Telegram Web Link
ከሰው ለተለዩት
✍🏽 ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ እንደጻፉት

የአንቀጸ ብፁዓን ተራራ፥ ወንጌል የተጀመረችበት፣ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ መምህርነቱን ለቤተ ክርስቲያን የገለጠበት ስፍራ ነው። ዘጠኙን ብፁዓን በስብከቱ የገለጣቸው በዚህ ተራራ ላይ ነው። ትምህርቱን ለመስማት በጉባኤው ለመገኘት ወደ ተራራው የወጡ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ከሁሉ ይልቅ ቀርበው ይሰሙት ነበር። “ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ” ማቴ 5፥1 እንዲል። እሱ ከተራራ ላይ ወጥቶ ከተቀመጠ ማን ከተራራው በታች ይቀራል ብለው እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚነሱ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ወደ ተራራ ወጥተው በተቀመጠበት ስፍራ ሲፈልጉት ይኖራሉ።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ፍጹማን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የበዙባት አገር ናት። ብዙዎቹ ዓለምን ንቀው ስብከቱን እየሰሙ ለመኖር ወደ ተራራው ይወጣሉ። እሱ ከፍ ካለው ቦታ ላይ ይቀመጣል። እነሱ ቃሉን ለመስማት እንዲመቻቸው ዝቅ ብለው ተቀምጠው “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው” ሲል ይሰሙታል። ጠቢባን ጥበባቸውን፣ ባለጠጎች ሀብታቸውን፣ የሕዝብ አለቆች ሹመታቸውን ትተው ይከተሉታል። በዚያ ዘመን ከክርስቶስ ጋር ወደ ተራራው ወጥቶ፣ ስብከቱን ሰምቶ ከአይሁድና ከአጋንንት በቀር ወደ ኋላ የተመለሰ የለም ማቴ 4፥10፣ ዮሐ 6፥66።

ከተራራ ወደ ተራራ ያመላልሳቸዋል፤ በትንሹ ተራራ ያስጀመራቸውን ትምህርት ወደ ረዥም ተራራ አውጥቶ ምሥጢሩን ያብራራላቸዋል። በመጀመሪያው ተራራ ላይ ደቀ መዝሙርነትን ያስጀምራቸዋል፤ በመጨረሻ የሚገናኙበት ተራራ ላይ አካሉ ባደረጋት ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾማቸዋል። ትንሹ ተራራ ያልኋችሁ የአንቀጸ ብፁዓን ተራራ ነው። ረዥሙም ተራራ ደብረ ታቦር ነው። የመጨረሻ ክከርስቶስ ጋር የተለያዩበት ተራራም ደብረ ዘይት ነው። በትንሹ ተራራ በአንቀጸ ብፁዓን በቃል የነገራቸውን ወንጌል ምሥጢሩን በዐይናቸው እንዲያዩት ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነው። በቤተ ክርስቲያን ላይ ካህናት አድርጎ በአንብሮተ እድ የሾማቸውም በደብረ ዘይት ነው ሉቃ 24፥50።
የቤተ ክርስቲያን ደቀ መዝሙርነቷ ዛሬም ልክ እንደ መጀመሪያው ነው። አንዳንዶቹ በልባቸው፤ አንዳንዶቹም በእግራቸውም በልባቸውም ከተራራ ወደ ተራራ እየተዘዋወሩ በዕዝነ ነፍሳቸው ትምህርቱን ይሰማሉ። በዚህ ሰሙን መታሰቢያቸውን ያከበርንላቸው አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞ ወጥተው መኖር የፈለጉት በተራራ ላይ የሰበካትን ወንጌል በልባቸው እያመላለሱ ለመኖር ነው። ከተራራው ጫፍ ወጥተው በተቀመጡ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደርሱ ቀርበው ስብከቱን ሲሰሙ ያገኟቸዋል። ቀርበው ሲሰሙ ይውላሉ። በሌላ ጊዜ ደግሞ ደብረ ዳሞ ደብረ ታቦርን ይሆንላቸዋል፤ ጌታ ልብሱ ነጭ ሆኖ፣ ሙሴና ኤልያስም ከሱ ጋር ሲነጋገሩ፣ አብ በደመና ሁኖ “የምወደው ልጄ” ብሎ ሲመሰክርለት ይሰማሉ። በተመስጦ ይዋጣሉ። ለሰው ከተደረገው የእግዚአብሔር ፍቅር የተነሣ ደንግጠው ዝም ይላሉ።

በነገራችን ላይ በቅዱስ ወንጌል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነበረባቸውን ቦታዎችና ታሪኩን ሊያስታውሱን የሚችሉ ኩነቶችን ሊገልጡልን የሚችሉ ምሳሌዎችን ማድረግ ለአንዳንዶቹ እንደሚመስላቸው ግብዝነት አይደለም። ራሱ ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ አንዳንድ ነገሮችን ያደረገው ነቢያት ያደርጉት በነበረበት መንገድና ቦታ ነው። ሙሴ ወደ ተራራ ወጥቶ እንደጸለየ እሱም ይህንኑ አደረገ ዘዳ 9፥9፣ ማቴ 4፥1። ኤልያስ በኮሬብ ፈፋ ውስጥ ያድር እንደነበረ እሱም በኤሌዎን ዋሻ ውስጥ ያድር ነበረ።

ከሁሉም ይልቅ የሚደንቀኝ ጌታ የሞት ፍርሃት በያዘው ሰው አምሳል የጸለየባት የጌቴሴማኒ ምሥጢር ነው። ከረዥም ዓመት በፊት በዚህ ስፍራ ይስሐቅ “አባቴ ሆይ በጉ ወዴት አለ?” ዘፍ 22፥7 ብሎ አብርሃምን የጠየቀው በዚህ ስፍራ ነበር። ተመልከቱ ይስሐቅ የአባቱን ፈቃድ መፈጸሙ አይቀርም፤ ነገር ግን ሞት እንዲቀርለት የፈለገ ይመስላል። ኢየሱስ ክርስቶስም መሥዋዕትነቱ የሚያስፈልገን ስለሆነ እንዳይቀር የሱም የባሕርይ አባቱ የአብም ፈቃድ ነው። ነገር ግን “አባት ሆይ ይህች ጽዋዕ ከኔ ትለፍ” ብሎ ይጣራል። እንዴት ያለ ነገር ነው?

ለማንኛውም የቦታና የሁኔታዎች መመሳሰል የሰውን ልብ በጊዜውና በቦታው እንዳለ ሆኖ እንዲረዳው ስለሚያደርግ ቅዱሳን ወደ ተራራ ወጥተው ገዳም አቅንተው በዐት ሠርተው የሚኖሩበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው። ከዓለም ተለይተው ወደ ተራራው በወጡ ጊዜ በቀራንዮ ተራራ ላይ ሊቀ ካህናት ሆኖ ያገኙታል። በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሠያሜ ካህናት ሆኖ በካህናት በጳጳሳት ላይ እጁን እየጫነ ሲሾማቸው ይመለከቱታል። ከዚህ መውረድ አይሆንላቸውም።

ቅዱስ ጴጥሮስ “በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው” ብሎ የጠየቀው ጥያቄ ለነሱ ተፈጽሞላቸው ከተራራው ሳይወርዱ እንደ አባ አረጋዊ ያሉት በዚያው ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሊኖሩ ከሞት ተሸሽገው የሚቀመጡበት መኖሪያቸው ያደርግላቸዋል። ከሰው ለተለዩት ከሰው የተለየ ነገር ያደርግላቸዋል። በዓለም ሳሉ ሞት እንዳያያቸው ይሸሽጋቸዋል። ሄኖክ ከሰዎች ተለይቶ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ እግዚአብሔርም ስለወሰደ አልተገኘም ዘፍ 5፥24። ኢልያስን በእሳት ሠረገላ ቢጭነው፤ ጠላቶቹን እሳት ከሰማይ አውርዶ እንዲያስበላቸው ለማድረግ ሥልጣን ቢሰጠው ከሰው የተለየ ነገር አደረገ ብሎ እግዚአብሔርን ሊወቅሰው የሚፈልግ ማነው? ከሰው ተለይቶ ቢለምኑት እግዚአብሔር ከሰው የተለየ ጸጋን ይሰጣል።
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
#አበው_ስለ_እመቤታችን_እንዲህ_አሉ

"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ"
#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው "
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ

"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት"
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ

"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ"
#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"
#ቅዱስ_ኤፍሬም

(በ Deacon Henok Haile የተሰባሰበ)


@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
  [       ትእግስትን በተመለከተ  !    ]

ሥቃዩን ሁሉ ታግሠው ኖሩ  !

" የቀደሙ አባቶቻችን ጻድቃን ቅዱሳን በእምነታቸው የእሳቱን እቶን አቀዘቀዙት በዚያም በባዕድ ሀገር ባርነቱን መከራውን ሥቃዩን ሁሉ ታግሠው ኖሩ
እኛ ጥቂቱን መከራ እንኳ ያለመታገሣችን ምክንያቱ እምነታችን ጎዶሎ ስለሆነ ነው በዚህም ምክንያት ትዕግሥት ከእኛ ዘንድ የራቀ ሆነ አንተ የሰውን ገንዘብ ብታጠፋ እምነትንም ብታጎድል ወደ ወኅኒ ቤት ትጣላለህ በዚያም መከራን ትቀበላለህ እንዲሁ በእግዚአብሔር ባትታመንና ወደ ድፍረት ኃጢአት ብትገባ በነፍስህ ጽኑ መከራን ትቀበላለህ፡፡

ስለዚህ በእግዚአብሔር አምላክህ ዘንድ ዋጋ እንዳታጣ ትዕግሥትን ገንዘብህ አድርገህ ተመላለስ አስቀድመህ የፈጸምከውም የጽድቅ ሥራ ዋጋ እንዳያጣ ወደ ኋላ አትመልከት በሕይወትህም ለእግዚአብሔር የምትቀና በሰው ዘንድ የታመንህ ሁን"

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ  
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
በበረሓው ጉያ ውስጥ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ ፦

አንድ ጊዜ  አባ መቃርዮስ  ከወንድሞች ጋር ወደ ግብጽ  ሲሔድ አንድ ልጅ ለእናቱ  << አንድ ሀብታም  አለ እርሱ ይወደኛል  እኔ እጠላዋለሁ ፤ አንድ ምስኪን አለ እርሱ ይጠላኛል እኔ እወደዋለሁ >> ብሎ ሲነግራት ሰማ ። ይህን ጊዜ  አባ መቃሪዎስ እጅግ ተደነቀ ። አብረውት የነበሩ ወንድሞችም  ምን እንዳስደነቀው ጠየቁት ። እርሱም ።<<በእውነት ባለጸጋ የተባለው ጌታችን ነው ። ነገር ግን እኛ አንወደዉም ።ምስኪን የተባለው ዲያብሎስ  ግን እኛን ይጠላናል እኛ ግን ክፋቱን እንወድለታለን ብሎ ነገራቸው ።
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፳ወ፫ ለጥቅምት ጊዮርጊስ

የጥቅምት ጊዮርጊስ #ሥርዓተ_ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷ


የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ፤ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዓጽሙ።

ዚቅ
ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ወከመ ወሬዛ ኀየል መላትሒሁ፤ጒርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ሰማየ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ፤ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ፤ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት፤ወአልዓላ እምኲሉ ዕለት፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ወኲሉ ይሴፎ ኪያከ።

አመላለስ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/፪/
ወኲሉ ይሴፎ ኪያከ/፬/

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
በ፪ ልዑለ ረሰዮ ለመሠረትኪ፤ዓረፋትኪ ዘመረግድ፤ደቂቅኪ ምሁራን በኀበ እግዚአብሔር፤ቆዓ ትጼኑ ቆዓ ጽጌ ወይን፤ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት፤ጽዮን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ጽጌ ደንጐላት ዘውስተ ቆላት።

መልክአ ጊዮርጊስ
ሰላም ለዘባንከ ዘተሞጥሐ ምንዳቤ፤ጊዜያተ ምዕተ መቅሰፍተ ጥብጣቤ፤ጊዮርጊስ ምዑዝ እምጼና ሐንክሶ ወከርቤ፤ኅሊናየ ዘተመነየ ወልሳንየ ዘይቤ፤እንበለ አጽርኦ ፍጡነ ኩነኒ ወሀቤ።

ዚቅ
ጊዮርጊስ ምሉዓ ፍቅር ከመ ጽጌ ረዳ፤ዘጥዑም ጼና መዓዛሁ፤አረጋዊ ዓፀደ ወይን ዘጽድቅ ዘይፈራ አስካለ ሕይወት።

ወረብ
ጊዮርጊስ ምሉዓ ፍቅር ከመ ጽጌ ረዳ ዘይወጽእ እምአፉሁ ዕጣነ ቅድስና/፪/
ለገቢረ ሠናይ ዘይውኅዝ ከመ ማይ ምስለ ገብረ ክርስቶስ/፪/

መልክአ ጊዮርጊስ
ሰላም ዕብል አፃብአ እዴከ የውጣ፤ወለአጽፋሪሆን ዓዲ ዲበ ከተማሆን ዘተለብጣ፤ጊዮርጊስ ኩኑን ለዓራተ ሐጺን በዉስጣ፤ቅዱሳት አብዒከ ዲበ ርእስየ ይሱጣ፤ቅብዐ ቅድስና ዕፍረተ ዘዕፁብ ሤጣ።

ዚቅ
ብፁዕ ጊዮርጊስ በጽጌ ሃይማኖት ሥርግው፤ከመ ርኄ አፈዉ ዜናሁ ፍትዉ።

ዓዲ ዚቅ
ሃሌ ሉያ አጻብኢሁ ፍሁቃት፤ከናፍሪሁ ጽጌ ዘወልድ እኁየ፤እለ ያዉኅዛ ከርቤ።

መልክአ ጊዮርጊስ
ሰላም ለመቃብርከ ምክሐ እድያሚሃ ወዓጸዳ፤ለምድረ ሙላድከ ልዳ፤ጊዮርጊስ ዘልፈ ሀብተ በረከት ዘእፈቅዳ፤ከመ ትጸጊ ሕንባበ ረዳ ለኢያሪኮ በዓዉዳ፤በዲበ ድማኅየ ትጽጊ እምሰማይ ወሪዳ።

ዚቅ
ዘይጸጊ ወይፈሪ እስከ አድያሚሃ ለዮርዳኖስ፤እስመ ስብሐተ ሊባኖስ ተዉህበ ሎቱ ለክብር ወለቀናንሞስ።

ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።

ወረብ
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም[፪]
ማርያም ተዓይል ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ከመ ዖፍ[፪]

ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጽፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ።

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ[፪]
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ[፪]

ዚቅ
ሰዓሊ ለነ ማርያም፤አክሊለ ንጹሐን ብርሃነ ቅዱሳን።

ምልጣን
ዝንቱሰ ብእሲ ኮከበ ክብር ዘዓቢየ ኃይለ ይገብር፤ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል ስምዓ ጽድቆሙ ለቅዱሳን፤አማን ብርሃን ሰምዓ ብርሃን።

እስመ ለዓለም
አግዓዝያን አንትሙ፤ከመ ፀሐይ ይበርህ ገጾሙ፤አክሊለ ስምዕ ዲበ ርእሶሙ ከመ ኮል መዓዛ አፉሆሙ፤ሠረገላሆሙ ጽኑዕ፤ምስለ መላእክት የኃድራ ነፍሳቲሆሙ።

እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
. የ አ ሚ ና ዳ ብ ፡ ሠ ረ ገ ላ ፡ አ ን ቺ ፡ ነ ሽ
༺◉❖═───◉●◉🌹🌹🌹◉●◉────═❖◉༻
#አባ_ሕርያቆስ ❝ የአሚናዳብ ሠረገላ አንቺ ነሽ በማለት አመስግኗታል መተርጉማኑ እመቤታችን በአሚናደብ ሠረገላ የተመሰለችበትን ምሥጢራዊ ምክንያት ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ የአሚናደብ ሠረገላ ልዝብና ፈጣን ምቹ ነበረች እመቤታችንም ለነፍስ ለሥጋ የምትመች በንጽሕና በቅድስና የለዘበች ለምሕረት የፈጠነች አፍጣኒተ ረድኤት ሰአሊተ ምሕረት ምዕራገ ጸሎት ናትና።

#አባ_ጊዮርጊስ_በሰዓታቱ ደግሞ ❝ በጭንቅ ጊዜ ረድኤትን የምታፋጥኚ ማርያም ሆይ ! እንደ ዐይን ጥቅሻ በላባ ቤት ያዕቆብን የረዳሽው አንቺ ነሽ በሁሉ ሐሳቧ በሁሉ ልቡናዋ አንቺን የማትወድ ነፍስ ከወገኗ ተለይታ ትጥፋ ። ❞ በማለት የአምላኳን እናት ሰማያዊቷን ንግሥት የዓለምን ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያምን የማትወድ ነፍስ እድል ፈንታዋ ጽዋ ተርታዋ ሲኦል መሆኑን ተናግሯል ።

#ቅዱስ_ያሬድም እመቤታችን አደፍ ጉድፍ የሌለባቸው ቅዱሳት ሕዋሳቶቿ በንጽሕና በቅድስና ያጌጡ ልብሶቿ እንደ ስሂን ሽቶ የጣፈጡ የቃሏ ንግግር ከወይን ይልቅ እንደሚጥም ሲዘምር እንዲህ አለ ፦

❝ እንደ ሮማን ቅርፊት ቀይ ናቸው የልብሶቿ መዐዛ ስሂን እንደሚባል ሽቱ መዐዛ ነው የአማኑኤል እናት ድንግል ማርያም በእሾህ መሐል ያበበች በእውነት #የሃይማኖት_አበባ_ናት የቃሏ ጥፍጥና ከወይን ይልቅ ያማረ የጣፈጠ ነው የቅዱስ ቃል መዝገቡ የሆንሽ ፈጣን ደመና ሆይ ! ከከናፍርሽ የማር ወለላ ይፈሳል ። ❞ በማለት የእመቤታችን ፍቅሯ ፣ ቃል ኪዳንዋን ፣ ንግግሯና ቃሏ እንደ ማር የሚጣፍጥ ለነፍስና ለሥጋ የሚመስጥ መሆኑን ዘምሯል ።

#ቅዱስ_ኤፍሬምም ❝ ሳይተክሏት ተተክላ ውኃ ሳያጠጧት ለምልማ አብባ አፍርታ የተገኘች የአሮን በትር ነበረች ያለዘርአ ብእሲ ሰው ሆኖ ያዳነን አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ! አንቺም እንደ እሷ ነሽ ❞ በማለት በንጽጽር መስሎ አመሰግኗታል

#አባ_ሕርያቆስ በቅዳሴው የእመቤታችን ውበት አፍአዊ ብቻ ሳይሆን ውሳጣዊ ፣ ሥጋዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ፣ ጊዜዊ ሳይሆን ዘለዓለማዊ በመሆኑ ውበቷ አምላክን ከዙፋኑ እንደሳበው ሲነግረን እንዲህ አለ ፦

❝ እግዚአብሔር አብ ከሰማይ ሆኖ በእውነት በአራቱ ማዕዘን ተመለከተ መረመረ ፤ በንጽሕና በቅድስና የተዘጋጀ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም ፤ ስላላገኘ መዐዛ ሃይማኖትሽን መዐዛ ምግባርሽን ንጽሕናሽን ቅድስናሽን ወደደ #ሥጋሽን_ለልጁ_ተዋሕዶና_ለልጁ_እናትነት_መረጠ ቢመርጥሽ የሚወደውን የሚወልደውን ፤ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን ውረድ ተወለድ ሙት ተሰቀል ብሎ ወደ አንቺ ሰደደ ❞ አለ ።

#አንቀጸ_ሰላማዊትሆይ_ሰላም_ላንቺ_ይሁን_ያንቺ_ሰላም_ከሁላችን_ጋር_ይሁን
#የጌታችን_እናት_እናታችን_ማርያም_ሆይ_ለምኚልን_ከደጅ_እንዳንቆም_አማልጂን

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
፯ኛ ዙር ዓመት ፭ኛ ሳምንት
ማሕሌተ ጽጌ
ጥቅምት ፳፭
በዓለ አቡነ አቢብ ወመርቆሬዎስ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለማኅበራዊ ሚዲያ ማድመቂያ በማኅሌቱ የሚታየው የሥርዓተ ቤተክርስቲያ ጥሰት ሊቆም ይገባል ሲሉ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ ለኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ተናገሩ። አቡነ ኤርሚያስ እንዳሉት ከበሮ ይዞ የሚሽከረከሩ፣ ጭፈራ የሚመስል በፍፁም ከኃይማኖታዊ የማይመስሉ ድርጊቶች በቤተክርስቲያን ላይ እየታዩ ነው፤ ይህን ድርጊት ለማስቆም ሊቃውት መናገር ፈርቷል አሁን ደፍረን መናገር አለብን ይህ ድርጊት መቆም አለበት ብሏል። አሁን አላዋቂዎች እና ደጋፊዎቻቸው እየበዙ አዋቂዎች እያነሱ መጥቷል፣ እነዚህ ከእምነቱ ውጪ የሆኑ ድርጊቶች ሲከናወኑ ማህሌቱ ደመቀ ይባል መሆን የለበትም ሊቃውት ይህን ማስቆም አለባቸው ብለዋል።

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ስርዓተ ማህሌት ዘጽጌ ዘሐምሳይ ሳምንት በዓለ አቡነ አቢብ ወቅዱስ መርቆሬዎስ

ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዐተ ማኅሌት መጀመሪያ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።


ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም ፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዚቅ
ዛቲ ይእቲ እኅተ ትጉሃን መላእክት፤ ወለተ ኄራን ነቢያት፤ እሞሙ ለሐዋርያት፤ ሞገሶሙ ለጻድቃን ወሰማዕት።

ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ።

ወረብ፦
ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ ንዒ ርግብየ ምስለ ሚካኤል/፪/
ወንዒ ሠናይትየ  ምስለ ገብርኤል ገብርኤል ፍሡሕ ሊቀ መላእክት/፪/

ዚቅ፦
ንዒ ርግብየ ወንዒ ሠናይትየ ቃልኪ አዳም ይጥዕመኒ እምአስካለ ወይን አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ ወተናግሮ በዓምደ ደመና እሞሙ ይእቲ ለሰማዕት ወእኅቶሙ ለመላእክት አርአዮ ለሙሴ ግብራ ለደብተራ።


ማኅሌተ ጽጌ፦
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቌ ባሕርይ ዘየኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኲሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ዘይኀቱ እምዕንቄ ባሕርይ/፪/
አክሊለ አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ፦
አክሊሎሙ ለሰማዕት ተስፋ መነኮሳት ሠያሚሆሙ ለካህናት፤ነያ ጽዮን መድኃኒት

ማኅሌተ ጽጌ
አንብርኒ ማርያም ውስተ ልብኪ ከመ ኅልቀት፤ በከመ ማዕተብ ፁርኒ (ዘትእምርት) በመዝራዕትኪ ልዕልት፤በእንተ ርስሐትየሰ ኢትመንንኒ ንግሥት፤እስመ ወሀብኩ ንብረትየ ለፍቅርኪ ሞት፤ ዘአሠርገዎሙ ለሰማዕት በጽጌሁ ሕይወት

ወረብ፦
አንብርኒ ማርያም ውስተ ልብኪ ከመ ኅልቀት በከመ ማዕተብ ዘትእምርት በመዝራዕትኪ ልዕል/፪/
በእንተ ርስሐትየሰ ኢትመንንኒ ኢትመንንኒ ንግሥት በእንተ ርስሐትየሰ/፪/

በከመ ከዋክብት ያሠረግውዎ በሰማይ በስኖሙ ከማሁ ሰማዕትኒ ያሠረግውዋ ለቤተ ክርስቲያን በገድሎሙ

ዓዲ (ሌላ) ዚቅ
አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት  አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት ሰንበተ ክርስቲያን ለዕረፍት ሠርዓ ሎሙ አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት ከመ ወርቅ በእሳት ፈተኖሙ አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት ወከመ ጽንሓሓ መሥዋዕት ተወክፎሙ አሠርገዎሙ ለሰማዕት በሰማያት

ማኅሌተ ፅጌ፦
ዘንተ(ዘኒ) ስብሐተ ወዘንተ(ወዘኒ) ማኅሌተ፤ተአምርኪ ጸገየ ወፈረየ ሊተ፤ከመ እሰብሕ ዳግመ እንዘ እጸውር ፀበርተ፤ምስለ እለ ሐፀቡ ኣልባሲሆሙ በደመ በግዑ ድርገተ፤ውስተ ባሕረ ማኅው ድንግል ክፍልኒ ቁመተ።

ወረብ፦
ምስለ እለ ሐጸቡ አልባሲሆሙ አልባሲሆሙ በደመ በግዑ/፪/
ክፍልኒ ቁመተ ድንግል ድንግል ውስተ ባህረ ማኅው/፪/

ዚቅ፦
አመ ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን፤ክፍልኒ ድንግል እቁም በየማን ምስለ አባግዕ ቡሩካን

ዓዲ ዚቅ፦
ገጹ ብሩህ ከመ ፀሐይ ወእምኵሉ ስነ ሠርጐ ሰማይ ለጊዮርጊስ ኅሩይ ዘተወልደ እመንፈስ ቅዱስ ወማይ አልባሲሁ በደመ በግዕ ዘሐፀበ ወእምሠረቅት መርዔቶ ዓቀበ

ሰቆቃወ ድንግል
እስከ ማእዜኑ እግዝእትየ ማርያም ውስተ ምድረ ነኪር ትሔልዊ፤ሀገረኪ ናሁ ገሊላ እትዊ፤ለወልድኪ ሕፃን ዘስሙ ናዝራዊ፤ለክብረ ቅዱሳን በከመ ይቤ ኦዝያን ዜናዊ፤እምግብጽ ይጼውዖ አቡሁ ራማዊ።

ወረብ
በከመ ይቤ ኦዝያን ኦዝያን ክብረ ቅዱሳን/፪/
እምግብጽ ይጼውዖ ለወልድኪ አቡሁ ራማዊ አቡ/፪
ዚቅ
ትንቢተ ኢሳይያስ ዘተብህለ እምግብፅ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን ጸዋዕክዎ


መዝሙር በ5-
ሃሌ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ጸገየ ወይን ወፈረየ ሮማን፤ወፈረዩ ኩሉ ዕጽወ ገዳም ቀንሞስ ዕቁረ ማየ ልብን፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ጸገዩ ደንጎላት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት ተሠርገወት ምድር በስነ ጽጌያት፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ እግዚአ ለሰንበት ወአቡሃ ምሕረት፤ማ፦ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ፤ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ


አመላለስ፦
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ዚአነ/፪/
ሠርዓ ለነ ሰንበተ ለዕረፍተ ወለመድኃኒት/፪/

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/27 07:25:10
Back to Top
HTML Embed Code: