Telegram Web Link
ሰሞኑን በተደረገዉ የነዳጅና የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ራይድ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ

የራይድ ትራንስፖርት አገልግሎት በመነሻ ያስከፍል በነበረዉ  አገልግሎቱ ላይ የ 30 ብር ጭማሪ ማድረጉን አስታዉቋል።

የነዳጅ ዋጋ በመጨመሩ እና በቅርቡ የተደረገዉ የዉጪ ምንዛሪ ማሻሻያ ምክንያት መነሻ ከ ነበረዉ 100 ብር ከትላንት ጀምሮ 130 ብር መሆኑን የሃይብሪድ ዲዛይንስ እና ራንድ መስራችና ስራ አስኪያጅ ሳምራዊት ፍቅሩ በተለይ ለካፒታል ተናግረዋል ።

ከዚህ በተጨማሪ በአዲሱ የዋጋ ማሻሻያዉ በኪሎ ሜትር የ 1 ብር ጭማሪ መድረጉን ነዉ የተናገሩት ።

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
Partner's Content: #Tecno

ታዋቂው የሆሊውዱ ትራንስፎርመር ፊልም ከቴክኖ ጋር አብሮ በመሆን ስፓርክ 30 ስልክን ይዘው ብቅ እንዳሉ ያውቃሉ?

ካላወቁ ፊልሙንም አዲሱን የስፓርክ 30 ስልኩንም በቅርበት ለማየት እሁድ ጥቅምት 3 ከ 7 ሰዓት ጀምሮ በሴንቸሪ ሲኒማ በነፃ ጋብዘነዎታል፡፡ ከልጆቾት እና ቤተሰቦት ጋር አዲሱን ስፓርክ 30 ስልክን እያዩ በተለያዩ ስጦታዎች እየተንበሸበሹ አዲሱን ትራንፎርመርስ ፊልም በኛ ግብዣ ይመልከቱ፡፡

@tecno_et @tecno_et
በኢትዮጵያና በኮርያ ሪፐብሊክ መንግስት መካከል የ10 ሚሊዮን ዶላር የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት ተፈረመ፡፡

አዲስ አበባ፡ መስከረም 30/2017 ዓ.ም (ንቀትሚ) በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና በኮሪያ ሪፐብሊክ አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ መካከል የኢትዮጵያ የጥራት አመራር አቅም ማጎልበቻ ፐሮጀክት የግብርና እና የተቀናበሩ የግብርና ምርት ውጤቶች ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ የሚያስችል የ10 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የፕሮጀክት ድጋፍ ስምምነት ተፈርሟል፡፡

Read More

Source: Ministryoftradeandregionalintegration
@Ethiopianbusinessdaily
በአዲስ አበባ ከተማ ለ1 ወር የሚቆይ የፋይዳ መታወቂያ የምዝገባ ዘመቻ በነገው ዕለት ይጀመራል።

በዘመቻው #ከአንድ_ሚሊየን በላይ ነዋሪዎችን ለመመዝገብ የታቀደ ሲሆን ምንም አይነት ክፍያ የለውም።

የፋይዳ ምዝገባ በሁሉም ወረዳዎች፤ ክፍለ ከተሞች፤ በኤጀንሲው ዋና መስሪያ ቤት እንዲሁም ሁለት ቅርንጫፎች ላይ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

Source: tikvahethmagazine
@Ethiopianbusinessdaily
የሪል_ስቴት_ልማት_እና_የማይንቀሳቀስ_ንብረት_ግብይትና_ግመታ_አዋጅ_2.pdf
1.7 MB
ያልተገነባ ቤት /ግንባታ ከማከናወናቸው በፊት ቤት የሚሸጡ ሪል ስቴት አልሚዎች የሚሰበስቡትን ገንዘብ በዝግ አካውንት እንዲያስቀምጡ ሊገደዱ ነው ፤ በተጨማሪ ግንባታው 80 በመቶ ላይ ያልደረሰን ቤት ለደንበኞች እንዳያስተላልፉ ሊከለከሉ ነው።

ይህንም የሚመለከት ረቂቅ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዛሬ ቀርቧል።

አዲሱ ረቂቅ አዋጅ ምን ይላል ?

Source: theethiopianeconomistview
@Ethiopianbusinessdaily
ኦክሎክ ሞተርስ ከቻይናው Global-Ucar Technology ጋር በጋራ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡

ኦክሎክ ሞተርስ ከቻይናው Global-Ucar Technology Co. Ltd ጋር በ250 ሚሊዬን ዶላር ኢንቨስትመንት በጋራ ለመስራት በዛሬው እለት ተፈራርመዋል፡፡

በ1997 ዓ/ም ምስረታውን ያደረገዉ አክሎክ ሞተርስ ከ Global-ucar Technology Co.Ltd ጋር በሚቀጥሉት አምስት አመት ዉስጥ 20 ሺህ ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች ለማቅረብ ስምምነት ፈፅመዋል፡፡

በተጨማሪም አክሎክ ሞተርስ 20ኛ ዓመት የምስረታ በዓሉን እያከበረ እንደሆነም ገልፆል፡፡
ድርጅቱ ውሊንግ፣በውጅንና የጂቶር ምርት የሆኑ የተለያዩ ሞዴል ተሽከርካሪዎችን ሀገር ውስጥ በመገጣጠም ላይ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

ኦክሎክ ሞተርስ ከአሥራ ስድስት በላይ የተለያዩ ሞዴል ተገጣጣሚ ተሸከርካሪዎችን ከውጭ በማስመጣት ሀገር ውስጥ ባስገነባቸው የተሸከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካዎቹ በመገጣጠም ለደንበኞቹ በማቅረብ ላይ እንደሚገኝም በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ተመላክቷል፡፡

Source: ethiofm
@Ethiopianbusinessdaily
Ethiopian rail requires $500M investment for expansion, upgrades

A recent report from Ethiopia Ministry of Transport and Logistics highlights the need for $500 million in investment to enhance the country's rail infrastructure. The report outlines plans to strengthen the Ethiopia-hashtag#Djibouti railway and expand access to international ports, crucial for the landlocked nation's trade.

The hashtag 752km Ethiopia-Djibouti railway, a key transport link between Addis_Abeba and the port of Djibouti, is set to undergo upgrades. The investment will also cover operational, legislative, and institutional reforms necessary for improving rail efficiency and safety standards.

Of the total investment, $300 million is earmarked for new port connections, while $200 million will go towards maintaining rolling stock and securing spare parts. The ministry also revealed plans to explore new railway...
.
.
.
Read More

Source: EthiopiaDjiboutiLogistics
@Ethiopianbusinessdaily
ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻን ከሚቀጥለው ሳምንት ጀምሮ መሸጥ እንደሚጀምር አስታወቀ

ግዙፉና መንግስታዊዉ የቴሌኮም አቅራቢያ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም 10 በመቶ ድርሻዉን ለህዝብ መሸጥ እንደሚጀምር ተሰምቷል ።

በኢትዮጵያ 130 ዓመታት ገደማ በመንግሥት በብቸኝነት ተይዞ የነበረዉን የቴሌኮም ዘርፍ ከረቡዕ ጥቅምት 6 ቀን 2017 ዓ.ም. ለግል ባለሃብቱ በይፋ መሸጥ እንደሚጀምር ከተቋሙ የተገኘው መረጃ ያመላክታል ።

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
Safaricom Ethiopia’s launch drives mobile data costs down by 70%

Since the launch of Safaricom Ethiopia, the cost of mobile data services in Ethiopia has fallen by up to 70%.

British International Investment (BII), one of the shareholders at Safaricom Ethiopia, disclosed that a UK-backed mobile network operator has helped millions of Ethiopians access superfast 4G mobile internet across the country.

It said that BII and Safaricom Ethiopia commissioned the report, entitled “Impact of Investment in the Ethiopian Telecoms Market – The Story So Far,” to take stock of how the Ethiopian telecoms market has changed and evolved since the liberalization process of the sector began in 2019.

Read More

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
Partner's Content: #Mesirat

የፋይናንስ ሪፖርቶቻችሁን እና የብድር ክፍያዎቻችሁን ማስተዳደር ከብዷችኋል?

"የፋይናንስ ግንዛቤዎች (Financial Insights) በሚል ርዕስ የተዘጋጀውን የቨርቹዋል ሥልጠናችንን በነፃ ይሳተፉ!
🗓 ጥቅምት 15, 2017 ዓ.ም
🕒 ከቀኑ 8:00 እስከ 11:00 ሰዓት

ለስልጠናው አሁኑኑ ይመዝገቡ! https://forms.gle/JEi2pdVZJjdxmU53A

#ፋይናንስ #Finance #መስራት
የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ተገልጿል።

የኢሚግሬሽን ዜግነትና አገልግሎት የፖስፖርት የግዜ ቆይታ ከ5 ዓመት ወደ 10 ዓመት ከፍ እንደሚል ገልጿል።

ፖስፖርት ለማደስ 5 ዓመት ይጠበቅ የነበረ ሲሆን ከአንድ ወር በኃላ ወደ ሥራ በሚገባው አሰራር መሰረት ግን ከ25 ዓመት በላይ ለሆናቸው ዜጎች በየ10 ዓመቱ እንደሚታደስ አገልግሎቱ ገልጿል።

Source: tikvahethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
መንግስት ነዳጅ ላይ ሊያደርግ ባሰበው ፊፎርም ምክንያት የዛሬ አመት አንድ ሊትር ነዳጅ ከ117 ብር በላይ እንደሚሆን ታውቋል

የንግድ እና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከቀናት በፊት የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻን በማድረግ የነዳጅ ችርቻሮ ዋጋን በየሶስት ወሩ እንደሚጨምር ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።

በዚህ መግለጫ ላይ ይፋ የተደረገው መረጃ "የተሟላ ማስተካከያ" እስከሚደረግ ድረስ ይህ በየሶስት ወሩ የሚደረገው ጭማሪ እንደሚቀጥል ነው።

ከዚህ መግለጫ ጋር አብሮ የተለቀቀ አንድ ሰነድ እንደሚያሳየው የአለም የነዳጅ ዋጋ አሁን ባለበት የሚቀጥል ቢሆን የዛሬ አመት የነዳጅ ዋጋ 117 ብር ይገባል።
.
.
.
Read More

Source: MeseretMedia
@Ethiopianbusinessdaily
Proposal to Push EU’s Deforestation Law Brews Good News for Ethiopia’s Coffee

Ethiopia’s coffee exporters heave a sigh of relief as the pending implementation of the European Union’s Deforestation Regulation (EUDR) gets tabled for a year-long extension.

Read More

Source: shegamedia
@Ethiopianbusinessdaily
አሃዱ ባንክ ያለመያዣ ብድር መስጠት ሊጀምር መሆኑን አስታወቀ

በጥቃቅንና አነስተኛ ንግድ ወይም በማምረት ስራ ላይ ለተሰማሩ የዘርፉ አንቀሳቃሾች ያለመያዣ ብድር ለመስጠት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ መድረሱን አስታዉቋል።

ባንኩ እንዳለው የገንዘብ እንቅስቃሴ ወይም (Cash flow) መሰረት ያደረገ ሲሆን፣ ይም "ማሕደር" የተባለ ቀላልና አመቺ የቴክኖሎጂ መተግበሪያን በመጠቀም ተበዳሪዎች የንብረት ዋስትና ማቅረብ ሳያስፈልጋቸው ብድር እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ብለዋል።

በዚህም ባንኩ "ከብዙዎች ለብዙዎች" የሚለውን መርሕ ተግባራዊ በማድረግ በጥቃቅን እና አነስተኛ የስራ ዘርፍ ለተሠማሩ የኢኮኖሚ አንቀሳቃሾች ያለመያዣ የብድር አገልገሎት ይሰጣል ተብሏል።

አሃዱ ባንክ አጠቃላይ ከሚሰጠው የብድር መጠን እስከ 25% የሚሆነውን ድርሻ ለዚህ ዘርፍ መመደብ የተገለፀ ሲሆን ይሀንን ተግባራዊ ለማድረግ ባንኩ ከኤስኤንቪ (SNV)፣ የኔዘርላንድ ልማት ድርጅት እና ከኬኤምዲ አፕሲስ (KMD Apsis) ጋር እንደሚሰራ አስታዉቋል ።

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
RLSD International Design award highlights sustainable fashion

The Real Leather. Stay Different. International Design Award recently concluded in London, showcasing innovative designs and a commitment to sustainable fashion. The event brought together designers from around the globe, emphasizing leather as a durable and eco-friendly material that intersects creativity with environmental responsibility.

A standout moment of the evening was the recognition of Ruth Girmay, who was honored as Africa’s Most Commendable Designer for her Overfishing Bag design, which addresses marine sustainability issues.

Read More

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
Daily_Quiz

Which strategy involves selling a product at a lower price to enter a competitive market?
Anonymous Quiz
19%
A. Price skimming
72%
B. Penetration pricing
4%
C. Bundle pricing
4%
D. Dynamic pricing
ዜና ማስተካከያ!

በአሁኑ ወቅት በሳፋሪኮም ይፋ የተደረገ የሞባይል ዳታ ላይ ቅናሽ የለም

የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ባለድርሻ የሆነው የብሪታንያ ዓለምአቀፍ ኢንቨስትመንት (British International Investment) ትላንት ጥቅምት 1 ቀን ለካፒታል የላከውን መግለጫ መሰረት በማድረግ በድረገፃችን እና በማህበራዊ ሚዲያ መስመሮቻችን ባጋራነው የእንግሊዘኛ ዜና የብሪታንያው ተቋም አሰራሁት ባለው ጥንቅር የሳፋሪኮም ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ የቴሌኮም ኢንደስትሪ መሰማራት ባለፋት አመታት በጥቅሉ የሞባይል ዴታ ወጪ በአገሪቱ እስከ 70 በመቶ እንዲቀንስ የበኩሉን ሚና መጫወቱን በማስመልከት ጥናቱን ጠቅሰን ዘግበን ነበር።

የዚህ ዜና ጥቅል ሃሳብ በማህበራዊ ትስስር ገጾቻችንም በአማርኛ ቀርቦ ነበር።
ሆኖም መሰረታቸውን ማህበራዊ ሚዲያ ላይ ያደረጉ ብዙ ተከታይ ያላቸው ግለሰቦች እና ተቋማት የአማርኛውን ዜና ሃሳብ በማዛባት ካፒታልን በመጥቀስ እንዲሁም ምንጭ ሳይጠቅሱ ጭምር ሀሳቡን በማዛባት ሳፋሪኮም የአገልግሎት ታሪፍ እንደቀነሰ አድርገው መረጃውን በማጋራት ለአንባቢያን ትክክለኛ ያልሆነ መረጃ ማቅረባቸውን ታዝበናል።

በመሆኑም አንባቢዎች ትክክለኛው ዘገባ ከታች ባሉት ማስፈንጠሪያዎች/ሊንኮች (በእንግሊዘኛ) ገብተው እንዲያነቡ እየጋበዝን ሳፋሪኮም በአሁኑ ይፋ ያደረገው ምንም አይነት የታሪፍ ቅናሽ የሌለ መሆኑን እንገልፃለን።

Read More

Source: capitalethiopia
@Ethiopianbusinessdaily
2024/11/15 18:55:52
Back to Top
HTML Embed Code: