Telegram Web Link
ቅበላ_በአለቃ አያሌው ታምሩ
<unknown>
◆ ቅበላ | አለቃ አያሌው ታምሩ ፨

× የካቲት 6፥ 1996 ዓ.ም ×

◦◍◦◍◦
- ቅበላና አስፈላጊነቱ
- ኢትዮጵያን የሚጠላው ፖለቲካ
- "አባታችን ሆይ" ስለምንለው ጸሎት
                ◦◍◦◍◦
🟢 🟡 🔴
አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም፨

~ የካቲት 30 | የመጥምቁ ዮሐንስ ቅድስት ራስ ከተቀበረች በዛሬው ቀን ተገኘች።

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ እንደጻፈውም ፦

የመጥምቁን አንገት ቆርጠው፣ በጻሕል አድርገው ወደ ኄሮድስ አመጡለት። እርሱም ለኄሮድያዳ ልጅ ሰጣት፤ እርሷም ለእናቷ ወስዳ ሰጠች።

ይቺም የረከሰች አመንዝራ ልትዳስሣት በወደደች ጊዜ በወጭቱ ውስጥ ጠጒሯ ተዘርግቶ (ክንፍ አውጥታ) ወደ አየር በረረች።

በአየርም ሁና የወንድምህን ሚስት ልታገባ አይገባህም እያለች የምትጮኽ ሆነች። እንዲህም እያለች ዐሥራ አምስት ዓመት ኑራ በዓረቢያ ምድር (ሚያዝያ 15) ዐረፈች፤ በዚያም ተቀበረች።

ነጋድያንም በዚያ ቦታ የሚያድሩ ሆነ። በእግዚአብሔርም ፈቃድ ሁለት አማንያን ነጋዴዎች ወደዚያ ቦታ ደርሰው አደሩ። ቅዱስ ዮሐንስም በሕልም ተገለጠላቸውና የከበረች ራሱን ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው።

እነርሱም አወጡዋት ከእርሳቸውም ጋር ወደ ቤታቸው ወስደው ታላቅ ክብርን አከበሯት።

✧◦✧◦✧

www.tg-me.com/Ewnet1Nat 🇨🇬
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930 🇨🇬
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
Top 49 minutes of natural disasters caught on camera. Most hurricane in history. USA part 2
እኔስ አባት አለኝ ፤ ዮሐንስ ይባላል ።
እንኳንስ ከምድሩ ከሲዖል ያድናል ።
አባት የሌላችሁ...
መምህር የሌላችሁ...
የሚያጽናና ወዳጅ የተቸገራችሁ...
ዮሐንስን ጥሩት አባቴ ብላችሁ
ከሚመጣው መዓት እንዲታደጋችሁ
ክርስቶስ እኮ ነው ሹሞ የሰጣችሁ
እንዳትጠፉ ብሎ በሲዖል ገብታችሁ ።

እንኳን ለሰማዕቱ፡ ለካህኑ፡ ለነብዩ፡ ለአጥማቂው፡ የዓለም ብርሃን ለሆነው የካህኑ ዘካርያስ ልጅ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ ክብረ በዓል አደረሳችሁ !
Audio
ገድለ መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዘወርኃ የካቲት
🟩 🟨 🟥
ኢትዮጵያ
የሥላሴ የክብራቸው መገለጫና መመስገኛ ምድር!
ኢትዮጵያ ርስተ ድንግል ማርያም!
ኢትዮጵያ የዓለም ብርሃን!
ኢትዮጵያ የዓለሙ ገዢ!

🍀 ዓቢይ ጾም [ ጾመ እግዚእ | ጾመ ሁዳድ ]
🍀

ዓቢይ ማለት «ዐብየ - ከፍ አለ» ከሚለው ግሥ የተገኘ ሲሆን
#ዐቢይ ማለት ከፍ ያለ ትልቅ ማለት ነው፡፡ ዐቢይ ጾም የተባለበት ምክንያት፦

[ሀ] ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የጾመው ጾም ስለሆነ፣
[ለ] በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት የሚበልጥ ስለሆነ፣
[ሐ] ሦስቱ ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች ማለትም ➻
#ትዕቢት#ስስት#ፍቅረ_ንዋይ ድል የተመቱበት ስለሆነ የሚሉት ይጠቀሳሉ።

❗️ “በዐቢይ ጾም መጀመሪያ ሱባኤ ፀሐይ እስኪገባ (እስከ 12 ሰዓት) ይጹሙ! ሌሎቹን ሳምንታት እስከ 11 ሰዓት ይጹሙ! በሰሙነ ሕማማት ግን ኮከብ እስኪወጣ (ምሽት 1 ሰዓት ድረስ) ይጹሙ!” ይላል (ፍት.ነገ.አን 15፥595)❗️

በቤተክርስቲያን ስያሜ መሠረት በዐቢይ ጾም ውስጥ የሚውሉ ሰንበታት እያንዳንዳቸው መጠሪያ ስም ሲኖራቸው እነርሱም፦
1. ዘወረደ
2. ቅድስት
3. ምኩራብ
4. መጻጉዕ
5. ደብረ ዘይት
6. ገብርኄር
7. ኒቆዲሞስ
8. ሆሳዕና ይባላሉ።

#እንኳን_አደረሳችሁ#እንኳን_አደረሰን !

ልዑል እግዚአብሔር አምላክ ጾሙን ንስሐ ገብተን፣ በእውነት ጾመን ከፈቃዱ ጋር የምንታረቅበት፥ የኢትዮጵያና የተዋሕዶን ትንሣኤ የሚረጋገጥበት ያድርግልን። ፍርዱን አጽንቶ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈጽመን፤ ጾመን ለማበርከት ያብቃን አሜን።

[ይጹም ልሳን ፤ ይጹም ዓይን ፤ ይጹም እዝን]

መጋቢት 1፥2016 ዓ.ም
አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ
www.tg-me.com/AlphaOmega930
http://www.tg-me.com/Ewnet1Nat
❗️የአባ ጳውሎስ ኑፋቄ እና የአባ ማትያስ ውጉዝነት ከአንዳንድ ያልታዩ ማስረጃዎች ጋር❗️

1▹ ያልተፈታው የአለቃ አያሌው ውግዘት ተቀባይነት አለው?

2▹ #_መንፈስ_ቅዱስን የሻረው የአባ ጳውሎስ (1987ቱ) ሕገ ቤ/ክ አሁን ላይ ተሻሽሏል?

3▹ ያሁኑስ (የአባ ማትያስ) ሕገ ቤ/ክ #መንፈስ_ቅዱስን ያከበረ ነው? ከውግዘት ያነጻቸዋል?

➻ አንዳንድ በስፋት ያልታዩ ማስረጃዎችን የያዘ፥
በአልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ የቀረበ፥

👇ሙሉውን የመብረቅ ምልክቱን በመንካት ከነማስረጃዎቹ ይመርምሩ።
Forwarded from አልፋና ዖሜጋ ዘተዋሕዶ (ዮሴፍ ETHIOPIA ◈ ኢ/ዓ/ብ)
‼️ እፈሩ! "የመናፍቃንን ቸርች የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በ2 ሚሊዮን ዶላር ገዛችው። የሕንጻውንም ቁልፍ ተቀበለች።" ይላል ይሄ የዛሬው ጉዳችሁ ደግሞ።

ውይ ቤተ ክህደት የጥፋት እርኩሰታችሁ ቅጥ አጣ !!!

በሉ ምንፍቅናችሁን እንዲህ በአደባባይ መስክሩልን እንጂ እነ የጉድ መካዘን !!

🛑
#ዋጋችሁን_ታገኛላችሁ ‼️
#ለታሪክ_ትቀመጥ !!

መጋቢት 03/2016 ዓ.ም

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
Audio
🇨🇬 የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት 7 ዓይነት ደብዳቤዎች

ለመላው የአዳም ዘር በሙሉ በድምፅ የቀረበ

ክፍል 1
Audio
የኢትዮጵያ የዓለም ብርሃናዊ መንግሥት 7 ዓይነት ደብዳቤዎች
ለመላው የአዳም ዘር በሙሉ በድምፅ የቀረበ

ክፍል 2
🟢 🟡 🔴
መጋቢት 5 | ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ( ገብረ ሕይወት ) በታላቅ ክብር ዐረፉ

ጻድቁ የተወለዱት ግብፅ (ንሒሳ አካባቢ) ሲሆን አባታቸው ስምዖን እናታቸው አቅሌስያ ይባላሉ።

አባታችን ገብረ ሕይወት የጻድቃን አለቃ፣ የቅዱሳን የበላይ፣ ተጋድሎአቸውና ድንቅ ተአምራቸው እንደ ሰማይ ከዋክብት የበዛ ቅዱስ ሰው ናቸው።

አባታችን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ለ562 ዓመታት በዚህች ዓለም ሲኖሩ:-

✧ እህል ያልቀመሱ (ምግባቸው ምስጋና ነውና)

✧ ልብስ ያልለበሱ (ጠጉር አካላቸውን ይሸፍን ነበርና)

✧ ሐዋርያዊ ሆነው ከግብፅ እስከ ኢትዮጵያ ብዙ ነፍሳትን ያዳኑ

✧ ኢትዮጵያን በ100 ዓመት ጸሎታቸው አስምረው አስራት እንድትሆናቸውም ተቀብለው ምድረ ከብድ አካባቢ አርፈዋል።

ጻድቁ ገብረ መንፈስ ቅዱስም ገብረ ሕይወትም ይባላሉ። በ562 ዓመታት ሕይወታቸው እንደ ሐዋርያት ከምድረ ግብፅ እስከ ኢትዮጵያ ወንጌልን ሰብከዋል። በዚህም በሚሊየን (አእላፍ) ለሚቆጠሩ ነፍሳት የድኅነት ምክንያት ሆነዋል።

ጻድቁ እንደ ሰማዕታትም ከከሃዲ ሰዎች ብዙ መከራን ተቀብለዋል። እንደ ባሕታውያን ለብዙ መቶ ዓመታት ሰው ሳያዩ ቆይተዋል። ለየት የሚለው ግን የጽድቅ ሕይወታቸው ነው። ከእልፍ አዕላፍ አጋንንት ጋር ተዋግተው ድል ማድረግ ችለዋልና።

በ8ኛው ክ/ዘመን አካባቢ የተወለዱት አባታችን ያረፉት በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን አካባቢ ነው። ፍጥረታትን ሁሉ አዘው መጋቢት 5 ቀን ሲያርፉ ግሩማን መላእክት ገንዘው አካላቸውን ሠውረዋል።

የጻድቁ በዓል ጥቅምት 5 ቀን የሚከበረው ብዙ ጊዜ መጋቢት 5 ዐቢይ ጾም ውስጥ ስለሚውል ተውላጥ (ቅያሪ) ሆኖ ነው።

ቸር አምላክ ከጻድቁ ዋጋና በረከት ይክፈለን።

www.tg-me.com/Ewnet1Nat
http://www.tg-me.com/AlphaOmega930
2024/09/27 23:23:45
Back to Top
HTML Embed Code: