Telegram Web Link
ደስታ ቢራቢሮ ሲሆን፤ ለመያዝ ብንሞክር የማይጨበጥ....ነገር ግን ፀጥ ብለን ስንቀመጥ ከአጠገባችን ብልጭ የሚል ነው።

🦋ለደስተኝነት አንድ መንገድ ነው ያለው። እሱም ከምኞታችን አቅም በላይ በሆኑ ነገሮች ላይ መጨነቅን ማቆም ነው። እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ እርግጠኛ ሁን ሊመጣ ያለውም አያረካህም። በበርሃ አበባ ሳትፈነድቅ በገነት ውበት አትመሰጥም። የፍላጎት ስሌትህን ወደ ጎን አርገውና፣ ስለ ንጋት ፀሀይዋ መሞቅ ፣ ስለ ቀኑ ብራነት፣ በነፃ ስለምትተነፍሰው ውድ አየር፣ ደክሞህ እንኳ ሰለማይደክማት ልብህ፣ በዙሪያህ ስላሉት ወገኖች፣ ይህንን ማንበብ  እንኳ ስላስቻለህ አይንህ ስታስብ ...
.
.
.
በደንብ ስታጤን ... በእርግጥ ከሌለህ ይልቅ ያለህ ብዙ እንደሆነ ትረዳለህ ፡፡ ያኔ እድለኝነት ይሰማሀል፡፡ ያኔ እንዳልጎደልክ ይገባሀል .... ያኔ አመሰጋኝ ትሆናለህ....

💎 የራስህ አመለካከት ሲጠራ ደስታህና መልክህ እንደፀሓይ ያበራል። በቁስ ያልተደገፈ ደስታ ውስጥህን ይሞላዋል፡፡ ነገ ራሱ የብዙ ዛሬዎች ድምር ነውና ለደስታህ ቀጠሮ አትያዝለት ...
የደስታህ ጊዜ አሁን ነው።

https://youtu.be/C6qboCAhUEY?si=i8VvdJ8aiDpEeK0P

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍ፔሩሉስ የተባለ ቀራጺ ባለእጅ ነበር። ካላጣው መሣሪያ ሰዎችን የሚጠብስና የሚያቁላላ የመዳብ ኮርማ ተጨንቆና ተጠቦ አበጀ። አገኘሁ ብሎ ፋላሪስ ለተባለ ጨካኝ ግሪካዊ ገዥ "እንሆ በረከት" በማለት ሰጠው። ፋላሪስ ይህን የመዳብ ኮርማ ሲያይ ተገረመ፤ ለአማልክቱ እጅ መንሻ፥ መባ አደረገው። ይህ የመዳብ ኮርማ በሆዱ በኩል ይከፈታል። ሰው በውስጡ ይጠበስበታል። በስተ ጉሮሮው በኩል ደግሞ ሰውዬው እየጮኸ ሲሰቃይ ይህን ድምፅ ወደ ኮርማ ድምፅ የሚቀይር ሽቦ ተበጅቶለታል።

💡ታዲያ ፔሩሉስ ሆዬ የኮርማውን ሆድቃ እየከፈተ "ፋላሪስ ሆይ፥ ያሻህን ሰው በኮርማው ውስጥ ጠርቅምበትና በሥሩ እሳት ልቀቅበት፥ ሰውዬው የሰቆቃ ድምፅ ሲያሰማ አንተ "እምቧ" የሚል የኮርማ ድምፅ ትሰማለህ” አለው። ፋላሪስም ይህን ካደመጠ በኋላ "ቀራፂ እንኪያስ ፔሩሉስ ሆይ፥ ና፥ አንተ መጀመሪያ ግባና አሠራሩን አሳየና" በማለት ግልፅ እንዲያደርግለት ፔሩሉስን በማታለል ወደ መዳቡ ኮርማ ይገባ ዘንድ ግድ አለው። ፔሩሉስ "እኔ ምንተዳዬ፥ ለሚቃጠለው ይብላኝለት" እያለ ጕረሮውን እየጠራረገ ገባ።

♦️ፋላሪስ የፔሩሉስ መሣሪያ አሽሙር ሳይመስለውም አልቀረም። ጨካኝ ሕፃናትን እንኳን ሳይቀር የሚበላ ርህራሄ የሌለው ገዢ ነበርና። ፔሩሉስም እንደ ገባ ይሄው ጨካኝ ገዥ በሥሩ የሚንቀለቀል እሳት ለቀቀበት። በመዳቡ ኮርማ ሆድ ውስጥ ያለው ፔሩሉስ ሆዱ ተላወሰ። ላንቃው እስኪበጠስ የምሩን ጮኸ።

ፋላሪስ "የታባቱንስ ይህ ከብት፤ ጨካኝ ነህ ማለቱም አይደል" እያለ ከዚያ የመዳብ ኮርማ ሩሑ ሳይወጣ አስወጣው። ያስወጣውም አዲሱ መዳብ ከጅምሩ እንዳይጨቀይበት ብሎ ነው። ከዚያም ከገደል አፋፍ አውጥቶ ወረወረው። የፔሩሉስ ዕጣ ፈንታ ይህ ሆነ።

💡በዚህ መሣሪያ የብዙዎች ሕይወት ተቀጠፈ። ጭስስ ብሎ የታቃጠለ ዐጥንታቸውም እንደ አልቦና አንባር ያገለግል ጀመር። የሚገርመኝ ይህ አይደለም። በፋላሪስ ላይ ቴሌማኹስ የተባለ ሌላ ጨቋኝ ገዢ ተነሣበት። እርሱንም ይዞ ከመዳቡ ኮርማ ከተተው፤ አቃጠለውም።

🔑እናም አማካሪ ሆይ፥ ስትመክር ጠንቀቅ ብለህ ምከር። ገዢ ሆይ፥ በጭካኔ መንገድ መሄዱ ይቅርብህ።

ናምሩድ

ማለፊያ የሆነች ቅዳሜን ተመኘን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍ሰው አገሩ ሰፈሩ ነው ህዝቦቼ እያለ ያደገው ጎረቤቶቹን ነው ።ማንነቱ የተጎነጎነው ከጎረቤቶች ማንነት እየተውጣጣ ጭምር ነው። ከሰፈር አግብቶ መውጣት በስራ ሌላ ቦታ መሄድ እና ያደክበት ስፍራ ሲፈርስ ልዩነቱ የትዬለሌ ነው ።

እሚፈርሰው ሰፈር ውስጥ ትዝታ ልጅነት ታሪክ ተጠቅልሏል ። ማህበራዊ ህይወት ያቆመን ህዝቦች ማህበራዊ ህይወታችን ሲበተን ማየት ድባቴው ካቅም በላይ ነው።

ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው ህልሙ ነው!
ምን አልባት እኛ ያለን የሆነ ሰው ፀሎቱ ነው !
ምን አልባት እኛ ያለፈን የማይጠቅመን ነው!
ምን አልባት ያሳመመን ሊያስተምረን ነው!
ምን አልባት የሆንነው የሆኑትን እንድንረዳ ነው !
ምን አልባት የተበለሻሸው እንድንቀያይረው ነው!
ምን አልባት አማራጭ ያጣነው አማራጭ እንድናመጣ ነው !

"እኛ በህይወት ካለን ሌላ ካዛንቺስ እንገነባለን ፣ መኖር እስከነ-ትግሉ እስከነ ፈተናው ደስ ይላል"።

                       አዳህኖም ምትኩ

  የካዛንቺስ ውብ ፈርጥ አለማየሁ ገላጋይ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💫May this Serve as a living tribute,
To Fendika Art Center.

Words of wisdom,
Shared by Melaku Belay ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍ተከታይህ ከህሊና ድህነት አያድንህም፤ ሃብት ንብረትህ አስተሳሰብህን አይቀርፅም፤ ወዳጆችህ ውስጣዊ ሰላም አይሰጡህም። በእውነት ካልተመራህ፣ በስረዓት ማሰብ ካልቻልክ፣ ጥያቄህን ካልመረጥክ፣ ተግባርህን ካልቆጠብክ ጉዞህን እንጂ መውደቂያህን አታስተውልም፤ ጭብጨባውን እንጂ ስህተትህን አትረዳም፤ ድጋፍህ እንጂ ጥፋትህ አይገባህም።

አዕምሮህን ክፍት ማድረግህ ሚዛናዊ ማንነት እንዲኖርህ ያደርግሃል። መስማት የሚፈልግ ሰው ሁሉ ይሰማህ ይሆናል፤ የሚወድህም ይከተልህ ይሆናል፤ የሚያምንብህም እንዲሁ ሊያሽቃብጥልህ ይችላል። እውነታ በሌለበት ግን ማንም ሰው እስከመጨረሻው አብሮህ እንደማይቆይ እወቅ። ጥልቁ ማንነትህ እንጂ የያዝከው ጊዜያዊ ንብረትና ዝና ነፃ አያወጣህም።

🔷ስትታወቅና ከፊት ስትሆን በእውቀት እና በጥበብ ካልተጓዝክ ብዙ ነገር ታበላሻለህ፡፡ በሰዎች ሙገሳና አድናቆት በሞቅታ መስመር ትስታለህ፡፡ ዛሬ ላይ  ሶሻል ሚዲያ ላይ ብዙ ተከታይ ለማግኘት ካሰብክ ካንተ ሚጠበቀው  ለገንዘብ ተገዝተህ ወጣ ያለ አቋም መያዝ፣ ሌላ ፆታን ማራከስ፣ ሌላውን ብሄር  በመጥፎ ማውገዝ ነው። ያኔ ማን ይሆን እሱ! እያለ ሁሉም ካለበት ቦታ እየሮጠ ይመጣልሃል።

♦️ወዲህ ግን ቁምነገር የሚጽፉ ተከታያቸው ጥቂት ብቻ የሆኑ ጠንካራ የማህበረሰብ አንቂዎች አሉ። ግና ሰው ስለራሱ ነውርና እንከን ለመስማት የሸሸበት የረሳበት ዘመን ላይ ነው ያለነው። ከዕውቀት ከጥበብ ይልቅ ስላቅና ፣ ዘለፋን  ያስበለጠበት ዘመን ላይ እንገኛለን። እስቲ ይሄን ሥልጣኔ ያለንበትን ነገር በጥሞና ተመልከቱ። የዘመንኛው ቁሳዊ ሥልጣኔ ግኝቶችን ልብ እንበል። ዓለም ላለባት ችግር መፍትሔ ከመሻት ይልቅ፤ ግኝቶቹ ራሳቸው ከምንም የከፋ ችግር እየሆኑ እንዲያውም የቀደሙትን ችግሮች እስከማስረሳት ደርሰዋል። ግኝቶቹ ከሚያስከትሉት ጠንቅ ይልቅ በግኝቶቹ የሚገኘው ኃይል ገንዘብና ዝና ይበልጥ ትኩረት ተሰጥቶታል ።

🔑እናም ወዳጄ ቁምነገሩን ስንቅ አርግ

ዋናው ጉዳይ የሰው ክትትል ወይም ጭብጨባ አይደለም፤ ከፈጠረህ አምላክ አንፃር ትክክል ከሆንክ የፍጡራን ክትትል አያሳስብህ። ፊት መሆን በሚችል ስብዕና ከፊት ቁም፣ ጊዜህን አፍ በመካፈት አትብላው፣ አለምን የገዙ ፣ በአስተሳሰብ ሊቅነታቸው አርአያነታቸውን የምንከተላቸው ፈላስፎች ፣ ተመራማሪዎች፣ የህይወት መንገድ እያመቻቹልን እነሆ በዚህ ተጓዙ፣ ያኛው የብዝኋኑ መንገድ አሜኬላና እንቅፋት አለው። የዓለም ምስጢራት የሚገለጡት በስውር መስመር ነው እያሉ አመላክተውናል።

ለሰው ልጅ በተሰጠው ወንበር ላይ ቁጭ ብለን ሰው የመሆናችንን፣ ሰው የመባላችንን ልዩ ገፀ-በረከት የሚያጎናፅፉን ሀብቶቻችን እንከተል።

💡ህሊና ይፈርዳል፣ የእራሱን ብይንም ይሰጣል። ስለተጨበጨበልህ እውነት ተናግረሃል ማለት አይደለም፤ ተቃውሞ ስለበዛብህም ውሸት ተናግረሃል ማለት አይደለም። ለሁሉም ሰው የተሰጠው ህሊና የመንገድህ መሪ፣ የንግግርህ ቆንጣጭ፣ የተግባርህ አራሚ ነው። ለመፍረድ አትቸኩል፤ ለንግግር አትጣደፍ፤ እውነታውን በጥላቻህ አትሸፍን፤ በእውቅናህ ሰላምን አትግፋ፤ በተሰሚነትህ ክፍተትን አታስፋ። ውሸት የአብሮነት ምክንያት ሆኖ አያውቅም፤ ተንኮል ፍቅርን አንግሶ አያውቅም፤ ጥላቻም የሰላምን በር ከፍቶ አያውቅም።

♦️ሁሉን ያገኘህው በፈጣሪህ ሞገስ እንጂ አንተ አምጥተህው አይደለምና ለበጎ ተጠቀመው። እውነትን በፍቅር ያዝ፣ ለሰላም ግድ ይኑርህ፣ ለመከባበርም ቅድሚያ ስጥ። ትዕቢትን፣ ጉራን፣ ጀብደኝነትን፣ ጥቅመኝነትን ከውስጥህ አስወግደው የመልካምነትን ስብዕና ገንባ፣ ጥሩ መሪ ፣ ጥሩ ተከታይም ሁን።

    ደርበብ ያለች ቅዳሚትን ተመኘን 😉

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
📍ከ150 አመት በኋላ ዛሬ በህይወት ካለነው ሰዎች አንዳችንም በህይወት አንገኝም። ዛሬ ላይ ከምንታገልላቸው ነገሮች 70 በመቶ የሚሆኑት ከ150 አመት በኋላ አንዳቸውም ለምልክት እንኳ አይገኙም፡፡ ፈጽመው ይጠፋሉ ይረሳሉ፡፡

🕯በጊዜው ግን ለሰው ልጅ የሞትና የህይወት ልዩነት የነበሩ፡፡ የሰው ልጅ በየጊዜው የሚታገልላቸው አብዛኞቹ ነገሮች ዛሬ ላይ ዞር ተብለው ሲታዩ አላፊ ጠፊ ሆነው እናስተውላቸዋለን፡፡ ሌላው ይቅርና በሽታ እንኳን ሩቅህ አይደለም፣ የተዘረጋው እጅ አሁን በቅፅበት ማጠፍ ሊቸግርህ  ይችላል። በሃብታችን በእውቀታችን በዝናችን .... አለን ባልነው ነገር ሁሉ መማፃደቁ ከንቱ ነው .... ሌላው ቢቀር የዘረጋነውን  የምናጥፈው በፈጣሪ ቸርነት ነው።

💡ታላቁ እስክንድር ወደ ሞት አፋፍ መቃረቡን ሲያውቅ፤ ወዳጆቹን ሰብስቦ እንዲህ አላቸው "ስትቀብሩኝ፤ እጄን ወደ ላይ አርጋችሁ ቅበሩኝ" አለ። ሰዎቹም ግራ ገብቷቸው ለምን እንደሆነ ጠየቁት፤ እሱም መልሶ ፤ "እጄን ወደላይ አድርጋችሁ ቅበሩኝ ያልኩት፤ ስሞት ከምድር ምንም ነገር ይዤ እንዳልሄድኩኝ ሰዎች እንዲያዩ ነው " አለ። ይህንን ያለው እንግዲህ በጊዜው አለምን ያስገበረው ታላቁ እስክንድር ነው።

🔷ብርሌ በመሰለ ዓለም ፡ መጥፊያው ሰፊ መልሚያው ጠባብ በሆነ ኑሮ፣ በዙፋን ላይ ካለ ንጉስ  በፈጣሪው የታቀፈ አማኝ ይበልጣል!! Impermanenceን በቅጡ የተረዳነው ያህል ሆኖ ያታልለናል። በሕይወት መንገድ ስለ ጤዛነት ብዙ እያየንም አልማር ብሎ የፈተነን አንጎላችን ብዙ ያነበብነና ያወቀ ይመስለዋል።

ማጠቃለያው፣

📍ህይወትን ቀለል አርገህ ኑር፡፡ ምንም ሆነ ምንም ዘላለም የሚኖር የለም፥ ከዚህች ምድር በህይወት የሚወጣ ሰውም የለም፡፡ከ150 አመታት በኋላ ዛሬ እንደ ትልቅ ሀብት የምናያቸው አብዛኞቹ ነገሮች ምንም ፋይዳ የሌላቸው ተራ ቁሶች ይሆናሉ፡፡

ምን ለማለት ነው ፥ ፍቅር ይግዛን ፥ መከባበርን እናስቀድም፣ከጀርባ መወጋጋት፣ መጠላለፍ አክሳሪ ነው፡፡ ህይወት ከማንም ጋር የምታደርገው ፉክክር አይደለችም፡፡ የሰው ሕይወት በምድር ላይ በጣም አጭር ናት። ኑሮ ማለት ደግሞ በውልደት እና በሞት መካከል ያለ የመሸጋገሪያ ጊዜ ነው። በድንገት ተጀምሮ በድንገት የሚቆም የመሸጋገሪያ ጊዜ.......

💡ቃሉም እንደሚለው "ሕይወታችሁ ምንድን ነው? ጥቂት ጊዜ ታይቶ ኋላ እንደሚጠፋ እንፋሎት ናችሁና።ያዕ 4፡14

💡ሀዲሱም እንዲል "ምድር ላይ ስትኖር እንደ እንግዳ እንደ መንገደኛ እንደ አልፎ ሂያጅ ሆነህ ኑር" (ነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዐ.ወ )

🔑 በዚህ ዓለም ላይ ምንም ቋሚ የሚባል ነገር የለም እንኩዋን ሰውና ግዑዝ ነገር ሁሉ አላፊ ነው . . . እንደ አልፎ ሂያጅ አልሆንም ብንልም ማለፋችን አይቀርምና መልካም ስራን ለነፍሳችን እናስቀድም ዘንድ ፈጣሪ ያግዘን።
         
                 ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💎የራስ ቀለም

"በዚህች አለም እንተን የሚመስል ሰው ተፈጥሮ አያውቅም ወደፊትም አይፈጠርም በቃ አንተ አንተን ሆነህ ብቻ አንዴ ተፈጥረሀል..." - ዴልካርኔጊ

💡 በራሳቹ ቀለም እጅግ ውብ ናቹህ በራሳቹ አለም እንደመልአክት ታብረቀርቃላቹህ በራሳቹህ መንገድ እንደንጉስ ትራመዳላቹህ ። ውበታቹህ እርሱ ነው እናንተነታቹህ የነፍሳቹህ ብርሀን መንገድ ነው። አለም በቀደደላቹህ ቦይ እንድትፈሱ ፈጣሪያቹህ አልተጠበበባችሁም በእናንተ የተጠበበ'በትን ህይወት ለመኖር ወደ ልባቹህ መቅደስ ብቻ ፍሰሱ... እግራቹህን ከልባቹህ ጋር አስተሳስሩ ልባቹህ ወደ መራቹህ ሂዱ ፣ ይሄ ነው ህይወት....... ይሄ ነው መተንፈስ..... ይሄ ነው መንቀሳቀስ.....

በእግርህ ከመተማመንህ አስቀድሞ ፡ የምትጓዝበት መንገድ ይኑርህ ፤ ምክንያቱም በዚህች ተራራማ ፣ ሜዳማ ፣ በረሃማና ረግረጋማ ዓለም ላይ እግር ያላቸው ሁሉ አይጓዙም መንገድ ያላቸው እንጂ ፡ ስለሆነም ከርምጃህ መንገድህ ይቅድም !"። ህይወትህን ከፉክክር አልቀው ወደ ተፈጥሮ ዝለቅ በፀሀይ መውጣት እና መጥለቅ ተመሰጥ በከዋክብቶች ፊት ዳንስን ደንስ ከጨረቃዋ ጋር ተወያይ በፅጌሬዳ ፍካታዊ ውበት ነፍስህን ከስነፍጥረት ጋር አዋህደው።
                  
የሕይወት ጎዳናህ ርዝማኔ ዕድሜህን የመወሰን አቅም ስለሚኖረው ፣በቀን ከፀሐይ ተዋህደህ አርቀው ፣ በምሽትም ከጨረቃ ተማክረህ አርቅቀው ፤ ስጋህን ከጀምበሯ ሙቀት አላምደው ፡ ነፍስህንም ከጨረቃዋ ብርሃን አስታርቀው ፤ፀሐይዋን የሚጋርድህ ፡ ከጨረቃዋም የሚደብቅህ አንዳችም ኃይል የለም ፤ ራስህ ካልሆንክ በቀር።

⌛️ተራራማ ፣ ሜዳማ ፣ በረሃማና ረግረጋማ የሕይወት ጎዳናህን ከጀምበሯ ዕለታዊ የብርሃን ዕድሜ አንፃር አንፅረህ በማስተዋል አስልተህ ቀምረው ፤ ተራራውን ፣ ሜዳውን ፣ በረሃማውንና ረግረጋማውን ምድራዊ ስፍራና የጎዳናህን አካል በጨረቃዋ ጥበባዊ ምስጢር መስጥረው ፤ ከጨረቃዋም የውበት ውቅያኖስ ቀለም በሰዓሊነት መንፈሳዊ ብሩሽህ እየጨለፍክ አስውበው።

📍ተፈጥሯዊ ነህና ስጋዊ ዓይንህ በቀን ብርሃን የመመልከት አቅም እንዳለው ሁሉ በምሽት የጨለማ ጊዜም መንፈሳዊ ዓይንህ የጠራ የማስተዋል ኃይልን ታድሏልና ሳትደናገጥ ሳትፈራ በራስ መተማመን ቀን ያየኸውን ተራራ ተንደርደረው ፣ የውቅያኖሱን ሞገድም ሰንጥቀህ ቅዘፈው ፣ በረሃማውን ረግረጋማውንም የጎዳና አካል፣ በእባብ ብልህነት በጊንጥም ፅናት በሌሊት ወፍ ምስጢራዊ አከናነፍ ተምሳሌታዊ ስልት በዝግታ በማስተዋል፣ ከጊዜም ሙዚቃዊ ስልተ-ምት ጋር ተዋህደህ በመዝናናት፣ መንፈሳዊ ክንፍህን እያርገበገብክ በዳንስህ ክነፍ-ብረር-ድረስ እንጂ ከአላማህ ፈፅሞ እትቁም።

💡ነፍስህን ለማደስ ከፀሐይዋ ብርሃን ሙቀት ውሰድ ፡ ከጨረቃዋም ብርሃን ውበትን ቅዳ ፤ልብ በል… ተፈጥሮ የሙዚቃ መሳሪያ ..... አንተ ዳንሰኛ.... ሕይወትም ሙዚቃ ናት። ፀሐይ ጨረቃና የሰማይ ከዋክብትም በጎዳናህ ክበባዊ ዙሪያ በሰልፍ እንደተኮለኮሉ በዳንስህ ለመዝናናት እንዳሰፈሰፉ ተመልካቾች መሆናቸውን ልብ በል።

🔑በተፈጥሯዊው ሕግ መሰረት ካንተ የሚጠበቀው የሕይወትን ሙዚቃ በነፍስ መንፈሳዊ ክንፍ እየደነስክ ጎዳናህን በዳንስ ልትበርበት እንደምትችል ብቻ ማመን ነው። ከሺ አመታት በፊት የተፃፈው ታላቁ መፅሃፍ ከሽህ አመታት ቡሃላም ይናገራል 'ዕመን እንጂ አትፍራ !' የትርጉሙ ምስጢር የጥበብ ተምሳሌትነቱም ይህ ነውና።

Tupaca Ela

             ውብ ሰንበት❤️

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
2024/11/15 10:18:51
Back to Top
HTML Embed Code: