Telegram Web Link
ገጣሚና ሰዓሊ ገብረ ክርስቶስ ደስታ

16ቱ የጥበብ ስራዎች ፤

#ታሪክን_ወደኋላ
"......መጀመሪያ እራስሽን ውደጂው፣ ከዛ በኋላ ሰውን መውደድ ጀምሪ። ከዚያ አካባቢሽን ሀገርሽን በእራሱ ጊዜ ትወጃለሽ። ችግሩ የሰው ልጅ መጀመሪያ መውደድ የሚጀምረው እራሱን ሳይሆን ሌሎችን ነው። ከዚያ ባደገ ቁጥር ሰዎችን ጠልቶ እራሱን መውደድ ይጀምራል።
......እና እንዳልኩሽ አንድ ሰው ሀገር ከመግዛት እራሱን መግዛት ይከብደዋል፣ እራሱን የገዛ ሰው ግን አለምን መግዛት ይችላል። ስለዚህ እራስን መውደድ፣ መግዛት እና ማሸነፍ ከሁሉም ይቀድማል።....."

".......ሁሌም ከማንም እንደማታንሺ አስቢ፣ ለእራስሽ ክብር ስጪ፣ ራስሽን ውደጂ፣ ሁሉንም እችላለው ብለሽ ተነሺ፣ ፈተናዎችን በጥበብ እንደምትወጪ እመኚ፣ አንብቢ፣ ሁሌም ለነገሮች ዝግጁ ሁኚ፣ ያኔ ሁሉም ሰው ያከብርሻል። ሁሉንም ታሸንፊያለሽ፣ ሁሉም ይወድሻል።

ሰነፍ አትሁኚ፣ የሰው ልጅ ውድቀት የሚጀምረው በስንፍናው ነው። ሰነፍ ሰው መጥፎ ነገሮችን ሁሉ በጫንቃው ይሸከማል። ምክንያቱም በስንፍናው ስጋው የሚበላው ያጣልና። ሰው ሰነፍ ከሆነ የሰውን ይመኛል። ሌባ ይሆናል፣ ውሸትን ይናገራል፣ ነውርንም ይፈጽማል። ስለዚህ ብርቱ ሰው መሆን አለብሽ።

አንቺ ማንንም መፍራት እና እንደዚህ ይሉኛል ማለት የለብሽም!! አንቺ በትክክል መልእክትሽን ካስተላለፍሽ ምን ችግር አለው ሰው የፈለገውን ቢል?? ሰውን አክብሪ!!!....."

#ምንጭ 👇
ከ "ውብ" መጽሐፍ የተወሰደ


Share :-
@ethioleboled
"የማላቅፍህ ስለምሰስትህ ነው…።"
              በሩት ሃብተማርያም ....👩‍💻
#ክፍል____1

ከማሰሮ የዘገንከውን ትኩስ እፍኝ አሹቅ ወደ  አፍህ ስታስጠጋው፣ አፍህ እዚህ 
የከንፈርህ ጥጋት  ጋር ስታደርሰው፣ 
ብርር’ድ ብሎብህ ያውቃል? ወይ ደሞ መንገድ ላይ ለማታውቀው ሰው በፈገግታ ሰላምታ ሰጥተህ  ስታልፍ ፈገግታህ በስንት ሰከንድ ይከስማል? የእግርህን አውራ ጣት የመታህ ትንሽ እንቅፋት ልብ 
ስር የሚገባ ህመም በስንት ደቂቃ 
በረደልህ? የጣቶችህን አንጓዎች 
እያጠፍህ ‘ቋ’ ለማድረግ የፈጀብህን 
ቅፅበት በቁጥር ታውቀዋለህ? 

በህልምህ ያየኸው ውብ ዓለም ልክ ዓይንህን ስትከፍት ለመጥፋት ከብርሃን ይፈጥን አይደል? ልክ እንደዛ ፣ ልክ እንደ ሁሉም ፍቅር ይበርድብኛል። በእጄ ሳልይዘው ይሰበርብኛል። ምን ላድርግ?
#የቀጠለ
"ዘንድሮ ፍቅር የለም!”
እያሉ በራሳቸው የፍርሃት ድንበር ውስጥ እንዳሉት ሰዎች አይደለሁም። ሰው የተባለ ፍጡር በህይወት እስካለ ድረስ
ፍቅር የትም አለ። አይታየንም እንጂ ያያዘን ቀጭን መሳይ ጠንካራ ድር ፍቅር ነው። አለ ብዬ አምኜው እየኖርኹ ታዲያ ስይዘው ለምን ጥብቅ አያደርገኝም? ስዳስሰው ቁንጥጫው የሚብሰው
ለምንድን ነው?

ስስመው ለምን ጥርሱን ያገጣል? መጣ
ብዬ “እሰይ! እሰይ! ከመጣህ ማርያም ታምጣህ!” ብዬ፣ ከንፈሬ ከማሰሪያው ተፈቶ ፈገግ ሳልል ወዴት ሄዶ ይጠፋብኛል? እንደ ማድጋ ሊጥ፣ ተሟጦ እንደሚጋገር፣ አሟጦ የሚያፈቅረኝ የት
ነው? ሁላችንም፣ እኔም አንተም ሳንዘጋው የተውነው የትዝታ በር አለን።
በቀጭን የምትነፍስ ትላንትን የምትናፍቅ ንፋስ የሚያሳልፍ በር አለን። አሁን ቁጭ ብዬ ሳስበው አጠገቤ የነበሩ፣ ያፈቀርኳቸው ፤ ያቀፍኝ ፤ ሳናይሽ አናድርም ልመናዎች ሁሉ የትዝታቸውን
በር መሸጎሪያ እንጂ በእያንዳንዳቸው ልብ ውስጥ የራሴ የትዝታ በር የለኝም።
ታዲያ ይሄ አያደክምም?

በዓለም ያንተን አይነት ፈገግታ ያለው አይቼ አላውቅም። ፈገግ ስትል ፊትህ ላይ ያለውን ኃይል አልችለውም። እወድሻለሁ ስትለኝ እያንዳንዷን ፊደል ሰንጥሬ ባያት ምንም ማብለጭለጫ ቅመም እንዳልተጨመረበት አውቃለሁ። ፊቴ ስትመጣ የዋህነትን ብቻ ትሰዋልኛለህ። ደስ ትለኛለህ። ዓይኔን ከድኜ እጄን ልሰጥህ እፈልጋለሁ። ታዲያ ግን እፈራለሁ። ፍርሃቴን አሸንፌ ባቅፍህ በማግስቱ ትተወኛለህ።

አነሳሴ ጋ አውግተን ሳንጨርስ ወድቄ 
እነቃለሁ። እንዲሁ ባይህ ይሻላል። እንዲሁ በሩቅ ብመኝህ ይሻላል። ምኞቴን ሸሽጌ ፤ ምኞትህን ሸፍኜ እንደ ሩቅ ዘመድ ብንተያይ ይሻላል። ላጣህ ስለማልፈልግ ነው ከጠረንህ አፍንጫዬን ያቀብኩት 
፤ እቅፌን ያቀዘቀዝኩት ዘላለም በልብህ እንድታቅፈኝ ነዉ። የ40 ቀን እድሌ ትለኝ ነበር አያቴ። ያኔ ታዲያ እስቅ ነበር።

40 እና እድል ምን እንዳቆራኛቸዉ ይደንቀኝ ነበር። አሁን በየቀኑ ሳይገባኝ አልቀረም። የ40 ቀን እድል አለን ሁላችንም። በማይታይ ማተብ አንገታችን ላይ ያለ።
            🌩🌩🌩🌩🌩
ተራራው ሰው፣ ሆኖ 
ከንፈሬን ባይስመኝ
ተራራው ሰው ሆኖ፣
ጡቴን ባይዳብሠው
ተራራው ሰው ሆኖ፣
ዓይን ዓይኑን ባላይ
ጸሀይ እሞቃለሁ፣ ወጥቼ ከላይ።


#ይቀጥላል ....

#ቻናሉን_ለማጋራት
                  ➘
          
@ethioleboled
📜❦ ══ •⊰❂⊱• ══
ቀን ቀን እስቃለሁ ..
<unknown>
ከላይ ከተፃፈው ፅሁፍ ጋር የሚሄድ ሙዚቃ ነው ተጋብዛችኋል 😍

#ቻናሉን_ለማጋራት
                  ➘
          
@ethioleboled
📜❦ ══ •⊰❂⊱• ══ ❦
በኔ መንገድ ካልሔድክ
መንገድህ ገደል ነው" ፣ ማለት የሚከጅል

"እንደኔ ካላሰብክ
ማሰብ አትችልም" ፣ ሊል የሚዳዳው ጅል

በህይወት መንገድ ላይ...
እንደራሴ ስጓዝ ፣ ነፍሴ ምትሞግተው

ስንት ገደል አለ
"ድልድይህ ነኝ" የሚል ፣ መሻገር ሲያቅተው፡፡

📝በላይ በቀለ ወያ📝

share
@ethioleboled
የ 3ቱ ከተሞች የትራፊክ ፖሊስ በዘመናቸው ፤

በአዲስ አበባ ፣ ድሬዳዋ እና አስመራ

በ 1920ዎቹ

#ታሪክን_ወደኋላ
"የማላቅፍህ ስለምሰስትህ ነው…።"
              በሩት ሃብተማርያም ....👩‍💻
#የመጨረሻ_ክፍል

... ከናፍቆት ጋር ድብብቆሽ መጫወት 
ስጀምር፣ ልክ እንደማንኛዉም ተጫዋች 
ተናፋቂው ተደብቆ ሲቀር ጨዋታዬን 
አቆማለሁ ብዬ ነበር። የመፈለግ ፅናቴ 
ተሰብሮ ወይም ሟሙቶ ያለቀ መስሎኝ 
ነበር።እንደዚህ የተደበቀበትን ጋራና 
ሰርጣሰርጥ ሁሉ በልቤ አስሳለሁ ብዬ 
አልነበረም። ልቤ ኩስ ኩስ ብላ ከእግሬ 
ስር እየተራመደች የምትመራኝና 
የምታወራኝ ይመስለኛል። እንዴ 
እሱም ጋር እኔም ጋር ልቤ ልትኖር 
አትችልም። ሲፈቀር ልብ ይሰ’ጣል ይሉ የለ እንዴ?  ታዲያ የኔ ልብ ይቺት ከፊቴ። ፍቅር ሳይሆን እልህ ነው እንዴ  የያዘኝ? የጨዋታ አሸናፊ አለመሆኔ ተሰምቶኝ ነዉ እንዴ? እያልኩ አስባለሁ።
#የቀጠለ
“ ሰማሽኝ እቴ አካልሽ ሁሉም እዚህ ነው። ሀሳብሽ ፤ ህልምሽ ፤ እርካታ እና ስሜትሽ
ሁሉም ሰዋዊ ስሜቶችሽ ናቸው እሱ
ጋር የተደበቁብሽ። ሰው ሲያፈቅር
ሰውነቱን ፣ ሰው የመሆኛ፣ ሰው የመባያ
ነገሮቹን ነው አሳልፎ ለሚያፈቅረው
የሚሰጠው። አብሬሽ ያለሁት ልብ
ተብዬ እንድጠራ የሚያደርጉ ስሜቶቼን
ስለወሰደብኝ ነው።” አለች ኩስ ኩስ
እያለች።

... ለነገሩ ልክ ናት እላለሁ። ምን
ታልሚያለሽ ቢሉኝ ከንፈሩ ስር
የማርያም ስሞሹ መሆን አይደል?
ምን ታስቢያለሽ ቢሉኝ ንፋስ የራሱን
ፀጉር ስንቴ ዳበሰችው? ጨረቃ ለምን
አዘቅዝቃ ታየዋለች? እንቅፋት መቶት
ይሆን? አንዷ ቁሌታም ስታልፍ አይታ
ተመኝታው ይሆን? አንድ ጤነኛ ሰው
እንዲህ ያስባል? ...አስቀድሰው ሲጨርሱ እንደሚሰጥ
ቁራሽ፤ቤቱ ቢሄድም የሚበላ እንደሌለው
ሰው ያቺን ቁራሽ እንደሚያጣጥማት
(እንደዛ ናፍቆቱ ይጣፍጠኛል) ፤
የመጨረሻ የጎለተችው ድንች ተሸጦላት
ለልጆቿ ራት መግዛት እንደምትፈልግ
እናት ገዢን በጉጉት እንደሚጠብቁ
ዓይኖቿ (እንደዛ በየቀኑ ለፍቅሩ እጓጓለሁ ) ፤ ረጅም ዓመት በደዌ ተሰቃይቶ ጎኖቹ ሁሉ በቁስል ነደው መተኛት እንደናፈቀው ፣ፈውስ መጣልህ፣ ጎንህ አገገመ ተብሎ የነገ ፈውሱን አስቦ
እንደሚጋደም ጎልማሳ (ልክ እንደዛ የፍቅር እፎይታን እናፍቃለሁ)።

... ዓይኔን አልነግረውም። ፍቅርህ
ላይመጣ ይችላል ብዬ አልነግረውም።
በሩቁ እያየነው እንደምንኖር አልነግረውም። ጉጉቱን አውቃለሁና
ቢጠብቅ ይሻላል። እጄን “ደረቱን አትዳብስም ፤ አንገቱ ዙሪያም ላትሆን ትችላለህ እኮ” ብዬ እንዴት ላስረዳው?
እግሮቼን “ወዳለበት አትሄዱም፣
ቁሙ!!” ማለት አልችልም። ከእግሬ
ቀድሞ የእርምጃ ሀሳቤ የት እንደሚሄዱ
ይነግራቸዋል። ማንንም ማዘዝ አልቻልኩም። ሀሳቤን ፤ ህልሜን ፤ ዓለሜን ሰጥቼ ነዋ የወደድኩት። ግን ትወደኛለህ?
#አለቀ

#ቻናሉን_ለማጋራት
                  ➘
          
@ethioleboled
📜❦ ══ •⊰❂⊱• ══ ❦📜
👨‍🌾👩‍🌾..የእረኛው የፍቅር ቃላት..👩‍🌾👨‍🌾

🗣...
ሳገኝሽ-
ላሜ ጠፍታ ሳገኛት እንደሚሰማኝ አይነት ስሜት፣
🗣
ስትስቂልኝ-
ከብቶቼ በልተው ሲጠግቡ እንደሚሰማኝ አይነት ሃሴት፣
🗣
ስታኮርፊ-
በሬዬን ዋዥማ የነፋው ያህል ይጨንቀኛል፣
እይዘው፣
እጨብጠው፣
የማደርገው ይጠፋኛል።
😍😍😍
አደራሽን በንግግሬ በምሳሌዬ አትሳቂ፣
የፍቅሬን ጽናት ለማውቅ ከፈለግሽ ከብት ጠብቂ።    😊😊😊

📖.....ዋዥማ ማለት የላሞችን ሆድ ውጥር አድርጎ ነፍቶ እስከሞት የሚያደርስ ችግር ይፈጥራል ተብሎ በተለምዶ የሚወሰድ የሳር አይነት ነው።

@ethioleboled ▬▭🌹▬▭▬🌹
2024/09/22 21:18:55
Back to Top
HTML Embed Code: