Telegram Web Link
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
🌹🌹🌹

በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች እመቤታችን ማርያም ሰኔ 21 ቀን ያደረገችው ተአምር ይኽ ነው፨
▰ ▰ ▰

በቂሣርያው ሊቀ ጳጳሳት በባስልዮስ ዘመን እንዲህ ሆነ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም ቤተ ክርስቲያን በሠራ ጊዜ በውስጡ የእመቤታችን የማርያምን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ሠሌዳ ፈለገ ሰዎችም በአንድ ባለጸጋ ዘንድ ስለ አለ አንድ መልካም ሠሌዳ ነገሩት።

ቅዱስ ባስልዮስም ሠሌዳውን እንዲሰጠው ወደ ባለጸጋው ላከ ባለጸጋውም ይህ ሠሌዳ ለልጆቼ ነው አለ እንጂ ፈቃደኛ አልሆነም።

ከዚያም አልፎ በመድፈር በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን ላይ የስድብ ቃል ተናገረ። ወዲያውኑም በድንገት ወድቆ ሞተ። ልጆቹም ፈሩ። ያንንም ሠሌዳ ከብዙ ወርቅና እንቊ ጋራ ወደ ቅዱስ ባስልዮስ አምጥተው የአባታቸውን በደል ያቃልልለት ዘንድ ለመኑት።

ቅዱስ ባስልዮስም ያንን ሠሌዳ ወስዶ የእመቤታችንን ሥዕል ይሥልበት ዘንድ ለሠዓሊ ሰጠው። እመቤታችንም ቅድስት ድንግል ማርያም በሌሊት ራእይ ለቅዱስ ባስልዮስ ተገለጸችለት። ሥዕሏንም በዚያ ሠሌዳ ላይ እንዳይሥል ከለከለችው። ከዐመፀኛ ሰው እጅ ወስዶታልና።

እጅግም ያማረ የእመቤታችን ሥዕሏ የተሣለበት የሁለት ደናግልም ሥዕል ያንዲቱ በቀኝ ያንዲቱ በግራ ሆኖ የተሣለበት ቀይ ሠሌዳ ያለበትን ቦታ ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ወደ አመለከተችው ወደዚያ ቦታ ሔደ። ያንንም ሠሌዳ አገኘው። ወደዚያች ቤተ ክርስቲያንም በታላቅ ደስታ አመጣው።

ከዚህም በኋላ ዳግመኛ በአንድ ጣዖት ቤት ሁለት ምሰሶዎች እንዳሉ አስረዳችው። እነርሱንም አምጥቶ በመቅደሱ ፊት ለፊት እንዲአቆማቸው በላያቸውም ሥዕሏን እንዲያኖር አዘዘችው።

ቅዱስ ባስልዮስም እነዚያን ምሰሶዎች ያመጣቸው ዘንድ ሔደ መሠርያኑም ሊከለክሉት ፈለጉ። ጌታችንም ኃይላቸውን ደመሰሰ። እነዚያንም ምሰሶዎች አምጥቶ በቤተ መቅደሱ ፊት ለፊት አቆማቸው። በላያቸውም የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕሏን አስቀመጠ። እግዚአብሔርም ከእነዚያ ምሰሶዎች በታች የውኃ ምንጭ አፈለቀ በውስጧም የሚታጠብ ሁሉ ከአለበት ደዌ ሁሉ የሚድን ሆነ።

እንዲሁም ከእመቤታችን ማርያም ሥዕል በሽተኞችን ሁሉ የሚፈውስ የዘይት ቅባት ፈሰሰ። ይህ ሁሉ የሆነ የእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ቤተ ክርስቲያን በከበረችበት በሰኔ ወር በሃያ አንድ ቀን ነው።

በዚያችም ቀን እንዲህ ሆነ። አንዲት ሴት መጥታ ታጠበች። ወዲያውኑም ሁለመናዋ በለምጽ ተሸፈነ። ቅዱስ ባስልዮስም ወደርሱ አስቀርቦ በእርሷ ላይ የሆነውን ጠየቃት። እርሷም የእኅቷን ባል እንደወደደችና እኅቷን በመርዝ ገድላ እንዳገባችው ነገረችው።

ቅዱስ ባስልዮስም ታላላቅ ሦስት ኃጢአቶችን ሠራሽ ግን ወደ እግዚአብሔር ንስሐ ግቢ ምንአልባት በደልሽን ይቅር ይልሽ እንደ ሆነ አላት። በዚያን ጊዜም ምድር ተሠንጥቃ እንደ ዳታን ዋጠቻት። እርሷ የረከሰች ስትሆን ወደ ቤተ ክርስቲያን መግባትን ደፍራለችና።

እኛ ሁላችን የክርስቲያን ወገኖች አምላክን ለወለደች ለእመቤታችን ለከበረች ድንግል ማርያም ለመታሰቢያዋ መንፈሳዊ በዓልን ልናደርግ ይገባናል። ስለ እርሷ ለአዳምና ለሁላችን ለልጆቹ ድኅነት ሆኖአልና ይህንንም በዓል ለማድረግ የሚተጋ የተመሰገነ ነው።

                     🌹🌹🌹
                  T.me/Ewnet1Nat
Audio
ድርሳነ ቅዱስ ዑራኤል ዘወርኃ ሰኔ.
◦ ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት ◦
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🟢🟡🔴
ሰኔ ፳፭ | በሰማዕትነት ያረፉ ክቡራን፦

#ቅዱስ_ይሁዳ_ሐዋርያ
በዘመነ ሐዋርያት ይሁዳ ተብለው ይጠሩ ከነበሩት አንዱ የሆነው ቅዱሱ የአረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ልጅ ሲሆን እናቱ ማርያም ትባል ነበር።

እናቱ ስትሞትበት ተጎድቶ የነበረ ቢሆንም ገና በልጅነቱ ድንግል ማርያም አግኝታው በፍጹም ጸጋ አሳድጋዋለች። አስተዳደጉም ከጌታችን ጋር በአንድ ቤት ነበር።

ጌታችን እርሱንና ወንድሞቹን (ያዕቆብና ስምዖንን) ከ72ቱ አርድእት ቆጥሯቸዋል። ቅዱስ ይሁዳ ወንጌል ላይ ከጌታችን ጋር መነጋገሩን ዮሐንስ ወንጌላዊ መዝግቧል። (ዮሐ. 14፥22)

ቅዱስ ይሁዳ ከጌታችን እግር 3 ዓመት ተምሮ፣ መንፈስ ቅዱስንም ተቀብሎ ብዙ አሕጉራትን ዙሯል። አይሁድንም አረማውያንንም ወደ ክርስቶስ ይመልስ ዘንድ ብዙ ድካምና ስቃይን በአኮቴት ተቀብሏል።

አንዲት አጭር (ባለ አንድ ምዕራፍ) መልእክትም ጽፏል። አጭር ትምሰል እንጂ ምሥጢሯ እጅግ የሠፋ ነው። ቅዱስ ይሁዳን በዚህች ቀን አረማውያን ገድለውት በሐዋርያነቱ ላይ የሰማዕትነትን ካባ ደርቧል።
🌿

#ቅዱስ_ጲላጦስ_መስፍን
ብዙዎቻችን መስፍኑን ጲላጦስ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ጌታችን እንዳይሰቀል ከአይሁድ ጋር ሲከራከር እናውቀዋለን።

የጌታችን ሞቱ በፈቃዱ ነበርና አይሁድ እንቢ ሲሉት የክርስቶስን ንጽሕና መስክሮ፣ እጁንም ታጥቦ ሰጥቷቸዋል። የጲላጦስ ታሪክ ግን እዚህ ላይ አያበቃም።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ ትንሣኤውን በራዕይ ገልጦለት አይሁድን ተከራክሯቸዋል። ውሸታም ወታደሮችንም ቀጥቷል።

በመጨረሻ ግን በሮም ቄሳር ተጠርቶ ከእሥራኤል እስከ ሮም ድረስ ሰብኮ በሮም አደባባይ አንገቱ ተሠይፏል።
🌿

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 26 | የሊቀ መላእክት #ቅዱስ_ገብርኤል በዓሉ ነው፨

በዚህች ቀን ኔቅሎን በሚባል አገር በፍዩም ገዳም ቤተ ክርስቲያኑ የተከበረችበት ነው።

በውስጧም ከቤተ ክርስቲያኗ የጣራ ዕንጨት ብዙ ተአምር ይገለጽ ነበር። ጽጋብ በሚሆንባት በዚያች ዓመት ውኃ ይንጠፈጠፋል። ረሀብ ከሆነ ግን ላብ እንኳ አይታይም ነበር።

የዚህ የከበረ የመላእክት አለቃ ገብርኤል ተአምራቶቹ ብዙዎች ናቸው።

እንዲሁም በዚሁ ወር ሰኔ 13 ቅዱስ ዳንኤል ነቢይን ያዳነበት በዓሉ ነው።

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን እኛንም በአማላጅነቱ ይማረን ረድኤቱም ከእኛ ጋራ ትሁን ለዘላለሙ አሜን።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
🟢🟡🔴
ሰኔ 28 | ተጋዳይ አባቶቻችን፦

፩- #አባ_ቴዎዶስዮስ

ጻድቁ 33ኛ የግብፅ ሊቀ ጳጳሳት ሲሆን ተወልዶ ያደገው በምድረ ግብጽ በ6ኛው መቶ ክ/ዘመን ነው። ከልጅነቱ መጻሕፍትን ተምሮ በመንኖ ጥሪት የሚኖር ደግ ሰው ነበር።

ያ ዘመን መለካውያንና ልዮናውያን (ክርስቶስን 2 ባሕርይ የሚሉ) የሰለጠኑበት ዘመን ነበር። በአንጻሩ ደግሞ ተዋሕዶን የሚያምኑ ሊቃውንትና ምዕመናን ቁጥራቸው የተመናመነ ነበር።

እረኝነት እንደተሾመም ተዋሕዶን ትቶ መለካዊነትን (ኩትልክናን) እንዲቀበል ግድ ቢሉት እምቢ በማለቱ በዚህ ምክንያት በቀጥታ ግዞት (ስደት) ተፈረደበት።

ስደት ሳያግደው ሕዝቡ በተዋሕዶ እንዲጸና መልእክት በየጊዜው ይጽፍላቸው ነበር። እጅግ ብዙ ከሆኑት መልእክቶቹ የተወሰኑት ዛሬም ድረስ #ሃይማኖተ_አበው መጽሐፍ ውስጥ ይገኛሉ።

አባ ቴዎዶስዮስ በብዙ ስቃይ ውስጥም ሆኖ ሕዝቡን ግን በመልካም እረኝነት ከምን*ፍቅና ታደገ። ፓትርያርክ የሆነው ለ32 ዓመታት ሲሆን 28ቱን በስደትና በመከራ ተጋድሎ ሰኔ 28 ዐረፈ።

፪- የምሥራቁን ኮከብ #ቅዱስ_ያዕቆብ_ዘእልበረዳይ መታሰቢያው ነው፡፡

ከላይ የዘከርነው አባ ቴዎዶስዮስ በግዞትና በስደት ሳለ ንግሥቲቱ ታኦድራ ትራዳው፣ ምዕመናንንም ትንከባከብ ነበር።

ቅዱስ ያዕቆብ ደግሞ ከሊቀ ጳጳሱ ዘንድ ክህነትን ተቀብሎ ከሶርያ እስከ ምድረ ግብጽ ስለ #ተዋሕዶ ሕልውና ተጋድሏል። ምናልባትም ከሐዋርያው #ቅዱስ_ጳውሎስ በኋላ በፈሊጥ ክርስትናን በማስፋፋት ቀዳሚ አባት ነው።

ለአገልግሎት ፈጣን እና ከቦታ ቦታ ገስጋሽ ስለሆነ "እል በረዲ" ተብሏል። ትርጉሙ ሠጋር በቅሎ፣ ፈጣን ሠረገላ እንደ ማለት ነው እንጂ የሀገሩ ስም አይደለም።

ብዙ ሕዝብ እያጠመቀ መለያ እንዲሆን በአንገት ላይ ጥቁር ማኅተብ ማሰርን ያስጀመረን ይህ አባት ነው።

፫- #ኣቡነ_ክፍለ_ሥላሴ ዘዛውል ወዘባንብቆ ዕረፍታቸው ነው።

አቡነ ክፍለ ሥላሴ በእናታቸው ማሕፀን ሳሉ የተመረጡ ስለነበሩ እግዚአብሔርን በመፍራት ይታወቁ ነበር። ስመ ሥላሴን በከንቱ አያነሡም ነበር።

ስመ እግዚአብሔርም ከተጠራባቸው በፍርሃት ይታዘዛሉ። እረኞችም ከብቶቻቸውን እንዲመልሱላቸው የእግዚአብሔርን ስም ከጠሩባቸው ይታዘዟቸው ነበር። በዚኸም ነገር አቡነ ክፍለ ሥላሴ ታላቁን ጻድቅ አቡነ ዐቢየ እግዚእን መሰሉ።

አቡነ ዐቢየ እግዚእ "ስለ እግዚአብሔር ብለህ" ብለው ጦር ላይ እንዲወድቁ፣ የአህያ ቁስል እንዲልሱ ቢጠየቁ ስለ ስሙ ክብር ብለው እሺ ያሉ አባት ናቸው።

አቡነ ክፍለ ሥላሴ ራሳቸው "በአባታችን በአብርሃም የመታሰቢያ ቀን ከናንተ እለያለሁ" እንዳሉ ሰኔ 28 ዐርፈዋል።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 29 | ከቅዱሳን ንጉሦች መካከል፦

👑 ኢትዮጵያዊው የንጉሥ ዳዊት ልጅ #ንጉሥ_ቴዎድሮስ_ቀዳማዊ ዐረፈ።

ይህም ቅዱስ ከታናሽነቱ በዕውቀትና በተግሣጽ አደገ። የቤተ ክርስቲያንንም መጻሕፍት የተማረ ደግሞም ቀስት ማፈናጠርንና ፈረስ ግልቢያን ተማረ። ኃይል ያለውም ብርቱ ሰው ሆነ።

ከታናሽነቱም ጀምሮ በእግዚአብሔር ፍቅር ታሠረ። ገንዘቡን ለድኆችና ለችግረኞች ይመጸውት ነበር። አብያተ ክርስቲያንንም እጅ መንሻ ከመያዝ ጋራ ይጎበኝ ነበረ። በጸሎትና በጾምም ይጋደል ነበረ።

ካንዲት ሴት በቀር አላገባም። በማንም ላይ ዐመፅና ግፍ ከቶ አልሠራም።

ወደ ኢየሩሳሌም ለመሔድ በአሰበ ጊዜ አባ ማርቆስን አማከረው። እርሱም በመንፈስ ቅዱስ ያውቅ ነበረና ክፍልህ አይደለም አለው።

ከዚህም በኋላ ባረፈ ጊዜ በክረምት ወራት በድኑን ሲወስዱ ሞልቶ የነበረው ወንዝ ወዲያና ወዲህ ተከፍሎ ተሻገሩ። በቀበሩበትም ቦታ ሕይወትነት ያለው ውኃ መነጨ እስከ ዛሬም አለ።

👑 ንጹሕ ጻድቅ የሆነ የሮሜ #ንጉሥ_ማርቆስ የዕረፍቱ መታሰቢያ ሆነ።

ይህም ቅዱስ በድንግልናው አምስት ዓመት ነገሠ። ሕዝቡንም እግዚአብሔርን በመፍራትና በቅን ፍርድ ጠበቀ።

እርሱንም ከመውደዳቸው የተነሣ ሚስትን እንዲአገባ መኳንንቱ አስገደዱት። እርሱ ግን በሌሊት ወደ ቤተ ክርስቲያን ገብቶ ከእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ፊት ቁሞ ጸለየ።

እመቤቴ ሆይ ላንቺና ለማይሻር ንጉሥ ልጅሽ እገዛ ዘንድ ወደ ምሔድበት ምሪኝ አላት። እርሷም ወደ ቶርማቅ ተራራ ሒድ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋራ ይኑር አለችው።

ከዚህም በኋላ በሌሊት ወጥቶ ሔደ። ወደ ባሕር ወደብም በደረሰ ጊዜ ያለ መርከብ ተሻግሮ ወደ ቶርማቅ ተራራ ደረሰ።

ከአጋንንት ጋራም እየተጋደለ በውስጡ ስልሳ ዓመት ኖረ። በዐረፈ ጊዜም መላእክት በልዩ ክብር ቀበሩት።

T.me/Ewnet1Nat
ጥቂት ነገር ስለ ምስራቅ ኦርቶዶክስ

በኢትዮጵያ ትንሳኤ ከሚፈጸሙ ትንቢቶች ውስጥ በዋናነት ከሚጠቀሱት አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት የሁለት ባህርይ አስተምህሮ ተከታዮችን አሸንፋ በዓለም የምትገንበት አንዱ ነው። ይህም በአባ ጊዮርጊስ መጽሐፈ ምስጢር፣ በገድለ አባ ሲኖዳ፣ በገድለ ፊቅጦር እና በሌሎችም ተጠቅሷል። በነዚህም ትንቢቶች ላይ የኢትዮጵያ ንጉስ ፓትሪያርኩ ከእስክንድርያ እንደሚነሳ፣ የሮሙ ንጉስ ደግሞ ከቁስጥንጥንያ እንደሚነሳ በግብጽም በአባ ሲኖዳ ገዳም ተገናኝተው የሃይማኖት ክርክር እንደሚያደርጉ በኋላም የኢትዮጵያው ንጉስ ከፓትርያርኩ ጋር እንደሚያሸንፍ በዝርዝር ተገልጿል። አባ ጊዮርጊስ ጨምረውም ኢትዮጵያውያን በኢየሩሳሌም ሌላም ተዐምር እንደሚያሳዩ ገልጸዋል።

ታዲያ ይህ የሃይማኖት ክርክር የሁለት ባህርይ እምነትን የሚከተሉትን የሚመለከት ይሁን እንጂ የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን ይሁን ወይስ ሌላ የሚለው በግልጽ አልተቀመጠም። ይህም ግልጽ ያልሆነበት ምክንያት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ተከታዮችም ከሞላ ጎደል የሁለት ባሕርይ አስተምህሮን የሚከተሉ መሆናቸው ነው። ስለዚህ በዚህ ጽሑፍ የምስራቅ ኦሮቶዶክስ አብያተ ክርሰቲያንን ታሪክና አስተምህሮ፣ ከሮም እና ቁስጥንጥንያ ጋር ያላቸውንም ቁርኝት እንመለከታለን።

የምስራቅ ኦሮቶዶክስ ቤተ ክርስቲያኖች መሠረታቸው የግሪክ ቤተክርስቲያን ናት። የግሪክ ቤተክርስቲያን ደግሞ የጥንቷ ቢዛንቲን ወይም ምስራቅ ሮም የምትባለው ናት። በኋላ ላይም የግሪክ አባቶች ወደ ምስራቅ አውሮፓ በመሄድ በአከባቢው ያሉ ህዝቦችን አስተምረው ወደ ክርስትና አምጥተዋል። እነዚህም ህዝቦች በየራሳቸው ቋንቋ እምነቱን ስርአቱን ተቀብለው የየራሳቸው ቤተክርስቲያን መሥርተዋል። ነገር ግን የሚከተሉት ትውፊትና ስርአተ ቅዳሴ ወዘተ የቢዛንቲንን ነው። ይኸውም "Byzantine rite" በመባል ይታወቃል። ሁሉም የየራሳቸው ፓትሪያርክ ቢኖራቸውም ግን የቁስጥንጥንያው ፓትርያርክ ግን (ዛሬም ድረስ እንደዛ ተብሎ ነው የሚጠራው፣ በቱርክ ውስጥ የሚገኘው) ከሁሉም በላይ ትልቅ ክብርና ስልጣን እንዳለው ይታሰባል። ዛሬ ላይ ጎልተው ከሚታወቁት የምስራቅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርሰቲያናት ውስጥ የግሪክ፣ የሩሲያ፣ የዩክሬን፣ የሰርቢያ እና የሮሜኒያ ቤተክርስቲያን ይገኙበታል።

ነገር ግን እነዚህ ቤተ ክርስቲያኖች መሠረታቸው የግሪክ ቤተክርስቲያን እንደመሆኑ፣ የግሪክ ቤተክርስቲያን ደግሞ የመለካውያን በመሆኗ እና የኬልቄዶን ጉባኤንም የምትቀበል በመሆኗ እነርሱም በተመሳሳይ ጉባኤ ኬልቄዶንን የሚቀበሉ እና የሁለት ባሕርይ አስተምህሮን የሚያራምዱ ናቸው። በብዙ መልኩም ከካቶሊክ ጋር የሚመሳሰሉበት ነገር አለ። የዚህን ታሪክ ደግሞ ወደ ኋላ ተመልሰን እንመልከት።

ጉባኤ ኬልቄዶንን የተቀበሉት አብያተ ክርስቲያን ሁለት ነበሩ እነርሱም የግሪክና የላቲን ቤተ ክርስቲያን ነበሩ። እነዚህም ከኬልቄዶን በኋላ ተጨማሪ ሶስት ጉባኤ አድርገዋል። ይኸውም በቁስጥንጥንያ ተጨማሪ ሁለት እና በኒቂያም ተጨማሪ አንድ ጉባኤ አድርገዋል። እናም ሁለቱ አብያተ ክርስቲያን ሰባት የቤተክርስቲያን ጉባኤ አለን ብለው ነው በቀኖናቸው የሚቀበሉት። በዚህም መሠረት የነሱ ልጆች የሆኑት ካቶሊክ እና ምስራቅ ኦርቶዶክስም የቤተክርስቲያን ጉባኤዎች 7 ናቸው ብለው ነው የሚያምኑት።

ታዲያ የግሪክና የላቲን ቤተክርስቲያኖች ኬልቄዶንን ተቀብለው የተዋህዶ አማኞችን እያሳደዱ ሲኖሩ፣ በግሪክ እና በላቲን ቋንቋ እየቀደሱ፣ የየራሳቸውን ፓትሪያርክ ይዘው ይኖሩ ነበር። ቆይቶ ግን የላቲኑ ቤተ ክርስቲያን ግሪኮች በኔ ስልጣን ስር ይሁኑ በኔ ስርም ይገዙ የሚል ጥያቄ አመጡ። በዚህም የሮሙ ፓትሪያርክ በዓለም ሁሉ ላይ ስልጣን ሊኖረው ይገባል የሚል ሀሳብ አመጡ። ይህ የሆነው ምናልባት የሮሙ መንበር የቅዱስ ጴጥሮስ መንበር ስለሆነና ጴጥሮስንም ጌታ የዓለም ፓትርያርክ ብሎ ስለሾመው ይሆናል (ያም ቢሆን ግን ልሎቹም ሐዋርያት በፓትርያርክነት ማዕረግ የተሾሙ ነበሩ) ፤ አንዳንዶች ደግሞ ሮም የመንግስቱ የመጀመሪያ መነሻ ናት፣ ቢዛንቲን ወይም ቁስጥንጥንያ ደግሞ በኋላ የመጣች ናት ስለዚህ ቁስጥንጥንያ በሮም ስር መሆን አለባት ከሚል የፖለቲካ ጥያቄ የተነሳ ነው የሚሉም አሉ።

የሆነው ሆኖ ግን የሮሟ ቤተክርስቲያን የስልጣን ጥያቄዋና በኋላም አዳዲስ ምንፍቅና በመፍጠሯ ምክንያት ከምስራቅ ኦርቶዶክስም እየተለየችና እየራቀች መጣች። ለምሳሌ "filioque" የሚባለው የኑፋቄ አስተምህሮ ይኸውም "መንፈስ ቅዱስ ከአብም ከወልድም ነው የሠረፀው" የሚለው ታዋቂው ነው። ትክክለኛው አስተምህሮ ግን መንፈስ ቅዱስ ከአብ ብቻ የሠረፀ መሆኑ ሲሆን፣ በኒቅያ ጉባኤ የተፃፈው የሃይማኖት ጸሎት ዋናው ግሪኩ ወደ ላቲን ሲተረጎም በመጣ የትርጉም ስህተት እርሱን ወደ ትልቅ ስህተት በማደጉ የተፈጠረ ኑፋቄ ነው። ይህ እና የስልጣን ጥያቄው ሌሎችም ችግሮች ተደምረው በአውሮፓውያኑ 1054 ዓ.ም የላቲኗ ቤተክርስቲያን ራሷን ከግሪክ ቤተክርስቲያን ፈጽማ ለየች። ራሷንም ካቶሊክ ብላ ጠራች። የቃሉ ትርጉም "ኩላዊት ቤተክርስቲያን" ቢሆንም የላቲኗ ቤተክርስቲያን ሳይገባት ስሙን ያዘች።

ቀጥሎም በኑፋቄ ላይ ኑፋቄን እየጨመረች፣ የራሷን አዲስ አስተምህሮ እየፈጠረች ሄደች። ፖፕ የተባሉት ጳጳሶቿም በስልጣን ጥም እጅግ የተለከፉ በመሆን ስልጣናቸውን ለመጠበቅ ረጅም ርቀት ሄዱ። ለራሳቸው እንዲመች እያደረጉም አዳዲስ እርስ በራሱ ሁሉ የሚጣረስ ከቤተክርስቲያን ዶግማ ፈጽሞ የወጣ አስተምህሮ የያዙ ሆኑ።

የግሪክ ቤተክርስቲያን ግን መለካውያን ቢሆኑም የካቶሊክን ያህል ርቀው አልሄዱም። ቢሆንም ግን ኑፋቄው እንዳለ አለ። እናም የካቶሊክን ቤተክርስቲያን አውግዘው የለዩ ሲሆን ራሳቸውን ኦርቶዶክስ ብለው ጠርተዋል። እኛ ቀጥተኛውን መንገድ ይዘናል የላቲን ቤተ ክርስቲያን ነች የሳተችው ሲሉ። ካቶሊክም በበኩሏ አውግዛ ለይታቸዋለች።

በዚህም ምክንያት ምስራቅ ኦርቶዶክሶች እና ካቶሊክ አንዱ አንዱን የለየ ቢሆኑም፣ ወደ አንድ ለመምጣት ግን ፍላጎቱ አላቸው። አሁንም ግን ካቶሊኮች ምስራቅ ኦሮቶዶክሶችን "ኑ በኛ ስር ሁኑ" እያሉ ነው ጥሪ የሚያቀርቡላቸው። በሌላ በኩል ደግሞ የተወሰኑ ካቶሊኮች "ቤተክርስቲያኗ መንገዷን ስታለች፣ መስተካከል አለባት" እና "ጳጳሱን አልቀበልም" ወዘተ የሚሉ ካቶሊኮች እየበዙ መጥተዋል። የምስራቅ ኦርቶዶክሶች ደግሞ በብዛትም እየጨመሩ እየጠነከሩ መጥተዋል። በአውሮፓና አሜሪካም ከካቶሊክና ፕሮቴስታንት የወጡ ብዙ ተከታዮች እያፈሩ ነው።

ስለዚህ፣ ወደፊት ከኢትዮጵያ ንጉስ ጋር ተገናኝተው የሚከራከሩት ካቶሊኮች ናቸው ወይስ ምስራቅ ኦርቶዶክሶች? ወይስ ሁለቱም? በቁስጥንጥንያ የሚቀመጠው ፓትሪያርክስ የግሪክ ቤተክርስቲያን አባት ነው ወይስ ካቶሊክ? የካቶሊኩ ፖፕ ከቁስጥንጥንያ ሊነሳ ይችላልን?

ደግሞም፣ በግሪካዊው መነኩሴ "ፓይሲዮስ" የተነገረው ትንቢትስ? ቱርክ ጠፍታ ሶስት ቦታ እንደምትከፋፈል፣ ሩሲያውያንም ለማን እንደሚሰጡ ግራ ሲገባቸው ለግሪክ እንደሚሰጧት የተነገረውስ እንዴት ይታይ ይሆን? እነዚህ ነገሮች ወደፊት ጊዜ የሚፈታቸው ቢሆንም አሁንም ፍንጮች ይታያሉ። ደግሞም በተለያዩ ሶሻል ሚዲያዎች ላይ ምስራቅ ኦርቶዶክሶች ከግብጽ፣ ኢትዮጵያ እና ሶርያውያን ጋር እየተገናኙ ማውራት፣ መጠየቅ፣ መከራከር መጀመራቸው ሁሉም ነገር ቅርብ እንደሆነ ማሳያ ነው።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ (ኢትዮጵያዊ የተክለሃይማኖት ወዳጅ🇨🇬🇨🇬🇨🇬)
🟢🟡🔴
ሰኔ 30 | ነቢይ ሰማዕትና ሐዋርያ የሆነ #መጥምቁ_ዮሐንስ ተወለደ።

ይህም በእናቱ ማኅፀን ውስጥ ሳለ ለእግዚአብሔር ልጅ የሰገደው ነው። ይህም በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ እጁን ጭኖ በውኃ ያጠምቀው ዘንድ የተገባው ነው።

በቅዱስ ወንጌል እንደ ተነገረ ወንድ ልጅን ትወልድ ዘንድ የኤልሳቤጥ የፅንሷ ወራት በተፈጸመ ጊዜ ወንድ ልጅን ወለደች። ዘመዶቿና ጎረቤቶቿ እግዚአብሔር ቸርነቱን እንዳበዛላት በሰሙ ጊዜ ስለርስዋ ደስ አላቸው።

በስምንተኛውም ቀን ሊገዝሩት መጡ በአባቱ ስም ዘካርያስ ብለው ጠሩት። እናቱ ግን አይሆንም ዮሐንስ ይባል አለች። ከዘመዶችሽ ስሙ እንዲህ የሚባል የለም አሏት።

አባቱንም ጠቅሰው ማን ሊባል ትወዳለህ አሉት። እርሱም ብራና ለምኖ ስሙ ዮሐንስ ይባል ብሎ ጻፈ። ሁሉም አደነቁ። ያን ጊዜም አንደበቱ ከድዳነት ተፈትቶለት ተናገረ። እግዚአብሔርንም ፈጽሞ አመሰገነው።

ስለ ልጁና ስለ መድኃኒታችን መምጣት ልጁ ዮሐንስም የልዑል ነቢይ እንደሚባልና በእግዚአብሔርም ፊት እንደሚሔድ ትንቢት ተናገረ።

ራሱ መድኃኒታችንም ስለርሱ ሲናገር ሴቶች ከወለዱአቸው መጥምቁ ዮሐንስን የሚበልጠው የለም ብሏል።

እኛም መድኃኒታችን እንዲምረንና ይቅር እንዲለን በአማላጅነቱ እያመን መታሰቢያውን እናድርግ፡፡

T.me/Ewnet1Nat
🌿☘️🌿
Audio
🟢🟡🔴 መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ፥ አለቃ አያሌው ታምሩ ሰኔ-30-1999 ዓ.ም

📌 አለቃ ከማረፋቸው ወር ከሁለት ሳምንት ቀደም ብሎ ያስተማሩት ትምህርት ነው!
Forwarded from Biruk
Audio
🟩 🟨 🟥
ማሳሰቢያ ከራዕይ ዮሐንስ 20 | ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ብቻ!

 ሐምሌ - 1 - 2016 ዓ.ም
🟢🟡🔴
ሐምሌ 2 | #ቅዱስ_ታዴዎስ ሐዋርያ ዐረፈ።

#_ቅዱስ_ታዴዎስ በቀደመ ስሙ #ልብድዮስ ይባል የነበረ ሲሆን በአንዳንድ መጻሕፍት ውስጥ (በተለይ በምሥራቅ ኦርቶዶክሶች) #ስምዖን እና #ይሁዳ እየተባለም ተጠርቷል።

ከቅዱስ ጴጥሮስ ጋር ወደ ስብከት ሲሄዱ ቢርባቸው አንድ ገበሬ ቤቱ ገብቶ ምግብ እስኪያመጣላቸው ድረስ አርሰው፣ ዘርተው፣ ወዲያው እሸት አድርሰዋል።

ቅዱስ ታዴዎስ በይበልጥ የሚታወቀው ደግሞ በግመልና መርፌ ተአምሩ ነው።

ይህም ቅዱስ ታዴዎስ የወንጌልን ትምህርት ለአንድ ሃብታም ጎልማሳ ቢነግረው ጎልማሳው ተቆጥቶ አነቀው።

አባት ጴጥሮስም የክርስቶስን ሐዋርያ እንዴት ደፍረህ ታንቃለህ አለው። ያን ጊዜም ተወው። ሐዋርያው ታዴዎስም ጌታችን እንዳንተ ላለው ሀብታም "ባለጸጋ ወደ መንግሥተ ሰማያት ከሚገባ ግመል በመርፌ ቀዳዳ ቢያልፍ ይቀላል" ብሎ በእውነት ተናገረ አለው።

ጎልማሳውም ይሄ እንዴት ይሆናል? ትክክል አይደለም አለ። ቅዱስ ታዴዎስም ጠባብ መርፌ እንዲያመጣ አዘዘው። በዚያም ጌታችንን "ኃይልህን ግለጥ" ብሎ ጸለየ።

እጁንም ዘርግቶ ባለ ግመሉን ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስም አንተ ከገመልህ ጋራ በመርፌ ቀዳዳ ውስጥ ግባና እለፍ አለው። ገብቶም አለፈ። ሕዝቡ የፈጣሪያችን የክርስቶስን ኃይል ይረዱ ዘንድ ዳግመኛ ገብተህ እለፍ አለው። ባለ ግመሉም በመርፌው ቀዳዳ ሦስት ጊዜ ከግመሉ ጋራ አልፎ ሔደ።

ሕዝቡም አይተው ከቅዱሳን ሐዋርያት አምላክ ከሕያው እግዚአብሔር ልጅ ከኢየሱስ ክርስቶስ በቀር ሌላ አምላክ የለም እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ተናገሩ።

ከዚህ በኋላ በብዙ አገሮችም ውስጥ ገብቶ ሰበከ። ከአይሁድና ከአረማውያንም መከራ ደረሰበት። ሐምሌ 2 ቀንም በሰላም ዐረፈ።

🌿🌿🌿

T.me/Ewnet1Nat
2024/09/24 22:29:39
Back to Top
HTML Embed Code: