Telegram Web Link
#መስከረም_8_ዘካርያስ_ይባላል

"ወናሁ አኀሥሥ ደመ እምእዴክሙ እምደመ አቤል ጻድቅ እስከ ደመ ዘካርያስ ወልደ በራክዩ ዘተቀትለ በማዕከለ ቤተ መቅደስ ወምሥዋዕ" ፦

(ከአቤል ጀምሮ በመቅደሱና በመሠዊያው መካከል አስከተገደለው እስከ በራክዩ ልጅ ዘካርያስ ድረስ የፈሰሰውን ደም ከእጃችሁ እፈልጋለሁ) ፤ ማቴ 23፡35፡፡

መስከረም 8 (ስምንት) የብቻው ተለይቶ "ዘካርያስ" ይባላል፤ የንጹሐን ካህናት ደም የፈሰሰበት መታሰቢያ ዕለት ነው፤ ያውም በሚያገለግሉበት በመሠዊያውና በመቅደሱ ደጃፍ በግፈኞች የተገደሉበት ።

ሁለት ዘካርያስ ተብለው የሚጠሩ ክህነትን ከትንቢት አስተባብረው የያዙ በተለያየ ጊዜ የተነሡ ሞታቸውና የደማቸው ጩኸት ተመሳሳይ የሆነ ፤ክርስቶስም ደማቸውን ከአይሁድ እጅ እንደሚፈልገው የተናገረላቸው ንጹሐን አበው ናቸው።
አንዱ በዜና መዋዕል ካልዕ ታሪኩ የተጻፈለት ሲሆን (2ኛ ዜና መዋ. 24፡21)፤
ሁለተኛው የዮሐንስ መጥምቅ አባት በሄሮድስ ክፋት በልጁ በቅዱስ ዮሐንስ ምክንያት በመሠዊያው እንደታረደ አበው የሚነግሩን ታሪክ ነው።

ዘካርያስ ወልደ ዮዳሄን ሲገድሉት ላያዝኑለት ተነጋግረው ፤ ራርተው ላይተውት ተማምለው፤ ነፍሱ ሳትወጣ ላይለቁት ለሞቱ ቃል ኪዳን ገብተው ፤ ከታች ድንጋይ ከላይ ድንጋይ አድርገው በዐለት ላይ አጋድመው ቀጥቅጠው ነበር የገደሉት ፤ ይህን ያደረጉ ሰዎችም እሱን ሳይገድሉ እህል እንዳይቀምሱ ጭምርም ተማምለው ነበር፣ መሐላቸውን በቤተ መቅደሱ አደባባይ ያለ ማንም ከልካይ ፈጸሙበት፤ እሱም ሲሞት፣ ነፍሱ ከሥጋው ከመለየቷ በፊት አንዲት ቃል አወጣ
"……እግዚአብሔር ይህንን ግፍ ይህንን ደም ይየው ይፈልገውም" (ዜና መዋ 24÷21)
በማለት የግፍ ሞት ጽዋውን ደም ገርገጭ አድርጎ ጠጣው!!!

በዚህም ምክንያት ደሙ ለብዙ ዓመታት ሲጮኽ እንደኖረ አበው ይነግሩናል።

ዛሬም እንደ ዘካርያስ በተወለዱበት ፤ ባደጉበትና ሀብት ንብረት ባፈሩበት ቀያቸው ተቀጥቅጠውና ታርደው የተገደሉ አባቶቻችን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ቁጥር ብዙ ነው!!!

የመግደል ኪዳን የሰይጣን መሐላ ያለ ማንም ከልካይ የተፈጸመባቸው ብዙ ናቸው!!!

ደማቸውም እስከ ሰማይ እየጮኸ ነው።
አገራችን የደም ምድር መሆኗ አዲስ አልሆን አለ …… ሞት ሲለመድ፤ መግደል ጀግንነት ሲሆን፤ ጩኸት አልደመጥ ሲል ....የግፍ ጽዋ መሙላት ምልክት ነው፡፡

"ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደስና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው የጻድቅ ደም ሁሉ ይደርስባችሁ ዘንድ።"
(ማቴ 23 : 35) ብሎ ጌታችን የተናገረውም ዘካርያስ እግዚአብሔር እንዲያይለት በጠየቀው መሠረት ራሱ እግዚአብሔር ወልድ ፦
"……እፈልገዋለሁ" በማለት ማረጋገጡ ነው።

ዛሬም ቢሆን የንጹሐንን ደም የሚያፈሱ ግፈኞች የግፍ ጽዋቸውን ከእግዚአብሔር ይቀበላሉ ።

መስከረም ስምንትን (8)
• እንደ አቤል በየዋህነት የተገደሉትን አቤሎችንና
• እንደ ዘካርያስ በመቅደስና በአደባባይ የታረዱ ዘካርያሶች ካህናትን እያሰብን እናከብረዋለን።

እግዚአብሔር ሆይ ደማችንን ከገዳዮቻችን እጅ ፈልግ!!!

ኦ እግዚኦ ረስያ ለደምነ ማኅተመ ደመ ኵሎሙ ሰማዕታተ ኢትዮጵያ!

❖ጌታ ሆይ አስከ ዛሬ የፈሰሰው ደማችንን የደማችን መፍሰስ ማብቂያ አድርግልን!!!!

ሀገራችንን ከረኀብና ከበሽታ ከእልቂት ይሠውርልን!

አሜን!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ - #መንፈሳዊው_መንገድ መጽሐፍ #አያሌው_ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
“አንድ ምንም እውቀቱና ልምዱ የሌለው ሰው ዝም ብሎ መሬት ስለ ቆፈረ ብቻ ወርቅ አያገኝም፡፡ ከዚያ ይልቅ ምንም ረብሕና ጥቅም የሌለውን ድካም ያተርፋል እንጂ፡፡ ባስ ካለም የቆፈረው ጉድጓድ ተደርምሶበት ሕይወቱን ሊያጣ ይችላል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ እንዴት እንደሚነበብና እንዴት መረዳት እንዳለበት ያለወቀ ሰውም ይህን ሰው ይመስላል፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
+ ዘኬዎስ አጭር ባይሆን +

ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት በኢያሪኮ እያለፈ ያለውን ክርስቶስን ለማየት ተቸገረ:: ሕዝቡ ብዙ ነውና የቆሙት ሁሉ ጌታን ከማየት ከለሉት:: የሾላ ዛፍ ላይ ወጥቶ ጌታን ለማየት ሲሞክር ጌታ አሻቅቦ አየው::

እሱ ዛፍ ላይ ጌታን ሊያይ እንጂ ሊታይ አልወጣም:: ጌታ ሊታዩ ከሚሞክሩ ይልቅ ሊያዩት የሚሹትን ይወዳልና ዘኬዎስን ጠራው::

ከምድር ቆመን ዓይናችንን አንጋጥጠን ማረን የምንለው ጌታ ዘኬዎስን ከምድር ሆኖ ወደ ላይ እያየ ና ልማርህ አለው:: "ዛሬ በቤትህ እውል ዘንድ ይገባኛል" አለው:: ጌታ ወደ ቤቱ ገባ:: ለዘኬዎስ ቤት መዳን ሆነለት::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ኖሮ ከሰዎች ጋር እየተጋፋ ጌታን ያይ ይሆናል እንጂ በጌታው ዓይን ለመታየት የሚያበቃ ትጋት አያሳይም ነበር:: ምናልባትም ሰዎችን ገለል በሉ እያለ በኩራት ሲጋፋ ከአንዱ ጋር ሲጣላ ሊቆይ ይችል ነበር::

ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ከዛፍ ላይ አይወጣም ነበር::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን የሠራዊት አምላክ ወደ ቤቱ አይገባም ነበር:: በኪሩቤል ላይ የሚቀመጠው ንጉሥ በቤቱ ወንበሮች ላይ የተቀመጠው ዘኬዎስ በማጠሩ ምክንያት ነው:: የዘኬዎስ ነፍስ የዳነው በቁመቱ ማጠር ነበር:: እግዚአብሔር የመዳኑን ቀን የቆረጠለት ቁመቱን ሲያሳንሰው ነበር:: በምድር በመጽሐፍ ቅዱስ በሰማይ በሕይወት መዝገብ ስሙ የተጻፈው ዘኬዎስ አጭር በመሆኑ ነው::

ስለ ቁመት የማወራ እንዳይመስልህ:: እግዚአብሔር ለነፍሳችን መዳን የሚያሳጥርብን ብዙ ነገር አለ::
እንደ ዘኬዎስ ቁመትህ አጭር ባይሆን የሚያጥርህ ነገር ግን አይጠፋም::

ይሄ ጎደለኝ የምትለው ከሰዎች አነስኩበት የምትለው ነገር አንዳች ነገር የለም? እሱን ማለቴ ነው::
ይሄ ይጎድለኛል ከሰው አንሳለሁ እያልክ አትማረር::
እጥረትህ መክበሪያህ ነው:: ጉድለትህም መዳኛህ ነው::

እግዚአብሔር ያጎደለብህ የመሰለህ ነገር ወደ ዛፍ እንድትወጣ ምክንያትህ ይሁን:: በጉድለትህ እንደ ዘኬዎስ ከፍ በልበት:: ያኔ ሰዎች አንተን አንጋጠው ከማየት ውጪ አማራጭ አይኖራቸውም::
ፈጣሪ በፍቅሩ ይይህ እንጂ ሰዎች ወዳንተ ያዘነብላሉ:: በቤትህ መዳን ይሆንልሃል:: ከዚያም ስላጠረህ ስለጎደለህ ነገር ፈጣሪህን ስታመሰግነው ትኖራለህ::

እመነኝ አንዳንድ ጉድለቶች እድሎች ናቸው::
ዘኬዎስ አጭር ባይሆን ይሄኔ በሾላው ዛፍ ጥርሱን እየፋቀ ይቀር ነበር::

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ግንቦት 23 2014 ዓ.ም.
አዲስ አበባ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
1 ሰው ለ10 ሰው ሼር በማድረግ ቻሌንጁን ይቀላቀላሉ
#ድንግል_ማርያም_እኮ
1. እግዚአብሄርን ልጄ የምትል። ሉቃስ 2:48
2. አምላክን የወለደች። ማቴ. 1:18፣ ራእይ 12:5
3. በድንግልና የወለደች። ማቴ. 1:22፣ ኢሳ. 7:14
4. መልአክ የሰገደላት፤ ያከበራት። ሉቃስ 1:28
5. በድምጿ ከማህፀን ፅንስ ያዘለለች። ሉቃስ 1:41
6. እግዚአብሄር እናቴ የሚላት።
7. መላእክት የማይነኩትን፣ የማያዩትን፣ ፊቱ የማይቆሙትን የዳሰሰች፣ ያቀፈች፣ የወለደች፣ ጡቷን ያጠባች። ሉቃስ 2:3
8. ከልጁዋ እርገት በኅላ ያረገች። መሀሊይ 4:8
9. የአዳም እና ሄዋን እርግማን ያልደረሰባት። መዝ. 44/5:11 ፣ 45/6:4
10. በጌታችን ቀኝ የምትቆም። መዝ. 44/5:9
11. የትውልድ ሁሉ እናት የሆነች። መዝ. 86/7:5
12. ትውልድ ሁሉ ብፅይት የሚሏት። ሉቃስ 1:48
13. ሁሉንም አይነት ፀጋ የተሞላች። ሉቃስ 1:28
14. ከሴቶች ሁሉ ተለይታ ቡሩክት የሆነች። ሉቃስ 1:28
15. ቡሩክት የተባለች። ሉቃስ 1:45
16. የሰውን ችግር ቶሎ የምትረዳ። ዮሀንስ 2:3
17. ማህፀንሽ እና ጡቶችሽ የተባረኩ ናቸው የተባለላት። ሉቃስ 11:27
18. ፀሀይን የተጎናፀፈች፣ ጨረቃን ከእግሮቿ በታች የተጫማች፣ በእራሷ ላይ አስራ ሁለት የከዋክብት አክሊል ያላት። ራእይ 12:1
19. ዘንዶውም ያደረሰባት። ራእይ 12:13
20. ሁለት ትልልቅ የንስር ክንፍ የተሰጣት። ራእይ 12:14
21. የመላእክት እህት፣ የሰማእታት እናት የሆነች።
22. ለዘላለም ድንግል የሆነች። ሂዝቅኤል 44:1-3
23. የእግዚአብሄር ከተማ የተባለች። ኢሳ. 60:14
24. የእግዚአብሄር አብ ሙሽራ የወልድ እና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ ሆነች። መዝ. 131/2:14 ፣ ሉቃስ 1:41
25. በሀሳብ፣ በስጋ እና በነፍስ ፍፁም ድንግል የሆነች።
26. ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ የሆነች።
27. በሰማያዊ ህብስት እና ፅዋ ያደገች።
28. በቤተ መቅደስ ያደገች። መዝ. 44/5:10
29. ሰው ሁሉ እናታችን ፅዮን የሚላት። መዝ. 86/7:5
30. በድምጿ መንፈስ ቅዱስ የሞላች። ሉቃስ 1:41
31. እግዚአብሄር በማህፀኗ ለማደር የመረጣት። መዝ. 131/2:12-13
32. በእለተ አርብ ልጁዋ የሰጠን እናታችን። ዮሀንስ 19:27
በዚህ ሁሉ የተመላች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ብቻ ናት።
@yedingelsitota21
@yedingelsitota21
@yedingelsitota21
005
#ቅዱስ ፋሲለደስ ሰማዕት (መስከረም ፲፩)

ለአንጾኪያ ነገሥታት አባታቸውና መካሪያቸው የሆነ #ቅዱስ_ፋሲለደስ በሰማዕትነት የድል አክሊልን ተቀበለ ንቆ ሰለ ተዋት ምድራዊት መንግሥት ፈንታም ሰማያዊት መንግሥት አገኘ ።

እርሱም ለሮም ንጉሥ የሠራዊት አለቃ ነው መንግሥቱም ሁለመናዋ በእርሱ ምክር የጸናች ናት ብዙዎችም ወንዶችና ሴቶች የቤት ውልዶች አገልጋዮች አሉት ዝምድናውም እንዲህ ነው ስሙ ኑማርያኖስ የተባለ የሮም ንጉሥ ለቴዎድሮስ በናድሌዎስ እናቱ የሆነች የቅዱስ #ፋሲለደስን እኅት አግብቶ #ዮስጦስን#ገላውዴዎስን#አባዲርን ወለደችለት እሊህም ለቅዱስ ፋሲለደስ የእኅቱ ልጆች ናቸው የቅዱስ ፋሲለደስም ሚስት ለ #ቅዱስ_ፊቅጦር እናት እኅት ናት ከእርሷም ስማቸው አውሳብዮስና መቃርስ የተባሉ ሁለት ልጆችን ወለደ በዚያም ወራት የቊዝና የፋርስ ሰዎች የሮምን ሰዎች ሊወጓቸው በላያቸው ተነሡ ያን ጊዜ የንጉሥ ልጅ ዮስጦስን የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስን ከጦር ሠራዊቶቻቸው ጋር ለውጊያ ላኳቸው።

ንጉሡ ኑማርዮስም ሌሎች ጠላቶች በተነሡበት በኩል ለጦርነት ሒዶ በውጊያው ውስጥ ሞተ የሮም መንግሥትም የሚጠብቃትና የሚመራት የሌላት ሆነች እንዲህም ሆነ በዚያ ወራት ስለ ጦርነት ለመደራጀት የሮም ሰዎች ከሀገሩ ሁሉ አርበኞች የሆኑ ሰዎችን ሰበሰቡ ከውስጣቸውም ከላይኛው ግብጽ ስሙ አግሪጳዳ የሚባል የፍየሎች እረኛ የሆነ አንድ ሰው አለ እርሱንም መኳንንቱ ወስደው በመንግሥት ፈረሶች ላይ ባልደራስ አድርገው ሾሙት እርሱም በጠባዩና በሥራው ሁሉ ኃይለኛና ብርቱ ነበር።

ከንጉሥ ኑማርያኖስ ሴቶች ልጆች አንዲቱ ወደርሱ በመስኮት ተመለከተች ወደደችውም መልምላም ወስዳ አገባችው ስሙንም ዲዮቅልጥያኖስ ብላ ሰይማ አነገሠችው ከጥቂት ቀኖችም በኋላ ሰማይና ምድርን የፈጠረ እግዚአብሔርን ትቶ ጣዖታትን አመለከ #ቅዱስ_ፋሲለደስም ሰምቶ እጅግ አዘነ የመንግሥትንም አገልግሎት ተወ ከዚህም በኋላ የንጉሥ ኑማርያኖስ ልጅ ዮስጦስና የፋሲለደስ ልጅ አውሳብዮስ ጠላቶቻቸውን ድል አድርገው የጠላቶቻቸውንም አገሮች አጥፍተው ደስ ብሏቸው ተመለሱ ነገር ግን የነገሠው ዲዮቅልጥያኖስ የክብር ባለቤት #ክርስቶስን ክዶ አምልኮ ጣዖትን አቁሞ አገኙት እጅግም አዘኑ ተቆጥተውም ተነሡ ሰይፎቻቸውን መዝዘው ዲዮቅልጥያኖስን ገድለው የንጉሥ ኑማርያኖስን ልጅ ዮስጦስን ሊያነግሡ ወደዱ ፋሲለደስም ከዚህ ሥራ ከለከላቸው ከዚህም በኋላ #ቅዱስ ፋሲለደስ ዘመዶቹን ሠራዊቱን አገልጋዮቹንም ሁሉ ሰበሰባቸውና በክብር ባለቤት በክርስቶስ ስም ደሙን ሊያፈስ እንደፈለገ አስረዳቸው ሁሉም እንዲህ ብለው መለሱለት አንተ በምትሞትበት ሞት እኛ ከአንተ ጋር እንሞታለን በዚህም ምክር በአንድነት ተሰማሙ ከዚህም በኋላ በንጉሥ ዲዮቅልጥያኖስ ፊት ቁመው ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ታመኑ ከእርሳቸውም ግርማ የተነሣ ታላቅ ፍርሃትን ፈራ እነርሱ የመንግሥት ልጆች ናቸውና።

#የቅዱስ ፊቅጦር አባት ኀርማኖስም ወደ ግብጽ አገር ይልካቸው ዘንድ በዚያም እንዲያሠቃዩዋቸው መከረው ሁሉንም እየአንዳንዳቸውን ለብቻቸው አድርጎ ላካቸው አባዲርንና እኀቱ ኢራኒን ወደ አንዲት አገር አውሳብዮስንና ወንድሙ መቃርስን ወደሌላ ቦታ ገላውዴዎስንም እንዲሁ አደረጉ በናድሌዎስ ቴዎድሮስም እሼ በሚባል ዕንጨት ላይ በመቶ ሃምሳ ሦስት ችንካር ተቸንክሮ ገድሉን ፈጸመ።

#ቅዱስ_ፋሲለደስን ግን አምስት ከተማዎች ወዳሉበት ወደ አፍሪካ ምድር ወደ መኰንኑ ወደ መጽሩስ ላከው መጽሩስም በአየው ጊዜ መንግሥቱን ክብሩን ስለ ተወ እጅግ አደነቀ #ክብር ይግባውና ጌታችን ክርስቶስም መልአኩን ልኮ በመንፈስ ወደ ሰማይ አውጥቶ በብርሃን ያጌጠ መንፈሳዊ ማደሪያን አሳየው ነፍሱም እጅግ ደስ አላት ከዚህም በኋላ ወደነበረበት መለሰው ባሮቹን ግን ነፃ ያወጣቸው አሉ የቀሩትም ከእርሱ ጋር የሰማዕትነት አክሊልን የተቀበሉ ሰባት ሺህ ሠላሳ ሦስት የሚሆኑ አሉ።

#ቅዱስ ፋሲለደስንም ታላቅ ስቃይን አሰቃዩት በመንኰራኲርና በተሣሉ የብረት ዘንጎች ሥጋውን ሰነጣጥቀውት ሞተ ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም ያለ ጥፋት ከሞት አድኖ አስነሣው አሕዛብም ሁሉ ይህን ድንቅ ተአምር በአዩ ጊዜ አደነቁ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አመኑ መኰንኑንም ረገሙት ጣዖቶቹንም ሰደቡ በእነርሱ ላይም ተቆጥቶ ራሶቻቸውን በሰይፍ ይቆርጧቸው ዘንድ ወታደሮቹን አዘዘ የሰማዕትነት አክሊልንም ተቀበሉ ቊጥራቸውም ዐሥራ አራት ሺህ ሰባት መቶ ወንዶች ሠላሳ ሰባት ሴቶች ናቸው ከዚህም በኋላ #ቅዱስ_ፋሲለደስን ሥጋው ሁሉ ቀልጦ እንደ ውኃ እስከሚሆን በብረት ምጣድ ውስጥ አበሰሉት መኰንኑም በተራራ ላይ ጥልቅ ጒድጓድ ቆፍረው በዚያ እንዲቀብሩት አዘዘ እንዲሁም አደረጉ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅዱስ ፋሲለደስን ከሞት ደግሞ አስነሣው ወደ መኰንኑም መጥቶ እንዲህ ብሎ ጮኸ መኰንን መጽሩስ ሆይ እፈር ከሀዲ ንጉሥህም የረከሱ ጣዖቶችህም ይፈሩ እነሆ ክብር ይግባውና ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ ያለ ጉዳት ከሞት ጤነኛ አድርጎ አስነሥቶኛልና።

ሕዝቡም ይህን ተአምር በአዩ ጊዜ ክብር ይግባውና በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አምነው በሰማዕትነት ሞቱ ቁጥራቸውም ሁለት ሺህ ሦስት መቶ ሆነ ከዚህም በኋላ #ቅዱስ ፋሲለደስን በውስጧ መጋዝ ካላት መንኰራኲር ላይ አውጥቶ ታላቅ ሥቃይን አሠቃየው ዳግመኛም በብረት ዐልጋ ላይ በሆዱ አስተኝተው ከበታቹ እሳትን አነደዱ ያን ጊዜም ክብር ይግባውና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት ከዚያ ስቃይም ውስጥ አንስቶ ያለ ጉዳት ጤነኛ አደረገው እንዲህም ብሎ ቃል ኪዳን ሰጠው

         #ፋሲለደስ ሆይ   

"  ዕውቅ መታሰቢያህን ለሚያደርግ ሁሉ ወይም ለድኆች በስምህ ምጽዋትን ለሚሰጥ ወይም ለተራቈተ ልብስን ወይም በመታሰቢያህ ቀን ለቤተ ክርስቲያን መባ ለሚሰጥ በብዙም ቢሆን በጥቂት መታሰቢያህን ለሚያደርጉ ሁሉ እኔ በደላቸውን ሁሉ እተውላቸዋለሁ መኖሪያቸውንም በመንግሥተ ሰማያት ከአንተ ጋራ አደርጋለሁ ። "

ጌታችንም ይህን ካለው በኋላ በታላቅ ክብር ወደ ሰማያት ዐረገ ቅዱስ ፋሲለደስም በፍጹም ደስታ ደስ ተሰኘ።
ከዚህም በኋላ መጽሩስ መኰንን ከአማካሪዎቹ ጋር ተማከረ እንዲህም አላቸው ስሙ ፋሲለደስ ስለሚባል ስለዚህ ሰው ምን ላድርግ እርሱን ያላሠቃየሁበት የሥቃይ መሣሪያ ምንም የቀረ የለም ከሐሳቡም አልተመለሰም እነርሱም እንዲህ ብለው መከሩት ራሱን በሰይፍ ቆርጠህ ከእርሱ ተገላገል እነሆ የዚች አገር ሰዎች በእርሱ ምክንያት አልቀዋልና።

#የቅዱስ ፋሲለደስን ራስ በሰይፍ እንዲቆርጡ መኰንኑ አዘዘና ቆረጡት የድል አክሊልን ተቀበለ ንቆ ሰለተዋት ምድራዊት መንግሥት ፈንታም ሰማያዊት መንግሥት አገኘ።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
264
††† እንኳን ለቅዱሳን አባቶቻችን ሊቃውንት ዓመታዊ የጉባኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ጉባኤ ኤፌሶን †††

††† ቤተ ክርስቲያን እግዚአብሔርን ያከበሩትን: እርሱም ያከበራቸውን ሰዎች 'ቅዱሳን' ትላለች:: ራሱ ባለቤቱ "ኩኑ ቅዱሳነ እስመ ቅዱስ አነ-እኔ ቅዱስ ነኝና እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" ብሏልና:: (ዼጥ. 1:15) እነዚህንም ቅዱሳን 'መላእክት: አበወ ብሊት: ነቢያት: ሐዋርያት: ሰማዕታት: ጻድቃን: ሊቃውንት: ደናግል: መነኮሳት: ባሕታውያን' ወዘተ. ብለን: ክፍለ ዘመን ሰጥተን በአበው ሥርዓት እናስባለን::

ከእነዚህ ቅዱሳን መካከልም አንዱንና ትልቁን ቦታ ቅዱሳን ሊቃውንት ይወስዳሉ:: 'ሊቅ' ማለት 'ምሑር: የተማረ: ያመሰጠረ: ያራቀቀ: የተፈላሰፈ: በእውቀቱ የበለጠ: የበላይ: መሪ: ሹም: ዳኛ' . . . ወዘተ ተብሎ ሊተረጐም ይችላል::

ወንጌል ላይም ጌታችን መድኃኔ ዓለም ኒቆዲሞስን "አንተ ሊቆሙ ለእሥራኤል-አንተ የእሥራኤል መምሕር (አለቃ) ነህ" ብሎታል:: (ዮሐ. 3:10) ስለዚህም 'ሊቃውንት' ማለት በእውቀት ከሁሉ በላይ የሆኑ እንደ ማለት ነው::

ዘመነ ሊቃውንት ተብሎ የሚታወቀው ከ3ኛው ክ/ዘመን መጨረሻ እስከ 6ኛው መቶ ክ/ዘመን አጋማሽ ያለው ሲሆን በዚህ ዘመን እንደ እንቁ ያበሩ: ብርሃንነታቸው በሰው ፊት የበራ ብዙ አበው ተነስተዋል:: ቅዱሳን ሊቃውንት ከሌሎች ምሑራን ቢያንስ በእነዚህ ነገሮች ይለያሉ:-
1.እንደ ማንኛውም ሰው ከተማሩ በኋላ እውቀቱ ይባረክላቸው ዘንድ ጠዋት ማታ በጾምና በጸሎት ይጋደላሉ::
2.አብዛኞቹ ቅዱሳን ሊቃውንት ገዳማዊ ሕይወትን ጠንቅቀው ያውቃሉ::
3.ምሥጢር ቢሰወርባቸው ሱባኤ ይገባሉ እንጂ በደማዊ ጭንቅላት አይፈላሰፉም::
4.ፍጹም መናንያን በመሆናቸው ሃብተ መንፈስ ቅዱስ እንጂ የሚቀይሩት ልብስ እንኳ የላቸውም::
5.እያንዳንዷን የመጽሐፍ ቃል ከማስተማራቸው በፊት በተግባር ይኖሯታል::
6.እረኞች ናቸውና ዘወትር ለመንጋው ይራራሉ::
7.ስለ ቀናች ሃይማኖት ብዙ ግፍን ተቀብለዋል::
8.በኃይለ አጋንንት የመጡ መናፍቃንን ኃይለ መንፈስ ቅዱስን ለብሰው: መጻሕፍትን አልበው: ጥቅስ ጠቅሰው መክተዋል::
9.ምግብናቸውንም ፈጽመው ዛሬ በገነት ሐሴትን ያደርጋሉ::

††† የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ የምትቀበላቸው የቅዱሳን ጉባኤያት 3 ብቻ ናቸው::
1ኛ.በ325 (318) ዓ/ም በኒቅያ 318ቱ ሊቃውንት ያደረጉትን
2ኛ.በ381 (373) ዓ/ም በቁስጥንጥንያ 150ው ሊቃውንት ያደረጉትን: እንዲሁም
3ኛ.በ431 (424) ዓ/ም በዚህች ቀን 200ው ሊቃውንት ያደረጓቸውን ጉባኤያት ትቀበላለች::
ይሕስ እንደ ምን ነውቢሉ:-
በወቅቱ ስመ ክፉ መናፍቅ ንስጥሮስ ተነስቶ የእስያ አብያተ ክርስቲያናትን አወካቸው:: ትምሕርቱ ክርስቶስን 2 አካል: ባሕርይ ነው (ሎቱ ስብሐት!) የሚል ነበር:: በእውነት እንየው ከተባለ ግን ጠቡና ጥላቻው ከድንግል ማርያም ጋር ነበር:: ምክንያቱም ጌታችንን ወደ 2 የከፈለው እመቤታችንን የአምላክ እናት አይደለሽም ለማለት ነው:: (ላቲ ስብሐት)

ነገሩን ቅዱስ ቄርሎስ በሰማ ጊዜ ወዳለበት ሒዶ ቢመክረውም ንስጥሮስ ሊሰማ አልፈለገም:: በዚህ ምክንያት በትንሹ ቴዎዶስዮስ (የቁስጥንጥንያ ንጉሥ) ትዕዛዝ በኤፌሶን ታላቅ ጉባኤ እንዲሰበሰብ ሆነ::

ይህ ጉባዔ በቤተ ክርስቲያናችን የመጨረሻው የተቀደሰ ጉባዔ ነው:: በ431 ዓ/ም በኤፌሶን ከተማ የመናፍቃኑን ጥርቅም ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና 200 ቅዱሳን ሊቃውንት ተገኙ::

የሚገባው ጸሎትና ሱባዔ ከተፈጸመ በኋላ ጉባዔው ተጀመረ:: አፈ ጉባዔው ሊቀ ማሕበር ማር(ቅዱስ) ቄርሎስ ነበርና በጉባዔ ፊት ንስጥሮስን ተከራክሮ ረታው:: ምላሽም አሳጣው:: ከቅዱሳት መጻሕፍት ክርስቶስ አንድ ባሕርይ መሆኑን: ድንግል ማርያምም ወላዲተ አምላክ መሆኗን እየጠቀሰ: በምሳሌም እያሳየ አስረዳ::

የሰይጣን ማደሪያ ንስጥሮስ ግን እንቢ: አላምንም በማለቱ ተወግዞ ተለየ:: ቅዱሳን ሊቃውንቱም በቅዱስ ቄርሎስ አርቃቂነት 12 አንቀጾችን አዘጋጅተው ወደ ዓለም ሁሉ ላኩ:: እሊህ አንቀጾች ዛሬም በሊቃውንቱ እጅ አሉ:: ይነበባሉ: ይተረጎማሉ::

ከእነዚህም አንዱ ድንግል ማርያም "ታኦዶኮስ (የእግዚአብሔር እናቱ) ናት" የሚል ነው:: እመቤታችንን የአምላክ እናት: ዘላለማዊት ድንግል: ፍጽምት: ንጽሕትና አማላጅ ብሎ ማመን ለሰማያዊ ርስት የሚያበቃ በጐ ሃይማኖት ነውና::

ጉባዔው ከተጠናቀቀ በኋላ ቅዱስ ቄርሎስ ንስጥሮስን ጠርቶ "በድንግል ማርያም እመን:: እርሷ ከልጇ ታስታርቅሃለች" ቢለው በድጋሚ "እንቢ" አለው:: ያን ጊዜ ሊቁ "ለአምላክ እናት ያልታዘዘ ምላስህ ላንተም አይታዘዝህ" ብሎ ረገመው:: ወዲያው ምላሱ ተጐልጉሎ ወጥቶ ደረቱ ላይ ወደቀ::

እንደ ውሻ እየተዝረከረከ ሂዶ ከወዳጆቹ ጋር ቁሞ ሳለ መሬት ተከፍታ ውጣዋለች::

††† አምላከ ሊቃውንት ዛሬም ያሉንን አባቶች ይጠብቅልን: ያንቃልን:: ከቅዱሳን ሊቃውንት በረከትም አይለየን:: የእመ ብርሃን ፍቅሯንም ያሳድርብን::

††† መስከረም 12 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱሳን 200ው ሊቃውንት (በኤፌሶን የተሰበሰቡ)
2.ቅዱስ ቄርሎስ ዓምደ ሃይማኖት
3.ጻድቅ ንጉሥ ቴዎዶስዮስ
4.ቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት
5.ቅዱሳን ኢያቄም ወሐና
6.ቅዱስ ኢሳይያስ ነቢይ

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት
2.ቅዱስ ላሊበላ ጻድቅ (ንጉሠ ኢትዮዽያ)
3.ቅዱስ ማቴዎስ ሐዋርያ
4.ቅዱስ ድሜጥሮስ
5.ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ
6.ቅዱስ ቴዎድሮስ ምሥራቃዊ (ሰማዕት)
7.ቅድስት ክርስቶስ ሠምራ
8.አቡነ ሳሙኤል ዘዋልድባ

††† "ስለዚህ በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያንን ትጠብቁአት ዘንድ መንፈስ ቅዱስ እናንተን ዻዻሳት አድርጎ ለሾመባት: ለመንጋው ሁሉና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ:: ከሄድሁ በኋላ ለመንጋው የማይራሩ ጨካኞች ተኩላዎች እንዲገቡባችሁ እኔ አውቃለሁ:: ስለዚህ 3 ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሰጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ::" †††
(ሐዋ. ፳፥፳፰)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
@petroswepawulos
@petroswepawulos
@petroswepawulos
ሰይጣን የኢዮብን ሀብት ሲያወድምበት ፣ ዐሥር ልጆቹን ሲገድልበት ፣ ጤናውን ሲወስድበት አንድ ነገር ግን አልነካበትም::

ሚስቱን::

ለምን?

ሚስቱን ያልነካው ምናልባት ነገረኛ ቢጤ ስለሆነች ከኢዮብ መከራ ውስጥ ተቆጥራ ይሆን? ሰይጣን ሚስቱን ያልነጠቀው " ታንገብግበው" ብሎ ይሆን?

ጠቢቡ "በዝናብ ቀን የሚያንጠባጥብ ቤትና ጠበኛ ሴት አንድ ናቸው" ይላል:: ምሳ.27:15 ምናልባት በሰይጣን እይታ ኢዮብን ለማማረር ሚስቱ መቆየት ነበረባት ይሆን?

በእርግጥ የኢዮብ ሚስት "ፈጣሪን ሰድበህ ሙት" የምትል መሆንዋን ስናይ ለኢዮብ ፈተና እንድትሆን ይሆናል ሳንል አንቀርም:: ሰይጣንም እንዲህ ብናስብ አይጠላም::

ነገሩ ግን ወዲህ ነው:: ሰይጣን የኢዮብን ሚስት እንዳይነካት ያደረገው የራሱ የእግዚአብሔር ትእዛዝ ነበር::

"ሕይወቱን ተወው እንጂ እነሆ እርሱ በእጅህ ነው" ብሎ እግዚአብሔር ለሰይጣን አስጠንቅቆት ነበር:: ሕይወቱን አትንካ የተባለው ሰይጣን ሌላውን ሁሉ ሲያጠፋ ሚስቱን ግን ያልነካው ሚስት ሕይወት ስለሆነች ነው:: ሚስቱን መንካትም ራሱን ኢዮብን መንካት ነበር:: አዎ ሚስት ሕይወት ናት:: እንደ ኢዮብ ሚስት ብትከፋም እንደ ምሳ. 31ዋ ሚስት መልካም ብትሆንም ሕይወት ናት:: ሕይወት ደስታም ኀዘንም አለበት:: "ሕይወት እንዲህ ናት" c'est la vie እንዲል ፈረንሳይ:: ራሱ ኢዮብም "በምድር ላይ የሰው ሕይወት ብርቱ ሰልፍ አይደለምን?" ብሎአል:: ኢዮ. 7:1

አዳምም አለ :-

"ይህች አጥንት ከአጥንቴ ይህች ሥጋ ከሥጋዬ ናት"

"አዳምም ሔዋንን ሕይወቴ ነሽ ይላት ነበር"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
መስከረም 2016 ዓ.ም.
ሕንድ ውቅያኖስ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ንጹሕ ሁኑ 
                                                  
Size:- 23MB
Length:-1:06:01
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
433
በዚ ቻናል ደስተኛ ኖት ???
Anonymous Poll
80%
ሀ' በጣም ደስተኛ ነኝ
20%
ለ'አይደለሁም ይሻሻል
540
“ስለ መተላለፋችን ምንም ዓይነት ቅጣት የማንቀበል ብንሆን ኖሮ እግዚአብሔር ኅሊናን የሚያህል ፈራጅ ዳኛ በውስጣችን አይፈጥርም ነበር፡፡”

ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
ብዙ ሰው "ያሰብኹት ሁሉ ምንም ሊሳካልኝ አልቻለም" እያለ ያጉረመርማል፤ "እግዚአብሔርማ እኔን ሳይተወኝ አልቀረም!" እያለ ፈጣሪውን ያማርራል። "ይሰጠኛል" ሳይሆን "አገኘዋለሁ" ብሎ ይጀምርና ሳይሆን ሲቀር በእጁ የነበረውን የነጠቀው ያህል አምላኩ ላይ ያለቅሳል። ስታቅድ ያላስታወስከውን አምላክ ያቀድከው ሲፈርስ ስሙን እየጠራህ ስለምን ትወቅሰዋለህ? በሕይወትህ መቼ ቦታ ሰጠኸው? እንደ ፈቃዴ ካልሆነ አልህ እንጂ መቼ "እንደ ፈቃድህ ይሁን" ብለህ ጸለይህ? ባላማከርከው ለምን ተከሳሽ ታደርገዋለህ?

ልሥራ ብለህ በተነሣህበትም ቀን እንዲሁ በግዴለሽነት ስሙን ጠርተህ እንደ ሆነም ራስህን መርምር? በትክክል ጸልየህና በመንገድህ ሁሉ ይመራህ ዘንድ ፈቅደህ ከጀመርህ ግን ግድ የለም እረኛህን እመነው። አንተ እንደ ሎጥ ከመረጥኸው እና ለጊዜው የገነት አምሳል ሆኖ ከሚታይህ ነገር ግን እግዚአብሔር ከማይከብርበት ከለምለሙ ሰዶምና ገሞራ ይልቅ፣ አሁን ብዙም ለአይን የማይስበው በኋላ ግን ወተትና ማር የሚያፈሰው ለልጅ ልጆችህም ርስት የሚሆነው እግዚአብሔር የሚሰጥህ ከነአን ይሻልሃል።

(Deacon Abel Kassahun Mekuria

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
በጸሎት ኃይል የሚያምን አንድ ጽኑዕ ክርስቲያን ነበር፡፡ ይህም ክርስቲያን ጥሪት የሌለው ደሃ፣ የሚበላ የሚቸግረው ረሃብተኛ፣ ልብሱ በላዩ ላይ አልቆ የታረዘ ምስኪን ነው፡፡ ከእለታት አንድ ቀን በጸሎት ሕይወቱ የነበረውን ትጋት በቅርበት ያውቅ የነበረው አንድ ወዳጁ እየተቆጣ 'ቢያንስ ለረሃብህ ማስታገሻ ቁራሽ ዳቦ እንኳን ማሰጠት ካልቻለ የአንተ ጸሎት ፋይዳው ምንድር ነው? ይቅርብህ በቃ! ፈጣሪህ አይሰማህም ማለት ነው' ሲል ተስፋ በሚያስቆርጥ ቃል ተናገረው፡፡ ያም ምስኪን ክርስቲያን እንዲህ ሲል መለሰለት፦ 'እግዚአብሔርማ አልረሳኝም። ለአንዱ ሰው ከዕለት እንጀራው የበለጠ አትርፎ በመስጠት ለእኔ እንዲያካፍለኝ መልእክተኛ አድርጎት ነበር፡፡ ነገር ግን ይህን አደራ የተቀበለው ሰው ዘነጋኝ፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሳይሆን አድራሹ ሰው ረስቶኛል!'

መጻሕፍት እንደሚያስተምሩን "የዕለት እንጀራችንን ስጠን" የሚለው ጸሎት ለመነኮሳት ሲሆን "ለዕለት"፣ በዓለም ለሚኖሩ ሰዎች ሲሆን ደግሞ "ለዓመት" የሚሆን እንጀራ ስጠን ማለት ነው። ታዲያ ለምን አንዳንዶች ከዓመት የሚተርፍ ብዙ እንጀራ ሲያገኙ፣ ሌሎች ደግሞ ለዕለት እንኳን የሚሆን ቁራሽ ያጣሉ ? መቼም 'ለሰው ፊት የማያዳላ' እግዚአብሔር "አድልዎ ቢኖርበት ነው" ብለን የድፍረት ቃል በእርሱ ላይ አንናገርም። (ሐዋ 10፥34) ይህ የሆነው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ትምህርት አትርፈው ያገኙ ሰዎች ምንም የሌላቸውን እንዲረዱ እና መግቦት የባሕርይው የሆነውን አምላካቸውን በጸጋ እንዲመስሉት ነው። በዚሁም ላይ በፈጠራቸው ሰዎች መካከል ያለውን የመተዛዘንና የፍቅር ትስስር የበለጠ ለማጠናከር ነው፡፡

'የዕለት እንጀራችንን ስጠን ለዛሬ' ብለን የለመንነው አምላክ ከዓመት እንጀራችን በላይ አትርፎ የሚሰጠን፣ የሚበቃንን ያህል ተመግበን በቀረው ለሌሎች አድራሽ መልእክተኞች እንድንሆን ነው። ስለዚህ ይህን የተጣለብንን አምላካዊ አደራ ባለመወጣት ድሆችን አንበድል፤ ተማርረው ከፈጣሪያቸውም ጋር እንዲጣሉ አናድርጋቸው።

(Deacon Abel Kassahun Mekuria)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 14:30:33
Back to Top
HTML Embed Code: