Telegram Web Link
🔴የሕይወት ግንድ ብዙ ቅርንጫፎች ነን!!

📍 አንድ ውቅያኖስ ላይ ነን  ‘የአንተ’ ታንኳ ሲናጥ ‘የእኔው’ ደንገል መንቀጥቀጥ ይጀምራል፣ ‘የእርሷ’ ጀልባ ሲቀዝፍ የባሕሩ ለመምቴ ይናጣል፣ የሰላምህ እርግብግቢት የሰላማችንን ንፋስ ይጠቅሳል… የሕመማችን ትንፋሽ የደስታ መንፈሷን ይበርዛል።ስለምን - ‘እኔም’፣ ‘አንተም’፣ ‘እርሷም’፣ ‘ሁላችንም' አንድ ነንና።

🔷መምህሩ ራማና ማሃርሺ …
“How are we Supposed to treat others?” ብለው ቢጠይቁት…
“There are no others” ሲል የመለሰው ለዚህ ነበር።

በተገበርከው ክፋት ብቻ ሳይሆን በተብሰልስሎትህ ሂደት ነገር ዓለማችን ይታወካል። በተነፈስከው በጎ ቃል አይደለም ባሰላሰልካት ደግነትም መውጣት መግባታችን ይዋባል… ብቻህን አይደለህምና የብቻ ሰላም የለህም… አልተነጣጠልንምና የብቻ ሕመምም አይኖርህም

የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን ፣ እኛም ሆንን በዙሪያችን ያለው የተፈጥሮ ስንክሳር የውቅያኖሱ አንድ ጠብታ ነው ፣ አንዲት ጠብታ የምትፈጥረው ለመምቴ /Ripple/ የሌላውን ለመምቴ ትነካለች… እኒህ የሃሳብ፣ የስሜትና የድርጊት ለመምቴዎች በሌላኛው ተፈጥሮ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አላቸው… በበጎም በክፉም… ተመልሰው ግን ወደ ምንጫቸው ይመጣሉ፣ በመዋኛ ገንዳ ውስጥ የፈጠርከው የውሃ ለመምቴ የገንዳውን ግድግዳ ገጭቶ ወዳንተ እንዲመለስ ማለት ነው።

🔶ከኔ ቤት ላይ የረጨኸው እሳት ከሆነ ነበልባሉ ያንተን ቤት ይነካል ፣ ሽቶ ስትረጨኝ የመዓዛው ቅንጣቶች ለአፍንጫህ ውብ ጠረን ይለግሳ፣ “You reap what you saw”ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል ፣ ይህን ምስራቃውያኑ Karma ሲሉት ሌሎች ደግሞ Boomerang ይሉታል… Boomerang አውስትራሊያኖቹ አቦርጂኒስቶች ከእንጨት የሚሰሩት ደጋን ቅርጽ ያለው የአደን መሳሪያ ሲሆን ወርዋሪው ዘንድ ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጎ የሚነደፍ ነው። ለሃሳብ፣ ለስሜትና ድርጊትህ መጠንቀቅ የሚኖርብህ ወላፈኑ ‘ለእኔም’፣ ‘ለእርሷም’፣ ‘ለእነርሱም’ እንደሚተርፍ በማሰብ ነው… ምክንያቱም
We are all One!

🔷ሰው ብቻ ሳይሆን ከዋክብቱ፣ ሕዋው፣ ምድሪቱ፣ እንስሳው… በሚታየውና በማይታየው ዓለም ያለው ነገር ሁሉ በአንዳች ተፈጥሯዊ ክር የተሳሰረ ነው… ማሰሪያው ስላልታየ መተሳሰሩ የለም አይባልም።

‘እዚያ ቤት ሲንኳኳ እኛ ቤት ይሰማል’ ‘ከወዲህ አንተን ሳማ እዚያ ከንፈር ትነክሳለህ’፣ ‘እከሊት ስታነሳኝ በስቅታዬ አውቀዋለሁ’፣ ‘የሰፈር ውሻ ሲያላዝን አንዱ አዛውንት ሊያልፉ ነው ማለት ነው’… ‘ውስጥህ ሲረባበሽ ራቅ ካለ ቤተሰብህ አልያም ወዳጅህ ቤት አንድ አደጋ አለ ማለት ነው’፣ 'ቅንድብህ ሲርገበገብ እንግዳ ሰው ልታይ ነው'፣ የጥንቶቹ ይሄ እውነት ስለገባቸው ይመስለኛል መሰል አባባሎች ያቆዩልን።

♦️በረከት በላይነህ "የመንፈስ ከፍታ" ላይ እንዲህ ይለናል👇

“የግልህ ወንዝ ስለሌለህ ብቻህን የምትሰራው ድልድይ የለም! የሰማዩ ርቀት፣ የምድሪቱ ስፋት በ’እኛ’ እንጂ በ’እኔ’ አይለካም፡፡ ውዱ ‘እኔ’ ከ’እኛ’ የተሰራው ነውና!”

🔷እዚህ ጋ ነው ስለ ዝምድናና ባዳነት ያለን ግንዛቤ መፈተሸ ያለበት፣ ስለ ዘርና ቀለም ያለን መረዳት መጤን ያለበት፣
Peter Russell “The Global brain” ብሎ ባሰናዳው ቪዲዮው ላይ አንድ በጨረቃ ላይ የተጓዘ የጠፈር ሳይንስ ተመራማሪ የተናገረውን ውብ ቃል ትሰማላችሁ
“When you are up there you are no longer an American citizen or a Russian citizen. Suddenly those boundaries disappear. You are a planetary citizen.”

🔑ኑረዲን ዒሳ በአንድ ግጥሙ.

“ባዳውን አፍቅሮ፣
ከባዳው ልጅ ፈጥሮ፣
እኔን ባዳዬ አለኝ - ሰባት ቤት ቆጥሮ፣
ልጁን ዘመዴ አለው - በፍቅር ታውሮ፡፡
ቅጠሉ ነኝና ለረጂሙ ሃረግ፣
እኔም ዘመዱ ሆንኩ - መቼስ ምን ይደረግ?” ብሏል…

❤️ፍቅር ሲገባን የልዩነት ቅዠት ይተናል ፣ ማንነት ሲገባን ሕብራችን ይታያል ፣ ጥበብ ሲያጥጠን ግን ልዩነት ያዜምልናል፣ ፍቅር ስንሰጥ በዙሪያችን ባሉት ላይ እርግብግቢቱ ፍቅርን ይወልዳል፣ክፉ ስናስብ ደግሞ በተቃራኒው ክፋት ይጠነሰሳል፣ከፊልዱ ውጭ እስካልሆንን ድረስ ከምላሹ ተጽዕኖ ልናመልጥ አንችልም።

                             ደምስ ሰይፉ
@bridgeThoughts
ውብ ቻናሉ ነው

         We are all One!
           ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍ደፋር መሆን ይኖርብናል ያልተሄደበትን መንገድ ለመሄድ መድፈር

ትእቢትን እልህን ጥላቻን ይሉኝታን ለመተው መድፈር

ራስን ለማዳመጥ መድፈር

💡አዎ ብዙ በደል ፈፅመሀል ተፈፅሞብሀል። ብዙ ሰው ጠልተሀል፣ ተጣልተሀል ፣  ተጠልትሀል ፣ ልብህ ተሰብሯል፣ ልቦችን ሰብርሀል ፣ግን ደግሞ ከዚህ ሁሉ ጋር ታርቀህና ራስህን አስታርቀህ ዳግም ለመውደድ ፣ ዳግም ለማዘን ፣ዳግም ለመርዳት፣ ዳግም እርዳታ ለመጠየቅና በቅንነትና በፍቅር ለመኖር ድፈር።

📍መጀመርያ ግን ከራስህ ጋር ለመታረቅ ድፈር። ራስህን ከነሙሉ ስህተቶቹ፣ ግድፈቶቹ ፣እንከኖቹ፣ውሸቶቹ፣ ቅጥፈቶቹ፣ አስመሳይነቶቹ ሁሉ ለመቀበል ለማዳመጥና ለመውደድ ድፈር

የፍቅር የይቅርታ ዘመን ነው ሲባል ወደሰማይ አታንጋጥ፣ ወደጎረቤቶችህና ጠላቶቸ ብለህ ወደፈረጅካቸው ሁሉ አታፍጥጥ

መጀመርያ ከራስህ ጋር ለመታረቅ ወደውስጥህ ተመልከት፣ ወደራስህ ተመለስ ፣ ውስጥህን ፣ልብህን ፣ ህሊናህን አፅዳ፣ሰው የሚሰጥህ ክብር አንተ ለራስህ በምትሰጠው ሚዛንና መጠን ነውና ለራስህ ትልቅ ዋጋና ብዙ ክብር ይኑርህ

💡ራስን መመልከት ራስን ወደ መሆን የሚያደርስ ወሳኝ መንገድ ነው። ራስህን ስትመለከት የወንድምህን ጉድፍ ሳይሆን የአንተን ተራራ ታስተውላለህ፥ በዚህ ውስጥ ደግሞ ተራራህን እየነቀልክ ራስን ወደ መሆን ታድጋለህ። ራስህን ስትሆን ብዙ ነገሮችን ታሸንፋለህ፥ መሰናክሎችን በቀላሉ አልፈህ፥ የነከሰህን የመከራ ጥርስ ውሃ የማድረግን ጥበብ ትጎናጸፋለህ።

🔑ብቻ ምን አደከመህ ራስህን ስትሆን ብዙ የደረብካቸው አላስፈላጊ ኮተቶችን ከራስህ ላይ አውርደህ፥ ንጹህ አንተነትህን ብቻ ያነገበ ማንነት ስትገነባ ያን ጊዜ ሰው መሆን ትጀምራለህ።እናም ራስህን ለመውደድ ድፈር።

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💡በየትኘውም የህይወት መንገድህ መልካም ስብዕናን አየዘራህ ስትጓዝ ባታይውም ለሌሎች ፍካት ሆኖ ይቆያል ።ደግነትህ ለብዙዎች የዕድሜ ማራዘሚያ ሰበብ ስለሆነ እንዳይከስም ጠብቀው። ለጋስ በመሆንህ በምላሹ ከሌሎች ምንም ነገር አትጠብቅ። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ መልካም ነገር ሁሌም ከፈጣሪህ በጎ ምላሽ አለው።

📍ህሊናህ ይረካ ዘንድ ከመቀበል ይልቅ ሰጪ ሁን። በምግባርህ ፈጣሪህን ለማስደሰት ሁሌም ጥረት አድርግ። እርሱ ከወደደህ ደስታ በእጅህ ትገባለች። በመልካም ስነ ምግባር ሽቶ የተርከፈከፈ ስብዕና ከመሬት በታች አፈር ለብሶ እንኳ መዓዛው ያውዳል።

💡አስተሳስብህ ካለባበስህ የበለጠ ሲያምር መልካምነትህ ከምትቀባው ሽቶ የበለጠ ሲያውድ ስነምግባርህ ከመልክህ የበለጠ ሲያምር የዝነጣ ጣሪያ ላይ ደርሰሀል ማለት ነው። ላመነን ሰው መታመን ከህሊና ወቀሳ መዳን ነው። ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፡፡ በህይወታችን የምናሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም።

  ውብ አዳር❤️

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthiohumanityBot
♦️ምክር ለወዳጅ

📍ወዳጄ ሆይ !

አዲስ ግኝት የመሰለህ እውቀት ከራስህ የመነጨ ሳይሆን ፈጣሪ ከሰጠህ አእምሮና አብርሆት የተገኘ ነው ። እውቀትን የጣለ እምነት ፣ እምነትን የጣለ እውቀት አይኑርህ ። እውቀት የሌለው እምነት ራስን ማደንቆር ነው ። የሚታወቅ ነገር ሳለ ፣ ማወቂያ መሣሪያው አእምሮ ከተሰጠህ የማወቅ ግዳጅ አለብህ ። ሰውን ሰው የሚያደርገው በእውቀት የተፈጠረና በእምነት የሚያድግ መሆኑ ነው ። እምነት የሌለው እውቀት ግን ማለስለሻ እንደሌለው ተሽከርካሪ እርስ በርሱ የሚፋጭ ፣ ድምፁ የሚረብሽ ፣ ዕድሜው የሚያጥር ነው ።

📍ወዳጄ ሆይ !

እኔ እንጂ እነርሱ ምን አለባቸው ? አትበል ። ብዙ ባለበት ዓለም ምንም የሌለበት ፍጡር የለም ። ሕፃናትም በረሀብ ፣ ልጆችም በበሽታ ይሰቃያሉ ። እንስሳትም በሰው የመጣውን ሐሣር ይካፈላሉ ። አንተ ስላለህ ሁሉ ያለው አይምሰልህ ። አንተ ስላጣህም ሁሉ ያጣ ሁኖ አይሰማህ  ፣ ብርታት ሌላውን ከማበርታት ይገኛል ። ሌላውን ስታበረታ አንተም በርትተህ ትገኛለህ ።

📍ወዳጄ ሆይ

ሰዎችን የምታሸንፋቸው በፍቅር ፣ የሚያሸንፉህ በክብር ነው ። እውነተኛ ፍቅር መስጠት ካልቻልህ በሽንገላ ራስህን ማድከም ፣ ትዝብት ላይ መውደቅ አያስፈልግህም። የጎላ ታይታ መውደድ ወደ ብዙ መሰወር ይለወጣል ። “እዩኝ ፣ እዩኝ ያለ ገላ ፣ ደብቁኝ ደብቁኝ ይላል” እንዲሉ ፣ ጓዳህን ለሁሉ አታሳይ፣ ምሥጢርህን በአደባባይ አትግለጥ። ክብር በትግል አይገኝም ፣ መፈራትም እውነተኛ ክብርን አያመጣም።

📍ወዳጄ ሆይ

ከፍታህን ከፍ ባለ ቃል ሳይሆን ከፍ ባለ ኑሮ ግለጠው። ሕያው መንፈስ አለህና በቁሳቁስ አትመካ፣ የሰው ንብረት አትቀማ! ሰውን ወልዶና ተዋልዶ ኑሮውን ከመሰረተበት መሬት አትንቀል፤ አታፈናቅል። እንጀራው ለሁሉ እንዲበቃ አድርገህ አስፋው! ለዚህ ፍቅር ያስፈልግሃል ፣ ይህ የሚቻለው ፍቅር ሲኖር ብቻ ነውና፣ ልብህ ለሰው ልጅ ሁሉ በፍቅር እንዲሞላ ይሁን።

📍ወዳጄ ሆይ

የሆነው መሆን ስላለበት ነው ። ፍርሃት የታዘዘን ነገር ከመምጣት አያድነውም ። በፈቃድህ ወደ እዚህች ዓለም ምንም ነገር አላመጣህምና ፣ እንዴት ይህ ይደርስብኛል? አትበል። የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚይሆን የተጠረበ ድንጋይ ሐውልት እንደሚይሆን ሁሉ ፣ እንተም በብዙ ችግሮች ውጣ ውረዶች ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን አትርሳ !

🔺ታዲያ ወዳጄ፦

ቅን ልብ የጨለማ ዘመን መብራት ነውና ቅንነት ይኑርህ ። ማስተዋል የሌለበትን ዓይናማነትን አትውደደው ። ሰውን በፍቅር እንጂ በኃይል አትሳበው ፣ የሚያደምጡህን አድምጣቸው ። ራስህ የሠራኸውን ራስህ እንዳታፈርሰው ሥራህን በችኩልነት አትፈጽም ፣ ትዕግሥት የጎደለው ቤት በተገነባ ቁጥር መፍረሱ ይፈጥናል ። የረዳሃቸው ሌሎችን ሲረዱ ለማየት ናፍቆት ይደርብህ፣ የሰው ሰውነቱ መታያው ልቡናው ዉስጥ በሰነቀው ቅንነት ነውና፣ በሽተኛን ከሚፈውስ ባለ ስጦታ ፣ የተከዘን ልብ የሚያጽናና ወዳጅ ይበልጣል።

               ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
🛑እያንዳንዳችን ፍቅርን የምንገልጽበት የራሳችን የሆነ መንገድ አለን። እናትና አባት ለልጆቻቸው፤ ወንድም ለእህቱ፤ እህት ለወንድሟ፤ ጓደኛ ለጓደኛ፤ ሚስት ለባሏ፤ ባል ለሚስቱ፤ ፍቅራቸውን በተለያየ መጠንና መንገድ ይገልጹታል። በፍቅር ስም ብዙ ስህተቶች ሲፈጸሙ ይስተዋላል። ፍቅር ስህተት ሆኖ ሳይሆን የሚገለጽበት መንገድ ልክ ስላልሆነ ብቻ። ምክንያቱም ፍቅር ምን ጊዜም በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ስህተት ሆኖ አያውቅም።

🔷ፍቅር ጉዳት የሚሆነው፤ ስህተት የሚመስለው የሰዎችን ልብ የሚሰብረው፤ ፍቅር ስህተት ሆኖ ሳይሆን ያስተላላፊው ስህተት ሲኖር ነው። ፍቅር ሳይበረዝ እና ሳይከለስ ለመተላለፍ ነጻነትን ይፈልጋል። ነጻነትን የተነፈገ ፍቅር ለተቀባዩ እዳ ይሆናል። ወላጆች ለልጆቻቸው ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ አለቅጥ ሲቆጣጠሩ በልጅ እና በወላጅ መካከል ያለው የግልጽነት ድልድይ ይሰበራል። ወላጅ ፍቅሩን “እኔ
አውቅልሃለው” በሚል አገላለጽ ሲገልጽ ልጆች በወላጅ ተጽዕኖ ነጻነታቸውን መስዋት ያደርጋሉ።

♦️ ይህ ማለት ወላጆች ልጆቻቸውን መቆጣጠር የለባቸውም ሳይሆን ፤ እስከምን ደረስ መሆነ እንዳለበት ልብ ሊባል ይገባል። ወላጆቻቸውን ፍራቻ ልጆች ብዙ ስህተቶችን ይፈጽማሉ ። ውድቀታቸውን እና የህይወት ፈተናዎቻቸውን ለወላጆቻው መግለጽ የሚከብዳቸው፤ ወላጆች ፍቅራቸውን የገለጹበት መንገድ ልክ ባለመሆኑ ነው። በተለይ በኛ ማህበረሰብ ግልጽነት የሚጎድለን ፤ ወላጆቻችን ፍቅር አንሷቸው ሳይሆን አገላለጻቸው ወደ ፍርሃት ስለሚወስደን ነው።

🔷በየትኛውም ቦታ እና ግንኙነት ፍቅር ህይወት ሊዘራ የሚችለው ነጻነት ስኖረው
ብቻ ነውና ፣ የምንወደውን ጽጌሬዳ ቆርጠን ቤት አናስቀምጠው ምክንያቱም ይሞታልና። ይልቁንም እውነተኛ ፍቅር ካለን ባለበት እንዲያብብ እንፈቅድለታለን። የምወዳቸውን ሰዎችም ማስተናገድ ያለብን እንዲህ ነው፤ እውነት የምንወዳቸው ከሆነ ነጻነታቸውን እንስጣቸው። በፍቅር ስም እነሱ የመረጡትን ሳይሆን እኛ የመረጥልናቸውን እንዲኖሩ አናስገድዳቸው።

📍በዚህም ምድር ላይ ለሰው ከነጻነት የበለጠ ስጦታ የለም። በነጻነት ውስጥ እምነት አለ በራሷ እንደትበር የተለቀቀች ወፍ ሌሎች በሷ እንደሚያምኑ ይሰማታል። በነጻነት ውስጥ ግልጽነት አለ፤ የሚሸፈን የሚከደን ምንም ነገር ስለሌለ። ፍቅር ደግሞ ያለእመነት እና ግልጽነት ዋጋ አይኖረውም። ለዚህ ነው ፍቅር እና ነጻነት ተለያይተው መሄድ የማይችሉት።

የምንወዳቸውን ሰዎች እናስብ ፍቅራችንን እንዴት እየገለጽንላቸው ነው? ነጻነታቸውን በሚጋፋ መልኩ ከሆነ እስቲ ትንሽ ቆም ብለን እናስብበት⁉️

           ውብ  አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
💎እንደ ወርቅ እንደ አልማዝ ሁኑ

ወርቅና አልማዝ ውድ ናቸው። የትም አይገኙም። ብዙ ተቆፍሮ፣ ተለፍቶ ነው የሚገኙት። የትም በቀላሉ የምትገኙ አትሁኑ። የራሳችሁን ዋጋ እንደ ወርቅ፣ እንደ አልማዝ ውድ የምታደርጉት ራሳችሁ ናችሁ። ለጠራችሁ ሁሉ አቤት፣ እንሂድ እንጂ ላላችሁ ሁሉ ወዴት አትበሉ።

💡Rarity [አለመገኘቱ] ብቻ ግን በቂ አይደለም። ወርቅና አልማዝ ጌጥ ናቸው። ያምራሉ። ወርቅ የቀይ ቢጫ ውብ መልክ አለው። አልማዝ በባህሪው colorless ከለር አልባ ነው። አልማዝ ብዙ አይነት ቀለም ይዞ የምናገኘው በውስጡ ካሉት impurities የተነሳ ነው። ግን መሰረታዊ ውበቱን አይቀንሱትም። የሰው ልጅ ውበት ንጽህና ነው። ንጹህ አካል፣ ንጹህ መንፈስ፣ ንጹህ አስተሳሰብ!!

📍አንድ ነገር በቀላሉ የማይገኝ ብቻ መሆኑ ተፈላጊ አያደርገውም። ዋናው ጉዳይ ባህሪያቶቹ ናቸው። የወርቅ በጣም ተፈላጊ ባህሪ ወርቅ አይዝግም። እንደ Iron ብረት ከሆንን ወደ ውስጣችን ሰርጎ የገባው ውሃ ሁሉ ያዝገናል። መንፈሳችንን ይረብሸዋል። ወርቅ ሁኑ። ወርቅ ሚሊየን አመት ውሃ ውስጥ ቢቀመጥ አይዝግም። በዚያ ላይ malleable ተዛዥ ተጣጣፊ ነው። እንደ ወርቅ ሊቀጥን የሚችል ሌላ ኬሚካል ኢለመንት የለም።

💡አልማዝ ደግሞ በጣም ጠንካራ ነው። ማንኛውንም ነገር በብቃት መቁረጥ ይችላል። በነገራችን ላይ አልማዝና ከሰል አንድ ናቸው ደግሞም አይደሉም። አንድነታቸው ሁለቱም የተሰሩት ካርበን ከሚባል ኢለመንት መሆኑ ሲሆን ልዩነታቸው እነዚህ የካርበን አተሞች በአልማዝና ከሰል ውስጥ ያላቸው ኬሚካል ስትራክቸር ነው። ከሰልን ወደ አልማዝ መለወጥ በብዙ ፓስካል ፕሬዠር [Pascal Pressure] ወይም ብዙ ግፊትና እና ብዙ ኬልቪን [Kelvin] ሙቀት ያስፈልጋዋል።

📍ውስጣችን ያለው ማንነት ካርበን ነው። ከሰል ወይም አልማዝ ማድረግ የኛ ፋንታ ነው። የህይወት ፈተና የከሰል ማንነታችንን ወደ አልማዝ የሚቀይር እርሾ ግፊት ነው። እነዚህ የወርቅና የአልማዝ ኬሚካላዊ ባህሪያት ብዙ ኢንደስትሪያል ጠቀሜታ አላቸው። ወደዚያ በዝርዝር አንገባም። አሁን የምንወስደው ከወርቅና ከአልማዝ ለህይወት የሚጠቅመንን ብቻ!

ቴውድሮስ ሸዋንግዛው

ውብ ሰንበት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
ትምክህት እና እብሪት
በሀይሉ ገ/መድህን
የጥበብ ምሽት

ማህበረሰብ አንቂው እና ወግ አዋቂው።

🔊አቶ በሀይሉ ገብረመድህን


ውብ ምሽት♥️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍በሱፊዎች ዘንድ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ..

♦️በስቃይ የተሞላ ህይወትን የሚመራ አንድ ሰው ነበር... ሰውዬው ወደ አምላኩ በሚጸልይበት ጊዜ ሁሉ "ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ እየኖረ ለምንድነው እኔ ብቻ የምሰቃየው?" እያለ ይጠይቅ ነበር፡፡

አንድ ቀን ጥልቅ በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለአምላኩ እንዲህ ሲል ጠየቀ... "አምላኬ የማንኛውንም ሰው ስቃይ ብትስጠኝ ልቀበል ዝግጁ ነኝ... እባክህ የእኔን ግን ውሰድልኝ... ከዚህ በላይ ልሸከመው አልችልም" ብሎ ተማረረ፡፡

ጸሎቱን ጨርሶ እንደተኛ ታዲያ ውብ የሆነ ህልም አየ... በህልሙ ውስጥ አምላክ ሰማይ ላይ ተከስቶ እንዲህ ሲል ይደመጣል... "ስቃያችሁን ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አምጡ..."

እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ስቃይ ያታከተው ስለነበር "የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፤ የእኔን ግን ውሰድልኝ፤ ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም" ብሎ ይጸልይ ነበር...

🔺በዚህም ምክንያት ሁሉም ሰው ስቃዩን በቦርሳ አጭቆ ወደ ቤተ መቅደሱ አመራ... ባለታሪኩን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጸሎቱ በአምላኩ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘለት በስፍራው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ነግሶ ነበር...

💡ከቤተ መቅደስ ሲደርሱ አምላክ እንዲህ ሲል እወጀ... "ቦርሳችሁን ከግድግዳው ስር አስቀምጡት"... ሁሉም ሰው ቦርሳውን አስቀምጦ ጨረሰ... አምላክም እንዲህ ሲል በድጋሚ አወጀ... "አሁን መምረጥ ትችላላችሁ፤ ማንኛውም ሰው የፈለገውን ቦርሳ መውሰድ ይችላል"...

🔺በዚህ ጊዜ ቀን ከሌሊት 'የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ' እያለ ሲጸልይ የነበረው ሰውዬ ሌላ ሰው የእርሱን ቦርሳ እንዳያነሳበት እየተጣደፈ ወደ ራሱ ቦርሳ ሄደ... ሁሉም ሰው እንደ ሰውዬው ሁሉ የየራሱን ስቃይ ያጨቀበትን ቦርሳ ፍለጋ ተራወጠ... በሚያስገርም ሁኔታ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ስቃይ በድጋሚ ለመሸከም ዝግጁ ነበር...

ምንድን ነበር የተከሰተው?...

💡በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳቸው የሌላኛቸውን ችግር ስቃይና መከራ ተመለከቱ... እንዲያውም ከራሳቸው የሚበላልጡ፣ የሌሎች ሰዎች ስቃይ የታጨቀባቸው ትላልቅ ቦርሳዎች እንዳሉም ተገነዘቡ... በዚህ ላይ ሁሉም ሰው ከራሱ ስቃይና መከራ ጋር ተላምዷል... የራሱን ስቃይ ማባበልና መቻል አይቸግረውም... የሌላውን ሰው የመከራ ቦርሳ ቢወስድ ግን ከቦርሳው ውስጥ ያለው አዲስ አይነት መከራ ምን አይነት እንደሆነ አያውቅም... ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል...

አላሚው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ በድጋሚ ጸለየ... "አምላኬ ስላሳየኸኝ ህልም አመሰግንሃለሁ...ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ደግሜ አልጠይቅህም... የሰጠኸኝን ነገር ሁሉ የሰጠኸኝ በምክንያት ነው" ሲል ተናገረ...

📍የቅናት ስሜት ካለባችሁ በማያቋርጥ ስቃይ ውስጥ ትወድቃላችሁ፤ የምትቀኑ ከሆነ ሀሰተኛ ትሆናላችሁ፤ ማስመሰልም ትጀምራላችሁ፤ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየትም ትሞክራላችሁ... የሆነ ሰው ጋር ኖሮ እናንተ ጋ የጎደለ ነገር ያለ ሲመስላችሁና ነገርዬውን ማግኘት የማትችሉ ከሆነ ከሰው ላለማነስ ብላችሁ የረከሱ ነገሮችን ማበጀት ትጀምራላችሁ...

💡ለቀናተኛ ሰው ህይወት ሲኦል ትሆንበታለች... ስለሆነም ቅናታችሁ ይጠፋ ዘንድ ራሳችሁን ከሌላው ጋር ማነጻጸር አቁሙ... ይህን ስታደርጉ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየት የምታደርጉትን ጥረትና ሌላውን ለመምሰል የምታደርጉትን ሙከራ ታቆማላችሁ...

🔑ይህ ሁሉ ሂደት የሰመረ የሚሆነው ግን ውስጣዊውን ሀብታችሁን ማሳደግ ስትችሉ ነው... ለማደግ ጣሩ... ይበልጥ እውነተኛ ግለሰብ ለመሆን ሞክሩ... እራሳችሁን አፍቅሩ... ለራሳችሁ ክብር ስጡ... ይህ ሲሆን የገነት በሮች ክፍት ይሆኑላችኋል... በእርግጥ ወደ በሮቹ ተመልክታችሁ ስለማታውቁ ነው እንጂ እስካሁንም በሮቹ ክፍት ነበሩ...

ደምስ ሰይፉ

ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@BridgeThoughts

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💎ወዳጄ ሆይ የሚገርም ነገር ልንገርህ ድልድይም ግርግዳም  ከድንጋይ ነው የሚሠራው። ግን ተግባራቸው ለየቅል ነው ድልድይ አንዱን ከሌላው ሲያገናኝ ግርግዳ ግን አንዱን ከሌላው ይለያል። ፍላጎትህ ሃሳብህ ተሰጥዎህ አልሳካ ቢልህ በፍላጎትህና ባንተ መካከል ያለውን ዶፍ  የሚያሳልፍህን ድልድይ ገንባ እንጂ ፍላጎትህን ግርግዳ ሠርተህ አትከልክለው አስተውል ያሰብከው ካልተሳካ የተስፋ መቁረጥ ግርግዳ ሳይሆን የጽናት ድልድይ ስራ። 

💡ጽናት- ድልድይ ነው፣ ተስፋ መቁረጥ - ግርግዳ ነው። ሁለቱም በቃላት ይገነባሉ። እናም ወዳጄ መማር ባለብህ ጊዜ ተማር፣ መሥራት ባለብህ ጊዜ ሥራ፣ መዝፈን ባለብህ ጊዜ ዝፈን፣ መዘመር ባለብህ ጊዜ ዘምር፣ መጻፍ ባለብህ ጊዜ ጻፍ። ያሰብከውን ነገር ለማድረግ ምቹ ጊዜ አትጠብቅ፣ ምቹው ጊዜ ሃሳቡ ወደ ጭንቅላትህ የመጣበት ጊዜ ነው።

💎ልብህ ያሰበውን ጥሩ ነገር ከመፈጸም አትቦዝን። ሃሳቡ በውስጥህ አርጅቶ እስኪሞት አትጠብቅ። ሰው በልቡ አላማውን ከጸነሰ በኋላ ወደ ቀኝ ወደ ኋላ ሳይወላውል፤ ወደ ግቡ የሚያደርሰውን ቀጥተኛ መንገድ ሊያሰምር ይገባዋል። የማስፈጸም ፍላጎት፤ የሚበቅለው “ይቻላል” ከሚል ስሜት ነው። ከአላማ ጋር የተሳሰረ አስተሳሰብ እጅግ ግዙፍ ሃይል ነው። አሁን ካለበት ሁኔታ ለተሻለ ኑሮ እና አስተሳሰብ እራሱን ያዘጋጀ ሰው፤ አይምሮውን በብልሃት የሚያሰራ ለስኬት የተዘጋጀ ነው።

💡ትላንት ነገ ያልነው ዛሬ፣ ቅድም ቡሃላ ያልነው አሁን ደረሰ፣ግን ማድረግ የፈለግነውን አላደረግን ይሆናል፣ሆኖም በዚህ ተስፋ አንቆርጥም፤ደግመን ምኞታችንን ለማግኘት ተስፋችንን ለመጨበጥ እናቅዳለን።የምንመኘውን ያን ምኞት፣ መሆን ያለብንን እስክንሆን አንቆምም፣ ተስፋም አንቆርጥም፡፡

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ

የጀመርኩትን አላቋርጥም ያለችው አትሌት መነጋገሪያ ሆናለች።

ሀገሯ ቡታንን በመወከል የሮጠችው ኪንዛንግ ላሃሞ የተባለች አትሌት በሴቶች የማራቶን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ካገኘችው አትሌት ሲፋን ሀሰን ከ1 ከሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ በመግባት ውድድሯን አጠናቃለች።

አትሌቷ ውድድሯን ስትጨርስ በቦታው የነበረው ታዳሚ እጅግ በጋለ ሞራል ተቀብሏታል።

የመጨረሻ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌቷ በፍጹም የጀመርኩትን ውድድር አላቋርጥም ብላ የውድድሩ የወርቅ አሸናፊ ከታወቀ ከ1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ ገብታለች።

80ኛ ደረጃ የወጣችው አትሌቷ ውድድሯን ለመጨረስ 3 ሰዓት ከ52 ደቂቃ / 4 ሰዓት ደገማ ወስዶበታል።

በዚህ ሁሉ ፥ የቴሌቪዥን ስርጭት  ያልተቋረጠ ሲሆን እያንዳንዷ እንቅስቃሴዋን ሲያሳይ ነበር ፤ በስፍራው የነበረው ተመልካችም የትም ሳይሄድ በክብርና በትልቅ ሞራል ተቀብሏታል።

የቡታኗ አትሌት የጀመረችውን ውድድር እስከመጨረሻ ድረስ ያለ ማቋረጥ ተፋልማ በመጨረሷ በበርካቶች " የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ " ተደርጋ ተወስዳለች።

ሁላችንም በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን የጀመርነውን መጨረስ፣ ለቆምንለት ዓላማ እስከመጨረሻው መሄድ እንዳለብን ያስተማረ ነው።

" እኔ አልችልም " ብለህ ተስፋ ቆርጠህ ከመቆም መራመድን ምረጥ ፣ ከውስጥ የመነጨ ጠንካራ መንፈስ ሲኖረን ምንም ያህል ችግር ምንም ያህል ስቃይ ከላያችን ቢረበረቡ ምንም ሳያሳስበን ምንም ተስፋ ሳያስቆርጠን ወደፊት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን። ሩጫችንንም መሰናክሉን እያለፍን እንሮጣለን። ከግባችንም እንደርሳለን። በተንቀሳቀስን ቁጥር ግባችን ጋር መድረሳችን የማይቀር ነው።

ውብ ሰንበት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💡 ትላንት አልፏል ስለዚህ ሞቷል። ነገ ደሞ ሚስጥር ነው ካልደረስንበት አናውቀውም።እንዲሁም ነገ ስጦታ ነው ካልተሰጠን አንደርስበትም። ዛሬ ግን በእጃችን ላይ ነው። ስለዚህ ስለ ትላንት በማሰብ ስለነገም በመጨነቅ ዛሬን አናበላሽዉ። ትልቅ ጥበብ ዛሬን መኖር ነው ከዛሬም ደሞ አሁን።

እናም ወዳጄ ያለን ዛሬ ላይ እናተኩር

💡 ሕይወት ትላንት ወይም ነገ አይደለችም። ሕይወት አሁን ናት። አሁንነት ሲያልፍ ትላንት ይሆናል የወደፊት አሁንነት ደግሞ ነገ ይሆናል። ሕይወት ተኖረ የሚባለው በአሁንነት ውስጥ ጤናማ በሆነ መልኩ ስንኖርበት ብቻ ነው። በአሁንነት ውስጥ ያልተኖረ ሕይወት የመከነ ሕይወት ነው።ዳሩ ግን ብዙዎቻችን በአሁንነት ውስጥ እየኖርን አለመሆኑ ነው። አእምሯችን በባለፈውና በወደፊቱ ጊዜ የተሞላ ነው። ከዚህም  የተነሳ አዘውትሮ ያስባል ይጨነቃል።

ዛሬ የትናንት ተማሪ ነው፡፡ ዛሬ ነገን ውብ ቀን ለማድረግ የሚሰራ በእጃችን ያለ መክሊታችን ነው፡፡ የትናንትን ኋላቀርነት የሚደግም የዛሬ ቀን ለዛሬም አይሆንም፣ ለነገም አይተርፍም፡፡ ያለፈውን ደካማ ነገር መሻር ሲገባ የምንደግም ከሆነ ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡ ትናንትን ወደነገ የሚያሻግረው ዛሬ ነው፡፡

⌛️ በትላንትናና በነገው አፍራሽ ስሜቶች ከመሞላትና ከመረበሽ በዛሬው ማንነት ውስጥ በትክክል መኖር ምርጫችን እናድርግ። ነገን የኖረ ማንም የለም። ነገን ስትደርስበት ህይወት እራሷ ትገለፅልሀለች። ሁሉም ነገር ጊዜ ተቀምሮለታል እኛ እድለኞች ነን ዛሬን ማየት ችለናልና።

         ያበራ ማንነት ለሁላችን
             ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
🔴እስቲ ዛሬ ስለ ሱፊዮች  እናውጋ  ቅዳሜ የምትደምቀው በእነሱ አስተምህሮቶች ነው።😉

.
. ተከተሉኝማ
.

🔷የሰረቀን ሁሉ እጅ በመቁረጥ፥ አይን ያጠፋን አይኑን በማጥፋት ልናተርፍ የምንችለው ብዙ እጀ-ቆማጣ እና ብዙ ዓይነ-ስውሮችን ነው!"- ይላሉ ሱፊዮቹ

ስለዚህም ይላሉ...

🔺"ማንም ይቅርታና ምህረትን ያላወቀ ሁሉ ፍቅርን አያውቅም፤ ፍቅርን ያላወቀ ደግሞ በፈጣሪው አልታቀፈም! ሕግጋቶቹ በሙሉ በፍቅር እንጂ በሌላ አልታቀፉምና!

🔹 ስለዚህም እኛ ተግባራትን በሙሉ የምንከውነው [ከገሀነም/ጀሃነም] ርቀን ወደ [ጀነት/ገነት] ለመግባት ሳይሆን ለሱ ካለን ፍቅር ነው! መፈ'ቀር ስለሚ'ገ'ባው ነው! የገነት ጉጉትም ሆነ የገሃነም ፍርሃት ከኛ ይራቅ!' እንደዛ ካልሆነ ግንኙነቱ የጥቅም ብቻ ይሆናል!" ይላሉ።

ይቀጥላሉም....

🔺አንዳንድ ሰዎች ጥቅሙን ብቻ ለማግኘት አስበው ፈጣሪን ያመልካሉ - ይህ የነጋዴዎች አምልኮ ነው!  አንዳንዶች ደግሞ ቅጣቱን በመፍራት {ከጀሃነም/ገሀነም} ርቆ {ገነት/ ጀነት} ለመግባት ሲሉ እርሱን ያመልኩታል - ይህ የፍርሀት አምልኮ ነው!

🔹አንዳንዶቹ ግን እርሱን የሚያመሰግኑት መመስገን ስለሚገባው አልፎም የእርሱን  ፍቅር እና ይቅር ባይነት በመረዳት ከልብ አመስጋኝነታቸውን ለመግለፅ ባህሪውን በተግባር ይኖሩታል - ይህ የነፃዎች አምልኮ ነው!

After all, if our actions are driven only by reward or punishment – if our seeking is for eternal life or otherwise – then we are motivated by greed and selfishness, not by faith or love.
— James Islington

ምስጋናን ጠብቀህ መልካም ሥራን የምትሠራ ከሆነ ወይም ቅጣትን ፈርተህ የምትሰጥ ከሆነ፣ ይህ ፍቅር ሳይሆን ራስ ወዳድነት ነው፡፡

📍ሰው በፍቅር ለመታቀፉስ ማሳያው ምንድን ነው?-
ሱፊዮችን እንጠይቃለን!
እነርሱም ይመልሳሉ!..

🔺ፍቅር ያለበት ሰው ዋና ባህሪው ይቅር ማለትን [ምህረት ማድረግን]ማወቁ ነው!
...ለሰው ይቅርታን ሳያደርግ ከሰማይ ይቅርታን እንደሚጠብቅ ሰው ከንቱ የለም!። ፍቅር-የፈጣሪ ዋና ባህሪና ስሙም ነው፥ እርሱም አፍቃሪዎችን እንጂ አስመሳዮችን አይወድም፥ ፍቅር የሌለው አምልኮም ጩኸት ብቻ ነው! ልብህ ከፈጣሪ ካልተገናኘ የቱንም ያህል ቃላት በፊቱ ብትደረድር ከንቱ ድካም ነው ። እንዲህ አይነቱ ሰውም ከቤቱ ውስጥ ቆሞ በሩን የሚያንኳኳ ሰውን ይመስላል ይላሉ...

📍እስቲ ይቅርታን በደንብ ግለፁልን?- ያለመታከት ሱፊዎችን እንጠይቃለን

🔹"ይቅርታ[ምህረት ማድረግ] ማለት ልክ እንደ [ፅጌረዳ] አበባው እየቀጠፍከውም እንደሚሰጥህ ጥሩ ሽታ ማለት ነው!" እኛ ሰዎች ግን ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ ስለምንሻ ነገሮች እንዳሰብናቸው ካልሆኑ ደስታችንን ያጎድሉብናል። ሰዎች ይቅር ሳይሉን ይቅር ማለቱን አንችልበትም ፤ ብንችልበት እንኳን ገር ደካማ የሆንን ይመስለናል። ለምናደርገው ነገር ሁሉ ምላሽ እንሻለን ፤ ለፍቅራችን፤ ለይቅርታችን ፤ ለክብራችን ምላሽ ካልተሰጠን ደስተኞች አይደለንም።

የሌላውን ምላሽ ሳንጠብቅ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ከቻልን ከራሳችን ላይ ትልቅ ቀንበር አነሳን ማለት ነው። ፈጣሪን እናስብ ያለ-ምላሽ ይቅር እንደሚባል ፤ ያለ-ምላሽ ቸር መሆን እንደሚቻል ማስረጃ ነው።

♦️በመጨረሻም ሱፊዎች እንዲህ ይሉናል

ዘር ሲበቅል ድምፅ የለውም ግን ዛፍ ሆኖ ሲወድቅ ትልቅ ድምፅ ያሰማል ብዙ ግዜ ውድቀትም ይህው ነው ጩህት አይጠፋውም ፍጥረት  ግን ምን ግዜም በዝምታ ውስጥ ነው። ይህ የዝምታ ሀይልና በዝምታ ማደግ ይባላል እናም ዝምታን የሚያሸንፍ ጬኸት ፍቅርን የሚያንበረክክ ብልጣ ብልጥነት የለም ።
ፍቅር ውብ ዝምታ ነው ፣ ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸው። ፈጣሪን የምንፈራውም ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታው ግርማ-ሞገሱ ውስጥ ለኛ በሚሰጠው የማያቋርጥ ፍቅር ሳይሆን አይቀርም።

ፏፏቴ የሆነች ቅዳሜን ተመኘን😊

የምንፓስተውን እያነበባቹ ሪአክት ማታረጉ ሰዎች ግን፦ ወይ አስሉ ወይ አስነጥሱ ብቻ የሆነ ነገር አድርጉ... ደህንነታቹ ሀሳብ ስለሆነብን...😉

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ህፃን ሄቨን ላይ የተደረገውን ድርጊት ለመናገር ሁሉ ያሸማቅቃል

ምን አይነት የጭካኔ ዘመን ውስጥ እንደደረስን የሚያሳይ ቆ ሻሻ የሆነ ግፍ😢ለቤተሰቦቿ ጥንካሬውን ያድላቸው ።

ይህው እናትም የልጄን ፍትህ አሰጡኝ እያለች የኢትዮጵያ ህዝብ እየለመነች ትገኛለች።

ለዚች እናትስ ምን ቃላት ያፅናናት ይሆን ?😪

ለህፃን ሄቨን ፍትህ ይገኝ ዘንድ ጫና ለመፍጠር እየተሰበሰበ ያለውን petition እንቀላቀል፣ ሼርም እናድርግ።

https://chng.it/rrSzFxp7PW

ድምፅ ሁኑ 🙏

ብላቴናዋ ሚጣ

@Ethiohumanity
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍አብዛኛዎቻችን የነፍስ ደስታን ተነጥቀናል። ቀና ብለን አንሄድም። ምሬት መለያችን ሆኗል። ከአፋችን በረከት የለም፣ ምስጋና የለም። ወዳጄ ሆይ በመኖር ሂደት በሚገጥሙህ ፈተናዎች ሁሉ አታማር። የዛሬን ቀን ማግኘትህ ብቻ ትልቅ ስጦታ ነውና በጥልቅ ደስ ይበልህ፤ የፈጠረህን በእጅጉ አመስግን።

💡ፀሐይ ስለ መጥለቋ ከተማረርክ ፣ ከዋክብትም ይሰወሩብሃል” ይባላል። ቢወጡም አታያቸውም ማለት ነው። ምሬት ዓይንን ያጨልማልና።  "ከምንማረርባቸው ነገሮች ይልቅ ልናመሰግንባቸው የሚገባን ብዙ ነገሮች አሉ። ስለተመረጥን በፈጣሪም ስለተወደድን ዛሬ ተሰቶናል፣ስለተደረገልን ነገር ሁሉ እናመስግን፤አሁን እየተደረገልን ስላለውም ነገር ሁሉ እናመስግን፤ ወደፊትም ስለሚደረግልን ነገር ሁሉ እናመስግን ምስጋና ህይወታችን ውስጥ ያለውን መልካም ነገር ያበዛልናልና።

📍እኛ ካሰብነው ይልቅ ያሰበልን ፈጣሪ ይበልጣል። ዋና ነገሬ ያለው እኔና ፈጣሪ ጋር ነው በማለት በእረፍት እንኑር፣ ሰማያዊ ጥበብ በጆሮ አይሰማም። እምነት በዓይን አይታይም። ለሆነልህ፣ ላለሆነልህ፣ ላለህ፣ ለሌለህ ዘወትር አመስግን ሁሌም ቢሆን ፈጣሪ ሁሉን በግዜው ውብ አድርጎ መስራት፣ ማከናወን ያውቅበታልና።

💡ፈጣሪህን አመስግን፣ ወላጆችህን አመስግን፣ ቤተሰብህን ባለቤትህን ልጆችህን አመስግን፣ እህቶችና ወንድሞችህን አመስግን፣ ጓደኞችህን፣ ጎረቤቶችህን፣ አለቆችህን፣ አመስግን። ሁሉም ላንተ ምንም ባይሰጡህ እንኳን አብረውህ እንዲሆኑ ስለተሰጠህ እድል አመስግን። ዛሬ በሕይወት ስላለህና ይህንንም መልዕክት በማንበብህ ዕድለኛ ነህ። ደስ ይበልህ!!
   
          ውብ አሁን !!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
2024/10/01 22:03:53
Back to Top
HTML Embed Code: