እራሳቸው ዓለምን እያጠፉ ነው እያለ ህዝብ የሚያዘናጋው ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
በመፀሀፍት የተፃፉት፣ በመፀሀፍ ቅዱስም የተቀመጠው የቅድስት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን እምነት ሁሉም ይፈፀማል ብሎ በእምነት ሲሰብክ----------------------------

"ቴ" የሚል ተፅፏል ምን እንደሆነ አይታወቅም፣ የተፃፈው ቢፈፀም ባይፈፀም አይገደንም በማለት አዋልድ መፃህፍትን ያራከሰው ከተዋህዶ ኦርቶዶክር የወጣ አስተምህሮ ያለው ማን ነው?

የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን
እግዚአብሔር ፈራጅ ነውና በፍርድ ሂደቱ ውስጥ ስራችሁን ስሩ፣ሀላፊነት ተወጡ፣ ጠማማችሁን አቅኑ፣ ለሀገራችሁ ተጋደሉ እያለ ሲመክር-
------------------------------------ መልእክታቱ ቁጭብሎ ተመልካች ነው ሚያረጋቸው እያለ ሰዎች ሰርተው ከሚያገኙ የሰረቁትን በማክበር፣ ምእመናን በማህተባቸው ሲሰቃዮ፣ሀገር በደም ስትጨቀይ ዝምታን በመምረጥ ከፊት መሆንን ያልመረጠው ማን ነው?

ህዝቡን ማን ያፅናና ፣ ማን ይሰብስብ በጎቹን፣
ተደፍራ፣ ተንቃ ሰሚ አጥታ ቤተክርስቲያን ፣
ልጆቿን እያየች እየታጠቡ በደም፣
ማንስ ይታደጋት እየተቃጠለች በቁም፣
አጥፊዎች እንዳሉ አለችና እውነት፣
ትሻለችና ፅኑ ፈትኖ ሚረዳት ፣
አስተዋይ እንሁን እንመርምር ሁሉንም፣
በእምነት ሳንፀና ሰብስቦ አያድነንም።


ለብዙ ዘመናት ዛሬም ድረስ ህዝቡን ወደ ንስሀ የመለሰ፣ ያፅናና መንገድ ያመላከተ የእግዚአብሔር ድምፅ የሚሰማበት በዚ ጨለማ ጭላንጭል ብርሃን ያየንበት የእውነተኛ እረኛ ድምፅ የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃንነትን የሚመሰክረው መልእክት ነው!!

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ሃይማኖት አይደለም መልእክት እንጂ

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ማሕበር አይደለም ቢሮ፣ ማህተም የለውም የተዋህዶ ኦርቶዶክስ የእውነተኞች አማኞች ቤተሰብ እንጂ

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት በቅርብ እውን የሚሆን በየቤቱ ሳይሆን ለዓለም ሁሉ በገሀድ የሚገለጥ የእግዚአብሔር እውነት ነው!!

ይህን ለማየት ልዑል እግዚአብሔር ይህን ጥፋት ያሻግረን ፣ድንግል እናታችን ታማልደን፣ ቅዱሳን መላእክት ይራዱን
ሥርዐተ_ቤተ_ክርስቲያንን_የሻረው_ሕግ_ክፍል_፩
<unknown>
#_ትእዛዜን_ጠብቁ

📣 አባታችን
#አለቃ_አያሌው_ታምሩ ፥ ከአባ አፈወርቅ ጋር በ፲፱፻፺፩ ዓ.ም ያስተማሩት_ክፍል ፩ ፦

🔸 "ተሞላቀቁ" አላለም

🔸 ከሰይጣን ጋር ያልተቋረጠው ትግልና መከራ

@Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
ሥርዐተ_ቤተ_ክርስቲያንን_የሻረው_ሕግ_ክፍል_፪
<unknown>
#_ግዝት_ቀልድ_አይደለም

📣 አባታችን
#አለቃ_አያሌው_ታምሩ ፥ ከአባ አፈወርቅ ጋር በ፲፱፻፺፩ ዓ.ም ያስተማሩት_ክፍል ፪ ፦

🔸 ኢትዮጵያ እንዲኽ ብለሻልና እነዚኽ ሦስቱ ይጠብቁሻል !

🔸 አባ ጳውሎስ እንዴት ቤ/ክንን አፈረሷት?

🔸 መልአክ በጭራፍ የገረፋቸው ኤጲስ ቆጶሳት

🔸 ሕዝቡን ስለሚያሰናክሉ "ባህታውያን" ተብዬዎች ( እኚኽ ባህታዊ አኹንም (በ2013ዓ.ም) ድረስ 'ንጉሡ በከተማ አለ' እያሉ ለመንግሥት እያወናበዱ አሉ)

@Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
ሥርዐተ_ቤተ_ክርስቲያንን_የሻረው_ሕግ_ክፍል ፫
<unknown>
#_ሥልጣነ_ክህነት_አንድ_ነው

📣 አባታችን
#አለቃ_አያሌው_ታምሩ ፥ ከአባ አፈወርቅ ጋር በ፲፱፻፺፩ ዓ.ም ያስተማሩት_ክፍል ፫ ፦

🔸 የቤ/ክንን ሕመም ዝም ብለን እያየን ነው፤ አልጠየቅንም 😔

🔸 እኔ ቤ/ክን አትግቡ፤ አትሳለሙ አላልኩም።

🔸 አባ አፈወርቅ፦የመጀመርያው የአለቃ አያሌው ተቃዋሚ

🔸 ሠራተኛ፥ አባት፥ ዓይን፥ ጠበቃ ጨምርልን ብላችሁ ለምኑ

@Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
እስካሁን በአደጋው የ23 ሰዎች ህይወት አልፏል

በ1 ሺ 775 ሄክታር ላይ የተዘራ ሰብል ወድሟል

48 መኖሪያ ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል ፤

2ሺህ 700 ነዋሪዎችም ከቀያቸው ተፈናቅለዋል ፤

አካባቢው በተደጋጋሚ ድርቅ ደርሶባቸው የቆዩ በመሆናቸው በመላ አገሪቱ የሚገኙ ዜጎች የእርዳታ እጃቸውን እንዲዘረጉ ጥሪ ቀርቧል።

20/12/2016
2024/09/29 14:22:18
Back to Top
HTML Embed Code: