Telegram Web Link
Palestinian Telegram channels report multiple Israeli attacks in Rafah

Footage shared online shows the aftermath of the attacks with casualties reported.

Israeli media says the IDF struck Rafah up to 15 times in a matter of minutes.
Gaza death toll tops 34,904 people with a further 78,514 injured, the enclave’s health ministry reported
🟢🟡🔴
ግንቦት 4 | አቡነ መልከጼዴቅ አረፉ።

ኢትዮጵያዊው ጻድቅ አቡነ መልከጼዴቅ በ13ኛው መ/ክ/ዘ መጨረሻ በንጉሥ ዐፄ በእደ ማርያም ዘመነ መንግሥት የነበሩ እደጃቸው የተቀበረውን ሰው አፈር የማያስበሉ እጅግ ድንቅ ቃልኪዳን ያላቸው ታላቅ አባት ናቸው።

እግዚአብሔር ወልድ የተገረፈውን ግርፋት እያሰቡ በየቀኑ እስከ 3ሺህ ድረስ ይሰግዱ ሰውነታቸውንም እንዲሁ ይገርፉ እንደነበር መጽሐፈ ገድላቸው ይናገራል።

የክርስቶስን መቸንከር እያሰቡ እጅና እግራቸውን፣ ወገብና ደረታቸውን በብረት ቸንክረው መከራውን ያስቡ ነበር። ጎኑ በጦር መወጋቱን አስበው አጥንታቸው እስኪሰበር ድረስ ጎናቸውን ወጉ። ሐሞትና ከርቤ መጠጣቱን አስበው እርሳቸውም መራራ ይጠጡና አንክርዳድን ይመገቡ ነበር። ሞቱን አስበው ደም እንባን ያነቡ ነበር።

የሰውን የድካሙን ዋጋ ፈጽሞ የማያስቀር አምላክ ሠራዊተ መላእክትን አስከትሎ መጥቶ፦

‹‹መገረፍህ፣ ስለ እኔ መገረፍ ይሁንልህ፣ የደምህ መፍሰስ ስለ እኔ ደም መፍሰስ ይሁንልህ፣ መቸንከርህም ስለ እኔ መቸንከር ይሁንልህ፣ ሞትህም ስለ እኔ ሞት ይሁንልህ›› ብሎ የሚከተለውን ቃልኪዳን ሰጥቷቸዋል።

‹‹ከዚህ ቦታ መጥቶ የተሳለመውን እምርልሃለሁ፤ ነፍሱ በአንተ ቃልኪዳን የማይማር በአንተ ቦታ ለመሳለምም፣ ንስሓ ለመግባትም ሆነ ለመቀበር አላቀርብብህም፤ መጥቶም የተቀበረውን ሥጋውን አፈር አይበላውም›› የሚል እጅግ ድንቅ ቃልኪዳን ነው መድኃኔዓለም የሰጣቸው።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
.         ☘️☘️☘️

#_ዳግም_ትንሣኤ ፡- በዚህ ዕለት ክርስቶስ ደቀመዛሙርቱ በተሰበሰቡበት ለሁለተኛ ጊዜ ተገልጦ ሰላምን መስበኩ እና ሥልጣንን መስጠቱ ይታሰባል፡፡

+ እንኳን አደረሳችሁ፤ መልካም በዓል!!! +
▸ አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ | www.tg-me.com/Ewnet1Nat
ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ ꔰ
🍀🍀🍀
#ዳግሚያ_ትንሣኤ
(መድኃኔዓለም አንዴ ብቻ ከተነሣ ለምን 'ዳግም' ተባለ?)

ለስም አጠራሩ ጌትነት ይድረሰውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከቅድስት ትንሣኤው በኋላ ለደቀ መዛሙርቱ በጉባኤ (በኅብረት ሳሉ) 3 ጊዜ ተገልጦላቸዋል፦

【1】 በዕለተ ትንሣኤ ምሽት በፍርሃት ሳሉ (ቅ/ቶማስ በሌለበት)፣

【2】ያላመነ ቅ/ቶማስን ለማሳመን በተነሣ በ8ኛው ቀን (ዳግማይ ትንሣኤ)፣

【3】ከተነሣ ከ23 ቀናት በኋላ በጥብርያዶስ ባሕር ዳርቻ ላይ ነው።

ጌታ አርባውን ቀን ለአንዱም ለሁለቱም በግል ይገለጥላቸው ነበር። እመቤታችንን ግን ፈጽሞ አይለያትም ነበር።

የክብር ባለቤት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤ ሳምንት ለሐዋርያው ቅዱስ ቶማስ ተገለጠለት። በእጆቹና በእግሮቹ ውስጥ የችንካሮቹን ምልክትም አሳየው። የቶማስንም እጅ ይዞ በመለኮታዊ ጎኑ ውስጥ አኖረውና በጦር የተወጋበትን ቦታ አሳየው ቶማስም "ጌታዬና ፈጣሪዬ መነሣትህን አመንኩ" አለ።

ጌታችንም "ብታየኝ አመንከኝ። የሚመሰገንስ ሳያየኝ የሚአምንብኝ ነው" ብሎ መለሰለት። ስለዚህ፦ ዳግመኛ ጌታችን ለሐዋርያት ቅዱስ ቶማስ ባለበት ለሁለተኛ ጊዜ ስለተገለጠ ዕለቱ "ዳግም ትንሣኤ" ተባለ። ዮሐ 20፥24-29።

በትርጓሜ ወንጌልም እንዲህ ይላል፦
ቶማስ በመድኃኒታችን ጎን ውስጥ እጁን በአስገባ ጊዜ እጁ በመለኮት እሳት ተቃጠለ፤ በመለኮቱም ደግሞ በታመነ ጊዜ እጁ ከመቃጠል ዳነች።

እንኳን አደረሳችሁ
🍀🍀🍀
Flash flooding in Afghanistan’s Baghlan province kills at least 60 people, mainly women and children — Local media
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
At least 300 killed as floods hit Afghanistan's Baghlan province
ጎሮ አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ‼️

ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 6:50 በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አጠገብ የተነሳዉ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በእሳት አደጋዉ በቤተክርስቲን ዙሪያ ያሉ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ ሙሉ የወደሙ እና በጋራዡ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች 66 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠርም 4 :10 ሰዓት መፍጀቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🟢🟡🔴
ግንቦት 5 | #ቅዱስ_ኤርምያስ_ነቢይ ዐረፈ።

እግዚአብሔር ኤርምያስን የጠራው ገና በሕጻንነቱ ነበር። "ከእናትህ ማሕጸን ሳትወጣ መርጬሃለሁ፤ ቀድሼሃለሁ" ሲልም በገሃድ መስክሮለታል። (ኤር. 1፥5)

ከቅዱሳን ነቢያት እንደ ኤርምያስ የተሰቃየና ያለቀሰ የለም። ከ70 ዘመናት በላይ ስለ ወገኖቹ አልቅሷልና። ሊቃውንት "ነቢየ ብካይ" (ባለ እንባው ነቢይ) ይሉታል።

እሥራኤላውያን ከመሪዎቻቸው ከነ ሴዴቅያስ ጋር በክፋት ተባብረውም ነበርና ኤርምያስን አልሰሙትም። ይልቁኑ ክፉ ቦታ ውስጥ አስረው አሰቃዩት። እግዚአብሔር ግን በኢትዮጵያዊው አቤሜሌክ አማካኝነት ከመከራው አዳነው።

የተሰበከላቸውን የንስሐ ጥሪ አልሰሙምና ስልምናሦር ማርኮ 10ሩን ነገድ ወደ አሦር (ነነዌ) አወረዳቸው። ናቡከደነፆር ደግሞ ሁለቱን ነገድ ባቢሎን አወረዳቸው።

ከቤተ መቅደስ ንዋያት እኩሉን ለምድር አደራ ሰጣትና ሸሸገችው። ነቢዩ እንደተናገረው ንጉሡ ናቡከደነጾር እኩሉን ገድሎ፣ እኩሉንም ማርኮ፣ ኢየሩሳሌምን አቃጥሎ፣ የአሕዛብ መዘባበቻ አድርጎ ባቢሎን አወረዳቸው።

ቅዱስ ኤርምያስን ግን ትሩፋን (ከመከራው የተረፉት) ይዘውት ወደ ግብፅ ወረዱ እንጂ አልተማረከም።

በዚያም ተአምራትን አድርጎ አራዊትን አጥፍቷቸዋል። ትንሽ ቆይቶ ግን እውነተኛ አባት፣ ነቢይ፣ መምህርም ነውና ወደ ሕዝቡ (ወደ ባቢሎን) ወርዷል።

ሰባው ዘመን ሲፈጸም እግዚአብሔር እንደ ቃል ኪዳኑ በኤርምያስ መሪነት እሥራኤል ወደ ኢየሩሳሌም ተመለሱ። አሁንም ግን ክፋታቸውን ይተው ዘንድ ፈቃደኞች አልነበሩምና ኤርምያስ ገሠጻቸው።

ስለ እነርሱ ሲል 70 ዘመን ያለቀሰውንና ምትክ የሌለውን አባታቸውን ወግረው ገደሉት።


(ሥዕሉን ተመልከቱት። ድንቅ ነው። ጥቅሱንም ገብታችሁ አንብቡት። ትንቢቱ ቀጥታ ለመድኃኔዓለም ቢሆንም...የጥር 15 2016 መግለጫን ልብ ይሏል)
በወላይታ ዞን ቦሎሶ ሶሬ ወረዳ ዩካራ ቀበሌ ዶንጎ ቀጠና ላይ በቀን 1/9/2016 ዓ.ሞ ከቀኑ 11:00 ጀምሮ በረዶ ቀላቅሎ  በጣለው ከባድ ዝናብ ምክንያት በበልግ ስብልና ሌሎች ንብረቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል።
❗️Ukrainian militants shell civilian district in Russia’s Belgorod

There is no official information about the number of injuries yet, Governor Gladkov said.
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Local media publishes moment Belgorod apartment building roof collapses — Unverified footage
2024/09/25 14:20:19
Back to Top
HTML Embed Code: