Telegram Web Link
ልብ ብለህ አድምጥ
- ኢትዮጵያዊነትን በልቡ ያነገሠ 
- ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ እምነትን በልቡ ላይ የተከለ
- ሰንደቋን የወደደ ያከበረ
ማንም ይሁን ማንም የትም ይሁን የት
ለኢትዮጵያዊነት ፍቅርና ክብር ያለው
ለተዋሕዶ እምነት ማዳንና እውነተኛነት
እምነቷም ትክክል ስለመሆኗ ስለ ቀናነቷ እግዚአብሔርም ዋጋ የከፈለላት መሆኗን በትክክል የተረዳ
ግራ ቀኝ የማይል
ምልክቷን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ሰንደቋን በልቡ የተከለ የለበሳት ማንም ይሁን ማንም ይድናል፡፡

ይሄው እንግዲህ ምስክርነት   እየነገርንህ ነው፡፡
ዛሬ በየበረሃው አሁን ይህንን ሥርዓት እንጥላለን ብለው ብዙ ሰዎች ተንቀሳቅሰውበታል፡፡በውጭም በአገር ውስጥም በምንም
አንዳንድ ጊዜ ይደንቀኛል ሳያቸው ባንዲራዋን ለብሰው በየበረሃው መሳሪያቸውን ይዘው አንግበው ከዚህ መንግሥት ጋራ እፋለማለሁ ብለው የሚወጡ የሚወርዱ፦ አትጠራጠር እንደ እነዚህ ዓይነት ሰዎች እኮ
ተስፋ ያደረጉት ማንን እንደሆነ አውቀሃል??
ኢትዮጵያዊነታቸውን ነው፡፡
ተስፋ ያደረጉት እኮ እግዚአብሔርን ነው፡፡
ተስፋ ያደረጉት ተዋሕዶ ኦርቶዶክስ  እምነትን ነው ፡፡
እምነትን ነው የጨበጡት ፡፡
ተስፋ ያደረጉትና የለበሱት ከልባቸውም አልፈው በላያቸው  አንገታቸው ላይ የጠመጠሙት የኢትዮጵያን ባንዲራ ሰንደቋን ነው፡፡አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን ነው፡፡
ያሸንፋሉ አትጠራጠር፡፡
እግዚአብሔርን ይዞ የማያሸንፍ አለ?
ምልክቱን እግዚአብሔር ያከበረውን ሰንደቅ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩን የቃል ኪዳን ምልክቱን የያዘ አያሸንፍም ብለህ ታስባለህ? ያሸንፋል፡፡
ኢትዮጵያዊነትን ልብሱ እና ሀብቱ ያደረገ የሚወዳት ያሸንፋል፡፡ ምን ትጠራጠራለህ ቢሰዋ እኮ በሰማዕትነት  በክብር በእግዚአብሔር እጅ ነው የሚሄደው በክብር መጣህ ልጄ ተሰዋህ ለእውነት ና የኔ ልጅ ብሎ ነው በክብር የሚቀበለው ፡፡

⚡️የሉቃስ ት/ት ክፍል 11ለ
🟢 🟡 🔴
ሚያዝያ 4 | #ቅዱሳን_ነገሥት_አብርሃ_ወአጽብሓ መታሰቢያቸው ነው፨

እናትና አባታቸው ንግሥት ሶፍያንና ንጉሥ ታዜር ይባላሉ። ልጅ ስላልነበራቸው ስእለት ቢሳሉ እግዚአብሔር በበረከት ስለጎበኛቸው ሶፍያ ጸነሰች፡፡

የጽንሷም ወራት በተፈጸመ ጊዜ ታኅሣሥ 29 ቀን በ 312 ዓ.ም መንታ ልጆችን ወለደች፡፡ ሕጻናቱ ከተወለዱበት ቀን ጀምሮ እንደ አዋቂ ሰው በፍቅር ተጠምደው አንዱ ለሌላው በማሰብ ጡት እየያዙ አንደኛው ለሁለተኛው ይሰጣጡ ነበር።

እንደ ሕጻናት ጸባይ አላለቀሱም። ነገር ግን "ይትባረክ እግዚብሔር አምላከ አበዊነ - የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን" እያሉ ያመሰግኑ ነበር።

ታላቁ አብርሃ በ364 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን እሑድ ዕለት ዐረፈ። ከ13 ዓመት በኋላ ታናሹ አጽብሓ በ379 ዓ.ም ጥቅምት 4 ቀን ዐረፈ።

በአንድ መንበር ነገሡ። ልደታቸውም ሆነ ሞታቸው አንድ ቀን ነው (የዕረፍታቸው ዓመቱ ይለያይ እንጂ) የተቀበሩበት ቦታም አንድ ነው።

የንግሥና ስማቸው ኢዛናና ሳይዛና ይባላል። በዘመናቸው ፍትሕ አልተጓደለም፤ ድሀ አልተበደለም፤ እንደ ነገሥታት ሥርዓት በቤታቸው በር ዘብ አላቆሙም።

ጌታችንም ለእነዚህ ቅዱሳን ነገሥታት ቃል ኪዳን ገብቶላቸዋል፦

🍀 ዝክራችሁን የዘከረ፣ ሥማችሁን የጠራ እምርላችኋለሁ፡፡

🍀 በስማችሁ ቀዝቃዛ ውኃ ያጠጣ እኔ የሕይወት ውኃ አጠጣዋለሁ፡፡ በስማችሁ ለተራበ እንጀራ ያበላ እኔ የሕይወትን እንጀራ አበላዋለሁ።

🍀 በስማችሁ ቤተ ክርስትያን ያሳነጸ በመንግሥተ ሰማያት ቤት እሰጠዋለሁ፡፡ በስማችሁ ማኅሌት የቆመ የመላእክትን ማኅሌት አሰማዋለሁ በማለት ቃል ኪዳን ሰጥቷቸዋል።

አምላከ አብርሃ ወአጽብሓ "ድሃ ተበደለ፣ ፍርድ ተጓደለ" የሚል ዳኛ፣ ሃይማኖቱ የቀና መሪን ፈጥኖ ያምጣልን።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
#ሚያዝያ_5 #ቅዱስ_ያሬድ ማኅሌታይ የልደቱ በዓል ነው፨
🟢🟡🔴
ሚያዝያ 5

ታላቁ ማኅሌታይ ካህኑ ቅዱስ ያሬድ ከእናቱ ቅድስት ክርስቲና (ታውክልያ) ከአባቱ ከቅዱስ አብዩድ (ይስሐቅ) በአኵስም (አክሱም) በ505 ዓ.ም ሚያዝያ 5 ቀን ተወለደ።

አባቱ የአክሱም ጽዮን ቄሰ ገበዝ ነበር። በዚያን ጊዜ የብሉያትና የሐዲሳት መምህራንና ተማሪዎች የሚገኙት አክሱም ጽዮን ነውና የአኵሱም ቤተ ቀጢን (ቤተ ጉባኤ) መምህር የነበረው የእናቱ ወንድም አጎቱ መምህር ጌዴዎን ይባል ነበር።

ቅዱስ ያሬድ የሰባት ዓመት ብላቴና በኾነ ጊዜ አባቱ ስለ ሞተ ትምህርት ቤት ከመግባቱ በፊት በዚያ ዘመን አጠራር ለጌታው ዐደረ።

ጌታውም የዐፄ ገብረ መስቀል ቢትወድድ አዛዥ ዜና ገብርኤል ይባላል። ያሬድን ዐቅሙ ለጉልበት ሥራ እንዳነሰ አይቶት "አንተ ልጅ ጋሻ ቢያስይዙህ አትችል፤ ሾተል ቢያሸክሙህ አይሆንልህ ለምን ከዚህ መጣህ?" ብሎ መለሰለት። ከዚያ በኋላ ከአጎቱ ዘንድ ሔደ።

መምህሩም "ከዚህ የመጣህበት ምክንያት ምንድን ነው?" አለው። እርሱም "መጽሐፍት እማራለኹ ብዬ ነው የመጣኹት" አለው። መምህር ጌድዎንም ዐቅሙንና ዕውቀቱን በመገመት ለተማሪዎች "በሉ ፊደል አስቆጥሩት" አላቸውና ትምህርቱን ጀመረ።

ኾኖም ቃለ እግዚአብሔርን የመቀበል ችሎታው ደካማ ስለነበር አብረው የሚማሩትም ሕፃናት "ሰነፍ ያሬድ ዕንጨት ስበር ውሃ ቅዳ" እያሉ አፌዙበት፤ ቀለዱበት።

አጎቱ ጌዴዎንም ከትምህርቱ ድክመት የተነሣ በጨንገር (በአለንጋ) ቢገርፈው ሕፃኑ ያሬድም በዚህ ተበሳጭቶና ተስፋ ቆርጦ ከአክሱም ከተማ ወጥቶ ወደ እናቱ መንደር ወደ መደባይ ወለል ደረሰ። ለጥሙ ከምንጭ ውሃ ጠጥቶ ለድካሙ ከዛፋ ጥላ ዐረፈ።

በምን ምክንያት ከጓደኞቹ በታች እንደኾነ ሲያስብና ሲያሰላስል ሲያዝንና ሲተክዝ ከቆየ በኋላ እግዚአብሔር አንድ የሚያጽናና ምልክት አሳየው። ይኸውም አንድ ትል የዛፏን ፍሬ ለመመገብ ፈልጎ ወደ ላይ እየወጣና እየወደቀ ተደጋጋሚ ሙከራ ሲያደርግ ከቆየ በኋላ በሰባተኛው ጊዜ ወደ ዛፋ ወጥቶ ፍሬዋን ሲመገብ ተመለከተ።

ተማሪ ያሬድም ከዚህ ትል ትዕግሥትን፣ ጽናትን፣ ጥረትን፣ ስኬትን ትምህርት ወስዶ እኔም እኮ ተስፋ ሳይቆርጥ ብዙ ጥረት ካደረግኹ እግዚአብሔር ያሳካልኛል ብሎ በተስፋ ተጽናንቶ እንደገና ወደ መምህሩ በመመለስ ትምህርቱን ለመቀጠል ወሰነ። ወደ መደባይ ያደረገው የነበረውን ጉዞ ሠርዞ ወደ አክሱም ከተማ ወደ መምህሩ ጌድዮን ጉባኤ ቤት ተመለሰ።

በመጸጸት አጎቱን "አባቴ ስለተቆጣኸኝና ስለገረፍከኝ ተበሳጭቼ ሔጄ ነበር። ነገር ግን በመንገድ ላይ እግዚአብሔር ስላስተማረኝ ተጸጽቼ መጥቻለኹ። ከእንግዲህስ ወዲህ እየተቆጣኽና እየገሠጽህ አስተምረኝ" ሲል አሳቡን ሳይደብቅ ገለጸለት።

አጎቱም ያሬድ ተጸጽቶ በመመለሱ በጣም ተደስቶ ዐይነ ልቡናውን ያበራለት። ዘንድ ፈጣሪውን እያለቀሰ በለመነለት ጊዜ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ለያሬድ ዕውቀትን ገለጸለት።

የያሬድ ኅሊናው ተከፍቶለት መዝሙረ ዳዊትን፣ ውዳሴ ማርያምን፣ መሓልየ ነቢያት፣ መሐልየ ሰሎሞንን፣ መጻሕፍተ ብሉያትንና ሐዲሳትን ንባባቸውን እስከ አገባባቸው አወቀ።

ቅዱስ ያሬድ ቅዱሳት መጻሕፍትን በቃሉ ይዞ ሲያስተምር ሳለ የትምህርቱን ጥራት፣ የሃይማኖት ጽናት፣ ደግነቱንና ትዕግሥቱን፣ ትሕትናውና ተልኮውን በመምህሩና በካህናቱ ተመስክሮለት የአክሱም ጳጳሱ አባ ዮሐንስ ሢመተ ዲቁና ሾመው።

ቅዱስ ያሬድ የታላቋ የአክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አጋልጋይ ዲያቆን ኾነ።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Audio
🇨🇬መግለጫ ከራዕይ ዮሐንስ 20
   05-08-2016 ዓ.ም
🟢 🟡 🔴
ሚያዝያ 6 | #የቅዱሳን_አዳምና_ሔዋን የዕረፍታቸው መታሰቢያ ነው፨

ጌታችን እግዚአብሔር ሥነ ፍጥረትን በዕለተ እሑድ መጋቢት 29 ቀን ጀመረ።

፩. በዕለተ እሑድ ዓለምን ካለመኖር ወደ መኖር አምጥቶ 8 ፍጥረታትን ፈጠረ፦

4ቱን ባሕርያተ ሥጋ
🔥እሳት
💦ውኃ
💨 ነፋስ
🌐 መሬት፣
መላእክትን፣ 7ቱን ሰማያት፣ ብርሃንን፣ ጨለማን ፈጠረ።

፪. [መጋቢት 30 ሰኞ] 1 ፍጡር፦ ጠፈር
፫. [ሚያዝያ 1 ማግሰኞ] 3 ፍጥረታት፦ እዝርዕት፣ አትክልት፣ ዕፅዋት

፬. [ሚያዝያ 2 ረቡዕ] 3 ፍጥረታት፦ ፀሐይ፣ ጨረቃና ከዋክብት
፭. [ሚያዝያ 3 ኀሙስ]፦ 3 ወገን የየብስ እንስሳትን

፮. [ሚያዝያ 4 ዓርብ] 3 ወገን የባሕር እንስሳትን ፈጥሯል። እነዚህን ቢደምሯቸው 21 ይሆናሉ።

ሚያዝያ 4 ቀን፥ አርብ ዕለት የእግዚአብሔር 22ኛውና የመጨረሻው ፍጥረት የሰው ልጅ ነውና ከ4 ባሕርያተ ሥጋ 5ኛ ባሕርየ ነፍስን አዋሕዶ ፈጥሮታል።

ከፍጥረታቱ አልቆ፣ በአርአያውና በአምሳሉ ከመፍጠሩ ባለፈ በነፍስ ሕያው አድርጎ በመንፈስ ቅዱስ አክብሮ ፈጥሮታል። ከዚያም ቅዱሳን መላእክት አዳም በተፈጠረ በ40 ቀኑ፣ ሔዋን በተፈጠረች በ80 ቀኗ የብርሃን ልብስ አልብሰው፦

"አዳምና ሔዋንን የፈጠረ እግዚአብሔር በባሕርዩ ቅዱስ ነው" እያሉ እየዘመሩ ወደ ገነት አስገብተዋቸዋል።

አባታችን አዳም፦

🍀 በኩረ ነቢያት
🍀 በኩረ ካህናት
🍀 በኩረ ነገሥትም ነው።

በርሱ ስህተት ዓለም ወደ መከራ ቢገባም ወልድን ከዙፋኑ የሳበው የአዳም ንስሐና ፍቅር ነው።

አባታችን ለ100 ዓመታት የንስሓ ለቅሶን አልቅሷል። ስለዚህ አባታችን አዳም ቅዱስ ነው። ከሌሎቹ ቅዱሳን ቢበልጥ እንጂ አያንስም።

ለአባታችን አዳም የተናገርነው ሁሉ ለእናታችን ሔዋንም ገንዘቧ ነው። ሚያዝያ 6 የሁለቱም የዕረፍታቸው መታሠቢያ ነው።


T.me/Ewnet1Nat
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሰበር መረጃ

ኢራን  እስራኤል ላይ የድሮን ጥቃት ከፈተች

ዛሬ ለሊቱን በተሰማው ዜና ኢራን እስራኤልን በድሮን (ሰው አልባ አውሮፕላን) ማጥቃት ጀምራለች። የሚሳኤል ጥቃትም እንደሚኖር ኢራን ገልጻለች።

እስካሁን ድረስ ከ100 በላይ የድሮን ጥቃቶችን እንደሰነዘረች ተሰምቷል።

የእስራኤል ጦርም የኢራን ድሮኖች ወደ እስራኤል እየተላኩ መሆኑን አረጋግጧል።  በትንሹ ከ100 በላይ ድሮኖች የእስራኤል አየር ክልል ሳይደርሱ መከላከል እንደተቻለ ገልጿል።

የአሜሪካ እና እንግሊዝ ጦርም እስራኤልን ለመከላከል የተላኩ ድሮኖችን መትተው እንደጣሉ ተዘግቧል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሊባኖስ ያለው ሄዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል የሚሳኤል ጥቃት እየፈፀመ ሲሆን የየመኑ ሁቲ ደግሞ እስራኤል ላይ የድሮን ጥቃት ከፍቷል።
Forwarded from Biruk
🟢🟡🔴
ኢትዮጵያ
¯¯¯¯¯¯¯¯
የቅድስት ሥላሴ የክብራቸው መገለጫ እና መመስገኛ ምድር

T.me/Ewnet1Nat
Audio
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን መግለጫ
ለኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን ቤተሰቦች ብቻ!
ሚያዚያ/8/2016 ዓ.ም
🟢 🟡 🔴
#ሚያዝያ_9

🍀 ለዘጠኝ ዓመት በባሕር ውስጥ ገብተው ቁልቁል ተዘቅዝቀው ለኢትዮጵያ የጸልዩት ታላቁ ጻድቅ #አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ እና

🍀 የእግዚአብሔርን ምስጋናን ከአፉ ፈጽሞ የማያቋርጥ፣ ከ45 ዓመታት ጽኑ ተጋድሎው በኋላ ወደ ብሔረ ብፁዓን ተነጥቆ ተወስዶ የቅዱሳንን አኗኗራቸውንና ገድላቸውን አይቶ የጻፈልን ታላቁ አባት #አባ_ዞሲማስ የዕረፍት በዓላቸው ነው።
አልፋና ዖሜጋ የንጽጽርና የትምህርት መገኛ አደባባይ
Photo
#ሚያዝያ_9
#አባ_ዞሲማስ

የከበረ ቀሲስ ዞሲማስ ከፍልስጥኤም ሰዎች ወገን ነው። ወላጆቹም ደጋጎች ክርስቲያኖች ናቸው። ይህንን ጻድቅ በወለዱት ጊዜ አምስት ዓመት አሳደጉት። ከዚያም የቤተክርስቲያን ትምህርትን የሀይማኖትንም ምስጢር ሕግና ሥርዓትንም እያስተማረ እንዲያሳድገው ለአንድ ሽማግሌ መምህር ሰጡት።

ያ ሽማግሌም ተቀበሎ ልጁ አደረገው። ትምህርቱንም ሁሉ አምላካዊ ጥበብ ሀይማኖትንም አስተምሮ አመነኰሰው። ዲቁናም አሾመው።

ሲበላም ቢሆን ሁልጊዜ ከአፉ ምስጋናዎችን አያቋርጥም። በዚያ ገዳም 45 ዓመት በተፈፀመለት ጊዜ ቅስና ተሾመ። ተጋድሎውንም ጨመረ።

በተጋድሎውም ማንም ምድራዊ የማይጎበኛትን ብሔረ ህያዋንን ጎብኝቷል።
🍀

በዚህ ቀን ብሔረ ብጹዐን ውስጥ የሚኖሩ ጻድቃን ይታሠባሉ። በሃይማኖት ትምህርት 5 ዓለማተ መሬት አሉ። እነሱም አቀማመጣቸው ቢለያይም ከላይ ወደ ታች፦

1. ገነት (በምሥራቅ)
2. ብሔረ ሕያዋን (በሰሜን)
3. ብሔረ ብጹዐን (ብሔረ - አዛፍ - እረፍት) {በደቡብ}
4. የእኛዋ ምድር (ከመሐል) እና
5. ሲዖል (በምዕራብ) ናቸው።

ከእነዚህ ዓለማት ባንዱ የሚኖሩ የብሔረ ብጹዐን ጻድቃን፦

▸ ኃጢአትን የማይሠሩ፣
▸ ለ1,000 ዓመታት የሚኖሩ፣
▸ ሐዘን የሌለባቸው፣
▸ በዘመናቸው 3 ልጆችን ወልደው (2 ወንድና አንድ ሴት) ሁለቱ ለጋብቻ፣ አንዱን ለቤተ እግዚአብሔር አገልግሎት የሚያውሉ ሰዎች ናቸው።

ቅዱሳኑ ወደዚህ ቦታ የገቡት በነቢዩ ኤርምያስ እና በቅዱስ እዝራ ዘመን ሲሆን አንዴ የተወሰኑት በዘመነ ሰማዕታት ወጥተው በዚህ ቀን ተሰይፈዋል።

በመጨረሻ ግን በሐሳዌ መሲሕ ዘመን ወጥተው ሰማዕትነትን ይቀበላሉ።
🍀

#አቡነ_እስትንፋሰ_ክርስቶስ

አባታቸው #ቅዱስ_መልአከ_ምክሩ ሲሆን የእናታቸው #ቅድስት_ወለተ_ማርያም ይባላሉ፡፡ ሁለቱም ደጋጎች እግዚአብሔር እንዳዘው በሕጉ ጸንተው ተስማምተው የሚኖሩ ነበሩ።

በጸሎቱ ሰውን የሚጠቅም በጻድቃንም ዘንድ የተመረጠ ልጅን ይሰጣቸው ዘንድ ዘወትር ወደ እግዚአብሔር እና ወደ ድንግል ማርያም ይለምኑ ነበር። ልመናቸውንም ሰምቶ አባታችን አቡነ እስትንፋስ ክርስቶስ ሚያዝያ 8 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 8 ቀን ተወለዱ። ሚያዝያ 9 ደግሞ የዕረፍታቸው በዓል ነው።

ጌታችንም ቃል ኪዳን ሲሰጣቸው፦ "ብዙ ኃጢአት የሠራ አረመኔም ቢሆን መታሰቢያህን ያደረገው እምርልሃለሁ፣ ዝክርህን የሚዘክር በዓልህን የሚያከብር ሰው ቢኖር እናትና አባቱ ሞተው ወደ ሲኦል ከወረዱ በኋላ መውጫ ከሌለው ከሥቃይ ቦታ ከሲኦል ስለ አንተ ብሎ አወጣቸዋለሁ" ብሏቸዋል።

T.me/Ewnet1Nat
የኛ እምነት የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ከሁሉም የምትለይ ናት፡፡ ይህንን ጨብጣችሁ ያዙ፡፡ ሁሉም ደግሞ የሚጠላት ናት የኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ቃሉን ልብ ብላችሁ አስተውሉ ፡፡ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ዋናው መሰረቱ ያ ቃል ነው፡፡ ብዙዎች ስለ ኦርቶዶክስ እያነሱ ኦርቶዶክስ ነን የሚሉም አሉ፡፡ በዓለም ላይ ብዙ አሉ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ትለያለች የኛ እምነት ትለያለች ፡፡
በምድር ላይ እንደ አሜባ ተባዝተው በድርጅትነት እና በተለያየ የእምነት ስያሜ ምድርን ከከደኑት ከ35,000 በላይ የእምነት ተቋማትን እና የእምነት ስያሜዎች ውስጥ የማትደመር ናት የእኛ እምነት!!! የምትለይም ናት የማትገናኝ የማትመሳሰልም ናት መሰረቷም ጥንት የተመሰረተችበትም እውነት ቸሩ መድኃኔ ዓለም የተከለው እውነት በእውነት እና በመንፈስ በእምነት የተመሰረተች ከጥንት ከብዙ ሺህ ዘመናት ጀምሮ የጸናች እግዚአብሔርን በመፈለግ በጥቂቱም ተነግሯቸው አባቶቻችን አብዝተው እግዚአብሔርን በመፈለግ በዛም ጉዟቸው እግዚአብሔርም ወዷቸው በታላቅነት በተጋድሎ ያለፉባት እግዚአብሔር ደግሞ በጣም በስስት የሚያያት ጥቂት ሕዞቦችን ያቀፈች ስማዊ ተዋህዶ ኦርቶዶክሶችን አይደለም የምላችሁ ሆነው እየኖሩበት ያሉትን እውነተኞቹን ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነትን እኒህን ነው፡፡ እያነሳኁላችሁ ያለሁት በእምነት የሚመስሏችሁን ሆነው የሚጓዙትን እያልኩ ነው ያለሁት ፡፡
በአመሰራረቷም ቸሩ መድኃኔ ዓለም መድሃኒታችን እየሱስ ክርስቶስ የተከላት በደሙ ያነጻት የተቀጠቀጠላት የተገረፈላት የተሰቃየላት ዛሬም በስስት ዓይኑ የሚያያት የኛ ቤተክስስቲያን ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነታችን ናት ኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ እምነት ፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግስት መግለጫ 07/08/2016 ዓ.ም ከ 27፡05 ጀምሮ እስከ 29፡56
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በኤምሬትስ በ75 አመታት ውስጥ ከፍተኛ መጠን ያለው ዝናብ ተመዘገበ

የዱባይ አለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያም በዝናብና ጎርፍ ምክንያት በረራ ለማስተናገድ መቸገሩ ተገልጿል።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
2024/09/27 11:19:43
Back to Top
HTML Embed Code: