Telegram Web Link
Audio
ድርሳነ ኪዳነ ምሕረት ዘወርኃ ግንቦት
Audio
መልክአ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ
Audio
የወንጌላዊው የቅዱስ ዮሐንስ የዓርብ ፀሎት
❗️በሜክሲኮ ኃይለኛ ንፋስ መድረክ አወደመ

በሜክሲኮ ለፖለቲካ ምርጫ በተዘጋጀ ቅስቀሳ ላይ ድንገተኛ ንፋስ መድረኩን ከጥቅም ውጪ አድርጎታል።

በአደጋው እስካሁን 9 ሰዎች ሲሞቱ 50 ያህሉ ደሞ ህክምና እያገኙ ነው።

= = = = = = = = = = = = = = = = = = = =
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 17 | የኢትዮጵያዊው ጻድቅ #አቡነ_ገብረ_ሚካኤል ዕረፍታቸው ነው፡፡

የትውልድ ሀገራቸው ትግራይ ገርዓልታ ነው፡፡ ጻድቁ አቡነ ገብረ ሚካኤል ወንጌልን ዞረው በማስተማርና አስደናቂ ፍልፍል ዋሻ ቤተ መቅደሶችን በማነጽ ብዙ የደከሙ ታላቅ አባት ናቸው፡፡

ከገርዓልታ በደቡባዊ አቅጣጫ የሚገኘው ይህ የአቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂ ገዳም እንደ ደብረ ዳሞ በገመድ ብቻ ከሚወጣው ከአቡነ ገብረ ናዝራዊ ገዳም ጋር ይዋሰናል።

በገዳሙ ውስጥ ጻድቁ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ብዙ ቅርሶች ይገኛሉ፡፡ የጌታችን የሾህ አክሊል ምሳሌ የሆነውና ጻድቁ ያደርጉት የነበረው የድንጋይ ቆብ፣ መቋሚያቸው፣ የእጅ መስቀላቸውና መጻሕፍቶቻቸው ይገኛሉ፡፡

ሌላው አስደናቂ ነገር ሀገሩ በረሃ ቢሆንም ጻድቁ ከኢየሩሳሌም ዮርዳኖስ ያመጡትና ዋሻው ውስጥ ጉድጓድ ቆፍረው ያጠራቀሙትን ውኃ መነኮሳቱ ሁልጊዜ የሚጠቀሙበት ቢሆንም ውኃው ግን ከዓመት እስከ ዓመት መጠኑ አይቀንስም፡፡

በገዳሙ ውስጥ ከዓመት እስከ ዓመት የምትበራው አንዲት ጧፍ ብቻ ናት፡፡

ጧፏ ነዳ የማታልቅ ስትሆን አለቀች ትቀየር ሳትባል አስገራሚ በሆነ ተአምር ከዓመት እስከ ዓመት ትበራለች፡፡ 

አቡነ ገብረ ሚካኤል አስደናቂውን ዋሻ ፈልፍለው ከጨረሱ በኋላ ግድግዳውና ዓምዶቹ ላይ የሳሏቸው የሐዋርያትና የቅዱሳን ሥዕላት ከጥንታዊነታቸው በተጨማሪ እጅግ ውብና አስደናቂ ናቸው፡፡


ዳግመኛም በዚህች ቀን መጽሐፈ አክሲማሮስን የጻፈልን የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳሳት #ቅዱስ_ኤጲፋንዮስ ዕረፍቱ ነው፨

                 ◦☘️☘️☘️
           ▸ www.tg-me.com/Ewnet1Nat
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መልእክታት ከምናስበው በላይ በከፍተኛ ሁኔታ እየተፈጸሙ ነው። አባቶች የተናገሯቸው ትንቢቶች በሙሉ አንዲቷም ሳትቀር እየደረሰች ነች። በሰፊው ከተዳሰሱት ትንቢቶች በተጨማሪ አለፍ አለፍ ብሎ የተጠቀሱ በአጭሩ የተቀመጡ ትንቢቶች ሳይቀሩ እየተፈጸሙ ናቸው። ከነዚህ ውስጥ ስለ ውጪ ሀገራት የተጠቀሱትን ከመልእክት 5 እና 8 አንስተን ብናይ፦

- ሀብታም የነበሩት ነጮች ደሃ ሆነው ወደ ልመና እንደሚገቡ የተገለጸው። በአሁኑ ወቅት በውጪ ሀገራት በተለይ በአሜሪካ ንብረታቸውን ሁሉ አጥተው የቤት ኪራይ መክፈል አቅቷቸው የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ እኑ ወደ ልመና የገቡ ሰዎችን በተለይ ነጮችን ማየት የተለመደ ሆኗል። ነገሩም እየተባባሰ ሄዷል።

- በቢላዋ/ስለት መወጋት እና ሴቶች መደፈር እንደሚከሰት ተገልጾ ነበር። አሁን ላይ በኢንግሊዝና ፈረንሳይ ሰዎች በቢላ ተወግተው መሞት እጅግ የተበራከተ ወንጀል ነው። በጣም በዙ ሰዎች በዚህ እየሞቱ ነው። በእስክንዲኔቪያ ሀገራት ደግሞ ሴቶቹ አስገድዶ የመድፈር ወንጀል በጣም በብዛት ይደርስባቸዋል። ይህም ወንጀል እጅግ የተበራከተ ሆኗል።



ሌሎችም በሰፊው የተዳሰሱ ትንቢቶችን ብንመለከት፤

- ታይቶ የማይታወቅ እጅግ ጥልቅ ሪሴሽን፦ ይህ በአሁኑ ወቅት እንደሚከሰት እውን ሆኗል። መላው ዓለም ወደ አደገኛ ሪሴሽንና የኢኮኖሚ ድቀት እንደሚገባ አሁን ላይ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ሪሴሽኑም በታሪክ ከታየው ሁሉ እጅግ ከፍተኛና አድቃቂ እንደሚሆን ይገመታል።

- የጦር መሳርያዎች ውድመት፦ በመልእክታቱ ብዙ ጊዜ የተገለጸው ሃያላኑ ሀገራት ያላቸው የጦር መሳሪያ ሁሉ እንደሚወድም፣ ከነ ማከማቻው ሁሉ ውድመት እንደሚገጥመው ተገልጿል። ይህም በሚያስገርም መልኩ እየተፈጸመ ነው። እነ ሩሲያ እጅግ ርካሽ የሆኑ ድሮኖችን በመጠቀም የምዕራባውያኑን ታንኮችና መርከቦች ከጥቅም ውጪ እያደረጉ ነው።

እነዚህ ድሮኖች "suicide drone" እና "kamikaze drone" በመባል ይታወቃሉ። ልክ እንደ አጥፍቶ ጠፊ ኢላማቸውን ተከታትለው በመሄድና በመምታት አብረው ይጋያሉ፣ ኢላማውንም ከጥቅም ውጪ ያደርጋሉ። ሩሲያ እነዚህን ርካሽ ድሮኖች በመጠቀም በቢሊዮን ዶላር የሚገመቱ እጅግ ብዙ የአሜሪካ እና የአውሮፓ ሰራሽ ታንኮችና ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን ከጥቅም ውጪ አድርጋለች።

በዚህም ምዕራባውያኑ ያላቸውን ታንኮችና መሳርያዎች ሁሉ ወደ ዩክሬን ቢልኩም ሁሉም እየወደመ ከስረዋል። በዚህም ካላቸው የጦር መሳርያ ክምችት እስከ ግማሽ የሚሆነውን ያጡ የአውሮፓ ሀገራት አሉ። በተጨማሪም ሩሲያ የዩክሬንን የጦር መሳርያ ፋብሪካዎችና መጋዘኖችን በተደጋጋሚ አውድማለች።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሩሲያ "kamikaze" ድሮኖች የዩክሬንን ታንክ ተከትለው ሲያጋዩ።

ድሮኗ ከጣቢያ ሆኖ የሚቆጣጠራት ፓይለት አለ። እሱም በአየር መቃወሚያዎች ሳይመታ እና ኢላማውን ሳይስት ተከታትሎ ይመታል።
ጥንተ በዓለ ጰራቅሊጦስ

ግንቦት 18 ቀን | እሑድ ዕለት
የክብር ባለቤት ጌታችን ከዐረገ በኋላ በዐሥረኛ፣ ከትንሣኤው በሃምሳኛ ቀን ለደቀመዛሙርቱ ከአብ የሚሠረጽ ሌላ አካላዊ ሕይወት ጰራቅሊጦስን እልክላችኋለሁ ብሎ ተስፋ እንደ ሰጣቸው በሐዋርያት ላይ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ ወረደ።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
በፓፑዋ ኒው ጊኒ በደረሰ የመሬት መንሸራተት 300 ሰዎች እና 1182 ቤቶች መቀበራቸው ተነገረ

የመሬት መንሸራተት አደጋው መንገዶችን በመዝጋቱ የነፍስ አድን ስራው በሄሊክፕተር ብቻ እየተከናወነ ነው ተብሏል።
በዩክሬን "Kharkov" ወይም "Kharkiv" በተሰኘው አከባቢ ሩሲያ በቅርቡ በከፈተችው ጥቃት ምክንያት የሞቱ የዩክሬን ተዋጊዎች መቃብር
🟢 🟡 🔴
ግንቦት 19 | በዚህ ቀን የከበሩ፦

● በወሎ ላስታ ሰውንና ዝንጀሮን በቃልኪዳን ያስተሳሰሩትና እመቤታችን ዕጣን እየሰጠቻቸው ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር የሥላሴን መንበር ያጠኑት #የእንጂፋቱ_አቡነ_ዮሴፍ ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ጌታችን 5 ጊዜ ከሞት ያስነሣው የ12 ዓመቱ ሕጻን ሰማዕት #ቅዱስ_ኤስድሮስ ዕረፍቱ ነው፡፡ ከእርሱም ጋር ማኅበርተኞቹ የሆኑ 8 መቶ 5 ሺህ ሰባት ሰዎች በሰማዕትነት ዐረፉ፡፡

● ጌታችን ተገልጦ ‹‹ለእናቴ ዓሥራት የሰጠኋት፣ ለወዳጄ ለጊዮርጊስ፣ ለባለሟሌ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ዓሥራት የሰጠኋት ይህችን ቅድስት ሀገር ያሬድንና ጊዮርጊስን ያፈራችውን ኢትዮጵያን በጸሎትህ ጠብቅ›› ብሎ ያዘዛቸው #የአክሱሙ_አቡነ_ዮሴፍ ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ስመ እግዚአብሔር ሲጠራባቸው ስለ ስሙ ክብር ሲሉ ራሳቸውን ለሞት አሳልፈው የሰጡት በጸሎታቸውም ውኃውን ደም ያደረጉት ታላቁ ተአምረኛው አባት #አቡነ_ዓቢየ_እግዚእ ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ጸሎት ማድረግ ሲጀምሩ ሰማያት ተከፍተው የመላእክትን አገልግሎት በግልጽ ይመለከቱ የነበሩትና ሰይጣን ለመጀመሪያ ጊዜ ከጳውሎስ ሳምሳጢን ጀምሮ እስከ ንስጥሮስንና ልዮን ድረስ ያስተማራትን የክህደት ትምህርት ከሀገራችን ያጠፉልን የሐይቁ #አቡነ_ብስጣውሮስ ዕረፍታቸው ነው፡፡

● ጌታችን ቤተ መቅደሱን በባሕር ላይ እንዲሠራ የነገረውና በምድራዊ ስንዴና ወይን ያይደለ መላእክት ሰማያዊ ኅብስትና ጽዋ እያመጡለት 22 ዓመት ሥጋ ወደሙን ሲፈትት የኖረው ጻድቁ ንጉሥና ካህን #ቅዱስ_ይምርሐነ_ክርስቶስ ልደቱ ነው፡፡

● በአባ መቃርስ ገዳም የሚኖር ቅዱስ አባት #ቀሲስ_ይስሐቅ ዕረፍቱ ነው፡፡

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
ኢየሱስ ክርስቶስ ካህኑ ለዓለም ንጉሠ ፅዮን ወንጉሠ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ
ድንግል ማርያም እሙ ወእምነ ንግሥተ ጽዮን ወንግሥተ ነገሥታት ዘኢትዮጵያ

19/9/2016 ድንቃ ድንቅ አስተማሪ ምስክርነት 👇👇👇
2024/09/25 16:24:07
Back to Top
HTML Embed Code: