Telegram Web Link
የበሰበሰው ጥርስ
(ካህሊል ጂብራን)

🔷በአፌ ውስጥ በስብሶ የሚያስቸግረኝ አንድ ጥርስ አለኝ በቀን ሰላማዊ ሆኖ ይውላል። ምሽቱ ሲገፋ፣ የጥርስ ሃኪሞቹ እንቅልፍ ሲጥላቸው እና መድሃኒት ቤቶቹ ሲዘጉ ግን ይጠዘጥዘኝ ይጀምራል።

አንድ እለት ትዕግስቴ ተሟጠጠና ወደ አንድ የጥርስ ሃኪም ሄጄ ያንን ስቃይ ያበዛብኝንና የምሽቴን ፀጥታ ወደ ማቃሰት እና ማጓራት በመለወጥ እንቅልፍ የነሳኝን ጥርስ እንዲነቅልልኝ ነገርኩት።

🔶 የጥርስ ሃኪሙ ራሱን ከግራ ቀኝ እየወዘወዘ "ጥርሱን ማዳን ስንችል መንቀሉ ቂልነት ነው" አለኝ። ከዚያም ጎንና ጎኖቹን በስቶ ቀዳዳዎቹን በማፅዳት ወደ ቀድሞ ሁኔታው ሊመልሰው እና ከብስባሴው ሐራ ሊያወጣው ያለውን መንገድ ሁሉ ተጠቀመ። መብሳቱን ከጨረሰ በኋላ በንፁህ ወርቅ ሞላውና "የበሰበሰው ጥርስህ አሁን ከጤነኞቹ የበለጠ ጠንካራና ብርቱ ነው" አለኝ በኩራት። አመንኩት። ከፈልኩትና ስፍራውን ለቅቄ ሄድኩ።

🔷ነገር ግን ገና ሳምንቱ ሳይገባደድ የተቀሰፈው ጥርስ ወደ ህመሙ ተመለሰና የነፍሴን ጥዑም ዜማ ወደ ለቅሶና ስቃይ ለወጠብኝ። እናም ወደ ሌላ የጥርስ ሃኪም አመራሁና "ምንም ጥያቄ ሳይጠይቀኝ ይህንን ጥርስ አውጥተህ ጣልልኝ። የደረሰበትና ያልደረሰበት ግልግልን እኩል አያውቃትም!" አልኩት።

ትዕዛዜን በማክበር ጥርሴን ነቀለልኝ። ከዚያም ጥርሴን እያየ "ይህ ጥርስ እንዲነቀል በማድረግህ መልካም አድርገሃል" አለ።

🔴 በአፍ ማህበረሰብ ውስጥ እስከ መንጋጋ አጥንት ድረስ የበሰበሱ ብዙ ጥርሶች አሉ። ይሁንና ማህበረሰቡ እነዚህን የተበላሹ ጥርሶች ለማስነቀልና ከስቃዩ ለመገላገል ምንም ጥረት አያደርግም። ራሱንም በወርቅ ፍቅፋቂ ይሞላል። አብዛኞቹ የበሰበሱትን የማህበረሰብ ጥርሶች በሚያብለጨልጭ ወርቅ እንደሚያክሙ የጥርስ ሃኪሞች ናቸው ።

እንደዚህ ተጠጋግነው በመደለል የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው ስቃይ ህመምና ሞት ዕጣ-ፈንታቸው ናቸው።

🔶ሃገር አፍ ውስጥ ብዙ የበሰበሱ፣ ያመረቀዙ ጥርሶች አሉ። ሃኪሞቹ ከመንቀል ይልቅ በወርቅ ፍቅፋቂ አክመዋቸዋል። ህመሙ ግን እንዳለ ነው።

የበሰበሰ ጥርስ ያለው ሃገር የታመመ ጨጓራ እንደሚኖረው እርግጥ ነው። በዚህ ያለመፈጨት ችግር ውስጥ የሚገኙ ብዙ ሃገራት አሉ።

🔷ሃገር ዳቦውን በበሰበሰ ጥርሱ እንደሚያኝክ እና እያንዳንዱም ጉርሻ ከተመረዘ ምራቅ ጋር በመዋሃድ በሽታውን በሃገሩ ጨጓራ ውስጥ እንደሚያሰራጭ ስትነግሯቸው "አዎ ግን የተሻሉ የጥርስ ሙሌቶች እና ማደንዘዣዎች እየፈለግን ነው" ይሏችኋል።

ውብ አዳር❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💡አንዳንዴ በመታነጽ ላይ ሳለህ የቦዘንክ ቢመስላቸው አትደነቅ። ስኬት ቀድሞ በመራ አይደለም። ከእውቀት ሥራን ባስቀደመም አይደለም። ሥራ በዕውቀት ካልሆነ ልፋት ነው።

አንተ ብቻ ለዕውቀት ትጋ ፣ ጊዜው ደርሶ ሥራ ስትሠራ ደግሞ "ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው" በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው ። ትጋት ጥሩ ነው ። ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፣በችኮላ መሥራትና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው ።

📍አየህ አንተ ስትታነጽ፣ ስትተጋ ማንም ልብ አይልህም። ያንተ ራስን ማነጽ አርቀው ለማያስቡት ቦዘኔነት ነው። ሲያዩህ መሬት አትቆፍርም፣ እንጨት አትልግም፣ ምስማር አትመታም፣ ልብስ አትሰፋም፣ ዳቦ አትጋግርም፣ መርፌ አትወጋም። ለእነርሱ አንተ እየቦዘንክ ነው።

💎መጨረሻ ተሳክቶልህ፣ በኑሮ ከፍ ብለህ ሲያዩህ ግን "እድለኛ ነህ" ይሉሃል። እውነት ነው እድል ማለት ስትተጋ ሳትታይ የተሻለ ውጤት ማስመዝገብ መቻል ነው። ስንዴዋ አፈር ውስጥ ገብታ ስትበሰብስ ውጤቱን ለሚያውቀው ለገበሬው እንጂ ለሌላው ብክነት ነው። ሌሎች ውጤቱን የሚያዩት ስንዴዋ ስታፈራ ነው። ዘሩን የሚያናንቁ በፍሬው ቢደነቁ አትገረም።

አንተ ግን ለሌሎች ታይታ ሳይሆን በገባህ መንገድ አቅጣጫህን መርጠህ ትጋ! አንድ ቀን ውጤቱን ሲያዩ "እድለኛ ነህ" ይሉሃል።

💡እናም ወዳጄ

ምስጋና የደስታ ውጤትና ምንጭ ናትና። ባለህ ተደሰት! የምትፈልገውን ለማግኘት በትዕግስት ትጋ! አትዋከብ! አትቸኩል።

ምስጋናህ ግን በኑሮህ ላይ ባለህ ደስታ ይገለጽ። ኑሮህ፣ ህይወትህ፣ ስብከትህ ደስታህን ይመስክር።

             ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔊በዶ/ር ምህረት ደበበ

ምርጫችሁ ስለሆንን
ስናመሰግን ከልብ ነው !!!

ውብ ሰንበት❤️
@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
🌗በምድር ላይ ዘላለም እንዲኖር የተፈረደበት አንድ ሰው ነበር፡፡ ይህን ፍርጃ ሲሰማ ሳቀ... ዘላለም መኖርስ እንዴት ቅጣት ይሆናል? አራት መቶ አመታት አለፉ ... አንድ ማለዳ ላይ ከአልጋው ሳይወርድ ማስብ ጀመረ... ዘመናትን በምድር ላይ ያሳለፈ... የአለማችን ምርጥ ሰዓሊ፣ ምርጥ ሙዚቀኛ ሆኗል፡፡ ብዙ ጀግኖች በጦር ሜዳ ገድሏል... የሚወዳቸው የቅርብ ወዳጆቹም እድሜያቸውን ጨርሰው ሄደዋል። ሁሉንም ምግብ ቀምሷል፤ ያልረገጠው የምድር ክፍል የለም። አሁን ላይ ግን ለምን ከአልጋው መውረድ እንዳለበት ግልጽ አልሆነለትም። ሁሉም ነገር ሰልችቶታል። ለእርሱ ምድር እስር ቤቱ ሆናለች፡፡ በስተመጨረሻም ቀናቶቹ ሁሉ ትርጉም አልባ ሆኑበት፡፡

📍የ”አምላክ” ትልቁ ጥበቡ ሞትን መፍጠሩ ይመስለኛል፡፡ እያንዳንዱ ሃይማኖት እግሩን ያቆመው በሞት ላይ ነው፡፡ ሞት ባይኖር የሰው ልጅ፣ በአምላክ አያምንም ነበር። ሃይማኖቶች እግር ይከዳቸዋል፡፡ …ዘር ካልሞተ/ካልበሰበሰ ፍሬ አይሆንም፡፡ በዚህች ሰከንድ በሰውነታችን ውስጥ ህዋሳት እየሞቱ እራሳቸውን ባያድሱ ህልው መሆን አንችልም፡፡ ሞት እንደብዙዎቻችን እምነት፣ የህይወት ማብቂያ አይደለም፡፡ ወደ ቀጣይ ምዕራፍ  መሸጋገርያ ድልድይ  እንጂ ፣ የብዙዎቹ ሐይማኖቶች  መሠረቱ ይሄ ነው ። እኛ ዘመናችንን ሙሉ ከሞት ለማምለጥ ብንመኝም፣ ሞት እርግማን ሳይሆን በረከት ነው ። ያለ ሞት “መኖር” ትርጉም ያጣል፡፡

💡ዘላለም የሚኖረው ሰው እያንዳንዱ ቅፅበቶቹ ጣዕም አልባ ይሆናሉ።  በዘላለማዊነት ውስጥ የሰውነት ባህሪ ይታጣል።የምንኖረው በአንፃራዊ አለም ውስጥ ነው። ሞትና ሕይወትም ሁለቱም የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ስለሆኑ ነው፡፡ ሞት ያለሕይወት፤ ህይወትም ያለሞት አልተፈጠረምና፡፡ ህይወትን ተቀብለህ ሞትን መተው አትችልም፡፡ ብዙዎች ከማያመልጡት ወጥመድ መሸሽ ይፈልጋሉ፡፡ ሞት የህይወትህ አካል ነው፡፡ ለሕያዋን ሁሉ የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ አስር ዓመትም፣ መቶ ዓመትም፣ ሺ ዓመትም በሕይወት ብትኖር ከሞት ጋር ክርክር የለህም፣ የትም ብትሄድ አታመልጠውም፡፡ ይልቁንስ ህይወትንም ሞትንም ጠልቀህ ከተገነዘብክ አኗኗርህንና አኳኋንህን፤ መካከሉን በማስተዋል ሕይወትህን እንድታስተካክል ይረዳሃል፡፡

🔑ሞት እና ጊዜ የተባሉ መልህቆች በሕይወታችን ውስጥ ያስፈልጉናል። ህይወት በትክክለኛው መንገድ ከተኖረ ሞት አይፈራም። ህይወትን ከኖራችሁ ሞትን በፀጋ ትቀበላላችሁ ምክንያቱም እንደ እረፍት፣ እንደ እንቅልፍ ትመለከቱታላችሁ። ከህይወት ጫፍ መድረስ ከቻላችሁ ሞት ውብ እረፍት ፣ ብረከት ይሆናል። በተቃራኒው ካልኖራችሁ ግን በርግጠኝነት ሞት ጊዜያችሁን ፣ የህይወት እድሎቻችሁን ይነጥቃችኋል። ካልኖራችሁ ነገ የሚባል ነገር የለም ፍርሃት ይነግሳል። ፍርሃቱ የሚመጣው በሞት ሳቢያ ሳይሆን በደንብ ህይወትን ካለመኖር ነው።"

               ውብ አሁን❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
💎በተሰጠን እድሜ በሀቅ መንገድ መሮጥ ነዉ

አንድ ቀን ስለ ዉልደትና ሞት ፍልስፍና ሲወራ በዋለበት የአንድ ወዳጃችን ጠባብ ክፍል ዉስጥ ከድር ሰተቴ የተወራውን ሁሉ ሲታዘብ ቆይና እንዲህ ብሎን ጥሎን ወጥቶ ሄደ ።

"ቢተኮስ ቢፎከር እኛ ምን አስፈራን
ሰተት ብለን ገብተን...
ሰተት ብለን ወጣን"

ሰተት ብለን በዉልደት በር እንደገባን ፣ በሞት በር ደግሞ ሰተት ብለን ዉልቅ እንላለን ። ብልጭ ብላ ድርግም እንደምትል ብርሃን ነን።... መነሻዋም ሆነ መድረሻዋ በግልጽ የማይታወቅ ብርሃን ።

📍ይህን ጥያቄ መመለስ ሳይሆን፣ ሰዉ የመሆን ቁም ነገሩ በተሰጠን እድሜ በሀቅ መንገድ መሮጥ ነዉ። በመጠላለፍ  ብልጣ ብልጥነት ሳይሆን በመደጋገፍ ሰዋዊነት። የክፋት ጠቢባን ለራሳቸው በሚመች መልኩ ያበጁልንን ቦይ ትተን የነብሳችንን እንከተል። ፈጣሪ የሰው ልጅን በእድሜው ብራና ላይ የየራሱን መልካም ታሪክ ይከትብ ዘንድ በስጋና ነፍስ ፈጥሮታል፣ የልባችሁን ሀቅ በመከተል ለሚደርስባችሁ የትኛውም ግፍ ፈጣሪ ከእናንተ ጎን ለመቆሙ አትጠራጠሩ።
   
      📓መንገደኛዉ ባለቅኔ
          ከድር ሰተቴ

ውብ ምሽት❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
🌍ምክር ለወዳጅ

📍ወዳጄ ሆይ

ወንዝ መርጦ አያጠጣም። አጎንብሶ ሊጠጣ ለወደደ ሁሉ ሳይሰስት ያጠጣል። ደግነትህ እንደ ወንዝ ይሁን! ሳትመርጥ፣ ለለመነህ ሁሉ እጅህን ዘርጋ። ሁልጊዜ እንደ ወንዝ የሚፈስ መልካምነት፣ በጎነት ይኑርህ። መርዳት ዕድል ነውና ተጠቀምበት ፡፡... ሌላው የወንዝ ውበቱ ዝቅ ብሎ በዝምታ መፍሰሱ ነው። ዝቅ ብሎ ሌሎችን ከፍ እንደማድረግ ምን ውብ ነገር አለ? ይህንን አደረግኩኝ፤ እንዲህ ደግ ሰራው እያሉ መጮህ የደግነትን ክብር ይነካል፤ እንደ ወንዝ በዝምታ፤ ለሌሎች መልካም መሆን ነው እውነተኛው ደግነት ነው። ወደኛ የመጣች ደግነት ወደሌሎቹ ካልሔደች ደስታ አይኖረንም  የተቀበልነውን ደግነት እኛም ለሌሎች እናሳይ፡፡ ጥሩ ሥራን ለሕሊና ምግብነቱ እንጂ ለሰማይ ሽልማቱ ብቻ አትሥራው ። የመልካም ነገር ዋጋ ከፋይ ፈጣሪ መኖሩንም እመን ።

📍ወዳጄ ሆይ !

ባለሀብት ብዙ ያለው ሳይሆን ካለው ብዙ የሚሰጥ ነው።ከሚደልሉ አንደበቶች የሚመፀውቱ እጆች እጅግ ይልቃሉ ። ልግስና ማለት የኪሳችንን ቦርሳ መክፈት መቻላችን ብቻ ሳይሆን ልባችን መክፈት መቻላችን ነው። አንተም ለመልካም ስራ እጅህን ለግስ "ልግስና የነፍስ ምግብ ነውና'' ደስታ ለሚሰጥ አብዝቶ ይመለስለታል። ሌሎችን መረዳት የመጀመርያው ንቃት እና ዕውቀት ነው፣ መንፈስህንም ወደ ላይ ክፍ ከፍ ያደርገዋል። ታላቅ የሆነ ጥበብ እና ማስተዋልንም ይዞልህ ይመጣል ። ደስተኛ የመሆን ቀላሉ መንገድም መልካም ነገር ማድረግ ነው። ውብ ነገርን ተመርኩዘው የሰሩት ስራ ሁሌም ውብ ነውና።

📍ወዳጄ ሆይ !

አቅመ ደካማን ሰው ጥሪቱን ብትገፈው የምታጌጠው በተቀደደው ልብሱ ነው ፣ ድሀን ዘርፈው ባለጠጎች የሆኑም ሲያፍሩ የሚኖሩ ናቸው ። አንተም የግፍን እንጀራ እንዳትበላ ተጠንቀቅ!! ጭካኔ የሕሊና ሰላምህን ያቀነጭራል። ፈጣሪ መስረቅን በትእዛዙ ቢከለክልህም ፣ የዘረፍከውን እንዳትበላ ግን በፍርዱ ያግድሃል።ፈጣሪ ባህሪና ተግባራችንን ያያል። ከሰው የወሰድነውን ከሰውየው ብንደብቅ ከአምላክ አንደብቅም። የምናተርፈው ነገር ቢኖር የሆነ ጊዜ ላይ የሚመጣ መጥፎ ስቃይን ነው። ያውም ለልጅ የሚተርፍ የበደል ክፍያን ነው፣.........የቆምን መስሎን የዘነጋን ሰው የዘራውን ያጭዳልና እናስተውል።

📍ወዳጄ ሆይ !

ከጓደኛህ መልካም የሆነውን ነገሩን አውጣለት ፣ አበረታታው ፣ እንደማይጠቅም አትንገረው ፣
ለሀዘኑ ሳይሆን ለደስታው ምክንያት ሁን ፣ ለስኬቱ እንጅ ለውድቀቱ መንስኤ
አትሁን ።መልካም ዘር ዘርተህ መልካም ምርት እፈስ፣ፍቅር የዘራ ፍቅር ያገኝል። ጥላቻ የዘራም ጥላቻ ያመርታል። ቅሬታ የተከለ ቅሬታ ይለቅማል። መልካም ዘር የዘራ መልካም ፍሬ ያጭዳል።አለም የአስተሳሰብህ ግልባጭ ናት፣ መስታወትህም ናት።

📍ወዳጄ ሆይ !

ከሚንጫጫ ብዙ ፣ ዝም ያለውን አንድ ሰው ፍራ ። ከሚጮኸው ውሻ ፣ የማትጮኸው ግመል ብዙ በረሃ ታቋርጣለች ። ያነበበ ቢተኛ እንኳ ነቅቶ የተኛ ነው ። ሳታነብ ሰው ሁሉ ከሚወድህ አንብበህ ብቸኛ ብትሆን ይሻላል ። ዓለም በጫጫታና በመዋከብ ውስጥ ብቻ ትልቁ ደስታ ያለ ይመስላታል፣ ዝም ያለች ጥበብ ግን አጥብቆ ለሚሻት እጅጉን ቅርብ ናት። ብልህና ትጉ የሆነ ማንኛውም ግለሰብ በየትኛውም የህይወት ዘርፍ ላይ ላሉበት ክፍተቶች በዙሪያው ከሚያስተውላቸው የቀን በቀን ክስተቶች እርማርትን ነቅሶ ይወስዳል፣ በሌሎች ላይ የሚመለከተውን ደካማና እኩይ አካሄድንም በራሱ ላይ እንዳይታይ በመጠንቀቅ እራሱን ወደተሻለ አቋም ያሸጋግራል!

📍ወዳጄ ሆይ !

ዓለም ዋዣቂ ናት ። ከፍና ዝቅ ስትል አትደናገጥ ፤ ፀሐይ ዝናብን ተከትላ ትፈነጥቃለች ። ከመከፋትም በኋላ ትልቅ መፅናናት ይሆናል ። ከሌሊት በኋላም ሌሊት አይመጣም ። ከሀዘን በኋላ ደስታ ይሆናልና በርታ!  መነቀፍን አትፍራ ፤ ነቀፋህን ግን አጥራው ፤ ስለ ሀሰት ሳይሆን ስለ እውነት ተገፋ ፤ ሁሌም ከሰዎች ውስጥ መልካም ገጻቸውን ፈልገህ አንጥረህ ተመልከት፣ ጥሩነታቸውን በማድነቅ ገንባ፣ ከአፍህ መልካም ቃል ይውጣ፤ መልካም ዘር ዝራ። ልብ በል! ክፋት፣ ጥላቻ፣ ቂም፣ ቅሬታ አይጠቅሙህም። ይልቅስ ይጎዱሃል፣ በሽታ ያመጡብሃል፣ ወደታች ይስቡሃል።

🔑እናም ወዳጄ

ዛሬ የመዝራት ዘመንህ ነገ መከርህ ነውና በእምነት እውነትን ዝራ ፤ በምታውቀው ቦታ ላይ አገልጋይ በማታውቀው መልካም ተግባር ላይ ደጀን ሁን ፤ በቦታህ መምህር ያለቦታህ ተማሪ ሁን ፤ ክብሩ እንዳይቀንስብህ ከዕቃ ትምክህት ፣ ከዕውቀት ሙግት ራቅ ።ሰዎች የዘሩትን ሲያጭዱ ስታይ አንተም ዛሬ እየዘራህ ነገ ደግሞ የምታጭድ መሆኑን አስብ። አለም ሁሉ ሲዋዥቅ፣ ሳትዋዥቅ የምትኖር እውነት ብቻ ናት ።

       መጪው ዘመን ሰላማዊ እንዲሆን
                ፈጣሪ ይዘዝልን❤️

ውብ አዲስ ዘመን😊

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
🌼እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ

🌼አዲስ ሀሳብ፣ አዲስ አስተሳሰብ፣
ከትላንት ስህተቶች የምንማርበት፣
አዲስ አላማ ቀርፀን የምናሳካበት፣
ጥላቻና ልዩነትን አስወግደን በአንድነትና በፍቅር ወደ ተሻለ እድገት የምንሸጋገርበት የተባረከ ዘመን ይሁንልን ! 

🌻ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ 2017 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሠላም አደረሳችሁ፤

❤️በዓሉ የሠላም፣ የጤና፣ የደስታ እና የፍቅር አመት እንዲሆን እንመኛለን።

መልካም አዲስ ዓመት ለሁላችን
💛 ስብዕናችን 💛

@EthioHumanity
@EthioHumanity
💡የሆነ መንደር ውስጥ አንድ ጅል ይኖራል። የመጨረሻ ጅል ከመሆኑ የተነሳ አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አይችልም። እና የመንደሩ ነዋሪዎች ይመጡና "አንተ ጅል ና እስቲ ከዚህ ምረጥና ውስድ" ብለው አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም ሲያስቀምጡለት አስሯን ያነሳል። "ይሄ (አምሳውን) ይሻልሃል" ሲሉት "እምቢ ብሎ ያለቅሳል።

🔆 "አይ ይሄ ጅል … ኑ ጉድ እዩ፤ ኑ ጉድ እዩ" ይሉና አስር ሳንቲም እና አምሳ ሳንቲም ድጋሚ ያስቀምጡለታል። አሁንም አስሯን ያነሳል። ኧረ ይሄ ይሻልሃል ሲሉት "እምቢ፣ እምቢ" ብሎ ያለቅሳል።

በኋላ በዚህ ጅል ዘመዶቹ እያፈሩ ሄዱ። አንዱ ዘመዱ መጣና "አንተ ጅል … ሁሌ ባንተ እንዳፈርን እንቅር? ኧረ ተው ግድ የለህም፣ ተው ግድ የለህም። አምሳ ሳንቲም እና አስር ሳንቲም መለየት አቅቶህ አምሳ ሳንቲም ሲሰጡህ በአስር ሳንቲም ታለነሳለህ? ኧንደው ምናለ አምሳውን ብታነሳ?" ብሎ ሲመክረው። "ጅልስ አንተነህ ነህ! አምሳውን ያነሳው ቀን አያስመርጡኝም።

🔆ማነው ጅል? እነሱ ወይስ ጅል ብለው የሚያስቡት ብልጥ? አያችሁ እሱ ብልጥ ጅል ነው፤ እስከ ኖረ ድረስ አስር፣ አስር ሳንቲሟን እየመረጠ የተጃጃለ መስሎ ያጃጅላቸዋል፤ ምክንያቱም አምሳዋ አንዴ ነች፤ አስሯ እስካለ ትቀጥላለች።

💡እንደነሱ ከሆነ አምሳ ሳንቲሟን የብልጠቱ፣ አስር ሳንቲሟን ደግሞ የጅልነቱ መገለጫ አድርገዋታል። ለሱ ግን አስር ሳንቲሟ የብልጠቱ መሰወሪያ፣ መደበቂያ ነች። አምሳዋን የመረጠ ቀን ጅልነቱ ያበቃል፤ ማንም አያስመርጠውማ። ምክንያቱም አውቋል፤ ነቅቷል ይሉታላ።

ዓለማየሁ ገላጋይ

ከሞኝ ብልጦች ብልጥ ሞኞች የሚያዋጣውን ያውቃሉ!

ሸጋ ቅዳሚትን ተመኘን😁

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
🌗ንብ እና እርግብ ተገናኝተው እየተጫወቱ ነው። እርግብም በማፅናናት መንፈስ ሆና <<እኔ የምልሽ ወይዘሪት ንብ እንዲህ ታትረሽ እየሰራሽና ማር እያመረትሽ የሰው ልጅ ግን ያንችን ማር እየሰረቀ እየበላና እየሸጠ ሲኖር ባንቺ ልፋት ሲከብር አያሳዝንሽም>> ? እርግብ ጠየቀቻት።

ንብ እንዲ ስትል መለሰች "በፍፁም አይሰማኝም፤ ምክንያቱም የሰው ልጅ ማሬን እንጂ ማር የማዘጋጀት ጥበቤን ሊሰርቀኝ አይችልም፡፡"

💡ሰዎች ብልጠታቸውን ተጠቅመው ገንዘባችንን፣ ያለንን ንብረት ሊወስዱብን ይችላሉ፤ ነገር ግን ያን ሁሉ እንድናፈራ ያስቻለንን እውቀትና ጥበብ መስረቅ አይችሉም፡፡ ስለዚህ በተወሰደብህ ነገር ላይ አትብሰልሰል። ባለህ እውቀት ላይ ትኩረትህን አድርግ።

ሕይወትህን መስዋዕት ያደረግህለት ሥራህ በተናደ ጊዜ ይህንን ፈተና ተቀብለህ ተስፋ ሳትቆርጥ የጠፋውን ሁሉ መልሰህ ለማቋቋም በደከመ መሣሪያህም ቢሆን ለመሥራት ሳታመነታ ተነሣ። የአሰራሩ ጥበብ እና ልምድ ያለው አንተ ጋር ነውና።

📍ከውድቀትህ በኋላ እንደገና መጀመርን አትፍራ፡፡ እንደገና ስትጀምር እኮ የምትጀምረው ከዜሮ ሳይሆን ከስህተትህ ትምህርትና ልምድ ካገኘህበት ደረጃ በመነሳት ነው። ከትናንትናው ዛሬ አድገሀል ፣ ተለውጠሀል፣ በስለሀል ፣ ጥበብ አግኝተሀል ፣ በርትተሀል፣ ነገሩ ገብቶሀል ማለት ነው ፡፡

🔑እናም ወዳጄ ማሰብ ላይ በርታ፤ መስራት ላይ ጠንክር፣ አምላክህን ይዘህ ፈተናህን ተጋፈጥ፣ በፀሎትህ ፅና፣ ምስጋናህን ደጋግመህ አቅርብ፣ ካንተ በላይ የሚሰራብህ፣ ተአምር የሚያደርግብህ ፈጣሪህ አብሮህ እንደሆነ አስብ። ብቻህን የሆንክ ቢመስልህ እርሱ ከጎንህ አለ፤ የተገፋህ ቢመስልህ በእርሱ እቅፍ ውስጥ ነህ፤ የወደክ ቢመስልህ እርሱ ያነሳሃል፤ በሚገባህ ስፍራም በክብር ያቆምሃል።

           ውብ አሁን❤️
                  
@Ethiohumanity
@Ethiohumanity

@EthiohumanityBot
📍ተፈጥሮ በአጠቃላይ እጅግ በጣም የተወሳሰበ  ሂደት ነው ፣ እናም በውስጡ  ጥሩም ይሁን መጥፎ ነገር እንደያዘ ለመናገር ከባድ ነው። ምክንያቱም የመጥፎ ነገር ውጤት ምን እንደሚሆን በጭራሽ አይታውቅም ፣ ወይም ደግሞ  መልካም ዕድል ምን ይዞ እንደሚመጣ በጭራሽ አይታውቅም።

🔆በአንድ ወቅት አንድ የቻይና ገበሬ ፈረሱ ሸሽቶ  ተሰወረበት ፡፡  የዚያን ዕለት ምሽት ሁሉም ጎረቤቶቹ ተሰብስበው ሊያፅናኑት መጡ ፡፡  እነሱም “ፈረስህ በመጥፋቱ በጣም አዝነናል ፡፡ ይህ በጣም መጥፎ ነገር ነው አሉት ፡፡
”ገበሬውም“ ምናልባት ”አላቸው ፡፡

በሚቀጥለው ቀን ፈረሱ ሰባት የዱር ፈረሶችን ይዞ ወደ ቤቱ ተመለሰ
ምሽት ላይ ሁሉም ጎረቤቶቹ ወደ ቤቱ በመምጣት“ ዕድለኛ ነህ በጣም ፡፡  እንዴት ያለ ታላቅ ክስተት!! አሁን እኮ ስምንት ፈረሶች አሉህ! ” አሉት።
ገበሬው እንደገና“ ምናልባት ”አላቸው ፡፡

በሚቀጥለው ቀን ልጁ ከፈረሶቹ አንዱን ለመጋለብ ሲሞክር  ወድቆ እግሩን ተሰበረ ፡፡  ጎረቤቶቹም “ ይሄ ደግሞ በጣም መጥፎ አጋጣሚ ነው” አሉት።
ገበሬውም በድጋሚ “ምናልባት” ብሎ መለሰላቸው ፡፡

🔆በሚቀጥለው ቀን የግዳጅ መኮንኖች ሰዎችን ወደ ጦርርነት ለማሰማራት በመጡበት ጊዜ የገበሬው ልጅ የተሰበረ እግር ስለነበረውው ልጁን አይመጥንም ብለው ጥለውት ሄዱ ፡፡  እንደገና ጎረቤቶቹ ሁሉ መጡ እና “ይሄ እንዴት ደስ ይላል ልጅህ እኮ ጦርነት ከመግባት ተረፈ!” አሉት ፡፡
አሱ ግን እንደገና “ምናልባት” አላቸው፡፡

🔑ገበሬው ስለ ትርፍ ወይም ኪሳራ ፣ ጥቅምና ጉዳት ከመሳሰሉ ነገሮች ከማሰብ በጥብቅ ተቆጥቧል፣ ምክንያቱም  የህይወት ክስተቶች በጭራሽ ይዘው የሚመጡትን ነገር ማናችንም አናውቅም። ብዙዏቻችን በህይወት ባህር ውስጥ የምንሰምጠው፤ እንደገበሬው ከኑሮ ጋር በቀላሉ መንሳፈፍን ስላለመድን ነው። በህይወታችን ወስጥ በእኛ ቁጥጥር ስር የሆኑ ነገሮች አሉ፤ ሌሎች ከእኛ ቁጥጥር ውጪ የሆኑ ደግሞ እጅግ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ።

💡በኑሮ ባህር ውስጥ መስመጥ የሚከሰተው ታዲያ፤ ከእኛ ቁጥጥር ወጪ የሆኑ ነገሮች ላይ ግትርነታችንን ለማሳየት ስንሞክር ነው። መለወጥ የማንችለውን ነገር በጉልበት ለመለወጥ ስንሞክር፤ የመዋኘት ጥበቡ ጠፍቶናል ማለት ነው። ህይወት ወደድንም ጠላንም ባልታሰቡ ፈተናዎች እና ስጦታዎች የተሞላች ነች። እንደ ገበሬው ረጋ ብለን ካልተንሳፈፍን በፍጹም ከለውጥ ጋር ተግባብተን ለመኖር አይቻለንም።

📍እናም ወዳጄ ዓለም እና የሰው ልጅ ተፈጥሮ በብዙ ስንክሳር የተሞሉ ናቸው። ባሳለፍከው ህይወት ብዙ ክስተቶች ታይተዋል። የሚያሳዝንም የሚያስደስቱም ሁኔታዎች የህይወት ገጾች ናቸው። ሁሉ ይመጣል፣ ሁሉም ይሄዳል። ያለፈውና የሚሄደውን በሰላም ሸኘው። አሁን ካለው ጋር በሰላም ተከባብረህና ተሳስበህ ኑር። ዘልዓለማዊ ክስተት የለም፣ ለውጥ እንጂ ። ከሁኔታዎች በላይ መሆንን እወቅበት። መረጋጋት መልካም ነው።

ውብ ምሽት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም በጤና አደረሳችሁ!

የመስቀል ደመራ በህብረት ቁሞ ደመቅ ያለ ብርሃን ይሰጣል።  የበዓሉ ውበት እና ድምቀት ህብር አንድነት ነው። በዓሉን በመረዳዳት፣ በመጠያየቅ፣ በመከባበር እና በፍቅር በማክበር አብሮነታችንን እናጠንክር።

          መልካም በዓል❤️

@Ethiohumanity
@Ethiohumanity
🛑‘የእኔ’ እንደምትለዋ ቃል ጣፋጭ ቃል የለችንም ፣ በየትኛውም ዕለታዊ የንግግር ብፌያችን ላይ የማትቀር ጨው ናት… ሁሉም ውስጥ አለች… ‘የኔ’ የባለቤትነት ማስረገጫም ናት ፣ ቤቱ የእኔ ነው፣ ዛፉ የእኔ ነው፣ ስራው የእኔ ነው፣ ብሩ የእኔ ነው፣ ሰፈሩ የእኔ ነው ፣ ሃገሩ የእኔ ነው፣ እውቀቱ የኔ ነው ፣ ሃሳቡ የኔ ነው…. ሺህ ምንተ ሺህውን ሁላ ጠቅልላ የእኔ /የእኛ የምታሰኝ አግላይ ነፍስያ አለች።

የኔታችን ከፋ ስትል ደግሞ ህይወት ያለውን ሰው እንደ ንብረት አድርጎ እስከማሰብ ይዘልቃል፣ የኔ ነው እሱ/እሷ እያልን እንደፈለግን የምንዘውረው የባለቤትነት ስሜት  አለ።

🔷የኔ ስለምትሉት ነገር በደንብ አስቡ እስኪ ፣ በስማችሁ የተመዘገበ ሃብት፣ እናንተን የሚያስጠራ ንብረት፣ የእርሱ/ሷ የሚባል አንድ ቁስ፣ እናም ያ ነገር የእናንተ የሆነበትን በቂ ምክንያት አስቡ እስኪ፣ ያላችሁበት የስልጣን ወንበር፣ በኑረት ውስጥ የቋጠራችሁት ጥሪት ፣ በላቤ በወዜ ያገኘሁት የምትሉት ወረት ፣ ድንገት ከእጃችሁ የገባ በረከት… ብቻ አንድ የኔነት.........

♦️እውነት ለመናገር  ምንም የላችሁም ፣ ኑረት የመዋጮ ውጤት ነው… እያንዳንዱ ስምረት ብዙ አለሁ ባይነትን ከጎኑ ይዟል። የሰው ልጅ ከእናቱ እቅፍ እስከ ቃሬዛ ሽክፍ ድረስ በመዋጮ ነው የሚጓዘው። ለብቻው መጥቶ፣ ለብቻው ኖሮ፣ ለብቻው የተሻገረ አንድ ስንኳ የለም፣  አለኝ የምትለውን ነገር ከመነሻው ጠገግ እስከ መድረሻው ጥግ ብታጠናው የኔ ያስባለህን አመክንዮ ባዶነት ትረዳለህ ፣ ከእኛ የሆነ አንዳች የለም ፣ በዙሪያችን ካለው ምልዓት ነው እንዳፈተተን የሸከፍነው፣ የእኛ ስለሆነ የተጨመረ ነገር አይደለም፣ ከነበረው ላይ ነው የተቀዳው።

🔷ታዲያ እኛ ዘንድ ስለምን ተጠጋ?… መንገድ ነን እኛ፣ ለሌሎች መድረሻ ቦይ ፣ እኛ ዘንድ ያለው ሌሎች ዘንድ እስኪደርስ ነው። አንባሪዎች ነን ፣ ባላደራ እንደማለት ነው። ከፍም ዝቅም ብሎ እኛን የተጠጋው ለጎደለው በእኛ በኩል እንዲደርስ ነው። እናም… ሃብታም አይደለም ያለው – ብዙ ሰጪ እንጂ፣ ድሃ አይደለም ያለው ጥቂት ሰጪ እንጂ፣ ምንም ሁን ግን የምትሰጠው አለህ ፣ ማንም ሁን የምትቀበለው አለህ፣ አንተ ለኑረት መጻተኛ ነህ ፣ አለቀ።

🔑ያፈራኸው ሃብት፣ ያካበትከው እውቀት፣ የኖርክበት ቀዬ፣ ያለፍክበት መንገድ፣ የታወቅህበት ፈለግ፣ ያቀረብከው ማዕድ፣ የተጠለልከው ታዛ፣ የተሰጠህ ማዕረግ፣ የጨበጥከው ሥልጣን ፣ የሁሉም እጅ አለበት።

💡ዲዮጋን ፈላስፋ ነው..."ምናምኒት የሌለው" ፈላስፋ፣ በዘመኑ የነበሩ ኃያላን መሪዎች ሳይቀሩ ለአማካሪነት የሚፈልጉት፣ የሚያውቁት በተገኘበት ቃሉን ለመስማት የሚሻሙበት፣ ዝናውን ከሩቅ የሰሙ ሀገር አቋርጠው ወንዝ ተሻግረው ሊያደምጡ የሚሹት ድንቅ የዘመኑ ፈላስፋ። ግን ደግሞ ምንም "የሌለው" ዓይነት… 'ንብረት' ከተባሉ ንብረቶቹ ውሻ፣ አንድ ከቀፎ የተሰራ ማደሪያና ውሃ መጠጫ ቅል ናቸው። ቅሉንም አንድ ቀን ወንዝ ሲሻገር፣ አንድ ሌላ ሰው በርከክ ብሎ በእጆቹ ውሃ እየጠለቀ ሲጠጣ ስላየው "ለካስ ቅልም ትርፍ ኖሯል?" ብሎ ጥሎታል...

📍ታላቁ እስክንድር አለምን በሙሉ እየተቆጣጠረ፡ ቆሮንጦስ ሲደርስ፡ እሱን ለማየትና ለማመስገን ሁሉም ሰው ተሰበሰበ፤ ዲዎጋን ግን አልመጣም። ታላቁ እስክንድር ለማየት የፈለገው ግን ዲዎጋንን ነበር። ንጉሱ ከኋላው በጣም ብዙ ሰው አስከትሎ እየሄደ ሳለ አቀበቱ ላይ ተንጋሎ ፀሐይ ሲሞቅ ዲዎጋንን አገኘው።

እስክንድርም ሰላምታ ካቀረበለት በኋላ እንዲህ አለው፦ ”ዲዎጋን!ስላንተ ጥበብ ብዙ ሰምቻለሁ። የማደርግልህ ነገር ይኖራል?“
”አዎ“ አለ ዲዎጋን ” ጸሀይዋን ስለጋረድከኝ ወደ ጎን ዞር በልልኝ“ አለው። ለሰማይና ለምድሩ የከበደውን ታላቁን ንጉስ በንቀት ስለተናገረ ብለው የእስክንድር ወታደሮች ሊቆራርጡት  ሰይፋቸውን ሲመዙ እስክንድር ግን "ተውት አትንኩት እኔ እስክንድርን ባልሆን ኖሮ ዲዎጋንን መሆን እመርጥ ነበር" አላቸው።

🔷ሕይወት ከቁሳዊው ዓለም ጀርባ ካረገዘችው ትክክለኛው እኔነት ውስጥ ካልሆነ በቀር ከውልደት እስከ ሥጋ ሞት በተዘረጋው አፍታ ውስጥ የምታጋብሰው ንብረት አልያም ስልጣን ያንተ አይደለም። ያንተ የሆነው የማይጠፋው ነው። ከኑረት ፈለግ ላይ የሥጋ ሞት ሲነጥልህ አብሮ የማይነጠለው፣ የመንፈስ ከፍታህ፣ የነፍስ ልዕልናህ ነው፣ ይህ ሃብት ሌባ ሲዘርፈው አልታየም፣ ብልና ዝገት ሲበላው አልታየም፣ እሳትና ጎርፍ ሲያወድመው አልታየም፣ የመድኅን ዋስትናም አይፈልግም፣ እውነተኛ ሃብትህ እርሱ ብቻ ነው፣ ሌላው ሁሉ ትርፍ ነው።

♦️ምንም ነገር ይኑርህ ምንም ነው… ልክ እንደ ቅዠት፣ አሁን ላይ ቁም ፣ ምንድነው ያለህ? እጅህ ላይ ያለው ከትናንት ያደረና በየትኛውም ቅጽበት ሊጠፋ የሚችል ነው።በነግ ተስፋህ ላይ የተንጠለጠለው ስለመምጣቱ የማታውቀው ምኞት ነው… አሁን ምንድነው ያለህ?… ምንም… አንተ ብቻ ነህ ያለኸው፣ ከእጅህ ያለውን ግን የኔ ነው እንዳልከው አጥተኸዋል፣ ቋሚ አይደለምና።

መልሰህ የምትሰጠውን ከእጅህ ታቆያለህና አንተ ባለጸጋ ነህ!!

                            ደምስ ሰይፉ

     ፏ ያለች ቅዳሜን ተመኘን!! 😉

@BridgeThoughts
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
2024/10/01 08:21:53
Back to Top
HTML Embed Code: