Telegram Web Link
💎በዚህ ምድር ላይ ሰው ሁሉ የዘራውን ያጭዳል። ይህ ህገ ተፈጥሮ ነው። በየትኛውም የዓለም ክፍል የሚሰራ ህግ ነው። እንደ ህገ-መንግስት በአንድ ሉአላዊ ሀገር ብቻ የተገደበ አይሆንም። በምድር ላይ ለሰራው ደግነት ይሁን ክፋት ብድራት መከፈሉ የማይቀር ይሆናል።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ የቻልከውን ያህል መልካም ውለታ ብትውል ብድራት ተከፋይ ትሆናለህ። ካለህ ላይ መስጠት ማለት ነው። … የምትሰጠው ነገር ባይኖርህ ጥሩ ፈገግታ ስጥ። ምናልባት ይህች ፈገግታ አንተ ባታውቅ እንጂ አንዲት የጨነቃት ነፍስ ትታደጋለች ።

💛ያንተ መልካም ስነምግባር ሌላውን ተመልካች ከተኛበት የመቀሰቀስ መግነጢሳዊ የስበት ኃይል እንዳላት አንተ አታውቅም ይሆናል። በዚህ ምድር ላይ የተዘራ ማንኛውም ነገር እንዲሁ ወድቆ የሚቀር ላይሆን ይችላል።

💫መልካም ገበሬ ለነፍሱም ለቤተሰቦቹም ብሎም ለሃገር ለህዝብ የሚተርፍ ዘር ዘርቶ ፍሬውን ይመግባል።  በየትኛውም የህይወት ሜዳ ላይ የሚገኝ እያንዳንዱ ግለሰብ መልካም ገበሬ ለመሆን የሚያግደው የለም።

🔆ሁሌም በጎ በጎውን ማሰብ ስትለማመድ መልካም ገበሬ ትሆናለህ።  ከራስህ አልፎ ተርፎ ለሌላው የሚጠቅም መልካም ሐሳብ ወደ ዓለም ብትልክ መልካምነት ዞሮ ይከፍልሃል። ብድራቱን ታገኛለህ። የጣልከው አልያም ያካፈልከው ሁሉ መልሶ ብድራቱን ይከፍልሃልም። …መልካም መሆን ኪሳራ ከሌለው ክፉ መሆን ምንም ትርፍ የለውም። … ወዲህም ባንተ ላይ እንዲሆንየማትፈልገውን ነገር በሌላው ላይ አታድርግ። …ፍቅር ትሻ እንደሆን ፥ ቀድመህ አንተ ፍቅር ስጥ።  ያልሰጡትን ለማግኘት ማሰብ ፥ ስንዴ ዘርቶ የጤፍ ምርት እንደመጠበቅ እንዳይሆን። … ከመስተዋት የተሰራ ቤት ውስጥ የሚኖር ሰው ከቤቱ ሆኖ  ወደ ውጭ ድንጋይ መወርወር የለበትም። 

💡ጋን በጠጠር ይደገፋል እንዲሉ ፤ እያንዳንዱ ሰው በሌላው ህይወት በቀጥታም ይሆን በተዘዋዋሪ  ተፅእኖ ማሳደሩ ህገ-ተፈጥሮ ነው።አይመለከተኝም፥ አይደርስብኝም የምትለው ነገር ላይሆን ይችላል። … ጉንፋን የያዘው ሰው አጠገብህ ተቀምጦ ቫዮረሱ አንተ ዘንድ እንዳይደርስ ለማድረግ አትችልም። በአንድም በሌላ መልክ ኢንተርአክሽን ይኖራል።

            ውብ ምሽት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
❤️ፍቅር ማለት በዚህ በምትመለከተው ጨለማ ውስጥ ከሚብለጨለጩት ቁጥር ስፍር የሌላቸው አምፓሎች መሀል ፣ነፍስ አንዷን መርጣ በብርሃኗ ስትደምቅ ነው።ብርሀን ሁሉ የነፍስን ጨለማ አይገፍም ቢበዛ የራስህን ብርሃን ትፈልግ ዘንድ ያግዝህ ይሆናል።ሰው የቱንም ያህል በደማቅ ብርሀን ቢከበብ፣እውነተኛውን የራሱን ብርሃን እስካላገኘ ድረስ ነፍሱ ጨለማ ውስጥ ናት።

❤️ፍቅርና ዝምታ መለኮታዊ ኃይሎች ናቸው።ፈጣሪን የምንፈራው ከተከታዮቹ ብዙ ጩኸት ይልቅ በጥልቅ ዝምታው ሳይሆን አይቀርም እናም በዝምታ ግርማ ሞገስ ውስጥ ባለ እውነተኛ ፍቅሩ።ዝምታን የሚያሸንፍ ጬኸት ፍቅርን የሚያንበረክክ  ብልጣ ብልጥነት የለም።   

አሌክስ አብርሀም

ውብ ምሽት !!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
ሰዓት እላፊ! (ፀዴ ቀደዳ ነው ሳትሰለች አንብበው)
💛


. [Restoring Faith in Humanity]

. ∞ ∞ ∞ ∞

እነሱም ይላሉ፣
ተኩሰን አንስትም፣
እኛም እንላለን፣
ቃታ አናስከፍትም።
እንዲህ ተባብለን፣ የተገናኘን 'ለት፣
ተሰብሰብ አሞራ ትበላለህ ዱለት።

-

የአዲስ አበባ ሠው ሆይ።

ይሄ የተጣድንበት እሳት፣ ይሄ እቶን፣ ይሄ ነበልባል፣ ይሄ ድውይ ጦርነት ስሙ የርስ በራስ ጦርነት (Civil War) ነው። በቀላል አማርኛ - የቀድሞው ኢህአዴግ ግንባር በስልጣን እና በሪሶርስ መስማማት አቅቶት #እርስ_በራሱ ስለተጣላና ስለተከፋፈለ ያወደቀብን ዳፋ፣ ያመጣብን ሲቪል ዋር ነው። የሲቪል ዋር ደግሞ ጀግና የለውም። ፈሪም የለውም። ፀጉረ ልውጥ - ባዳና ባንዳ የለውም። ድሉም ችንፈቱም፣ ገድሉም ውርደቱም የኔና ያንተ ነው። #የኛው ገመና፣ የኛው ነውር ነው።

እውነት ነው።

ት*ግሬዎቹ ላመኑበት ባመኑበት በታላቅ ጀግንነት ተዋግተዋል። እኛም ላመንንበት ባመንንበት በታላቅ ጀግንነት ገጥመናቸዋል። እነሱም ዘራችንን ሊያጠፉ ወጉን ብለዋል። እኛም አገር ሊያፈርሱ ወጉን ብለናል። ሁሉም የየራሱን Narrative ይዞ አውደ ውጊያ ወርዷል። አፋፍ ለአፋፍ፣ ምሽግ ለምሽግ፣ ጢሻ ለጢሻ፣ ቆረንጦ ለቆረንጦ በታላቅ ወንዳ ወንድነት ገጥሟል። ታላቅ ገድልን ተጋድሏል። አቸናፊም ተቸናፊም ታሪክ አስጽፏል። ታሪክ ሰርቷል።

የሸገር ሰው ሆይ።

አሁን በቀጣይ ሳምንታት አቸነፍን ብለን፣ መቀሌ ገባን ብለን። ምናልባትም የህወሃት አመራሮችና የጦር ጄነራሎች በወንድ ልጅ/ በማርያም መንገድ እንዲሼሹ ተደረጉ ብለን። አልያም አይበለውና ተማርከው ወታደራዊ ፍርድ ቤት ቀረቡ ብለን የት*ግሬውን ቅስም የመስበርና የማሳጣት ፕሮፓጋንዳ ውስጥ ከገባን #ትልቁን ስእል (The Big Picture) እንስታለን። የቅሽምናን Cycle እናስቀጥላለን።

አትርሳ።

ት*ግሬው እኮ የአገርህ ልጅ ነው። በደም፣ በባህል፣ በእምነት፣ በአኗኗር፣ በወኔ በኑሮ አንተን መሳይ ነው። ቢያኮርፍም፣ በቃኝ ካንተ ጋራ አብሮ መኖር፣ ፍታኝ ልፋታህ ቢልም ዘመድህ ነው። በሕግ በዜግነት ያንተ አይነት መብትና ግዴታ ያለው ኢትዮጵያዊ ነው። በታሪክ ደግሞ ሃገር ግንባታ ላይ፣ ዳር ድንበር ማስጠበቅ ላይ፣ ኢትዮጵያን ማቅናት ላይ አኩሪ ገድል ያለው፣ ታላቅ አስተዋጽኦን ካበረከቱ ጥቂት ነገዶች ውስጥ #ከላይ የሚመደብ ነው።

በዚህ።

ወደ ገደለው - አሁን በዚህ አስቀያሚ ጦርነት ሳቢያ Average ኢትዮጵያዊ ከተጋፈጠው መከራ በላይ ት*ግሬው ተጋፍጧል። ከየትኛውም ክልል በላይ የትግራይ ክልል የፈርኦን ዘመን ዳፋዎችን ተቀብሎ ኖሯል።

አስበው።

ለሁለት አመት ልጆቹን ት/ቤትና ኮሌጅ አልላከም። ብሩን አውጥቶ አስቤዛ እንዳይገዛ ባንክ ተዘግቶበታል። ስልክ ኢንተርኔት ተቋርጦበታል። እንዳይነግድ፣ እንዳይወጣ እንዳይገባ መንገድ ተዘግቶበታል። ደሞዝ አልተሰጠውም። ባጀት አልተለቀቀለትም። አልዘራም፣ አልነገደም። እዚህ ግባ የሚባል ምርጥ ዘር፣ ማዳበሪያና መድሃኒት አላገኘም፤ አልተሰራጨለትም። በላዩ ላይ ህወሃት አልዋጋ ያላትን ወጣት በሙሉ በግድም በውድም በአፈሣ ወስዳ ማግዳዋለች።

እና።

እናማ ጦርነትን እና ረሃብን አንድ ላይ ሲያስተናግድ የነበረ ክልል ሕዝብ ተቸነፈ፣ ጊዜ ጣለው ብለን የቅስም ሰበራና የማቅለል፣ የማዋረድ (Humiliation) ፕሮጀክት ውስጥ ከገባን ነግ በኔን የማናውቅ፣ ያልበሰልን፣ ከታሪክ የማንማር ጉፋያዎች ነን ማለት ነው።

እኔ ልፍረድ።

ወደ ኋላ እንይ። መላውን የትግራይ ስፍራ አጠቃላዩን የትግራይ 52 ወረዳዎችና አራት ዞኖች በተደጋጋሚ ጎቦኝቻለሁ። በስራ የአለም አቀፍ NGO የResearch ጥናት ሃላፊ ሆኜ አጥንቻለሁ። ዞሬ ሰርቼበታለሁ። ሕዝቡን፣ ኑሮውን፣ ባህሉን፣ ውሎውን፣ ደግነቱን፣ አዲስ ሰው ወዳጅነቱን፣ በትክክል አውቀዋለሁ። ከእጁ በልቻለሁ - ጠጥቻለሁ። እንደ ሠው ተከብሬ ተስተናግጃለሁ። ዘርህ ሐማሴን፣ ዘመዶችህ ኤርትራ ናቸው ነው ብሎ የጠላኝ የገፋኝ አልነበረም።

ትግሬውን የማውቀው 22 ላይ ሲጨስ፣ ሲጨፍርና ብር ሲበትን ሳይሆን ትግራይ ላይ ሠርክ ኑሮን ሲገፋና ሲጋፋ ነው።

አንተ ፍረድ።

ከሌላው ክልል #በተለየ መልኩ ከትግ*ሬዎቹ ክልል ሄዶ የሰራ ሠው። መቀሌ/አክሱም/አዲግራት ዩንቨርሲቲ የተማረ ሠው፣ ከትግሬዎቹ ጋራ በክልላቸው የኖረ ሠው፣ ሰዎቹንና ባህሪያቸውን ሲወድዳቸው እንጂ ሲጠላቸው አጋጥሞኝ አያውቅም። ሲናፍቅ እንጂ ሲያማርር ሰምቼ አላውቅም። እንግዳን መውደድ፣ የመሃል አገርን ሰው ማክበር ጥጉና ማሳያው ናቸው። ያያቸው የሚመሰክርላቸው ጥሬ ሐቃቸው ነው። ካየህ ከኖርክ፣ ከተማርክ ከነበርክ ምስክር ነህ አንተ።

ስማኝ የሸገር ልጅ።

አገርህን የምትወድድ ከሆነ፣ ኢትዮጵያን የምታፈቅር ከሆነ፣ ሕዝቦቿ ወገኖቼ ናቸው የምትል ከሆነ፣ በት*ግሬ ዘመድህ ችንፈትና ውድቀት አትደሰትም። አትፈነጥዝም። በቀል እያሰብክ የመጨረሻውን ሳቅ ልገልፍጥ አትልም።

ሞክር።

የድርሻህን ሞክር። የአቅምህን ወርውር። DO Something.

. . . ደውል።

በቅርብህ የምታውቀው የትግራዋይ ወዳጅህ፣ ጓደኛህ፣ ባልደረባህ፣ ጎረቤትህ፣ ደንበኛህ ጋራ አሁኑኑ ደውል። ወይንም ቴክስት ጻፍለት። ጠፋሁበት ብለህ፣ እስከዛሬ የት ነበርኩ ብለህ ሼም #አይያዝህ

ዝም አትበለው።

አዋራው፣ ጠይቀው። ዘመድ አዝማድ፣ ቤተሰቦችህ እንዴት ናቸው ብለህ ጠይቀው። ስራ ላጣ፣ ተሰድዶ ለመጣ፣ ለተፈናቀለ፣ እዚህ ለተቸገረ፣ ቤት ኪራይ ለጎደለው፣ ወይንም እዛ ላለ ሰው ምን ልርዳ ምን ላግዝ ብለህ ጠይቀው። ያቅሜን ልወርውር በለው። እሱ ሼም #ይሉኝታ ስለሚቆልፈው፣ አንተው አደፋፍረው። ከድባቴው አውጣው። አበረታታው። ያልፋል ይሄም በለው። መጣላት መታረቅ በኛ አልተጀመረም ብለህ አስረዳው። . . . ዘር ብሔር ሳትቆጥር መከታ ሁነው።

¤

. [ይሄ መልካምነትህ #ላንተ ሶስት ጥቅም አለው]

1 - የምታምንበት ፈጣሪ ብድራትህን ይከፍልሃል።
2 - የምትወዳት አገርህ ላይ ቂምና ቁርሾ ትቀንሳለህ።
3 - ህሊናህ፣ አእምሮህ ሰላም ያገኛል።

-

. . . ማን ያውቃል - ነገ የዚህ ገበሬ ስድራ ገዛ፤ የዚህችን ምንም የማታውቅ ንጽህት ትግራወይቲ ህጻን የወደፊት እጣፈንታ ላይ የተስፋ ጭላንጭል ያበራኸው አንተ ትሆን ይሆናል።

¤

“Love and kindness are never wasted. They always make a difference. They bless the one who receives them, and they bless you, the giver.”

– Barbara De Angelis

📝Eyob Mihreteab

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
💎መዘግየትህን አትጥላው!

ነገሮች በፍጥነት እንዲሳኩልህ አትፈልግ! መዘግየትህን አትጥላው! በትምህርት፣ በስራ፣ በሀብት፣ በፍቅር ግንኙነት ወይ በትዳር አንተ እንዳሰብከው አለመሆኑ ለበጎ እንደሆነ አስብ።

💡ልብ እንበል!!

ጉንደን ካስበችው ለመድረስ ሺ ጊዜ ከምሰሶው ላይ ትወድቃለች።

ንብ ጣፋጩን ማር ለመጋገር ሚሊዮን ጊዜ አበቦች አካባቢ ትመላለሳለች:: ወዳጄ ስኬት ትኩረትንና ትእግስትን ይጠይቃል..

🕰ወደ ኋላ የተንደረደረ ረጅም ርቀት እንደሚተኮስ አስብ፤ ወዳጄ ጥያቄህ ቶሎ ያልተመለሰው ጊዜው ስላልደረሰ ወይ ደግሞ ፈጣሪ የተሻለውን ሊሰጥህ ይሆናል። አንተ ብቻ ጥረትህን ሳታቋርጥ ታገስ፤ የህይወትህ ፀሀይ መውጣቷ አይቀርም!

💎ፋንዲሻ እንዴት አማርሽ ቢሏት እሳቱን ስለቻልኩት አለች ይባላል ፣ በህይወት መስመር ስኬትን ለማግኘት የግድ መከራውን ማለፍ አለብን!!

ውብ ምሽት!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍ደስታ የምኞት ውጤት፣ የማሳደድ ትርፍም አይደለም። ደስታን ተመኝቶ ያገኘ፣ አሳድዶ የያዘ የለም።

🔶ደስታ ከገንዘብ ብዛት፣ከስልጣን ሹመት፣ ስጋዊ ስሜትን ከማርካት ወይም ከሳይንስ አይመነጭም፡፡ ደስታ በቁጥር አይመጠንም፡፡ መጋዘኖች አያከማቹትም፡፡ ዩሮ ወይም ዶላር አይገዛውም፡፡ ደስታ ከውስጥ የሚሰማ ነገር ነው፡፡ የነፍስ መስከን፣ የቀልብ መረጋጋት፣ የልቦና መስፋት፣ የሕሊና መርካት ውጤት ነው፡፡የአዕምሮአችንን ተፈጥሮ በትልቅ ተረድተን ከተጠቀምበት እውነተኛ ደስታ እና ነፃነት ማግኘት እንችላለን ፡፡

🔷አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው።ምክንያቱም አንተ ያለህን ሙሉ ጤና የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።

ቁሉፉ ነን እኛ…የራሳችን ደስታ
ውብ አሁን!!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💎ጊዜ ሰታችሁ ቀና ምልክታችሁን ስላከፈላችሁን ክበሩልን።ብርታት ስለሆናችሁንን ከልብ እናመሰግናለን።

ፈጣሪ ያክብርልን  🙏

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
🌗የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ!!

🌬እዚህች ምድር ላይ ስንኖር በትንሹም ይሁን በትልቁ በየደቂቃው እንለዋወጣለን። ቢታወቀንም ባይታወቀንም ነው እንግዲህ ቢያንስ ገላችን የበላውን ያንሸራሽራል፣ ሕዋሳት ይሞታሉ ይወለዳሉ። ቢያንስ አንዲት ፀጉር ትበቅላለች ወይም ትረግፋለች። ፊኛችን ሳያቋረጥ በፈሳሽ ይሞላል። ጊዜው ሲደርስም ይጎላል።

ሕይወት እንግዲህ እንዲህ ነው፤ ይሄ ዑደትና የዝግመት ለውጥ አይበቃንምና ደሞ አንዳንድ ጊዜ እጅግ የሚለውጠን ቀውስ ይመጣብናል ገላችን፣አዕምሮአችን ይታመማል እንረበሻለን፣እንጨነቃለን።ሕይወት እንግዲህ ይሄ ነው ሰው በግሉ፣ ሕብረተሰብም ተፈጥሮው ይመስሉኛል።

📍ይሄን ደጋግሜ መገንዘቤ፣ደጋግሜም በነዚህ ሁኔታዎች ውስጥ ማለፌ ያስተማረኝ ነገር አለ።መረባበሽ ፋይዳ እንደሌለው የተረጋጋ ታዛቢ፣ የመነኩሴ አመለካከት አለኝ። ከፍ ዝቅ ያለ ነገር ሲያጋጥመኝ በረጉ ዓይኖቼ አያለሁ። በቀዘቀዘ መንፈስና አካል እቀበለዋለሁ እንደሚለወጥ ስለማውቅ!"የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ" ሲሉ አዛውንት ዝናቡን ፍራው ማለታቸው አይደለም። ዝናቡን ማወቃቸው ነው። የተወሰነለት ዕድሜ አለው፣ ያውም አጭር ማለታቸው ነው። ሰው ቢያንስ በተስፋ የችግሮቹን ዘመን ያልፋል ማለታቸው ነው።

/ከአዳም ረታ አንደበት/

🌪በእርግጥም የሚገጥሙንና የሚያጋጥሙንን ክስተቶችና ፈተናዎች መወሰን ባንችል እንኳን፣ ምላሻችንንና ግብረ-መልሳችንን መወሰን እንችላለንና ዘወትር የመጣው እስኪያልፍ፣ የቀለጠው እስኪ ረጋ፣ የነደደው እስኪ ከስል፣ በሰከነ አዕምሮ፣ በተረጋጋ መንፈስ፣ በአንድ ልብ መቀበሉንና ማሳለፋን እንወቅበት።

       ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
💫አፍርሰህ አትገነባም.

የሄደ ነገር ተመልሶ ይመጣል። ሰብረህ ያጠፍኸው የመሰለህ ነገር ይዘገይ ይሆናል እንጂ አይቀርምና አፀፍውን መልሶ ሊያስታቅፍህ ምንአልባትም እጥፍ ድርብ አድርጎ ደጃፍህ ላይ ቆሞ በርህን ያንኳኳል። ኃላፊነት በንግግር፣ ተግባርና ሁሉም መስክ ላይ እንዲንፀባረቅ የተገባው በእዚህና መሰል ምክንያቶች ነው።

💡እርግጥ ነው ኃላፊነትን በፀጋ መቀበል እና ሳይሸራርፉ በተጨባጭ መወጣት ፈታኝ ነው። አስተዋይ አእምሮ እና ቅን ልቦና በምርጫና መንገድህ ካልተለየህ ግን በድል ትወጣዋለህ። ድሉም ከበደል የፃዳ ይሆናል። ድሉ ከራስህ አልፎ አለምን ስለሚጠቅም መልካሙ ስርህ ሄዶ ዞሮ ሲመለስ በጎ ምላሽ ማግኘትህ አይቀሬ ነው። ወርቅ ለሰጠ ወርቅ እና ጠጠርም ለሰጠ ጠጠር ማግኘት ተፈጥሯዊ ህግና የህይወት ነባራዊ እውነታ ነውና።

💎መልካምነት ከማንም በላይ ላራስ ነው ጥቅምና ፍይዳው። ቅን ሀሳብ አሳቢውን ይባርካል። ሴራ፣ ተንኮል እና ክፍት ህሊናና ልብህን ከሞላው ግን ሌላው ይቅርና መልካም እንቅልፍ እንኳ ብርቅ እና ሩቅ እንደሚሆኑብህ ልነግርህ እችላለሁ።

🔆አዳርህ በመባነን እና መበርገግ ይሞላል። ቀን ያሳደድከው በህልምህ መግቢያና መሸሸጊያ ጥግ ያሳጣሀል። ቀን ከሌት የዘራሀቸው ክፋቶች ሌሎችን ብቻ ሳይሆን የአንተን የገዛ ራስህንም ገላም ይቧጥጣሉ። ከአንተ የመነጨና ተንደርድሮ የተተኮሰ ኃይል በእኩል መጠን እና ልክ አጥፊ እንደሆነ ራስህንም ያጠፍል፤ አልሚ ከአደረከው ደግሞ ቅድሚያ አንተን እና የእኔ የምትለውን ሁሉ ባርኮ ለሌሎች ይተርፋል።

ይህ የህይወት ሀቅ ከፊዚክስ action/reaction ተፈጥሮአዊ ህግ ጋር ይመሳሰላል። አፍርሰህ አትቆምም። ጠልተህ ፍቅርን አታተርፍም። ወደህ ላትከበር፣ ትህትናን ሰጥተህ ልትናቅ፣ አሳቢና አስታዋሽ ሆነህ ሳለ ልትረሳ አትችልም። ምክንያቱ ደግሞ ምዕራባዊያን እንደሚሉት የሄደ ነገር ተመልሶ ይመጣልና ነው (what goes around comes around)። አበውም አሳ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል፣ የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል፤ በቆፈሩት ጉድጒድ መቀበር አይቀርም ወዘተረፈ ብለውናል።

ነጋሽ አበበ

ሰናይ ምሽት ይሁንልን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
በአንዲት ትንሽየ ከተማ ውስጥ ለብዙ ዘመናት ማራኪ ስዕሎችን በመሳል ለከተማዋ ነዋሪዎች እና ከሩቅ አካባቢ ለሚመጡ እንግዶች በጥሩ ዋጋ እየሸጠ ደስታ የተሞላበት ሕይወት የሚኖር አዛውንት ነበር። ከዕለታት አንድ ቀን በከተማዋ ውስጥ ከሚገኙ ድሃዎች
መካከል አንዱ መጣና ሰዓሊውን «በሥራህ ብዙ ገቢ እያገኘህ ለምንድን ነው በከተማዋ ያሉ የኔ ቢጤ ደሃዎችን ለመርዳት ንፉግ ያደረገህ ??...

የዚያ ልኳንዳ ቤት ባለቤት እዚህ ግባ የሚባል ገንዘብ ሳይኖረው ለድሃዎች በየቀኑ ስጋ ያድላል፤ በተመሳሳይ ሁኔታ የዚያ ዳቦቤት ባለቤት ዘወትር በየቀኑ በነፍስ ወከፍ ለድሃዎች ዳቦ ይሰጣል» በማለት ጠየቀው። ሰዓሊው ምንም መልስ ሳይሰጠው በሰከነ መንፈስ ታጅቦ በስሱ ፈገግ አለ።

ድሃው በሰዓሊው ዝምታ ተበሳጭቶ ከቤቱ ውስጥ ተስፈንጥሮ ወጣ። ወደ መሃል ከተማ በመገስገስ አላፊ አግዳሚውን እያስቆመ «ሰዓሊው ብዙ ኃብት ቢያከማችም ድሃወችን
ለመርዳት ፍላጎት የሌለውና ስስታም ነው» በማለት ወሬ መንዛት ጀመረ። የአካባቢው ነዋሪዎች በሰዓሊው ላይ ጥርስ ነከሱበት። ማህበራዊ መገለል ደረሰበት። የሚያናግረው አንድ ሰው እንኳ አጣ።

ከተወሰኑ ቀናት በኋላ አዛውንቱ ሰዓሊ ክፉኛ ታመመ። ከአካቢቢው ነዋሪዎች መካከል አንድም ሰው ትኩረት የሰጠው አልነበረም። ከጎኑ ማንም ሳይኖር ብቻውን ሞተ።

ቀናት በንፋስ ፍጥነት ነጎዱ። የከተማዋ ነዋሪዎች የልኳንዳ ቤቱ ባለቤት ለድሃዎች በነጻ የሚያድለውን ስጋ እንዳቆመ አስተዋሉ። የዳቦ ቤቱ ባለቤትም ለሚስኪኖች በነጻ
የሚያከፋፍለውን ዳቦ እንዳቋረጠ ተገነዘቡ። ድሃዎቹ በልኳንዳ ቤቱ በር ፊት ለፊት ቆመው የለመዱትን ስጋ ለማግኘት ቢማጸኑም ሰሚ አጡ። በዳቦ ቤቱ መስኮት ዙሪያ ቢያንዣብቡም
ለስም እንኳ የሚያዳምጣቸው አንድ ሰው አጡ።

የከተማዋ ነዋሪዎች ተሰብስበው የልኳንዳ እና ዳቦ ቤቶቹን ባለቤቶች «ዘወትር በየቀኑ ለድሃዎች ትሰጡ የነበረውን ስጋ እና ዳቦ ለምን
አቆማችሁ» ብለው ሲጠይቋቸው «በየቀኑ ለከተማዋ ድሃዎች በነጻ የምንሰጠውን የስጋና ዳቦ ዋጋ በየወሩ የሚከፍለን አዛውንቱ ሰዓሊ ነበር። ከሱ ህልፈት በኋላ ክፍያ የሚፈጽምልን
ሰው ባለመኖሩ በነጻ ማደሉን አቋርጠነዋል» በማለት ወሽመጥ ቆራጭ ምላሽ ሰጧቸው።

💫የተወሰኑ ሰዎች ባንተ ላይ ክፉ ጥርጣሬ ሊያሳድሩ ይችላሉ። አንዳዶች ደግም እንደ ሐጫ በረዶ የጠራህ አድርገው ሊስሉህ ይችላሉ። ሁለቱም አይጠቅሙህም። አይጎዱህምም።
ቁም ነገሩ ያለው ፈጣሪ ስላንተ የሚያውቀው ትክክለኛ ማንነትህ ላይ ነው። ለክፉ አሳቢዎች ክፋ ምላሽ ላለመስጠት ጥረት አድርግ።

🌔 ደግነትህ ለብዙዎች የዕድሜ ማራዘሚያ ሰበብ ስለሆነ እንዳይከስም ጠብቀው። ለጋስ በመሆንህ በምላሹ ከሌሎች ምንም ነገር አትጠብቅ። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ መልካም ነገር ሁሌም ከፈጣሪህ በጎ ምላሽ አለው።
ህሊናህ ይረካ ዘንድ ከመቀበል ይልቅ ሰጪ ሁን። በምግባርህ ፈጣሪህን ለማስደሰት ሁሌም ጥረት አድርግ። እርሱ ከወደደህ ደስታ በእጅህ ትገባለች።በመልካም ስነ ምግባር ሽቶ የተርከፈከፈ ስብዕና ከመሬት በታች አፈር ለብሶ እንኳ መዓዛው ያውዳል።
               
ውብ  አሁን❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💡'እኔ ማን እንደሆንኩኝ አታውቅም, ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ'

'She doesn't know who I am, but I know who she is

💎 የ85 አመት አዛውንት ናቸው ከ 60 ዓመት በላይ ከባለቤታቸው ጋር በትዳር ኖረዋል, ባለቤታቸውን በሄዱበት ሁሉ እጃቸውን አጥብቃ እንድትይዛቸው ባለመሰልቸት ይጠይቋታል, ስትቆም ቆመው ስትቀመጥ ተቀምጠው ስታስቸግር አብረው ተቸግረው . . . ሳይሰለቹ የድሮ ፍቅራቸውን ሳይቀንሱ በ 85 ዓመት የአዛውንት ጉልበታቸው አሁንም በትዕግስት አብረዋት አሉ :: ሰዎች ሚስታቸው ምን ሆና እንዲህ እንደሆነች ይጠይቃሉ “አልዛይመርስ' የመርሳት በሽታ አለባት” ሲሉ ይመልሱላቸዋል

💡እና ምንም አታስታውስም ? ምንም !ያን ሁሉ ዓመት የሕይወት ውጣውረዳችንን,ደስታችንን ሀዘናችንን ወልደን ኩለን መዳራችንን ዘመድ አዝማድን ኧረ እኔንም ዘንግታኛለች
እናም "ሚስትህ እጅህን ብትለቅህ ትጨነቃለህ ማለት ነው ?" ለምን አልጨነቅም ምንም ነገር ማንንም አታስታውስም እኮ በዚህ ዓለም ያላትን ነገሮች ሁሉ ረስታለች እኔንም ጭምር , ለብዙ አመታት አላወቀችኝም እና ያለኔ ማን አላትና ነው የማልጨነቀው ?!

💎 "እናም አንተን ባታውቅህም በየቀኑ መንገድ ላይ እየመራሃት ትቀጥላለህ" ማለት ነው ,
ፈገግ አሉና አይኖቼን እምባ ባቀረሩ አይናቸው እየተመለከቱ . "እኔ ማን እንደ ሆንኩኝ አታውቅም ግን እኔ ማን እንደሆነች አውቃለሁ " ውዷ ከ 60 ዓመት በላይ ብዙ ነገር የሰጠችኝ ሕይወቴ ናት " እናም ሕይወቴን ሙሉ በሄደችበት ሁሉ አብሪያት አለሁ , ሰው ካለ ህይወቱ ምን ሕይወት አለው ... እከተላታለሁ።

መልካሞችን ሁሌም ያብዛልን።

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
📍መስጠት ካልቻልኩ መቀበል አይሆንልኝም "

🔵ደግነት ልቤ ውስጥ በተዘራ ጊዜ ፍሬውን አጭጄ እሰበስብና ለተራቡት እሰጣቸዋለሁ . . .ነፍሴ የወይን ፍሬ ባበቀለች ጊዜ ፍሬዎቹን ጨምቄ የተጠሙትን አጠጣቸዋለሁ ::

🟢ውስጤ በብርሃን በተሞላች ጊዜ የውስጤን ፋኖስ የመስኮቴ ጫፍ ላይ አስቀምጣትና በጨለማ ለሚጉዋዙት ብርሃን እሆናቸዋለሁ :: ጥላቻን ከልቤ ያጠፋልኝ ዘንድ ሁልጊዜም የፍቅርን ችቦ መጨበጥ እሻለሁ ::

🟡ሰዎች በዘርና በቀለም ተለያይተው በተለያዩ አህጉራትና ሀገራት ይኖራሉ ,,,,, እኔ ግን ለሁሉም ማህበረሰቦች እንግዳ ነኝ ከየትኛውም ሀገር አልወግንም። መላው ዓለም ሀገሬ ነው፣
የሰው ልጅ ሁሉ ወገኔ ነው ።

🔴የአዳም/አደም ልጆች ደካማ ሆነው በተለያዩ ጉዳዮች መከፋፈላቸው የሚያሳዝን ነው , ዓለም ሳትከፋፈልም ጥብብ ያለች ናት ይህችን ጠባብ ዓለም በግዛት ፣ በሰፈር፣በአውራጃ መከፋፈሉ በአላዋቂነት የታጀበ ሞኝነት ይመስለኛል . . . . !

"ካህሊል ጂብራን"

ውብ ምሽት ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔑የማንፈልገው ነገር ባይኖር የምንፈልገውም አይኖርም !

📍ልዩነት የምንወደው ሳይሆን የምንቀበለው ነው ። ማንም ለራሱ ሀሳብ ቅድሚያ ቢሰጥ ፣ ተቃራኒውን ለመቀበል ደስታ ባይታይበት አይገርምም ። " የእኔ ሀሳብ ወይም ሞት ! " ማለት ግን ራስን ማስቀደም ሳይሆን ልዩነትን ማጥፋት ነው ። ይህ እውነትን ለመስቀል ገመድ ማዘጋጀት ይሆናል   የወደድነውን ያገኘነው ካልወደድነው መሀል መርጠን መሆኑን ልብ ማለት ያሻል ።

🛑 እኛ የወደድነው ብቻ ቢኖር ፣ የምንጠላው ወይም የማንወደው ባይኖር የምንወደውን መውደዳችንን በምን እናውቀው ነበር  ? የምንጠላውን የሚወዱት እንዳሉ መረዳት ብቻ ሳይሆን ለምንወደው ነገር ማነፃፀሪያ እንዲሆነንም ያስፈልገናል ። የማንወደውን ነገር ከማጥፋት ለሚወዱት መተው ያስፈልገናል ።  የምንፈልገው ነገር መኖሩን ያወቅነው የማንፈልገው በመኖሩም ጭምር ነው ።

                ቴዎድሮስ ተ/አረጋይ

           ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
ለጁምኣችን!
💚

" መወደድም ሲሳይ ነው" አሉ ። ምነው ቢሉ ነብዩ ዩሱፍን ዓ.ሰ (ዮሴፍን) አርቀው የጣሉት የገዛ ወንድሞቹ ፥ አንስተው ያከበሩት መኳንንት ባዶቹ ።

መውደቅ መጨረሻ አይሆንም ፥ ምነው ቢሉ ዮሴፍ ዓ.ሰ ለንግስና የታጨው እስር ቤት እያለ ነውና ፥ መነሳትም ተክትሎታልና ።

ሰው ኹሉን አወቅ ነኝ ይላል እንጂ ስለ ህልውናው በመተርጎም ፥ ውስጥ ውስጡን ትርጉምን ሁላ የምታስከነዳ ገራም የመለኮት ሥርዓት አለች ።መታገስ ነጃ ያወጣል ምነው ቢሉ የመለኮት ሥርዓት ኹሉን በገራምነት እንደምታስከነዳ ማመን ነውና ።

📝ሰለዲን አሊ

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
❤️ሁሉም ሰው ዋጋ አለው!

💎ሰው የሚሰጥህ ክብር አንተ ለራስህ በምትሰጠው ሚዛንና መጠን ነውና ለራስህ ትልቅ ዋጋና ብዙ ክብር ይኑርህ፣ ማንኛውም ሰው በማንኛውም አይነት ስራ ዘርፍ ቢሰማራ የተወሰነ ቀናት እስኪለምደው ይቸገራል እንጂ ስራውን የማይወጣበት ምንም አይነት ምክንያት የለም !

💡ዕድሉን ስላላገኘ እንጂ ሰው ሁሉ ወሳኝ ጠቃሚ ነው ነገር ግን በሌሎች ዘንድ ቦታውን ባለመግኘቱ እና ተቀባይ ባለመኖሩ ሊወድቅ ይችላል !ሰው ቦታን ይለምዳል እንጅ ቦታ ሰውን አይለምድም !ከደካማ ስር ብትሆን ማንነትህ አይወርድም እንዲውም ምርኩዝ ትሆነዋለህ !ከጠንካራ ጎን ብትቆም በሱ ወንበር አትመራም በራስህ ህሊና እንጅ !

💎ሰውን በአስተሳሰቡ እንጅ በፍፁም በአለባበሱ አትመዝነው፡፡ ምክንያቱም ሰው ቦታን ይቀይራል እንጅ ቦታ ሰውን አይቀይርም! ጠንካራ ሰዎች ሌሎችን ከፍ እንጅ ዝቅ አያደርጉም እና  ጠንካራ ከሆንክ ለሰው ትልቅ ቦታ ስጥ ብዙ ዋጋም ይኑርህ።

🐝 Bee A Good Human

Our life can be translated into love,We can color our whole life with kindness, transforming our everyday activities and ejoying our everyday ways of being with human warmth. Our Life Can Be Translated into Love.

💙እራስህን በሰላም ፣ በብርሃን ፣ በጥበብ ፣በንቃተ-ህሊና ሸፍነው፡፡የአንተ ሃላፊነት ይህ ነው ፡፡ደስታ እና ርህራሄ በህይወት መንገድህ አይለዩህ፣ ከተፈጥሮ ጋር እጅ ለእጅ ተያይዘህ ኑር  ፡፡ይህን ለማድረግ ሁሌም ከልብህ ጀምር።ሁሌም ይህን አድርግ፣ሁሌም ይህንን ሁን ፡፡

  ፏፏቴ የሆነች ቅዳሜን ተመኘን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💡ሕይወት በ’የኔ’ እና ‘የኛ’ የምናሳንሰው ነገር የላትም… ከጽንፍ አልባው ምልዓት ላይ በተገለጸልን ልክ የገባንን ሁሉ የእኔ/ኛ አንልም… እኛ ራሳችንን ያንን ምልዓት አይደለን? “You are not a drop in the ocean; you are the entire ocean in a drop” ይላል Rumi

❤️ ይህን ሁለንተና በግላዊነት መያዝ አይቻልም… የኔ ብሎ ማሳነስ አይቻልም… እኛው ራሳችን ሁለንተናውን ነንና ፣ ብዙ የአለማችን እሳቤዎች ከሕይወት በተናጥሎ የመኖርን ቅዠት ይሰብካሉ… ውቅያኖሱን ሆነህ ሳለ የውቅያኖሱን ‘አንድ ጠብታ ወስደህ’ የኔ ማለት ከራስም ያሳንሳል…ከራስህ ተነጥለህ ‘የራስህ’ ሊኖርህ አይችልም።

💡የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን ፣ከኔ ቤት ላይ የረጨኸው እሳት ከሆነ ነበልባሉ ያንተን ቤት ይነካል ሽቶ ስትረጨኝ የመዓዛው ቅንጣቶች ለአፍንጫህ ውብ ጠረን ይለግሳል ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል ይህን ምስራቃውያኑ Karma ሲሉት ሌሎች ደግሞ Boomerang ይሉታል Boomerang አውስትራሊያኖቹ አቦርጂኒስቶች ከእንጨት የሚሰሩት ደጋን ቅርጽ ያለው የአደን መሳሪያ ሲሆን ወርዋሪው ዘንድ ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጎ የሚነደፍ ነው… ለሃሳብ፣ ለስሜትና ድርጊትህ መጠንቀቅ የሚኖርብህ ወላፈኑ ‘ለእኔም’፣ ‘ለእርሷም’፣ ‘ለእነርሱም’ እንደሚተርፍ በማሰብ ነው ምክንያቱም We are all One!

💎በረከት በላይነህ "የመንፈስ ከፍታ" ላይ እንዲህ ይለናል
“የግልህ ወንዝ ስለሌለህ ብቻህን የምትሰራው ድልድይ የለም! የሰማዩ ርቀት፣ የምድሪቱ ስፋት በ’እኛ’ እንጂ በ’እኔ’ አይለካም፡፡ ውዱ ‘እኔ’ ከ’እኛ’ የተሰራው ነውና!”

ደምስ ሰይፉ

           ውብ አሁን!!❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
2024/11/15 18:09:07
Back to Top
HTML Embed Code: