Telegram Web Link
ነበር....3





"እቴቴ..."...ደነገጠ።

"አሁኑኑ ልብስህን ሰብስብ...."....አሁንም ትዕዛዝ...

"ለምን...?"....ጠየቀ...

"ምንም የመጠየቅ መብት የለህም...የምልህን አድርግ!!!"....ይሄን ሲሉ እርሱ የሚያውቀው እንስፍስፍ ድምፃቸው ተለይቷቸው ነበር....

"እቴቴ አልገባኝም..."

"ሁሉንም ነገር አውቃለው..."....ይሄን ሲሉ ደግሞ ከድንጋጤም የላቀ ድንጋጤ...ከበድንነት የባሰ መበደን...ነብሱ ከስጋው ተላቀቀ....

"ማለት...እ...ምንድን ነው ምታውቂው..."...

"ስለ ሁሉም..."

"አታውቂም....አይይይ እቴቴ ምንም አታውቂም...ብታውቂማ....ብታውቂ...እ...እ..."....እንባው ከቃላቶቹ ጋር እሽቅድድም ገባ....


"ሽሽሽሽሽ....አትጩህ....ሁሉንም አውቃለሁ...ልብስህን ያዝና እንሂድ.."....አሉት ለእርሱ ብቻ በሚሰማ ድምፅ...ከመኝታ ቤቱ በር ላይ ተለጥፈው ከሚያዳምጡት ሰዎች ጆሮ ለማምለጥ...ለታ ከቅድሙም መበደኑ ያሁኑ ባሰ...ደነዘዘ....አይኑ ቀና ብሎ ሊያያቸው ድፍረት አጣ...


ይሄኔ የክብሮም እናት እሱን ትተው ከቁም ሳጥኑ አናት ላይ ወዳለው ሻንጣ ሽቅብ አማተሩ...ከዛም ቁም ሳጥኑን ከፍተው መርጦ እንዲለብሰው ሳይሆን እንዲሁ ሻንጣው እንዲሞላ ብቻ ጠቀጠቁት.....


"እንሂድ!"...አሉት ጀርባቸውን ለእርሱ ፊታቸውን ለበሩ ሰጥተው...
"ወዴት..."...ጠየቀ...
"ልጄ ወደ ሄደበት!!!!"


ከመኝታ ቤቱ ተያይዘው ወጡ....


ከዋናው በር ሳይወጡ ድንገት ለታ "እማ" ብሎ ተጣራ......አኳሀኑን አይተው ስንብቱ ፀበል ሳይሆን ለዘላለም ከማይመለስበት የሚሄድ የመሰላቸው እናቱ እንባቸው የሚገራ አልነበረም....አባቱ ዝም እንዳሉ ናቸው...የእሳቸውን መልስ የሚጠብቅ በረከተ....እሳቸው ግን በመመለስ ፈንታ ከነዝምታቸው አቀረቀሩ። የክብሮም እናትና እናቱ ተቃቅፈው መላቀሳቸውን ጀመሩ....


ይመስላል እንጂ የክብሮም እናት እንባ ለለታ አልነበረም....እንደዋዛ መጣሁ ብሎ ለቀረ ልጃቸው እንጂ....


"አይዞሽ እታግዬ..እኔ እናቱ እያለሁለት..."..ይላሉ የክብሮም እናት

"ግድ የለሽም እኔም አብሬያችሁ ልምጣ...ደግሞ አልጠመቅም ብሎ ሊያስሸግርሽ ይችላል...እናቱ አይደለሁ አመሉን አውቃለሁ..."....ይላሉ የለታ እናት....

"በትግል ነው ያሳመንኩት እታግዬ ደግሞ ከእኔ ውጪ ማንም አብሮት እንደማይመጣ በክብሮሜ ምዬለታለሁ...".....ድምፃቸውን ቀስ አድርገው ከለታ እናት ጆሮ ስር ቃላት ወረወሩ....

ጎረቤቱ በሩን ግጥም አርጎ ዘግቶ የሚፈጠረውን ያያል...በመሀል የክብሮም እናት እንደ ሙሴ በትር ሰልፉን ሰንጥቀው ወጡ....ለታ ከተገተረበት አለ....እናቱ እያገለባበጡ ይስሙታል....

"ተይ እንጂ ሆዱን አታባቢው...ና ልጄ ና...".....ለታ አሁንም ካለበት ንቅንቅ አላለም....የክብሮም እናት ተመልሰው ሄደው እጁን ይዘውት ወጡ...ለታ አሁን ሰው አይደለም...አሻንጉሊት ነው...ለታ አሁን በክብሮም እናት ብቻ የሚሰራ ማሽን ነው...ለታ አሁን የክብሮም እናት ብቻ የሚያጫውቱት ከረንቡላ ነው።


ተያይዘው ወጡ።



የለታ ቤተሰቦች ልጃቸውን ለክብሮም እናት አስረክበው መላቀሳቸውን ተያይዘውታል...በአንድ በኩል የልጃቸው መገራት እና ወደ ፀበል መሄድ አንዳች እፎይታን አላብሷቸዋል...እንዲሁ ግን ግር ያላቸው ነገር አለ...እንዴት የለታ ሀሳብ በቅፅበት ተቀየረ...? አያውቁም...ቢሆንም እንደ ሁለተኛ እናቱ በሆኑት የክብሮም እናት ላይ ሙሉ እምነት አላቸው...የገቡበት ራይድ ከአይናቸው እስኪሰወር ቆመው በአይናቸው ሸኙት.....


ሹፌሩ ከማናቸውም ጋር ምንም አላወራም...ዝም ብሎ መንገዱን ይሄዳል...



ለታ ሹፌሩ የክብሮም እናት ቅጥረኛ እንደሆነ ጠረጠረ...ቢሆንም ምንም ከማለት ተቆጠበ....መኪናው ወደነ ክብሮም ቤት አይደለም የሚሄደው...ቀስ በቀስ መኪናም ሰውም እየቀነሰ ሄደ....የልቡ መራድ ሲያይልበት መዳረሻቸውን ለመጠየቅ ደፈረ...


"ወዴት ነው ምንሄደው..."...አለ አንዴ ሹፌሩን አንዴ የክብሮም እናትን እያየ...


"እቴቴ..."....ተጣራ...አሁንም መልስ የለም....እሳቸው እንኳን አቤት ሊሉ ቀርቶ ወደ እርሱ ቢያዩ የሚረገሙ ይመስል ፊት ነስተውታል....




*



"ፍትህ ግን ቆንጆ ናት አይደል...."...ለታ ነው ይሄን ባዩ

" ቆንጆ አታውቅም "...መለሰ ክብሮም..

"እያት እስኪ ምን ይወጣላታል"

"ወደሀታል...?"...ክብሮም ጠየቀ...

"አልወጣኝም...እንዲሁ ነው..."

"አደራህን እንዳይወጣህ...እኔ የፉንጋ ጓደኛ መሆኔ ሳያንስ ደግሞ የፉንጋ አጎት መሆን አልፈልግም...ካካካካ...ልጃችሁን አሰብኩት...ካካካካ"


"በለው ከምኔው አጋብተኧን ከምኔው ወለድን...."...ለታ በክብሮም ተረባ ውስጡ አይረበሽም...ፉንጋነቱንም አይክድም...ፍትህ ፉንጋ መባሏና በክብሮም አይን ማነሷም አልጎረበጠውም...በትንሹ በእርዋ ላይ secure የመሆን ስሜት ሽው አለበት....


ከስራ ባልደረባቸው ከፍትህ ልደት ላይ ተገኝተው ጥግ ይዘው ያወራሉ...


"ግን የምሯን 25 አመቷ ነው"...ለታ የግርምት በሚመስል ድምፀት ይቺን አለ።

"ምነው አትመስልም አይዞህ አታስብ...በደንብ ትፈለፍላላችሁ...አታይም አቀለጣጠፏን...እኔን ወንድሜ አሳሰበህ አይደል ሜኖፖዝዋ ካካካካ"...

"ኧረ በፈጠረህ ድምፅህን ቀንስ..."....ለታ በክብሮም ድምፅ ተሳቀቀ...

"ለማንኛውም ወደ ቁም ነገሩ ስንገባ ትክክለኛውን ሰው ነው የጠየቅከው...ና ጠጋ በል"...አለ ክብሮም በሹክሹክታ...

"ስማ....25 አመት ንዑስ ቁጥር D ላይ ናት....

"ምን ማለት ነው ደግሞ ይሄ...."

"ማለትማ 25ተኛ አመቷን ለአራተኛ ጊዜ እያከበረች ነው...ምን አልባት E ካልገባ ቀጣይ 26 የመብላት ተስፋ አለን...ካካካካካ..."....ይሄኔ ለታ ሳቁን መቆጣጠር አቃተው....ቦታ ተቀያየሩና የለታ ሳቅ የፍትህ ትኩረት ጋር ደረሰ...


"ኧረ በፈጠረህ ለታ ፍትህ አኳሀናችን ግራ እያጋባት ነው እያየችን ነው"....ክብሮም ይሄን ሲል ለታ ሳቁን ባንዴ ቆረጠው...

"ኧረ ጓዴ ለዚህ ነበር ያዙኝ ልቀቁኝ..."


"ካየችን ይደብራታል ብዬ እኮ ነው..."


"በዚህ አይነት ሌላም ነገር ስታቋርጥ አትቸገርም ካካካካ..."....የሁለቱም ሳቅ ጣሪያ ነካ...





አላለቀም....ኧረ react....ዝም ብዬ ከምፅፍ ስሜታችሁን ልወቀው....ከወደዳችሁት 👍 ተጫኑ




Shewit dorka





https://www.tg-me.com/ethioleboled
ግርማዊ ጃንሆይ (ቀ.ኃ.ሥ) ከልጃቸው ልዕልት ፀሐይ ጋር ፤

ጳጉሜ/ 1928 ዓ.ም

ኢንግላንድ -- ለንደን

#ታሪክን_ወደኋላ
ነበር...4






"ፍትህ ግን እንደስሟ ናት..."....አለ ለታ ከርቀት አተኩሮ እያያት...አስተያየቱን ላየ ሰው ሳይሆን የፀሀይ ወገግታን የሚመለከት ይመስላል....

"ካካካካ እንደስሟ...ስትል"....ክብሮም ከሳቁ በኃላ ስለ ፍትህ ፍትህነት እንዲብራራለት ጠየቀ...ለታም ማብራራት ያዘ....

"የህፃን ልጅ ልብ ነው ያላት...እንደህፃን ልጅ የለሰለሰ ገላዋን እንጂ ማንም ልቧን አያይም...."....


"አየኧው እኮ አንተ...አይበቃም ካካካ....መቼ ነው ደግሞ ውጯን ጨርሰህ ወደ ውስጧ የገባኧው ካካካካ...."

"ድሮም ቁም ነገር ሲወራ ችግር አለብህ..."...ለታ በክብሮም ቀልድ ለመጀመሪያ ጊዜ ተበሳጨ....

"የምሬን እኮ ነው...ፍትህ እንደስሟ ፍትህ ናት ስትለኝ እንድታብራራልኝ እድሉን ሰጠሁህ...ከዛ አንተ ምን አልከኝ 'የህፃን ልጅ ልብ 'ምናምን...it doesn't make sense..."

"ምኑ ነው ውሀ ማያነሳው...?"...ለታ ጠየቀ....

"ህፃን ልብ አላዋቂ ነው...ፍትህ ደግሞ ከማንም በላይ አዋቂ ነው...ህፃንነት ለእኔ ብቻ የሚል ጥሬነት ነው...ፍትህ ግን ብስል ነው...ፍትህ የለሰለሰ መሬት ብቻ አይደለም...አንዳንዴም ከእሾህ መሬት የበለጠ አድሚ ነው...."

"ኧረ ክብሮም ተረጋጋ ምንድን ነው ይሄ ሁሉ ፍልስፍና...."

"ይሄን ለማወቅ መፈላሰፍም መጠበብም አያስፈልግም....በቀላሉ አይንህን መክፈት ብቻ ነው ሚጠበቅብህ....ፍትህን ቀለል አርገህ 'እንደ ስሟ ናት' እንድትል ያደረገህ የማላውቀው ትውውቅ ካለ ንገረኝ...ካልሆነ ግን የለሰለሰ ገላዋን ከጠራው ቆዳዋ ጋር ደምረህ ከዛም እንደ ባዘቶ የጠራ ጥርሷን እንደማስረጃ ተጠቅመህ ምንም ስለማታውቀው ልቧ ማውራት አትችልም...."....ክብሮም ይሄን ሲል ለታ የሆነ ቦታ ጋር እንዳዳለጠው ገባው....ምነው ምላሴን በቆረጠው አለ በልቡ...

"አልገባህም ...አንተ ምኑም አልገባህም...."....ለታ ይሄን ካለ በኃላ ከክብሮም የሚሰነዘርበትን ጥያቄ እያሰበ በላብ ተጠመቀ...ክብሮም ከጨዋታ አዋቂነቱ ሌላ ቁም ነገረኛም ነው...በምክንያታዊነት ያምናል...

"ምኑ ነው ያልገባኝ...."....የክብሮም ጥያቄ ተከተለ....ይሄኔ ለታ የያዘውን ቢራ በአንድ ትንፋሽ ጨለጠ...ክብሮም የጓደኛውን አኳሀን አይቶ ፍቅር ቢጤ ነገር ጀማምሮት ይሆናል አለ በልቡ...


"በጣም እየመሸ ነው...ብንሄድ ይሻላል..."....ለታ ነው ይሄን ባዩ...ከጥያቄው ሽሽት እንጂ ገና ከምሽቱ ሁለት ሰአት ነበር....ክብሮም ምንም ነገር ማለት አልፈለገም...

'ፍቅር ውስጥ ነው...ክብሮም በቃ ጓደኛህን ከራሱ ጋር ተወው'....ብሎ ራሱን ገሰፀ።



**



መኪናቸው መጓዙን አላቆመም....


"እቴቴ...."....አለ እየፈራም እየተባም

"እቴቴ አትበለኝ....!!".....ጭራሽ እርሱ አይቶአቸው የማያውቅ ሌላ ሰው ሆኑበት።


"...አንዴ መኪናውን አቁምልኝ...."


ሹፌሩ መልስ ነፈገው....ያለው አማራጭ ዝምታ ብቻ እንደሆነ እያሰበ አይኑን ወደ መስኮቱ ሰደደ...ሰማዩ እንደማልቀስ እያለ ነው...ከመኪናው መውጣት ብችል እና ለቅሶውን ብቀላቀለው ብሎ ተመኘ... ...የሰማዩ ለቅሶ እያየለ መጣ...አሁን ከመኪናው ወርዶ የሰማዩን ለቅሶ ካልተቀላቀለ ሰማዩ ለቅሶ በላኸኝ ብሎ የሚወቅሰው መሰለው....


እየሄዱ ነው....


ሹፌሩ ተንጠራርቶ በለታ በኩል ያለውን የመኪና መስኮት ዘጋው...በመኪናው መስኮት ተሞርኩዘው ከዝናቡ ጋር የሚያወሩት የለታ አይኖች አጫዋች አጡ...የዝናቡ ወሬ ቆረፈደ....ምናል ንፋስ እንኳን እንዲያዋራኝ ትንሽ ሽንቁር ቢተውልኝ አለ በልቡ.....


"እባክሽ እቴቴ የሆነ ነገር በይኝ...."

"ደርሰናል"...





አላለቀም......



Shewit dorka





https://www.tg-me.com/ethioleboled
አንተነትህን ሙሉ የሚያረግህ ሰው ሳይሆን አንተን ሙሉ በሙሉ የሚቀበልህ ሰው ነው የሚያስፈልግህ።

😌 ቡድሁ😌

📚 @ethioleboled
ፍቅር ማለት የተናገርካቸው ሳይሆን የተገበርካቸው ነው።

💡ቡድሀ💡

📚 @ethioleboled
ራስን መለወጥ @Bemnet_Library.pdf
36.5 MB
ርዕስ=ራስን መለወጥ
ደራሲ=ማይልስ ሙንሮ

📚 @ethioleboled
ሾተላዩ ሰላይ @Bemnet_Library.pdf
59.4 MB
ርዕስ=ሾተላዩ ሰላይ
ደራሲ=ኬን ፎሌት

📚
@ethioleboled
የነፍስ መንገድ @Bemnet_Library.pdf
20.3 MB
ርዕስ= የነፍስ መንገድ

ደራሲ=ኦሾ(Osho)

📚 @ethioleboled
የዶርም ወግ....


ምነው በእኩለ ለሊት ለምትሉኝ አንባብያን ሰሙነ ማማረር ላይ እንደሆንኩ ልነግራችሁ እወዳለሁ።


"ከእዚህ ጊቢ በሰላም ከወጣሁ ወደፊት ማንኛውንም ከባድ ሁኔታ ማለፍ እችላለሁ....."

"እስማማለሁ"

"እዚህ ጊቢ ለሚመጡ ነው ማዝነው..."

"ፎቁን ሲያዩት እኮ ደህና ጊቢ ይመስላል..."

" በእኔ የደረሰ በእናንተም አይድረስ...እኔ እንደተሸወድኩት እንዳትሸወዱ ምናምን እያልኩ ነው ከበር የምመልሳቸው..."

"ምኑም የጤና ጊቢ አይመስልም...."

"ጤናችንን አጥተን መውጣታችን ነው..."


የ pharmacy ትምህርት 6 አመት ከተደረገባቸው ጓደኞቼ ጋር እያወራን ነው....

"የኮሮና ጊዜ የተበላሸው scedule እንዳለ ሆኖ አንድ አመት የሚያስጨምር የኮርስ መጨመር እንኳን በሌለበት ሁኔታ ለምን 1 አመት ተጨመረ...ማንም አያውቅም...."የትምህርት ሚኒስቴር ትዕዛዝ ነው"...ነው የሚለው ጥገራው..የትምህርት ሚኒስቴር ህግ የሚሰራው ለዚህ ጊቢ ብቻ ነው...."...ጦ ናት።





"እኔ እንኳን ተመራቂ ነኝ...ይብላኝ ለከራሚ...."....እኔ ነኝ።እኔ ከmedical labratory ትምህርት ክፍል ነኝ። እኔም የዚህ ኢ-ፍትሀዊነት ተጠቂ ነኝ...4 አመት የነበረው ኮርስ 5 አመት ሆኖብኛል...

እንዴት 5 አመት ሆነ...lag አርገሽ ነው ሌባ...የሚሉኝ ሰዎች አልጠፉም....እንዴት ማለት ጥሩ ብዬ የተነገረኝን ስነግራቸው የስላቅ ሳቃቸው ያመልጣቸዋል....የምር ያስቃል እኮ...

"ሰኔ 30 የተበጀተ በጀት በዛው አመት ማለትም ከአንድ ወር በኃላ ሀምሌ ላይ አልቆ 5 ወር እረፍት ተሰጠን..."...የሚል ሰበብ አያስቅም ነው የምትሉኝ...

አንድ material or reagent በሌለበት ጊቢ

"ለትምህርት ጥራት ሲባል 7 አመትስ ብትቆዩስ ምን አለበት ...."...የሚል ቀልድ አያስቅም ነው ምትሉኝ...


እናቴ መመላለስ ሳበዛ ምን ብትለኝ ጥሩ ነው....

"ለምን ምሳ እየቋጠርሽ አትሄጂም....ከዛ ጊቢ እኛ ሀብታም ነን...😂"



"ባለስልጣኖቹ የጀመሩት ፎቅ...ወይ ሆቴል ብቻ whatever ካላለቀ እኛ እዚው እድሜያችን ማለቁ ነው..."

"እኔ እኮ አጥር ለሌለበት ጊቢ በአጥር ዘሎ መግባት አይቻልም ሲሉ ነው በእነርሱ ተስፋ የቆረጥኩት..."

"በቃ በቃ ዝም በሉ...በቃ በቃ አናውራው...pc አቀብዪኝ ፊልሜን ልይበት....ተቃጠልኩ እኮ...."


"አንድ መንገድ ብቻ ባለው ጠባብ ጊቢ ውስጥ አሸን አዛዥ ምን ይሉታል...ባላየ ማለፍ ራሱ እኮ አይታሰብም በቀን ሰላሳ ጊዜ ሰላም እየተባባልን ካካካ..."

"የምንሳልበት የምንሞረድበት የህይወታችን ክፍል ነው ...ለበጎ ነው ብለን እናስብ...."

"እንደዛ ማሰቡ ባይከፋም ሮቦት መሆን ግን ሰልችቶኛል....በሆነ አካል መመራት...programmed እንደተደረገ አካል እላይ ባሉ አካላት መሽከርከር..."

"አሁን ተሳሳትሽ...."

"ምኑ ጋር ነው የተሳሳትኩት...."

"እላይ ባሉት አካላት ብቻ አይደለም...እታች ያለም ስልጣኑን ሊያሳይሽ የቻለውን ያደርጋል...የምር የዚህ ጊቢ በማንኛውም ዘርፍ የመቀጠሪያ መስፈርት 'ተማሪዎችን ማንገላታት...ማስመረር...ተማሪዎችን ውሻ ማድረግ.....ማመናጨቅ...መበደል...'...እና የመሳሰሉት ስርአት አልበኝነቶች ነው የሚመስሉኝ...."


"ደግሞ በሆነ አካል መሽከርከር ከጊቢም ከወጣን በኃላ አይቀርልንም...እሱ ደግሞ የህዝብነት መስፈርት ይመስለኛል...."


"ፖለቲካ ውስጥ ገባን ሳናስበው...."


"በቃችሁሁሁ እንዴ በቃ እንዳታሳብዱኝ...እንዴ ያማችኃል እንዴ በቃን በጌታ ባሰብኳቸው ቁጥር እየነደድኩ ነው...ሸ መስኮቱን ክፈቺው በጌታ ጋልኩ በንዴት....."




ከምናሳብዳት ብለን አቆምን....ግን የምር እውነቷን ነው ሮቦት መሆን ይሰለቻል።



ሸዊት ነኝ የሚዛን ቴፒ ቀበጥ የጤና ጊቢ ምርኮኛ😂....ብሶቴን ጨርሳችሁ ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ....ይሄን ጊቢ ስቦጭቅ እንደተመረቅኩ ነው ሚሰማኝ😂 መልካም አዳር።





https://www.tg-me.com/ethioleboled
በህይወቱ ለመጀመርያ ጊዜ ስላፈቀራት ሴት ታሪክ በውስጥ መስመር ካጋራኝ የቻናሉ ተከታይ ፅሁፍ

የቃላት ማሻሻያ ተደርጎበት የቀረበ

📜....📝
በእውነት ነው ምላቹሁ በህይወቴ የዛሬ 14 አመት ገደማ በጣም የምወዳት ቆንጅዬ ሴት ገጠመችኝ እሷን ለማገኘት ያልሆንኩት ያልደረሰብኝ ስቃይ የለም እኔ 18 ቀበሌ ልጅ ስሆን እሷ የ42 ቀበሌ ልጅ ናት በመሀላችን አስፓልት ነው የሚለየን ምንም የደሀ ልጅ ብትሆንም ለኔ ልዩ ሴት ነበረች። እስካሁንም ለኔ ልዩ ናት።

ትዝ ይለኛል የዛኔ በኢት..አቆጣጠር በ1986 አ.ም የ8 ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ እሷን ካየሁ በኋላ ሚኒስትሪ ሁለት ጊዜ ወድቅያለሁ ሀሳቤ ሁሉ እሷጋ ነበር። ቤቴ ውስጥ ሆኜ መሽቶ እስኪ ነጋ በጣምም ይጨንቀኝ ነበር። በሷ ጉዳይ ያልተጣላሁት ጎረምሳ የለም እሷን ለማግኘት በራሴ ላይ ትልቅ ችግር እየፈጠርኩ ሄድኩ። ከቤተሰብ ጋር አለመስማማት፣ ጸባዬ ሁሉ ተቀየረ።

ቤተሰቦቼ እኔን ይናፍቁኝ ጀመር ውሎዬ ከሷ ጋር... ጠዋት እነሳና ሰፈሯ እቤታቸው ፊትለፊት መገተር ሆነ ስራዬ ታሪኳን ስታጫውተኝ ልገልጽላት የማልችለው ፍቅር ያዘኝ እንቅልፍ ነሳችኝ ቤቴ ውስጥ ምንም ነገር አልጥም አለኝ የሚያሳስበኝ ምን ጊዜም የሷ ችግር ብቻ ነው። ስለቤተሰቦቿ ጠይቂያት እናቷ በህይወት አለመኖራቸውን እህት ወንድም እንደሌላት አባቷ በፖለቲካ ችግር እስር ቤት መሆኑን እና በእንጀራ እናት መቅረቷን ገለጸችልኝ።

እንጀራ እናቷም በጣም እንደምትበድላት ነገረችኝ እኔም አይዞሽ ከጎንሽ ነኝ እላት ነበር እንጀራ እናቷ እንጀራ በመጋገር ሲሆን ኑራቸውን ሚገፉት ልጅቷ ደግሞ የተጋገረውን እንጀራ አምጥታ እኛ ሰፈር ነበር ምትሸጠው አንድ ቀን ትዝ ይለኛል በጣም ስለምወዳት "ፎቶ በቀለ" ሄደን ፎቶ አብረን መነሳት አለብን ብያት ቀጠሮ ይዘን ሁለት የቁም ፎቶ ጭንቅላት ለጭንቅላት ተደጋግፈን ተነሳን::

የዛን ቀን የእንጀራ እናቷ ከባድ ቁጥጥር ይቆጣጠሯት ስለነበር ጉሊት ፈልገው አጧት መሰለኝ ለሶስት ቀን ያህል መምጣት ተወች ምን ይዋጠኝ የዛን ቀን የጀመረኝ በሽታ ልክ እንደ እርጉዝ ሴት ጠናብኝ በጣም ተረበሽኩ ምሽት ያበሳጨኝ ጀመር የዛን ጊዜ ከምሽት ይልቅ ንጋትን ብቻ እመርጥ ነበር ሲነጋ አድፍጬ በራቸው ላይ መጎለት ጀመርኩ በጠዋት እየተነሳው ብቻ ከሶስት ቀን በኋላ ወደመደበኛው ስራዋ ተመለሰች እኔም መንገድ ላይ እየጠበኳት የያዘችውን መሶብ በጭንቅላቴ እየተሸከምኩላት ወደ ገበያው ማድረሴን ተያያዝኩት የያዘችው እንጀራ እንዳያድር ብዙ እጥርላት ነበር😂😂😂

ብቻ ገበያተኛ ሲመጣ ሰርገኛ ነው ቀጭ ቀጭ አይልም አረ ጥሩ እንጀራ ነው ማለቱን ተያያዝኩት ተመስገን እንጀራውም ቶሎ ቶሎ ማለቅ ጀመረ በንደዚህ አይነት ሁኔታ በጣም እንዋደድ ጀመር ትምህርቴን ብዙም መከታተል ትቻለሁ በመሀል አንድ ቀን አባቴ የክፍለ ሀገር ሹፌር ስለነበር (ነብሱን ይማረው) መሶቧን ተሸክሜላት ያየኛል አይቶኝ እንዳላየ ሆኖ አለፈኝ ወደቤት ገባ እኔም በጣም ደነገጥኩ መኪናውን ሳየው ቶሎ እሷን አድርሼ ተመልሸ ቤቴ ገባሁ። ሰላም አልኩት እሱም ሰላም አለኝ በጣም ሀይለኛ ስለነበር ሁላችንም እንፈራዋለን።

አባቴም "ስማ ልጄ አልታይም ብለህ ከምትሰራው ስራ እታያለሁ ብለህ ብትተወው ይሻልሀል::" ብሎኝ ዝም አለኝ እኔም እሺ አልኩት እያሳሳቀ ነበር የተናገረኝ:: ፋዘርም አንድ ቀን አድሮ ወደስራው ሄደ እኔም በጣም ስለምወዳት በወቅቱ አንድ እንጀራ ዋጋው ስሙኒ ነበር(25 ሳንቲም) ስሯ እየተቀመጥኩ የአንድ ብር ከሰባ አምሳንቲም እንጀራ ቁጭ ብዬ እየገዛኋት እበላ ነበር። (አስቡት 7 እንጀራ😂)

እኔም እሷም ሆነን በቃ ምን ልበላቹሁ እኔ ግን በዛን ሰአት ለፍቅራችን መስዋት መክፈሌ ነው እንሸጥና እንጀራውን ካላለቀ ችግር እንደሚደርስባት ስለማውቅ በቃ እኔው እራሴ እየገዛሁ አብረን ሜዳው ላይ ደረቅ እንጀራ እንበላ ነበር ቁንጣን እስኪይዘን ድረስ 🙈

በእውነት ነው ምላቹሁ ከሷ ጋር እንደዚህ አይነት ኑሮ ስንገፋ ከርመን እንደተለመደው አባቴ ምን ያህል ሀይለኛ እንደሆነ ነግርያቹሀለሁ እኔ በሌለሁበት ወንድሜን የሱንም ያንተንም ደብተር አምጣ ይለዋል። የኔን ደብተር ሲከፍተው ውስጡ ሙሉ ሴሜስተር አንድ ገፅ አልተፃፈበትም ነገርግን ውስጡ የኔንና የሚሚን ፎቶ ያየዋል።

ልክ እንደፈረደብኝ ወደ ቤት ስገባ ቤቱ ጸጥ ጭር ብላል ማን የት ምኑጋ እንዳለ አይታየኝም ከውጪ ስለገባሁ የሰማሁት ያባቴን ድምጽ ብቻ ነው እሱም ና ና ወደዚህ የሚል እኔም አቤት ብዬ ገባሁ የቤቱ በር ተቆለፈ ጎረቤት መጥቶ እንዳይገላግለን 😭😭😭

ከዛው አምጣ ደብተሮቹን አለኝ አመጣሁለት ትምህርት ለምድነው ማትማረው የኔ ጎረምሳ ብሎ ተውኝ ዋጋዬን ሰጠኝ ቦታ ሳይመርጥ አገራችን ትዝ ካላቹሁ ብረት ምጣድ አለ በጣሳ ሻውር መውሰጃ እሱ ላይ ሳሙና አረፋ ተመታና እዛ ላይ ሆኜ የዱላ መአት ወረደብኝ ብድግ እያልኩ ቁጭ ብረምጣዱ ላይ ሆኜ በመጨረሻም ዱላውን ስላልቻልኩት በጣም ስለበዛብኝ ቤት ውስጥ በገመድ ታስሬ ነበር።

እንደበግ ቤት ውስጥ ታስሮ መቀመጥ ስላልቻልኩ የታሰርኩትን ገመድ በጥሼው እሷን ፍለጋ ወደ ሰፈሯ ሄድኩኝ በወቅቱ ስነግራት በጣም አዘነች አለቀሰች የት አባቴ ልውሰድህ አለችኝ በወቅቱ እሷም ሆነች እኔም ችግር ላይ ነን ያለነው ምንም ገንዘብ አልነበረኝም ከእንጀራው ሂሳብ ላይ አጉድላ 3ብር ሰጠችኝ በዛው ዘመድጋ ሄድኩ ለምን እሷን ማየት ነብሴ ይፈልጋል ግን ሊመጣ የሚችለውን ችግር እያሰብኩ ብዙ ጊዜ ሆነን ከሷም ከቤተሰብ ጋርም ሳንገናኝ እዚህ ያለሁበት አገር እህት ነበረችኝ ደብዳቤ ጽፌላት ሁሉንም ነገር ጨረስኩ።

ከአገር ለመውጣት ሁለት ቀን ሲቀረኝ ከአባቴ ጋር ይቅር ይቅር እንድንባባል ከቤተሰብ ጋር አስታረቁኝ እሷንም አግኝቻት በጣም አዘነች እና መቼም እዛ ቴሌፎን ችግር ታውቁታላቹሁ በስደት ላይ ሆነን ሶስት ጊዜ አቀረቡልኝ በአራተኛው እንዲህ አይነት ስም አናውቅም ይሉኛል።

እና የመጀመሪያ ፍቅር አያድርስ ነው የአንድ ብር ከሰባምሳንቲም እንጀራ በየጊዜው ያስበላል ብላቹሁ አታምኑኝ ይሆናል እና እናንተም የደረሰባቹሁን እስኪ ጻፉት ወደዚህ ለመራሽኝ እህቴ እድላዊት በጣም ነው ማመሰግንሽ አክባሪሽ ጣሴ ጣሱካካካ ☺️☺️😔

#ያጋሩ
       ➴
@ethioleboled ▬▭🌹▬▭▬🌹
የተሰበሩ ክንፎች .pdf
25.9 MB
📓 ርዕስ፡ የተሰበሩ ክንፎች
✍️ ደራሲ ፡ ካህሊል ጂብራን

📚 @ethioleboled
ቀላሉን ነገር አታካብድ @Bemnet_Library.pdf
34.3 MB
📓 ርዕስ፡ ቀላሉን ነገር አታካብድ
✍️ ደራሲ ፡ሪቻርድ ካርሰን

📚 @ethioleboled
📝አንዳንድ ታሪኮች ርዕስ የላቸውም--ተነግረው እንዳልተነገሩ ይረሳሉ።

📝አንዳንድ ሰዎች ስም የላቸውም--ኖረው እንዳልኖሩ ይቆጠራሉ።

📝አንዳንድ ገድሎች አልተዘከሩም--የባከኑ መስዋቶች ይባላሉ።

📝አንዳንድ ቅሌቶች ሰው ፊት አልታዩም--እንዳልተፈፀሙ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይቀራሉ።

📝አንዳንድ አወዳደቆች ከትዝብት ተጋርደዋል--ዙሪያውን ገላምጠን ልብሳችንን አራግፈን እንቀጥላለን።

📝አንዳንድ ህዝቦች በወል ተረስተዋል--ለመታሰቢያነት የቀረላቸው  ምንም የለም።

📝አንዳንድ ኮቴዎች በመርሳት ተጠቅተዋል--አንዳንድ ወኔዎች ለሞት ዳርገዋል--ከሁሉም በላይ ግን አንዳንድ ልቦች በሶስት መሀላ ተክደዋል።

📓ሀገር ያጣ ሞት
              ✍️ ሄኖክ በቀለ ለማ

🔵 @ethioleboled
እንዲው በደፈና "ወደድኳት! አበድኩላት።" የሚያሰኝ ድፍን ፍቅር አልነበረም የያዘው።በርህራሄ እና በመተሳሰብ ላይ መሰረቱን የጣለ እውን የሚዳሰስ እና የሚጨበጥ፤ንፋስ የማይገፋውና ውርጭ የማያበርደው ፍቅር.....

📓ወገግታ
                      ✍️ የሺጥላ ኮኮብ

📚 @ethioleboled
ወገግታ @Bemnet_Library.pdf
11 MB
📓 ርዕስ፡ ወገግታ
✍️ ደራሲ ፡የሺጥላ ኮኮብ

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
⚪️#ልጅ ፡ አባቴ ባህሪዬ እንዴት ቢሆን ደስ ይልሃል ?

#አባት፡ እንደዚህ ሁን ልጄ

⚪️#ልጅ ፡ እንዴት ?

#አባት ፡ እንደ ውሃ ሁን ባስቸገረ ግዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈለገ ጊዜ ግን እንዲገኝ ዛፍ ማሳደጉን አይተውምና ፤

እንደጨውም ሁን ለሁሉም ምግብ ቢፈለግም በቀላሉ ይገዛ ዘንድ ግን-ዋጋው ውድ አይደለምና ፤ ከሁሉ ከሁሉ-ግን እንደ ወተት ሁን በተውት ግዜ በሌላ-መልክ ተመልሶ ይመጣል እንጅ አይበላሽምና-በተገፋም ግዜ ከፍ ከፍ ይላልና።

⚪️#ልጅ፡ እሽ አባቴ እንዳልሆንስ የምትፈልገው የለም ?
#አባት አለ ልጄ፤ እንደዚህ አትሁን

#ልጅ ፡ እንዴት ?

⚪️#አባት፡ልጄ ሆይ እንደ መርፌ አትሁን የሌሎች ብዙ ቀዳዳ እየደፈነ የራሱን አንዷን መድፈን አይችልምና፤

እንደ መቋሚያም አትሁን ለሌሎች መደገፊያ እየሆነ ለራሱ ግን መቆም አይችልምና ፤

ከሁሉ ግን እንደ ደወል አትሁን ! ከሁሉ ቀድሞ ነቅቶ ሌሎችን ለቅዳሴ ቢቀሰቅስም እርሱ ግን አያስቀድስምና።
...
............
**** መልካም ቀን
መርሳት ግን እንደመተው ቀላል አይደለም።
➡️አንዳንዴ useless እንደሆንን ሊሰማን ይችላል፤

አንዳንዴ ሰዎች እንዲረዱን ፈልገን አልተረዱን ይሆናል፤

አንዳንዴ ምክንያቱንም ሳናውቀው በምንወዳቸው ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻ ተስሎ አይተን ይሆናል፤

አንዳንዴ ለሰዎች ከሰጠነው አክብሮት በተቃራኒ ንቀት ተቀብለን ይሆናል፤

አንዳንዴ እድሜያችንን ሙሉ ስንመኘው የነበረና ትልቅ የመሠለን ነገር ስናገኘው ትንሽ ሆኖብን ይሆናል፤

👍አንዳንዴ ለሰዎች መድረስ ፈልገን ሁኔታ፣ ጊዜና አቅም አጥተን መድረስ አልቻልን ይሆናል፤

አንዳንዴ አንደመልአክ የምናያቸውን ሰዎች በህይወት አጥተን ይሆናል፤

አንዳንዴ ለቤተሰቦቻችን ልንፈጥርላቸው እንፈልግ የነበረውን ዓለም ቀርቶ ትንሽ እንኳን ልንደግፋቸው አለመቻላችን አሳዝኖን ይሆናል፤

አንዳንዴ ሁሉም ነገር ትርጉም አጥቶብን ይሆናል፤

አንዳንዴ ሁሉም ቀን አሰልቺ፣ በድብርት የተሞላ እና ተመሳሳይ ሆኖብን ይሆናል፤

አንዳንዴ ከዛሬ የበለጠ ነገ ጨለማ ሆኖ ታይቶንም ሊሆን ይችላል፤

አንዳንዴ ሁሉም ነገር መኖር ራሱ ሳይቀር ከብዶን ይሆናል፤

አንዳንዴ ...

አንዳንዴ...

አንዳንዴ...

ግን It's okay to feel bored, sad, useless, and hopeless at times.. 

live

Lough

Love

ከሁሉም በላይ የተሻለ ጊዜ ከፊት አለ። 💙

በውስጣችሁ ያለውን ክፋት በውስጣችሁ ባለው መልካምነት የምታሸንፉበት የተዋበ ቀን ይሁንላችሁ
every friend you invite! 🎉

🌟 Share this link: https://www.tg-me.com/botifyai_bot?start=referral_6405623892




Best ai bot arif Nw mokrut
2024/09/22 17:22:11
Back to Top
HTML Embed Code: