Telegram Web Link
➦'' ከመብል  ከመጠጥ  ታቅቦ የሚጾም አንድ ሰው በሐሜት  የሰዎችን ሥጋ መብላት ከቀጠለ ይህ ጾም የግብዝነት ነው።" (ከሃሜት ተጠበቁ!)
      ማር ይስሕቅ በመጽሐፍተ መነኮሳት

➦እስመ በጾም ኤልያስ ሰማያተ ዐርገ ዳንኤል ድኅነ እምአፈ አናብስት ወሶስና ድህነት እምእደ ረበናት [ ኤልያስ በጾም ወደ ሰማይ ዐረገ ዳንኤልም ከአናብስት አፍ ዳነ ሶስናም በጾም ከሐሰት ምስክሮቹ ከረበናት እጅ ዳነች።] (ቅዱስ ያሬድ)

#ጾመኢየሱስ
🟩 🟨 🟥
#የታሪክ_ማስታወሻ
#ሊቀ_ሊቃውንት_አያሌው_ታምሩ ገና በፊቱኑ በቤታቸው #የቃልኪዳን_ሰንደቁን ይሰቅሉ እንደነበር፦

❝ ነሐሴ 1 ቀን 1995 ዓ.ም፥ በጾመ ፍልሰታ የመጀመርያ ቀን ፎቶ ግራፍ ላነሣቸው አለቃ ቅጥር ግቢ ተገኘሁ። ለቀኑ 9፡30 ቢሆንም አለቃ ጸሎታቸውን ካሳረጉ በኋላ ተጠራሁ።

የጸሎት ቤቷ ውስጥ #የቅዱስ_ጊዮርጊስ እና #የእመቤታችን ሥዕል፣ የሻማ መቅረዝ፣ የዕጣን ሙዳይ፣ የጸበል ጄሪካን፣ መጽሐፍ ቅዱስ፣ መቋሚያ፣ መቁጠሪያ፣ ነጭ ጭራ፣ ከዘራ (ትርከዛ)፣ ዓይኔን የሳበኝ #አረንጓዴ_ቢጫ_ቀይ_ባንዲራ በግልጽ ይታያል።

አለቃም አያይዘው " #የኢትዮጵያ_ባንዲራ #መንፈሳዊ_መልእክት ስለሆነና ለኢትዮጵያም የረጅም ጊዜ የነጻነት አርማ ስለሆነ በዚህ ጊዜ 'ለአባታችን ለጻድቁ ለኖኅ  የሰጠኸውን ቃል ኪዳን አስበህ አገርህን ኢትዮጵያን አትርሳ' እያልኩ ለመጸለይ እንዲመቸኝ ነው

የኢትዮጵያ ክረምት በኖኅ ቃልኪዳን ላይ የተመሠረተ ነው። ስለዚህ ክረምቱ ከሰኔ ጀምሮ በመስከረም ወር ይጨርሳል። በዚህ መሠረት ኢትዮጵያ እግዚአብሔርን ብቻ ስታመልክና ስታገልግል በኖረችበት ዘመን ሁሉ ክብሯ አልተገሰሰም፤ ሀብቷ አልቀነሰም። ይህን ሁሉ ኢትዮጵያዊ እንዲያውቀው እፈልጋለሁ። ...❞

📝 ቁምነገር መጽሔት 1995 ዓ.ም

አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
▯www.tg-me.com/Ewnet1Nat
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የእኛ ዘመን አያሳየን ጉድ የለውም !

ወቅቱ ቤተክርስቲያን ከመቸውም በላይ ወደእግዚአብሔር ጩኸቷን የምታሰማበት ፤ ከቦታ ቦታ እንኳን መንቀሳቀስ ብዙም የማይፈቅደው ታላቁ የጾም ወቅታችን ጾመ ኢየሱስ ( ሁዳዴ ጾም) አቢይ ጾም ነው። እና የቤተክርስቲያን ተጠሪዎቻችን ናቸው የምትሏቸው፤ እነሱም ሳያፍሩና ሳይፈሩ "የቤተክርስቲያን የበላይ ጠባቂና ተጠሪዎቿ ነን" የሚሉ "ጳጳሳቶቻችሁ" ከአስመሳይዋ የዲያብሎስ ወኪል የ8ኛው ሺ ፍጻሜ ማሳያ አዳነች አበቤ ጋር  ወደ ሙስሊሞች መንደር ለማፍጠር ጎራ ብለውላችኋል።  እንግዲህ ሙስሊሞች ራሳቸውን ስለሚያውቁ እኛ ጋር አይመጡም በእኛ ቤት አናት ላይ ፊጢጥ ያሉ የጉልበት ምንደኛ "ጳጳሳትና ካህናት" ግን ከአንድም ሁለት ሦስቴ የሙስሊሞች በአል አድማቂ የበኣል ካህናት ሆነዋል ። ለማንኛውም በሚድያ የሚቀርበውን አይተን ተበሳጭተን... የማይቀርበውን አስበን ደግሞ እያዘንን እያለቀስን ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ እባክህ ፍረድ እንላለን !! አሜን ጌታ ሆይ ቤትህን በሚያፈርሱ ምንደኞች ተኩላዎች ላይ ለምዳቸውን ግፈፍ ፍርድህንም ግለጥ አሜን!!

#ለታሪክ_ትቀመጥ !
#መጋቢት_20_2016
www.tg-me.com/Ewnet1Nat
በድሬዳዋ ከተማ ትናንት ወደ ማታ አካባቢ ከባድ ዝናብ መጣሉን ተከትሎ በከተማዋ ድንገተኛ ጎርፍ ተከስቶ የንብረት ጉዳት ደርሷል። ለጉልት ገበያ ሲያገለግሉ የነበሩ በሸራ የተሰሩ ቤቶች በጎርፉ ተወስደዋል።
እስካሁን በሰው ላይ የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ የታወቀ ነገር የለም።
🔔 በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ኢሉ ወረዳ የአስጎሪ ርጳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አገልጋዮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ።
በታጣቂዎች የተገደሉት አገልጋዮች ስም:-
1.ቀሲስ ቸርነት ብዙወርቅ ቄሰ ገበዝ
2.ቀሲስ ሳሙኤል ወደጆ ቀዳሽ ካህን
3.መሪጌታ ያሬድ የደብሩ መሪጌታ እንዲሁም
4.ዲ/ን ቤዛ ባዬ የደብሩ ጠቅላላ አገልግሎት ናቸው።

በተለይም የደብሩን መሪጌታ መጀመሪያ እጃቸውን ቆርጠው ለውሻ በመስጠት ከዚያ በኋም እያንዳንዱን አካላቸውን በገጀራ በመቆራረጥ እንደገደሏቸው የዐይን እማኞች ገልጸዋል። ሌሎችም አገልጋዮች በተመሳሳይ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ እንደተገደሉ ለማወቅ ተችሏል።
🔔 በአፋር ክልል፣ በአፋር እና ኢሳ ሱማሌ ጎሳዎች መካከል በድጋሚ በተያዘው ሳምንት ግጭት ማገርሸቱን ታውቋል። ግጭቱ የተከሰተው፣ በገቢ ረሱ ዞን (ዞን ሦስት) አሚባራ ወረዳ ውስጥ አፋርና ሱማሌ ክልሎች በሚወዛገቡበት ገዳማይቱ ቀበሌ እንደኾነ እና። በግጭቱ ቁጥራቸው ያልታወቁ ሰዎች ሳይገደሉና ሳይቆሰሉ እንዳልቀሩ ተነግሯል። ካለፉት ጥቂት ወራት ወዲህ፣ በአፋሮች እና ኢሳ ሱማሌዎች መካከል የሚደረጉ በትጥቅ የተደገፉ ግጭቶች ተበራክተዋል።[ዋዜማ]
🟢🟡🔴
መጋቢት 21 | ከዐለት ላይ ውኃ እያፈለቁ ድውያንን የሚፈውሱት #አባ_ሊባኖስ_ዘመጣዕ ዓለምን ፍጹም በመናቅ መንነዋል።

እርሳቸውም የአባታችን የተክለ ሃይማኖት ገዳም ‹‹ደብረ ሊባኖስ›› በስማቸው የተሰየመላቸው ናቸው። አባ ሊባኖስ አባታቸው አብርሃም እናታቸው ንግሥት ይባላሉ።

እነርሱም በወርቅና በብር እጅግ የበለጸጉ ሮማዊ ናቸው፡፡ ልጃቸውን አባ ሊባኖስን በሃይማኖት በምግባር ኮትኩተው ካሳደጓቸው በኋላ ዕድሜያቸው ሲደርስ በቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ያጋቧቸው ዘንድ ከቁስጥንጥንያ አገር ሚስት ባመጡለት ጊዜ እርሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ።

ወደጫጉላቤትም መግባትን እምቢ አለ፡፡ በዚህም ጊዜ ነቢዩ ሳሙኤልን እንደጠራው አባታችንንም እግዚአብሔር ሦስት ጊዜ በስማቸው ጠራቸውና ‹‹ከአባትህ ተለይ አንተ የመንግሥተ ሰማያት ሙሽራ ነህ እንጂ የዚህ ምድራዊ ዓለም ሙሽራ አይደለህም›› አላቸው።

አባታችንም ‹‹ወዴት እሄዳለሁ? ምንስ ላድርግ?›› ባሉ ጊዜ ወዲያው የታዘዘ መልአክ በሌሊት መጥቶ ከአባታቸው ቤት አውጥቶ ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስ ዘንድ አደረሳቸው።

ታላቁ አባት አባ ጳኩሚስም ለአባ ሊባኖስ በዓት በመስጠት ገዳመ ሥርዓትን፣ አስኬማ መላእክትን፣ ቅናተ ዮሐንስን አስተምረዋቸው አመነኮሷቸውና ከ8ቱ ቅዱሳን ጋር እንዲገናኙ አደረጓቸው።

ከዚህም በኋላ ያ ከአባታቸው ቤት ወስዶ አባ ጳኩሚስ ገዳም ያደረሳቸው ያ መልአክ ድጋሚ ተገለጠላቸውና ‹‹ወደ ቅድስት ሀገር ኢትዮጵያ ሂድና ተጋድለህን በዚያ ፈጽም ዝናህ በስፋት ይነገራል፣ ለብዙዎችም አባት ትሆናቸዋለህ›› አላቸው።

ቀጥሎም ራሱ መልአኩ ወደ ኢትዮጵያ አመጣቸውና በአክሱም ተቀመጡ፡፡ በዚያም ብዙ ከተጋደሉ በኋላ ወደ ሸዋ መጡና ወንጌልን ዞረው አስተምረው ብዙ ድውያንን ፈውሰው ከዓመታት ቆይታ በኋላ ተመልሰው አክሱም ሄዱ።

T.me/Ewnet1Nat
ኢትዮጵያ "መጻጒዕ"ዋ፥
መከራ አልጋዋ!

— አለቃ አያሌው ታምሩ —
እመአምላክ የእኛ እናት
---------------------------------
ስሟ የሚጣፍጥ እንደ ማር ወለላ
ጸጋን የተሞላ የለም ከእርሷ ሌላ
ወደ ሲኦል ገብቶ በእሳት ከሚበላ
ማርያም ማርያም ይበል ዓለም በጠቅላላ ።
-------------------------------------------
ቢያወሩ ቢያዜሙ ምድር ከሰማይ ጋር
አንደበት አውጥታ ፀሐይ ብትመሰክር
ጻድቃን ሰማእታት ሊቁ ቢመራመር
ሀይቆች ቀለም ሆነው ቢጻፍ ቢዘረዘር
ጥልቅ እና እረቂቅ ነው የእመብርሃን ነገር
ማንም ያላወቀው ከልጇ በስተቀር
ከሦስቱ ሥላሴ የተሰጣት ክብር
ቢተረክ አያልቅም ይጠልቃል ከባህር!!
-------------------------------------------
እንደ  ማርያም ያለ ጸጋን የተሞላ
ሰማይ እና ምድር ፍጥረታት ጠቅላላ
አንድ ላይ ቢከማች ከደጋ እስከ ቆላ
ማንም አያክልም የጸጉሯን ዘለላ
እመአምላክ ልዩ ናት የነፍሳችን ጥላ
በከንቱ ይጠፋል ድንግልን የጠላ ።
------------------------------------
የልቤ መጽናኛ የነፍሴ መድኃኒት
ቁርስ ምሳ እራቴ የቤቴ በረከት
የሞሶቤ እንጀራ የጓዳየ ሙላት
የአንደበቴ ጣእም የህሌናየ እረፍት
የአርያም ንግሥት የመለኮት እናት
አንች ነሽ ተስፋዬ ኪዳነምሕረት ።
--------------------------------------
ቢጠሩት ቢጠሩት ስሟ የማይሰለች
ልቧ የማይጨክን እርግብ ስለሆነች
ውሃ በጫማዋ ለውሻ ያጠጣች
ለአዳም ዘር ጠቅላላ ዛሬም እየራራች
የበደለን ሁሉ ምራ ታስምራለች ።
---------------------------------------
ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን አዳራሹ አድርጓት
በሆዷ ሲቀመጥ እሳተ መለኮት
ፍጹም ሳትቃጠል የብርሃን እናት
ንጉሡን ስትወልደው በከብቶቹ በረት
በእስትንፋሳቸው እንስሳት ሲያሞቁት
ከሰማያት ወርደው ቅዱሳን መላእክት
የጌታን ትትና ፍቅሩን ተረድተውት
መሬት ላይ ተነጥፈው ሲያቀርቡለት ስብሃት
እግዚአብሔር ከአዳም ጋር ስለታረቀላት
የጠፋው ሲመለስ ድንግልን ደስ አላት ።
------------------------------------------
በማይጠቅም ፍሬ ጠፍተን የመለሰን
ጨለማውን ገፎ ብርሃን ያለበሰን
መስቀል ተሸክሞ ፍቅር የሰበከን
ዲያብሎስን አስሮ ከእስራት የፈታን
እናት እንድትሆነን እናቱን የሰጠን
የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤል ይመስገን ።
-------------------------------------------
እንኳን እኔ ከንቱው የዓለም መሀይም
እጸዋቶች ብዕር ባህር ቢሆን ቀለም
መላእክት ቢጽፉት ድንቅ ክብሯ አያልቅም
የማረባ ከንቱ ወንበደ ብሆንም
በጨነቀኝ ጊዜ ስላት ድንግል ማርያም
ታማልደኛለች ከመድኃኔዓለም ።
------------------------------------------
እኔ መሀይሙ ከንቱ የሆንኩት ሰው
የአንችን ቅድስና ክብርሽን ላልገልጸው
መከተብ ጀምሬ ባወጣ ባወርደው
ሰማይ ሆኖብኛል ቧጥጨ እማልወጣው
ጥበብ ስጭኝና መቸም ከማያልቀው
እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ስምሽን ላወድሰው ።
---------------------------------------------
ሀጢያት ባጎደፈው በክፉ አንደበቴ
ማርያም ማርያም እያልኩ ስጠራሽ እናቴ
ችላ የማትይኝ ፍቱን መድኃኒቴ
በደሌን ሳትቆጥሪ ማሪኝ እመቤቴ ።
-----------------------------------------
ገሀነብ እንዳንገባ ሲዖልን እንዳናይ
እንዳይውጠን ዘንዶው ያነ ነፍሰ ገዳይ
ስምሽን ስንጠራ እራርተሽ ድንግል ሆይ
አማልጅን ከልጅሽ አስታርቂን ከአዶናይ ።
-------------------------------------------
ቁሳቁስ ተወዶ ሰው ከረከሰበት
ፍቅር እንደ ውሃ ከቀዘቀዘበት
የአዳም ዘር እንደ በግ ከሚታረድበት
ርሃብ ጦርነት ስደት ከበዛበት
ትዳር እና ህንጻ ቤት ከሚፈርስበት
ጎሳ ዘረኝነት ከተንሰራፋበት
ከዚህ ክፉ ዘመን ሰላም ከሌለበት
ከዘንዶው ሰውረሽ እመአምላክ የኛ እናት
የኢትዮጵያን ትንሣኤ አሳይን በቅጽበት(3) ።
      ወስብሐት ለእግዚአብሔር
      ወለወላዲቱ ድንግል
      ወለመስቀሉ ክቡር
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
🇨🇬 በእንተ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ሣልሳዊ፦

👑 «...ንጉሠ - ነገሥት ቴዎድሮስ ኢትዮጵያዊ የተዋህዶ ኦርቶዶክስ ልጅ ነው ፡፡ በመልእክቶቹ ሁሉ እንደተናገረው ድሃ ጎስቋላ ሊቅ ያልሆነ ምናምንቴ ሰው ነው ፡፡ ስለሱ መመረጥ የታወኩ ነውም ብለው ለመቀበል የተቸገሩ እንዳሉ ግልፅ ነው ፡፡

👑 በቁጥር ቀላል ያልሆኑ በብዙ ምክንያቶች እራሳቸውን ቴዎድሮስ ነን ብለው አምነው የቆሙ ሰዎች አሉ ፡፡ ይህ ምንም አይደለም ሁሉ ወደፊት ስለሚገለጥ ወደ ብርሃንም ስለሚወጣ እንደዚህ ያሰቡበትንና ያመኑበትን መንገድ ስለሚገለፅ ብዙም ከዚህ በላይ መግለፁ ወቅታዊ አይሆንም ፡፡

👑 ንጉሡና ሌሎችም አባቶች እዚሁ ኢትዮጵያ ውስጥ ነው ያሉት ፡፡ ከዋናው ከተማ ጀምሮ በሁሉም የአገሪቱ ክልል በተለያየ ጉዳይ እየተንቀሳቀሱ ሁሉንም ድርጊት ይከታተላሉ ፡፡ በመገለጡ ሰአት በቀዳማይ ምክትልነትና በምክትልነት በግራና በቀኝ የሚሆኑ በንጉሥ ማእረግ ያሉ ዛሬም አብረውት በሥራው ሁሉ እያገዙትና አብረውም እየሰሩ ነው ፡፡ ሌሎች 37 የሚሆኑ በንጉሥ ማእረግ ያሉ በየባእታቸው ሆነው ፤ በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ሕብረትና አንድነት በሁሉም እያገዙ የሚገኙ ናቸው ፡፡ ሁሉም ሊያውቀው የሚገባው ቢኖር ዘመናዊ መገናኛ እስካለ ድረስ ፤ በቴሌግራም የዮሐንስ ራእይ 20 ቻናል ላይ ስለሁሉም ሁኔታ በቀጥታ የሚገለፅበት ይሆናል ፡፡ የንጉሠ ነገሥቱም ፣ የንጉሦቹም ድምፅ የምትሰሙበት የሚገለጥበት ነው ፡፡ ከዚህ በተረፈ በኢትዮጵያ የአለም ብርሃን መልእክታት በግልፅ የምታገኙት ነው ። ቴሌግራሙም እስካለ ድረስ ነው የሚያገለግለው ፡፡ ከዚህ ውጪ የሚመጣ ነገር የለም ፡፡ ተስፋ የምታደርጉት የኢትዮጵያ ትንሳኤም ሆነ የንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስና አብረውት የሚገለጡት ንጉሦች እንዲሁም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ታላላቅ አባቶች መላውን ዓለም በተዋህዶ እምነት የሚመሩት በይፋ የሚገለፅበት የሚታወቅበት ይኸው መንገድ ብቻ ነው ፡፡ ከዚህ በዘለለ ሌላ እውነት አለን ካላችሁ በርቱ ቀጥሉበት እንላለን ፡፡ ዳኛው በሰማይ በመንበሩ ሆኖ ሁሉንም ስለሚመለከት እንደየታመንበት ፍርዱም ትእዛዙም አብረው ይገለጣሉ ፡፡

👑 በሌላ በኩል -- እንደ እውነቱ ከሆነ እኔን ለምትቃወሙ ቅሬታም የለብኝ እኔ ዛሬም ነገም የምለው የማምነው የምረዳው አምላኬም ያስተማረኝ እውነትና እውነትን ብቻ መግለፅ ነው ፡፡ ስለዚህ እኔ ከሁሉ የማንስ ነኝ ፡፡ በሁሉም ገፅታ ከኔ ትበልጣላችሁ ብዬ አስባለሁ ፡፡ ግን በምን መስፈርት እኔን እንደመረጠ እኔም ስለማልረዳ እናንተ ቅር የተሰኛችሁ ሁሉ መድሃኒያለምን ድንግልን ጠይቁ መልስን ታገኛላችሁ ፡፡ ይህን ያልኩት በዚህ ምክንያት እንዳትሰናከሉ በማሰብ ነው ፡፡

👑 ንጉሥ ዳዊትን ልኡል ሲመርጠው ታላላቅ ወንድሞቹን እንዳላስደሰተ ሁሉ ሳሙኤልንም ግራ አጋብቶአል ፡፡ ጌታ ግን ለሳሙኤል መልስ ሰጥቶታል መልሱም እግዚአብሔር ልብን እንደሚያይ ውጪያዊ ገፅታን እንደማይመለከት አረጋግጦለታል ፡፡ ነቢያትን በተለይም ሃዋሪያትን ጌታ የመረጠው ከተናቀው ሥፍራ እንደሆነ ሁሉም የሚያውቀው ነው ፡፡ በሥራዬ ለእግዚአብሔር ምንም የሠራሁት በምግባሬም ያስደሰትኩበት ሥራ የለኝም ። በአንድ ነገር ብቻ አስቦኝ ይሆናል ብዬ እገምታለሁ ፡፡ እሱም የፈጠረኝን አምላኬን ከከፋው ሃጢያቴ ያዳነኝን እንደሰው የቆጠረኝን አምላኬን ውዳቂ ነው ብላ ያልተወችን እናቴን ድንግልን አብዝቼና በፍፁም ልቤ እወዳቸዋለሁ። ሌላ የማውቀው ሰርቼ ያስደሰትኩበት ምንም የለኝም ፡፡ እውነቱ ይህ ነው ፡፡

👑 እንግዲህ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ ማነው ለምትሉ ሁሉ ፣ ለወዳጅም ለጠላትም ፤ ግራ ገባን ለምትሉ ከላይ ምንነቱን በመጠኑ እንድታውቁት ለማድረግ ጥሬአለሁ ፡፡ ጊዜው ሲደርስ የሱንም የሌሎችንም ማንነት በግልፅ የምታዩበት ጊዜ ይመጣል ፡፡ መታገሥ ነው ፡፡

👑 አንድ ነገር እርግጥ እንዲሆንላችሁ የምፈልገው ሁሉንም እውነት መገለፅም ቢሆን በራእይ ዮሐንስ 20 ቻናል ላይ በልጃችን በተከፈተው ገፅ ላይ የምትሰሙት ይሆናል ፡፡ መልእክታቱም ሁሉ አንዱ የኛ መግለጫ መስመር ናቸው ፡፡ እነዚህም ሁሉ በመከራው ክብደት ቢዘጉ ሌላ መንገድ እናዘጋጃለን ፡፡ በዚያን ሰአት መነቃነቅ ቀርቶ መደበቂያ የሚያጣው ከሃዲው ትውልድ ይጨነቅ እንጂ ! እኛ እውክታ የለብንም ፡፡

👑 ሌላው ጉዳይ ንጉሠ ነገሥት ቴዎድሮስ እኔ ነኝ የሚሉ እጅግ ብዙ ሰዎች እንዳሉ ይገመታል ፡፡ ብዙም ሲናገሩ እየተሰሙ ናቸው ፡፡ እኔም እየሰማሁ ነው ፤ ከመገረም ውጪ ምን ይባላል ፡፡ እርግጥ ነው ሁሉም ወደ ብርሃን ሲወጣ ማ ምን እንደሆነ ልኡልና ድንግል ስለሚገልጡት መታገሥና መጠበቁ መልካም ነው ብዬ አምናለሁ ፡፡

👑 እንግዲህ እውነቱን ለናፈቃችሁ ይኸው እውነቱን ገልፀናል ፡፡ በኛ ዘንድ ትመዘገቡ ዘንድ ባስታወቅነው መሰረት የተመዘገባችሁ ፤ ስለአመንበት መዝግበናል ፡፡ መታወቂያ የወሰዳችሁ መልካም አድርጋችኋል ፡፡ ለአገልግሎት ስለሆነ የወሰዳችሁት በሰአቱ ትጠቀሙበታላችሁ ፡፡ በመታወቂያው ላይ ያለው ፊርማ የኔው መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ፡፡
...»

🇨🇬 ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት ዘጠነኛ መልዕክት ገጽ 49–50
ተጻፈ ታኅሣሥ 21/2013 ዓ.ም
🟢🟡🔴
መጋቢት 23 | ዝክረ #አለቃ_አያሌው_ታምሩ

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ምስክር የሆኑት አለቃ አያሌው ታምሩ፤ ከአባታቸው ከአቶ ታምሩ የተመኝና ከእናታቸው ከወይዘሮ አሞኘሽ አምባዬ፥ በጎጃም ክፍለ ሀገር በብቸና አውራጃ በእነማይ ወረዳ በታላቁ ደብር ወገዳም በደብረ ድማኅ ቅዱስ ጊዮርጊስ ልዩ ስሙ ቤተ ንጉሥ በተባለ ቦታ መጋቢት ፳፫ ቀን ሺሕ ፱፻፲፭ ዓመተ ምሕረት በዕለተ ሆሣዕና ተወለዱ።

ያለፈውንም የወደፊቱንም የሚያውቅ ልዑል እግዚአብሔር ለበለጠ ክብርና አገልግሎት ያዘጋጃቸው ቢሆንም ዕድሜአቸው ለትምህርት ሳይደርስ ገና የሦስት ዓመት ተኩል ሕፃን ሳሉ በፈንጣጣ ሕመም ምክንያት የዐይናቸውን ብርሃን አጥተዋል።

የስምንት ዓመት ዕድሜ ልጅ ሳሉ በዓለ ተክለ አልፋን ለማክበር ከአባታቸው ጋር ወደ ዲማ እንደ ሄዱ በዚያው ትምህርታቸውን ለመቀጠል ስላሰቡ ወደ ቤታቸው አልተመለሱም። በ15 ዓመታቸው የቅኔ መምህር ለመሆን በቁ።
◦◦◦
🍀 አጭር የሕይወት ታሪካቸው👇
https://www.tg-me.com/christian930/3776

🍀 አባቴና እምነቱ (PDF) የአለቃ አያሌው ታምሩ የሕይወት ታሪክ መጽሐፍ 👇
https://www.tg-me.com/christian930/3613

🍀 የሕይወት ታሪካቸው (በድምፅ) 👇
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/11722

🍀 ቃለ ውግዘት 👇
https://www.tg-me.com/Ewnet1Nat/2959

🍀 ቃለ ውግዘቱ በራሳቸው ድምፅ 👇
https://www.tg-me.com/aleqayalew/4613
◦◦◦
በረከታቸው ትድረሰን።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
አለቃ_አያሌው_ታምሩ_100ኛ_ዓመት_የልደት_መታሰቢያ_ዜና_ሕይወቱ_ወዕረፍቱ_ለአቡነ_ወልደ_7eeeTfQqTHc.mp4
319 MB
🟩🟨🟥 ዜና ሕይወቱ ወዕረፍቱ ለአቡነ ወልደ ጊዮርጊስ ዘውእቱ አለቃ አያሌው ታምሩ ዘዲማ ።

⚡️ Documentary (ዘጋቢ)
⚡️ የጊዜ ቆይታ - 3፡15 ሰዓት
⚡️ መጠን - 319 MB

መጋቢት 23/1915 ዓ.ም ተወልደው ነሐሴ 14/1999 ዓ.ም ከዚህ ዓለም ድካም ያረፉ አባት ።

🌿 መጋቢት 23/2015 ዓ.ም የ100ኛ ዓመት የልደት በዓላቸው መታሰቢያ ነው ፤ እንኳን አደረሳችሁ ! በረከታቸው ይደርብን !

መጋቢት 21/2015 ዓ.ም
አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
www.tg-me.com/AlphaOmega930
🟢 🟡 🔴
መጋቢት 24 | #አቡነ ተክለሃይማኖት ተጸነሱ፨

በዚህች ቀን ጌታችን በቃሉ ''ሐዲስ ሐዋርያ'' ብሎ የሾማቸው የኢትዮጵያ ብርሃኗ የሆኑ የደብረ ሊባኖሱ አቡነ ተክለ ሃይማኖት የተጸነሱበት ነው፡፡

እግዚአብሔር አምላካችን ለኢትዮጵያ ሐዲስ ሐዋርያ አድርጎ የመረጣቸው ጻድቁ አባታችን ተክለ ሃይማኖት በሊቀ መላእክት በቅዱስ ሚካኤል አብሳሪነት ከአባታቸው ከካህኑ ጸጋ ዘአብና ከእናታቸው ከቅድስት እግዚእ ኀረያ መጋቢት 24 ቀን ተፀንሰው ታኅሣሥ 24 ቀን 1197 ዓ.ም ተወለዱ፡፡

ጻድቁ በተወለዱ በሦስተኛው ቀን ከእናታቸው ዕቅፍ ወርደው ‹‹አሐዱ አብ ቅዱስ አሐዱ ወልድ ቅዱስ አሐዱ ውእቱ መንፈስ ቅዱስ›› ማለትም ‹‹አንዱ አብ ቅዱስ ነው፤ አንዱ ወልድ ቅዱስ ነው፤ አንዱ መንፈስ ቅዱስ ቅዱስ ነው›› በማለት የፈጠራቸውን አምላክ አመስግነውታል፡፡

ወላጆቻቸውም ስማቸውን ፍሥሐ ጽዮን አሏቸው፡፡ ይኸውም የጽዮን ተድላዋ ደስታዋ ማለት ነው፡፡ የወላጆቻቸው የቀድሞ ስማቸው ዘርዐ ዮሐንስና ሣራ ይባል ነበር።

የአባታችን ቅዱስ ተክለ ሃይማኖት ዋና ዋና ዓመታዊ በዓላት

1. መጋቢት 24 (ጽንሰታቸው)
2. ታኅሣሥ 24 (ልደታቸው)
3. ኅዳር 24 (ከ24ቱ ካህናተ ሰማይ ጋር ያጠኑበት)
4. ጥር 24 (እግራቸው የተሰበረበት)
5. ሚያዝያ 22 (6 ክንፍ የተቀበሉበት)
6. ግንቦት 12 (ፍልሰታቸው)
7. ነሐሴ 24 (ዕረፍታቸው)

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
2024/09/27 15:28:09
Back to Top
HTML Embed Code: