Telegram Web Link
📍በሱፊዎች ዘንድ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ..

♦️በስቃይ የተሞላ ህይወትን የሚመራ አንድ ሰው ነበር... ሰውዬው ወደ አምላኩ በሚጸልይበት ጊዜ ሁሉ "ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ እየኖረ ለምንድነው እኔ ብቻ የምሰቃየው?" እያለ ይጠይቅ ነበር፡፡

አንድ ቀን ጥልቅ በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለአምላኩ እንዲህ ሲል ጠየቀ... "አምላኬ የማንኛውንም ሰው ስቃይ ብትስጠኝ ልቀበል ዝግጁ ነኝ... እባክህ የእኔን ግን ውሰድልኝ... ከዚህ በላይ ልሸከመው አልችልም" ብሎ ተማረረ፡፡

ጸሎቱን ጨርሶ እንደተኛ ታዲያ ውብ የሆነ ህልም አየ... በህልሙ ውስጥ አምላክ ሰማይ ላይ ተከስቶ እንዲህ ሲል ይደመጣል... "ስቃያችሁን ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አምጡ..."

እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ስቃይ ያታከተው ስለነበር "የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፤ የእኔን ግን ውሰድልኝ፤ ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም" ብሎ ይጸልይ ነበር...

🔺በዚህም ምክንያት ሁሉም ሰው ስቃዩን በቦርሳ አጭቆ ወደ ቤተ መቅደሱ አመራ... ባለታሪኩን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጸሎቱ በአምላኩ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘለት በስፍራው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ነግሶ ነበር...

💡ከቤተ መቅደስ ሲደርሱ አምላክ እንዲህ ሲል እወጀ... "ቦርሳችሁን ከግድግዳው ስር አስቀምጡት"... ሁሉም ሰው ቦርሳውን አስቀምጦ ጨረሰ... አምላክም እንዲህ ሲል በድጋሚ አወጀ... "አሁን መምረጥ ትችላላችሁ፤ ማንኛውም ሰው የፈለገውን ቦርሳ መውሰድ ይችላል"...

🔺በዚህ ጊዜ ቀን ከሌሊት 'የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ' እያለ ሲጸልይ የነበረው ሰውዬ ሌላ ሰው የእርሱን ቦርሳ እንዳያነሳበት እየተጣደፈ ወደ ራሱ ቦርሳ ሄደ... ሁሉም ሰው እንደ ሰውዬው ሁሉ የየራሱን ስቃይ ያጨቀበትን ቦርሳ ፍለጋ ተራወጠ... በሚያስገርም ሁኔታ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ስቃይ በድጋሚ ለመሸከም ዝግጁ ነበር...

ምንድን ነበር የተከሰተው?...

💡በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳቸው የሌላኛቸውን ችግር ስቃይና መከራ ተመለከቱ... እንዲያውም ከራሳቸው የሚበላልጡ፣ የሌሎች ሰዎች ስቃይ የታጨቀባቸው ትላልቅ ቦርሳዎች እንዳሉም ተገነዘቡ... በዚህ ላይ ሁሉም ሰው ከራሱ ስቃይና መከራ ጋር ተላምዷል... የራሱን ስቃይ ማባበልና መቻል አይቸግረውም... የሌላውን ሰው የመከራ ቦርሳ ቢወስድ ግን ከቦርሳው ውስጥ ያለው አዲስ አይነት መከራ ምን አይነት እንደሆነ አያውቅም... ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል...

አላሚው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ በድጋሚ ጸለየ... "አምላኬ ስላሳየኸኝ ህልም አመሰግንሃለሁ...ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ደግሜ አልጠይቅህም... የሰጠኸኝን ነገር ሁሉ የሰጠኸኝ በምክንያት ነው" ሲል ተናገረ...

📍የቅናት ስሜት ካለባችሁ በማያቋርጥ ስቃይ ውስጥ ትወድቃላችሁ፤ የምትቀኑ ከሆነ ሀሰተኛ ትሆናላችሁ፤ ማስመሰልም ትጀምራላችሁ፤ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየትም ትሞክራላችሁ... የሆነ ሰው ጋር ኖሮ እናንተ ጋ የጎደለ ነገር ያለ ሲመስላችሁና ነገርዬውን ማግኘት የማትችሉ ከሆነ ከሰው ላለማነስ ብላችሁ የረከሱ ነገሮችን ማበጀት ትጀምራላችሁ...

💡ለቀናተኛ ሰው ህይወት ሲኦል ትሆንበታለች... ስለሆነም ቅናታችሁ ይጠፋ ዘንድ ራሳችሁን ከሌላው ጋር ማነጻጸር አቁሙ... ይህን ስታደርጉ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየት የምታደርጉትን ጥረትና ሌላውን ለመምሰል የምታደርጉትን ሙከራ ታቆማላችሁ...

🔑ይህ ሁሉ ሂደት የሰመረ የሚሆነው ግን ውስጣዊውን ሀብታችሁን ማሳደግ ስትችሉ ነው... ለማደግ ጣሩ... ይበልጥ እውነተኛ ግለሰብ ለመሆን ሞክሩ... እራሳችሁን አፍቅሩ... ለራሳችሁ ክብር ስጡ... ይህ ሲሆን የገነት በሮች ክፍት ይሆኑላችኋል... በእርግጥ ወደ በሮቹ ተመልክታችሁ ስለማታውቁ ነው እንጂ እስካሁንም በሮቹ ክፍት ነበሩ...

ደምስ ሰይፉ

ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@BridgeThoughts

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💎ወዳጄ ሆይ የሚገርም ነገር ልንገርህ ድልድይም ግርግዳም  ከድንጋይ ነው የሚሠራው። ግን ተግባራቸው ለየቅል ነው ድልድይ አንዱን ከሌላው ሲያገናኝ ግርግዳ ግን አንዱን ከሌላው ይለያል። ፍላጎትህ ሃሳብህ ተሰጥዎህ አልሳካ ቢልህ በፍላጎትህና ባንተ መካከል ያለውን ዶፍ  የሚያሳልፍህን ድልድይ ገንባ እንጂ ፍላጎትህን ግርግዳ ሠርተህ አትከልክለው አስተውል ያሰብከው ካልተሳካ የተስፋ መቁረጥ ግርግዳ ሳይሆን የጽናት ድልድይ ስራ። 

💡ጽናት- ድልድይ ነው፣ ተስፋ መቁረጥ - ግርግዳ ነው። ሁለቱም በቃላት ይገነባሉ። እናም ወዳጄ መማር ባለብህ ጊዜ ተማር፣ መሥራት ባለብህ ጊዜ ሥራ፣ መዝፈን ባለብህ ጊዜ ዝፈን፣ መዘመር ባለብህ ጊዜ ዘምር፣ መጻፍ ባለብህ ጊዜ ጻፍ። ያሰብከውን ነገር ለማድረግ ምቹ ጊዜ አትጠብቅ፣ ምቹው ጊዜ ሃሳቡ ወደ ጭንቅላትህ የመጣበት ጊዜ ነው።

💎ልብህ ያሰበውን ጥሩ ነገር ከመፈጸም አትቦዝን። ሃሳቡ በውስጥህ አርጅቶ እስኪሞት አትጠብቅ። ሰው በልቡ አላማውን ከጸነሰ በኋላ ወደ ቀኝ ወደ ኋላ ሳይወላውል፤ ወደ ግቡ የሚያደርሰውን ቀጥተኛ መንገድ ሊያሰምር ይገባዋል። የማስፈጸም ፍላጎት፤ የሚበቅለው “ይቻላል” ከሚል ስሜት ነው። ከአላማ ጋር የተሳሰረ አስተሳሰብ እጅግ ግዙፍ ሃይል ነው። አሁን ካለበት ሁኔታ ለተሻለ ኑሮ እና አስተሳሰብ እራሱን ያዘጋጀ ሰው፤ አይምሮውን በብልሃት የሚያሰራ ለስኬት የተዘጋጀ ነው።

💡ትላንት ነገ ያልነው ዛሬ፣ ቅድም ቡሃላ ያልነው አሁን ደረሰ፣ግን ማድረግ የፈለግነውን አላደረግን ይሆናል፣ሆኖም በዚህ ተስፋ አንቆርጥም፤ደግመን ምኞታችንን ለማግኘት ተስፋችንን ለመጨበጥ እናቅዳለን።የምንመኘውን ያን ምኞት፣ መሆን ያለብንን እስክንሆን አንቆምም፣ ተስፋም አንቆርጥም፡፡

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ

የጀመርኩትን አላቋርጥም ያለችው አትሌት መነጋገሪያ ሆናለች።

ሀገሯ ቡታንን በመወከል የሮጠችው ኪንዛንግ ላሃሞ የተባለች አትሌት በሴቶች የማራቶን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ካገኘችው አትሌት ሲፋን ሀሰን ከ1 ከሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ በመግባት ውድድሯን አጠናቃለች።

አትሌቷ ውድድሯን ስትጨርስ በቦታው የነበረው ታዳሚ እጅግ በጋለ ሞራል ተቀብሏታል።

የመጨረሻ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌቷ በፍጹም የጀመርኩትን ውድድር አላቋርጥም ብላ የውድድሩ የወርቅ አሸናፊ ከታወቀ ከ1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ ገብታለች።

80ኛ ደረጃ የወጣችው አትሌቷ ውድድሯን ለመጨረስ 3 ሰዓት ከ52 ደቂቃ / 4 ሰዓት ደገማ ወስዶበታል።

በዚህ ሁሉ ፥ የቴሌቪዥን ስርጭት  ያልተቋረጠ ሲሆን እያንዳንዷ እንቅስቃሴዋን ሲያሳይ ነበር ፤ በስፍራው የነበረው ተመልካችም የትም ሳይሄድ በክብርና በትልቅ ሞራል ተቀብሏታል።

የቡታኗ አትሌት የጀመረችውን ውድድር እስከመጨረሻ ድረስ ያለ ማቋረጥ ተፋልማ በመጨረሷ በበርካቶች " የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ " ተደርጋ ተወስዳለች።

ሁላችንም በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን የጀመርነውን መጨረስ፣ ለቆምንለት ዓላማ እስከመጨረሻው መሄድ እንዳለብን ያስተማረ ነው።

" እኔ አልችልም " ብለህ ተስፋ ቆርጠህ ከመቆም መራመድን ምረጥ ፣ ከውስጥ የመነጨ ጠንካራ መንፈስ ሲኖረን ምንም ያህል ችግር ምንም ያህል ስቃይ ከላያችን ቢረበረቡ ምንም ሳያሳስበን ምንም ተስፋ ሳያስቆርጠን ወደፊት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን። ሩጫችንንም መሰናክሉን እያለፍን እንሮጣለን። ከግባችንም እንደርሳለን። በተንቀሳቀስን ቁጥር ግባችን ጋር መድረሳችን የማይቀር ነው።

ውብ ሰንበት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💡 ትላንት አልፏል ስለዚህ ሞቷል። ነገ ደሞ ሚስጥር ነው ካልደረስንበት አናውቀውም።እንዲሁም ነገ ስጦታ ነው ካልተሰጠን አንደርስበትም። ዛሬ ግን በእጃችን ላይ ነው። ስለዚህ ስለ ትላንት በማሰብ ስለነገም በመጨነቅ ዛሬን አናበላሽዉ። ትልቅ ጥበብ ዛሬን መኖር ነው ከዛሬም ደሞ አሁን።

እናም ወዳጄ ያለን ዛሬ ላይ እናተኩር

💡 ሕይወት ትላንት ወይም ነገ አይደለችም። ሕይወት አሁን ናት። አሁንነት ሲያልፍ ትላንት ይሆናል የወደፊት አሁንነት ደግሞ ነገ ይሆናል። ሕይወት ተኖረ የሚባለው በአሁንነት ውስጥ ጤናማ በሆነ መልኩ ስንኖርበት ብቻ ነው። በአሁንነት ውስጥ ያልተኖረ ሕይወት የመከነ ሕይወት ነው።ዳሩ ግን ብዙዎቻችን በአሁንነት ውስጥ እየኖርን አለመሆኑ ነው። አእምሯችን በባለፈውና በወደፊቱ ጊዜ የተሞላ ነው። ከዚህም  የተነሳ አዘውትሮ ያስባል ይጨነቃል።

ዛሬ የትናንት ተማሪ ነው፡፡ ዛሬ ነገን ውብ ቀን ለማድረግ የሚሰራ በእጃችን ያለ መክሊታችን ነው፡፡ የትናንትን ኋላቀርነት የሚደግም የዛሬ ቀን ለዛሬም አይሆንም፣ ለነገም አይተርፍም፡፡ ያለፈውን ደካማ ነገር መሻር ሲገባ የምንደግም ከሆነ ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡ ትናንትን ወደነገ የሚያሻግረው ዛሬ ነው፡፡

⌛️ በትላንትናና በነገው አፍራሽ ስሜቶች ከመሞላትና ከመረበሽ በዛሬው ማንነት ውስጥ በትክክል መኖር ምርጫችን እናድርግ። ነገን የኖረ ማንም የለም። ነገን ስትደርስበት ህይወት እራሷ ትገለፅልሀለች። ሁሉም ነገር ጊዜ ተቀምሮለታል እኛ እድለኞች ነን ዛሬን ማየት ችለናልና።

         ያበራ ማንነት ለሁላችን
             ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
🔴እስቲ ዛሬ ስለ ሱፊዮች  እናውጋ  ቅዳሜ የምትደምቀው በእነሱ አስተምህሮቶች ነው።😉

.
. ተከተሉኝማ
.

🔷የሰረቀን ሁሉ እጅ በመቁረጥ፥ አይን ያጠፋን አይኑን በማጥፋት ልናተርፍ የምንችለው ብዙ እጀ-ቆማጣ እና ብዙ ዓይነ-ስውሮችን ነው!"- ይላሉ ሱፊዮቹ

ስለዚህም ይላሉ...

🔺"ማንም ይቅርታና ምህረትን ያላወቀ ሁሉ ፍቅርን አያውቅም፤ ፍቅርን ያላወቀ ደግሞ በፈጣሪው አልታቀፈም! ሕግጋቶቹ በሙሉ በፍቅር እንጂ በሌላ አልታቀፉምና!

🔹 ስለዚህም እኛ ተግባራትን በሙሉ የምንከውነው [ከገሀነም/ጀሃነም] ርቀን ወደ [ጀነት/ገነት] ለመግባት ሳይሆን ለሱ ካለን ፍቅር ነው! መፈ'ቀር ስለሚ'ገ'ባው ነው! የገነት ጉጉትም ሆነ የገሃነም ፍርሃት ከኛ ይራቅ!' እንደዛ ካልሆነ ግንኙነቱ የጥቅም ብቻ ይሆናል!" ይላሉ።

ይቀጥላሉም....

🔺አንዳንድ ሰዎች ጥቅሙን ብቻ ለማግኘት አስበው ፈጣሪን ያመልካሉ - ይህ የነጋዴዎች አምልኮ ነው!  አንዳንዶች ደግሞ ቅጣቱን በመፍራት {ከጀሃነም/ገሀነም} ርቆ {ገነት/ ጀነት} ለመግባት ሲሉ እርሱን ያመልኩታል - ይህ የፍርሀት አምልኮ ነው!

🔹አንዳንዶቹ ግን እርሱን የሚያመሰግኑት መመስገን ስለሚገባው አልፎም የእርሱን  ፍቅር እና ይቅር ባይነት በመረዳት ከልብ አመስጋኝነታቸውን ለመግለፅ ባህሪውን በተግባር ይኖሩታል - ይህ የነፃዎች አምልኮ ነው!

After all, if our actions are driven only by reward or punishment – if our seeking is for eternal life or otherwise – then we are motivated by greed and selfishness, not by faith or love.
— James Islington

ምስጋናን ጠብቀህ መልካም ሥራን የምትሠራ ከሆነ ወይም ቅጣትን ፈርተህ የምትሰጥ ከሆነ፣ ይህ ፍቅር ሳይሆን ራስ ወዳድነት ነው፡፡

📍ሰው በፍቅር ለመታቀፉስ ማሳያው ምንድን ነው?-
ሱፊዮችን እንጠይቃለን!
እነርሱም ይመልሳሉ!..

🔺ፍቅር ያለበት ሰው ዋና ባህሪው ይቅር ማለትን [ምህረት ማድረግን]ማወቁ ነው!
...ለሰው ይቅርታን ሳያደርግ ከሰማይ ይቅርታን እንደሚጠብቅ ሰው ከንቱ የለም!። ፍቅር-የፈጣሪ ዋና ባህሪና ስሙም ነው፥ እርሱም አፍቃሪዎችን እንጂ አስመሳዮችን አይወድም፥ ፍቅር የሌለው አምልኮም ጩኸት ብቻ ነው! ልብህ ከፈጣሪ ካልተገናኘ የቱንም ያህል ቃላት በፊቱ ብትደረድር ከንቱ ድካም ነው ። እንዲህ አይነቱ ሰውም ከቤቱ ውስጥ ቆሞ በሩን የሚያንኳኳ ሰውን ይመስላል ይላሉ...

📍እስቲ ይቅርታን በደንብ ግለፁልን?- ያለመታከት ሱፊዎችን እንጠይቃለን

🔹"ይቅርታ[ምህረት ማድረግ] ማለት ልክ እንደ [ፅጌረዳ] አበባው እየቀጠፍከውም እንደሚሰጥህ ጥሩ ሽታ ማለት ነው!" እኛ ሰዎች ግን ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ ስለምንሻ ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ ደስታችንን ያጎድሉብናል። ሰዎች ይቅር ሳይሉን ይቅር ማለቱን አንችልበትም ፤ ብንችልበት እንኳን ገር ደካማ የሆንን ይመስለናል። ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ እንሻለን ፤ ለፍቅራችን፤ ለይቅርታችን ፤ ለክብራችን ምላሽ ካልተሰጠን ደስተኞች አይደለንም።

የሌላውን ምላሽ ሳንጠብቅ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ከቻልን ከራሳችን ላይ ትልቅ ቀንበር አነሳን ማለት ነው። ፈጣሪን እናስብ ያለ-ምላሽ ይቅር እንደሚባል ፤ ያለ-ምላሽ ቸር መሆን እንደሚቻል ማስረጃ ነው።

♦️በመጨረሻም ሱፊዎች እንዲህ ይሉናል

ዘር ሲበቅል ድምፅ የለውም ግን ዛፍ ሆኖ ሲወድቅ ትልቅ ድምፅ ያሰማል ብዙ ግዜ ውድቀትም ይህው ነው ጩህት አይጠፋውም ፍጥረት  ግን ምን ግዜም በዝምታ ውስጥ ነው። ይህ የዝምታ ሀይልና በዝምታ ማደግ ይባላል እናም ዝምታን የሚያሸንፍ ጬኸት ፍቅርን የሚያንበረክክ ብልጣ ብልጥነት የለም ።
ፍቅር ውብ ዝምታ ነው ፣ ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸው። ፈጣሪን የምንፈራውም ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታው ግርማ-ሞገሱ ውስጥ ለኛ በሚሰጠው የማያቋርጥ ፍቅር ሳይሆን አይቀርም።

ፏፏቴ የሆነች ቅዳሜን ተመኘን😊

የምንፓስተውን እያነበባቹ ሪአክት ማታረጉ ሰዎች ግን፦ ወይ አስሉ ወይ አስነጥሱ ብቻ የሆነ ነገር አድርጉ... ደህንነታቹ ሀሳብ ስለሆነብን...😉

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ህፃን ሄቨን ላይ የተደረገውን ድርጊት ለመናገር ሁሉ ያሸማቅቃል

ምን አይነት የጭካኔ ዘመን ውስጥ እንደደረስን የሚያሳይ ቆ ሻሻ የሆነ ግፍ😢ለቤተሰቦቿ ጥንካሬውን ያድላቸው ።

ይህው እናትም የልጄን ፍትህ አሰጡኝ እያለች የኢትዮጵያ ህዝብ እየለመነች ትገኛለች።

ለዚች እናትስ ምን ቃላት ያፅናናት ይሆን ?😪

ለህፃን ሄቨን ፍትህ ይገኝ ዘንድ ጫና ለመፍጠር እየተሰበሰበ ያለውን petition እንቀላቀል፣ ሼርም እናድርግ።

https://chng.it/rrSzFxp7PW

ድምፅ ሁኑ 🙏

ብላቴናዋ ሚጣ

@Ethiohumanity
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍አብዛኛዎቻችን የነፍስ ደስታን ተነጥቀናል። ቀና ብለን አንሄድም። ምሬት መለያችን ሆኗል። ከአፋችን በረከት የለም፣ ምስጋና የለም። ወዳጄ ሆይ በመኖር ሂደት በሚገጥሙህ ፈተናዎች ሁሉ አታማር። የዛሬን ቀን ማግኘትህ ብቻ ትልቅ ስጦታ ነውና በጥልቅ ደስ ይበልህ፤ የፈጠረህን በእጅጉ አመስግን።

💡ፀሐይ ስለ መጥለቋ ከተማረርክ ፣ ከዋክብትም ይሰወሩብሃል” ይባላል። ቢወጡም አታያቸውም ማለት ነው። ምሬት ዓይንን ያጨልማልና።  "ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ ነገሮች አሉ። ስለተመረጥን በፈጣሪም ስለተወደድን ዛሬ ተሰቶናል፣ስለተደረገልን ነገር ሁሉ እናመስግን፤አሁን እየተደረገልን ስላለውም ነገር ሁሉ እናመስግን፤ ወደፊትም ስለሚደረግልን ነገር ሁሉ እናመስግን ምስጋና ህይወታችን ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ያበዛልናልና።

📍እኛ ካሰብነው ይልቅ ያሰበልን ፈጣሪ ይበልጣል። ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም። ለሆነልህ፣ ላለሆነልህ፣ ላለህ፣ ለሌለህ ዘወትር አመስግን ሁሌም ቢሆን ፈጣሪ ሁሉን በግዜው ውብ አድርጎ መስራት፣ ማከናወን ያውቅበታልና።

💡ፈጣሪህን አመስግን፣ ወላጆችህን አመስግን፣ ቤተሰብህን ባለቤትህን ልጆችህን አመስግን፣ እህቶችና ወንድሞችህን አመስግን፣ ጓደኞችህን፣ ጎረቤቶችህን፣ አለቆችህን፣ አመስግን። ሁሉም ላንተ ምንም ባይሰጡህ እንኳን አብረውህ እንዲሆኑ ስለተሰጠህ እድል አመስግን። ዛሬ በሕይወት ስላለህና ይህንንም መልዕክት በማንበብህ ዕድለኛ ነህ። ደስ ይበልህ!!
   
          ውብ አሁን !!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
💡ሁሉም ነገር ከራስ ይጀምራል። አንተ እና እኔ “ከእኔነታችን” ጀርባ “እኛነታችን” እንዳለ እንዘነጋዋለን። እያንዳንዳችን ከሃገር ደመራ ውስጥ የተሰገሰግን ችቦዎች ነን። አንዱ ሲጎድል ደመራው ቀጥ ብሎ ለመቆም ይቸግረዋል። ሃገርም እንደዛ ናት ብዬ አምናለው። “ሃገር” የሚለው ትልቅ ማንነት የሚፈጠረው “እኔ” በሚባሉ ጥቃቅን ማንነቶች ነው። እኛ ማንነታችንን መቅረፅ ሲሳነን ከእኛ አልፈን ቤተሰብን፤ ከቤተሰብ አልፈን፤ ማህበረሰብን፤ ከማህበረሰብ አልፈን ሃገርን እንጎዳለን።

🌍ሃገር የሚፈጠረው ከምንድን ነው? ከግለሰብ አይደለምን? ታዲያ ስለምን የግለሰብ አስተዋጽዎ እንደ ኢምንት ይቆጠራል? “እኔ ብቻ እንዲህ ባደርግ፤ ምን ዋጋ አለው?” የሚለው አስተሳሰብ የሚመጣው፤ “እኛን” ከ “እኔ” ስንነጥለው ነው። ተቀበልነውም አልተቀበልነውም ሁላችንም ሃገር ነን። የአንዳችን ቀጥ ብሎ አለመቆም የሃገርን ደመራ ያንገዳግደዋል።ሰዎች እራሳቸውን መለወጥ ሲችሉ፤ ያለምንም ድካም ቤተሰብ ይለወጣል፤ ማህበረሰብ ይለወጣል፤ ሃገር ትለወጣለች። ሃገር የብዙ “እኔዎች” ድምር ናት። ታዲያ ለምን ለውጣችን ከእኛ አይጀምርም?

📍በተተራመሰው አሰራር ውስጥ የእኔ አስተካክሎ መስራት ምን ለውጥ ያመጣል? የምንለው ብዙዎቻችን ነን። ግን አስቡት ሁላችንም እንደዛ ባንል እና ብንለወጥ፤ ትርምስምሱ አይሰተካከልም ትላላችሁ? እኔ በግሌ የሁሉም ነገር መሰረት ከገዛ እራሳችን ይጀምራል ብዬ አምናለው። ሃላፊነት የጎደለው ትውልድ፤ ታሪክ ለመስራት እንዴት ይችላል?

🌍ሁላችንም መልካም ቤተሰብ፤ መልካም ማህበረሰብ፤ ድንቅ ሃገር፤ እንዲኖረን እንመኛለን ብዬ አምናለው። ነገር ግን ሃገር የ”እኔ” ድምር መሆኑን ዘነጋንና፤ እራሳችንን ከለውጥ ሰልፈኛነት አወጣን። አስቡት፤ ሁሉም ሃላፊነቱን ወስዶ፤ እራሱን መለወጥ ቢችል፤ ስለ ትልቁ ለውጥ እንጨነቅ ነበር?

📍ሃገርን እንደ አንድ ንፁህ ባህር አስቧት፤ ሁሉም ያሻውን ቆሻሻ የሚደፋባት፤ ግን ያን ባህር ለማፅዳት ቢታሰብ መፍትሄው ምንድን ነው? ሁሉም የራሱን ሃላፊነት መውሰድ !!! “እኔ ቆሻሻ መድፋት ብተው፤ ሌላው ይደፋ የለ?” የሚል አስተሳሰብ ባይኖር፤ ሁሉም ባይሆን አብዛኛዎቹ ቆሻሻ መድፋታቸውን ያቆማሉ። መቼም ከብዙ ቆሻሻ ትንሽ ቆሻሻ ይሻላል።

እናም ሌላው ስለሚያደርገው ነገር ባንጨነቅ እና የራሳችንን ሃላፊነት ወስደን የገዛ እራሳችንን ብንለውጥ፤ ቢያንስ ካለብን ቆሻሻ፤ በእጅጉ የቀነሰ ቆሻሻ ነው የሚኖረን።

💎የኔ መልዕክት፤ እራስን ስለመለወጥ ነው፤ የእያንዳንዳችን መልካም ማሰብ፤ በጎ ማድረግ፤ ቀና መመልከት፤ ስራ መውደድ፤ ለውጡ ለገዛ እራሳችን ብቻ አይደለም። የሁሉም ነገር መሰረት “እኔ” ነው። “እኔ” ሲደመር ብዙ “እኔዎች” ናቸው ማህበረሰብን፤ ብሎም ሃገርን የሚፈጥሩት። ሰው ከሆንክ መኖርህን የምትለካው ለሌላው  በምትሰጠው  ስጦታ  ነው ሌላው  ደግሞ የሰው ልጅ ሁላና መላው ተፈጥሮ ነው - ስጦታህ ደግሞ ምንም ሳይሆን ፍቅር ብቻ ነው . ሁሉ  በየራሱ  ዱር  ውስጥ  እየኖረ ሀገሬ የስህተት ማዘያ አንቀልባ ስትሆን ሳያት አዝናለሁ። እኔ እንደወጣት ትልቅ ምኞት አለኝ። መልካም እራዕይ ያለው ትውልድ ለመፍጠር፤ ሁላችንም የገዛ እራሳችንን መፈተሽ አለብን።

🌍 “እኔ መልካም ባደርግ፤ ሌላው አያደርግም” ብለን የተሻለ ነገር ለማድረግ አንቆጠብ፤ እንደዛ ማለት ካቆምን ብዙ “እኔዎች” ይለወጣሉ፤ ብዙ “እኔዎች” ሲለወጡ፤ ማህበረሰብ ብሎም ሃገር ትለወጣለች። በመጨረሻ ሁላችንም ለማንኘውም ነገር ሃላፊነታችንን እንድንወጣ እለምናለው።

"ከህይወት ጽዋ እስካሁን እሬት ስንጠጣ ቆይተናል፤ አቅጣጫችንን መለወጥ ያለብን አሁን ነው፤ በራሳችን ላይ ከመዝመት የበለጠ ንቅናቄ (Revolution) የለም።"
- በዓሉ ግርማ

             ሚስጥረ አደራው

         ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
የበሰበሰው ጥርስ
(ካህሊል ጂብራን)

🔷በአፌ ውስጥ በስብሶ የሚያስቸግረኝ አንድ ጥርስ አለኝ በቀን ሰላማዊ ሆኖ ይውላል። ምሽቱ ሲገፋ፣ የጥርስ ሃኪሞቹ እንቅልፍ ሲጥላቸው እና መድሃኒት ቤቶቹ ሲዘጉ ግን ይጠዘጥዘኝ ይጀምራል።

አንድ እለት ትዕግስቴ ተሟጠጠና ወደ አንድ የጥርስ ሃኪም ሄጄ ያንን ስቃይ ያበዛብኝንና የምሽቴን ፀጥታ ወደ ማቃሰት እና ማጓራት በመለወጥ እንቅልፍ የነሳኝን ጥርስ እንዲነቅልልኝ ነገርኩት።

🔶 የጥርስ ሃኪሙ ራሱን ከግራ ቀኝ እየወዘወዘ "ጥርሱን ማዳን ስንችል መንቀሉ ቂልነት ነው" አለኝ። ከዚያም ጎንና ጎኖቹን በስቶ ቀዳዳዎቹን በማፅዳት ወደ ቀድሞ ሁኔታው ሊመልሰው እና ከብስባሴው ሐራ ሊያወጣው ያለውን መንገድ ሁሉ ተጠቀመ። መብሳቱን ከጨረሰ በኋላ በንፁህ ወርቅ ሞላውና "የበሰበሰው ጥርስህ አሁን ከጤነኞቹ የበለጠ ጠንካራና ብርቱ ነው" አለኝ በኩራት። አመንኩት። ከፈልኩትና ስፍራውን ለቅቄ ሄድኩ።

🔷ነገር ግን ገና ሳምንቱ ሳይገባደድ የተቀሰፈው ጥርስ ወደ ህመሙ ተመለሰና የነፍሴን ጥዑም ዜማ ወደ ለቅሶና ስቃይ ለወጠብኝ። እናም ወደ ሌላ የጥርስ ሃኪም አመራሁና "ምንም ጥያቄ ሳይጠይቀኝ ይህንን ጥርስ አውጥተህ ጣልልኝ። የደረሰበትና ያልደረሰበት ግልግልን እኩል አያውቃትም!" አልኩት።

ትዕዛዜን በማክበር ጥርሴን ነቀለልኝ። ከዚያም ጥርሴን እያየ "ይህ ጥርስ እንዲነቀል በማድረግህ መልካም አድርገሃል" አለ።

🔴 በአፍ ማህበረሰብ ውስጥ እስከ መንጋጋ አጥንት ድረስ የበሰበሱ ብዙ ጥርሶች አሉ። ይሁንና ማህበረሰቡ እነዚህን የተበላሹ ጥርሶች ለማስነቀልና ከስቃዩ ለመገላገል ምንም ጥረት አያደርግም። ራሱንም በወርቅ ፍቅፋቂ ይሞላል። አብዛኞቹ የበሰበሱትን የማህበረሰብ ጥርሶች በሚያብለጨልጭ ወርቅ እንደሚያክሙ የጥርስ ሃኪሞች ናቸው ።

እንደዚህ ተጠጋግነው በመደለል የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ስቃይ ህመምና ሞት ዕጣ-ፈንታቸው ናቸው።

🔶ሃገር አፍ ውስጥ ብዙ የበሰበሱ፣ ያመረቀዙ ጥርሶች አሉ። ሃኪሞቹ ከመንቀል ይልቅ በወርቅ ፍቅፋቂ አክመዋቸዋል። ህመሙ ግን እንዳለ ነው።

የበሰበሰ ጥርስ ያለው ሃገር የታመመ ጨጓራ እንደሚኖረው እርግጥ ነው። በዚህ ያለመፈጨት ችግር ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሃገራት አሉ።

🔷ሃገር ዳቦውን በበሰበሰ ጥርሱ እንደሚያኝክ እና እያንዳንዱም ጉርሻ ከተመረዘ ምራቅ ጋር በመዋሃድ በሽታውን በሃገሩ ጨጓራ ውስጥ እንደሚያሰራጭ ስትነግሯቸው "አዎ ግን የተሻሉ የጥርስ ሙሌቶች እና ማደንዘዣዎች እየፈለግን ነው" ይሏችኋል።

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💡አንዳንዴ በመታነጽ ላይ ሳለህ የቦዘንክ ቢመስላቸው አትደነቅ። ስኬት ቀድሞ በመራ አይደለም። ከእውቀት ሥራን ባስቀደመም አይደለም። ሥራ በዕውቀት ካልሆነ ልፋት ነው።

አንተ ብቻ ለዕውቀት ትጋ ፣ ጊዜው ደርሶ ሥራ ስትሠራ ደግሞ "ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው" በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው ። ትጋት ጥሩ ነው ። ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፣በችኮላ መሥራትና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው ።

📍አየህ አንተ ስትታነጽ፣ ስትተጋ ማንም ልብ አይልህም። ያንተ ራስን ማነጽ አርቀው ለማያስቡት ቦዘኔነት ነው። ሲያዩህ መሬት አትቆፍርም፣ እንጨት አትልግም፣ ምስማር አትመታም፣ ልብስ አትሰፋም፣ ዳቦ አትጋግርም፣ መርፌ አትወጋም። ለእነርሱ አንተ እየቦዘንክ ነው።

💎መጨረሻ ተሳክቶልህ፣ በኑሮ ከፍ ብለህ ሲያዩህ ግን "እድለኛ ነህ" ይሉሃል። እውነት ነው እድል ማለት ስትተጋ ሳትታይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻል ነው። ስንዴዋ አፈር ውስጥ ገብታ ስትበሰብስ ውጤቱን ለሚያውቀው ለገበሬው እንጂ ለሌላው ብክነት ነው። ሌሎች ውጤቱን የሚያዩት ስንዴዋ ስታፈራ ነው። ዘሩን የሚያናንቁ በፍሬው ቢደነቁ አትገረም።

አንተ ግን ለሌሎች ታይታ ሳይሆን በገባህ መንገድ አቅጣጫህን መርጠህ ትጋ! አንድ ቀን ውጤቱን ሲያዩ "እድለኛ ነህ" ይሉሃል።

💡እናም ወዳጄ

ምስጋና የደስታ ውጤትና ምንጭ ናትና። ባለህ ተደሰት! የምትፈልገውን ለማግኘት በትዕግስት ትጋ! አትዋከብ! አትቸኩል።

ምስጋናህ ግን በኑሮህ ላይ ባለህ ደስታ ይገለጽ። ኑሮህ፣ ህይወትህ፣ ስብከትህ ደስታህን ይመስክር።

             ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔊በዶ/ር ምህረት ደበበ

ምርጫችሁ ስለሆንን
ስናመሰግን ከልብ ነው !!!

ውብ ሰንበት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
🌗በምድር ላይ ዘላለም እንዲኖር የተፈረደበት አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህን ፍርጃ ሲሰማ ሳቀ... ዘላለም መኖርስ እንዴት ቅጣት ይሆናል? አራት መቶ አመታት አለፉ ... አንድ ማለዳ ላይ ከአልጋው ሳይወርድ ማስብ ጀመረ... ዘመናትን በምድር ላይ ያሳለፈ... የአለማችን ምርጥ ሰዓሊ፣ ምርጥ ሙዚቀኛ ሆኗል፡፡ ብዙ ጀግኖች በጦር ሜዳ ገድሏል... የሚወዳቸው የቅርብ ወዳጆቹም እድሜያቸውን ጨርሰው ሄደዋል። ሁሉንም ምግብ ቀምሷል፤ ያልረገጠው የምድር ክፍል የለም። አሁን ላይ ግን ለምን ከአልጋው መውረድ እንዳለበት ግልጽ አልሆነለትም። ሁሉም ነገር ሰልችቶታል። ለእርሱ ምድር እስር ቤቱ ሆናለች፡፡ በስተመጨረሻም ቀናቶቹ ሁሉ ትርጉም አልባ ሆኑበት፡፡

📍የ”አምላክ” ትልቁ ጥበቡ ሞትን መፍጠሩ ይመስለኛል፡፡ እያንዳንዱ ሃይማኖት እግሩን ያቆመው በሞት ላይ ነው፡፡ ሞት ባይኖር የሰው ልጅ፣ በአምላክ አያምንም ነበር። ሃይማኖቶች እግር ይከዳቸዋል፡፡ …ዘር ካልሞተ/ካልበሰበሰ ፍሬ አይሆንም፡፡ በዚህች ሰከንድ በሰውነታችን ውስጥ ህዋሳት እየሞቱ እራሳቸውን ባያድሱ ህልው መሆን አንችልም፡፡ ሞት እንደብዙዎቻችን እምነት፣ የህይወት ማብቂያ አይደለም፡፡ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ  መሸጋገርያ ድልድይ  እንጂ ፣ የብዙዎቹ ሐይማኖቶች  መሠረቱ ይሄ ነው ። እኛ ዘመናችንን ሙሉ ከሞት ለማምለጥ ብንመኝም፣ ሞት እርግማን ሳይሆን በረከት ነው ። ያለ ሞት “መኖር” ትርጉም ያጣል፡፡

💡ዘላለም የሚኖረው ሰው እያንዳንዱ ቅፅበቶቹ ጣዕም አልባ ይሆናሉ።  በዘላለማዊነት ውስጥ የሰውነት ባህሪ ይታጣል።የምንኖረው በአንፃራዊ አለም ውስጥ ነው። ሞትና ሕይወትም ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ስለሆኑ ነው፡፡ ሞት ያለሕይወት፤ ህይወትም ያለሞት አልተፈጠረምና፡፡ ህይወትን ተቀብለህ ሞትን መተው አትችልም፡፡ ብዙዎች ከማያመልጡት ወጥመድ መሸሽ ይፈልጋሉ፡፡ ሞት የህይወትህ አካል ነው፡፡ ለሕያዋን ሁሉ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ አስር ዓመትም፣ መቶ ዓመትም፣ ሺ ዓመትም በሕይወት ብትኖር ከሞት ጋር ክርክር የለህም፣ የትም ብትሄድ አታመልጠውም፡፡ ይልቁንስ ህይወትንም ሞትንም ጠልቀህ ከተገነዘብክ አኗኗርህንና አኳኋንህን፤ መካከሉን በማስተዋል ሕይወትህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡

🔑ሞት እና ጊዜ የተባሉ መልህቆች በሕይወታችን ውስጥ ያስፈልጉናል። ህይወት በትክክለኛው መንገድ ከተኖረ ሞት አይፈራም። ህይወትን ከኖራችሁ ሞትን በፀጋ ትቀበላላችሁ ምክንያቱም እንደ እረፍት፣ እንደ እንቅልፍ ትመለከቱታላችሁ። ከህይወት ጫፍ መድረስ ከቻላችሁ ሞት ውብ እረፍት ፣ ብረከት ይሆናል። በተቃራኒው ካልኖራችሁ ግን በርግጠኝነት ሞት ጊዜያችሁን ፣ የህይወት እድሎቻችሁን ይነጥቃችኋል። ካልኖራችሁ ነገ የሚባል ነገር የለም ፍርሃት ይነግሳል። ፍርሃቱ የሚመጣው በሞት ሳቢያ ሳይሆን በደንብ ህይወትን ካለመኖር ነው።"

               ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
💎በተሰጠን እድሜ በሀቅ መንገድ መሮጥ ነዉ

አንድ ቀን ስለ ዉልደትና ሞት ፍልስፍና ሲወራ በዋለበት የአንድ ወዳጃችን ጠባብ ክፍል ዉስጥ ከድር ሰተቴ የተወራውን ሁሉ ሲታዘብ ቆይና እንዲህ ብሎን ጥሎን ወጥቶ ሄደ ።

"ቢተኮስ ቢፎከር እኛ ምን አስፈራን
ሰተት ብለን ገብተን...
ሰተት ብለን ወጣን"

ሰተት ብለን በዉልደት በር እንደገባን ፣ በሞት በር ደግሞ ሰተት ብለን ዉልቅ እንላለን ። ብልጭ ብላ ድርግም እንደምትል ብርሃን ነን።... መነሻዋም ሆነ መድረሻዋ በግልጽ የማይታወቅ ብርሃን ።

📍ይህን ጥያቄ መመለስ ሳይሆን፣ ሰዉ የመሆን ቁም ነገሩ በተሰጠን እድሜ በሀቅ መንገድ መሮጥ ነዉ። በመጠላለፍ  ብልጣ ብልጥነት ሳይሆን በመደጋገፍ ሰዋዊነት። የክፋት ጠቢባን ለራሳቸው በሚመች መልኩ ያበጁልንን ቦይ ትተን የነብሳችንን እንከተል። ፈጣሪ የሰው ልጅን በእድሜው ብራና ላይ የየራሱን መልካም ታሪክ ይከትብ ዘንድ በስጋና ነፍስ ፈጥሮታል፣ የልባችሁን ሀቅ በመከተል ለሚደርስባችሁ የትኛውም ግፍ ፈጣሪ ከእናንተ ጎን ለመቆሙ አትጠራጠሩ።
   
      📓መንገደኛዉ ባለቅኔ
          ከድር ሰተቴ

ውብ ምሽት❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
🌍ምክር ለወዳጅ

📍ወዳጄ ሆይ

ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነትህ እንደ ወንዝ ይሁን! ሳትመርጥ፣ ለለመነህ ሁሉ እጅህን ዘርጋ። ሁልጊዜ እንደ ወንዝ የሚፈስ መልካምነት፣ በጎነት ይኑርህ። መርዳት ዕድል ነውና ተጠቀምበት ፡፡... ሌላው የወንዝ ውበቱ ዝቅ ብሎ በዝምታ መፍሰሱ ነው። ዝቅ ብሎ ሌሎችን ከፍ እንደማድረግ ምን ውብ ነገር አለ? ይህንን አደረግኩኝ፤ እንዲህ ደግ ሰራው እያሉ መጮህ የደግነትን ክብር ይነካል፤ እንደ ወንዝ በዝምታ፤ ለሌሎች መልካም መሆን ነው እውነተኛው ደግነት ነው። ወደኛ የመጣች ደግነት ወደሌሎቹ ካልሔደች ደስታ አይኖረንም  የተቀበልነውን ደግነት እኛም ለሌሎች እናሳይ፡፡ ጥሩ ሥራን ለሕሊና ምግብነቱ እንጂ ለሰማይ ሽልማቱ ብቻ አትሥራው ። የመልካም ነገር ዋጋ ከፋይ ፈጣሪ መኖሩንም እመን ።

📍ወዳጄ ሆይ !

ባለሀብት ብዙ ያለው ሳይሆን ካለው ብዙ የሚሰጥ ነው።ከሚደልሉ አንደበቶች የሚመፀውቱ እጆች እጅግ ይልቃሉ ። ልግስና ማለት የኪሳችንን ቦርሳ መክፈት መቻላችን ብቻ ሳይሆን ልባችን መክፈት መቻላችን ነው። አንተም ለመልካም ስራ እጅህን ለግስ "ልግስና የነፍስ ምግብ ነውና'' ደስታ ለሚሰጥ አብዝቶ ይመለስለታል። ሌሎችን መረዳት የመጀመርያው ንቃት እና ዕውቀት ነው፣ መንፈስህንም ወደ ላይ ክፍ ከፍ ያደርገዋል። ታላቅ የሆነ ጥበብ እና ማስተዋልንም ይዞልህ ይመጣል ። ደስተኛ የመሆን ቀላሉ መንገድም መልካም ነገር ማድረግ ነው። ውብ ነገርን ተመርኩዘው የሰሩት ስራ ሁሌም ውብ ነውና።

📍ወዳጄ ሆይ !

አቅመ ደካማን ሰው ጥሪቱን ብትገፈው የምታጌጠው በተቀደደው ልብሱ ነው ፣ ድሀን ዘርፈው ባለጠጎች የሆኑም ሲያፍሩ የሚኖሩ ናቸው ። አንተም የግፍን እንጀራ እንዳትበላ ተጠንቀቅ!! ጭካኔ የሕሊና ሰላምህን ያቀነጭራል። ፈጣሪ መስረቅን በትእዛዙ ቢከለክልህም ፣ የዘረፍከውን እንዳትበላ ግን በፍርዱ ያግድሃል።ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። የምናተርፈው ነገር ቢኖር የሆነ ጊዜ ላይ የሚመጣ መጥፎ ስቃይን ነው። ያውም ለልጅ የሚተርፍ የበደል ክፍያን ነው፣.........የቆምን መስሎን የዘነጋን ሰው የዘራውን ያጭዳልና እናስተውል።

📍ወዳጄ ሆይ !

ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው ፣
ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ
አትሁን ።መልካም ዘር ዘርተህ መልካም ምርት እፈስ፣ፍቅር የዘራ ፍቅር ያገኝል። ጥላቻ የዘራም ጥላቻ ያመርታል። ቅሬታ የተከለ ቅሬታ ይለቅማል። መልካም ዘር የዘራ መልካም ፍሬ ያጭዳል።አለም የአስተሳሰብህ ግልባጭ ናት፣ መስታወትህም ናት።

📍ወዳጄ ሆይ !

ከሚንጫጫ ብዙ ፣ ዝም ያለውን አንድ ሰው ፍራ ። ከሚጮኸው ውሻ ፣ የማትጮኸው ግመል ብዙ በረሃ ታቋርጣለች ። ያነበበ ቢተኛ እንኳ ነቅቶ የተኛ ነው ። ሳታነብ ሰው ሁሉ ከሚወድህ አንብበህ ብቸኛ ብትሆን ይሻላል ። ዓለም በጫጫታና በመዋከብ ውስጥ ብቻ ትልቁ ደስታ ያለ ይመስላታል፣ ዝም ያለች ጥበብ ግን አጥብቆ ለሚሻት እጅጉን ቅርብ ናት። ብልህና ትጉ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ላይ ላሉበት ክፍተቶች በዙሪያው ከሚያስተውላቸው የቀን በቀን ክስተቶች እርማርትን ነቅሶ ይወስዳል፣ በሌሎች ላይ የሚመለከተውን ደካማና እኩይ አካሄድንም በራሱ ላይ እንዳይታይ በመጠንቀቅ እራሱን ወደተሻለ አቋም ያሸጋግራል!

📍ወዳጄ ሆይ !

ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!  መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሁሌም ከሰዎች ውስጥ መልካም ገጻቸውን ፈልገህ አንጥረህ ተመልከት፣ ጥሩነታቸውን በማድነቅ ገንባ፣ ከአፍህ መልካም ቃል ይውጣ፤ መልካም ዘር ዝራ። ልብ በል! ክፋት፣ ጥላቻ፣ ቂም፣ ቅሬታ አይጠቅሙህም። ይልቅስ ይጎዱሃል፣ በሽታ ያመጡብሃል፣ ወደታች ይስቡሃል።

🔑እናም ወዳጄ

ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።ሰዎች የዘሩትን ሲያጭዱ ስታይ አንተም ዛሬ እየዘራህ ነገ ደግሞ የምታጭድ መሆኑን አስብ። አለም ሁሉ ሲዋዥቅ፣ ሳትዋዥቅ የምትኖር እውነት ብቻ ናት ።

       መጪው ዘመን ሰላማዊ እንዲሆን
                ፈጣሪ ይዘዝልን❤️

ውብ አዲስ ዘመን😊

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ

🌼አዲስ ሀሳብ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣
ከትላንት ስህተቶች የምንማርበት፣
አዲስ አላማ ቀርፀን የምናሳካበት፣
ጥላቻና ልዩነትን አስወግደን በአንድነትና በፍቅር ወደ ተሻለ እድገት የምንሸጋገርበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን ! 

🌻ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ 2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ፤

❤️በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የፍቅር አመት እንዲሆን እንመኛለን።

መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችን
💛 ስብዕናችን 💛

@EthioHumanity
@EthioHumanity
2024/11/14 15:34:10
Back to Top
HTML Embed Code: