Telegram Web Link
#ነሐሴ_7
ሰላም ለኪ የምትለዋለን የዘወትር ጸሎት የደረሱት ጻድቁ
#ዓፄ_ናዖድ ዕረፍታቸው ነው።

ሃገራችን ኢትዮጵያ ምስፍና ከክህነት፣ ንግሥናን ከጽድቅ ያጣመሩ ብዙ መሪዎች ነበሯት። ከእነዚህ አንዱ ደግሞ ዓፄ ናዖድ ናቸው።

ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 እስከ 1499 ዓ.ም ሲሆን ለእመቤታችን በነበራቸው ልዩ ፍቅር ይታወቃሉ። ካህን እንደ ነበሩም ይነገራል።

ዛሬ ሁላችን የምንወዳትን ጸሎት (ሰላም ለኪ፣ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ . . .) የደረሷት እርሳቸው ናቸው። ትልቁን መልክአ ማርያምም ደርሰዋል። ይህ መልክእ ጣዕሙ ልዩ ነው።

የጻድቁ ንጉሥ ሚስት (ማርያም ክብራ)፣ ልጆቻቸው (አፄ ልብነ ድንግልና ቡርክት ሮማነ ወርቅ) እጅግ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩ።

ንጉሡ አፄ ናዖድ ከባለሟልነት የተነሣ ድንግል ማርያምን "እመቤቴ ስምንተኛው ሺ መቼ ይገባል? ጊዜውስ እንዴት ያለ ነው?" አሏት።

እመ ብርሃንም በአካል ተገልጻ የዘመኑንና የሰውን ክፋት ነገረቻቸው። ንጉሡም አዝነው "እመቤቴ! ከዛ ዘመን አታድርሺኝ" አሏት።

በዚህ ምክንያት የስምንተኛው ሺህ ዘመን መስከረም 1 በ1500 ዓ.ም ሊገባ እርሳቸው ነሐሴ 7 ቀን በ1499 ዓ.ም ዐርፈዋል።


🌹🌹
T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ነሐሴ 8 | ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ ዕረፍታቸው ነው።

አቡነ ኂሩተ አምላክ ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው።

እርሳቸውም የዓፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው። ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኩስናን ተምረዋል።

ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው።

አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ።

ሁለት ድንጋዮችንም በተአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል።

እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ « ዓቃቤ ሰዓት » እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል።

የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ።

አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ ፰(8) ቀን በክብር ዐርፈዋል።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
⭕️የአባ ጳውሎስ ገድል - በእግዚአብሔር ፈንታ ራሳቸውን የተኩ አመፀኛው ፓትርያርክ
ገነት በዐፀደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን ከፈረሳቸው ወርደው ለእመቤታችን እንደሰገዱላት (የበዓለ ደብረ ምጥማቅ ሥዕል)
"እውነትና ንጋት....!"

#ለታሪክ_ትቀመጥ!

ነሐሴ 8/2016
`
✥ ◦ ✥ ◦ ✥
#_ማ_ስ_ታ_ወ_ሻ
| ምእመናን ተጠያቂ ናቸው! |
◦ ◦ ◦
ወገኖቼ፥ በአሁኑ ጊዜ ይሄ በዓይናችሁ የምታዩት ድርጊት ነው።

በቤ/ክ የሚሾሙ ሰዎች በሙሉ፣ ሹመቱንም የሚያጸድቁት ካህናት እላይ ያሉት ሥራ ፈልገው ለመቀጠር በቤ/ክ አገልግሎት ለመቀጠር የሚመጡ ኹሉ ጉቦ ከፍለው እንጂ ጉቦ ሳይከፍሉ በምንም ተአምር በእውቀታቸው፣ በመንፈሳዊ ብቃታቸው ተለክተው ታይተው ሥራ አያገኙም። በቤ/ክ አገልግሎት ውስጥ አይመደቡም።

ለዘበኝነት መቀጠር ታሪፍ ወጥቶለታል እኮ ወገኖቼ! ለዘበኝነት፣ ለዲያቆን አገልግሎት፣ ለክህነት፣ በአስተዳዳሪነት በየደረጃው ለመሾም የገንዘብ የጉቦ መጠን ደረጃ ወጥቶለታል። በግልጽ በይፋ በቤተ ክህነቱ ውስጥ ይሄ የሚከናወን ሥራ ነው።

አንድ ዘበኛ 80ሺህ፣ 70ሺህ፣ 60ሺህ ይጠየቃል። እንደ ቤ/ክኗ ገቢ ማመንጨት። ቤ/ክኗ ሰፊ ገበያ ካላት እዛ ለመቀጠር ደመወዙም ከፍ ስለሚል ጉቦውም ከፍ ያለ ነው። ዲያቆንም ኾኖ እዚያ ለመቀጠር እንደዚያው ጉቦ ከ100ሺህ በላይ 200ሺህ 300ሺህ ሊኾን ይችላል። እንደገቢው፤ ወይ 10ሺህ ደመወዝ ይኖረዋል ወይ ከዚያም በላይ ሊኖረው ይችላል።

አስተዳዳሪማ እንግዲያው አስቡት! ግማሽ ሚልዮን ሚሊዮንም ሊከፍል ይቻላል። በጣም ቁልፍ የኾኑ ቦታዎች ላይ ካሉ ደሞ ከሚልዮን በላይ ቁጥሩ እንዲህ ነው አይባልም እንግዲህ ይሄ ኹሉ ተደልድሎ ተቀምጧል። በዚህ ነው አሁን ሥራ የሚካኼደው። የቤ/ክ አገልጋይ ተብለው ዛሬ በየቦታው የተሰማሩት ኹሉ እነዚኽ ናቸው።

ወገኖቼ፥ ልብ በሉ! አሁን ጨርሶ በሐሰት ሰነድ፥ የሐሰት ሰነድ እየተዘጋጀ በዚሁ ጉቦ መሠረት ምንም ከቤ/ክ አገልግሎት ጋር ከእምነቱ ጋር ትውውቅ የሌላቸው ሰዎች በጉቦ ቀጥታ እየተቀጠሩ እዛ ውስጥ የሚፈጸሙ አገልግሎቶችን ቅዳሴውንም ምኑንም ኹሉንም ነገር ያጠናሉ። ካሴት ላይ ቀርጸው እያጠኑ ተመሳስለው ይጓዛሉ።

አንዳንዱ ምንም የማያውቅ የፖለቲካ ሹመኛው ደግሞ፥ የራሱ ደመወዙ ከፍተኛ ከኾነ ወይ አስተዳዳሪ ይኾናል ወይ 40ሺህ 30ሺህ ይኾናል ደመወዙ፥ የሚያውቅ በቅዳሴ ላይ የሚቆምለት፥ በሰዓታቱም በኪዳኑም በተራው ሰዓት ለሚቆምለት ካህን ለሚያውቅ ካህን ደመወዝ ከራሱ ላይ ቆርጦ እየሰጠ ያ እየሔደ አገልግሎት እየሰጠ እሱ ከፍተኛውን ደመወዝ ይበላል። ሌላውን ሥራውን ደሞ ይሠራል። ይሄም ሰው ካህን ነው። ይሄም ሰው ቤ/ክ አስተዳዳሪ ነው።

ቤ/ክ እንዲህ ነበረች ስታውቋት?! ቤ/ክ በአባቶቻችን ዘንድ በቀደምው ዘመን እንዲህ ነበረች?! ሕጉን መቀየሩን ተውቱ እርሱን ጨርሶ አብቅቷል፤ የመናፍቅ ቤት አድርገዋል፤ የካቶሊክ አድርገዋል።

እንደገና ለማስመሰሉም እኮ፥ አስመስሎ ለመጓዙም እኮ የማያውቀውን ምንም እውቀት የሌለውን እምነቱም የሌለውን አምጥተው ገንዘብ እየኮለኮሉ ነው። ማንን ፈርተው?

የዚህ ኹሉ ተጠያቂ ምእመኑ ነው። የዚህ ኹሉ ተጠያቂ አሁንም አብሮ ከእነርሱ ጋር የሚጓዘው ምእመን ነው። በቅርብ ፍርድኽን ታገኛለህ ኹሉህም! እግዚአብሔር ፍርዱን ከቤ/ክ ነው የሚጀምረው! ከቤ/ክናችን ውስጥ ይጀምራል! ጽዳቱ ከዚያ ይጀምራል!
▬ ▭ ▬
🇨🇬 | የኢ.ዓ.ብ የሉቃስ ወንጌል ትምህርት ፭ | 🇨🇬
| 🕛 ▸ ከ 13፡10 - 17፡35 |

www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
🙋 ጥያቄ 2) "ኢትዮጵ" ማለት የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም ምን ማለት ነው?

(ጥያቄውን ከመለሱ በኋላ የመልሱን መጠነኛ ማብራሪያ ከጥያቄው ጠርዝ ላይ 💡ምልክት ጠቅ አድርገው ይመልከቱ!)
ኢትኤል (ኢትዮጵ) ማነው? በአጭሩ፦

ኢትኤል የመጀመሪያ መጠሪያ

ኢትዮጵ በእግዚአብሔር የተቀየረ መጠሪያ

ኢትኤል ማለት የእግዚአብሔር ስጦታ ማለት ሲሆን በአምላክ የተቀየረው መጠሪያ ኢትዮጵ ማለት የወርቅ ስጦታ ማለት ነው። (ኢትዮጵያን ያህል ምድር ርስት ተሰጥቶት በስሙ ስትሰየምለት እውነትም በእግርጥ ከወርቅ የበለጠ ስጦታ ከአምላኩ ተቀብሏል!)

አባቱ፦ ታላቁ መልከጼዴቅ
እናቱ፦ የቴድአል ልጅ ሲና

በእግዚአብሔር የታዘዘለት ምድር፦ "ግዮን በሚፈስበት ምድር ትኖራለህ፤ ስምህም
#ኢትዮጵ ትባላለህ!"

አብራም (አብርሃም) በኢትዮጵ አባት መልከጼዴቅ ሲባረክ የሰጠውን አስራት ይኸውም እንቆአርያውን አንድ መደብ ፤ ሕብስት የያዘ የወርቅ መሶብ፤ ወይን የያዘ የወርቅ ገንቦ አንድ መደብ አድርገው 3 ቦታ መድበው ለሶስት ማለትም (አባት መልከጼዴቅ ልጆች ሃሙራቢና ኢትኤል) እጣ ቢጣጣሉ እንቆአርያው ለኢትኤል ፤ የወርቅ መሶቡ ለአባታቸው ለመልከጼዴቅ ፤ የወርቅ ገንቦው ደግሞ ለሃሙራቢ ደረሰ።

መልከጼዴቅም ትንቢት ተናገረ እንዲህም አለ፦ "አንተ የግዮን ውሃ የምትጠጣ እንቆአርያ የደረሰህ የያዝከውን እንቆአርያ ከምድር ከምታገኘው ሉልና የከበረውን ዮጵ እንቁ ከወርቅ ሃመልማል ጋር ይዘህ መጥተህ ለአምላክህ ለጌታህ ጋዳ አቅርብለት። ከርቤና እጣን አምጥተህ አጢስለት፡ በፊቱም ስገድለት፤ ይሄም የምትሰግድለት ሰው የሰላምና የደህንነት ንጉሥ ነው" አለው። በዚህም ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተወለደ ጊዜ ቀድሞ ምልክቱ እንደተነገረው በልጆቹ የታዘዘውን ፈጽሟል። ርስት ምድሩም ግዮን የሚፈስበት ምድር እንደሆነ ከአባቱ ቃልን ተቀብሎ አባቱ መልከጼዴቅ እንዳዘዘው ልጆቹንና ሚስቱን (ወደኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ንቅዮጵ - ንቅዮጳግዮን ተብላለች) ይዞ ወደግዮን ምድር መጥቷል። ኢትኤል መባሉም ቀርቶ ዮጵ በተባለው ወርቅና በእንቁ ድንጋዮች በምድርም በረከት ስለበለጸገ ኢትዮጵ ተብሏል። ምድሪቱንም በስሙ ኢትዮጵያ ብሎ ጠርቷታል።

በርስቱ ምድርም ሲኖር የተድአልን ልጅ እንቅዮጵን አግብቶ 10 ወንዶችንና 3 ሴቶችን ወልዷል።

ስለ ታላቁ ኢትዮጵ ብዙ ማለት ቢቻልም ለመነሻ ያኽል ያገኘነውን በጥቂቱ አቅርበናል።
#Alert🚨

ከተ.መ.ድ የጤና ኤጀንሲ እንደተገኘው መረጃ በቅርቡ ኤምፖክስ (Mpox) ለመጀመሪያ ጊዜ በ4 የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ፦
- በጎረቤታችን ኬንያ ፣
- በቡሩንዲ ፣
- በሩዋንዳ
- በኡጋንዳ ተገኝቷል። ሀገራቱም ሪፖርት አድርገዋል። በነዚህ ሀገራት ውስጥ የታየው በሽታ በኮንጎ ካለው ጋር የተገናኘ ነው።

የዝንጀሮ ፈንጣጣ ወይም Mpox በሽታ የሚከሰተው በቫይረስ አማካኝነት ነው።

ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል። በወሲባዊ ግንኙነት ፣ በቆዳ ንክኪ ፣ በቅርብ ርቀት ሆኖ ማውራት/ መተንፈስ ፣ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ባለ የቅርብ ግንኙነት ይተላለፋል።

አሁን ላይ #ዋነኛዎቹ ናቸው የሚባሉት ሁለቱ የቫይረሱ ዝርያዎች Clade 1 - በማእከላዊ አፍሪካ ውስጥ ያለ ፤  Clade 1b - እጅግ በጣም አደገኛ የሆነው አዲስ የቫይረሱ ዝርያ ነው።
🟥🟥🟥🟥🟥
''-በሽታዎች እጅግ አደገኛ በሆኑ ቫይረሶች እየፈሉ ይመጣሉ። በሚሊዮኖች የሚቆጠሩትን የአዳም ዘር ምልእክት አልባ የሆኑትን ሁሉ ያጠፋሉ
📌 ኢትዮጵያ  የዓለም ብርሃን መልእክት 5 ገጽ  17
Audio
መልክአ አቡነ መዝገበ ሥላሴ
Audio
ጸሎተ አቡነ እስትንፋሰ ክርስቶስ
ተገደሉ‼️

በአርሲ አንድ ካህንን ጨምሮ አጠቃላይ 6 የሚደርሱ ሰዎች በታጣቂዎች መገደላቸው ተገለፀ‼️

በአርሲ ሀገረ ስብከት አሰኮ ወረዳ ጢዮ ቀበሌ ጠለታ ጨፋ ከተማ የጠለታ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ካህንን ጨምሮ 6 ኦርቶዶክሳውያን በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች መገደላቸው ታውቋል።

ግድያው የተፈጸመው ከነሐሴ 7 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ሲሆን ከሞቱት በተጨማሪም 3 ሰዎች ከባድ ጥቃት ደርሶባቸው በህክምና ላይ እንደሚገኙ ከአካባቢው የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

በታጣቂዎቹ የተገደሉትን ሰዎች አስከሬናቸውን ለማንሳትና ለመቅበር አስቸጋሪ በመሆኑ ከቤተክርስቲያኑ ራቅ ወዳለ ቦታ በመውሰድ የቀብር ሥርዓቱን ለመፈፀም ተገደዋል።

በተለያየ መንገድ ቤተ ክርስቲያንን ሲረዱ የነበሩ ኦርቶዶክሳውያን ተለይተው ሀብት ንብረታቸው መቃጠሉንና የአካባቢው ምእመናንም ቤታቸውን ትተው በዱር በስጋት ውስጥ ናቸው ብለዋል፡፡
2024/09/24 12:23:02
Back to Top
HTML Embed Code: