Telegram Web Link
በሙቀት ሳቢያ ባለፉት 3 ወራት ከ24 ሺህ በላይ ሰዎች በስትሮክ ተጠቅተዋል
በህንድ ባለፉት 3 ቀናት ውስጥ በከፍተኛ ሙቀት ሳቢያ ከ50 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ።
በሀገሪቱ ያጋጠመውን ከፍተኛ ሙቀት ተከትሎ 33 ገደማ ሰዎች በሰሜናዊዋ ኡታህ ፓርዴሽ ክልል ውስጥ ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ በኦዲሻ ደግሞ 20 ገደማ ሰዎች በሙቀት ሳቢያ ህይወታቸው አልፏል።
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እንደ ጅረት የሚወርደው ናዳ

በታይዋን ኬሉንግ በተባለ አካባቢ ከባድ የመሬት መንሸራረተት አደጋ አጋጥሟል።

ድንገተኛው አደጋ በርካታ ተሽከርካሪዎች ላይ ጉዳት አድርሶ መንገድ መዝጋቱም ታውቋል።

11 ተሽከርካሪዎችን ያዳፈነው ናዳ ሁለት ሰዎችን ለከባድ ጉዳት መዳረጉ ነው የተገለጸው።

ሀገር ሰላም ብለው ሲጓዙ የነበሩ አሽከርካሪዎች ያልጠበቁት አደጋ ሲከሰት በተሽካሪያቸው ላይ የገጠሟቸው ካሜራዎች ቀርጸውታል።
👆
«ትራንስፖርት ፍጹም ይበላሻል በየትኛውም አለም መኪና ፣ ባቡር፣ አውሮፕላን፣ መርከብ ሁሉም ለመገልገል ያስቸግራል አደጋቸውም የበዛ ይሆናል፡፡ ለምህረት ያልታደሉትን ለማጥፋት ሞት ሁሉንም መገልገያዎች ወደ መግደያነት ይለውጣቸዋል፡፡ »

► ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 3 ተፃፈ 19/07/2001 ዓ፡ም
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 29 | ከተሰዓቱ ቅዱሳን የሆኑ #አቡነ_አፍጼ እና #አቡነ_ጉባ በዓላቸው ነው፡፡

ከዘጠኙ ቅዱሳን ውስጥ አራቱ በምድር ላይ ሞትን ሳያዩ የተሰወሩ ናቸው፡፡ እነዚህም አቡነ አረጋዊ፣ አቡነ ገሪማ፣ አቡነ ሊቃኖስና አቡነ አፍጼ ናቸው።

☘️ አቡነ አፍጼ ☘️

አቡነ አፍጼ የተወለዱት እስያ ውስጥ በ5ኛው መቶ ክ/ዘመን ሲሆን ወላጆቻቸው አቡሊዲስና አቅሌስያ ይባላሉ፡፡

ሕዝቡ በጣዕመ ስብከታቸው ይገረም ስለ ነበር ‹‹አፍፄ-አፈ ዐፄ›› ብሏቸዋል፡፡ ይኽም የዐፄ/የንጉሥ አንደበት ያለው›› ወይም ‹‹ንግግር አዋቂ›› ማለት ነው፡፡

አቡነ አፍጼ ከ200 ዓመታት በላይ ቤተ ክርስቲያንን አገልግለው ግንቦት 29 ቀን በ684 ዓ.ም በሞት ፈንታ ተሰውረዋል፡፡

☘️ አቡነ ጉባ ☘️

እርሳቸውም የተወለዱት ታኅሣሥ 29 ቀን 336 ዓ.ም በመንፈቀ ሌሊት ነው፡፡ አባታቸው ጌርሎስ እናታቸው ቴዎዶክስያ የተባሉ ደጋግ ቅዱሳን ናቸው፡፡

አቡነ ጉባ በተወለዱ ቀን ጌታችን ከመላእክቱ ጋር በመውረዱ ቤታቸው ለ7 ቀናት በብርሃን ተሞልቶ ነበር፡፡ ሕጻኑ ጉባም ፈጣሪያቸውን ሃሌ ሉያ ብለው አመስግነዋል። በዚህም ቀን ዐረፉ።
🍀

#አቡነ_መዝራዕተ_ክርስቶስ
አባታቸው ለባሴ ክርስቶስ የዐፄ ፋሲል የቅርብ ወዳጅ የነበረ የጦር አዛዥ ደጃዝማች ሲሆን እናታቸው ሚላንያ ትባላለች፡፡ ጻድቁ ታኅሣሥ 29 ቀን በጎንደር ተወለዱ፡፡

ዓፄ ፋሲል ሴት ልጃቸውን ሊድሩላቸው ሲሉ ሸሽተው መነኮሱ። ከዛም በአርማጭሆ ደብረ ሙጅና፣ በዋልድባ፣ በጉንዳጉንዲ ማርያም፣ በመጠራ በምንኩስና ሲጋደሉ ኖሩ።

በዋልድባ ገዳም ሥዕለ ማርያምን በጎኑ ታቅፎ ሲያዝን ለብዙ መናንያን የተሰወረችው ደብረሲና የተባለች ቅድስት ቦታ ተገልጣላኋለች።

በኋላም በመሠረቷት በማይ ዱር ገዳም በ93 ዓመታቸው ግንቦት 29 ዐረፉ።

T.me/Ewnet1Nat
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 30 | የከበሩ ቅዱሳን እናቶቻችን፦

☘️ቅድስት ዜና ማርያም☘️

ከአባቷ ከገብረ ክርስቶስ ከእናቷ አመተ ማርያም በ11ኛው መ/ክ/ዘ በቅዱስ ላሊበላ ዘመነ መንግሥት በምድረ ነጋሲ በጎጃም ምድር ግንቦት 30 ቀን ተወለደች።

ለአቅመ ሔዋን በደረሰች ጊዜ በንጽሐ ድንግልና በአቡነ እንድርያስ ዋሻ ለ25 ዓመት በጾም በጸሎት፣ በቅል ውስጥ የሚገኘውን መራራ ፍሬ ከኮሶ ጋር በአንድነት ደርጣ (አዋሕዳ) በመመገብ እስከ ሕይወቷ ፍጻሜ ድረስ የጌታችንን ሕማም በማሰብ ተጋድላለች።

ለጻድቋ ቅድስት ዜና ማርያም የተሰጠ ቃል ኪዳን

እግዚአብሔር መርጦና ፈቅዶ በጻድቋ አማላጅነት ካለበት ሥፍራ ተነሥቶ የጻድቋን ደጅ የረገጠ "የ3 ግመል ጭነት ጤፍ ወይም የሦስት አህያ ጤፍ ያህል ነፍሳትን እምርልሻለሁ፤ ከሲዖልም እሳት ነፍሳትን አወጣልሻለሁ" ተብላለች።

☘️ቅድስት አርዋ☘️

ቅድስት አርዋ ሁሉ ያላት ስትሆን ስለ መንግሥተ ሰማያት ሁሉን ንቃለች። በተለይ ደግሞ ሥጋዊ ፍትወትን ትገድል ዘንድ ያሳየችው ተጋድሎ በዜና ቤተ ክርስቲያን የተደነቀ በመሆኑ "መዋኢተ ፍትወት" (የሥጋን ፍላጎት ድል የነሣች) አስብሏታል።

በሐሰት ክስ ተገድላ እግዚአብሔር አስነሥቷታል። በመጨረሻም አንድ ጎልማሳ ይመኛት ነበርና አስገድዶ ሊገናኛት ሲዘጋጅ እመቤታችን መጥታ ነፍሷን ተቀብላታለች። ይህም ግንቦት 30 ቀን ነው።

☘️ቅድስት ወለተ ማርያም☘️

ትውልዷ ጎንደር ሲሆን በዐፄ ወናአግ ሰገድ ዘመን የነበረች ከቤተ መንግሥት ወገን የሆነች ጻድቅ እናት ናት። ደብረ ሊባኖስ ሄዳ ከመነኰሰች በኋላ ወደ ጣና ገዳም ገብታ በጣና ባሕር ውስጥ ለ11 ዓመት ቆማ የጸለየች ድንቅ እናት ናት።

ከእናቶቻችን ረድኤትና በረከትን ያሳትፈን፤ በጸሎታቸው ይማረን።
T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 1 | እስራኤል የተባለ የያዕቆብ ልጅ #ጻድቁ_ዮሴፍ እና ሚስቱ #ቡርክት_አሰኔት ዕረፍታቸው ነው፡፡
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
🟢🟡🔴 ሰኔ 1 | እስራኤል የተባለ የያዕቆብ ልጅ #ጻድቁ_ዮሴፍ እና ሚስቱ #ቡርክት_አሰኔት ዕረፍታቸው ነው፡፡
ቅዱስ ዮሴፍ ያዕቆብ (እስራኤል) ከሚወዳት ሚስቱ ራሔል ከወለዳቸው 2 የስስት ልጆቹ አንዱ ነው። ቅዱሱ ምንም እናቱ ብትሞትበትም በአባቱና በፈጣሪው ፊት ሞገስ ነበረው። ምክንያቱም ቅን ታዛዥና የፍቅር ሰው ነበርና።

እንዲያ አምርረው ለሚጠሉት ወንድሞቹ እንኳን ክፋትን አያስብም ነበር። ይልቁኑ ለእነሱ ምሳ (ስንቅ) ይዞ ሊፈልጋቸው በበርሃ ይንከራተት ነበር እንጂ።

መንገድ ላይ ቢርበው አለቀሰ እንጂ ስንቃቸውን አልበላባቸውም። የአባቶቹ አምላክ ግን ድንጋዩን ዳቦ አድርጎ መግቦታል። 10ሩ ወንድሞቹ ግን ስለ በጎነቱ ፈንታ ሊገድሉት ተማከሩ። ከፈጣሪው አግኝቶ በነገራቸው ሕልም "ሊነግሥብን ነው" ብለው ቀንተውበታልና።

በፍጻሜው ግን በይሁዳ መካሪነት ለዐረብ ነጋድያን ሸጠውታል። በዚህም ለምስጢረ ሥጋዌ (ለጌታ መሸጥና ሕማማት) ምሳሌ ለመሆን በቅቷል። ወንድሞቹ ለክፋት ቢሸጡትም ቅሉ ውስጡ ፈቃደ እግዚአብሔር ነበረበትና በባርነት በተሸጠበት በጲጥፋራ ቤት ፈጣሪው ሞገስ ሆነው።

ወጣትነቱን በፍቅረ እግዚአብሔር ሸብ አድርጎ አስሮ ነበርና የጲጥፋራ ሚስት የዝሙት ጥያቄ አላንበረከከውም። "ማንም አያየንም" ስትለውም "እፎ እገብር ኃጢአተ በቅድመ
እግዚአብሔር" (ማንም ባያይስ እንዴት በፈጣሪየ ፊት ኃጢአትን አሠራለሁ?) በማለት ከበደል አምልጧል። ስለዚህ ፈንታም የእሥር ቅጣት አግኝቶታል።

ጌታ ከእርሱ ጋር ቢሆን በእሥር ቤትም ሞገስን አገኘና አለቅነትን ተሾመ።

ከዚያም የንጉሡን (የፈርዖንን) ባለሟሎች ሕልም ተረጎመ። ቀጥሎም ንጉሡን በሕልም ትርጓሜ አስደመመ። ፈርዖንም ቅዱሱን በግዛቱ (ግብጽ) ላይ ሾመው።

ቅዱስ ዮሴፍ በምድረ ግብጽ ነግሦ ሕዝቡን ከረሃብ ታደገ። ለቅዱስ አባቱ ለእሥራኤልና ክፉ ለዋሉበት ወንድሞቹም መጋቢ ሆናቸው።

አስኔት (አሰኔት) የምትባል ሴት አግብቶም ኤፍሬምና ምናሴ የተባሉ ልጆችን አፍርቷል። በመንገዱ ሁሉ እግዚአብሔርን አስደስቶ ከአባቱ ዘንድም ምርቃትና በረከትን ተቀብሎ በ110 ዓመቱ በዚህች ቀን በመልካም ሽምግልና ዐርፏል።

ወገኖቹም በክብርና በእንባ ቀብረውታል። "አጽሜን አፍልሱ" ብሎ በተናገረው ትንቢት መሠረትም ልጆቹ (እነ ቅዱስ ሙሴ) ከግብጽ ባርነት ሲወጡ አጽሙን ወደ ከነዓን አፍልሠዋል።

              ◦☘️☘️☘️
🟢🟡🔴
ሰኔ 2 | #የቅዱስ_ዮሐንስ_መጥምቅ እና #የቅዱስ_ኤልሳዕ_ነቢይ ዐፅም በአንድነት ፈለሰ፨

የቅዱስ ዮሐንስ ራስ በአንድ አርዮሳዊ እጅ ሳለች፥ መጥምቁ ዮሐንስ ለአባ አንያኖስ ተገለጠለትና ራሱ የምትገኝበትን ቦታ ነገረው። እንደዛሬው ባለ ዕለት ግንቦት 30 ቀን ከዚያ አወጣት፡፡ ይህም የካቲት 30 ቀን ከአገኟት በኋላ ዳግመኛ ከነቢዩ ኤልሳዕ መቃብር ውስጥ ያገኙበት ነው፡፡

በ350 ዓ.ም አካባቢ ክፉ የነበረው ንጉሥ ዑልያኖስ ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሞክሮ ነበር። ለዚህ እንዲረዳው በ70 ዓ.ም የፈረሰውን የአይሁድ ቤተ መቅደስ አንጻለሁ ቢልም 3 ጊዜ ፈረሰበት።

ምክንያቱን ቢጠይቅ "የክርስትያኖች አጽም በሥሩ ስላለ አውጥተህ አቃጥል" አሉት።

ሲቆፈር የሁለቱ ቅዱሳን አጽም በምልክት በመታወቁ በኢየሩሳሌም የነበሩ ክርስቲያኖች በብዙ ብር ገዝተው ሰኔ 2 ቀን ወደ ግብፅ አውርደው ለቅዱስ አትናቴዎስ ሰጥተውታል። እርሱም በስደት ላይ ነበርና በክብር ደብቋቸዋል።

በኋላም በቅዱስ ቴዎፍሎስ ዘመን ቤ/ክናቸው ታንጾ በዚህ ቀን ተቀድሷል። በቅዳሴው ሰዓትም ቅዱስ ቴዎፍሎስ ዮሐንስ መጥምቁና ቅዱስ ኤልሳዕ ወርደው ሕዝቡን ሲባርኩ በይፋ ተመልክቷል።
🍀

በዚችም ቀን የአቡነ ተክለ ሃይማኖት የአክስት ልጅ፣ እንደ ነቢዩ ኤልያስ እሳት ከሰማይ አውርደው በፈንታሌ ተራራ ላይ ሰሪቲ ለምትባል ጠንቋይ እየተላላኩ ሕዝቡን የሚያስቱና የሚያሰቃዩ 473,000 አጋንንት በአንድ ጊዜ ያጠፉ ታላቁ #አቡነ_ቀውስጦስ_ዘመሐግል መታሰቢያቸው ነው።

የታናሽ ወንድማቸው የዐፄ ይኩኖ አምላክ ልጅ ዐፄ አምደ ጽዮን የአባቱን እቁባት በማግባቱ እንደ መጥምቁ ዮሐንስ ሄደው ንጉሡን ቢገሥጹት በግዞት ወስዶ ጎናቸው በጦር ወግቶ ገድሏቸዋል፡፡

ልደታቸውም ሆነ ዕረፍታቸው ከእመቤታችን ልደትና ዕረፍት ጋር አንድ ቀን ነው።

T.me/Ewnet1Nat
🟢🟡🔴
ሰኔ 3 | አቡነ #_ተጠምቀ_መድኅን የዕረፍታቸው በዓል ነው፨

ጻድቁ የተወለዱት በአፄ ሱስንዮስ ዘመን በ1610 ዓ/ም ሲሆን ወላጆቻቸው ወልደ ክርስቶስና ወለተ ማርያም ይባላሉ።

ታኅሣሥ 2 ቀን እንደ መወለዳቸው ክርስትና የተነሱት ጥር 11 ቀን ነበርና ካህኑ "ተጠምቀ መድኅን" አላቸው። በምድረ ጎጃም ከበቀሉ ታላላቅ ቅዱሳን አንዱ የሆኑት አባ ተጠምቀ መድኅን ገና ከሕጻንነታቸው ጀምሮ #ጸጋ_እግዚአብሔር የጠራቸው ነበሩ።

ሕጻን እያሉ #ቃለ_እግዚአብሔር መማር ቢፈልጉም አባታቸው በግድ እረኛ አደረጋቸው። እርሳቸው ግን በሕጻን ልባቸውም ቢሆን ቤተሰብን ማሳዘን አልፈለጉም።

ይልቁኑ ወደ በርሃ ይወርዱና አንበሳውን፣ ነብሩን፣ ተኩላውን ሰብስበው፦ "በሉ እኔ ልማር ልሔድ ስለ ሆነ እስከ ማታ ድረስ ጠብቁልኝ" ብለው ለአራዊቱ አደራ ይሰጣሉ። አራዊቱ ከበጉ፣ ከፍየሉ፣ ከላሙ ጋር ሲቦርቁ ይውላሉ:: ተጠምቀ መድኅን ደግሞ ዳዊቱን ወንጌሉን ሲማሩና ሲጸልዩ ውለው ማታ ይገባሉ።

ተጠምቀ መድኅን በሕጻንነታቸው ቁርስና ምሳቸውን ለነዳያን በመስጠት በቀን አንድ ማዕድ ብቻ ይቀምሱ ነበር። 23 ዓመት ሲሞላቸው ወደ #መርጡለ_ማርያም ሔደው መንኩሰዋል። ከዚህ ጊዜ በኋላ ለ37 ዓመታት፦

▸ በፍጹም ተጋድሎ ኑረዋል
▸ ራሳቸውን ዝቅ አድርገው አገልግለዋል
▸ ከጎጃም እስከ ሱዳን ድረስ ወንጌልን ሰብከው በርካቶችን አሳምነው አጥምቀዋል (ካህን ናቸውና)
▸ "7" ገዳማትንና "12" አብያተ ክርስቲያናትን አንጸዋል።

ጻድቁ በተሰጣቸው መክሊት አትርፈው በ60 ዓመታቸው በ1670 ዓ.ም (#በዐፄ_ዮሐንስ_ጻድቁ ዘመን) ዐርፈዋል።

☘️☘️☘️
T.me/Ewnet1Nat
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
📌 «እግዚአብሔርም የመጀመሪያው እርምጃ በቤተክርስቲያን ላይ እንዲጀምርና እንዲጸዳ ወስኗል፡፡ ትዕዛዝም ተላልፏል፡፡»

⚡️ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክት 10 ገጽ 28 በቀን 7/5/2015 .ዓ.ም የተጻፈ፡፡
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጊዜ የማይገልጠው እውነት የለም‼️

"በሲኖዶስ ውስጥ ከተሰበሰቡት ጳጳሳት ከአሥራ ሰባት(17) የማያንሱ የደህንነት ሰራተኞች መሆናቸውን ለመሆኑ ወገኖቼ ታውቃላችሁ!? ለስለላ የተሰማሩ፡ ለፖለቲካው ሰራተኛ የሆኑ በድፍረት የክብር ልብስ የሆነውን የክብር፣ ሰውን የመባረኪያ፤ ከኀጢአት ከእስራት የመፍቻ ሃይል የሆነውን መስቀል በእጃቸው  የጨበጡ ደፋሮች የዲያብሎስን ስራ የሚሰሩ፤ ቀሚሱን ለብሰው ስለፖለቲካው  የሚተጉእነዚህ በሲኖዶስ ውስጥ ተሰግስገው ህይወት እንዴት ነው  የሚገኘው??

ዛሬ ዓለም እንደ ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ደብዳቤ ጥር 7/2012  እንደታዘዘው ስትበጠር ይኸው ሲኖዶስ ወይም የዓለም አብያተ ክርስቲያን  ጉባኤ ለምን አቤት ብሎ አያስቆመውም? አዎን! ህይወት የላቸውም። ከሃዲዎች ናቸው። ፈጣሪያቸውን የካዱ። በሳይንስ፡ በምርምር፡ በጥንቆላ፡ በትብተባ የተሸፈኑ ናቸው።..."

ፅሑፉ ሚያዝያ 11/2012ዓ.ም ዕለተ ትንሣኤ በድምፅ ከተላለፈው
ከመግለጫ 3 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን የተወሰደ ነው።

ሙሉውን ፅሑፍና መግለጫ ለማግኘት፦
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/1921
#ለታሪክ_ትቀመጥ ‼️
ሰኔ 3፥2016
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Ankara swamped by powerful flooding - again

Just a month after the Turkish capital suffered torrential downpours that left streets completely submerged, severe rainfall on Saturday has swept away cars and left a chaotic center.

Many streets remain all but impassable as several transport routes - including the metro - have been paralyzed.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Lava flow covers road to Grindavik - Drone Footage

Iceland's active volcano has stabilised since its fifth and most powerful eruption last month.

Authorities say the lava flow has started to slow as it moves across the Reykjanes Peninsula, but it has again engulfed a road which had recently been repaired and reopened.
#Update

የማላዊ ምክትል ፕሬዝዳንት እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናትን ይዞ ሲጓዝ የነበረውን ከራዳር እይታ የተሰወረው አውሮፕላን #ስብርባሪ ተገኘ።

አውሮፕላኑ መከስከሱ ተረጋግጧል።

ምንም የተረፈ ሰው የለም።

በአውሮፕላኑ ውስጥ ምክትል ፕሬዜዳንቱ ሳውለስ ቺሊማን እና የቀድሞው ፕሬዜዳንት ባኪሊ ሙሊዚ ባለቤት / የቀድሞ ቀዳማዊ እመቤት ሻኒል ዲዚምቢሪን ጨምሮ 10 ሰዎች ነበሩ።

ሁሉም መሞታቸው ነው የተሰማው።

Photo Credit - Hopewell
2024/09/25 20:26:38
Back to Top
HTML Embed Code: