Telegram Web Link
🔴ምን እንደሚቆጨኝ ታውቃለህ ?

ካንተ ጋር ያሳለፍነው ሳይሆን

ተስፋ ያደረግኩት ነው
💙🔚
አልቦ ዘመድ - ብርሃኑ ድንቄ.pdf
3.5 MB
"አልቦ ዘመድ" እንደያዘው ጠቃሚ ሀሳብ ብዙም ያልተዋራለትና ያልተነገረለት ምርጥ መጽሐፍ ነው።አንብቡና አትርፉበት።

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
💫ለፈገግታ 😁



ህፃን ማጫወት አለ አይደለ "አቡቱቱ ምንድ ነው እሹ...እምሽቅንን"...ምናምን ማለት ብፈልግም አልችልበትም ነበር።እንደምችል ያወቅኩት ከትናንት ወዲያ ነው....😁


ነገሩ እንዲህ ነው...ከዶርሜ የወጣሁት ምሳ ልበላ ነው...በልቼ በዛው class ልገባ...ታዲያ እጄን ታጥቤ መመገቢያ ካርዴን ላወጣ እጄን ኪሴ ስከት ነገርየው የለም...ወደ ቦርሳዬ ተሻገርኩ...አሁንም የተቀየረ ነገር የለም...I was like "ቤብ prank መሆኑ ነው...አትቀልድ በናትህ..."...(ቤብ ያልኩት መመገቢያ ካርዴን ነው...😁)...መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች ያሉት ለእኔ መሆን አለበት አልኩ በሆዴ...


ወደ ቲከሯ አይኔን ስሰድ ተስፋ ቆረጥኩ...ይቺ ሴትዮ መመገቢያ ካርድ ይዤ እንኳን ባታስገባኝ ደስ እንደሚላት ሁሌ ፊቷን በማገለባበጥ ትነግረኛለች....አልሰማትም እንጂ....ሰአቴን አየሁ...ዶርም ሄዶ መምጣት አይታሰብም...ካፌው ሊዘጋ 2 ደቂቃ ነው የቀረው..."እና ውጪ አትበዪም ወይ" ካላችሁኝ ደግሞ እፈነክታችኃለሁ😏


ይቺ ሴትዮ ያለ ካርድ እንድታስገባኝ ሁለት መስፈርት ማሟላት አለብኝ....


አንደኛው ወንድ መሆን ነው።...እሱን አልችልም...በዚህ አጋጣሚ ለእኛ ጊቢ ወንዶች ያለኝ አድናቆት ላቅ ያለ ነው...በቃ አንድ ቃል ወርወር...ከዛ ጥርስ በጥርስ ማድረግ...ከቲከር እስከ ወጥ ጨላፊ...ከኩባያ አጣቢ እስከ ሳህን አጣቢ..ከዳቦ አከፋፋይ እስከ ላይብረሪስት(ዳቦ ስል ሌላ ነገር እንዳታስቡ🙄)....ወይ ጥበሷቸው ከአመት አመት ከምታቁለጨልጯቸው😂

ሁለተኛው ደግሞ ልጇን ማጫወት😓...
ከራሴ ጋር እየተሟገትኩ ተጠጋሁ...


"አቡቱቱቱ እምንድነው እሹ የእኔ ሚጢጢ....እምሽቅንንን..."...ጀመርኩ...የሆነ ሰአት ለአፍታ ዝም እያልኩ እሄ ድምፅ ከእኔ መውጣቱን መፈተሽ ገባሁ....ድዱን እያሰጣ ተጠጋኝ...ከዛ ሊፋታኝ ነው...

"ኧረ በናትህ አትጃጃል እርቦኛል ለራሴ...".....በሆዴ ነው።ሴትየዋ ደስታ ሊገላት ደረሰ...እንኳን ካርዴን እንደረሳሁ ላብራራ ቀርቶ ታምኑኛላችሁ  ሳልጠየቅ እንደገባሁ..(ወዲያው የወለዱት ሲሳም....የሚባለው ተረት ነው የመጣልኝ) ....


እስከዚህ እኮ ደህና ነበርኩ....ዛሬ ካርዴን ይዤ በኩራት ላጥ ላጥ ብዬ ልገባ ስል ህፃኑ ገና ሲያየኝ እየተፍነከነከ ሲወጣብኝ ነው በቃ እንደ ማበድ ያደረገኝ.... ከሁለት ቀን በፊት ያደረግኩትን ረገምኩት..


"አንተ እኩያህ መሰልኩህ እንዴ...ኧረ በፈጠረህ እኔ ሰላማዊ ሰው ነኝ...ምኔ ነው ኢቶጲስን የሚመስለው...."....አሁንም በሆዴ ነው🤨



እኔ ብቻ ነኝ ግን....?



ሸዊት


👉
https://www.tg-me.com/ethioleboled
Based on true story❤️

   

       ግን የኔ አይደለም😊...አደራ ቤተሰብ "የእኔ አይደለምን ምን አመጣው"....ምናምን ብላችሁ ነገር ባለመብላት ተባበሩኝ...ከተስማማን ፅሁፌን እነሆ.......



ለመጀመሪያ ጊዜ መታቀፍ ፈለግኩ...ልብ በል...ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ያልኩት...


ከዛ አንተ ምን አደረግክ???


የመታቀፍ ፍላጎቴን...በሰው ጉያ የመደበቅ ፍላጎቴን...ለአፍታ የመሰወር ፍላጎቴን...እነዚህን ከመታቀፍ ጋር የሚደመሩ የመጀመሪያ  ስሜቶቼን የመጨረሻ አደረግካቸው...

እግዚአብሄር ይስጥህ ሳልወድ በግዴ ይቺን መከረኛ አለም ተጋፈጥኳት.. መራራ ፅዋዋን ጠጣሁ...እድሜ ላንተ ሞቴ የቀረበ በመሰለኝ ማግስት  ከአምላኬ ጋር ተጣበቅኩ...አላስጠጋ ስትለኝ እርሱ ሰበሰበኝ...ለአፍታ ነክተህ ለመመለስ የተጠየፍካት እኔን እርሱ ሳያቅማማ እቅፍቅፍፍፍ አረገኝ....


ያኔ እኮ ካንተ ጋር መጥፋት ፈልጌ ነበር...እጅህን መያዝ ፈልጌ ነበር...አንተ ጋር የምመጣው እኮ እንደምለው ልወቅስህ አልነበረም...ይዘኧኝ ጥፋ ልልህ ነበር እኮ አመጣጤ...ያኔ ምኞቴ አንድ ብቻ ነበር...እንድትፈቅድልኝ ብቻ ነበር የምፈልገው...


ህይወቴ ብልህ መልስህ ምን ነበር...?
ብስምህስ መልስህ ምን ነበር....?
ውስጤ ያለውን ጠራርጌ እንዳልነግርህ ፊትህ ገፋኝ...


ከዚህ መከረኛ ስሜት መላቀቂያ ባጣ ባልንጀሮችህን የሙጥኝ አልኩ...ቢያንስ ስላንተ ለመስማት...በሰአቱ ደህንነትህን ማወቅ በጥቂቱም ቢሆን ያሳርፈኝ ነበር....


አሁንም እምብዛም አላረፍኩም...ባንደኛው ቀን ያበጠ ይፈንዳ ከዚህ በላይ ምን ይመጣል ብዬ ስሜቴን አንድም ሳላስቀር ነገርኩህ....


ከዛ መልስህ ምን ሆነ....?


"ለወንድ ብለሽ እንደዚህ አትሁኚ...."...የዛን እለት ስብራቴን በምንም አትጠግነውም...በዘመነ ኮሮና  አንተ ጋር ለመምጣት ተከናንቤ የወጣሁት ነጠላ በእንባ ረጠበ...እሱ ጋር ነኝ ብዬ ረግጬው ያለፍኩትን የሰፈሬን ታቦት ስመለስ በደንብ አስተዋልኩት...


አውጣኝ ከዚህ ስሜት...እኔስ ልጅህ አይደለሁም ወይ አልኩት...ምነው የሞቴን ደብዳቤ እንትለውጠው የግድ ባህራንን መሆን አለብኝ ወይ አልኩት...እየሞትኩ እኮ ነው እንዴት አይታይህም ...ከፈጣሪዬ አማልደኝ ብዬ አለቀስኩበት....ምን እንደገረመኝ ታውቃለህ ረግጣኝ ሄደች ብሎ ጥያቄዬን አለመናቁ....


ረሳሁህ...ልክ እንዳልተፈጠርክ...በቃሽ ሲለኝ ብዙ የምኖርበት አላማ እንዳለኝ ገለጠልኝ....ሲገባኝ ለካ አንተ የሞቴ ደብዳቤ ነበርክ...አንተን ከአእምሮዬ ነጠቀህና የምኖርባቸውን ምክንያቶች ሰገሰገ...ደብዳቤዬን ቀየረው...አየህ እኔም ባህራን ሆንኩ..

ለመጨረሻ ጊዜ ላንተ የምፅፈው ይሄንን ነው..ስላላቀፍከኝ አመሰግናለሁ ....ስለገፋከኝ እግዚአብሄር ይስጥህ...ርቀህ ከፈጣሪዬ ስላቀረብከኝ እድሜ ይስጥህ......


እስቲ የተዉንን ሰዎች እናመስግናቸው....በነርሱ ድልድይነት ከፍ ያለ ቦታችንን ለገለፁልን ሰዎች አንዴ ከመቀመጫችን ተነስተን🙏





Shewit dorka





https://www.tg-me.com/ethioleboled
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
አትሂጂብኝ…

ገና በጠዋጡ ስልኬ እየጮኸ ከተኛሁበት ቀሰቀሰኝ ማን እንደሆነ እንኳን ሳላይ ስልኩን አንስቼ "እእእ..." አልኩኝ ሄሎ ማለቱ ትንሽ ከብዶኛል "ያቡ የት ነህ? ቤት ነህ? ማታ በጊዜ ገባህ? ራስህን አመመህ እንዴ? አሁን ቤት ነህ አደል?" የመአት ጥያቄ ይዘንብ ጀመር

ግራ ገባኝ "ማነው" ብዬ ስልኩን ከጆሮዬ ላይ አንስቼ አይኔን የምችለውን ያህል ጠበብ አርጌ ማን እንደሆነ ለማየት ሞከርኩ ግን ማየት አልቻልኩም አይኔን ደጋግሜ እየጨፈንኩ እና እየገለጥኩ ስልኩን ለማየት ሞከርኩ ጨፍኜ በገለጥኩ ቁጥር እንደ አዲስ እየደበዘዘ ይታየኛል... ደነገጥኩ "እንዴ! አይኔ ምን ሆኖ ነው" ከተኛሁበት ተስፈንጥሬ አልጋው ላይ ቁጭ ለማለት ስሞክር የሆነ ነገር ጭንቅላቴን የመታኝ ይመስል ራሴን ወጥሮ ያዘኝ በትንሹ ራሴን ነቅነቅ እያረኩ ከቆየሁ በኋላ አይኔን አሸት ከቅድሙ የበለጠ አሁን ብዥ አለብኝ ፈራሁ አይኔ ማየት ሊያቆም ትንሽ ደቂቃ የቀረው መሰለኝ በዚ መሀል በእጄ ከያዝኩት ስልክ "ሄሎ ያቡ አይሰማም ሄሎ ሄሎ" ይላል

የወንድ ድምፅ ነው...ማን እንደሆነ በድምፁ ለመለየት እንኳን አልቻልኩም ጆሮዬም ልክ እንደ አይኔ ብዥብሎበታል

ምን ሆኜ ነው ዛሬ!? ጭራሽ እውን አልመስል ብሎ "በህልሜ ነው" እያልኩኝ ራሴን ማሳመን ጀመርኩ ከስልኩ ሚወጣው ድምፅ አሁንም ይሰማኛል

"ሄሎ..ሄሎ..ሄሎ ያቡ"

ከጓደኞቼ ውስጥ አንዱ እንደሆነ አውቄያለሁ ነገር ግን ማንእንደሆነ ማወቅ አልቻልኩም

ባለማወቄ እያፈርኩ "ሄሎ ማን ልበል" አልኩኝ

"ያቡ ቀሰቀስኩህ እንዴ ዳግም ነኝ"

ዳግም ማነው? ዳግም ሚባል ጓደኛ አለኝ?

በድጋሚ ሼም እየያዘኝ

"ይቅርታ ዳግም አላወኩህም" አልኩት

እየሳቀ ''ኸረ ያቡ ስካሩ አሁንም አለቀቀህም ወይስ እየቀለድክ ነው ይልቅ አሁን እንዴት ነህ? ማታ ኮ ጠጥተህ" እስኪጨርስ አልጠበኩትም

"ጠጥተህ ምን!? ማ እኔ ጠጥቼ?" ስልኩ ተቋረጠ

ራሴን በጥያቄ ማስጨነቅ ጀመርኩ "ማታ የት ነበርኩ? አሁንስ የት ነኝ?" ያለሁበትን ቦታ በ አይኔ እየዞርኩ ማየትጀመርኩ

ቤት አደለሁም! አሁን የበለጠ ደነገጥኩ ዙሪያዬን ሳይ አንድ ጠበብ ያለ ቤርጎ ውስጥ ግድግዳ ላይ ከተሰቀለ ቴሌቪዥን እና ጥግ ላይ ብቻውን ከተቀመጠ ወንበር ጋር ራሴን አገኘሁት

ካለሁበት ተነስቼ ለመውጣት ብሞክርም ሚዛኔን መጠበቅስላልቻልኩ እየተንገዳገድኩ የክፍሉ ውስጥ ወዳለው አንድ ወንበር ላይ ሄጄ ተቀመጥኩ ራሴን መጠየቅ ጀመርኩ "ምን ጠጥቼ ነው? ለማስታወስ በጣም እየሞከርኩ ነው "ማታ የት ነበርኩ? ከማን ጋር ነበርኩ? ማነው እዚ ያመጣኝ? አሁንስ ለምንድነው ሚያዞረኝ?" ራሴ በጥያቄ ብዛት ሊፈነዳ ደረሰ

በዚ መሀል እጄ ላይ ያለው ስልኬ ድጋሚ ጠራ

አይታየኝም ብዬ ስላሰብኩ ማን እንደሆነ ለማየት አልሞከርኩም ዝም ብዬ አነሳሁት "ሄሎ" አለኝ...አሁን የማን ድምፅ እንደሆነ ለየሁ "ሄሎ ዳጊ ኸረ ምንድነው የት ነኝ በጣም እያመመኝ ነው' ብዬ የ እርዳታ ጥሪ በሚመስል ጥያቄ ተማፀንኩት "ተነስና ፊትህን ታጠብ ትንሽ ቀለል ይልልሀል" አለኝየጓደኝነቱን

እኔ ግን ፊቴን ከመታጠቤ የበለጠ ያስጨነቀኝ ብዙ ነገር አለ

መጠየቅ ጀመርኩ "ማታ ምን ተፈጠረ" ብዬ የመጀመሪያ

ጥያቄዬን አቀረብኩለት

''ኸረ ያቡ ማታ ኮ በጣም ጠጥተህ ማይሆን ነገር ስትናገር ነበር

"በደንብ ማስታውሰው ሰላም ጋር ደውለህ ብዙ ነገርእንዳልካት ነው"

ይሄን ስሰማ የልብ ምቴ ጨመረ ሰሊ የኔ ፍቅረኛ ናት ምናልባት እሷ ጋ ደውዬ እወድሻለሁ ያላንቺ መኖር አልችልም ምናምን ብዬ ነው ሚሆነው ብዬ እያሰብኩ.. "እሷ ጋር ደውዬ ምን አልኩ?" መልሱን ቶሎ እንዲመልስልኝ እኔም ቶሎ ነው የጠየኩት ከመጀመሪያው ጀምሮ ይነግረኝ ጀመር "እየሰደብካት ነበር "ከዛሬ በኋላ ላይሽ አልፈልግም ባንቺ ምክንያት ብዙ ነገር አጥቻለሁ ከሂወቴ ውጪልኝ ምናምን። ብቻ ብዙ ነገር ብለሀል ያቡ" ብሎ ዝም አለ ልቤ ሲመታ ጆሮዬ ድረስ ይሰማኛል

"ማ..! እኔ ነኝ ሰሊ ጋር ደውዬ ይሄን ያልኩት?'' ለራሴ ማመን እያቃተኝ ጠየኩት

"ለሊቱን ሙሉ ስትደውልልህ ነበር አላነሳኸውም?''

"ቆይ አንዴ" አልኩና ስልኩን ዘግቼ ማን እንደደወለ መየትጀመርኩ

ድነጋጤው ነው መሰለኝ አሁን ጥርት ብሎ ነው ሚታየኝ

46 missed call .. ይላል እሷ ነችእጄ መንቀጥቀጥ ጀመረ...


ፀሀፊ የአብስራ

ከወደዱት ይቀጥላል ግን 👍👍ላይክ እያረጋችሁ
መህምሩ ለተማሪዎች ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ነገር በሙሉ ጽፋችሁ በነገው ዕለት እንድትመጡ ብሎ አዘዘ..

☑️“በዚያ ምሽት ተማሪው ሕልሙን እና ማሳካት የሚፈልገውን ሁሉ ጻፈ እናም እንዲህ ይል ነበር በመጪው 10 ዓመታት የፈረስ እርሻ ባለቤት እንደሚሆን፣ አራት ሕንጻዎች እንደሚኖሩት፣ 200 ሄክታር የእርሻ መሬት እና 4,000 ካሬ ቤት እንደሚኖረው ጻፈ ለዚህም ዝርዝር የወለል ፕላን አዘጋጀ። እና በሚቀጥለው ቀን ለአስተማሪው አስረከበው።

ከሁለት ቀናት በኋላ ወረቀቱን መልሶ ተቀበለ።
አስተማሪው ወረቀቱ ላይ ጉልህ "ኤፍ"አድርጎበታል። ልጁም ተበሳጭና መምህሩን ሄዶ አናገረ።

⚫️አስተማሪውም ይህ እንደ አንተ ላለው ወጣት ልጅ ከእውነታው የራቀ ሕልም ነው። ገንዘብ የለህም፣ የድሃ ቤተሰብ ልጅ ነህ፣ ምንም ሀብት የለህም። የፈረስ እርሻ ባለቤት መሆን ብዙ ገንዘብ ይጠይቃል። 4ሺህ ካሬ እና ትልቅ እርሻ ላንተ "ላም አለኝ በሰማይ ነው" ብሎ ተዛባበተበት። እናም እንዲህ አለ "ማታ እንዳዲስ ሊሳካ የሚችል እቅድ ጻፍና ውጤትህን አስተካክልልሃለው"

➡️"ልጁ ወደ ቤቱ ሄዶ ብዙ አሰበበት። አባቱንም ምን ማድረግ እንዳለበት ጠየቀ። አባቱም "ተመልከት ፣ ልጄ፤ እዚህ ጋር የራስህን ሐሳብ መወሰን አለብህ። እኔ ግን በጣም አምንብሃለውና ልብህን ስማ" አለው።
በነገታው እቅዱን ምንም ሳይቀይር መልሶ ሰጠ አስተማሪውም በ"ኤፍ ግሬዱ" ጸና።

ከዓመታት በኋላ ያ መምህር አርጅቶም እያስተማረ ሳለ አንድ ቀን ማለዳ ላይ በቴሌቭዥን የአንድ ወጣት ቃለመጠይቅ ይቀርብ ነበር... ወጣቱ ልጅ እያለ አሳካዋለሁ ካለው አንድም ያልቀረው የናጠጠ ሀብታም ሆኖ ነበር። እንዲህ አለ "ሕልሜን አስተማሪዬ ሊሰርቀኝ ሲታገል እንደምንም ነበር የተረፍሁት... እኔም ህልሜን እሱም ኤፉን ወሰደ"

➡️የዛኑ ቀን መምህሩ ለተማሪዎቹ ወደፊት ማሳካት የምትፈልጉትን ጻፉልኝ ብሎ አዘዘ በነገታው መለሱለት ለሁሉም የሰጠው ውጤት "ኤ"ነበር።
***
➡️ሞራል፡ መምህራን የጠቀሙ መስሏቸው የስንቱን ሕልም ሰረቁ። በሕልማችሁ አትደራደሩ ለማሳካት የምታስቡት ሁሉ የሚደረስበት እና የተደረሰበት
ነው።
***
💫ዝም ብላችሁ ሳቁ😂😂


እኔ ሲጀመር እነዚህ ጓደኛ ተብዬዎች እያሉ ጤነኛ አልሆንም😁...በሳቅ ቢሞት ኖሮ ይሄኔ ሞቼ ተረስቼ ነበር.....

ከአራት ወር በፊት የሆነ ታሪክ ነው።

አንድ ጓደኛዬ ናት....ላይብረሪ ስትገባ ያየኃት ግፋ ቢል ከ 5 ደቂቃ በፊት ነበር....እየተክለፈለፈች ስትወጣ ጤንነቷ አጠራጥሮኝ መጠየቅ....

"ደህና ነሽ ሴትዮ...አሁን አ እንዴ የገባባሽው...."

"ባክሽ ፋራው መጥቶ ነው...."(የፋራውን ማንነት ለማወቅ ማንበባችሁን መቀጠል ነው)....ማውራቷን ቀጥላለች...."ግራ ግብት የሚለኝ ከየት ነው ሚመጣው...በቀን ሰላሳ ጊዜ ቆይ ሌላ ጓደኛ የለውም እንዴ..."


"ካካካካካ....."....።

"ቆይ ግን እዚ ቅርብ አለ አ እንዴ  እዛ አትሄጂም..."

"ባክሽ ተዘግቷል..."...ከዚህ ንግግሯ በኃላ እንደመሮጥ እያለች ከአይኔ ተሰወረች።

ማታ ላይ ሀዘን የወረራት ሴት መስላ ዶርም ተቀምጣ አገኘዋት...ቆሌዬን አረጋግቼ ምን እንደሆነች መጠየቅ....መልሷን ስሰማ እኔም ነጠላ ዘቅዝቄ ከእሷ ጋር "አይ ሰው ከንቱ" ማለት ጀመርኩ....

"ቅድም ፋራውን ላባርር ሽንት ቤት በገባሁበት ስልኬ ከእጄ አምልጦኝ ገባ....".....ነበር መልሷ(ፋራው ማን እንደሆነ የገባው...😉)

"ማለት ያንቺ ስልክ... ማለት አዲሱ ስልክሽ...."....መቀጠል አልቻልኩም....



አሁን ከአራት ወር ቤተሰብ ጅንጀና በኃላ ባለ ስልክ ሆናለች....(የኔዎቹ አስራ አራት አመት ቢጀነጀኑም ኮሽ አይልባቸውም😕).....ከዛላችሁ እኔ እህታችሁ አዲሱን ስልክ አስታኮ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ምክር ቢጤ መወርወር አሰኘኝ...

"አደራ ከዚህ በኃላ ስልክሽን ይዘሽ መፀዳጃ ቤት አትግቢ...አንዳንዴ ፋራውን ፊት ለመንሳት ሞክሪ...ማስተዋል አለብሽ...ገብቶሻል አ አለማስተዋል ይታይብሻል..ነገ ምን ይመጣብኛል...."....ምናምን እያልኩ ከእርስ እየወጣሁም እየገባሁም ስቀበጣጥር አስቁማኝ ....


"ኧረ ጀለስ አረጋጊው...በዚህ አራት ወር የሆንኩትን እኔ ነኝ የማውቀው..."...ብላ ዝም አለች..

"so ከዚህ በኃላ ስልክሽን ይዘሽ ሽንት ቤት አለመግባት ነው አየሽ ለምሳሌ..."....ያልኩትን ሳልጨርስ ምን ብትለኝ ጥሩ ነው😂😂

"ሴትዮ አፍሽን ዝጊ...አይገርምሽም እንደውም ከዚህ በኃላ አላ*ም...."

"ካካካካካካካካካ እውነትም መሮሻል...."


😂😂😂😂


እና አንዳንዴ የገባበት ሁኔታ በደንብ አድርጎ የመከረውን ሰው መምከር ትርፉ አፍ ማድከም ነው።


መልካም ውሎ።



ሸዊት።



https://www.tg-me.com/ethioleboled
ለፈገግታ😂




"ማንን ነበር ያስገባሽው"....

"ማለት ማሚ..."(የዶርም ተቆጣጣሪ ፕሮክተሮችን ማሚ ነው ምንለው)

"ጥለኃኝ አትሂድ እያልሽ የነበረው ማንን ነው...."

"ኧረ ማሚ ትረካ እየሰራሁ  ነው....ከፈለግሽ ላሰማሽ"


"ኧረ...ትረካ...ሌላስ...እኔ መጫወቻሽ ነኝ....አታታልዪኝም....አሁን ስታዋሪው የነበረው ልጅ ማነው...".....ብላ ባልዲ ውስጥ ሳይቀራት ፈተሸች😂....የሆነ ሰአት የፒሲ ቦርሳ ስትከፍት ሳቄ አመለጠኝ....እግረ መንገዷን ስቶቭ ካላቸው ብላ ይሆናል ብዬ ራሴን አረጋጋውና ሳቄን አባርኩት....

"ይኧውልሽ ሸዊት ትሰሚኛለሽ አንቺም ጎረምሳሽም ችግር ውስጥ ከምትገቡ በጨዋ ደንብ እንነጋር...ቆይ በመስኮት አዘልለሽው ነው...."....አልረዳ ስትለኝ ሪከርድ እያደረግኩ የነበረውን የትረካ ክፍል ከፈትኩላት....

"አዎ እንደዛ ነበር ለጎረምሳሽ ስትይው የነበረው...ከተያዝኩ እንደዚህ አታልላታለሁ ብለሽ ቀድመሽ ተዘጋጅተሽልኛል አንቺ....እከከከከከ ባለጌ...አይጣል አንቺን የወለደች ቱቱ....."....ውሀ በሚያነሳ ነጥብ ላይ ፕሮክተር ይረዳኛል ብሎ ከማስረዳት አንድ አህያ ጋር ሄዳችሁ

"እኔ ህይወት መሮኛል...ቺኬ ጥላኝ ፈርጥጣ ይኧው ምግብ የመጨረሻ ዘግቶኛል"....ብትሉት የወንድምነቱን ይመክራችኃል😂 አፍ አውጥቶ "በቃ ብሮ ተዋት...እኔ ጋር አንድ አራት አሉ...ያው አህያ ስለሆኑ እንዳይደብርሽ እንጂ...እና አንድ አንዴ እኔ ጋር እየመጣሽ ጋጪ... ያጋጥማል...."....ሊላችሁ ሁላ ይችላል😂


ብቻ ከብዙ ንትርክ በኃላ ጓደኛዬ መጣች....

"ማሚ አንዴ ነይ ላናግርሽ..."...ብላ ይዛት ስትወጣ ምን ብላ እንደምታሳምናት ግራ እየገባኝ መምጣታቸውን በጉጉት መጠበቅ ያዝኩ።


ከጥቂት ደቂቃዎች በኃላ ተያይዘው መጡ...ለያዥ ለገናዥ ያስቸገረችው ሴትዮ አሁን እንደ ተነፈሰ አፉፋ ሙሽሽ ብላለች...ጓደኛዬ ፊት ላይ የታፈነ ሳቅ አለ...ሴትየዋ ፊት ላይ ደግሞ የሆነ አይነት አዘኔታ....

"ምፅ...ዘንድሮ ነው አይደል የምትመረቂው...."

"አዎ ምነው...."...ይሄኔ ጓደኛዬ ከነ ሳቀ ፊቷ ከጎኔ ቆመችና በእጇ ቀስ አድርጋ ጎነተለችኝ....

"አይዞሽ...እኔም ሴት ልጅ አለኝ...አይዞሽ እማ...የኪዳነ ምህረትን ፀበል ተጠመቂ...አይዞሽ ምንም አያመጣም...አይነጥላ እኮ ነው....ውይ የእኔ እናት....."......ጓደኛዬ የሚተናነቃት ሳቋን በውሸት ሳል እየደበቀች ክንዴን በስሱ ትቆነጥጠኛለች።

ጀለስ ለካ መንፈስ ያማታል ብላት ነው ያረጋጋቻት....


"አንድ አንዴ በሀይለኛው ያስጮሀታል ስላልኳት የሚጮሁ ፓርቶች ላይ መስኮት መዝጋትና በር መጠቅጠቅ አይጠበቅብሽም...እኔ ጓደኛሽ ልኑርልሽ ካካካካካ".....


አሁን ይቺን ልጅ ብገላት ይፈረድብኛል🤨



እናላችሁ አሁን እንደ እንቁላል ነው treat የምደረገው😂



የትረካውን ሊንክ ቻናሌ ላይ ታገኙታላችሁ😊መልካም አዳር።




https://www.tg-me.com/ethioleboled
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
አትሂጂብኝ…

ፀሀፊ የአብስራ

እስካሁን የዘነበብኝ እያንቀጠቀጠኝ ነው

የነ ሰላምን በር በሀይል ማንኳኳት ስጀምር

እናቷ ከ ጊቢው ውስጥ ሆነው "ኸረ ማነው!'' እያሉ በሩንለመክፈት እየመጡ ነው

ድጋሚ በሩን በሀይል ደበደብኩት

"ኸረ ቀስ ማነው!'' እናትየው እየተቆጡ በሩን ከፈቱት
የሰላምን እናት ለመጀመሪያ ግዜ በአካል አየኋቸው እስከዛሬ የማውቃቸው ሰላም ስለ እሳቸው ስትነግረኝ ነው

ዛሬ ግን አይን ለ አይን ተያየን

ከሰላም ጋር በጣም ነው ሚመሳሰሉት

በተለይ አይናቸው እና አፍንጫቸው አከባቢ እራሷ ሰላምን!ሰላም ቁጭ በእናቷ ነው የወጣችው!

በሩን ከከፈቱ በኋላ የልብሴ መጨቅየት እና የሰውነቴን መንቀጥቀጥ ሲያዩ ደነገጡ

እብድ መስያቸው ነው መሰለኝ ግራ ተጋብተው "ምነው ልጄ ምን ሆንክ" ብለው ጠየቁኝ ገረመኝ! ድምፃቸውም ከሰላም ጋር አንድ አይነት!

ብርዱ እያንቀጠቀጠኝ ''ሰሰሰ....ሰ..ሰላምን ፈልጌ ነው"
ቆጣ ብለው "ሰላም የለችም!'' አሉ "የ.የ.የ.የ የት ሄ.ሄደች?"

አልኩኝ በ እናትየው ትከሻ በኩል ወደ ጊቢው እያየሁ "እኔ ምን አውቄ" አሉና በሩን ገፈተሩት እዛው በቆምኩበት በሩ "ጓ..." ብሎ ተዘጋ

ጠረጠርኩ...እናትየው የሆነ ሚያውቁት ነገር ሳይኖር አይቀርም ምናልባ ሰላም ስለኔ ነግራቸው ይሆን? አይ አይ አይሆንም! ልትነግራቸው አትችልም!

ሰላም ትመጣለች ብዬ ስላሰብኩ እዛው በር ላይ እየተንቀጠቀጥኩ ተቀምጫለሁ እጄን ወደ አፌ አስጠግቼ በ አፌ ትንፋሽ እጄን ለማሞቅ እየሞከርኩ ነው

"ትትትትት..ት ት ትመጣለች"

አዛው በሩን ተደግፌ እንደተቀመጥኩ ግራና ቀኙን እያየሁ ቀኑ መሸ ምንም ሰው ሚባል ነገር ሰፈር ውስጥ የለም ብርዱ ከቅድሙ አሁን እየባሰ ሲመጣ እንደምንም ተነስቼ ወደ ቤት ሄድኩ

ቤት እንደገባሁ የረጠበውን ልብሴን ቀይሬ አልጋዬ ላይ ጋደም ብዬ እየተንቀጠቀጥኩ እንቅልፍ ወሰደኝ
ጠዋት ከ እንቅልፌ ስነሳ ግን በጣም ታመምኩ ያስለኛል፣ ያስመልሰኛል፣ ራሴ ግሏል፣ ያዞረኛል...በትላንቱ ዝናብ እና ብርድ ምክንያት እንደሆነ ገብቶኛል

እንደዚሁ በህመም ለ አራት ቀን ስሰቃይ ከቤት ሳልወጣ

ታምሜ ያሳለፍኩት አራት ቀን ሰላምን እንዳላገኝ አርጎኛል ገና ያመመኝ ቀን ነበር የሰላም ነገር ያስጨንቀኝ መደወሌን አላቋረጥኩም ሁሌ እደውላለሁ ግን ስልኳ ሁሌ ዝግ ነው ዛሬ ተሽሎኝ ቤቷ እሄዳለሁ! ወይም ደሞ ነገ ይሻለኝና እሄዳለሁ እያልኩ አራት ቀን በስቃይ ካሳለፍኩ በኋላ በ አምስተኛው ቀን ባይሻለኝም ተሽሎኛል ብዬ ራሴን አሳምኜ ከቤት ወጣሁ

እነ ሰላም ቤት ስደርስ እንደበቀደሙ በሩን በሀይል አላንኳኳሁም

ረጋ ብዬ በሩን "ኳ.ኳ.ኳ.ኳ.ኳ.ኳ" አረኩት "ማነው" አሁንም የበቀደሙ ድምፅ

በሩ እስከሚከፈት መጠበቅ ጀመርኩ

በድጋሚ "ማነው!"

አሁንም መልስ አልሰጠሁም ዝምታን መረጥኩ

በሩ ተከፈተ
የሰላም እናት ለ ሁለተኛ ጊዜ አዩኝ

"እንዴት ኖት እማማ..ባለፈው መጥቼ ሰላም የለችም

ዝም ብዬ መቆየት ስላልቻልኩ

ብለውኝ ነበር ዛሬ ትኖራለች ብዬ ነው የመጣሁት" ፊታቸውን አኮሳትረው በዝምታ ያዩኝ ጀመር "ዛሬም የለችም?'' አልኩኝ ዝም ብለው የቆዩት የሰላም እናት "ሰላም ከዚ በኋላ እዚ የለችም" ብለው በሩን ዛሬም ወርውረው ዘጉብኝ

ደነገጥኩ...ቆይ ምንድነው የተፈጠረው? ለምድነው ሰላም ቤቷ የሌለችው? ለምንስ ነው እናትየው ሲያዩኝ እንደዚ የተበሳጩት? ብዙ ጥያቄ በውስጤ እየተመላለስ ያስጨንቀኝ ጀመረ

ጭንቀቱን መቋቋም ሲያቅተኝ ስልኬን አንስቼ ለሁሉምየሰላም ጓደኞች መደወል ጀመርኩ

አስካሁን ስድስት ጓደኞቿ ጋር ደውዬ አናውቅም ብለውኛል በ ሰባተኛው መቅደስ ጋር ደወልኩ..

"ሄሎ መቅዲ! ከሰላም ጋር ተገናኝታቹ ታውቃላቹ እንዴ?!

"ያቡ ሰላምታ አይቀድምም?"

ለሰላምታ ጊዜ አልነበረኝም ስልኩት ዘግቼ ሌላኛዋ ጓደኛዋጋር ደወልኩ

"ሄሎ ኤፍራታ ሰሞኑን ሰላምን አግኝተሻት ታውቂያለሽ?!

"እእእእእ...አው ምነው?"

ስፈልገው የነበረውን መልስ ሰማሁ! በውስጤ ኡፍፍፍፍፍስል ይሰማኛል

"የት ናት?" ሰሞኑን ትንሽ ተጣልተን ላገኛት አልቻልኩምበናትሽ ላወራት ፈልጋለው የት ናት?"

"እሱን ልነግርህ አልችልም"

"ለምን!?" ግራ ገብቶኝ ጠየኳት

"እሺ እኔ እንደነገርኩህ እሷ እንዳትሰማ!"

"አትሰማም እውነት አልነግራትም ንገሪኝ"

"አክስቷ ጋር ሀዋሳ ሄዳለች"

"ሀዋሳ !?"

አላለቀም
ከወደዳችሁት ይቀጥላል
Https://www.tg-me.com/ethioleboled
እንባና ሳቅ @Bemnet_Library.pdf
17 MB
--

ርዕስ=ዕንባና ሳቅ(ልቦለድ)

ደራሲ=ገበየሁ አየለ

የገፅ ብዛት= 223

📚 @Bemnet_Library
አስበህ ሀብታም ሁን! @Bemnet_Library.pdf
18.5 MB
ሚኪ "Think and Grow Rich" ወይም በአማርኛው "አስብህ ሀብታም ሁን" የሚለውን "የናፖሊዮን ሂል" መጽሐፍ ጠይቋል፤ይህው ሚኪ መልካም ንባብ😘

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
የፍቅር ኬሚስትሪ @Bemnet_Library.pdf
23.5 MB
ሮዝ "የፍቅር ኬሚስትሪ" የተሰኘውን
የብርሀኑ ንጉሴ ምርጥ መጽሐፍ ጠይቃለች፤ ይህው ሮዝዬ መልካም ንባብ😘

📚 @ethioleboled
የጭን ቁስል @Bemnet_Library.pdf
15.6 MB
ዳምጦ "የጭን ቁስል" የተሰኘውን የተክሉ ጥላሁንን መጽሐፍ ጠይቋል፤ይህው ዳምጦዬ መልካም ንባብ😁

📚 @ethioleboled
የብርሃን ፈለጎች @Bemnet_Library.pdf
7.3 MB
ዳንኤል "የብርሃን ፈለጎች " የተሰኘውን የአለማየሁ ገላጋይ መጽሐፍ ጠይቋል፤ይህው ዳኒ መልካም ንባብ😘

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
የአና ማስታወሻ @Bemnet_Library.pdf
13.9 MB
ሄለን "በአና ፍራንክ" የተፃፈውን "የአና ማስታወሻን" ጠይቃለች።ይሄ መጽሐፍ አለማችን ላይ በጣም ከተወደዱና ዝናን ካተረፉ መጽሐፎች ውስጥ አንዱ ነው።ይህው ሄሉዬ መልካም ንባብ😘

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
አትሂጂብኝ…

ፀሀፊ የአብስራ


ሀዋሳ እንደሄደች ስሰማ ወደ ሀዋሳ መሄድ እንዳለብኝ ወሰንኩ

እንደ ሁል ጊዜው መሽቶ ነጋ
ሲነጋ ግን እኔ ወደ ሀዋሳ የሚሄድ አውቶቢስ ውስጥ ተቀምጫለሁ

12 ሰዓት ሲሆን አውቶቢሱ ጉዞውን ወደ ሀዋሳ ጀመረ ህመሙ አልተሻለኝም በጣም እያመመኝ ነው

ሰላምን እያሰብኩ መሄዴ ግን በትንሹም ቢሆን ህመሙንእያስረሳኝ ነው

በተቀመጥኩበት የ አውቶቢስ ወንበር አንገቴን ዘንበል አርጌ እንቅልፍ በትንሹ ወሰድ መለስ እያረገኝ ነው አሞኛል.. እያቃሰትኩ ነው.. ለኔ ግን አልታወቀኝም! እንደዚሁ ህመም እያሰቃየኝ ሀዋሳ ደረስኩ
የ አውቶቢሱ ረዳት ከእንቅልፌ ቀስቅሶ
"አባ ተነስ ደርሰሀል!'' ሲል ሰማሁት
ሰውነቴ ዝሏል መነሳት ከበደኝ

ከተቀመጥኩበት እንዲያነሳኝ ለረዳቱ እጄን ሰጠሁት እሱም ደግፎ ከመኪናው አወረደኝ

የተሸከምኩት ትንሽዬ ቦርሳ ኩንታል ሙሉ ማዳበሪያ የተሸከምኩ ያህል ከበደኝ
ቦርሳው ብቻ ሳይሆን የለበስኩት ልብስም ሳይቀር ሸክም ሆኖብኛል

ከመኪናው እንደወረድኩ አይኔን ጠበብ አድርጌ ያለሁበትን ማየት ጀመርኩ ተመሳሳይ አውቶቢሶች ተደርድረው
ቆመዋል ፀሀይ ለኔ ብቻ ያበራች ይመስል ሰውነቴን ማቃጠል

ጀምራለች የማላውቀው ከተማ ላይ ከማላውቃቸው ሰዎች ጋር መሆኔ
ትንሽ አስፈራኝ ትከሻዬ ላይ ያለውን ቦርሳ መሬት ላይ ጣል አረኩት ኡፍፍፍፍ ትንሽ ቀለል አለኝ

አሁን የት ነው ምሄደው? ጎኔን ማሳርፍበት ቦታ ማግኘት አለብኝ!

በአይኔ ታክሲ እየፈለኩ ነው
ብዙ የታክሲ ረዳቶች የሚሄዱበትን ቦታ ስም እየጠሩ ሰውእየጫኑ ነው

"ፒያሳ ፒያሳ" የላል አንዱ የታክሲ ረዳት ከሩቅ ሆኖ!

ፒያሳ ሀዋሳ ውስጥ ካሉት ፀዴ ሰፈሮች አንዱ ነው ለምሳሌ ቦሌ ለ አዲስ አበባ የሚሰጠውን ድምቀት ያክል ለ
ሀዋሳ ደሞ ፒያሳ አለችለት!

ወደ ፒየሳ መሄድ ብፈልግም ገና ከዚ ተነስቼ ታክሲው
ያለበት ድረስ እንደምሄድ ሳስብ ህመሜ እና ድካሜ ተደምረው እንዳልሄድ ከለከሉኝ..

"ፒያሳ ፒያሳ!'' እያለ ከሚጠራው ትንሽ ቀረብ ብሎ ደሞ "ሞቢል፣ ጥቁር ውሀ" ይላል ሌላ ታክሲ

ሁለቱም እሩኡኡኡ.....ቅ የሆኑ ያክል ተሰማኝ ራሴን በጣም እያዞረኝ ስለነበር የጣልኩትን ቦርሳዬን አንስቼ አጠገቤ ወዳለው ታክሲ ውስጥ ዘው ብዬ ገባሁ

እኔ የገባሁበት የታክሲ እረዳት ከውጪ ሆኖ .ዳቶ.......  ዳቶ

ዳቶ የት እንደሆነ አላውቅም...ነገር ግን አማራጭ ዳቶ የት እንደሆነ አላውቅም...ነገር ግን አማራጭ
አልነበረኝም ደክሞኛል፣ አሞኛል፣ ሰውነቴ ዝሏል፣

እርቦኛል። የማላውቀው ከተማ ታምሜ መምጣቴ ሳያንስ፤የማላውቀው ሰፈር ሄጄ ልንከራተት ነው።ኤጭ ምን አይነት እዳ ነው!! ምርር አለኝ


ዳቶ የሚባለው ሰፈር ደረስኩ.. ገና ከታክሲው ወርጄ ቀና ስል "ፕላዛ የ እንግዳ ማረፊያ" የሚል ትልቅ ፅሁፍ ያለበት

ፎቅ አየሁ

እንዳሰብኩት ሳልደክም ማረፊያ ቦታ ማግኘቴ ደስ እያለኝ ገብቼ አንድ ከፍል ይዤ የዛለውን ሰውነቴን አሳረፍኩት
እዛው ጋደም ባልኩበት እንቅልፍ ወሰደኝ
ትንሽ ቆይቼ ከ እንቅልፌ ነቃሁ

እንደነቃሁ ስልኬን ከኪሴ አውጥቼ ኤፍራታ (የሰላም ጓደኛ) ጋር ደወልኩላት
አነሳችው

"ሄሎ ኤፍራታ እንዴት ዋልሽ?"

"ደና ነኝ እንዴት ነህ?"

"ደና ነኝ ሰላም ሀዋሳ አክስቷ ጋር ናት ብለሽኝ ነበር

አደል?"

"አው አው! እኔ እንደነገርኩህ ግን ማወቅ የለባትም חו!"

"ማንም አያውቅም አታስቢ፤ አሁን እሷን ፍለጋ ሀዋሳውስጥ ዳቶ ሚባል ሰፈር ነው ያለሁት።

"ምን..!" ደነገጠች

"አው ምነው!'' እኔንም አስደነገጠቺኝ

"እንዴት! ቆይ ባንተ ምክንያት ነው እንዴ ስልኳን አጥፍታ
አክስቷ ጋር የሄደችው?"

"እኔንም ግራ ያጋባኝ እሱ ነው?"

"ቆይ ምን ተፈጥሮ ነው?" ጠየቀቺኝ

መመለስ ማልፈልገውን ጥያቄ!

ምን ብዬ ነው ምነግራት?

ሰክሬ እገልሻለው አልኳት ነው ምላት?
ምን ብዬ? ምን ተብሎ ይነገራል?

"ምነው ዝም አልክ ነገረኛ! ምን ተፈጥሮ ነው!'' ለሁለተኛ

ጊዜ ጠየቀቺኝ

"ይኸውልሽ ኤፊ" ከ አንድ ሳምንት በፊት ከ ጓደኞቼጋር ተገናኝተን እየጠጣን ነበር... ከዛ ትንሽ ከጠጣን በኋላ እየሩስ እኔ ጋ ደወለች...ትንሽ ሞቅ ብሎኝ ስለነበር እየተቆጣሁ እና እየተሳደብኩ ስልኩን ዘጋሁባት እሷ ግን ደጋግማ መደወል ጀመረች እኔም በተደጋጋሚ ስልኩን
እያነሳሁ እየተሳደብኩ ዘጋሁት
በዚ መሀል ሰላም እኔ ጋር ደወለች እኔም እየሩስ የደወለች መስሎኝ ስልኩን አንስቼ

"አንቺ ከሀዲ ከዚ በኋላ ካንቺ ጋር ምንም የማወራው

ነገር የለም ተይኝ ከዚ በኋላ ድጋሚ ለመደወል ብትሞክሪ ያለሽበት ድረስ መጥቼ አንቄ እገልሻለሁ" ብዬ ስልኩን ለ አንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ዘጋሁባት

በነጋታው ከ እንቅልፌ ነቅቼ ስልኬን ስከፍተው ሰላም እኔጋር 46 ጊዜ ደውላ ነገበርመልሼ ስደውል ስልኳ እምቢ አለኝ

አንዱ ጓደኛዬ ጋር ደውዬ ስጠይቀው ማታ የተፈጠረውንነገር በሙሉ ነገረኝ እንጂ እኔ ምንም የማስታውሰው ነገር አልነበረም"
ይሄን ሁሉ ነገር ሳወራ ኤፍራታ ዝም ብላ እየሰማቺኘሰ ነበር

ትንሽ ዝም ብላ ከቆየች በኋላ
"እሺ ቆይ አድራሻዋን ልላክልህ" አለችና ስልኩን ዘጋችው
አሁን ትንሽ ህመሙ ቀለል ብሎልኛል
በጣም ስለራበኝ ምግብ አዘዝኩ...

ብዙም ሳይቆይ አንድ አስተናጋጅ ምግቡን ይዞ መጣ ያመጣውን ምግብ አስቀምጦ ሊወጣ ሲል "ሰው ብጠይቅህ ታውቃለህ?" አልኩት ደገምኩለት "እዚ ሀዋሳ ሰው ፈልጌ ነው የመጣሁት ቤት አስተናጋጅ ይሄን ጥያቄ መጠየቄ ለራሴምበ እጁ የያዘውን የለስላሳ መክፈቻ እያሽከረከረ "ምን አልከኝ ወንድሜ?" አለ

እባክህ ምታውቅ ከሆነ ብትረዳኝ?"

ከዛሬ ውጪ አይቼ የማላውቀውን አንድ የምግብ ገርሞኛል...ቢጨንቀኝ ኮ ነው!

የያዘውን የለስላሳ መክፈቻ ወደ ኪሱ ከተተና "የምትፈልገው ሰው የት ሰፈር ነው?" ሲል ጠየቀኝ

ስልኬ በትንሹ ጮኾ ዝም አለ

አንስቼ አየሁት ኤፍራታ የሰላምን አድራሻ በ message ላከችልኝ
"Ye akstua sm belay nesh nw yalechbet sefer demo 05" ...

ፈጠን ብዬ ለ አስተናጋጁ "ያለችበት ሰፈር 05 ነው በላይ ነሽ ምትባል ሴቲዮ" ታውቃታለህ?"

አስተናጋጁ ፈገግ እያለ "አላውቃትም! ነገር ግን ሀዋሳ ውስጥ ያለ ሰው ፈልገህ ልታጣ አትችልም! ነገ ስራ እረፍት ስለሆንኩ አብረን ሄደን እንጠይቃለን"

"የምርህን ነው!??"

"አው ችግር የለውም"

Https://www.tg-me.com/ethioleboled
2024/09/21 23:05:28
Back to Top
HTML Embed Code: