Telegram Web Link
የዶርም ወግ....


ምነው በእኩለ ለሊት ለምትሉኝ አንባብያን ሰሙነ ማማረር ላይ እንደሆንኩ ልነግራችሁ እወዳለሁ።


"ከእዚህ ጊቢ በሰላም ከወጣሁ ወደፊት ማንኛውንም ከባድ ሁኔታ ማለፍ እችላለሁ....."

"እስማማለሁ"

"እዚህ ጊቢ ለሚመጡ ነው ማዝነው..."

"ፎቁን ሲያዩት እኮ ደህና ጊቢ ይመስላል..."

" በእኔ የደረሰ በእናንተም አይድረስ...እኔ እንደተሸወድኩት እንዳትሸወዱ ምናምን እያልኩ ነው ከበር የምመልሳቸው..."

"ምኑም የጤና ጊቢ አይመስልም...."

"ጤናችንን አጥተን መውጣታችን ነው..."


የ pharmacy ትምህርት 6 አመት ከተደረገባቸው ጓደኞቼ ጋር እያወራን ነው....

"የኮሮና ጊዜ የተበላሸው scedule እንዳለ ሆኖ አንድ አመት የሚያስጨምር የኮርስ መጨመር እንኳን በሌለበት ሁኔታ ለምን 1 አመት ተጨመረ...ማንም አያውቅም...."የትምህርት ሚኒስቴር ትዕዛዝ ነው"...ነው የሚለው ጥገራው..የትምህርት ሚኒስቴር ህግ የሚሰራው ለዚህ ጊቢ ብቻ ነው...."...ጦ ናት።





"እኔ እንኳን ተመራቂ ነኝ...ይብላኝ ለከራሚ...."....እኔ ነኝ።እኔ ከmedical labratory ትምህርት ክፍል ነኝ። እኔም የዚህ ኢ-ፍትሀዊነት ተጠቂ ነኝ...4 አመት የነበረው ኮርስ 5 አመት ሆኖብኛል...

እንዴት 5 አመት ሆነ...lag አርገሽ ነው ሌባ...የሚሉኝ ሰዎች አልጠፉም....እንዴት ማለት ጥሩ ብዬ የተነገረኝን ስነግራቸው የስላቅ ሳቃቸው ያመልጣቸዋል....የምር ያስቃል እኮ...

"ሰኔ 30 የተበጀተ በጀት በዛው አመት ማለትም ከአንድ ወር በኃላ ሀምሌ ላይ አልቆ 5 ወር እረፍት ተሰጠን..."...የሚል ሰበብ አያስቅም ነው የምትሉኝ...

አንድ material or reagent በሌለበት ጊቢ

"ለትምህርት ጥራት ሲባል 7 አመትስ ብትቆዩስ ምን አለበት ...."...የሚል ቀልድ አያስቅም ነው ምትሉኝ...


እናቴ መመላለስ ሳበዛ ምን ብትለኝ ጥሩ ነው....

"ለምን ምሳ እየቋጠርሽ አትሄጂም....ከዛ ጊቢ እኛ ሀብታም ነን...😂"



"ባለስልጣኖቹ የጀመሩት ፎቅ...ወይ ሆቴል ብቻ whatever ካላለቀ እኛ እዚው እድሜያችን ማለቁ ነው..."

"እኔ እኮ አጥር ለሌለበት ጊቢ በአጥር ዘሎ መግባት አይቻልም ሲሉ ነው በእነርሱ ተስፋ የቆረጥኩት..."

"በቃ በቃ ዝም በሉ...በቃ በቃ አናውራው...pc አቀብዪኝ ፊልሜን ልይበት....ተቃጠልኩ እኮ...."


"አንድ መንገድ ብቻ ባለው ጠባብ ጊቢ ውስጥ አሸን አዛዥ ምን ይሉታል...ባላየ ማለፍ ራሱ እኮ አይታሰብም በቀን ሰላሳ ጊዜ ሰላም እየተባባልን ካካካ..."

"የምንሳልበት የምንሞረድበት የህይወታችን ክፍል ነው ...ለበጎ ነው ብለን እናስብ...."

"እንደዛ ማሰቡ ባይከፋም ሮቦት መሆን ግን ሰልችቶኛል....በሆነ አካል መመራት...programmed እንደተደረገ አካል እላይ ባሉ አካላት መሽከርከር..."

"አሁን ተሳሳትሽ...."

"ምኑ ጋር ነው የተሳሳትኩት...."

"እላይ ባሉት አካላት ብቻ አይደለም...እታች ያለም ስልጣኑን ሊያሳይሽ የቻለውን ያደርጋል...የምር የዚህ ጊቢ በማንኛውም ዘርፍ የመቀጠሪያ መስፈርት 'ተማሪዎችን ማንገላታት...ማስመረር...ተማሪዎችን ውሻ ማድረግ.....ማመናጨቅ...መበደል...'...እና የመሳሰሉት ስርአት አልበኝነቶች ነው የሚመስሉኝ...."


"ደግሞ በሆነ አካል መሽከርከር ከጊቢም ከወጣን በኃላ አይቀርልንም...እሱ ደግሞ የህዝብነት መስፈርት ይመስለኛል...."


"ፖለቲካ ውስጥ ገባን ሳናስበው...."


"በቃችሁሁሁ እንዴ በቃ እንዳታሳብዱኝ...እንዴ ያማችኃል እንዴ በቃን በጌታ ባሰብኳቸው ቁጥር እየነደድኩ ነው...ሸ መስኮቱን ክፈቺው በጌታ ጋልኩ በንዴት....."




ከምናሳብዳት ብለን አቆምን....ግን የምር እውነቷን ነው ሮቦት መሆን ይሰለቻል።



ሸዊት ነኝ የሚዛን ቴፒ ቀበጥ የጤና ጊቢ ምርኮኛ😂....ብሶቴን ጨርሳችሁ ስላነበባችሁት አመሰግናለሁ....ይሄን ጊቢ ስቦጭቅ እንደተመረቅኩ ነው ሚሰማኝ😂 መልካም አዳር።





https://www.tg-me.com/ethioleboled
በህይወቱ ለመጀመርያ ጊዜ ስላፈቀራት ሴት ታሪክ በውስጥ መስመር ካጋራኝ የቻናሉ ተከታይ ፅሁፍ

የቃላት ማሻሻያ ተደርጎበት የቀረበ

📜....📝
በእውነት ነው ምላቹሁ በህይወቴ የዛሬ 14 አመት ገደማ በጣም የምወዳት ቆንጅዬ ሴት ገጠመችኝ እሷን ለማገኘት ያልሆንኩት ያልደረሰብኝ ስቃይ የለም እኔ 18 ቀበሌ ልጅ ስሆን እሷ የ42 ቀበሌ ልጅ ናት በመሀላችን አስፓልት ነው የሚለየን ምንም የደሀ ልጅ ብትሆንም ለኔ ልዩ ሴት ነበረች። እስካሁንም ለኔ ልዩ ናት።

ትዝ ይለኛል የዛኔ በኢት..አቆጣጠር በ1986 አ.ም የ8 ተኛ ክፍል ተማሪ ነበርኩ እሷን ካየሁ በኋላ ሚኒስትሪ ሁለት ጊዜ ወድቅያለሁ ሀሳቤ ሁሉ እሷጋ ነበር። ቤቴ ውስጥ ሆኜ መሽቶ እስኪ ነጋ በጣምም ይጨንቀኝ ነበር። በሷ ጉዳይ ያልተጣላሁት ጎረምሳ የለም እሷን ለማግኘት በራሴ ላይ ትልቅ ችግር እየፈጠርኩ ሄድኩ። ከቤተሰብ ጋር አለመስማማት፣ ጸባዬ ሁሉ ተቀየረ።

ቤተሰቦቼ እኔን ይናፍቁኝ ጀመር ውሎዬ ከሷ ጋር... ጠዋት እነሳና ሰፈሯ እቤታቸው ፊትለፊት መገተር ሆነ ስራዬ ታሪኳን ስታጫውተኝ ልገልጽላት የማልችለው ፍቅር ያዘኝ እንቅልፍ ነሳችኝ ቤቴ ውስጥ ምንም ነገር አልጥም አለኝ የሚያሳስበኝ ምን ጊዜም የሷ ችግር ብቻ ነው። ስለቤተሰቦቿ ጠይቂያት እናቷ በህይወት አለመኖራቸውን እህት ወንድም እንደሌላት አባቷ በፖለቲካ ችግር እስር ቤት መሆኑን እና በእንጀራ እናት መቅረቷን ገለጸችልኝ።

እንጀራ እናቷም በጣም እንደምትበድላት ነገረችኝ እኔም አይዞሽ ከጎንሽ ነኝ እላት ነበር እንጀራ እናቷ እንጀራ በመጋገር ሲሆን ኑራቸውን ሚገፉት ልጅቷ ደግሞ የተጋገረውን እንጀራ አምጥታ እኛ ሰፈር ነበር ምትሸጠው አንድ ቀን ትዝ ይለኛል በጣም ስለምወዳት "ፎቶ በቀለ" ሄደን ፎቶ አብረን መነሳት አለብን ብያት ቀጠሮ ይዘን ሁለት የቁም ፎቶ ጭንቅላት ለጭንቅላት ተደጋግፈን ተነሳን::

የዛን ቀን የእንጀራ እናቷ ከባድ ቁጥጥር ይቆጣጠሯት ስለነበር ጉሊት ፈልገው አጧት መሰለኝ ለሶስት ቀን ያህል መምጣት ተወች ምን ይዋጠኝ የዛን ቀን የጀመረኝ በሽታ ልክ እንደ እርጉዝ ሴት ጠናብኝ በጣም ተረበሽኩ ምሽት ያበሳጨኝ ጀመር የዛን ጊዜ ከምሽት ይልቅ ንጋትን ብቻ እመርጥ ነበር ሲነጋ አድፍጬ በራቸው ላይ መጎለት ጀመርኩ በጠዋት እየተነሳው ብቻ ከሶስት ቀን በኋላ ወደመደበኛው ስራዋ ተመለሰች እኔም መንገድ ላይ እየጠበኳት የያዘችውን መሶብ በጭንቅላቴ እየተሸከምኩላት ወደ ገበያው ማድረሴን ተያያዝኩት የያዘችው እንጀራ እንዳያድር ብዙ እጥርላት ነበር😂😂😂

ብቻ ገበያተኛ ሲመጣ ሰርገኛ ነው ቀጭ ቀጭ አይልም አረ ጥሩ እንጀራ ነው ማለቱን ተያያዝኩት ተመስገን እንጀራውም ቶሎ ቶሎ ማለቅ ጀመረ በንደዚህ አይነት ሁኔታ በጣም እንዋደድ ጀመር ትምህርቴን ብዙም መከታተል ትቻለሁ በመሀል አንድ ቀን አባቴ የክፍለ ሀገር ሹፌር ስለነበር (ነብሱን ይማረው) መሶቧን ተሸክሜላት ያየኛል አይቶኝ እንዳላየ ሆኖ አለፈኝ ወደቤት ገባ እኔም በጣም ደነገጥኩ መኪናውን ሳየው ቶሎ እሷን አድርሼ ተመልሸ ቤቴ ገባሁ። ሰላም አልኩት እሱም ሰላም አለኝ በጣም ሀይለኛ ስለነበር ሁላችንም እንፈራዋለን።

አባቴም "ስማ ልጄ አልታይም ብለህ ከምትሰራው ስራ እታያለሁ ብለህ ብትተወው ይሻልሀል::" ብሎኝ ዝም አለኝ እኔም እሺ አልኩት እያሳሳቀ ነበር የተናገረኝ:: ፋዘርም አንድ ቀን አድሮ ወደስራው ሄደ እኔም በጣም ስለምወዳት በወቅቱ አንድ እንጀራ ዋጋው ስሙኒ ነበር(25 ሳንቲም) ስሯ እየተቀመጥኩ የአንድ ብር ከሰባ አምሳንቲም እንጀራ ቁጭ ብዬ እየገዛኋት እበላ ነበር። (አስቡት 7 እንጀራ😂)

እኔም እሷም ሆነን በቃ ምን ልበላቹሁ እኔ ግን በዛን ሰአት ለፍቅራችን መስዋት መክፈሌ ነው እንሸጥና እንጀራውን ካላለቀ ችግር እንደሚደርስባት ስለማውቅ በቃ እኔው እራሴ እየገዛሁ አብረን ሜዳው ላይ ደረቅ እንጀራ እንበላ ነበር ቁንጣን እስኪይዘን ድረስ 🙈

በእውነት ነው ምላቹሁ ከሷ ጋር እንደዚህ አይነት ኑሮ ስንገፋ ከርመን እንደተለመደው አባቴ ምን ያህል ሀይለኛ እንደሆነ ነግርያቹሀለሁ እኔ በሌለሁበት ወንድሜን የሱንም ያንተንም ደብተር አምጣ ይለዋል። የኔን ደብተር ሲከፍተው ውስጡ ሙሉ ሴሜስተር አንድ ገፅ አልተፃፈበትም ነገርግን ውስጡ የኔንና የሚሚን ፎቶ ያየዋል።

ልክ እንደፈረደብኝ ወደ ቤት ስገባ ቤቱ ጸጥ ጭር ብላል ማን የት ምኑጋ እንዳለ አይታየኝም ከውጪ ስለገባሁ የሰማሁት ያባቴን ድምጽ ብቻ ነው እሱም ና ና ወደዚህ የሚል እኔም አቤት ብዬ ገባሁ የቤቱ በር ተቆለፈ ጎረቤት መጥቶ እንዳይገላግለን 😭😭😭

ከዛው አምጣ ደብተሮቹን አለኝ አመጣሁለት ትምህርት ለምድነው ማትማረው የኔ ጎረምሳ ብሎ ተውኝ ዋጋዬን ሰጠኝ ቦታ ሳይመርጥ አገራችን ትዝ ካላቹሁ ብረት ምጣድ አለ በጣሳ ሻውር መውሰጃ እሱ ላይ ሳሙና አረፋ ተመታና እዛ ላይ ሆኜ የዱላ መአት ወረደብኝ ብድግ እያልኩ ቁጭ ብረምጣዱ ላይ ሆኜ በመጨረሻም ዱላውን ስላልቻልኩት በጣም ስለበዛብኝ ቤት ውስጥ በገመድ ታስሬ ነበር።

እንደበግ ቤት ውስጥ ታስሮ መቀመጥ ስላልቻልኩ የታሰርኩትን ገመድ በጥሼው እሷን ፍለጋ ወደ ሰፈሯ ሄድኩኝ በወቅቱ ስነግራት በጣም አዘነች አለቀሰች የት አባቴ ልውሰድህ አለችኝ በወቅቱ እሷም ሆነች እኔም ችግር ላይ ነን ያለነው ምንም ገንዘብ አልነበረኝም ከእንጀራው ሂሳብ ላይ አጉድላ 3ብር ሰጠችኝ በዛው ዘመድጋ ሄድኩ ለምን እሷን ማየት ነብሴ ይፈልጋል ግን ሊመጣ የሚችለውን ችግር እያሰብኩ ብዙ ጊዜ ሆነን ከሷም ከቤተሰብ ጋርም ሳንገናኝ እዚህ ያለሁበት አገር እህት ነበረችኝ ደብዳቤ ጽፌላት ሁሉንም ነገር ጨረስኩ።

ከአገር ለመውጣት ሁለት ቀን ሲቀረኝ ከአባቴ ጋር ይቅር ይቅር እንድንባባል ከቤተሰብ ጋር አስታረቁኝ እሷንም አግኝቻት በጣም አዘነች እና መቼም እዛ ቴሌፎን ችግር ታውቁታላቹሁ በስደት ላይ ሆነን ሶስት ጊዜ አቀረቡልኝ በአራተኛው እንዲህ አይነት ስም አናውቅም ይሉኛል።

እና የመጀመሪያ ፍቅር አያድርስ ነው የአንድ ብር ከሰባምሳንቲም እንጀራ በየጊዜው ያስበላል ብላቹሁ አታምኑኝ ይሆናል እና እናንተም የደረሰባቹሁን እስኪ ጻፉት ወደዚህ ለመራሽኝ እህቴ እድላዊት በጣም ነው ማመሰግንሽ አክባሪሽ ጣሴ ጣሱካካካ ☺️☺️😔

#ያጋሩ
       ➴
@ethioleboled ▬▭🌹▬▭▬🌹
የተሰበሩ ክንፎች .pdf
25.9 MB
📓 ርዕስ፡ የተሰበሩ ክንፎች
✍️ ደራሲ ፡ ካህሊል ጂብራን

📚 @ethioleboled
ቀላሉን ነገር አታካብድ @Bemnet_Library.pdf
34.3 MB
📓 ርዕስ፡ ቀላሉን ነገር አታካብድ
✍️ ደራሲ ፡ሪቻርድ ካርሰን

📚 @ethioleboled
📝አንዳንድ ታሪኮች ርዕስ የላቸውም--ተነግረው እንዳልተነገሩ ይረሳሉ።

📝አንዳንድ ሰዎች ስም የላቸውም--ኖረው እንዳልኖሩ ይቆጠራሉ።

📝አንዳንድ ገድሎች አልተዘከሩም--የባከኑ መስዋቶች ይባላሉ።

📝አንዳንድ ቅሌቶች ሰው ፊት አልታዩም--እንዳልተፈፀሙ ሁሉ በጨለማ ውስጥ ይቀራሉ።

📝አንዳንድ አወዳደቆች ከትዝብት ተጋርደዋል--ዙሪያውን ገላምጠን ልብሳችንን አራግፈን እንቀጥላለን።

📝አንዳንድ ህዝቦች በወል ተረስተዋል--ለመታሰቢያነት የቀረላቸው  ምንም የለም።

📝አንዳንድ ኮቴዎች በመርሳት ተጠቅተዋል--አንዳንድ ወኔዎች ለሞት ዳርገዋል--ከሁሉም በላይ ግን አንዳንድ ልቦች በሶስት መሀላ ተክደዋል።

📓ሀገር ያጣ ሞት
              ✍️ ሄኖክ በቀለ ለማ

🔵 @ethioleboled
እንዲው በደፈና "ወደድኳት! አበድኩላት።" የሚያሰኝ ድፍን ፍቅር አልነበረም የያዘው።በርህራሄ እና በመተሳሰብ ላይ መሰረቱን የጣለ እውን የሚዳሰስ እና የሚጨበጥ፤ንፋስ የማይገፋውና ውርጭ የማያበርደው ፍቅር.....

📓ወገግታ
                      ✍️ የሺጥላ ኮኮብ

📚 @ethioleboled
ወገግታ @Bemnet_Library.pdf
11 MB
📓 ርዕስ፡ ወገግታ
✍️ ደራሲ ፡የሺጥላ ኮኮብ

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
⚪️#ልጅ ፡ አባቴ ባህሪዬ እንዴት ቢሆን ደስ ይልሃል ?

#አባት፡ እንደዚህ ሁን ልጄ

⚪️#ልጅ ፡ እንዴት ?

#አባት ፡ እንደ ውሃ ሁን ባስቸገረ ግዜ እሳትን ቢያጠፋም በተፈለገ ጊዜ ግን እንዲገኝ ዛፍ ማሳደጉን አይተውምና ፤

እንደጨውም ሁን ለሁሉም ምግብ ቢፈለግም በቀላሉ ይገዛ ዘንድ ግን-ዋጋው ውድ አይደለምና ፤ ከሁሉ ከሁሉ-ግን እንደ ወተት ሁን በተውት ግዜ በሌላ-መልክ ተመልሶ ይመጣል እንጅ አይበላሽምና-በተገፋም ግዜ ከፍ ከፍ ይላልና።

⚪️#ልጅ፡ እሽ አባቴ እንዳልሆንስ የምትፈልገው የለም ?
#አባት አለ ልጄ፤ እንደዚህ አትሁን

#ልጅ ፡ እንዴት ?

⚪️#አባት፡ልጄ ሆይ እንደ መርፌ አትሁን የሌሎች ብዙ ቀዳዳ እየደፈነ የራሱን አንዷን መድፈን አይችልምና፤

እንደ መቋሚያም አትሁን ለሌሎች መደገፊያ እየሆነ ለራሱ ግን መቆም አይችልምና ፤

ከሁሉ ግን እንደ ደወል አትሁን ! ከሁሉ ቀድሞ ነቅቶ ሌሎችን ለቅዳሴ ቢቀሰቅስም እርሱ ግን አያስቀድስምና።
...
............
**** መልካም ቀን
መርሳት ግን እንደመተው ቀላል አይደለም።
➡️አንዳንዴ useless እንደሆንን ሊሰማን ይችላል፤

አንዳንዴ ሰዎች እንዲረዱን ፈልገን አልተረዱን ይሆናል፤

አንዳንዴ ምክንያቱንም ሳናውቀው በምንወዳቸው ሰዎች ፊት ላይ ጥላቻ ተስሎ አይተን ይሆናል፤

አንዳንዴ ለሰዎች ከሰጠነው አክብሮት በተቃራኒ ንቀት ተቀብለን ይሆናል፤

አንዳንዴ እድሜያችንን ሙሉ ስንመኘው የነበረና ትልቅ የመሠለን ነገር ስናገኘው ትንሽ ሆኖብን ይሆናል፤

👍አንዳንዴ ለሰዎች መድረስ ፈልገን ሁኔታ፣ ጊዜና አቅም አጥተን መድረስ አልቻልን ይሆናል፤

አንዳንዴ አንደመልአክ የምናያቸውን ሰዎች በህይወት አጥተን ይሆናል፤

አንዳንዴ ለቤተሰቦቻችን ልንፈጥርላቸው እንፈልግ የነበረውን ዓለም ቀርቶ ትንሽ እንኳን ልንደግፋቸው አለመቻላችን አሳዝኖን ይሆናል፤

አንዳንዴ ሁሉም ነገር ትርጉም አጥቶብን ይሆናል፤

አንዳንዴ ሁሉም ቀን አሰልቺ፣ በድብርት የተሞላ እና ተመሳሳይ ሆኖብን ይሆናል፤

አንዳንዴ ከዛሬ የበለጠ ነገ ጨለማ ሆኖ ታይቶንም ሊሆን ይችላል፤

አንዳንዴ ሁሉም ነገር መኖር ራሱ ሳይቀር ከብዶን ይሆናል፤

አንዳንዴ ...

አንዳንዴ...

አንዳንዴ...

ግን It's okay to feel bored, sad, useless, and hopeless at times.. 

live

Lough

Love

ከሁሉም በላይ የተሻለ ጊዜ ከፊት አለ። 💙

በውስጣችሁ ያለውን ክፋት በውስጣችሁ ባለው መልካምነት የምታሸንፉበት የተዋበ ቀን ይሁንላችሁ
every friend you invite! 🎉

🌟 Share this link: https://www.tg-me.com/botifyai_bot?start=referral_6405623892




Best ai bot arif Nw mokrut
እፎይታ @OLDBOOKSPDF.pdf
17.9 MB
📚ርዕስ:- እፎይታ The Count of mònte
📝ደራሲ:-Alexander Dumas
👤ትርጉም:-ተሾመ ዳምጠው
📜ዘውግ:- ልብወለድ
📅ዓ.ም:- 1982 እኤአ
📖የገፅ ብዛት:- 602

📌ማጋራት አይዘንጋ!
@ETHIOLEBOLED
የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ የመታሰቢያ ሐውልት ፤

ሚያዝያ/ 1928 ዓ.ም

አዲስ አበባ

#ታሪክን_ወደኋላ
አልቦ ዘመድ - ብርሃኑ ድንቄ.pdf
3.5 MB
"አልቦ ዘመድ" እንደያዘው ጠቃሚ ሀሳብ ብዙም ያልተዋራለትና ያልተነገረለት ምርጥ መጽሐፍ ነው።አንብቡና አትርፉበት።

ማጋራት መተሳሰብ ነው!
📚 @ethioleboled
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
ክፍል አንድ

ታስታውቃለች ብዙ ፍቅር አግኝታ ነው ያደገችው ፤ የለመደችውን እንክብካቤ አልሰጠኋትም መሰለኝ ወይ ደግሞ አንደበቴ እና ሁኔታዬ አልተገጣጠመላትም ።

ግራ ገብቶታል ።

በፈለገችው ሰዓት አታገኘኝም ፣ ባላሰበችው ጊዜ ከብዙ እወድሻለሁ ጋጋታ ጋ እጠራታለሁ...አታመነታም ትመጣለች ።

ካለ እቅዶ እንበላለን ፣ እንጠጣለን ፤ ሞቅ ይለናል ። አልጋ ቦታ ቀድሜ ባሰብኩት መሰረት እወስዳታለሁ ፤ ልብሷንም እሱንም ምንቅርቅር እያደረኩ አራቁታታለሁ።  

እንደምወዳት እየነገርኩ አልጋው ላይ እየገለባበጥኩ ፣ እየተገለባበጠችልኝ እወስባታለሁ ።

ሁኔታዋ መቁነጥነጧ ደስ ይለኛል

እርቃኗን ለብዙ ሰው የታየች  አይመስለኝም ከተወሰብን በኋላ ቶሎ ትከናነባለች ፤ ጡቷን ፣ ገላዋን  ምናምን በአንሶላ ትከዳድናለች ።

ወሲብ ላይ እንደፈለገችው አትቃትትም ወይ ከቃተተች በኋላ አንገቴ ውስጥ ትወሸቃለች ፤ ታፍራለች ነፃ መሆን ይሳናታል

ሻወር ቤት ተጣጥቤ ስመለስ ቅር ያለው አይን አያለሁ ፤ ቀስ ብላ አይኗን ከእኔ አሽሻ ሻወር ቤት ትገባለች ፤ ሻወሩን ትከፍተዋለች  ሻወሩን እንደከፈተችው የምታለቅስ ይመስለኛል።

Empty sex አለመደችም ።

ስሜቷ ተብትቧት መላመድ አጃጅሏት በፈለኳት ሰዓት እስሬ አለመጥፋቷ ይዶክካታል ።

ከመርኋ ጋ አኗኗሯ ተጣርሶባታል ፤ ሁኔታዬ እንደምትፈልገው ፣ እንደምትመኘው አይደለም መሰለኝ !

አብሬያት ያለሁት እኔ ልኳ እንዳልሆንኩ ገብቷታል ፤ ልቤ ላይ ቦታ እንዳላት እና እንደሌላት እርግጠኛ አይደለችም ፤ እልህ እና ግራ መጋባት ነው ከእኔ ጋ ያጣበቃት ።

ልምድ ስለምበልጣት ፣ በእሷ ልክ ስለማልወዳት ሁኔታዋን ከስሜት ውጪ ሆኜ ማጤን አልከበደኝም ።

እያንዳንዱን ነገሬን ትመራመራለች ፤ በዋዛ የማወራውን ነገር ሁሉ ትርጉም ትፈልግለታለች ።

ታሳዝነኛለች ።

ልጅነቷ ያሳሳል ። ስንዋሰብ ፊቷ ፣ አተነፋፈሷ  መቅበጥበጦ ይማርከኛል

ስለምታፈቅረኝ እንድወስባት እንደፈቀደች
ለመናዘዝ ስትዳክር ። ምን ማለት እንደፈለገች ስለሚገባኝ  እያብራራች ውስጤ ሲፈግግ ይታወቀኛል።

የዋህነቷን እየተነተንኩት ነው ። ይብላኝ ለቀጣዩ...፦



ስላሳዘነቺኝ መከርኳት ፣ ጥሩ ሰው ስለሆነች መብከንከኗ አሳዝኖኝ መከርኳት ፣

ይሄውልሽ ሃሴት

ሁኔታችን ላይ ከሚገባው በላይ እየተመሰጥሽ ነው !...አትመሰጪ ቀለል አድርጊው  don't take everything  seriously  አንቺ በጣም አሪፍ ልጅ ነሽ ትበዥቢኛለሽ አንጂ አታንሺብኝም.... ምናምን .... ገለመሌ.... እያልኩ ቢራ እየተጎነጨው  ተረጋግቼ  መከርኳት።

ዝም ብላ በትዝብት ስትሰማኝ ቆይታ ሳቀች፤  እየጠጣነው የነበረው ቢራ አስክሯት መስሎኝ ነበር

<< አየህ አሸናፊ ሰዉ ሲያወራ ደስ ይላል፤ ፈታ ብሎ  እየተመፃደቀ ነው  ፣ መልሱ አያስጨንቀውም፣ አይፈራም ፣ ከተሸነፈው ሰው የሚሰነዘረው   አፀፋ ማታ እቤቱ ገብቶ እንቅልፍ እንዳይነሳው አይጨነቅም ።

ስላሸነፍክ ነው የተመፃደከው ።እኔ ላይ የሆንከውን መንቀባረር እና መፈላሰፍ ሌላ ያፈቀርካት ጋር እንደማታንፀባርቀው አንተም እኔም እናውቃለን ።!

ጥሩ ሰው ማለት ለሆነ ሰው ብሎ ክፉ እንደሆነ አክት የሚያደርግ እንጂ በአሰብኩልሽ በኩል ቅዱስ ነኝ ፣ፈላስፋ ነኝ የሚል አይደለም ።

እንደ አንተ አይነት ወንዶች ሂዱ ስትባሉ እንደምትመጡ ተረድቻለሁ   በRevers psychology  ማኔጅ የምትደረግ ወንድ እንደሆንክ ይገባኛል ። ራሴን ስለማከብር በቁም ነገር መሃል  game አልወድም ።

አንተ ሳትደክም ያገኘኸው ላይ ውበት ያለ አይመስልህም ። የነገሮችን ትልቅነት በሚያለፋ ልክ ነው የምትመዝነው  ።!

እምባዬ የሚታገለኝ በገባኝ ጉዳይ እየተሸነፍኩ መሆኔ ሲገባኝ ነው !።

ሴት ልጅ ከወሲብ በኋላ የምትታቀፈው መታቀፍ፣ የምትሰማው እወድሻለሁ ትጣፍጫለሽ ትረካ፤ ወሲብ ስታደርግ ካለው ደስታ አያንስም ሊያውም ይበልጣል እንጂ ።

አንተ ማግኘት ላይ እንጂ ማቆየት ላይ Lazy ስለሆንክ ስሜትህን ካራገፍክ በኃላ  ሮጠህ ሻወር ቤት ሄደክ ብቻህን እየዘፈንክ  ትደሰታለህ ።

እስቲ ግዜ ወስደህ  የምትልክልኝ ቴክስቶችን እያቸው፤ የምታወራኝ ነገሮችን እየው.... ግራ ይገባል እኮ ....ግራ እያጋባኸኝ ግራ ሲገባኝ ልትመክረኝ ለምን ቃላት ትሞርዳለህ

..እ  ?

በጣም ካዘንክልኝ ለምን እርግፍ አድርገህ አተወኝም ...??!

አንጠልጥሎ ከመያዝ አክብሮ መተው እንደሚበልጥ አታውቅም ? !


የመጨረሻው ክፍል ይቀጥላል ግን React እና Like👍👍 ካረጋችሁ
💥📚ኢትዮ-ልቦለድ📚📖💥
Photo
ክፍል ሁለት ፦

ይሄውልሽ ሃሴት.... አንድም እንኳን
ካልሽው ስህተት አለው ማለት አልችልም ።

ነገር ግን ፦

በስሜት ውስጥ ሆነሽ እየታገልሽ ነው ። 
ምንም ብርቱ ቢሆን ስሜቱን ብቻ  የሚከተል ሰው የሚያሸንፍ አይመስለኝም ።

ራስ ወዳድ ስለሆንሽ ይመስለኛል ራስሽን ለጥቂት ቀን ማስደበር ከብዶሽ ዘለቄታዊ ደስታሽን ጠላት የሆንሽው

በርግጥ ፦

ድብርትሽን  ያበዛው 'ego' ሽ  ይመስለኛል። ራሴ ነኝ  ከምትይው እና በዙሪያሽ ናት ከሚሏት ጋ የምቶኚው ተጣርሶብሽ ነው  ኣ?

እንግዲህ ይመስለኛል ነው ፦

ሰው ራሱን ሲቀበል እና ሲወቅስ ነው ራሱን መግዛት እና ማሸነፍ የሚችለው ። የኔ ድክመት እና ማንነት ላይ ስፔሻላይዝ ያደረግሺውን ያህል ራስሽ ላይ ተመሰጪ  እስኪ ።

ሰው መጀመርያ ራሱን ሲያሸንፍ ነው በሌላው የማይሸነፈው.... በርግጥ ፍቅር የመሸናነፍ ጉዳይ አይደለም የሁኔታ እንጂ .....

በነገራችን ላይ ብሪሊያንት ነሽ ፣
ከጠበኩት በላይ ሁኔታዬን መረዳትሽ ደስ ይላል ነገር ግን  ማወቅ እና ያወቁትን መኖር ይለያያል።

ይልቁንስን ሃሱ   ፦

መሳቅ እየቀነሽ ነው  እንደውም እየተውሽ ነው ። አብረሺኝ ሆነሺም፣ ተለይተሽኝም ሁሉንም  እንቅስቃስዬን እያማሽው ነው

ጉድለትን ብቻ ማየት የሰነፍ ሰው በሃሪ ነው ።!

ትንሽ ፈታ እያልሽ ፦

ፈታ እያልኩ አለመታገሌ ፣ በወደኩ ቁጥር በእልህ ለመነሳት መጣሬ ደጋግሞ ጥሎኛል ደጋግሜ ልደምቅበት በተገባ ስፍራ አንሻለሁ።

ባይሆን  ፦

ሁሉም ነገር ቁምነገር አይደለም ሁሉም ነገር ጨዋታ አይደለም ።  አንድ ነገር ላይ ብቻ ሙጭጭ ማለት ድሉም እጦቱም ዋጋ ያስከፍላል።

እንከን በመተንተን ሰንፍናዬን በማጉላት ቅያሜ እንጂ ፍቅር አይገኝም ።በዚህ ውድድር አለም የሚያስወድደው  የሰዎችን ድክመት  እየነገርን አይደለም የሚወደድ ነገራቸውን እያሳየናቸው  ጭምር እንጂ

በነገራችን ላይ፦

ነገረኛ ሰዎች ውስጥ ያለው ሎጂክ ለክስ እንጂ ለደስታ የሚረዳቸው አይመስለኝም ። 

ሃሴት ....ቅንድቧን ከፍ አድርጋ አይኗን ፈጠጥ  አድርጋ እ ... ነገረኛ ነሽ እያልከኝ ነው ?

አላልኩም... ትልቅ ሰው ወሬን ሰፋ አድርጎ ሃሳብ አሳክሎ ማውራት አለበት የሚል ፈሊጥ ስላለኝ ጨዋታውን ማስፋፋቴ ነው  ........ ... ሃሳቡ ላይ እናተኩር ካልወከለሽ እሚወክለን ላይ እያተኮርን እንቃደድ ፦

ይልቁንስ ፦

ይገባኛል ህይወት ማለት ያላገኘነው እና ያጣነው ነው ። የሰው ልጅ ቀልቡ የበለጠ የሚገዛው በሁለት ሁነት ነው  ። 

ምድር ደም ካጣነው ነገር ውጪ መኖር የምንለማመድበት የምንፈልገውን የምናሳድድበት  ያለንን ለማቆየት የምንታገልበት ሜዳ ናት ።

በርግጥ ምድር  የምንፈልገውን ሁሉ መስጠት አትችልም ንፉግ ናት ...... !

የሆነው ሆኖ

ሂድ ስባል የምመጣ ባተሌ መሆኔን ማወቅሽ አስገርሞኛል ።
      


አይ እዮብ .... እንደ ወንድ ልጅ ጅል ፍጡር እንደሌለ ምስክር ትሆናለ አይደል ?

እንከኔ ያልከውን ሁሉ በምክር ስም ወርውረሃል ።

ሴት  እኮ አስራ አምስት አመት የሚበልጣት አዳም ሲሰጣት በአስራምስት  አመት ካልበለጣት 'Match' እንደማታደረገው ፈጣሪ ቀመሩን ሰርቶ ነው ።

ለወንድ ጡንቻ የጨመረለት እርቀታችን እሩቅ ስለሆነ ካሳ ነው

'anyways' እስካሁን  እየተሰናበትኩ እንደሆነ አልገባህም ።

የሄደን ሰው ሂጂ ማለት ጥላኝ ሄዳ አይደለም ልኬያት ነው ለማለት እንዲመችህ ነው ።

አያያዝህን አልወደድኩትም አልኩህ እኮ ፦
አታፈቅረኝም አልኩህ እኮ፦
ሁኔታህ ገብቶኛል አልኩህ እኮ ፦

አንተ ራስህ የስሜትህ ባሪያ ባትሆን የማትወዳትን ልጅ ተስገብግበህ አትወስባትም ነበር ። ሰው በወደቀበት ጉዳይ ላይ አዋቂ ሆኖ ሲመጣ ሳቄን መቆጣጠር ነው የሚያቅተኝ ።

ቅድም የደሰኳርከው ዲስኩር አብዛኛው ስላንተ ነው።
እኔን  አይወክለኝም !!

የሚያናድድ ነገር እያየሁ የምስቀው ስለምንድን ነው? ትክክል ማለት አንተ የምትፈልገው ሲደረግ ነው ? ?

ሰው አይደለሁም ወይ?
ስሜት የለኝም ወይ?

እያስከፋኝ ባለ ሰው ፊት ሳልደሰት ደስ ሳይለኝ የምስቀው ስለምንድ ነው?

ይልቁንስ ፦

Choose of paradox እያሰቃየህ ነው ።  ከእኔ ጋ የማትሆነው ስላልወደድከኝ አይደለም ሌሎች የሚፈልጉህ የመሰሉህ ሰዎች  ፍላጎትህ ላይ እንዳታተኩር አድርገውህ ነው ።

'improve your focus!'

አንበሳ ሲያድን አደኑ ስኬታማ የሚያደርገው ሊበላት ካሰባት ውጪ ሌላ ነገር ላይ ትኩረቱን ስለማያደርግ ነው ።  በልጅነት እንክብካቤ አላገኘህም መሰለኝ ተወዳጅ መሆንህን ለራስ ለማስመስከር እየባዘንክ ትመስለኛለህ ።

ከዛ ያሸነፍክ የመሰልካቸው ሰዎች ላይ እየመከርክ ትልቅ ነኝ ፣ አዋቂ ነኝ ዲስኩር ትደሰኩራለህ ። አስር ጊዜ ስለማሸነፍ እና ስለመሸነፍ ትተነትናለህ ።

የአሸናፊ 'Mentality' የሌለው ሰው ነው ሁሌ ስለመሸናነፍ የሚተነትነው  !!

ካንተ ጋ የነበርኩበት ጊዜን አልወደውም ።  ከትውስታዬ መሃደር ከትዝታዬ 'Deliberately ' እፍቅሃለሁ ።

ደስስ እያለኝ  ነው ስለይህ !! ሰነፍ ሰው ከሂወት ሲሄድ እጦት አይደለም ድል  ነው !!


ይሄ ሁሉ አንብባችሁማ👍👍 ተጭናችሁ እለፉ
ከአንድ ሳምንት በፊት ደውላ እንደደበራትና ከቻልኩ እንዳገኛት ጠይቃኝ ነበር!....እኔም በሰዓቱ “ውይ አንቺና ድብርት ግን ስትዋደዱ!... ወይ ለምን ተጋብታችሁ አብራችሁ አትኖሩም እ'? ብዬ ቀለድሁባት

...እሷም “ ሰርግ ደግሰን እወቁልን አላልንም እንጂ ከተጋባንማ ቆየን እኮ"አለችኝ...ያው ሁሌ ስለምንቀላለድ ንግግሯን ከ ቁም ነገር ሳልቆጥረው ሰሙኑን እንደማገኛት ነግሪያት ስልኩን ዘጋሁት!

ከሁለት ቀን በኋላ ደግማ ደወለችልኝ...ጫጫታ ቦታ ነበርኩ!...ስልኬ ሶስት ግዜ እንደ ጠራ አነሳሁትና “ቤቲዬ ጫጫታ ቦታ ላይ ነኝ ያለሁት አይሰማኝም መልሼ ልደውልልሽ!?...አልኳት!

"እዮብ በጣም ከፍቶኛል ምትችል ከሆነ አሁን ቤት ና በናትህ..አለችኝ

ያለሁበት ቦታ ጫጫታ ብዙም እያሰማኝ ስላልነበር “ቆይ ቤቲዬ ከ 5 ደቂቃ በኋላ ደውልልሻለሁ እሺ' ብዬ ስልኩን ዘጋሁት!....ቀኔ አድካሚ ስለነበር መደወሉን ረስቼ ቤቴ እንደገባሁ እራቴን እንኳ ሳልበላ ተኛሁ!...ጠዋት ተነስቼ ስልኬን ሳየው ቴክስት ገብቶልኛል... ቤቲ ነበር የላከችው!..ሰዓቱን አየሁት!... ትናንት ምሽት ሁለት ሰዓት

ነው የተላከው….. “ቻው እሺ እዮብዬ የማልደበርበት ቦታ ሄጃለሁ" ይላል!...ምን ለማለት ፈልጋ ነው? ግራ ገባኝ...ስልኳ ላይ ደወልኩ አይነሳም!...ደጋግሜ ሞከርኩ መልስ የለም!...ጫማዬን አደረኩና የቤቴን በር እንኳ ሳልቆልፍ በፍጥነት ወጣሁ!

የነ ቤቲ በር ላይ ስደርስ ድንኳን ተጥሏል! ልቤ ለሁለት ሲሰነጠቅ ተሰማኝ!...እግሬ እየተንቀጠቀጠ ወደ ውስጥ ገባሁ!...እናትየው የቤቲን ፎቶና የሆነ ወረቀት በእጃቸው ይዘው ግራና ቀኝ በሁለት ሰዎች ተይዘው እያቃሰቱ ቁጭ ብለዋል! ...ሰማይ ምድሩ ተደበላለቀብኝ!...የግዴን “ም… ምንድነው ማዘር'' ብየ ጠየኳቸው!...ምንም መልስ አልሰጡኝም!...ከ ጎን ያለችው ልጅ እምባ በተናነቀው ድምፅ! ልጃቸው አርፋለች አለችኝ!....''ማ ..ቤቲ?'' አልኳት...''አዎ'' አለችኝ!....''እራሷን ከ ማጥፋቷ በፊት ይሄን ወረቀት ፅፋ ነበር'' ብላ ከ እናትየው እጅ ላይ ወረቀቱን ወስዳ ሰጠችኝ!...እጄ እየተንቀጠቀጠ ተቀበልኳትና አየሁት ....''አይዞሽ የሚለኝ ሰው ብቻ ነበር የፈለኩት ....'' ይላል! ምንም አላልኩም.... ወረቀቱን እንደያዝኩ እግሬን እየጎተትኩ ከድንኳኑ ወጣሁ!...በእርግጥ ወዴት እንደምሄድ አላውቅም!

! ይሄ ፅሁፍ የሚያስተምረን በሂወታችን ችላ የምንለው ነገር እስከ ሂወት ማጣት ድረስ ዋጋ እንደሚያስከፍለን ነው


::አንበበው ከወደደት👍👍 ተጭናችሁ እለፉ
2024/09/22 05:36:43
Back to Top
HTML Embed Code: