Telegram Web Link
ገጣሚና ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ

16ቱ የጥበብ ስራዎች ፤

#ታሪክን_ወደኋላ
"......መጀመሪያ እራስሽን ውደጂው፣ ከዛ በኋላ ሰውን መውደድ ጀምሪ። ከዚያ አካባቢሽን ሀገርሽን በእራሱ ጊዜ ትወጃለሽ። ችግሩ የሰው ልጅ መጀመሪያ መውደድ የሚጀምረው እራሱን ሳይሆን ሌሎችን ነው። ከዚያ ባደገ ቁጥር ሰዎችን ጠልቶ እራሱን መውደድ ይጀምራል።
......እና እንዳልኩሽ አንድ ሰው ሀገር ከመግዛት እራሱን መግዛት ይከብደዋል፣ እራሱን የገዛ ሰው ግን አለምን መግዛት ይችላል። ስለዚህ እራስን መውደድ፣ መግዛት እና ማሸነፍ ከሁሉም ይቀድማል።....."

".......ሁሌም ከማንም እንደማታንሺ አስቢ፣ ለእራስሽ ክብር ስጪ፣ ራስሽን ውደጂ፣ ሁሉንም እችላለው ብለሽ ተነሺ፣ ፈተናዎችን በጥበብ እንደምትወጪ እመኚ፣ አንብቢ፣ ሁሌም ለነገሮች ዝግጁ ሁኚ፣ ያኔ ሁሉም ሰው ያከብርሻል። ሁሉንም ታሸንፊያለሽ፣ ሁሉም ይወድሻል።

ሰነፍ አትሁኚ፣ የሰው ልጅ ውድቀት የሚጀምረው በስንፍናው ነው። ሰነፍ ሰው መጥፎ ነገሮችን ሁሉ በጫንቃው ይሸከማል። ምክንያቱም በስንፍናው ስጋው የሚበላው ያጣልና። ሰው ሰነፍ ከሆነ የሰውን ይመኛል። ሌባ ይሆናል፣ ውሸትን ይናገራል፣ ነውርንም ይፈጽማል። ስለዚህ ብርቱ ሰው መሆን አለብሽ።

አንቺ ማንንም መፍራት እና እንደዚህ ይሉኛል ማለት የለብሽም!! አንቺ በትክክል መልእክትሽን ካስተላለፍሽ ምን ችግር አለው ሰው የፈለገውን ቢል?? ሰውን አክብሪ!!!....."

#ምንጭ 👇
ከ "ውብ" መጽሐፍ የተወሰደ


Share :-
@ethioleboled
"የማላቅፍህ ስለምሰስትህ ነው…።"
              በሩት ሃብተማርያም ....👩‍💻
#ክፍል____1

ከማሰሮ የዘገንከውን ትኩስ እፍኝ አሹቅ ወደ  አፍህ ስታስጠጋው፣ አፍህ እዚህ 
የከንፈርህ ጥጋት  ጋር ስታደርሰው፣ 
ብርር’ድ ብሎብህ ያውቃል? ወይ ደሞ መንገድ ላይ ለማታውቀው ሰው በፈገግታ ሰላምታ ሰጥተህ  ስታልፍ ፈገግታህ በስንት ሰከንድ ይከስማል? የእግርህን አውራ ጣት የመታህ ትንሽ እንቅፋት ልብ 
ስር የሚገባ ህመም በስንት ደቂቃ 
በረደልህ? የጣቶችህን አንጓዎች 
እያጠፍህ ‘ቋ’ ለማድረግ የፈጀብህን 
ቅፅበት በቁጥር ታውቀዋለህ? 

በህልምህ ያየኸው ውብ ዓለም ልክ ዓይንህን ስትከፍት ለመጥፋት ከብርሃን ይፈጥን አይደል? ልክ እንደዛ ፣ ልክ እንደ ሁሉም ፍቅር ይበርድብኛል። በእጄ ሳልይዘው ይሰበርብኛል። ምን ላድርግ?
#የቀጠለ
"ዘንድሮ ፍቅር የለም!”
እያሉ በራሳቸው የፍርሃት ድንበር ውስጥ እንዳሉት ሰዎች አይደለሁም። ሰው የተባለ ፍጡር በህይወት እስካለ ድረስ
ፍቅር የትም አለ። አይታየንም እንጂ ያያዘን ቀጭን መሳይ ጠንካራ ድር ፍቅር ነው። አለ ብዬ አምኜው እየኖርኹ ታዲያ ስይዘው ለምን ጥብቅ አያደርገኝም? ስዳስሰው ቁንጥጫው የሚብሰው
ለምንድን ነው?

ስስመው ለምን ጥርሱን ያገጣል? መጣ
ብዬ “እሰይ! እሰይ! ከመጣህ ማርያም ታምጣህ!” ብዬ፣ ከንፈሬ ከማሰሪያው ተፈቶ ፈገግ ሳልል ወዴት ሄዶ ይጠፋብኛል? እንደ ማድጋ ሊጥ፣ ተሟጦ እንደሚጋገር፣ አሟጦ የሚያፈቅረኝ የት
ነው? ሁላችንም፣ እኔም አንተም ሳንዘጋው የተውነው የትዝታ በር አለን።
በቀጭን የምትነፍስ ትላንትን የምትናፍቅ ንፋስ የሚያሳልፍ በር አለን። አሁን ቁጭ ብዬ ሳስበው አጠገቤ የነበሩ፣ ያፈቀርኳቸው ፤ ያቀፍኝ ፤ ሳናይሽ አናድርም ልመናዎች ሁሉ የትዝታቸውን
በር መሸጎሪያ እንጂ በእያንዳንዳቸው ልብ ውስጥ የራሴ የትዝታ በር የለኝም።
ታዲያ ይሄ አያደክምም?

በዓለም ያንተን አይነት ፈገግታ ያለው አይቼ አላውቅም። ፈገግ ስትል ፊትህ ላይ ያለውን ኃይል አልችለውም። እወድሻለሁ ስትለኝ እያንዳንዷን ፊደል ሰንጥሬ ባያት ምንም ማብለጭለጫ ቅመም እንዳልተጨመረበት አውቃለሁ። ፊቴ ስትመጣ የዋህነትን ብቻ ትሰዋልኛለህ። ደስ ትለኛለህ። ዓይኔን ከድኜ እጄን ልሰጥህ እፈልጋለሁ። ታዲያ ግን እፈራለሁ። ፍርሃቴን አሸንፌ ባቅፍህ በማግስቱ ትተወኛለህ።

አነሳሴ ጋ አውግተን ሳንጨርስ ወድቄ 
እነቃለሁ። እንዲሁ ባይህ ይሻላል። እንዲሁ በሩቅ ብመኝህ ይሻላል። ምኞቴን ሸሽጌ ፤ ምኞትህን ሸፍኜ እንደ ሩቅ ዘመድ ብንተያይ ይሻላል። ላጣህ ስለማልፈልግ ነው ከጠረንህ አፍንጫዬን ያቀብኩት 
፤ እቅፌን ያቀዘቀዝኩት ዘላለም በልብህ እንድታቅፈኝ ነዉ። የ40 ቀን እድሌ ትለኝ ነበር አያቴ። ያኔ ታዲያ እስቅ ነበር።

40 እና እድል ምን እንዳቆራኛቸዉ ይደንቀኝ ነበር። አሁን በየቀኑ ሳይገባኝ አልቀረም። የ40 ቀን እድል አለን ሁላችንም። በማይታይ ማተብ አንገታችን ላይ ያለ።
            🌩🌩🌩🌩🌩
ተራራው ሰው፣ ሆኖ 
ከንፈሬን ባይስመኝ
ተራራው ሰው ሆኖ፣
ጡቴን ባይዳብሠው
ተራራው ሰው ሆኖ፣
ዓይን ዓይኑን ባላይ
ጸሀይ እሞቃለሁ፣ ወጥቼ ከላይ።


#ይቀጥላል ....

#ቻናሉን_ለማጋራት
                  ➘
          
@ethioleboled
📜❦ ══ •⊰❂⊱• ══
ቀን ቀን እስቃለሁ ..
<unknown>
ከላይ ከተፃፈው ፅሁፍ ጋር የሚሄድ ሙዚቃ ነው ተጋብዛችኋል 😍

#ቻናሉን_ለማጋራት
                  ➘
          
@ethioleboled
📜❦ ══ •⊰❂⊱• ══ ❦
በኔ መንገድ ካልሔድክ
መንገድህ ገደል ነው" ፣ ማለት የሚከጅል

"እንደኔ ካላሰብክ
ማሰብ አትችልም" ፣ ሊል የሚዳዳው ጅል

በህይወት መንገድ ላይ...
እንደራሴ ስጓዝ ፣ ነፍሴ ምትሞግተው

ስንት ገደል አለ
"ድልድይህ ነኝ" የሚል ፣ መሻገር ሲያቅተው፡፡

📝በላይ በቀለ ወያ📝

share
@ethioleboled
የ 3ቱ ከተሞች የትራፊክ ፖሊስ በዘመናቸው ፤

በአዲስ አበባ ፣ ድሬዳዋ እና አስመራ

በ 1920ዎቹ

#ታሪክን_ወደኋላ
"የማላቅፍህ ስለምሰስትህ ነው…።"
              በሩት ሃብተማርያም ....👩‍💻
#የመጨረሻ_ክፍል

... ከናፍቆት ጋር ድብብቆሽ መጫወት 
ስጀምር፣ ልክ እንደማንኛዉም ተጫዋች 
ተናፋቂው ተደብቆ ሲቀር ጨዋታዬን 
አቆማለሁ ብዬ ነበር። የመፈለግ ፅናቴ 
ተሰብሮ ወይም ሟሙቶ ያለቀ መስሎኝ 
ነበር።እንደዚህ የተደበቀበትን ጋራና 
ሰርጣሰርጥ ሁሉ በልቤ አስሳለሁ ብዬ 
አልነበረም። ልቤ ኩስ ኩስ ብላ ከእግሬ 
ስር እየተራመደች የምትመራኝና 
የምታወራኝ ይመስለኛል። እንዴ 
እሱም ጋር እኔም ጋር ልቤ ልትኖር 
አትችልም። ሲፈቀር ልብ ይሰ’ጣል ይሉ የለ እንዴ?  ታዲያ የኔ ልብ ይቺት ከፊቴ። ፍቅር ሳይሆን እልህ ነው እንዴ  የያዘኝ? የጨዋታ አሸናፊ አለመሆኔ ተሰምቶኝ ነዉ እንዴ? እያልኩ አስባለሁ።
#የቀጠለ
“ ሰማሽኝ እቴ አካልሽ ሁሉም እዚህ ነው። ሀሳብሽ ፤ ህልምሽ ፤ እርካታ እና ስሜትሽ
ሁሉም ሰዋዊ ስሜቶችሽ ናቸው እሱ
ጋር የተደበቁብሽ። ሰው ሲያፈቅር
ሰውነቱን ፣ ሰው የመሆኛ፣ ሰው የመባያ
ነገሮቹን ነው አሳልፎ ለሚያፈቅረው
የሚሰጠው። አብሬሽ ያለሁት ልብ
ተብዬ እንድጠራ የሚያደርጉ ስሜቶቼን
ስለወሰደብኝ ነው።” አለች ኩስ ኩስ
እያለች።

... ለነገሩ ልክ ናት እላለሁ። ምን
ታልሚያለሽ ቢሉኝ ከንፈሩ ስር
የማርያም ስሞሹ መሆን አይደል?
ምን ታስቢያለሽ ቢሉኝ ንፋስ የራሱን
ፀጉር ስንቴ ዳበሰችው? ጨረቃ ለምን
አዘቅዝቃ ታየዋለች? እንቅፋት መቶት
ይሆን? አንዷ ቁሌታም ስታልፍ አይታ
ተመኝታው ይሆን? አንድ ጤነኛ ሰው
እንዲህ ያስባል? ...አስቀድሰው ሲጨርሱ እንደሚሰጥ
ቁራሽ፤ቤቱ ቢሄድም የሚበላ እንደሌለው
ሰው ያቺን ቁራሽ እንደሚያጣጥማት
(እንደዛ ናፍቆቱ ይጣፍጠኛል) ፤
የመጨረሻ የጎለተችው ድንች ተሸጦላት
ለልጆቿ ራት መግዛት እንደምትፈልግ
እናት ገዢን በጉጉት እንደሚጠብቁ
ዓይኖቿ (እንደዛ በየቀኑ ለፍቅሩ እጓጓለሁ ) ፤ ረጅም ዓመት በደዌ ተሰቃይቶ ጎኖቹ ሁሉ በቁስል ነደው መተኛት እንደናፈቀው ፣ፈውስ መጣልህ፣ ጎንህ አገገመ ተብሎ የነገ ፈውሱን አስቦ
እንደሚጋደም ጎልማሳ (ልክ እንደዛ የፍቅር እፎይታን እናፍቃለሁ)።

... ዓይኔን አልነግረውም። ፍቅርህ
ላይመጣ ይችላል ብዬ አልነግረውም።
በሩቁ እያየነው እንደምንኖር አልነግረውም። ጉጉቱን አውቃለሁና
ቢጠብቅ ይሻላል። እጄን “ደረቱን አትዳብስም ፤ አንገቱ ዙሪያም ላትሆን ትችላለህ እኮ” ብዬ እንዴት ላስረዳው?
እግሮቼን “ወዳለበት አትሄዱም፣
ቁሙ!!” ማለት አልችልም። ከእግሬ
ቀድሞ የእርምጃ ሀሳቤ የት እንደሚሄዱ
ይነግራቸዋል። ማንንም ማዘዝ አልቻልኩም። ሀሳቤን ፤ ህልሜን ፤ ዓለሜን ሰጥቼ ነዋ የወደድኩት። ግን ትወደኛለህ?
#አለቀ

#ቻናሉን_ለማጋራት
                  ➘
          
@ethioleboled
📜❦ ══ •⊰❂⊱• ══ ❦📜
👨‍🌾👩‍🌾..የእረኛው የፍቅር ቃላት..👩‍🌾👨‍🌾

🗣...
ሳገኝሽ-
ላሜ ጠፍታ ሳገኛት እንደሚሰማኝ አይነት ስሜት፣
🗣
ስትስቂልኝ-
ከብቶቼ በልተው ሲጠግቡ እንደሚሰማኝ አይነት ሃሴት፣
🗣
ስታኮርፊ-
በሬዬን ዋዥማ የነፋው ያህል ይጨንቀኛል፣
እይዘው፣
እጨብጠው፣
የማደርገው ይጠፋኛል።
😍😍😍
አደራሽን በንግግሬ በምሳሌዬ አትሳቂ፣
የፍቅሬን ጽናት ለማውቅ ከፈለግሽ ከብት ጠብቂ።    😊😊😊

📖.....ዋዥማ ማለት የላሞችን ሆድ ውጥር አድርጎ ነፍቶ እስከሞት የሚያደርስ ችግር ይፈጥራል ተብሎ በተለምዶ የሚወሰድ የሳር አይነት ነው።

@ethioleboled ▬▭🌹▬▭▬🌹
❤️እንደምትሄጂ ባውቅ -❤️

በእግሬ አንቺን ጋ ለመምጣት ከቃሊቲ አራብሳ እሄድ ነበር ?
አናደድሽኝ ብዬ ብዙ አረቄ በባዶ ሆዶ አጠጣ ነበር ?
ደክሞኝ ዝዬ አልጋ ላይ እንደበድን ተንጋልዬ <<አንገናኝ ወይ?>> ስትይኝ ተወርውሬ ያለሽበት እመጣ ነበር ?

ተሳፈጠሽ ብዬ ከወጠምሻ ጋ ታግዬ እሰበር ነበር?

እንደምቴጂ ባቅ ....!

ድብን ፤ቅንት ፤ እርር ብዬ ስሜቴን አፍን ነበር ?
ሁሉን ትቼ ከሷ በቀር ብዬ አለምን ችላ እል ነበር ? 🔠

እንደምቴጂ ባቅ ...!
ሳልሳሳ በደንብ እስምሽ እተኛሽ አልነበር?
በራስሽ ጥፋት የተጣላሽውን ተደርቤ ጠላት አደረገው ነበር ?
ደብሮኝ ተደሰተች ብዬ እቦርቅ ነበር ?

እንደምቴጂ ባቅ ...

ብቻዬን ሆኜ ሳልም እቅዴ ውስጥ አኖርሽ ነበር?
ገመናሽን ገመናዬን እንደዛ አርቀን እንገላለጥ ነበር?

እንኳን እንደምቴጂ አላወኩ ይሄን ሁሉ ትዝታ ከየት አመጣ ነበር ?
!
ሌሊት ነበር፤ አንድ ሰው በመንገድ ላይ እየነዳ መኪናው በገዳሙ አቅራቢያ ይበላሽታል። እናም ወደ ገዳም ሄዶ በሩን አንኳኳ። መነኩሴው ወደ ውጭ ወጥቶ በሩን ሲከፍት “መኪናዬ ተበላሸ። እዚህ ለአንድ ሌሊት መቆየት እችላለሁን?” አለ። መነኩሴውም ጥያቄውን ተቀበለ። መነኮሳቱንም ማቆየት ብቻ ሳይሆን መገቡት አልፎ ተርፎም መኪናውን አስተካከሉለት።

ሰውየው ለመተኛት ሲሞክር እንግዳ የሆነ ድምጽ ሰማ። በሚቀጥለው ቀን ጠዋት ስለዚያ ድምጽ መነኩሴውን ጠየቀ ነገር ግን መነኩሴው “መነኩሴ ስላልሆንክ ልንነግርህ አንችልም” አለው። ሰውየው ቅር ቢሰኝም አመስግኖት መንገዱን ቀጠለ።

ከተወሰኑ ዓመታት በኋላ፤ ያው መኪና በተመሳሳይ ገዳም ፊት ለፊት ይበላሻል። አሁንም እንደበፊቱ ሁሉ መነኮሳት ተቀብለው መግበውት መኪናውን አስተካከሉለት። እናም ለመተኛት ሲሄድ ሰውዬው ከዚህ ቀደም የሰማውን ተመሳሳይ እንግዳ ድምጽ ይሰማል።

በማግስቱ ጠዋት ስለዚያ ጫጫታ መነኩሴን ይጠይቃል፤ ግን መነኩሴም ተመሳሳይ መልስ ሰጡት “መነኩሴ ስላልሆንክ ልንነግርህ አልችልም" ሰውዬውም "ስለዚያ ድምጽ ለማወቅ መነኩሴ መሆን ግድ ከሆነ፤ "እንዴት መነኩሴ መሆን እችላለሁ?” መነኩሴም መለሰ ፣ “መነኩሴ ለመሆን ከፈለክ የምድርን አሸዋ መቁጠር እና ቁጥሩን ለኔ መንገር አለብህ ይህን ስታገኝ መነኩሴ ትሆናለህ ” አለው።

ሰውየው ለዚህ ተግባር ተነስቶ ከአርባ ዓመታት በኋላ ተመልሶ የገዳሙን በር አንኳኩቶ “መላውን ምድር ተዘዋውሬ 222,345,323,954,110,958,203 የአሸዋ ጠጠር በምድር ላይ እንዳለ አገኘሁ” አለ።

መነኩሴ ሰውየውን በማመስገን “አሁን ወደ ድምጹ የሚወስደውን መንገድ እናሳይሃለን” አለው። መነኩሴ ወደ አንድ የእንጨት በር እየመራው “ሰውየው የሚፈልገው ድምፅ ከዚያ በር በስተጀርባ ነው” ሲል ተደሰተ። በሩን ለመክፈት ሲሞክር ግን ያ በር እንደተዘጋ ተረዳ። ስለዚህ በሩን ለመክፈት ቁልፉን እንዲሰጠው መነኩሴውን ጠየቀ። መነኩሴ ቁልፉን ሰጠው። ሰው በሩን ከፍቶ ከዚያ በር ጀርባ ከድንጋይ የተሠራ ሌላ በር አየ። ዳግመኛ ሰው በሩ እንደተቆለፈ ስላየ የዚያ በር ቁልፍ ጠየቀ። ሰው የድንጋይ በር ሲከፍት ከወርቅ የተሠራ ሌላ በር አገኘ ግን ተቆልፏል።

መነኩሴው የዚያን በር ቁልፍም ሰጠው። እንደገና ከሩቢ የተሠራ ሌላ በር ነበር። በሌላ ተከታታይ በር እስኪያልፍ ድረስ ይህ ይቀጥላል። በመጨረሻ መነኩሴው “ይህ የመጨረሻው በር ነው እና እዚህ የዚህ በር ቁልፍ ይኸው” አለ። ሰውየው በመጨረሻ እፎይታ አግኝቶ በሩን ከፍቶ ገባ እና ከዚያ በር በስተጀርባ የድምፅ ምንጭ በማግኘቱ ተገረመ ግን ምን እንደ ሆነ ልነግራችሁ አልችልም .. ምክንያቱም እናንተ መነኩሴዎች አይደላችሁም።
***

ኃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን። ሌሎች ታሪኮችን እና የመጻሕፍት ጥቆማዎች ለማግኘት ገጻችንን ላይክ፤ ለሌሎች እንዲደርስ ደግሞ ሼር ያድርጉ። እናመሰግናለን!
***
ሁሉንም ነገር ማወቅ አለብን ብላችሁ ታስባላችሁ
?
ከአእምሮ በላይ ነው።

በቅድሚያ ምስሉን በማስተዋል ተመልከቱና
ወፊትዋን ምን አየሰራች እንደሆነና ግንዱ ላይ ያለውን ምን እንደሆነ ገምቱ?

ወፊትዋ በእንጨት ላይ የተጠጠጠች የተዋጣላት መሃንዲስ የግንደ ቆርቁር ወፍ አይነት ናት።የምትመገበው ፍራፍሬ ሲሆን በክረምት ወቅት ዛፎች ፍሬን አፍርተው ፍሬያቸውም እስኪ በስል ደሰረ ለሷንም ለልጆቿኝም የሚሆን ምግብ
አይኖርም።

ይህም ማለት ክፉ ጊዜ መሆኑ ማለት ነው። ታዲያ ወፊትዋ ምኔ ሞኙ ሆነችና?ሲበዛ ብልህና አርቆ አሳቢ የእዋፍት አዋቂ ናት። ለክፉ ጊዜ የሚሆን ምግብ ማስቀመጥ ሊኖርባት ነው።
🚢🚢🚢
ዛፎቹን ፍሬ አፍርተው ፍሬያቸውንም ደርቆ ከማራገፋቸው በፊት በጠንካራ
ምንቃርዋን የዛፎቹን ግንድ ጥንቃቄ ጥበብን በተሞላበት ዲዛይን በመበሳሳት
አስቀድማ የፍራፍሬ ማስቀሙጫ ቀዳዳዎች ታዘጋጃለች።

ግንዱ የመበሳሳት ስራን እንዳጠናቀቀች ቀጣዩ ስራዋ የሚሆነው ፍራፍሬ ለቀማ ነው። ከየዛፎቹ እየሄደች አንዳንድ ፍሬ በመልቀም ፍሬዎቹ በበሳሳችው ቀዳዳ ውስጥ ትወትፈዋለች። ፍራፍሬዎቹ ስታስቀምጥ በዘፈቀደ ሳይሆን እያንዳንዱ ፍሬ እንደየ የጨቀዳዳው ስፋት መጠን መጠን ሄዶ ግጥም የሚል ነው።

ፍሬውን ቀዳዳው ውስጥ እንዲገባ ቀዳዳውንም በደንብ እንዲይዝ ፍሬውን ቀደዳዳው አፍ ላይ ወተፍ ታደርግና በምኝቃርዋ ወደ ውስጥ መታ መታ ታደርገዋለች።አንድም ፍሬ አይወድቅም።
🚢🚢🚢

ፈጣሪ ፍጥረታቱን እንዴት አድሮጎ ነው የፈጠራቸው? ፋጣሪ ሆይ ከማር
በላይ የሚጣፍጠው የጥበብን ስራ እንዳይ ስለፈቀድክልኝ አመሰግናለሁ።
ተፈጥሮን ማንበብና ማስተዋልን ከፍጥረታቱም መማር ባለመቻላችን ከጥበብ ቅና እውቀት አራራቀን።
👉🏾Rezenom Almaw

🚢
ርእስ፦ የስኬት ፍልስፍና

📝💓 ፀሀፊ ናፖሊዮን ሂል

✍️ተርጓሚ ራሴለህ ጋሻው

✍️✍️ዘውግ Psychology

✍️📝የገፅ ብዛት 203







OUTWITTING THE DEVIL የተሰኘው መጽሐፉ ለ70 አመታት ሳይታተም ተደብቆ ቆይቷል፡፡ ይህ #የስኬት_ፍልስፍና በሚል ተተረጎመ
የስኬት ፍልስፍና @Enmare.pdf
54 MB
የስኬት ፍልስፍና


ርእስ፦  የስኬት ፍልስፍና

📝💓 ፀሀፊ  ናፖሊዮን ሂል

✍️ተርጓሚ  ራሴለህ ጋሻው

✍️✍️ዘውግ Psychology

✍️📝የገፅ ብዛት 203







OUTWITTING THE DEVIL የተሰኘው መጽሐፉ ለ70 አመታት ሳይታተም ተደብቆ ቆይቷል፡፡ ይህ #የስኬት_ፍልስፍና በሚል ተተረጎመ
አባቴ ድሃ ታግሎ ኗሪ ነበር ። ነፍስ እስካውቅ የሆነ ኮት ነበረው ፤ ዘወትር ነበር የሚያደርገው ፤ እሱን ኮት ሳይለብስ ከመንገድ ባገኘው የማልፈው ሁላ ነው የሚመስለኝ ።

ረጋ አባባሉ የሞላለት ያስመስለዋል ።
በትንሽ በትልቁ አይናደድም ፤ በትንሽ በትልቁ አይመክረኝም ። ከሰው ጋ ሲጣላ አጋጥሞኝ አያውቅም ።

ሰላማዊ ሰው ነው ፤ ሁሉንም ሰው በሙሉ ስም ነው የሚጠራው እኔንም ጭምር ። እናቴን ግን ያቆላምጣታል ። እሷ ጋ ሲደርስ የሚሆነው መሆን ለየት ይላል ፤ ይቀልዳል ፣ ያሾፍባታል ግንባሯን ይስማታል ።

አጠገባችን ላሉ እጅግ ከእኛ የበለጠ ደሃ ለነበሩት እማማ አዛሉ እና ከእኛ ቤት ፊት ለፊት ሰፊ ትልቅ ግቢ ላላቸው ለዲታው ጋሽ ይልማ የሚሰጠው ሰላምታም ተመሳሳይ ነው።

አባቴ ችግር ሲያወራ አይቼው አላውቅም ፤ ዝም ብሎ የቻለውን ያደርጋል ፤ ምን አልባት ለእኔ ማውራት አያበድረኝ ፣ አይሞላልኝ ብሎ ይሆናል እንዳልል ስራ ላለው ለታላቅ ወንድሜም እንኳን አያወራም ።

ስራ በያዝኩ በሶስተኛ ወሬ በአንዴ አራት ሙሉ ልብስ ገዛሁለት ። ደስ አለው በጣም ።
እጄን ይዞ
አትጣ
ሞገስ ልበስ
የአንተ የሆነ ሁሉ ይባረክልህ ብሎ መረቀኝ

በአራተኛው ቀን ........ከገዛህልኝ ሁለቱን ሙሉ ልብስ ለወዳጄ እና ለበሪሁን መስጠት ፈልጌ ነበር አለኝ (ወዳጄ እና በሪሁን ወንድሞቹ ናቸው)

ቅር ይልህ ይሆን ብሎ አይን አይኔን አየኝ

አጠያየቁ አስተያየቱ የሆነ የሚያሳዝን ነው ፤ አንጀቴን በላው

ከእነሱ ጋ በጋራ መዘነጥ ፈልጎ ከእነሱ ተለይቶ ላለመድመቅ ነው መሰለኝ

ሌላ ቃል ስላጣው አይ ጋሼ ብዬ እጁን ሳምኩት!!!
© Adhanom Mitiku
2024/09/22 05:42:55
Back to Top
HTML Embed Code: