Telegram Web Link
🟢🟡🔴
ሰኔ 8 | #_የእመቤታችን_ማርያም ቅዳሴ ቤት ተከናወነ፨

በዚች ቀን አምላክን የወለደች በሁለት ወገን ድንግል የሆነች የእመቤታችን ማርያም በስደቷ ወቅት ልጇ ያፈለቀው የውኃ ምንጭ ዘንድ ያለች የቤተ ክርስቲያንዋ ቅዳሴ ነው።

ይኽም ከእመቤታችን 33ቱ ዋነኛ በዓላት አንዱ ነው።

ይህም እንዲህ ነው፦ ለጻድቁ ዮሴፍ የእግዚአብሔር መልአክ በሕልም ተገልጾለት ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ግብጽ አገር ሒድ አለው። ዮሴፍም ነቅቶ ተነሣ።

ክብር ይግባውና ሕፃኑን ጌታችንን እናቱንና እኅቷ ሰሎሜን ይዞ ወደ ግብጽ አገር ሔዱ። በዚያም በውስጧ ባሉ በብዙ አገሮች እየዞሩ ሦስት ዓመት ከስድስት ወር ኖሩ። የእመቤታችን ስደት የጀመረው ግንቦት 24 ቀን ነው። ለ3 ዓመት ከ6 ወርም ተወዳጅ መድኃኒት ልጇን ይዛ በስደት ቆይታለች።

ሄሮድስም ከሞተ በኋላ የእግዚአብሔር መልአክ ለዮሴፍ ሁለተኛ ተገለጠለት። ወደ እስራኤልም አገር ሕፃኑንና እናቱን ይዞ እንዲመለስ አዘዘው።

በሚመለሱም ጊዜ ወደ መዓልቃ ደረሱ። ከዚያም ወደ መጣርያ አገር ደረሱ ይቺም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ውኃ ያፈለቀባትና የመታጠቢያ ቦታ የሆነች ናት። እርሷም እስከ ዛሬ አለች።

ሰዎችም ከአገሩ ሁሉ ከየነገዱ ሁሉ መጥተው አምላክን ወደ ወለደችና በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ ወደ ጸናች ቅድስት ድንግል እመቤታችን ማርያም ይለምናሉ። ከተባረከውም የውኃ ምንጭ ታጥበው ከደዌያቸው ሁሉ ይድናሉ። በዛሬዪቱ ቀን ከከበረች ቤተ ክርስቲያንም ይባረካሉ።

እርሷን እመቤታችንን ለመረጣትና ለወደዳት በሥጋም እናቱ ላደረጋት ስለርሷም ዘመድ ለሆነንና ወደርሱ ላቀረበን ወራሾቹም ላደረገን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን ለዘላለሙ አሜን።

                🌹
T.me/Ewnet1Nat
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🟢🟡🔴
ሰኔ 9 | #አቡነ_በኵረ_ድንግል በዓላቸው ነው፨

እኚህም የአቡነ ብፁዓ አምላክ ረዳት ሲሆኑ አቡነ ብፁዓ አምላክ ካረፉ በኋላ በደብረ ምዕዋን ምንኩስና ተሹመው ብዙ አገልግለዋል።

የአቡነ በኵረ ድንግል አባታቸው ማርቆስ እናታቸው እግዚእክብራ ይባላሉ ሁለቱም ጻድቅ ነበሩ።

አቡነ በኵረ ድንግል በእናታቸው ማኅፀን እያሉ ብዙ ተአምራትን አድርገዋል። በተወለዱ ጊዜ የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም ሥዕል ከተወደደ ልጇ ከቸሩ መድኃኔዓለም ጋር በልባቸው ተሥሎ ተወለዱ።

ሲወለዱም እንደሌሎች ቅዱሳን ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ›› እያሉ አመሰገኑት ።

ወላጆቻቸው በ40ኛ ቀናቸው ሊያጠምቋቸው ወደ ቤተ ክርስቲያን ሲወስዷቸው የሚያጠምቃቸው ኤጲስ ቆጶስ የእመቤታችንን ሥዕል እና የመድኃኔዓለም ሥዕል በልባቸው ተሥሎ አይቶ ሜሮን ሊቀባቸው ሲል ደነገጠ። ቅዱስ ሚካኤል ግን ተገልጦ ኤጲስቆጶሱን ያለ ፍርሃት እንዲያጠምቃቸው አዘዘው።

በተጠመቁ ጊዜ የብርሃን እናት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከተወዳጅ ልጇ ጋር ተገኝታ በመስቀሉ ምልክት ባርካቸው የመስቀል ምልክትም በሥጋቸው ላይ ዳግመኛ ተሥሏል።

ለመማር በደረሱ ጊዜ ግዕዝ ፣ ዐረብኛ ፣ ዕብራይስጥ፣ ግሪክ፣ ሮማንስ፣ ብሉይና ሐዲሳት፣ ሌሎችም ብዙ ቅዱሳት መጻሕፍትን ተምረዋል።

☘️◦ ከተሰጣቸው ቃል ኪዳን ◦☘️

. . በስምህ የሚዘክር፣ ስምህን የሚጠራ፣ በዓለ ዕረፍትህን የታመመውንና የታሰረውን የሚጠይቅ፣ የተራበውን የሚያበላ፣ የተጠሙትን ያጠጣ፣ በስምህ ልጁን የሚጠራ፣ እኔ ኃጢአቱን ይቅር እለዋለሁ፤ ክፉም አያገኘውም።

በስምህ በታነጸው ቤተክርስቲያን ቅዱስ ቁርባንን የተቀበለውን እምርልሀለሁ፤ እኔ ኃጢያቱን ይቅር እለዋለሁ።

       ◦☘️☘️☘️
T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 11

ስንክሳሩ ንጽሕናውንና ቅድስናውን ለማጠየቅ ሲል "የመልአክት አርአያ ያለው" ብሎ የገለጸው ሰማዕቱ #ቅዱስ_ገላውዴዎስ ዕረፍቱ ነው፡፡

#አቡነ_መዝሙረ_ድንግል
ሀገራቸው ጎጃም ሲሆን ታላቅ የቤተ ክርስቲያናችን ባለ ውለታ ናቸው።

ጻድቁ በአምስት ሊቃውንት እየተመሩ በአራት ዓመት ጊዜ ውስጥ አራቱን ወንጌላት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች በመተርጎም በግእዝ፣ በአረማይክ፣ በዕብራይስጥና በዐረብኛ ጽፈው በአራት ዓምት ያዘጋጁ ታላቅ አባት ናቸው። ዛሬም በሞጊና ገዳም ይገኛል።

ከዚህም ሌላ ነገረ ማርያምንም በግእዝና በዕብራይስጥ አዘጋጅተው ጽፈውታል። ሌሎችንም በርካታ መጻሕፍት ወደ ተለያዩ ቋንቋዎች እየተረጎሙ ጽፈው ያስቀመጡ ነበር።

ጸሎተኛ፣ ደራሲ፣ ባሕታዊ፣ ጻድቅና መናኝ የሆኑት አቡነ መዝሙረ ድንግል ሰኔ 11 ዐርፈው የተቀበሩት ጣና ክብራን ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ነው።

#_አቡነ_ገብረ_ኢየሱስ
ለግብፃውያን አባቶች ትንቢት ይነግሯቸው የነበሩት ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ ገብረ ኢየሱስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ በሀገራችን ብዙ ተአምራትን በማድረግ ወንጌልን ሲሰብኩ ከኖሩ በኋላ የግብፅ ገዳማትን ለመሳለም ወደ ግብፅ ወርደው አባ መቃርስ ገዳም ገቡ፡፡

ከዚያም ወጥተው በአባ ዮሐንስ ሐፂር ገዳም ገብተው በዚያ ብዙ ጊዜ ተቀመጡ፡፡ አቡነ ገብረ ኢየሱስ ታላቅ የሆነ ሀብተ ትንቢት የተሰጣቸው አባት ስለሆኑ በዚህም ግብፃውያኑ ይቀኑባቸው ነበር፡፡

በወቅቱ የነበረው የግብጻውያኑ ንጉሥ በጣም ብዙ ሚስቶች የነበሩት ቢሆንም አቡነ ገብረ ኢየሱስ ሄደው በድፍረት አስተምረውትና ገሥጸውት በአንድ ሚስት ብቻ እንዲጸና አድርገውታል።

የአባታችን ገድላቸው በጣና ይገኛል። ዐርፈው የተቀበሩት ግን በዛው በግብጽ በቊስቋም ገዳም ነው። ግብጻውያን ታቦት ቀርጸው በዓል ያደርጉላቸዋል።
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 12 | በዚህች ቀን፦

የከበረ #የመላእክት_አለቃ_ቅዱስ_ሚካኤል በነገዱ ውስጥ በመላእክት ሁሉ ላይ በብዙ ክብር የተሾመበት፣

ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የሚበር ንሥረ አርያም የሚባል ውዳሴው እንደ ማር የጣፈጠ ንዑድ ክቡር የሆነ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል #_ቅድስት_አፎምያን ያዳነበት፣

ዳግመኛም መልአከ ብርሃን ቅዱስ ሚካኤል #_የቅዱስ_ባህራን_ቀሲስ የሞት ደብዳቤ ቀዶ እርሱን ለታላቅ ክብር ያበቃባት ቀን ናት፡፡

🍀 ዳግመኛም ካህን እና ንጉሥ፣ ጻድቅ እና ንጹሕ #ቅዱስ_ላሊበላ የዕረፍቱ በዓል ነው።

#_እንኳን_በቸርነቱ_አደረሳችሁ
T.me/Ewnet1Nat
☘️ቅዱስ ላሊበላ ንጉሠ ኢትዮጵያ☘️

▸ ቅዱስ፣ ንጹሕ፣ ካህን ወንጉሥ ቅዱስ ላሊበላ (ላል-ይበላ) ታኅሣሥ 29 ተወለደ፤ ሰኔ 12 ተጋድሎውን ጨርሶ ዐረፈ።

ሙሉውን ታሪክና ቃልኪዳን ለማንበብ 👇
Audio
ድርሳነ ቅዱስ ሚካኤል ዘወርኃ ሰኔ.
Audio
ገድለ ቅዱስ ላሊበላ ዘወርኃ ሰኔ
የሟቾች ቁጥር ወደ 550 ማደጉ ተሰማ

አመታዊውን የሀጂ ስነስርአት ለመካፈል ወደ ሳኡዲ ካቀኑ ሰዎች መካከል ከ550 በላይ ሰዎች በሙቀት መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

ከከፍተኛ የሙቀት መዕበል ጋር በተያየዘ በሚፈጠሩ በሽታዎች ነው ሃጃጆቹ ህይወታቸው ያለፈው፡፡ ከሟቾቹ መካከል 323 የግብጽ ፣ 144 የኢንዶኔዢያ፣ 35 የቱኒዝያ ፣ 11 የኢራን ፣ 6 የሴኔጋል ዜግነት ያላቸው ሃጃጆች ናቸው ተብሏል፡፡

የሟች ቤተሰቦች በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሳኡዲ ሆስፒታሎች ዘመዶቻቸውን በማፈላለግ ላይ ሲሆኑ ዮርዳኖስ በበኩሏ በሃጂ የሞቱ ዜጎቿን ለመቀበር 41 የመቃብር ስፍራዎችን ማዘጋጀቷን በትላንትናው እለት አስታውቃለች፡፡
በጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ምክንያት የሦስት ኢትዮጵያውያን አሽከርካሪዎች ሕይወት አለፈ‼️
በጎረቤት አገር ጂቡቲ ባለው ከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ባለፉት ሁለት ሳምንታት ውስጥ ሦስት የከባድ መኪና አሽርካሪዎች እና የመኪና ጥገና ባለሙያ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሕይወት እንዳለፈ የኢትዮጵያ ከባድ መኪና አሽከርካሪዎች ማኅበር አስታወቀ።
እነሆ፥ እንደ ምድጃ እሳት የሚነድድ ቀን ይመጣል፤ ትዕቢተኞችና ኃጢአትን የሚሠሩ ሁሉ ገለባ ይሆናሉ፤ የሚመጣውም ቀን ያቃጥላቸዋል፥ ሥርንና ቅርንጫፍንም አይተውላቸውም፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር። ሚል 4፥1

እነሆ ይመጣል የተባለው መምጣቱን ልብ ያልው ልብ ይበል።
በከባድ ሙቀት ህይወታቸው ያለፈ ሀጃጆች ቁጥር ከ1 ሺህ ተሻገረ

1081 የ10 ሀገራት ዜጎች ህይወታቸው ማለፉ የተነገረ ሲሆን፥ ከ650 በላዩ ግብጻውያን ናቸው ተብሏል። በዘንድሮው ሃጂ የተመዘገበው ጉዳት ከ2015 ወዲህ ከፍተኛው መሆኑ እየተነገረ ነው።
2024/11/16 13:44:46
Back to Top
HTML Embed Code: