Telegram Web Link
💎የመሰብሰብ ጉጉትህ ላይ እስካልሰለጠንክ ድረስ የሚበቃ ነገር የለም፤ ጊዜ በጨመረ - ቀን በተቆጠረ ልክ የፍላጎት አድማስ እየሰፋ፣ የመጨመር ሃሳብ እየተንሰራፋ ይቀጥላል...

💡የመጨመር ጉጉት ጉድለት ላይ ብቻ ከመቆዘም የሚፈጠር ህመም ነው፤ በቃኝ አለማወቅ ልክን የመሳት አባዜ ነው... ምን 'ሀብታም' ብትሆን በፍላጎትህ ላይ ገዢ እስካልሆንክ ድረስ የደስታን ደጅ አትረግጥም...

📍በሕይወት ውስጥ በቃኝ የማለትን ያህል ምልዓት የለም!! ብዙ ሰው "ያለኝ ይበቃኛል" እያለ ያጣቅሳል - እንደ ጥቅሱ ግን አይኖርም፤ ጥያቄው ታዲያ 'ያለው ስንት ሲሆን ነው የሚበቃው?' የሚለው ነው፤

የኑሮ ቅንጦት የበዛበትም፣ መኖር ቅንጦት የሆነበትም እኩል 'ያለኝ ይበቃኛል' ካለ ልክ አይሆንም... ስሜትም አይሰጥም።

📍ቁምነገሩ 'ያለህ መብቃቱ' ሳይሆን ባለህ መብቃቃቱ ነው... ሁሉም ሰው 'ያለኝ ይበቃኛል' ሲል 'የሚገባውን' ብቻ ይዞ ላይሆን ይችላል... የተትረፈረፈለትም - ትራፊ ያጠጠበትም አንድ ሊሆን አይችልም... ግና የሚብቃቃ ሰው በውስንነት ውስጥ ሆኖም ጉድለት አይሰማውም...

💎ስትብቃቃ ያለህ ምንም ያህል ይሁን ደስታ ሳይርቅህ ትኖራለህ፤ ስታግበሰብስ ግን ምድሪቱ ሙሉ ስጦታ ሆና ብትቀርብልህ እንኳ በቃኝ አያውቅህም...አንተ ዘንድ የበዛው ከሌላው ጎድሎ ነው፤ በማትፈልገው ጊዜ በስብሶ ሳትጥለው በሚፈልገው ጊዜ ለሚጠቀመው ስጠው!!

ደምስ ሰይፉ
@BridgeThoughts
[የግል ቻናሉ ነው ተቀላቀሉት ]

ውብ አዳር ❤️

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthiohumanityBot
🛑 ኢኮኖሚክስ ላይ 'Water & Diamond paradox' የሚባል እሳቤ አለ... ለኑረት ወሳኙ ነገር ውሃ ነው ፣ ግን 'እርካሽ' ነው። አልማዝ ለህላዌ የሚያበረክተው ድንቡሎ የለም  ግን ውድ ነው። ለዚህም ይመስላል አንስታይን "The important things are always simple" ማለቱ...

ዘግይቶም ቢሆን የሚገባህ እውነት ነገሮችን በውድና ርካሽ የሚፈርጀው አስተሳሰብ እንጂ የነገሩ ወሳኝነት አለመሆኑ ነው። እርግጥ ማሕበረሰባዊ ስምምነቶች ለተፈጥሮ ህግ ከመገዛት ይልቅ መንጋነትን ያበረታሉ።

ለምሳሌ፦
፨ ዋናው ቁምነገር አብሮነትና ፍቅሩ ቢሆንም ውዱ ግን ሰርጋችን ነው...
፨ ትልቁ እውቀት ራስን ማወቅ ቢሆንም ውዱ ግን ከአስኳላ የምንገዛው ነው።
፨ ጠቃሚው ውበት ጸጥታ ቢሆንም የምንከፍለው ግን ለሚበጠብጠን ጩኸት ነው።
፨ ጤናችን ያለው ንጹህ ውሃ ውስጥ ቢሆንም ብዙ የምንከፍለው ግን ለመታመሚያችን አልኮል ነው... ወዘተ

እልፍ ርቀት ሮጠህ ስታበቃ ቆም ብለህ 'ለዚህ ጉዳይ ይህን ያህል ዋጋ መክፈል ነበረብኝን?' ብለህ ብትጠይቅም መሮጥህን ግን አታቆምም።

በዙሪያህ ያሉ ነገሮች ጡዘትህን እንጂ ቆምታህን አያበረቱም ፣ ይልቁን በውድድር ውስጥ እንድትቆይ ይገፉሃል ከጓደኛህ ትወዳደራለህ ፣ ከጎረቤትህ ትወዳደራለህ፣ከባልደረባህ ትወዳደራለህ ፣ ከንግድ አቻዎችህ ትወዳደራለህ... እናም በምስሉ ላይ እንደምታየው ማቆሚያ በሌለው ዙረት [Vicious circle] ውስጥ ትቧችራለህ።

📍ዛሬ የሆነ ነገር ለማግኘት ትሮጣለህ... ደርሰህ ስትይዘው ይቀልብሃል፣ነገ ሌላ ለመጨበጥ ትዘረጋለህ፣ ደርሰህ ስታየው 'ለዚህ ነው በሬዬን ያረድኩት?' ያስብልሃል... እንደገና ሌላ ሩጫ. እንደገና ሌላ ፍለጋ... እንደገና ሌላ መባከን...

እጅህ ላይ ያለው ካላስደሰተህ እርግጠኛ ሁን ሊመጣ ያለውም አያረካህም። በበርህ አበባ ሳትፈነድቅ በገነት ውበት አትመሰጥም። ደስታን ከውጭ ከመፈለግ በላይ ጉድለት የሚመስለኝ ይህ ነው። እየፈለጉ መቀጠልን ማቆም ባይቻል በደረሱበት አለመብቃቃት ትልቅ ጉዳት ነው የደረስክበት ደግሞ 'አሁን' ነው ይህ ቅጽበት.አሁንና እዚህ።

አንድ ጊዜ የምረቃዬ መጽሔት ላይ ከፎቶ ስር ለሚሰፍር ጽሑፍ 'የእኔ ቀን ነገ ናት' የሚል ቃል ሰጥቼ ነበር... አሁን ላይ ቆም ብዬ ሳስብ 'ምን ሆኜ ነው ግን' እላለሁ. እንዴት ሰው እርግጠኛ ከሚሆንበት ዛሬ ይልቅ በማያውቀው ነገ ላይ የደስታውን ውበት ያንጠለጥላል?  ደስታ ኑረትን ግድ ይላል እኮ... 'ነገ እንትን ሳገኝ እደሰታለሁ' የምትል ከሆነ ለመደሰት ቀጠሮ እየሰጠህ ነው፣ ከዚያም በላይ ደስታህን በነገሩ መኖር አለመኖር ላይ እየመሰረትክ፣

ደግሞስ 'ለደስታ ምን ያህል ነው የሚበቃን?' ስንት ብር? ስንት መኪና? ምን ያህል ቁስ?

በዙሪያዬ ብዙ 'ያላቸው' - ተነጫናጮች እና ደግሞ 'ምንም የሌላቸው' ደስተኞች አየሁ ፣ ብዙ ሃብታም የበሽታ ቋቶችና ድሃ ፍልቅልቅ ፊቶችን ሳስተውልም ይሄ ጥያቄ ትዝ ይለኛል፦
.
.
መልሱ እኮ በአጭሩ "ደስታ ውስጣዊ እንጂ ቁሳዊ [ሰበባዊ] አይደለም" የሚለው ነው። ሆኖም በተግባባንበት መንገድ ሄጄ 'ለመደሰት ስንት ያስፈልገናል?' እላለሁ ፦ ምንም አይበቃንም!!* ምናልባት ምድርን የሚያህል ሃብት ቢኖረን እንኳ ሌላ ፕላኔት ማሰሳችን አይቀርም፣ ደስታ ግን ከብዛትም ሆነ ከነገር ጋር አትቆራኝም።

አዎን... ደስተኛ መሆን ካሻህ ባለህ ተብቃቃ Be Content እልሃለሁ!!

📍'የሰው ልጅ ፍላጎት ገደብ የለውም' በሚል ከንቱ ስብከት እየተነዱ 'ያለኝ ይበቃኛል' ማለት እንደሚከብድ ግልጽ ነው።ያም ሆኖ በፍላጎታችን ላይ የምንሰለጥን እንጂ ፍላጎት የሚሰለጥንብን እንዳልሆንን ማወቅም ጠቃሚ ይመስለኛል። አግበስባሽነት በማግኘት ላይ እንድትመሰጥ እንጂ ባለህ ደስታ እንድትፈጥር ፣ አሁን ያለህን ሐይወት እንድታጣጥም ዕድል አይሰጥምና።       

                     ደምስ ሰይፉ
                  @BridgeThoughts
    

            ውብ አሁን ❤️

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthiohumanityBot
🔴የሕይወት ግንድ ብዙ ቅርንጫፎች ነን!!

📍 አንድ ውቅያኖስ ላይ ነን  ‘የአንተ’ ታንኳ ሲናጥ ‘የእኔው’ ደንገል መንቀጥቀጥ ይጀምራል፣ ‘የእርሷ’ ጀልባ ሲቀዝፍ የባሕሩ ለመምቴ ይናጣል፣ የሰላምህ እርግብግቢት የሰላማችንን ንፋስ ይጠቅሳል… የሕመማችን ትንፋሽ የደስታ መንፈሷን ይበርዛል።ስለምን - ‘እኔም’፣ ‘አንተም’፣ ‘እርሷም’፣ ‘ሁላችንም' አንድ ነንና።

🔷መምህሩ ራማና ማሃርሺ …
“How are we Supposed to treat others?” ብለው ቢጠይቁት…
“There are no others” ሲል የመለሰው ለዚህ ነበር።

በተገበርከው ክፋት ብቻ ሳይሆን በተብሰልስሎትህ ሂደት ነገር ዓለማችን ይታወካል። በተነፈስከው በጎ ቃል አይደለም ባሰላሰልካት ደግነትም መውጣት መግባታችን ይዋባል… ብቻህን አይደለህምና የብቻ ሰላም የለህም… አልተነጣጠልንምና የብቻ ሕመምም አይኖርህም

የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን ፣ እኛም ሆንን በዙሪያችን ያለው የተፈጥሮ ስንክሳር የውቅያኖሱ አንድ ጠብታ ነው ፣ አንዲት ጠብታ የምትፈጥረው ለመምቴ /Ripple/ የሌላውን ለመምቴ ትነካለች… እኒህ የሃሳብ፣ የስሜትና የድርጊት ለመምቴዎች በሌላኛው ተፈጥሮ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አላቸው… በበጎም በክፉም… ተመልሰው ግን ወደ ምንጫቸው ይመጣሉ፣ በመዋኛ ገንዳ ውስጥ የፈጠርከው የውሃ ለመምቴ የገንዳውን ግድግዳ ገጭቶ ወዳንተ እንዲመለስ ማለት ነው።

🔶ከኔ ቤት ላይ የረጨኸው እሳት ከሆነ ነበልባሉ ያንተን ቤት ይነካል ፣ ሽቶ ስትረጨኝ የመዓዛው ቅንጣቶች ለአፍንጫህ ውብ ጠረን ይለግሳ፣ “You reap what you saw”ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል ፣ ይህን ምስራቃውያኑ Karma ሲሉት ሌሎች ደግሞ Boomerang ይሉታል… Boomerang አውስትራሊያኖቹ አቦርጂኒስቶች ከእንጨት የሚሰሩት ደጋን ቅርጽ ያለው የአደን መሳሪያ ሲሆን ወርዋሪው ዘንድ ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጎ የሚነደፍ ነው። ለሃሳብ፣ ለስሜትና ድርጊትህ መጠንቀቅ የሚኖርብህ ወላፈኑ ‘ለእኔም’፣ ‘ለእርሷም’፣ ‘ለእነርሱም’ እንደሚተርፍ በማሰብ ነው… ምክንያቱም
We are all One!

🔷ሰው ብቻ ሳይሆን ከዋክብቱ፣ ሕዋው፣ ምድሪቱ፣ እንስሳው… በሚታየውና በማይታየው ዓለም ያለው ነገር ሁሉ በአንዳች ተፈጥሯዊ ክር የተሳሰረ ነው… ማሰሪያው ስላልታየ መተሳሰሩ የለም አይባልም።

‘እዚያ ቤት ሲንኳኳ እኛ ቤት ይሰማል’ ‘ከወዲህ አንተን ሳማ እዚያ ከንፈር ትነክሳለህ’፣ ‘እከሊት ስታነሳኝ በስቅታዬ አውቀዋለሁ’፣ ‘የሰፈር ውሻ ሲያላዝን አንዱ አዛውንት ሊያልፉ ነው ማለት ነው’… ‘ውስጥህ ሲረባበሽ ራቅ ካለ ቤተሰብህ አልያም ወዳጅህ ቤት አንድ አደጋ አለ ማለት ነው’፣ 'ቅንድብህ ሲርገበገብ እንግዳ ሰው ልታይ ነው'፣ የጥንቶቹ ይሄ እውነት ስለገባቸው ይመስለኛል መሰል አባባሎች ያቆዩልን።

♦️በረከት በላይነህ "የመንፈስ ከፍታ" ላይ እንዲህ ይለናል👇

“የግልህ ወንዝ ስለሌለህ ብቻህን የምትሰራው ድልድይ የለም! የሰማዩ ርቀት፣ የምድሪቱ ስፋት በ’እኛ’ እንጂ በ’እኔ’ አይለካም፡፡ ውዱ ‘እኔ’ ከ’እኛ’ የተሰራው ነውና!”

🔷እዚህ ጋ ነው ስለ ዝምድናና ባዳነት ያለን ግንዛቤ መፈተሸ ያለበት፣ ስለ ዘርና ቀለም ያለን መረዳት መጤን ያለበት፣
Peter Russell “The Global brain” ብሎ ባሰናዳው ቪዲዮው ላይ አንድ በጨረቃ ላይ የተጓዘ የጠፈር ሳይንስ ተመራማሪ የተናገረውን ውብ ቃል ትሰማላችሁ
“When you are up there you are no longer an American citizen or a Russian citizen. Suddenly those boundaries disappear. You are a planetary citizen.”

🔑ኑረዲን ዒሳ በአንድ ግጥሙ.

“ባዳውን አፍቅሮ፣
ከባዳው ልጅ ፈጥሮ፣
እኔን ባዳዬ አለኝ - ሰባት ቤት ቆጥሮ፣
ልጁን ዘመዴ አለው - በፍቅር ታውሮ፡፡
ቅጠሉ ነኝና ለረጂሙ ሃረግ፣
እኔም ዘመዱ ሆንኩ - መቼስ ምን ይደረግ?” ብሏል…

❤️ፍቅር ሲገባን የልዩነት ቅዠት ይተናል ፣ ማንነት ሲገባን ሕብራችን ይታያል ፣ ጥበብ ሲያጥጠን ግን ልዩነት ያዜምልናል፣ ፍቅር ስንሰጥ በዙሪያችን ባሉት ላይ እርግብግቢቱ ፍቅርን ይወልዳል፣ክፉ ስናስብ ደግሞ በተቃራኒው ክፋት ይጠነሰሳል፣ከፊልዱ ውጭ እስካልሆንን ድረስ ከምላሹ ተጽዕኖ ልናመልጥ አንችልም።

                             ደምስ ሰይፉ
@bridgeThoughts
ውብ ቻናሉ ነው

         We are all One!
           ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍ደፋር መሆን ይኖርብናል ያልተሄደበትን መንገድ ለመሄድ መድፈር

ትእቢትን እልህን ጥላቻን ይሉኝታን ለመተው መድፈር

ራስን ለማዳመጥ መድፈር

💡አዎ ብዙ በደል ፈፅመሀል ተፈፅሞብሀል። ብዙ ሰው ጠልተሀል፣ ተጣልተሀል ፣  ተጠልትሀል ፣ ልብህ ተሰብሯል፣ ልቦችን ሰብርሀል ፣ግን ደግሞ ከዚህ ሁሉ ጋር ታርቀህና ራስህን አስታርቀህ ዳግም ለመውደድ ፣ ዳግም ለማዘን ፣ዳግም ለመርዳት፣ ዳግም እርዳታ ለመጠየቅና በቅንነትና በፍቅር ለመኖር ድፈር።

📍መጀመርያ ግን ከራስህ ጋር ለመታረቅ ድፈር። ራስህን ከነሙሉ ስህተቶቹ፣ ግድፈቶቹ ፣እንከኖቹ፣ውሸቶቹ፣ ቅጥፈቶቹ፣ አስመሳይነቶቹ ሁሉ ለመቀበል ለማዳመጥና ለመውደድ ድፈር

የፍቅር የይቅርታ ዘመን ነው ሲባል ወደሰማይ አታንጋጥ፣ ወደጎረቤቶችህና ጠላቶቸ ብለህ ወደፈረጅካቸው ሁሉ አታፍጥጥ

መጀመርያ ከራስህ ጋር ለመታረቅ ወደውስጥህ ተመልከት፣ ወደራስህ ተመለስ ፣ ውስጥህን ፣ልብህን ፣ ህሊናህን አፅዳ፣ሰው የሚሰጥህ ክብር አንተ ለራስህ በምትሰጠው ሚዛንና መጠን ነውና ለራስህ ትልቅ ዋጋና ብዙ ክብር ይኑርህ

💡ራስን መመልከት ራስን ወደ መሆን የሚያደርስ ወሳኝ መንገድ ነው። ራስህን ስትመለከት የወንድምህን ጉድፍ ሳይሆን የአንተን ተራራ ታስተውላለህ፥ በዚህ ውስጥ ደግሞ ተራራህን እየነቀልክ ራስን ወደ መሆን ታድጋለህ። ራስህን ስትሆን ብዙ ነገሮችን ታሸንፋለህ፥ መሰናክሎችን በቀላሉ አልፈህ፥ የነከሰህን የመከራ ጥርስ ውሃ የማድረግን ጥበብ ትጎናጸፋለህ።

🔑ብቻ ምን አደከመህ ራስህን ስትሆን ብዙ የደረብካቸው አላስፈላጊ ኮተቶችን ከራስህ ላይ አውርደህ፥ ንጹህ አንተነትህን ብቻ ያነገበ ማንነት ስትገነባ ያን ጊዜ ሰው መሆን ትጀምራለህ።እናም ራስህን ለመውደድ ድፈር።

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
💡በየትኘውም የህይወት መንገድህ መልካም ስብዕናን አየዘራህ ስትጓዝ ባታይውም ለሌሎች ፍካት ሆኖ ይቆያል ።ደግነትህ ለብዙዎች የዕድሜ ማራዘሚያ ሰበብ ስለሆነ እንዳይከስም ጠብቀው። ለጋስ በመሆንህ በምላሹ ከሌሎች ምንም ነገር አትጠብቅ። የጊዜ ጉዳይ ቢሆን እንጂ መልካም ነገር ሁሌም ከፈጣሪህ በጎ ምላሽ አለው።

📍ህሊናህ ይረካ ዘንድ ከመቀበል ይልቅ ሰጪ ሁን። በምግባርህ ፈጣሪህን ለማስደሰት ሁሌም ጥረት አድርግ። እርሱ ከወደደህ ደስታ በእጅህ ትገባለች። በመልካም ስነ ምግባር ሽቶ የተርከፈከፈ ስብዕና ከመሬት በታች አፈር ለብሶ እንኳ መዓዛው ያውዳል።

💡አስተሳስብህ ካለባበስህ የበለጠ ሲያምር መልካምነትህ ከምትቀባው ሽቶ የበለጠ ሲያውድ ስነምግባርህ ከመልክህ የበለጠ ሲያምር የዝነጣ ጣሪያ ላይ ደርሰሀል ማለት ነው። ላመነን ሰው መታመን ከህሊና ወቀሳ መዳን ነው። ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፡፡ በህይወታችን የምናሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም።

  ውብ አዳር❤️

@Ethiohumanity
@EthioHumanity

@EthiohumanityBot
♦️ምክር ለወዳጅ

📍ወዳጄ ሆይ !

አዲስ ግኝት የመሰለህ እውቀት ከራስህ የመነጨ ሳይሆን ፈጣሪ ከሰጠህ አእምሮና አብርሆት የተገኘ ነው ። እውቀትን የጣለ እምነት ፣ እምነትን የጣለ እውቀት አይኑርህ ። እውቀት የሌለው እምነት ራስን ማደንቆር ነው ። የሚታወቅ ነገር ሳለ ፣ ማወቂያ መሣሪያው አእምሮ ከተሰጠህ የማወቅ ግዳጅ አለብህ ። ሰውን ሰው የሚያደርገው በእውቀት የተፈጠረና በእምነት የሚያድግ መሆኑ ነው ። እምነት የሌለው እውቀት ግን ማለስለሻ እንደሌለው ተሽከርካሪ እርስ በርሱ የሚፋጭ ፣ ድምፁ የሚረብሽ ፣ ዕድሜው የሚያጥር ነው ።

📍ወዳጄ ሆይ !

እኔ እንጂ እነርሱ ምን አለባቸው ? አትበል ። ብዙ ባለበት ዓለም ምንም የሌለበት ፍጡር የለም ። ሕፃናትም በረሀብ ፣ ልጆችም በበሽታ ይሰቃያሉ ። እንስሳትም በሰው የመጣውን ሐሣር ይካፈላሉ ። አንተ ስላለህ ሁሉ ያለው አይምሰልህ ። አንተ ስላጣህም ሁሉ ያጣ ሁኖ አይሰማህ  ፣ ብርታት ሌላውን ከማበርታት ይገኛል ። ሌላውን ስታበረታ አንተም በርትተህ ትገኛለህ ።

📍ወዳጄ ሆይ

ሰዎችን የምታሸንፋቸው በፍቅር ፣ የሚያሸንፉህ በክብር ነው ። እውነተኛ ፍቅር መስጠት ካልቻልህ በሽንገላ ራስህን ማድከም ፣ ትዝብት ላይ መውደቅ አያስፈልግህም። የጎላ ታይታ መውደድ ወደ ብዙ መሰወር ይለወጣል ። “እዩኝ ፣ እዩኝ ያለ ገላ ፣ ደብቁኝ ደብቁኝ ይላል” እንዲሉ ፣ ጓዳህን ለሁሉ አታሳይ፣ ምሥጢርህን በአደባባይ አትግለጥ። ክብር በትግል አይገኝም ፣ መፈራትም እውነተኛ ክብርን አያመጣም።

📍ወዳጄ ሆይ

ከፍታህን ከፍ ባለ ቃል ሳይሆን ከፍ ባለ ኑሮ ግለጠው። ሕያው መንፈስ አለህና በቁሳቁስ አትመካ፣ የሰው ንብረት አትቀማ! ሰውን ወልዶና ተዋልዶ ኑሮውን ከመሰረተበት መሬት አትንቀል፤ አታፈናቅል። እንጀራው ለሁሉ እንዲበቃ አድርገህ አስፋው! ለዚህ ፍቅር ያስፈልግሃል ፣ ይህ የሚቻለው ፍቅር ሲኖር ብቻ ነውና፣ ልብህ ለሰው ልጅ ሁሉ በፍቅር እንዲሞላ ይሁን።

📍ወዳጄ ሆይ

የሆነው መሆን ስላለበት ነው ። ፍርሃት የታዘዘን ነገር ከመምጣት አያድነውም ። በፈቃድህ ወደ እዚህች ዓለም ምንም ነገር አላመጣህምና ፣ እንዴት ይህ ይደርስብኛል? አትበል። የቀለጠ ወርቅ ጌጣጌጥ እንደሚይሆን የተጠረበ ድንጋይ ሐውልት እንደሚይሆን ሁሉ ፣ እንተም በብዙ ችግሮች ውጣ ውረዶች ባለፍክ ቁጥር አንተነትህ እያደገ መሆኑን አትርሳ !

🔺ታዲያ ወዳጄ፦

ቅን ልብ የጨለማ ዘመን መብራት ነውና ቅንነት ይኑርህ ። ማስተዋል የሌለበትን ዓይናማነትን አትውደደው ። ሰውን በፍቅር እንጂ በኃይል አትሳበው ፣ የሚያደምጡህን አድምጣቸው ። ራስህ የሠራኸውን ራስህ እንዳታፈርሰው ሥራህን በችኩልነት አትፈጽም ፣ ትዕግሥት የጎደለው ቤት በተገነባ ቁጥር መፍረሱ ይፈጥናል ። የረዳሃቸው ሌሎችን ሲረዱ ለማየት ናፍቆት ይደርብህ፣ የሰው ሰውነቱ መታያው ልቡናው ዉስጥ በሰነቀው ቅንነት ነውና፣ በሽተኛን ከሚፈውስ ባለ ስጦታ ፣ የተከዘን ልብ የሚያጽናና ወዳጅ ይበልጣል።

               ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
🛑እያንዳንዳችን ፍቅርን የምንገልጽበት የራሳችን የሆነ መንገድ አለን። እናትና አባት ለልጆቻቸው፤ ወንድም ለእህቱ፤ እህት ለወንድሟ፤ ጓደኛ ለጓደኛ፤ ሚስት ለባሏ፤ ባል ለሚስቱ፤ ፍቅራቸውን በተለያየ መጠንና መንገድ ይገልጹታል። በፍቅር ስም ብዙ ስህተቶች ሲፈጸሙ ይስተዋላል። ፍቅር ስህተት ሆኖ ሳይሆን የሚገለጽበት መንገድ ልክ ስላልሆነ ብቻ። ምክንያቱም ፍቅር ምን ጊዜም በየትኛውም ጊዜ እና ቦታ ስህተት ሆኖ አያውቅም።

🔷ፍቅር ጉዳት የሚሆነው፤ ስህተት የሚመስለው የሰዎችን ልብ የሚሰብረው፤ ፍቅር ስህተት ሆኖ ሳይሆን ያስተላላፊው ስህተት ሲኖር ነው። ፍቅር ሳይበረዝ እና ሳይከለስ ለመተላለፍ ነጻነትን ይፈልጋል። ነጻነትን የተነፈገ ፍቅር ለተቀባዩ እዳ ይሆናል። ወላጆች ለልጆቻቸው ያላቸውን ፍቅር ለመግለጽ አለቅጥ ሲቆጣጠሩ በልጅ እና በወላጅ መካከል ያለው የግልጽነት ድልድይ ይሰበራል። ወላጅ ፍቅሩን “እኔ
አውቅልሃለው” በሚል አገላለጽ ሲገልጽ ልጆች በወላጅ ተጽዕኖ ነጻነታቸውን መስዋት ያደርጋሉ።

♦️ ይህ ማለት ወላጆች ልጆቻቸውን መቆጣጠር የለባቸውም ሳይሆን ፤ እስከምን ደረስ መሆነ እንዳለበት ልብ ሊባል ይገባል። ወላጆቻቸውን ፍራቻ ልጆች ብዙ ስህተቶችን ይፈጽማሉ ። ውድቀታቸውን እና የህይወት ፈተናዎቻቸውን ለወላጆቻው መግለጽ የሚከብዳቸው፤ ወላጆች ፍቅራቸውን የገለጹበት መንገድ ልክ ባለመሆኑ ነው። በተለይ በኛ ማህበረሰብ ግልጽነት የሚጎድለን ፤ ወላጆቻችን ፍቅር አንሷቸው ሳይሆን አገላለጻቸው ወደ ፍርሃት ስለሚወስደን ነው።

🔷በየትኛውም ቦታ እና ግንኙነት ፍቅር ህይወት ሊዘራ የሚችለው ነጻነት ስኖረው
ብቻ ነውና ፣ የምንወደውን ጽጌሬዳ ቆርጠን ቤት አናስቀምጠው ምክንያቱም ይሞታልና። ይልቁንም እውነተኛ ፍቅር ካለን ባለበት እንዲያብብ እንፈቅድለታለን። የምወዳቸውን ሰዎችም ማስተናገድ ያለብን እንዲህ ነው፤ እውነት የምንወዳቸው ከሆነ ነጻነታቸውን እንስጣቸው። በፍቅር ስም እነሱ የመረጡትን ሳይሆን እኛ የመረጥልናቸውን እንዲኖሩ አናስገድዳቸው።

📍በዚህም ምድር ላይ ለሰው ከነጻነት የበለጠ ስጦታ የለም። በነጻነት ውስጥ እምነት አለ በራሷ እንደትበር የተለቀቀች ወፍ ሌሎች በሷ እንደሚያምኑ ይሰማታል። በነጻነት ውስጥ ግልጽነት አለ፤ የሚሸፈን የሚከደን ምንም ነገር ስለሌለ። ፍቅር ደግሞ ያለእመነት እና ግልጽነት ዋጋ አይኖረውም። ለዚህ ነው ፍቅር እና ነጻነት ተለያይተው መሄድ የማይችሉት።

የምንወዳቸውን ሰዎች እናስብ ፍቅራችንን እንዴት እየገለጽንላቸው ነው? ነጻነታቸውን በሚጋፋ መልኩ ከሆነ እስቲ ትንሽ ቆም ብለን እናስብበት⁉️

           ውብ  አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
💎እንደ ወርቅ እንደ አልማዝ ሁኑ

ወርቅና አልማዝ ውድ ናቸው። የትም አይገኙም። ብዙ ተቆፍሮ፣ ተለፍቶ ነው የሚገኙት። የትም በቀላሉ የምትገኙ አትሁኑ። የራሳችሁን ዋጋ እንደ ወርቅ፣ እንደ አልማዝ ውድ የምታደርጉት ራሳችሁ ናችሁ። ለጠራችሁ ሁሉ አቤት፣ እንሂድ እንጂ ላላችሁ ሁሉ ወዴት አትበሉ።

💡Rarity [አለመገኘቱ] ብቻ ግን በቂ አይደለም። ወርቅና አልማዝ ጌጥ ናቸው። ያምራሉ። ወርቅ የቀይ ቢጫ ውብ መልክ አለው። አልማዝ በባህሪው colorless ከለር አልባ ነው። አልማዝ ብዙ አይነት ቀለም ይዞ የምናገኘው በውስጡ ካሉት impurities የተነሳ ነው። ግን መሰረታዊ ውበቱን አይቀንሱትም። የሰው ልጅ ውበት ንጽህና ነው። ንጹህ አካል፣ ንጹህ መንፈስ፣ ንጹህ አስተሳሰብ!!

📍አንድ ነገር በቀላሉ የማይገኝ ብቻ መሆኑ ተፈላጊ አያደርገውም። ዋናው ጉዳይ ባህሪያቶቹ ናቸው። የወርቅ በጣም ተፈላጊ ባህሪ ወርቅ አይዝግም። እንደ Iron ብረት ከሆንን ወደ ውስጣችን ሰርጎ የገባው ውሃ ሁሉ ያዝገናል። መንፈሳችንን ይረብሸዋል። ወርቅ ሁኑ። ወርቅ ሚሊየን አመት ውሃ ውስጥ ቢቀመጥ አይዝግም። በዚያ ላይ malleable ተዛዥ ተጣጣፊ ነው። እንደ ወርቅ ሊቀጥን የሚችል ሌላ ኬሚካል ኢለመንት የለም።

💡አልማዝ ደግሞ በጣም ጠንካራ ነው። ማንኛውንም ነገር በብቃት መቁረጥ ይችላል። በነገራችን ላይ አልማዝና ከሰል አንድ ናቸው ደግሞም አይደሉም። አንድነታቸው ሁለቱም የተሰሩት ካርበን ከሚባል ኢለመንት መሆኑ ሲሆን ልዩነታቸው እነዚህ የካርበን አተሞች በአልማዝና ከሰል ውስጥ ያላቸው ኬሚካል ስትራክቸር ነው። ከሰልን ወደ አልማዝ መለወጥ በብዙ ፓስካል ፕሬዠር [Pascal Pressure] ወይም ብዙ ግፊትና እና ብዙ ኬልቪን [Kelvin] ሙቀት ያስፈልጋዋል።

📍ውስጣችን ያለው ማንነት ካርበን ነው። ከሰል ወይም አልማዝ ማድረግ የኛ ፋንታ ነው። የህይወት ፈተና የከሰል ማንነታችንን ወደ አልማዝ የሚቀይር እርሾ ግፊት ነው። እነዚህ የወርቅና የአልማዝ ኬሚካላዊ ባህሪያት ብዙ ኢንደስትሪያል ጠቀሜታ አላቸው። ወደዚያ በዝርዝር አንገባም። አሁን የምንወስደው ከወርቅና ከአልማዝ ለህይወት የሚጠቅመንን ብቻ!

ቴውድሮስ ሸዋንግዛው

ውብ ሰንበት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
ትምክህት እና እብሪት
በሀይሉ ገ/መድህን
የጥበብ ምሽት

ማህበረሰብ አንቂው እና ወግ አዋቂው።

🔊አቶ በሀይሉ ገብረመድህን


ውብ ምሽት♥️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
📍በሱፊዎች ዘንድ የሚነገር አንድ ታሪክ አለ..

♦️በስቃይ የተሞላ ህይወትን የሚመራ አንድ ሰው ነበር... ሰውዬው ወደ አምላኩ በሚጸልይበት ጊዜ ሁሉ "ሁሉም ሰው ደስተኛ ሆኖ እየኖረ ለምንድነው እኔ ብቻ የምሰቃየው?" እያለ ይጠይቅ ነበር፡፡

አንድ ቀን ጥልቅ በሆነ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ሆኖ ለአምላኩ እንዲህ ሲል ጠየቀ... "አምላኬ የማንኛውንም ሰው ስቃይ ብትስጠኝ ልቀበል ዝግጁ ነኝ... እባክህ የእኔን ግን ውሰድልኝ... ከዚህ በላይ ልሸከመው አልችልም" ብሎ ተማረረ፡፡

ጸሎቱን ጨርሶ እንደተኛ ታዲያ ውብ የሆነ ህልም አየ... በህልሙ ውስጥ አምላክ ሰማይ ላይ ተከስቶ እንዲህ ሲል ይደመጣል... "ስቃያችሁን ሁሉ ወደ ቤተ መቅደሱ አምጡ..."

እያንዳንዱ ሰው የየራሱ ስቃይ ያታከተው ስለነበር "የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ፤ የእኔን ግን ውሰድልኝ፤ ከዚህ በላይ መሸከም አልችልም" ብሎ ይጸልይ ነበር...

🔺በዚህም ምክንያት ሁሉም ሰው ስቃዩን በቦርሳ አጭቆ ወደ ቤተ መቅደሱ አመራ... ባለታሪኩን ጨምሮ ሁሉም ሰው ጸሎቱ በአምላኩ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘለት በስፍራው ላይ ከፍተኛ የደስታ ስሜት ነግሶ ነበር...

💡ከቤተ መቅደስ ሲደርሱ አምላክ እንዲህ ሲል እወጀ... "ቦርሳችሁን ከግድግዳው ስር አስቀምጡት"... ሁሉም ሰው ቦርሳውን አስቀምጦ ጨረሰ... አምላክም እንዲህ ሲል በድጋሚ አወጀ... "አሁን መምረጥ ትችላላችሁ፤ ማንኛውም ሰው የፈለገውን ቦርሳ መውሰድ ይችላል"...

🔺በዚህ ጊዜ ቀን ከሌሊት 'የማንኛውንም ሰው ስቃይ ለመቀበል ዝግጁ ነኝ' እያለ ሲጸልይ የነበረው ሰውዬ ሌላ ሰው የእርሱን ቦርሳ እንዳያነሳበት እየተጣደፈ ወደ ራሱ ቦርሳ ሄደ... ሁሉም ሰው እንደ ሰውዬው ሁሉ የየራሱን ስቃይ ያጨቀበትን ቦርሳ ፍለጋ ተራወጠ... በሚያስገርም ሁኔታ እያንዳንዱ ሰው የየራሱን ስቃይ በድጋሚ ለመሸከም ዝግጁ ነበር...

ምንድን ነበር የተከሰተው?...

💡በህይወታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ አንዳቸው የሌላኛቸውን ችግር ስቃይና መከራ ተመለከቱ... እንዲያውም ከራሳቸው የሚበላልጡ፣ የሌሎች ሰዎች ስቃይ የታጨቀባቸው ትላልቅ ቦርሳዎች እንዳሉም ተገነዘቡ... በዚህ ላይ ሁሉም ሰው ከራሱ ስቃይና መከራ ጋር ተላምዷል... የራሱን ስቃይ ማባበልና መቻል አይቸግረውም... የሌላውን ሰው የመከራ ቦርሳ ቢወስድ ግን ከቦርሳው ውስጥ ያለው አዲስ አይነት መከራ ምን አይነት እንደሆነ አያውቅም... ምናልባት የባሰም ሊሆን ይችላል...

አላሚው ሰው ከእንቅልፉ ሲነቃ በድጋሚ ጸለየ... "አምላኬ ስላሳየኸኝ ህልም አመሰግንሃለሁ...ከዚህ በኋላ እንዲህ አይነቱን ጥያቄ ደግሜ አልጠይቅህም... የሰጠኸኝን ነገር ሁሉ የሰጠኸኝ በምክንያት ነው" ሲል ተናገረ...

📍የቅናት ስሜት ካለባችሁ በማያቋርጥ ስቃይ ውስጥ ትወድቃላችሁ፤ የምትቀኑ ከሆነ ሀሰተኛ ትሆናላችሁ፤ ማስመሰልም ትጀምራላችሁ፤ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየትም ትሞክራላችሁ... የሆነ ሰው ጋር ኖሮ እናንተ ጋ የጎደለ ነገር ያለ ሲመስላችሁና ነገርዬውን ማግኘት የማትችሉ ከሆነ ከሰው ላለማነስ ብላችሁ የረከሱ ነገሮችን ማበጀት ትጀምራላችሁ...

💡ለቀናተኛ ሰው ህይወት ሲኦል ትሆንበታለች... ስለሆነም ቅናታችሁ ይጠፋ ዘንድ ራሳችሁን ከሌላው ጋር ማነጻጸር አቁሙ... ይህን ስታደርጉ ያልሆናችሁትን መስላችሁ ለመታየት የምታደርጉትን ጥረትና ሌላውን ለመምሰል የምታደርጉትን ሙከራ ታቆማላችሁ...

🔑ይህ ሁሉ ሂደት የሰመረ የሚሆነው ግን ውስጣዊውን ሀብታችሁን ማሳደግ ስትችሉ ነው... ለማደግ ጣሩ... ይበልጥ እውነተኛ ግለሰብ ለመሆን ሞክሩ... እራሳችሁን አፍቅሩ... ለራሳችሁ ክብር ስጡ... ይህ ሲሆን የገነት በሮች ክፍት ይሆኑላችኋል... በእርግጥ ወደ በሮቹ ተመልክታችሁ ስለማታውቁ ነው እንጂ እስካሁንም በሮቹ ክፍት ነበሩ...

ደምስ ሰይፉ

ውብ ቅዳሜ❤️

@EthioHumanity
@BridgeThoughts

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💎ወዳጄ ሆይ የሚገርም ነገር ልንገርህ ድልድይም ግርግዳም  ከድንጋይ ነው የሚሠራው። ግን ተግባራቸው ለየቅል ነው ድልድይ አንዱን ከሌላው ሲያገናኝ ግርግዳ ግን አንዱን ከሌላው ይለያል። ፍላጎትህ ሃሳብህ ተሰጥዎህ አልሳካ ቢልህ በፍላጎትህና ባንተ መካከል ያለውን ዶፍ  የሚያሳልፍህን ድልድይ ገንባ እንጂ ፍላጎትህን ግርግዳ ሠርተህ አትከልክለው አስተውል ያሰብከው ካልተሳካ የተስፋ መቁረጥ ግርግዳ ሳይሆን የጽናት ድልድይ ስራ። 

💡ጽናት- ድልድይ ነው፣ ተስፋ መቁረጥ - ግርግዳ ነው። ሁለቱም በቃላት ይገነባሉ። እናም ወዳጄ መማር ባለብህ ጊዜ ተማር፣ መሥራት ባለብህ ጊዜ ሥራ፣ መዝፈን ባለብህ ጊዜ ዝፈን፣ መዘመር ባለብህ ጊዜ ዘምር፣ መጻፍ ባለብህ ጊዜ ጻፍ። ያሰብከውን ነገር ለማድረግ ምቹ ጊዜ አትጠብቅ፣ ምቹው ጊዜ ሃሳቡ ወደ ጭንቅላትህ የመጣበት ጊዜ ነው።

💎ልብህ ያሰበውን ጥሩ ነገር ከመፈጸም አትቦዝን። ሃሳቡ በውስጥህ አርጅቶ እስኪሞት አትጠብቅ። ሰው በልቡ አላማውን ከጸነሰ በኋላ ወደ ቀኝ ወደ ኋላ ሳይወላውል፤ ወደ ግቡ የሚያደርሰውን ቀጥተኛ መንገድ ሊያሰምር ይገባዋል። የማስፈጸም ፍላጎት፤ የሚበቅለው “ይቻላል” ከሚል ስሜት ነው። ከአላማ ጋር የተሳሰረ አስተሳሰብ እጅግ ግዙፍ ሃይል ነው። አሁን ካለበት ሁኔታ ለተሻለ ኑሮ እና አስተሳሰብ እራሱን ያዘጋጀ ሰው፤ አይምሮውን በብልሃት የሚያሰራ ለስኬት የተዘጋጀ ነው።

💡ትላንት ነገ ያልነው ዛሬ፣ ቅድም ቡሃላ ያልነው አሁን ደረሰ፣ግን ማድረግ የፈለግነውን አላደረግን ይሆናል፣ሆኖም በዚህ ተስፋ አንቆርጥም፤ደግመን ምኞታችንን ለማግኘት ተስፋችንን ለመጨበጥ እናቅዳለን።የምንመኘውን ያን ምኞት፣ መሆን ያለብንን እስክንሆን አንቆምም፣ ተስፋም አንቆርጥም፡፡

ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
📍የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ

የጀመርኩትን አላቋርጥም ያለችው አትሌት መነጋገሪያ ሆናለች።

ሀገሯ ቡታንን በመወከል የሮጠችው ኪንዛንግ ላሃሞ የተባለች አትሌት በሴቶች የማራቶን ውድድር የወርቅ ሜዳሊያ ካገኘችው አትሌት ሲፋን ሀሰን ከ1 ከሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ በመግባት ውድድሯን አጠናቃለች።

አትሌቷ ውድድሯን ስትጨርስ በቦታው የነበረው ታዳሚ እጅግ በጋለ ሞራል ተቀብሏታል።

የመጨረሻ ደረጃ ይዛ ያጠናቀቀችው አትሌቷ በፍጹም የጀመርኩትን ውድድር አላቋርጥም ብላ የውድድሩ የወርቅ አሸናፊ ከታወቀ ከ1 ሰዓት ከ30 ደቂቃ በኃላ ገብታለች።

80ኛ ደረጃ የወጣችው አትሌቷ ውድድሯን ለመጨረስ 3 ሰዓት ከ52 ደቂቃ / 4 ሰዓት ደገማ ወስዶበታል።

በዚህ ሁሉ ፥ የቴሌቪዥን ስርጭት  ያልተቋረጠ ሲሆን እያንዳንዷ እንቅስቃሴዋን ሲያሳይ ነበር ፤ በስፍራው የነበረው ተመልካችም የትም ሳይሄድ በክብርና በትልቅ ሞራል ተቀብሏታል።

የቡታኗ አትሌት የጀመረችውን ውድድር እስከመጨረሻ ድረስ ያለ ማቋረጥ ተፋልማ በመጨረሷ በበርካቶች " የተስፋ አለመቁረጥ ምሳሌ " ተደርጋ ተወስዳለች።

ሁላችንም በምንም አይነት ሁኔታ ቢሆን የጀመርነውን መጨረስ፣ ለቆምንለት ዓላማ እስከመጨረሻው መሄድ እንዳለብን ያስተማረ ነው።

" እኔ አልችልም " ብለህ ተስፋ ቆርጠህ ከመቆም መራመድን ምረጥ ፣ ከውስጥ የመነጨ ጠንካራ መንፈስ ሲኖረን ምንም ያህል ችግር ምንም ያህል ስቃይ ከላያችን ቢረበረቡ ምንም ሳያሳስበን ምንም ተስፋ ሳያስቆርጠን ወደፊት ግስጋሴያችንን እንቀጥላለን። ሩጫችንንም መሰናክሉን እያለፍን እንሮጣለን። ከግባችንም እንደርሳለን። በተንቀሳቀስን ቁጥር ግባችን ጋር መድረሳችን የማይቀር ነው።

ውብ ሰንበት❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanityBot
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
💡 ትላንት አልፏል ስለዚህ ሞቷል። ነገ ደሞ ሚስጥር ነው ካልደረስንበት አናውቀውም።እንዲሁም ነገ ስጦታ ነው ካልተሰጠን አንደርስበትም። ዛሬ ግን በእጃችን ላይ ነው። ስለዚህ ስለ ትላንት በማሰብ ስለነገም በመጨነቅ ዛሬን አናበላሽዉ። ትልቅ ጥበብ ዛሬን መኖር ነው ከዛሬም ደሞ አሁን።

እናም ወዳጄ ያለን ዛሬ ላይ እናተኩር

💡 ሕይወት ትላንት ወይም ነገ አይደለችም። ሕይወት አሁን ናት። አሁንነት ሲያልፍ ትላንት ይሆናል የወደፊት አሁንነት ደግሞ ነገ ይሆናል። ሕይወት ተኖረ የሚባለው በአሁንነት ውስጥ ጤናማ በሆነ መልኩ ስንኖርበት ብቻ ነው። በአሁንነት ውስጥ ያልተኖረ ሕይወት የመከነ ሕይወት ነው።ዳሩ ግን ብዙዎቻችን በአሁንነት ውስጥ እየኖርን አለመሆኑ ነው። አእምሯችን በባለፈውና በወደፊቱ ጊዜ የተሞላ ነው። ከዚህም  የተነሳ አዘውትሮ ያስባል ይጨነቃል።

ዛሬ የትናንት ተማሪ ነው፡፡ ዛሬ ነገን ውብ ቀን ለማድረግ የሚሰራ በእጃችን ያለ መክሊታችን ነው፡፡ የትናንትን ኋላቀርነት የሚደግም የዛሬ ቀን ለዛሬም አይሆንም፣ ለነገም አይተርፍም፡፡ ያለፈውን ደካማ ነገር መሻር ሲገባ የምንደግም ከሆነ ወደፊት መራመድ አንችልም፡፡ ትናንትን ወደነገ የሚያሻግረው ዛሬ ነው፡፡

⌛️ በትላንትናና በነገው አፍራሽ ስሜቶች ከመሞላትና ከመረበሽ በዛሬው ማንነት ውስጥ በትክክል መኖር ምርጫችን እናድርግ። ነገን የኖረ ማንም የለም። ነገን ስትደርስበት ህይወት እራሷ ትገለፅልሀለች። ሁሉም ነገር ጊዜ ተቀምሮለታል እኛ እድለኞች ነን ዛሬን ማየት ችለናልና።

         ያበራ ማንነት ለሁላችን
             ውብ አሁን❤️

@EthioHumanity
@EthioHumanity

@EthioHumanitybot
2024/11/14 15:27:23
Back to Top
HTML Embed Code: