Telegram Web Link
በብራዚል 58 መንገደኞችንና 4 የበረራ ሰራተኞችን አሳፍሮ የነበረ አውሮፕላን ተከስክሶ የሁሉም ህይወት አልፏል።

አውሮፕላኑ ንብረትነቱ የቫፖስ ሲሆን የተከሰከሰው በሳኦፖሎ ግዛት ነው።

ከካስካቬል ወደ ሳኦፖሎ ከተማ ወደሚገኝ ዋናው ኤርፖርት ሲበር ነበር።

አውሮፕላኑ ' ቪንሄዶ ' የተባለ ከተማ ላይ ሲደርስ በቪድዮው እንደሚታየው ከላይ ወደታች ወርዶ ተከስክሷል።

በዚህም አንድም የተረፈ ሰው የለም።

የአደጋው መንስኤ ለጊዜው አልታወቀም
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ፅዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

በ 5/12/2016 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት ይለቀቃል 👇👇👇
ወለተ ማርያም ከአሰላ.amr
781 KB
የእህታችን ወለተ ማርያም እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አሰላ
5/12/2016
ክፍል = ፩

👉 ወደ ፈጣሪያቸው የተመለሱ የኢትዮጵያ ዓለም ብርሃንን ምክር ድምጽ
የሰሙና የተገበሩት ፤ ሁሉም ቅዱሳን ሊቃነ መላእክት ድንግልም ሁሉም ሰማእታት ቅዱሳን ወዳጆቻቸውን በሥላሴ ፊት
አቅርበው ማልደው ለታመኑባቸው ለወደዷቸው ሁሉ ምህረትን አስገኝተዋል ፡፡ በዚህም መሰረት ለወዳጆቻቸው
በየግንባራቸው ላይ ምልክት ተደርጓል ፡፡

👉 የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አስር ገፅ 30 የተወሰደ
ወለተ ማርያም ከአሰላ .amr
561.1 KB
የእህታችን ወለተ ማርያም እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አሰላ
5/12/2016
ክፍል =፪

👉 ዛሬ ኢትዮጵያ እንደ ሥጋው እይታ ድሃ ናት። እንደመንፈሳዊው ግን ባለጸጋ ናት። ያዕቆብ አባታችን
በእምነት ጉዞው በቤተል የገጠመው ምን እንደሆነ በትምህርታችን ወቅት ገልፀንላችኋል። መሰላል ከምድር
ወደሰማይ ተዘርግቶ ቅዱሳን መላእክት ሲወጡበት ሲወርዱበት በአናቱም ልዑል ተቀምጦበት ነበር ያየው።
እጅግ በመደነቁ ይህ ቦታ እጅግ የተከበረ የእግዚአብሔር ስፍራ ነው በማለት የድንጋይ ሃውልት አቁሞ ዘይት
ቀብቶ አፍስሶበት ነበር፣ ወደእናቱ ወገኖች የተሰደደው። በቦታው እግዚአብሔር በግልጽ ነበር ለአብርሃም
የገባውን ቃል ከሱም ጋር እንደሚያጸና የነገረው! ሲመለስም 20 ዓመታትን በአጎቱ ቤት ሲያሳልፍ እግዚአብሔር
አልተለየውም ነበር። ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር ተመልሰህ ወደአባትና እናትህ ሂድ ስላለው ቃሉን
በመጠበቅ ወደዚያው ሲጓዝ በቤተል ድጋሚ እግዚአብሔር ተገልጦለት ቃሉን እንደሚያጸና! ለአብርሃም
ለይስሐቅ የገባውን ቃል ከሱም ጋር እንደሚያጸና አረጋግጦለታል።

👉 የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት ዘጠኝ ገፅ 32 የተወሰደ
ወለተማርያም ከአሰላ.amr
1.4 MB
የእህታችን ወለተ ማርያም እጅግ ድንቅ ምስክርነት
ከቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ = አሰላ
5/12/2016
ክፍል = ፫

👉 በቃ ከእንግዲህ የእግዚአብሔር ቁጣ በልጆች
እግር ስር በመጀመሪያ ኢትዮጵያና አካባቢዋን አስከትሎም መላውን ዓለም እስኪጥልና እስኪያስገዛ ድረስ
የሚቆም የሚዘገይ ወይም የሚታቀብ ነገር የለም። ከዚህ በታች የሚገለጹት እርምጃዎች በሙሉ ያለውን
የነበረውን የሚገሰግሰውንም እርምጃ ኢላማቸው በይበልጥ የሚያተኩርበትን ለማረጋገጥ ታስቦ የተዘረዘረ ነው።
እንደተጨማሪ ማጠናከሪያ መሆኑን ለማሳወቅም ነው።

👉 የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት ስምንት ገፅ 43 የተወሰደ
🙋 ጥያቄ 2) "ኢትዮጵ" ማለት የቃሉ ቀጥተኛ ትርጉም ምን ማለት ነው?

(ጥያቄውን ከመለሱ በኋላ የመልሱን መጠነኛ ማብራሪያ ከጥያቄው ጠርዝ ላይ 💡ምልክት ጠቅ አድርገው ይመልከቱ!)
Anonymous Quiz
43%
❶) "የአምላክ ስጦታ"
9%
❷) "የአምላክ ብርሃን"
46%
❸) "የወርቅ ስጦታ"
2%
❹) "የወይን ስጦታ"
"ሕዝቡም ከጭንቁ የተነሳ ዓይኑ እያየው ቤቱ ንብረቱ ስለሚፈርስ፤ ሞትን አይፈራም። ስለሆነም በመንግሥትም ሆነ በሚታመንበት ኃይል ላይ ዘምቶ መተላለቅ ይሰፍናል።"

👉 ከኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልዕክት አምስት ገፅ 38 የተወሰደ። መስከረም 21/2004 ዓ.ም።
🟢🟡🔴
ነሐሴ 6 | መድኃኔዓለም ከኹሉ አስቀድሞ ትንሣኤውን የገለጠላት #ቅድስት_ማርያም_መግደላዊት ዕረፍቷ ነው።

ይህችን ቅድስት "ማርያም" ያሏት ወላጆቿ ሲሆኑ "መግደላዊት" እያሉ የጠሯት ደግሞ ሐዋርያት ናቸው።

ለምን እንዲህ ብለው ጠሯት ቢሉ፦ በዘመኑ "ማርያም" የሚባሉ ብዙ ሴቶች ነበሩና ከእነሱ ለመለየት ነው። አንድም ሃገሯ ከእሥራኤል አውራጃዎች በአንዱ (በመግደሎን አውራጃ) ተወልዳ ያደገች ናትና።

ማርያም መግደላዊት ይህ ቀረሽ የማይሏት ቆንጆ ነበረችና ሰዎች ያደንቋት፣ ወንዶች ይከተሏት ነበር። በዚህም 7 አጋንንት ተጠግተው 7 ዓይነት ኃጢአትን ያሠሯት ነበር። በተለይ ደግሞ በዝሙት፣ በትውዝፍት (ምንዝር ጌጥ) እና ትዕቢት በእጅጉ የታወቀች ነበረች።

በዚያ ወራት የክብር ባለቤት #ጌታችን_ኢየሱስ_ክርስቶስ ሥጋችንን ተዋሕዶ ያስተምር ነበርና "ጌታ ኃጥአንን አይጸየፍም። አጋንንትንም ያስወጣል" ብለውም ነገሯት።

ወደ እርሱ ብትሔድ ኩላሊትን የሚመረምር አምላክ ነውና አቀረባት። በቸርነቱም ከራስ ጸጉሯ እስከ እግር ጥፍሯ የሞሉትን 7 የአጋንንት ነገድ አስወጣላት። ከ36ቱ ቅዱሳት አንስት አንዷ ትሆን ዘንድ መርጦ ተከታዩ አደረጋት።

ቅድስት ማርያም መግደላዊት ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ለ40 ቀን #መጽሐፈ_ኪዳንን#ትምህርተ_ኅቡዓትን ተምራለች።

እናታችን #ማርያም_መግደላዊት በስብከተ ወንጌልም የተመሰከረላት ነበረች። የመጀመሪያዋ የሐዲስ ኪዳን #ዲያቆናዊት ሴት ስትሆን ክርስትናንም ተዟዙራ ሰብካለች።

ስለ ቅዱስ ስሙም ሽሙጥን፣ ስድብን፣ መንገላታትን እና ግርፋትን ታግሣለች። በተለይ አይሁድ ብዙ አሰቃይተዋታል።


🍀 በየዓመቱ ነሐሴ ፮ ቀን ሶሀባ በሚባለው ቦታ ቆመው በጸለዩበት ወንዝ ላይ ዓሣ ከሰማይ የሚዘንምላቸው መናኔ መንግሥት #አቡነ_ኢዮስያስ ዕረፍታቸው ነው።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
#ነሐሴ_7
ሰላም ለኪ የምትለዋለን የዘወትር ጸሎት የደረሱት ጻድቁ
#ዓፄ_ናዖድ ዕረፍታቸው ነው።

ሃገራችን ኢትዮጵያ ምስፍና ከክህነት፣ ንግሥናን ከጽድቅ ያጣመሩ ብዙ መሪዎች ነበሯት። ከእነዚህ አንዱ ደግሞ ዓፄ ናዖድ ናቸው።

ጻድቁ ንጉሥ የነገሡት ከ1487 እስከ 1499 ዓ.ም ሲሆን ለእመቤታችን በነበራቸው ልዩ ፍቅር ይታወቃሉ። ካህን እንደ ነበሩም ይነገራል።

ዛሬ ሁላችን የምንወዳትን ጸሎት (ሰላም ለኪ፣ እንዘ ንሰግድ ንብለኪ . . .) የደረሷት እርሳቸው ናቸው። ትልቁን መልክአ ማርያምም ደርሰዋል። ይህ መልክእ ጣዕሙ ልዩ ነው።

የጻድቁ ንጉሥ ሚስት (ማርያም ክብራ)፣ ልጆቻቸው (አፄ ልብነ ድንግልና ቡርክት ሮማነ ወርቅ) እጅግ መልካም ክርስቲያኖች ነበሩ።

ንጉሡ አፄ ናዖድ ከባለሟልነት የተነሣ ድንግል ማርያምን "እመቤቴ ስምንተኛው ሺ መቼ ይገባል? ጊዜውስ እንዴት ያለ ነው?" አሏት።

እመ ብርሃንም በአካል ተገልጻ የዘመኑንና የሰውን ክፋት ነገረቻቸው። ንጉሡም አዝነው "እመቤቴ! ከዛ ዘመን አታድርሺኝ" አሏት።

በዚህ ምክንያት የስምንተኛው ሺህ ዘመን መስከረም 1 በ1500 ዓ.ም ሊገባ እርሳቸው ነሐሴ 7 ቀን በ1499 ዓ.ም ዐርፈዋል።


🌹🌹
T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ነሐሴ 8 | ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_ኂሩተ_አምላክ ዕረፍታቸው ነው።

አቡነ ኂሩተ አምላክ ሰባቱ ከዋክብት ከተባሉት ቅዱሳን አንዱ አቡነ ኂሩተ አምላክ ሲሆኑ እሳቸውም ታላቁን ገዳም ዳጋ እስጢፋኖስን የመሠረቱት ናቸው።

እርሳቸውም የዓፄ ይኩኖ አምላክ የወንድም ልጅ ናቸው። ከደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለሃይማኖት ጋር ሆነው በሐይቅ እስጢፋኖስ ገዳም ከአባ ኢየሱስ ሞዐ ሥርዓተ ምንኩስናን ተምረዋል።

ንጉሡ አቡነ ተክለ ሃይማኖትን ለመላዋ ኢትዮጵያ ሊቀ ካህናት፣ አቡነ ኂሩተ አምላክን ደግሞ ዓቃቤ ሰዓት አድርገው ሾሟቸው።

አቡነ ኂሩተ አምላክም በዓቃቤ ሰዓትነት ለጥቂት ጊዜ ካገለገሉ በኋላ በዓለም በመንግሥት ተቀምጦ ከማገልገል ይልቅ ከከተማ ወጥቶ ከሰው ተለይቶ እግዚአብሔርን ማገልግል ይበልጣል በማለት የተቀበሉትን መዓርገ ሢመት ንቀው በመተው አልባሌ መስለው ታቦተ እስጢፋኖስን ከሐይቅ ይዘው መልአክ እየመራቸው ወደ ጣና ባሕር ዳርቻ ደረሱ።

ሁለት ድንጋዮችንም በተአምራት እንደ ታንኳ አድርገው በመጠቀም ባሕሩን በበትረ መስቀላቸው እየቀዘፉ ዳጋ ወደተባለው ደሴት ገብተው ጥቂት ዕረፍትን አድርገዋል።

እሳቸው ያን ጊዜ ያረፉበት ቦታ ዛሬም ድረስ « ዓቃቤ ሰዓት » እየተባለ በመዓርግ ስማቸው ይጠራል።

የጣናን ባሕር እንደ ታንኳ ተጠቅመው የተሻገሩባቸው እነዚያ ሁለት ትላልቅ ድንጋዮችም ዛሬ በገዳሙ ውስጥ የጻድቃን ማረፊያ (ምዕራፈ ጻድቃን) ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ በክብር ተቀምጠው ይገኛሉ።

አቡነ ኂሩተ አምላክ በቦታው ላይ ሥርዓቱን አጽንተው ተጋድሎአቸውን ጨርሰው ነሐሴ ፰(8) ቀን በክብር ዐርፈዋል።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
⭕️የአባ ጳውሎስ ገድል - በእግዚአብሔር ፈንታ ራሳቸውን የተኩ አመፀኛው ፓትርያርክ
ገነት በዐፀደ ነፍስ ያሉ ቅዱሳን ከፈረሳቸው ወርደው ለእመቤታችን እንደሰገዱላት (የበዓለ ደብረ ምጥማቅ ሥዕል)
"እውነትና ንጋት....!"

#ለታሪክ_ትቀመጥ!

ነሐሴ 8/2016
2024/09/29 06:25:18
Back to Top
HTML Embed Code: