Telegram Web Link
'ወትባርክ አክሊለ አመተ ምህረትከ; ወይጸግቡ ጠላተ ገዳም; ወይረዉዩ አድባረ በድዉ' መዝ ፷፬-፲፩ እንኳን ለ2014 ዓ.ም ዘመነ ማርቆስ በሠላምና በጤና አደረሳችሁ Happy New Year
ጥበብ ቤትዋን ሠራች፥ ሰባቱንም ምሰሶችዋን አቆመች።
ፍሪዳዋን አረደች፥ የወይን ጠጅዋን ደባለቀች፥ ማዕድዋን አዘጋጀች።
ባሪያዎችዋን ልካ በከተማይቱ ከፍተኛ ስፍራ ላይ ጠራች።
አላዋቂ የሆነ ወደዚህ ፈቀቅ ይበል፤ አእምሮ የጐደላቸውንም እንዲህ አለች።
ኑ፥ እንጀራዬን ብሉ፥ የደባለቅሁትንም የወይን ጠጅ ጠጡ።አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።
ፌዘኛን የሚገሥጽ ለራሱ ስድብን ይቀበላል፥ ኅጥአንም የሚዘልፍ ነውርን ያገኛል።
ፌዘኛን አትገሥጽ እንዳይጠላህ፤ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል።
ለጠቢብ ሰው ትምህርትን ስጠው፥ ጥበብንም ያበዛል፤ ጽድቅንም አስተምረው፥ እውቀትንም ያበዛል።
 የጥበብ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው፤ ቅዱሱንም ማወቅ ማስተዋል ነው።
 ዘመንህ በእኔ ይበዛልና፥ የሕይወትህም ዕድሜ ይጨመርልሃልና
ማዕድናት ወይም የከበሩ ድንጋዮች 365 ሲሆኑ እነኚህም ማዕድናት ከሰዉ ልጅ ጋር ከፍተኛ ቁርኝት ፈጥረዉ ሰዉን ከፍ ካለ ቦታ ላይ ያስቀምጡታል። ለምሳሌ አንድ ሰዉ የተወለደበትን ወርና ቀን ይዞ ያ ሰዉ በተወለደበት ቀንና ወር የሚነግሰዉን ማዕድን ካወቀና ካገኘዉ በሚኖርበትና በሚራመድበት ምድር ላይ በረከትን ክብርን ያገኛል። ከአስራ ሁለቱ የከበሩ ማዕድናት ዉስጥ
1ኛ አሜቴስ ለጥይት
2ኛ ያክንት ለነገስታት
3ኛ ክርስጵራስስ አልወጣ ላለች ለተጨነቀች ነፍስ
4ኛ ወራዉሬ መደባለቂያ
5ኛ ቢረሌ ለሌሎች አድናቶችን
6ኛ ክርስቲሎቤ ለቤት መስሪያ
7ኛ ሰርዲዎን ጦር ሽጉጥ ማርከሻ
8ኛ ሰርዶንክስ ለባሕር ጉዞ
9ኛ መረግድ ለድል
10ኛ ኬልቄዶን የሙት
11ኛ ሰንፔር ለከይሲ
12ኛ ኢያስጲድ አቃቢ
ለአብነት እነዚህን ጠቀስን።
Channel photo updated
# የዳዊት ገቢር
መዝሙር ፳
እግዚኦ በኃይልከ ይትፌሳ ንጉስን....
በረከት ከቤት በራቀ ጊዜ በረከት ያድርብህ ዘንድ 4ጊዜ በአራት አቅጣጫ አንብብ የከሴ ተቀጽላ አምጥተህ በዉኃ ዘፍዝፈር ቤትህን እርጨዉ። በቤትህ በረከት ይሞላል።
🌼🌼ስምንቱ አቅጣጫዎች🌼🌼
የምንኖርባት ዓለም በስምንት አቅጣጫዎች የተከፈለች ሲሆን አራቱ አበይት አቅጣጫዎችና አራቱ ንኡሳን አቅጣጫዎች ተ ብለው ሲከፈሉ እነዚህም ከአራቱ አበይት አቅጣጫዎች ዉስጥ 1.ምስራቅ
2.ሰሜን
3.ምዕራብ
4.ደቡብ ተብለዉ ሲታወቁ
የተቀሩት አራቱ ንዑሳን አቅጣጫዎች
1.ባህር
2.አዜብ
3.ሊባ
4.መስዕ ተብለዉ ይታወቃሉ።
የአራቱ አበይት አቅጣጫዎች መነሻቸዉ የሰዉን አካል ቅርጽ ለመግለጽና ለሌሎች ነገሮች መወከያና መጠቆሚያ የነበረ ሲሆን ነገር ግን በብዙ ተምሳሌት ለሆኑ ነገሮች ጥቅም ላይ ዉለዋል ከዚህ ዉስጥም የምስራቅን አቅጣጫ ከፀሐይ መዉጫና ከሰዉ መወለድ ጋር ሲመሳሰል በተቃራኒዉ የምዕራብን አቅጣጫ ከፀሀይ መግቢያና ከሰዉ ህልፈት ጋር ይመሰላል። በጥንታዊ የሰው ልጆች ስልጣኔ ላይም እነዚህ አቅጣጫዎች በኪነ-ህንፃዎችን ላይ ታይተዋል ለዚህም ማሳያ ይሆን ዘንድ በካህኑ ንጉስ ላሊበላ በቤተ ጊዮርጊስና እንዲሁም በካህኑ ንጉስ ይምርሀነ ክርስቶስ ቤተ መቅደሶች ላይ ይህንን አበይትና ንዑሳን የተባሉት አቅጣጫዎችን ጠብቀዉ ተፈልፍለዋል ። ንኡሳን ብለን ያስቀመጥናቸዉ ባህር አዜብ ሊባ መስዕ የተባሉት አቅጣጫዎችን ጥንታዊ በሆኑ በሰዉ ልጆች ስልጣኔ ላይ የተለያዩ ቁሶችን የተለያዩ የከበሩ ማዕድናትን የተለያዩ የጥበብ መጽሐፍቶች ከተማዎችን በነዚሁ በንዑሳን አቅጣጫዎች አስቀምጠዉባቸዋል ይህም የተመረጠበት ምክንያት እነዚህ አቅጣጫዎች በቀላሉ ጠላት የማይደፍራቸዉና ሊገኙ የማይችሉ የሚስጥር ጓዳዎች ስለሆኑ ነዉ። የሰዉ ልጅ እነዚህን አራት አቅጣጫዎች ተከትሎ አምሳሎቻቸዉን ተገንዝበን የፍጥረታትን መሠረት እንዲሁም የዉስጣችንን እና በሀገራችን ቀደምት ጥንታዊ የሆኑ ጥበቦችን ለመረዳት ያስችለናል።
ባራባራ
መሊጦን
ሱርቲዮን
አግራማጣ

እሳት
አየር
ዉኃ
መሬት



ሚካኤል
ገብርኤል
ሩፋኤል
ዑራዔል

ምልክኤል
ሕልመልሜሌክ
ሚላኤል
ናርኤል
ወታቦተ መልከ ጼዴቅኒ እምነ እብን ቅዱስ ዘቀደሱ መላእክት ወአንበርዋ ማእከለ ሕንብርታ ለምድር።
ቤታችን ጨልሟል ነገር ግን መዛግብቶቻችን ላይ የብርሀናት ጭላንጭል ይታያል ቤታችንን እንፈትሽ ወደ ቀደመዉ ተፈጥሯዊዉ እረፍት እንመለስ!

አ40
ዳ100
ም4=144

ኢ40
የ90
ሱ7
ስ7=144

#####የፊደል አዋጅ ኁልቁ ፊደላት
ሀገራችን ኢትዮጵያ ጥንታዊና ባለ ብዙ ሀብት ባለቤት ካደረጓት ዉስጥ የራሷ የሆነ ፊደል የራሷ የሆነ ቁጥር የራሷ የሆነ ስርዓት እምነትና ባሕሎቿ ናቸዉ። የአንድን ሀገር ቀደምትነት የሚለካዉ በቤቷ ዉስጥ ባሉት ሀብቶች ሲሆን ሀገራችንም ኢትዮጵያ እነዚህንና ሌሎች ጥልቅ የሆነ ሀብት ያላት ሀገር መሆኗን ሁሉም ያዉቃል ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያዉያኖች በቤታችን ዉስጥ ያለዉን ሀብታችንን ሳናዉቅ ከቤታችን ዉጪ ባለ የባዕዳንን አስተምህሮት ፍለጋ ቤታችን ዉስጥ ያለዉን ዘንግተነዋል። በቅርብ ያለ ጸበል ልጥ መንከሪያ ይሆናል እንደተባለሁ ሁሉ ቤታችን ዉስጥ ያለዉን  ዕዉቀት ንቀነዉ ከረሳነዉ ብዙ አመታት ተቆጥረዋል። የረሳናቸዉንና አገልግሎታቸዉን ያላወቅናቸዉ እዉቀቶችን ጥናት ከማድረግ ይልቅ የዉጪ ሀገር ሰዉ መጥቶ አጥንቶ ባቀረበልን ሀሳብ ላይ  ብቻ አምነን  ተቀምጠናል።ለምን?
ቀደምት ኢትዮጵያዉያን ትልቅ የሆነ የማይነቃነቅ መሠረት በዓለት ላይ ጥለዉልን አልፈዉ እኛ ግን እነሱ ባስቀመጡልን የዓለት መሰረት ላይ ቤታችንን መገንባት ሲገባን ሌላ አዲስ መሠረቱም በአሸዋ ላይ የሆነ መሠረት ካልቆፈርን በማለት አይምሮዋችንን ካደከምነዉ ቆይተናል። ሁሉም ኢትዮጵያዊ በቤቱ ያሉትን ዕዉቀቶች መመልከት መጠቀምና በራሱ ሀሳብ ላይ መቆም ይገባዋል። ንቃተ ልቦናችንን ልናበረታዉና ያላስተዋልነዉን ልናስተዉለዉ ይገባል።።።።።።።!!!
##ኁልቁ ፊደላት የፊደል አዋጅ አቆጣጠርና ህግ ነዉ።ይህም የፊደል አቆጣጠርና ህግ ፳፮ቱ የግዕዝ ፊደላትን የሚመለከት ሲሆን ፊደላቶቹም የራሳቸዉ የሆነ ቁጥር ዉክልና አላቸዉ ፊደል ቁጥር አለዉ ቁጥርም ፊደል አለዉ።ይህንን የፊደል ህግ ቀደምት ኢትዮጵያውያን ለኛ ለልጆቻቸዉ ያስቀመጡበት ምክንያት ጥበብን እንድንረዳ እንዲሁም ጥንታዊ የሆኑ መዛግብቶችን ስንመረምር ምዕራፍና ቁጥሮቻቸዉ በዚሁ የፊደር አቆጣጠርና ህግ የተጻፉ በመሆኑ የመዛግብቶቹን አዘጋጆች ከማን ዘንድ እንደሆኑና ሀሳባቸዉን እንድንረዳና መሰረታቸዉን አዉቀን በጥበብ እንድንኖር ይረዳናል ከዚህም በተጨማሪ ስለ ከዋክብት ስለ ሰዉ ልጅ ባህሪና ስለ ዓዉዶች ፊደላትና ቁጥሮች ከሰዉልጆች ጋር ስላላቸዉ ቁርኝት በደምብ እንድንረዳና ጠልቀን እንድናዉቅ ይረዳናል። ###የፊደል አዋጅ አቆጣጠርና ህግ አገልግሎትና ጥቅማቸዉም ቀደምት ጠቢባን ስሞችን ከተፈጥሮ እንዲሁም ከሰማያዊ ስርዓቶች ጋር ያላቸዉን ዉክልናና ተምሳሌት እንድንረዳና እንድንገለገልባቸዉ እንድንጠቀምባቸዉ ከትበዉ አስቀምጠዉልናል። ይህንንም አቆጣጠርና ህግ ለመረዳት በቅድሚያ የራሳችን የሆነዉ ቁጥር ማወቅና መረዳት ይጠበቅብናል ይህም ማለት የምንኖርበትን ቤት የቤተሰባችንን ቋንቋ ማወቅ ሲሆን ይህንንም የገዛ ቤታችንን ቋንቋ ካላወቅንና ካልተረዳን በገዛ ቤታችን ባዳ እንደመሆን ይቆጠራል ስለዚህ ግዕዝን ማወቅ ቁጥሮቹን መረዳትና መለየት አስፈላጊና መሠረታዊ ነዉ ።የፊደል አዋጅ አቆጣጠርና ህግን በሀያ ስድስቱ የግእዝ ፊደላት ላይ የተወከሉትን በዝርዝር እናስቀምጣለን።
ሀ፩
ለ፪
ሐ፫
መ፬
ሠ፭
ረ፮
ሰ፯
ቀ፰
በ፱
ተ፲

ኀ፳
ነ፴
አ፵
ከ፶
ወ፷
ዐ፸
ዘ፹
የ፺
ደ፻

ገ፪፻
ጠ፫፻
ጰ፬፻
ጸ፭፻
ፀ፮፻
ፈ፯፻
ፐ፰፻

###የአቆጣጠር ህግ
ከ ሀ እስከ ሆ የሚገኙትን ፊደሎች በሚጀምርባቸዉ ፊደር ጠቅልሎ ይቆጥረዋል ይህ  ማለትም ለምሳሌ  ሄዋን የሚለዉን ስም (ሄ) በ(ሀሌታዉ ሀ፩) ዉስጥ አስገብቶ ነዉ የሚቆጥረዉ። ሄ(ሀ፩) ዋ(ወ፷) ን(ነ፴) ሲሆን ድምራቸዉም ፺፩ የሚመጣ ሲሆን የቁጥሩና የሄዋን ተምሳሌቱም ሴቶችን ሲወክል እነሱም ልጅን በመዉለድ ተፈጥሮን የሚያስቀጥሉ ሲሆን የምኖርበትም ምድር በየ ፺፩ ቀናት ዉስጥ እየተዋለዱ ወቅቱን የሚመግቡ መጋቢያን ከዋክብት በየዘጠና አንድ ቀናት ምግብናቸዉን ጨርሰዉ አዲስ መጋቢ የሚመጣበትና የሚቀያየርበት የቁጥር ልኬት ነዉ።
እንዲሁም ከሰዉ ወገን የሆኑትን ሁሉ
ቁጥራቸዉን ያመሳስለዋል ለምሳሌ አዳም እና ኢየሱስ እንዲሁም በራዕይ ዮሐንስ የተጠቀሱትን መቶ አርባራት ሺ ህጻናትን በቁጥር ልኬት አንድ አድርጎ የሰዉ ልጆች ወገንነት ያመላክተናል።

ዉድ የጠልሰም ሀሳብ ተከታታዮች ከኁልቁ ፊደላ ጋር ያላችሁን ሀሳብ የምታዉቁትንና የሚሰማችሁን አካፍሉን።


በቀጣይ
#ኁልቁ ፊደላትና የሰዉ ልጆች ባህሪ አወጣጥ
#አራቱ ባህሪያትና አራቱ ወቅቶች ምግብናቸዉ
#አራቱ አዉዶች አንዷ ቀን
#አስራ ሁለቱ ከዋክብት
የጠልሰም ቤተሰቦች
ሄኖክ
መልከጼዴቅ
ኤልያስ
ነአኩቶ ለአብ
ሌሎችም ሞትን ያልቀመሱት ስለምን ይመስሏቹኃል? እኛስ ህያዋን ሁነን ስለምን ታላቂቷን ቀን መጠበቅ አልቻልንም? ፈጣሪ ለሰዉ ልጅ ሁሉን ሰጥቶ ሳለ የሰዉ ልጅ ግን ከሞትጋር የተዋዋለዉ ዉሉ ምንድነዉ? ሞትስ ማን ነዉ? ስለምንስ ነፍስ ስጋ መንፈስ በተዋህዶ ሰዉ (ባለ ሶስት አንድ) ሁነን ሳለ ለነፍሳችን ብለን ስጋችንን መነጠላችንና መንፈሳችንን እንድንዘነጋ ለምን ተፈለገ? መሠረታችን ህያዉ ሁኖ ሳለ ስለምን መጨረሻችን ሞት ሆነ? የሞት መሠረት ሟች ያደርጋል! የህያዉ መሠረት ህያዉን ያደርጋል! መሠረታችንን እንፈልግ ወደ ራሳችን እንመልከት!
የጠልሰም ቤተሰቦች
ሄኖክ
መልከጼዴቅ
ኤልያስ
ነአኩቶ ለአብ
ሌሎችም ሞትን ያልቀመሱት ስለምን ይመስሏቹኃል? እኛስ ህያዋን ሁነን ስለምን ታላቂቷን ቀን መጠበቅ አልቻልንም? ፈጣሪ ለሰዉ ልጅ ሁሉን ሰጥቶ ሳለ የሰዉ ልጅ ግን ከሞትጋር የተዋዋለዉ ዉሉ ምንድነዉ? ሞትስ ማን ነዉ? ስለምንስ ነፍስ ስጋ መንፈስ በተዋህዶ ሰዉ (ባለ ሶስት አንድ) ሁነን ሳለ ለነፍሳችን ብለን ስጋችንን መነጠላችንና መንፈሳችንን እንድንዘነጋ ለምን ተፈለገ? መሠረታችን ህያዉ ሁኖ ሳለ ስለምን መጨረሻችን ሞት ሆነ? የሞት መሠረት ሟች ያደርጋል! የህያዉ መሠረት ህያዉን ያደርጋል! መሠረታችንን እንፈልግ ወደ ራሳችን እንመልከት!
ተጋበዙልኝ
ሰዉ መሆን በቂ
2025/04/10 01:45:02
Back to Top
HTML Embed Code: