Telegram Web Link
ቤዛ ኲሉ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ቤዛ ኲሉ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
አንፈርዓጹ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - አንፈርዓጹ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimonot
@mezigebehayimanot
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው 16k
ዝማሬ ዳዊት
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለንግዶች ማረፊአ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደርያ /2/
አዝ
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
አዝ
ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ላለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
አዝ
የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉስ መቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተልሄም ታዉራ
ዝማሬ ሲወጣ ከርስቱ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
አዝ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰዉ
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለዉ
ገረማት ጥበቡ ታናሹአን ሙሽራ
ተዋህዳልና ቃል ከ ስጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ይኸው ተወለደ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ይኸው ተወለደ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ስብሐት ለእግዚአብሔር

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
አማን በአማን
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - አማን በአማን

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
#ቁጣ ድል አይንሣህ

ወንድምህን ከሚገባው ይልቅ ለማክበር ሰውነትህን አትጋት ባገኘህውም ጊዜ እጁን እግሩን ሳመው በጎ አድርግለት አክብረህ ወደህ እየው ሥራው ባይደለ ሥራ አመስግነው ከአንተም በተለየ ጊዜ የእሱን ነገር ተናገር ከበጎ ሥራው ወገን መናገር በሚቻልህ ገንዘብ በጎ በጎ አድርግለት በጎ ነገር በመናገርህ ወደ በጎ ሥራ ትስበዋለህ ታነቃቀዋለህ አንተ ባመሰገንከው ምስጋና አንተ ባከበርከው ክብር የተነሣ ያፍር ዘንድ እንዳመሰገንከው ያልሆነ እንደሆነ ያፍራል እንዲህ የሆነ እንደሆነ ዘርአ ትሩፋትን ትዘራበታለህ፡፡

ነፍስህ ከለመደችው ባልንጀራህን ከማክበር የተነሣ በጎ ነገርን መውደድ በልቡናህ ይቀርጻል ፍጹም ትሕትናን ገንዘብ ታደርጋለህ ሳትጥር ብዙ ሥራ ትሠራልህ የምታከብረው በጎውን ሰው ብቻ አይደለም ነውር ያለበትም ቢሆን አክብረው እንጂ እንዲህ የሆነ እንደሆነ አንተ ካከበርከው ክብር የተነሣ አፍሮ ካንተ ድኅነትን ያገኛል።

ገንዘብህ የምትሆን ይህችን ጥበብ ለሁሉ አድርጋት ጥበብም የተባለች ሰውን ማክበር ለሰው ማዘን መራራት ናት አንዱንስ እንኳን አትቈጣ ተቈጥተህ አታሳዝነው ቍጣ ድል አይንሳህ ስለ ሃይማኖትም ቢሆን ሥራው ክፉ ስለሆነም ቢሆን ሰው እንዳታማ ተጠበቅ እንጂ አትፍረድበት በልዕልና ፊት አይቶ ሳያዳላ የሚፈርድ ዳኛ ክርስቶስ አለንና ወደ በጎ ሥራም ልትመልሰውም ብትወድ እዘንለት እያለቀስህ የለዘበ ነገር ንገረው በቍጣ አትናደድበት ጸብ ያለህ ይመስለዋል ፍቅር ውስጣዊ ቍጣን አይሻምና።

ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
#ሱባዔ_እንዴት_እንግባ?


1.ሱባዔ መያዝ ስለፈለግንበት ጉዳይ ማሰብ እና መለየት፡- ዓላማ የሌለን ዝርው የሆነ ያልተሰበሰበ አእምሮ ይዘን እንዳንገባ ፤ ከቅዱሳን በረከት ለመሳተፍ፤ወይም የግል ሕይወት ጉዳይ፡- ሥራ፣ትምህርት፤ትዳር…የሀገርና የቤተ ክርስቲያን የመሳሰሉትን ጉዳዮች ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡

2. ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ስለ ሱባዔ በደንብ ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል፡- መጀመሪያ ከንስሐ አባቶቻችን ጋር መመካከር፤ ቀጥሎም ስለ ሱባዔ ከሚያውቁ መንፈሳውያን አባቶች መጠየቅ ያስፈልጋል፤ ብዙዎችን ሱባዔ ማለት ቀልድ የሚመስላቸው ዝምም ብለው የሚጀምሩት ጉዳይ ሆኗል፤ በዚህም ምክንያት የብዙዎች ሕይወት የሰይጣን መጫወቻ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡

3.ስለምንቆይባቸው የቀናት ብዛት በሚገባ በማሰብ መወሰን፡ -ሱባዔ ማለት ቀጥታ ትርጉሙ ሰባት ማለት ይሁን እንጂ የግድ ግን ሰባት ቀን ወይም ሰባት ዓመት መኖር ማለት አይደለም፤ ይህ ለተሰጣቸውና ከዓለም ሙሉ ሕይወታቸውን ላገለሉ ሰዎች እንጂ ለዓለማውያን የተሰጠ አይደለም፤ ሃያ አራት ሰዓት ወይም 48 ሰዓት ወይም ደግሞ 72 ሰዓት (ሦስት ቀናት) ሊሆን ይችላል፤ ከዚህ ጀምሮ እንደየዓቅማችን 7፣14፣21….ቀናት እያልን ልናሳድገው እንችላለን፡፡ ይህም የሚጠቅመን ምናልባት ባለማወቅ ከጀመርነው በኋላ ፈተናው ሲፀናብን እንዳናቋርጥና ከእግዚአብሔር ጋር እንዳንጣላ ነው፤ይህንንም ጌታችን በምሳሌ እንዲህ ሲል አስተምሮናል "ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ኪሳራውን የማይቆጥር ማነው? ያለዚያ መሠረቱን ቢመሠርት ሊደመድመውም ቢያቅተው ያዩት ሁሉ፡-ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ" (ሉቃ 14፡28-30) በማለት አጋንንት፤ የመናፍቃን መሳለቂያ እንዳንሆን ያስጠነቅቀናል፡፡

4. የምንጸልያቸውን ጸሎቶች መለየት፡- በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ብዙ ዓይነት ጸሎት መኖሩ ይታወቃል፤ሁሉንም እንጸልያለን ብንል ዓይናችን ይፈዛል አንደበታችን ይላሻል፤ ስለዚህም በየሰዓቱና በየዕለቱ የምንጸልያቸውን ጸሎቶች በመለየት ሳናስታጉል በትጋት መጸለይ አለብን፤ በጸሎት ጊዜም ሰጊድ(ስግደት)፤አስተብርኮ(መንበርከክ)፤ አንቃዕድዎ(ማንጋጠጥ) ከእንባ ጋር መረሳት የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው፤ እነዚህንም ያስተማረን ራሱ ጌታችን መሆኑን ልብ ይሏል! ማቴ 26፡39፤ሉቃ 22፡42፤ዮሐ 11፡41፡፡

5.የምንመገባቸውን የምግብ ዓይነቶች ለይቶ መወሰንና እናም የመመገቢያ ሰዓትን ማወቅ፡- ምግብ መጠጥ ኃጢአት ምንጮች ናቸው፤ በተለይም አብዝቶ መመገብ ልዩ ልዩ ዓለማዊ ነገሮችን እንድናስብ ከማድረጉ በተጨማሪ እንዳንጸልይና እንዳንሰግድ በማድረግ ይጫነናል፤ ስለዚህ የምንመገበው ለቁመተ ሥጋ ያህል ብቻ እና በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ብቻ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆኑን ሠለስቱ ደቂቅ እና ነቢዩ ዳንኤል ናቸው፤ዳን 21 ቀናት) ሳዝን ነበርኩ ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም" (ዳን 10፡2-4)፡፡

6. ለሱባዔ በወሰንባቸው ጊዜያት ከማንኛውም ዓለማዊ ጉዳይ ጋር ያለንን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ለማቋረጥ መወሰን፡- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥርዓተ ጸሎትን ሲያስተምረን "አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በሥውር ላለው አባትህ ጸልይ በሥውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል“ (ማቴ 6፡6) ብሎ እንደነገረን በሱባዔ ጊዜ መገናኘት ያለብን ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ነው፤ ማንኛውም ጉዳያችን እና ማንነታችንም ሳይቀር በእርሱ እጅ መውደቅ አለበት፡፡

የልብ ሱባዔ እኖዲሆን የልብ ጸሎት እንድንጸልይ እግዚአብሔር ይርዳን!!!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ሐዋርያት ያስተማሩት እውነተኛ ሀይማኖት 
                                                  
Size:- 60MB
Length:-2:58:02
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from 💎Super📣ፕሮሞሽን
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእናቷ ማህፀን ሳለች ከሞት ያስነሳችው ሰው ማነው?
Forwarded from Josy Quality Button
ግሩም ድንቅ የሆነ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል
2024/09/21 19:40:29
Back to Top
HTML Embed Code: