Telegram Web Link
📍የተሻለ አለህ

በአውሎ ንፋስ ውስጥ ብትሆን፣ ዶፍ ዝናብ ቢወርድብህ፣ ዋጋህ ያነሰበት፣ መኖርህ የማይቆጠርበት፣ አበርክቶትህ የማይታይበት፣ ስራህ የማያፈራበት፣ ማንነትህ የማይመረጥበት ስፍራ ብትኖር እንኳን ፈጣሪ አብሮህ ካለ ሁሌም የተሻለ ከፍ ያለ ነገር አለህ።

🔷ምንም እንኳን እምነታችን ቢጎድል፣ ክፋታችን ቢበዛ፣ ሃሳባችን ቢያንስ፣ ምግባራችን የወረደ፣ ስራችንም አሳዛኝ ቢሆንም ፈጣሪ ግን ጥሎ አይጥለንም።፣ ትቶ አይተወንም ሁሌም ይመለከተናልና መቼም ችላ አይለንም። የተውን ሰዎች ይኖራሉ፣ ያገለሉን፣ የተጠየፉን እንዲሁ እንደዋዛም የናቁን ሰዎች ይኖራሉ ዋናው ነገር ግን በፈጠረን አለመገፋታችን አለመረሳታችን ነው።

♦️የተሻለ አለህ! ከዛሬው የላቀ፣ ከትናንት የገዘፈ፣ ከአሁንህ ያየለና ከፍ ያለ ስፍራ ይኖርሃል። የማይቀየሩ የሚመስሉ ከባድ ሁኔታዎች ይቀየራሉ፤ ይወርዱ የማይመስሉ ሸክሞች፣ ይፈቱ ያልመሰሉ ችግሮች፣ ይስተካከሉ ያልመሰሉ ውጥንቅጦች ይወርዳሉ፣ ይፈታሉ፣ ይስተካከሉ።

እምነትህ ቢፈተን ግራ አትጋባ ይልቅ ለተሻለ ክብር እንደታጨህ አስተውል፤ በፈተናህ ብዛት አትደናገር ይልቅ የድልህ ቀን ቅርብ እንደሆነ አስተውል። በጫናዎች ብዛት የማትሸበር፣ ለምድራዊ ፈተና የማትበገር፣ ከፈጣሪህ ውጪ እንዳልሆንክ አስተውል።

🔷አንዳንዴ ማሳለፍ እየቻልን አቅፈናቸው የምንቀጥላቸው ብዙ ኮተቶቻችን ጣእሙን ማየት እንዳንችል ሁሉ ነገራችንን ዘግተንባቸዋል። ለማማረር እንጂ ለማመስገን ስንፈናል ለማዘን እንጂ ለመደሰት ጉልበት አጠተናል። መቆየት በማይገባን ቦታ ላይ በመቆማችን ማሳለፍ የሚገባንን አላፊ ሃሳቦችን እንዳያልፋ መንገድ ዘግተንባቸዋል እሰኪ ነቅነቅ እንበል እናሳልፋቸው የሚመጡት ሁሉ እንደአመጣጣቸው እንሸኛቸው አኛም ከቆምንበት አስተሳሰብ ስናልፍ ሁሉም ጊዜያዊ መሆኑን እናውቃለን።

ሁሉም ያልፍ የለ ትላንትናም አልፏል ዘሬም ታልፋለች ነገም ትቀጥላለች እኔም አንተም እናልፋለን ምክንያቱም ሁሉም ያልፋል።ሁሉን የፈጠረ፣ ሁሉን የያዘ፣ በሁሉ ውስጥ ያለው አምላክህ ባንተ ውስጥ ስለመኖሩ አትጠራጠር፤ ለተሻለው ስፍራ እንደሚያበቃህ እምነት ይኑርህ።

🔑ማሰብ ላይ በርታ፤ መስራት ላይ ጠንክር፣ አምላክህን ይዘህ ፈተናህን ተጋፈጥ፣ በፀሎትህ ፅና፣ ምስጋናህን ደጋግመህ አቅርብ፣ ካንተ በላይ የሚሰራብህ፣ ተአምር የሚያደርግብህ ፈጣሪህ አብሮህ እንደሆነ አስብ። ብቻህን የሆንክ ቢመስልህ እርሱ ከጎንህ አለ፤ የተገፋህ ቢመስልህ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነህ፤ የወደክ ቢመስልህ እርሱ ያነሳሃል፤ በሚገባህ ስፍራም በክብር ያቆምሃል።

ውብ አሁን ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💎እንደ ንስር ወደ ላይ ከፍ በል

ወዳጄ ንስር ሁን በቀቀንነት ይቀርብህ። በቀቀን የሌሎችን ሰዎች ሕይወት በመመሰል ውድድር ከፍ ብሎ መብረር አይችልም። ስጦታውን፣ እውቀቱን እና ክህሎቱን ከማዳበር ይልቅ ሌሎችን መስሎ መኖር ይመቸዋል።

ሕይወት ደግሞ በተቃራኒው ከበቀቀኖች ይልቅ ለንስሮች ፍሬዋን ትሰጣለች። ተፈጥሮ ብዙ ቀለም ፣ ብዙ ዕድል፣ ብዙ ፈተና ናት። ንስር አሞራ የለውጥ ተምሳሌት ተደርጎ የሚወሰደው በስራ የዳበረ ከእውነተኛው ዓላም ጋር የተሰናሰለ ስብእና ስለገነባ ነው።

📍ንስር የአእዋፋት ሁሉ ንጉስ ነው ሲባል በዋዛ እንዳይመስላችሁ። ንስር የሃይል ሚዛኑን ለመጠበቅ በቂ የሆነ ልምምድ የሚያደረግ ፣ የሚፈልገውን ነገር ከማድረግ  የማይቆጠብ ቁርጠኛ የስነ ልቦና ተምሳሌት ነው ። ህይወቱን ሙሉ ትኩስ ስጋ እያደነ ነው የሚኖረው ። የሞተ ነገር አይነካም። የእለት ሲሳዩን እያደነ ይበላል እንጅ እንደ ቁራ የሞተ በክት እያሸተተ አይቀላውጥም። ሃይሉን እያደሰ የእንደገና ድልና ስኬቱን እያጣጣመ በንግስናው እስከወዲያኛው ይዘልቃል።

ሰማዩ ሲጠቁር ደማናው ወጀቡንም ሲያይል ሌሎች እዕዋፋት በየ አለቱና በየጥሻው ችፍርግ ወስጥ ይደበቃሉ በቤት ታዛ ስርም ይደበቃሉ። ንስር ግን ደስ ይለዋል ወጀቡ ሲጀምር ንፋሱን በመሞገት የራሱን ጥንካሬ ይላካበታል።  የነፋሱን አቀጣጫ በመከተልም ይበራል። ረሱን ወደላይ ለማምጠቅና የከፍታውን ጫፍ ለመጨበጥ ይጠቀምበታል ፣ በዚህም ጥንካሬውን ይለካበታል።

💎ንስር ወጀብ ከመምጣቱ ብዙ አስቀድሞ ማወቅ ይችላል። እንዳወቀም ከፍታ ቦታ ለይ ይቀመጥና ንፋሱን ይጠብቃል። ወጀቡ ሲመጣ ከተቀመጠበት በመብረር ንፋሱ አግዞት ከወጀቡ በላይ እንዲበር ያደርገዋል። ወጀቡ ከታች ያለውን ዓለም ሲያተራምሰው፣ ንስሩ ከወጀቡ በላይ ይንሳፈፋል። እዚህ ላይ አንድ ነገር ልብ እንበል። ንስሩ ወጀቡን አላመለጠውም ፤ ተጠቀመበት እንጂ !!

📍የሕይወት ወጀብ ወደ እኛ ሲመጣ፣ ልክ እንደ ንስሩ ከወጀቡ በላይ መብረር እንችላለን፤ በሽታን፣ አደጋን፣ ውድቀትን፣ እና ሃዘንን ወደ ሕይወታችን የሚያመጣውን ንፋስ ለከፍታችን መወጣጫ ልናደርገውው እንችላለን።

🔑እናም ወዳጄ

አንተም መከራንና ፈተናን አትፍራ በወጀብና በዐውሎ ነፋስ ውስጥም ቢሆን መንገድ አለና መከራውን ግብግቡን የአዳዲስ ሐሳቦች መነሻ የጥናካሬህ መለኪያ አቅምህን የምትጠቀምበት አጋጣሚ፣ አልፎም ወደ ላይ የምትመጥቅበትና ከችግር ደመናዎች በላይ የምትንሳፈፍበት ዕድል አድርገው። እንደ ሌሎች ወፎች ከመከራው አትሽሽ ከችግሩንም አትደበቅ መከራን ለጥንካሬና ለበረከት ተጠቀምበት።

          ውብ የስኬት ጊዜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🌗በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል ስንት ወርቅ ይዛችሁ እንደመዳብ ካቀለላችሁት ከእጃችሁ ሲወጣ ይቆጫችኋል። ዛሬ እናታችሁ አጠገባችሁ ስላለች አመስግኑ ዛሬ አባታችሁ ስላለ ተመስገን በሉ ዛሬ ጤና ስላላችሁ ፣ ዛሬ ወጥታችሁ መግባት ስለምትችሉ አመስግኑ።

💡ይህ ሁሉ ባይኖራቸሁ እንኳን በህይወት ስላላችሁ ተመስገን በሉ፣ በህይወት ያለ ነውና የተበላሸውን ማስተካከል የሚችለው። በህይወት ከመኖር በላይ ዋጋ ያለው ነገር የለም፤ የምናገኘውም የምናጣውም በህይወት ስላለን ነው። መኖርን ደግሞ በነፃ ነው ያገኘነው፣ ምሬት ዓይንን ያጨልማልና ደስተኛና አመስጋኝ እንሁን።

💡እጅግ ውድ የሆኑ ነገሮች በነፃ ነው የተሰጡን፡፡ ፈጣሪ የአቅማችንን ልክ ስለሚያውቅ የከበሩትን ነገሮች ያለክፍያ አስረከበን፡፡ አየር፣ውሀ፣ ደማችን፣ አካላችን፣ ፀሀይዋ፣ ዝናቡ እና አፈሩ በክፍያ ቢሆኑ ማን መግዛት ይችል ነበር? ህልውናችን በነኝህ ነገሮች እጅግ የመቆራኘቱን ያህል በገንዘብ የሚገዙ ቢሆኑ ኖሮ እኔነኝ ያለ የምድር ባለጠጋስ ወጪውን ይችለው ነበር ወይ ?

❤️በነፃ የተሰጡን ባይኖሩ ኖሮ ሰው በውድ የሚራኮትባቸው ቁሶችስ መች ይኖሩ ነበር፡፡ ሰው ርካሹን በውድ ይሸጣል ፈጣሪ ግን ውዱን በነፃ ይሰጣል፣ ማጉረምረሙን ትተን ስለ ፈጣሪ ለጋስነት እናመስግን ከምናስበው በላይ ባለፀጎች ነን፡፡

🌗ስለ ሁሉ ነገር አመስጋኝ ሁን ማመስገን ስትጀምር አለም ወደአንተ ታዘነብላለች ነገሮች በሙሉ መልካም ይሆናሉ። ካሰብከው በላይ ሁሉ ነገር ሲስተካከል ሲያምር ታየዋለህ በምድር ላይ ሁሉ ነገር ለመልካም እንደሆነ ስታውቅ፣በማመስገን ስትታጀብ ቤትህም ይደምቃል ኑሮህም ይሞቃል በረከት ሁሉ ወዳንተ ይመጣል።

ልባችን ሁሌም ለምስጋና ክፍት ይሁን!

         ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ጨለማው ላይ ብታፈጥ ያለ ሰዓቱ አይነጋም።ፈጣሪህን ትተህ በመከራህ ላይ ብታፈጥ አንዳች ጥቅም የለውም። ካስተዋልከው ጨለማም ውበት አለው። ከካባ ይልቅ ደማቅ ነው። እሾህም አበባ አለው። ክፉ ሰውም አንድ ጥሩ ነገር አለው። ልብ አድርግ ለክረምት በጋ፤ ለሌሊት ቀን አለው። ላንተም ጊዜ አለህ። ጊዜን የሚሰጥ ራሱ ጊዜ ሳይሆን የጊዜ ባለቤት ፈጣሪ እንደሆነ እመንና ጠብቅ።

ጊዜ ለታጋሾች የማታሳየው የለም። መስበርም መጠገንም ትችላለች ፣ አንተርሳ ትዘቀዝቃለች ፣ ዘቅዝቃ ታቃናለች። ለጊዜ የሚሳናት የለም፣ እንዳወጣች ታወርዳለች ። አንተም በፈታኝ ጊዝያቶች ክብርህን ጠብቅ። ፈተና ውስጥ እንኳ ብትሆን የሥሜት ብስለትህን እና ራስ ገዝነትህን አሳይ። ታጋሽ፣ ፅኑ፣ ተረጂ ለመሆን እንዳትዘነጋ።

📍እንደ እንስት ውበት ያጌጠው  ህይወታችን ፣ ቀን ሲገፋ ይደበዝዛል እስከተፈቀደልን አብርተን ጊዜ ሲቋጭ ጭልመት እንላበሳለን። አጥቶ ማግኘት እንዳለው አግኝቶ ማጣት አለ ፣ ብርሀኑ ቢጨልም አንከፋ ለበጎ ነው፣ ጭልመት በብርሃን ሲቀየር አንገረም። ምንም ዘላለም ሊቆይ አልመጣም።

ተስፋ ከቤታችን አይጥፋ!
             ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍#እሮጣለሁ

ወደ ጎዳና እየወጡ ያሉ ወገኖቻችን ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት የሚፈልግበት ደረጃ ላይ ደርሷል።

❤️ሁላችንም በትብብር ችግሩን ለመቅረፍ የሚጠበቅብንን እንወጣ። የሜሪጆይ ቤተሰብ እያደረገ ያለውን ጥረት እደግፋለሁ።

እኔም ከቤተሰቤ ጋር በሜሪጆይ ሩጫ ላይ እሳተፋለሁ።

ታህሳስ 14; 2016 ተመዝግቧል! እሮጣለሁ፤

#ወገኖቼን_ከጎዳና_አነሳለሁ

1) የሩጫው መሪ ቃል፡-
አሳሳቢ ደረጃ ላይ የደረሰው ወደ ጎዳና የወጡ ወገኖቻችን በተለይም ከልጅ ጋር ጎዳና ያሉትን እናቶች በማሰብ፤ የሩጫው መሪ ቃል “እሮጣለሁ፤ ወገኖቼን ከጎዳና አነሳለሁ!” የሚል ነው፡፡

2) ሩጫው የሚደረግበት ቀን፡- ታህሳስ 14፤ 2016

3) መነሻና መድረሻ፡- ከቴዎድሮስ አደባባይ እስከ መስቀል አደባባይ

4) ሩጫው የሚሸፍነው ኪሎ ሜትር፡-               5 ኪሎ ሜትር

5) የቲሸርት ዋጋ፡- 400 ብር ለአዋቂዎች እና 300 ብር ለልጆችና አዋቂዎች

6) ቲሸርት ስርጭት የሚደረግባቸው ቀኖች፡- ከታህሳስ 8 – 13፤ 2016 ዓ.
ቲሸርት መግዢያ መንገዶች፤

በሜሪጆይ ቴሌግራም ቦት @MaryJoybot በኩል መመዝገብ ይችላሉ

ለበለጠ መረጃ፤ ስልክ 0994535353 | 0983636363 | 0987626262
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
❤️ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነታችን እንደ ወንዝ ይሁን! ሳንመርጥ፣ ለለመነን ሁሉ እጃችንን እንዘርጋ። ወንዝ ወደፊት ብቻ የሚሄድ ወደኋላ የማይመለስ ሲሆን ቀጣይነቱን ይመሰክራል፤ የኛም ደግነት እንዲሁ ዛሬ ተጀምሮ ነገ የማያበቃ፤ ሁልጊዜ እንደ ወንዝ የሚፈስ መልካምነት፣ በጎነት የተሞላበት ይሁን።

📍መርዳት ዕድል ነውና እንጠቀምበት! ከእኛ የሆነ ምንም ነገር የለም  ለፈጣሪ እጅ ሆነን እንደምንሰጥ ልናስብ ይገባናል። እውነተኛ ስጦታ ከትርፍ ሳይሆን ካለን ላይ ነውና ተጎድተን እስክንሰጥ ድረስ ገና እንዳልሰጠን ልንረዳ ይገባል፡፡

እያዩ ፈንገስ በመድረኩ ላይ ሲናገር

"ላለመርዳት ኪስህን ሰበብ አታድርግ። ባዶ ኪስ ነህ ማለት የምትሰጠው ምንም ነገር የለህም ማለት አይደለም፤ ቢያንስ የምትሰጠው ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ አለክ ማለት እንጂ።

ባዶ ኪስ የሆነ ሱሪ መስጠት ቢያቅትህ፥ በባዶ ኪስህ እጁን እንዲያስገባ ፍቀድለት። ቢያንስ አንድ እጁን ከብርድ ትከላከላለህ'' ይለናል ።

❤️እናም ወዳጄ ሰው ሁን

ሰውን እንደራስ ለመውደድ ቅን አዕምሮ፤ ደግ ልብ ይፈልጋል፡፡  አንተም ፈጣሪን የምትሻ ከሆነ ወደ እሱ ቤት መሄድ አለብህ። ቤቱም የሰው ልጅ ሁሉ ነው ፤ አስተውል ያንተ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድረስላቸው ፡ የወደቁትን አንሳ ያዘኑትን አጽናና የተራቡትንም ሽራፊ ቁራሽ አትንፈግ የታመመን ጠይቅ፣ የተቸገረን እርዳ፣ አግዝ ታማኝ ሁን! በዚህ ልክ ለፈጣሪ ስትቀርብ፣ ስኬትህም ሆነ በረከትህ ወዳንተ ይመጣሉ።

ፈጣሪ ለሁላችንም ልበ ሰፊና ቅን ልቦና ይስጠን!

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
💡ያለፈ ጥረታችንን ሳስታውስ ከሞከርነው ነገር ይልቅ ያልሞከርነው ነው እሚቆጨኝ። ሃገር ስትታመም፣ ብርድ ብርድ ሲላት፣ ተስፋና ሥጋት፣ ወኔና ፍርሃት፣ ምርቃትና እርግማን - እንዳሻው ሲንጣት ከሆነብን ይልቅ እየሆነ ያለው ያሳስበኛል ፣ ከእሳቱ በላይ አያያዙ ያሰጋኛል፣ ከጥያቄው በላይ ምላሹ ይስበኛል።

📍ችግር ፈቺነት ከሚጠይቀው ጥበብ ውስጥ ዋነኛው የሚመስለኝ ለሌላ እንከን ገርበብ የማይልን በር የመተው ብልህነት ነው። አንድን ሕመም ስታክም 'ከተጠባቂው' ጎንዮሽ እንከን ውጭ ሌላ ህመም እንዳልፈጠርክ ማረጋገጥ ግዴታህ ነው። በስመ መድኃኒት የተገኘው አይደነጎርም፣ አንድ ችግር ፈትቷል ተብሎ ለሌሎች ችግሮች ሰበብ እንዲሆን አይተውም፣ በእውቀት እንጂ በደመነፍስ አይቃኝም።

💡በእንዲህ ዓይነት ጊዜ ጥሞና ነው የሚያስፈልገን፣ የሰከነ ውይይት ነው የሚያሻን፣ 'ምን ብናደርግ ይበጃል?' መባባል አለብን። ጊዜው እሾህ እያወጣን ጦር የምንተክልበት አይደለም፣ እንቅፋት እየነቀልን ፈንጂ የምንቀብርበት አይደለም፣ ጀግነን አዙሪቱን እኛው ጋ የምናቆምበት እንጂ፣ የክብሪቱን እሳት እፍ በምትልበት ሰዓት ካላጠፋኸው እፍ ብሎ ያጠፋሃል።

📍'ካልደፈረሰ አይጠራም' የሚል አስተሳሰብ የሚያቀነቅኑ ሰዎች ዛሬም በዙሪያችን እንዳሉ ማሰብ ያደክማል፣ ሳይደፈርስ ማጥራት ከተቻለ ለምን ይደፍርስ ብሎ መጠየቅ ግን ግድ ነው። የደፈረሰ ሁሉ ይጠራል ወይ ማለትም ያስፈልጋል፣ ድፍርስ ሲጠራ ዝቃጭ እንደሚተው አለመርሳትም ደግ ነገር ነው። ምንም ብንታገል ልናስቀር የማንችለው አንድ ነገር ለውጥ ብቻ ነው፣ ለበጎ አልያም ለክፉ እንዲሆን የማድረጉ ድርሻ ግን እጃችን ላይ አለ። ችግሩ 'እንዲሆን' የምንፈልገው አለ - ሆነን ግን አንጠብቀውም.. 'እንዲመጣ' የምንሻው አለ - የምናዋጣው ግን የማይገባውን ነው።

💡በእንዲህ ያለ ቀውጢ ጊዜ ወሳኙ ሰው አንተ ነህ፣ ዘረኛ ሳይሆኑ ነው ዘረኝነትን ማረቅ የሚቻለው፣ ሳይሰርቁ ነው ዘራፊነትን ማስቆም የሚቻለው፣ አድማጭ ሆኖ ነው ጫጫታን ማስቆም የሚቻለው፣ ግማሽ መንገድ መጥቶ ነው 'እስኪ እንነጋገር' የሚባለው፣ለውጡን ተለወጠው እንጂ ከሌሎች አትጠብቀው፣ አርዓያ ሁን የሚመለከቱህ አሉ ፣ የሚከተሉህ አሉ።

ፊት መሆን በሚችል ስብዕና ከፊት ቁም፣ ጊዜህን አፍ በመካፈት አትብላው፣ ስህተት በመንቀስ አትሙላው ብሽሽቁ፣ አተካራው፣ መናቆሩ፣ ጎራ ማበጀቱ ፣ አሁን ፈጽሞ አይጠቅምም። እንዲመጣ የምትፈልገው ለውጥ አሁን አንተ ያልሆንከው ወይም የሌለህ ከሆነ ለውጡ መቼም አይመጣም መቼም!!

🔑 የትኛውም የችግር ቁልፍ የፍቅር ስሪት ከሌለው መሰበሩ አይቀርም ፣ ወደድክም ጠላህ እውነተኛውና ዘላቂው ኃይል ፍቅር ብቻ ነው ፣ የረቀቀ ሳይንስም ሆነ የጠለቀ አስተሳሰብ ፍቅርህን አያክልም፣ የገዘፈ ኃይልም ሆነ ልክ የለሽ ስልጣን ፍቅርህን አይተካም፣ የፍልስፍናህ ጥግም ሆነ የልሂቅነትህ ጠገግ አፍቃሪነትህን አይተካከልም።

የአብሮ መኖር እንከናችንን የሚደፍን ሕብር እንጂ የመለያየት ግንብ የሚገነባ መዝሙር ሰልችቶናል፣ ከነበርክበት 'የተሻለ' ብርሃን ስትፈልግ ወደ አልነበርክበት ጨለማ አለመግባትህን ማረጋገጥ ብልህነት ነው!!

  ደምስ ሰይፉ

ውብ ጊዜ ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
🎄በመላው ዓለም ለምትኖሩ የክርስትና እመነት ተከታይ እህት ወንድሞቻችን እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን።

💛በአሉ የሰላም የፍቅርና የደስታ ይሁንልን🎄

❤️🏑 መልካም የገና  በአል 🏑


@ETHIOHUMANITY
@ETHIOHUMANITY
💡ወንድሜ! ራስ ወዳድነት የታወረ የበላይነትን የመሻት መክንያቱ ነው።የወንድምህ የበላይ የመሆን ፍላጎት ጎሳና ነገድ እንዲፈጠር ምክንያቱ ሆነ፤ጎሳና ነገድ ደግሞ እርስ በርስ መጋደልና አንዱን መጨቆን አስከተለ።

📍ፍቅር በእዉቀት ሃይል ታምናለች ፤ ፍትህ ደግሞ በጨለማው አላዋቂነት ላይ ትሰለጥናለች። ታላቋን ባቢሎን ካጠፍ ፣የኢየሩሳሌምን መሰረቶች ካናወጠ፣ሮምን ከፍርስራሿ ጋር ካስቀረዉ ከዚያ ሰልፍ ከሚያቀብል ሥልጣን፣አላዋቂነትና ጭቆናን ከሚያንሰራፋ የሥልጣን ሃይል ጋር ፍፁም ትቃረናለች። ዳሩ ታላላቅ ሰዎች ተብለው ሲጠሩ የኖሩ እንዲህ አይነቶቹ ወንጀለኞች ናቸው።

📍አኔ የምቀበለው ብቸኛ ስልጣን በተፈጥሮ ሕግ ላይ የተመሰረተዉን ፍትሕና እሱን የሚቀበለውን እዉቀት የያዘውን ብቻ ነው። የራሱን ጉዳይ ብቻ የሚያቅፍ ባለሥልጣን ላይ ፍትህ ምን የምታደርግ መስልሃል?

አንተ ወንድሜ ነህ፤ስለዚህ እወድሃለሁ! ፍቅር ደግሞ ታላቅ ፍትህ ነው! ከየትኛውም ጎሳ ወይም ነገድ ብትመጣ  ለአንተ የምሰጠው ፍትህ "ፍቅር" ብቻ ነው።

❤️ፍቅር ስለ ራስ ብቻ ማሰብ ሳይሆን ስለሌላውም ማሰብ ነው ። ፍቅር ሲታመም ሁሉም ነገር ይታመማል። ስብእናም አስተሳሰብም  ስሜትም ይታመማል ። ወዳጀ ሆይ አንተም አስተውል ያንተ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ ድረስላቸው ከራስህ ከፍታ ይልቅ ለሰዎችና ለሃገርህ ከበሬታ ይኑርህ ፡፡የወደቁትን አንሳ ያዘኑትን አጽናና ፍቅር ስጣቸው እርሱ ከሁሉም ይበልጣልና!!

                     ካህሊል ጂብራን

ውብ አሁን ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
«እናንተ የዓለም ብርሃን ፣ የምድርም ጨው ናችሁ»

🔷ብርሐንና ጨው ከተባልን ዘንዳ፤ እንግዲያውስ እውነተኛው ብርሐንና እውነተኛው ጨው ምንድነው አልን ! ቃሉን ልንተነትን ሳይሆን ቃሉ ያጫረብንን መረዳት ከአኗኗራችን ዘይቤ ጋር አዛምደን፣ በዘመናችን ታይታ ወዳድነት እና የመታየት ልክፍት፥ ሳናውቅ ለገባን እኛ ነገሩን ለማስታወስ ያህል ይህን አልን!

📍ብርሐን ያሳያል እንጅ አይታይም! ብርሐን የማይታየው ጨለማ ውስጥ ስለሆነ አይደለም፣ ይልቁንም ብርሐን ብርሐኑን የሚያበራው ወደራሱ ሳይሆን ወደሌሎች በመሆኑ ነው! ሌላውን ለማሳየት እንጅ ራሱን ለማጉላትና ለማድመቅ የሚታገል ብርሐን በዙሪያው የሚረጨው ጨለማ ብቻ ነው! እዚህ ላይ ብርሐን ስል የብርሃን ምንጩን ጭምር ማለቴ ነው።ብርሃን ተፈጥሮው ማሳየት እንጅ መታየት አይደለም።

🔷ፀሐይ በምትረጨው ብርሃን ዓለም ይነጋል ፤ ፍጥረት ሁሉ ይደምቃል፣ ተክሎች ያድጋሉ፣ አበቦችም ይፈካሉ፣ ቆፈን ይገፈፋል፤ ፀሐይን ራሷን ግን ለሴከንዶች እንኳን ማየት አንችልም።ታሳያለች እንጅ አትታይም! የቤታችንን አንፖል ከነመኖሩ የምናስታውሰው ቤታችን ሲጨልም ብቻ ነው፣ ግን ሁሉን ነገር የምናየው ከአንፖሉ በሚወጣው ብርሃን ነው። አንድ ሰው ሻማ የሚለኩሰው ሻማውን ሲያይ ለማምሸት አይደለም ፣ በሻማው ብርሃን አካባቢውን ሊያደምቅ ነው! መታየትን የምትሳሳ ነብስ ብርሐን አይደለችም፤ ይልቅ ብርሐን ያስፈልጋታል፤ በሌሎች ጨለማ የምትሳለቅ ነፍስ ብርሐን በውስጧ የለም ፣ብርሐን በተገኘበት የሌሎችን ጨለማ ያነጋል እንጅ በጨለማቸው አይዘባበትም።

📍ጨው እና ብርሃን ተመሳሳይ ባህሪ አላቸው፤ ጨው ብቻውን ምግብ ነኝ ብሎ ማዕድ ላይ አይኮፈስም፤ ቢኮፈስም የሚነካው የለም! ጨው ምግቡ ውስጥ አይታይም ግን ምግቡን ያጣፍጣል! በአጭሩ ነፍሳችሁ መታየትን መጉላትን መደነቅን መወደስን ከፈለገች «ሰዋዊ ነው» በሚል ትሁት መታበይ ራሳችሁን አታታሉ። እንደዛ ካሰባችሁ ብርሐንም ጨውም አይደላችሁም! እንደውም ትክክለኛ ጨውነታችሁ የሚታወቀው በእናተ በጎነት ሌሎች ሲወደሱ ነው! በተረት እንዝጋው «በጨው ደንደስ በርበሬ ተወደስ» ይሄው ነው!

አሌክስ አብርሃም

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
እነዚህ መፅሐፎች ቅፆች ያሉት ሰው የሚሸጥ ካለ እንደው ወይም የምታውቁት ሰው ካለ ብትተባበሩኝ

@Nagayta በዚህ ሊንክ ልታገኙኝ ትችላላችሁ
🔺“ሰው - ራሱን እንኳ የሚያስደምመውን ተቃርኖ በውስጡ ተሸክሞ የማይፈራ።

“ሰው” -ጨክኖ መግደልን ከአፍቅሮ መግደል ጋር አስማምቶ ሲኖር እንቅልፍ የማያጣ።

ሰው' -ሰፍሮ ያልጨረሰው መሬት ቢጠበኝ ብሎ የሚሰፋ።

“ሰው -የስጋ ደካማነቱን ማካካሻ ከምናቡ ቆርጦ፥ በስራው፣ በሰራው እና በሚሰራው፤ ደካማነቱን የረታ፣ የሚረታ።

“ሰው -የማያቋርጥ የተቃርኖ ጅረት፣ የማይጠግ ጥበብ ምንጭ፤ የፍርሀት ልጅ፣ የድፍረት ወላጅ።

“ሰው - ምንነቱ ከማንነቱ የተምታታ፤ ምንነቱ ማለቂያ ቢስ፣ በማንነት የሚታሰር።

ሰው ፥ ይህ ሰው! እንዴትና በምን ?” ምንስ ሆኖ ?” ራሱን፣ ማንነቱን፣ ሰው-እነቱን ረሳ ?! ከዚህ በላይስ ምን ይገርማል !

📍ለማንኛውም ካላስታወሳችሁ አይፈረድባችሁም፡፡ ራሱን የረሳ ሰው፥ ሌላ ነገር አስታውስ ተብሎ ሊጠየቅ አይገባም፡፡ ግን ለምን አይገባም ?” ባይገባም፣ ባይገባም ግን ይጠየቃል፤ ይጠይቃል፣ ይመልሳል። የሆነውን ሳይሆን ያልሆነውን፣ የኖረውን ሳይሆን የተነገረውን፣ እውነቱን ሳይሆን የተባለውን ይመልሳል።

ሰው መሆን በጣም ይደንቃል። ሰው መሆኑን የረሳ ሰው፥ ወንድ መሆኑን ግን ሲያስታውስ አይደንቅም ?” ሰው መሆኑን የረሳ ሰው፥ ነጭ ወይም ጥቁር መሆኑን ሲያስታውስ አይደንቅም ?”

መሬት ላይ የተፈጠረ ሰው፥ መሬትን ረስቶ ሀገሩን ሲያስታውስ አይደንቅም ?” ከሌላው ጋር መግባቢያ ቋንቋ እንዳለውና ይህም ደግሞ ከየትኛውም ፍጡር እንደሚለየው ረስቶ፥ መናገሪያውን ማስታወሱ አይደንቅም ?”

ብትረሱም አልፈርድባችሁም። ዞሮ ዞሮ ምንም ነገር እንዳለኝ ወይም እንደነበረኝ ያወቅሁት፥ ሳይኖረኝ ሲቀር ነው። እናትም፣ ቋንቋም፣ ሀገርም፣ አያትም፣ አባትም፣ ሃይማኖትም ሁሉም፡፡

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
⚡️የጨረቃዋን ውበት የሚሻ ጨለማውን አይሸሽም፣ ጽጌረዳዋን ብሎ የሄደ እሾሁን ፈርቶ አይመለስም
ፍቅርን ከልቡ የሚፈልግ ሰው ከራሱ አይደበቅም ፣እራሱን ፈጽሞ አይሸሽም ።

የምንፈራው ነገር ብዙ ጊዜ የምንመኘውና የሚበጀንን ነገር ነው። ሰዎች ከእውነተኛ ፍላጎታችን የመሸሽ ባህሪ አለን። በምክንያቶች እራሳችንን እያታለንን፤ ሊነቃ የሚታገለውን ድብቅ ምኞታችንን መልሰን እናስተኛዋለን።

ፍርሃታችንን ብንከታተለው..ጥበባችንንም እዛው ማግኘታችን አይቀም። ለዚህም ነው ልትገባበት የምትፈራው ዋሻ ውስጥ ነው ሀብትህን የምታገኘው የሚባለው። ውብ ነገሮችን ለማግኘት ሰው ፍርሃቱን አልፎ መሄድ አለበት፤ በምንፈግልጋቸው ነገሮችና በእኛ መካከል የቆመው ትልቁ ግድግዳ ካለማውቅ የሚመነጨው ፍርሃት ነው:: ጨለማውን የደፈረ ጨረቃን፤ እሾሁን ያልፈራ ጽጌረዳዋን፤ እራሱን ያወቀ ፍቅርን ማግኘቱ አይቀርም::

🔑ፍርሃታችንን....እንከተለው ፤ የፍርሃት ዱካ እውነትኛ ምኞታችንን ያሳይን ይሆናል። ያንቀላፋውን ምኞት የሚቀሰቅሰውም ይኸው ለፍርሃት የምንሰጠው ምላሽ ብቻ ነው።

             ውብ አሁን♥️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍በሠዎች ዘንድ ተስፋ የሌለን ብንመስልም እንኳ ዋናው ነገር በፈጣሪ ዘንድ ያለው ተስፋችን ነው። ሕይወት ጠመዝማዛ ብትሆንም ውብና ተስፋን የተሞላች ናት።

💡በዚህ አለም ሁሉ ነገር አበቃ፣ አከተመ ባልንበት ጊዜ የሚቀጥል የተሻለ እድል፣ የምናውቀውና የተለመደው በር የተከረቸመ ቢመስልም ወለል ብሎ የሚከፈት ሌላ በር፣ ዙሪያችን ጭው ያለ በረሃ ቢሆንም የለመለመ መስክ የሆነ ስፍራ ላይ እንዳለ ተምሬያለሁ።

📍ህይወት እንደ ሳንቲም ናት ሁለት ገፅታዎች አሏት ፣ ተቃራኒ ግን ማይነጣጠሉ ገፅታዎች ። በህይወት እስካለን ካአንዱ ገፅ ብቻ ስንኖር ማለፍ የለም፣ እያንዳንዷ ሁኔታ ከጀርባዋ ተቃራኒ ገፅ አላት እናም ሳንቲም ያለ ግልባጭ ገፁ ምሉዕ እንደማይሆነዉ ያለ ሀዘን ደስታ ፣ ያለ ሞት ህይወት ፣ ያለ  ለቅሶ ሳቅ ፣ያለ ድህነት ሀብት ፣ ህይወትን ከነ ህብረ ቀለሟ አምነን መቀበል አለብን ፡፡

💡እድል ፊቷን ያዞረችብን በመሰለን ጊዜ እንኳ ቢሆን አብዝቶ በትጋት መጓዝ እንጂ ተስፋ መቁረጥ አይገባም። ትጋት የተስፋ ልጅ ናት። ተስፋ ደግሞ በእኛና በፈጣሪ መካከል የእምነት ድልድይ ስለመኖሩ ማረጋገጫ ነውና!
"ዛፍ ቢቆረጥ ደግሞ ያቆጠቁጥ ዘንድ፣ ቅርንጫፉም እንዳያልቅ ተስፋ አለው" ።

አለማየሁ ዋሴ

ውብ አሁን♥️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍ወዳጄ ሆይ

አትድከም፣ አትዘን ማን ያውቃል ሸክምህና ህመምህ ሁሉ ተራግፎ ሌላ ሰው ሆነህ ትነሳ ይሆናል። ያለን ፈጣሪ እንኳን በአንድ ሙሉ ሌሊት፣ በቅጽበት ጊዜ ዉስጥም ብዙ ተዓምር ይሠራል።

በቀልባቸው ንፅህና ብቻ ሰላማቸው የበዛ ሰዎች አሉ። ቀልባችሁ ንፁህ ሲሆን ሰላማችሁ ይበዛል፣  ለሌሎች መልካም ስትመኙ በረከታችሁ ይሰፋል። ልብህ የተጠራጠረዉን ነገር ተው፤ ልብ ከዐይን በላይ ያያልና።ወደ ፊት የሚሆነውን ሳትበሳጭ ሳትሰለች በትግስት ጠብቅ።የማይረባና ጥቅም የሌለው ነገር በመከተል ጉልበትህን አታባክን።

ወዳጄ ሆይ

ከሐዘን በኋላ ደስታ እንጂ ምን አለ!
ማጣትን ማግኘት እንጂ ሌላ ምን ይከተለዋል! ምሽቱስ እየነጋ አይደል የሚሄደው?? ከጨለማ በኋላ ብርሃን እንጂ ምን ይመጣል፡፡ የጨለመው ይበራል ፣ የጠፋዉም ይገኛል ።

ሕይወትህን መስዋዕት ያደረግህለት ሥራህ በፈረሰና በተናደ ጊዜ ይህንን ክፋ ፈተና ተቀብለህ ተስፋ ሳትቆርጥ የጠፋውን ሁሉ መልሰህ ለማቋቋም በደከመ መሣሪያ ለመሥራት ሳታመነታ ተነሣ።ያለነው የፈተና ምድር ውስጥ ነው። በበሽታ መፈተን አለ። በኀጢአት መፈተን አለ። በዕዳ መፈተን አለ ፣ የምድር ፈተናዎቿ ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም።

እናም ወዳጄ

ያለህን የሌለህን ገንዘብህን ሁሉ አንድነት አከማችተህ ስትሰራበት ሁሉንም ባንድ ጊዜ ስትከሥር አጣሁ ከሠርኩ ብለህ ቃል ሳትተነፍስ አሁንም ሰርተህ ለማተረፍ ከሥር ጀምረህ እንደ ገና አንድ ብለህ ድከም። ዐሳብህ ጉልበትህ ሥሮችህ ታክቶዋቸው በደከሙ ጊዜ ልብህ ብቻ ይበርታ።

ንፋስ የማይወዘዉዘው ዛፍ የለም። ሀሳብ ወስዶ የማይመልሰው ሰዉም የለም። እንዲህም ሆኖ የማይወድቅ ዛፍ አለ። በፈተና የሚፀና የሚበረታ ሰዉም አለ።

            ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
2024/11/14 15:29:26
Back to Top
HTML Embed Code: