Telegram Web Link
#ሱባዔ_እንዴት_እንግባ?


1.ሱባዔ መያዝ ስለፈለግንበት ጉዳይ ማሰብ እና መለየት፡- ዓላማ የሌለን ዝርው የሆነ ያልተሰበሰበ አእምሮ ይዘን እንዳንገባ ፤ ከቅዱሳን በረከት ለመሳተፍ፤ወይም የግል ሕይወት ጉዳይ፡- ሥራ፣ትምህርት፤ትዳር…የሀገርና የቤተ ክርስቲያን የመሳሰሉትን ጉዳዮች ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡

2. ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ስለ ሱባዔ በደንብ ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል፡- መጀመሪያ ከንስሐ አባቶቻችን ጋር መመካከር፤ ቀጥሎም ስለ ሱባዔ ከሚያውቁ መንፈሳውያን አባቶች መጠየቅ ያስፈልጋል፤ ብዙዎችን ሱባዔ ማለት ቀልድ የሚመስላቸው ዝምም ብለው የሚጀምሩት ጉዳይ ሆኗል፤ በዚህም ምክንያት የብዙዎች ሕይወት የሰይጣን መጫወቻ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡

3.ስለምንቆይባቸው የቀናት ብዛት በሚገባ በማሰብ መወሰን፡ -ሱባዔ ማለት ቀጥታ ትርጉሙ ሰባት ማለት ይሁን እንጂ የግድ ግን ሰባት ቀን ወይም ሰባት ዓመት መኖር ማለት አይደለም፤ ይህ ለተሰጣቸውና ከዓለም ሙሉ ሕይወታቸውን ላገለሉ ሰዎች እንጂ ለዓለማውያን የተሰጠ አይደለም፤ ሃያ አራት ሰዓት ወይም 48 ሰዓት ወይም ደግሞ 72 ሰዓት (ሦስት ቀናት) ሊሆን ይችላል፤ ከዚህ ጀምሮ እንደየዓቅማችን 7፣14፣21….ቀናት እያልን ልናሳድገው እንችላለን፡፡ ይህም የሚጠቅመን ምናልባት ባለማወቅ ከጀመርነው በኋላ ፈተናው ሲፀናብን እንዳናቋርጥና ከእግዚአብሔር ጋር እንዳንጣላ ነው፤ይህንንም ጌታችን በምሳሌ እንዲህ ሲል አስተምሮናል "ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ኪሳራውን የማይቆጥር ማነው? ያለዚያ መሠረቱን ቢመሠርት ሊደመድመውም ቢያቅተው ያዩት ሁሉ፡-ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ" (ሉቃ 14፡28-30) በማለት አጋንንት፤ የመናፍቃን መሳለቂያ እንዳንሆን ያስጠነቅቀናል፡፡

4. የምንጸልያቸውን ጸሎቶች መለየት፡- በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ብዙ ዓይነት ጸሎት መኖሩ ይታወቃል፤ሁሉንም እንጸልያለን ብንል ዓይናችን ይፈዛል አንደበታችን ይላሻል፤ ስለዚህም በየሰዓቱና በየዕለቱ የምንጸልያቸውን ጸሎቶች በመለየት ሳናስታጉል በትጋት መጸለይ አለብን፤ በጸሎት ጊዜም ሰጊድ(ስግደት)፤አስተብርኮ(መንበርከክ)፤ አንቃዕድዎ(ማንጋጠጥ) ከእንባ ጋር መረሳት የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው፤ እነዚህንም ያስተማረን ራሱ ጌታችን መሆኑን ልብ ይሏል! ማቴ 26፡39፤ሉቃ 22፡42፤ዮሐ 11፡41፡፡

5.የምንመገባቸውን የምግብ ዓይነቶች ለይቶ መወሰንና እናም የመመገቢያ ሰዓትን ማወቅ፡- ምግብ መጠጥ ኃጢአት ምንጮች ናቸው፤ በተለይም አብዝቶ መመገብ ልዩ ልዩ ዓለማዊ ነገሮችን እንድናስብ ከማድረጉ በተጨማሪ እንዳንጸልይና እንዳንሰግድ በማድረግ ይጫነናል፤ ስለዚህ የምንመገበው ለቁመተ ሥጋ ያህል ብቻ እና በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ብቻ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆኑን ሠለስቱ ደቂቅ እና ነቢዩ ዳንኤል ናቸው፤ዳን 21 ቀናት) ሳዝን ነበርኩ ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም" (ዳን 10፡2-4)፡፡

6. ለሱባዔ በወሰንባቸው ጊዜያት ከማንኛውም ዓለማዊ ጉዳይ ጋር ያለንን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ለማቋረጥ መወሰን፡- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥርዓተ ጸሎትን ሲያስተምረን "አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በሥውር ላለው አባትህ ጸልይ በሥውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል“ (ማቴ 6፡6) ብሎ እንደነገረን በሱባዔ ጊዜ መገናኘት ያለብን ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ነው፤ ማንኛውም ጉዳያችን እና ማንነታችንም ሳይቀር በእርሱ እጅ መውደቅ አለበት፡፡

የልብ ሱባዔ እኖዲሆን የልብ ጸሎት እንድንጸልይ እግዚአብሔር ይርዳን!!!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
✝️ ያልተቋረጠ የክህነት ቅብብሎሽ✝️
፩) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ
፪) ቅዱስ ማርቆስ
፫) አናንዮስ
፬) መልዮስ
፭) ካርዳኖስ
፮) ፐሪሙስ
፯) ዮስጦስ
፰) ኦማንየስ
፱) ማርያኒስ
፲) ክላንድንያስ
፲፩) አግሪጳኖስ
፲፪) ዩልያኖስ
፲፫) ዲሜጥሮስ ፩ኛ (ባሕረ ሐሳብ የተገለጠለት)
፲፬) ኤራቅሊስ
፲፭) ዲዮናስዮስ
፲፮) ማክሲመስ
፲፯) ቴዎናስ
፲፰) ጴጥሮስ ፩ኛ (ተፍጻሜተ ሰማዕት)
፲፱) አኪላስ
፳) እለእስክንድሮስ ፩ኛ (የጉባኤ ኒቅያ አፈጉባኤ)
፳፩) አትናቴዎስ
፳፪) ጴጥሮስ ፪ኛ
፳፫) ጢሞቴዎስ ፩ኛ (የጉባኤ ቁስጥንጥንያ አፈጉባኤ)

፳፬) ቴዎፍሎስ
፳፭) ቅዱስ ቄርሎስ ፩ኛ (የጉባኤ ኤፌሶን አፈ ጉባኤ

፳፮) ቅዱስ ዲዮስቆሮስ ፩ኛ
፳፯) ጢሞቴዎስ ፪ኛ
፳፰) ጴጥሮስ ፫ኛ
፳፱) አትናቴዎስ ፪ኛ
፴) ዮሐንስ ፩ኛ
፴፩) ዮሐንስ ፪ኛ
፴፪) ዲዮስቆሮስ ፪ኛ
፴፫) ጢሞቴዎስ ፫ኛ
፴፬) ቴዎዶስዮስ ፩ኛ
፴፭) ጴጥሮስ ፬ኛ
፴፮) ድምያኖስ
፴፯) አንስታትዮስ
፴፰) እንድራኒቆስ
፴፱) ብንያሚ ፩ኛ
፵) አጋቶን
፵፩) ዮሐንስ ፫ኛ
፵፪) ይስሐቅ
፵፫) ስምዖን ፩ኛ
፵፬) እለእስክንድሮስ ፪ኛ
፵፭) ቆዝሞስ ፩ኛ
፵፮) ቴዎድሮስ ፩ኛ
፵፯) ሚካኤል ፩ኛ
፵፰) ሚናስ ፩ኛ
፵፱) ዮሐንስ ፬ኛ
፶) ማርቆስ ፪ኛ
፶፩) ያዕቆብ
፶፪) ስምዖን ፪ኛ
፶፫) ዮሴፍ ፩ኛ
፶፬) ሚካኤል ፪ኛ
፶፭) ቆዝሞስ ፪ኛ
፶፮) ሱንትዩ ፩ኛ
፶፯) ሚካኤል ፫ኛ
፶፰) ገብርኤል ፩ኛ
፶፱) ቆዝሞስ ፫ኛ
፷) መቃርዮስ ፩ኛ
፷፩) ቴዎፋኖስ
፷፪) ሚናስ ፪ኛ
፷፫) አብርሃም
፷፬) ፊላታዎስ
፷፭) ዘካርያስ
፷፮) ሱንትዩ ፪ኛ
፷፯) ክርስቶዶሉስ
፷፰) ቄርሎስ ፪ኛ
፷፱) ሚካኤል ፬ኛ
፸) መቃርዮስ ፪ኛ
፸፩) ገብርኤል ፪ኛ
፸፪) ሚካኤል ፬ኛ
፸፫) ዮሐንስ ፭ኛ
፸፬) ማርቆስ ፫ኛ
፸፭) ዮሐንስ ፮ኛ
፸፮) ቄርሎስ ፫ኛ
፸፯) አትናቴዎስ ፫ኛ
፸፰) ገብርኤል ፫ኛ
፸፱) ዮሐንስ ፯ኛ
፹) ቴዎዶስዮስ ፪ኛ
፹፩) ዮሐንስ ፰ኛ
፹፪) ዮሐንስ ፱ኛ
፹፫) ብንያሚ ፪ኛ
፹፬) ጴጥሮስ ፬ኛ
፹፭) ማርቆስ ፭ኛ
፹፮) ዮሐንስ ፲ኛ
፹፯) ገብርኤል ፬ኛ
፹፰) ማቴዎስ ፩ኛ
፹፱) ገብርኤል ፭ኛ
፺) ዮሐንስ ፲፩ኛ
፺፩) ማቴዎስ ፪ኛ
፺፪) ገብርኤል ፮ኛ
፺፫) ሚካኤል ፭ኛ
፺፬) ዮሐንስ ፲፪ኛ
፺፭) ዮሐንስ ፲፫ኛ
፺፮) ገብርኤል ፯ኛ
፺፯) ዮሐንስ ፲፬ኛ
፺፰) ገብርኤል ፰ኛ
፺፱) ማርቆስ ፭ኛ
፻) ዮሐንስ ፲፭ኛ
፻፩) ማቴዎስ ፫ኛ
፻፪) ማርቆስ ፮ኛ
፻፫) ማቴዎስ ፬ኛ
፻፬) ዮሐንስ ፲፮ኛ
፻፭) ጴጥሮስ ፭ኛ
፻፮) ዮሐንስ ፲፯ኛ
፻፯) ማርቆስ ፯ኛ
፻፰) ዮሐንስ ፲፰ኛ
፻፱) ማርቆስ ፰ኛ
፻፲) ጴጥሮስ ፮ኛ
፻፲፩) ቄርሎስ ፬ኛ
፻፲፪) ዲሜጥሮስ ፪ኛ
፻፲፫) ቄርሎስ ፭ኛ
፻፲፬) ዮሐንስ ፲፱ኛ
፻፲፭) መቃርዮስ ፫ኛ
፻፲፮) ዮሳብ ፪ኛ
፻፲፯) ቄርሎስ ፮ኛ
፻፲፰) አቡነ ባስልዮስ ዘኢትዮጵያ
፻፲፱) አቡነ ቴዎፍሎስ ዘኢትዮጵያ
፻፳) አቡነ ተክለሃይማኖት ዘኢትዮጵያ
፻፳፩) አቡነ መርቆሬዎስ ዘኢትዮጵያ
፻፳፪) አቡነ ጳውሎስ ዘኢትዮጵያ
፻፳፫) አቡነ ማትያስ ዘኢትዮጵያ

የክህነት ምንጭ ከሆነው ከጌታችን ከመድኃኒታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጀምሮ እስከአሁኑ ፓትርያርካችን እስከ አቡነ ማትያስ ያለው የክህነት ቅብብሎሽ ከላይ ያለውን ይመስላል። የእያንዳንዱ ቄስ፣ ዲያቆን፣ ጳጳስ ክህነት ቢቆጠር ነቁ እና የክህነቱ ባለቤት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።

በጉልበት ራሳቸውን የሾሙ እና ከቀኖና ቤተክርስቲያን ባፈነገጠ መልኩ የተሿሿሙ ሰዎች ክርስቶሳዊ የሆነው ክህነት የላቸውም። ይህም ማለት ቀድሰው ምሥጢራትን አይለውጡም። ጸጋ እግዚአብሔርን አያሰጡም። ስለዚህ ሕገወጥነትን አምርረን ልንቃወም ይገባናል።
          
©ዘአማን
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
9. በሀገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ የሚገኙ መንግስታዊም ሆነ መነግስታዊ ያልሆነ ተቋማት፤ አኃት አቢያተ ክርስቲያናት፤ የምሥራቅ ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት፤ የሮም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እና ሌሎች አብያተ ክርስቲያናት፤ የዓለም አቢያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት፤ የመላው አፍሪካ አብያት ክርስቲያናት ጉባዔ እና ሌሎች የአብያተ ክርስቲያናት እና የሃይማኖት ጉባኤዎች በሙሉ እነዚህ የተወገዙት ግለሰቦች የኢትዮጵያ ኦርቶደክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማይወክሉ እና ምንም አይነት የሥራ ግንኙነት የሌላቸው መሆኑ ታውቆ ማናቸውም ግንኙነት በቤተ ክርስቲያኑቱ ስም እንዳያደርጉ በጽሑፍ አንዲገለጽ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
  
11. እነዚህ ግለሰቦች የፈጸሙት ተግባር ሃይማኖቱን የሚወድ፣ አባቶቹን የሚያከብር እና አስተዋይ የሆነውን የትግራይ ሕዝብ የማይወክል፣ የራሳቸውን የሥልጣን ጥማት ለማርካት ያደረጉት ሕገወጥ የቀኖና ጥሰት መሆኑ እንዲታወቅ፤ በተጨማሪም ለሚያሠራጩት የሐሰት አሉባልታ ወደፊት ተገቢው መልስ እንዲሰጥበት ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

12. ይኽ ሕገወጥ አደረጃጀት ከረጅም ጊዜ ጀምሮ የታሰበበት፤ በየጊዜው የነበሩ የፖለቲካ እና የመንግሥት ኃላፊዎች በመታገዝ ሥር የሰደደ ድብቅ አጀንዳ በሚያስፈጽሙ ግለሰቦች የተቀናበረ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ ተገንዝቦ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞታል፡፡ በመሆኑም ሕገ ወጥ አደረጃጀትን ማምከን እና ቤተ ክርሰቲያንን ነፃ ማድረግ የሚቻለው ጠንካራ ውስጣዊ አደረጃጀት እና ዓለም አቀፍ እንቅስቃሴ ሲደረግ በመሆኑ ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ ሊቃውንት፣ መላው ውሉደ ክህነት፣ ወጣቶች ሰንበት ትምሀርት ቤት አባላት፣ መንፈሳውያን ማኅበራት፣ ምእመናን እና የቤተ ክርስቲያን ወዳጆች በሙሉ በመጾም፣ በመጸለይ፣ የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮና መዋቅር በጠበቀ መልኩ  በመደራጀት አፍራሽ እና የጥፋት መረጃዎችን፣ በመሰብሰብ፣ በመተንተን፣ ለውሳኔ በማቅረብ የቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ደኅንነት እስኪረጋገጥ ድረስ ያለማቋረጥ በመንፈሳዊ ተጋድሎ መበርታትና የመጣብንን ፈተና በጽናት መታገል እንደሚገባ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ ያሳስባል፡፡ 

13.  በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በተለያዩ ክፍሎች እየተከሠተ ያለውን የሰላም መደፍረስ እና የእርስ በርስ ግጭት ምክንያት የሰው ሕይወትና የንብረት ውድመት የተፈጠረ አለመግባባት ካለፈው ስህተታችን በመማር ችግሩን ተቀራርቦ በውይይትና በእርቅ እንዲፈታ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለሁሉም አካላት የሰላም ጥሪዋን ታስተላልፋለች፡፡

14.  እንደ ሀገር የገጠመንን የሰላም መደፍረስ በተመለከተ ዘላቂ መፍትሔ በማፈላለግ እንደ ቤተ ክርስቲያን ስለ ሰላም ጉዳይ የሚሠሩ ከብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ከሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን፣ ከሀገር ሽማግሌዎች እና ምሁራን ያካተተ ዐቢይ ኮሚቴ በቋሚ ሲኖዶስ በኩል ተቋቁሞ ሥራው እንዲሠራ ወስኗል፡፡ 
  
በመጨረሻም እስከ አሁን ድረስ በተፈጠረው ችግር ምክንያት ከቅድስት ቤተ ክርስቲያን ጎን በመሆን አጋርነታችሁን ያሳያችሁ፣ ለቤተ ክርስቲያን አንድነት እና ሉዐላዊነት መከበር የበኩላችሁን በመወጣት መግለጫ የሰጣችሁ ሁሉ በልዑል እግዚአብሔር ስም እያመሰገንን ለወደፊቱም በጸሎታችሁ እና በመልካም አጋርነታችሁ ከጎናችን እንድትሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡

             እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ
                ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም. 
                     አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
የመጻሕፍትን ትምህርት የሚጠግባቸው የለም

Size:-45.7MB
Length:-2:11:16

   በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
            መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን |

በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር የምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናንና ምእመናት እንዲሁም ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት በሙሉ እግዚአብሔር አምላካችን በይቅርታውና በምሕረቱ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ አምስት ዓመተ ምሕረት የድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታ በሰላም አደረሳችሁ:: “ወእምኵሉስ ዘይቀድም ተፋቀሩ በበይናቲክሙ በምልአ ልብክሙ እስመ ተፋቅሮ' ይደፍኖን ወይደመስሶን

ለኵሎን ኃጣውእ! ከሁሉ አስቀድሞ በሙሉ ልባችሁ እርስ በርሳችሁ ተፋቀሩ፣ መፋቀር ሁሉንም

ዓይነተ ኃጢአት ይሸፍናልና ይደመስሳልምና (፩ ጴጥ.፬-፰)

ሁላችንም እንደምናውቀው የቅዱስ ወንጌል አስተምህሮ መሠረትና ጣርያ ወለልና ግድግዳ በፍቅርና በፍቅር ብቻ የተገነባ ነው፡ ፍቅር እግዚአብሔር ዓለምን ያዳነበት መድኃኒት ነው፣ ፍቅር የጥላቻና የመለያየት ግንብን ንዶ ይቅርታንና አንድነትን የሚገነባ ጠንካራ ዓለት ነው፣ ፍቅር መጽናናትንና ደስታን የሚያፈራ ጣፋጭ ተክል ነው፤ በፍቅር ለፍቅር የሚደረግ ሁሉ ፍሥሐን እንጂ ጸጸትን አያስከትልም

በመሆኑም በሰብአዊ ድክመት ምክንያት ሰዎች ፍቅርን ሙሉ በሙሉ በሚፈለገው ደረጃ ባንጠብቀውም በዓለማዊም ሆነ በመፈንሳዊ ሕይወት ከፍቅር የበለጠ ጠቃሚ ነገር የለም ፍቅር የማይሻርና ለዘላለሙ ጸንቶ የሚኖር እንደሆነ በቅዱስ መጽሐፍ ተመዘግቦአል፤ ምክንያቱም ፍቅር ከሞት በኋላም ቢሆን በእግዚአብሔር መንግሥት ይቀጥላልና ነው ዛሬ የሚጀመረው የድንግል ማርያም ጾመ ፍልሰታም በፍቅር ለፍቅር የተፈጸመ ነው፣ ይኸውም ቅዱሳን

ሐዋርያት የድንግል ማርያምን የማረፊያ ቦታ ለማየት ሲሉ የጾሙት ጾም ነው! ቅዱሳን ሐዋርያት የገለፁት ፍቅረ ድንግል ማርያምን ብቻ ሳይሆን ያረፈችበትንም ቦታ ጭምር ያመለከተ ነበረ፤ ይህ ሊሆን የቻለው ከልብ የሆነ እውነተኛ ፍቅር በሐዋርያት ዘንድ ስለነበረ ነው፡፡ እኛም ዛሬ የምንጾመው ይህንን የማርያም ጾም እንደ አበው ሐዋርያት ፍቅረ ድንግል ማርያም በልባችን ውስጥ ተተክሎ ስላለ ነው፤ እግዚአብሔር በፍቅርና በሃይማኖት የሚቀርብለትን ሁሉ ይቀበላልና የሐዋርያትን ጾምና ጸሎት ተቀበሎ ጥያቄአቸውን መልሶአል።

ዛሬም ይህንን ጾም የምንጾመው እግዚአብሔር ጾማችንን ተቀብሎ የልባችንን መሻት ይፈጽምልናል ብለን

ነው፣ በፍቅርና በሃይማኖት አስክ ጾምን ደግሞ እግዚአብሔር ይቀበለናል፤

የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት !

እንደ እግዚአብሔር ቃልም እንደ አባቶቻችን ትውፊትም የጾመ ፍልሰታ ጾም ሲጾም የበደለ ይቅርታ ጠይቆ፣ ተገቢውንም ካሣ ከፍሎ፣ ቂም በቀሉን አሰርዞ፣ ፍቅርን መሥርቶ ነበረ የተበደለም በበኩሉ ዕርቅን አውርዶ፣ ይቅርታን ሰጥቶ የእእምሮ ማለስለሻና ማስረሻ የሆነውን ካሣውን ተቀብሎ ተሙንና በቀሉን ከአእምሮው አውጥቶና አጽድቶ፤ ለእግዚአብሔር ስል ከልቤ ይቅር ብያለሁ ብሎ፣ ስመ እግዚአብሔርን ጠርቶ በፍቅር ይታረቃል

በዚህ ሁኔታ ፍጹምና ልባዊ ፍቅር ተይዞ ሲጾም ሁሉም ዓይነተ : ኃጢአት ሙሉ በሙሉ ይደመሰስለታል ፤ እግዚአብሔርም ይቅርታ ጠያቂውንም፣ ይቅርታ ሰጪውንም አሸማጋዩንም ይባርካል፤ ማኅበረ ሰቡም በዚህ ቅዱስና ሃይማኖታዊ ባህልና ትውፊት ተጠብቆ ለብዙ ዘመናት አንድነቱንና ሃይማኖቱን ወንድማማችነቱንና ነጻነቱን አስጠብቆ እስከ ዛሬ ደርሶአል | ይህ ለሀገራችን ታላቅ የሆነ የእግዚአብሔር በረከት ነበረ፣ ይህ እውነተኛ በረከት በአሁኑ ጊዜ ቸል በመባሉ ፈተናችን በዝቶአል፤ እንደ እውነቱ ከሆነ ሰው በኃጢአት ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ ጥልና መገዳደል በየትኛውም ጊዜ፤ በየትኛውም ሀገር በየትኛውም ማኅበረ ሰብ ይከሠታል፤ ዛሬም በሀገራችን በተፈጠረው አለመግባባት


ከባድ ችግር ተፈጥሮአል የሚያስገርመው ነገር ቢኖር እንዴት እንደባህላችንና እምነታችን በቀላሉ በዕርቅና በይቅርታ ማስተካከል አቃተን የሚለው ነው፡ የዘመናችን ልዩ ነገር ይህ ነው ለዚህም ብዙ የተለያየ ምክንያት ሊኖረው ይችላል፣ በሃይማኖት ዓይን ሲታይ ግን ለእግዚአብሔር ቃል የምንሰጠው ክብር በእጅጉ ስለተቀነሰ ነው የሚል ሆኖ ይገኛል፣ ይህ ዝንባሌ አሁን ላለውም ሆነ ለሚመጣው ትውልድ አደገኛ ስለሆነ የኦርቶዶክስ ሕዝበ ክርስቲያንም ሆነ ሌሎቹ ኢትዮጵያውያን ሁሉ ይህንን በጥልቀት ሊያጤኑትና ሊያርሙት ይገባል።

የተወደዳችሁ የመንፈስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናንት | ሽማግሌ የሀገር በረከት ነው፤ አስታራቂ ሽማግሌ የችግር ሐኪምና ፈዋሽ ነው፣ የፍቅርና የተግባቦት መሐንዲስም ነው፤ በእግዚአብሔርም የሚያስታርቁ የእግዚአብሔር ልጆች ናቸው” ተብሎ ውዳሴ ተችሮአቸዋል፣ እነዚህን ሽማግሌዎች ተጠቅመን ችግሮቻችንን መፍታት ጊዜው የሚጠይቀው አስገዳጅ ጉዳይ ሆኖአል፤ ሁሉም ታየ፤ ሁሉም ተሞከረ፣ ዘላቂ መፍትሔ ሲያመጣ ግን አልታየም፤ እንዲያውም ችግሩ ወደ ሃይማኖት ተዛምቶ ቤተ ክርስቲያንም የገፈቱ ቀማሽ ለመሆን ተገዳለች፡፡

በተጨባጭ እንደሚታውቀው ሕዝብንና ሃይማኖትን ነጣጥሎ ሰላምን ማረጋገጥ ከቶውኑ ሊታሰብ

አይችልም ምክንያቱም ሕዝብ የሃይማኖቱ ቤተሰብ ነው፤ ሃይማኖቱም በሕዝቡ መንፈስ ውስጥ ነግሦ

የሚኖር መለኮታዊ ኃይል ነውና፣ ከዚህ አንጻር “ወልድ ሲነካ አብ ይነካ" እንደሚባለው ሕዝቡ ሲነካ

ሃይማኖቱ ይነካል፣ ሃይማኖቱ ሲነካ ደግሞ ሕዝቡ ይነካል፤

በመሆኑም በተካሄደው ግጭት ብዙ ነገሮች መመሳቀላቸው የማይካድ ቢሆንም ችግሩ በዕርቅና በካሣ

በይቅርታና በመተው ካልተዘጋ ለማንም ስለማይበጅ ከባድ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች ለዕርቅ ዝግጁ እንዲሆነ፣ የበደሉም እንዲክሱ የሀገር ሽማግሌዎችም የማስታረቅ ስራን በሐቅ በገለልተኝነትና ዕንባን በሚያደርቅ ስልት እንዲሸመግሉ መንግሥትም የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ በዚህ አጋጣሚ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡ የገጠመንን ፈተና ሁሉ ሊያቀልልንና ሊያስወግድልን የሚችል እግዚአብሔር ስለሆነ፤ በዚህ የጾመ ማርያም ወቅት ምእመናን በተመሥጦና በንሥሐ ሕይወት ለእግዚአብሔር በመንበርከክ ስለ ሰላምና ፍቅር እንዲማፀኑ፣ ካላቸውም በረከት ለተራቡትና ለተፈናቀሉት እንዲለግሱ ሁሉም ወገኖች በሆነው

በመጨረሻም

ነገር ይብቃን ብለው ወደ ሰላማዊ አማራጭ እንዲቀርቡ በእግዚአብሔር ስም አባታዊ መልእክታችንን

እናስተላልፋለን፡፡

መልካም የጾመ ማርያም ሱባዔ ያድርግልን እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ነሐሴ 1 ቀን 2015 ዓ.ም.
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
+++ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" +++

ያኔ የገዳሙ መጋቢ የነበሩት አባ ተጠምቀ በጭንቀት ተውጠዋል። ከአቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ እግር ስር ወድቀው "ግድ የልዎትም አባ የዛሬው ጉዞ ይቆይዎ። እኔ ጥሩ ሕልም አላየሁም። እባክዎ እግርዎን ከዚህ ቤት አያንሡ፤ እንደው እባክዎ" እያሉ ይለምኗቸዋል። አቡነ ጎርጎርዮስ ግን ወደ መቂ ጊዮርጊስ ለአገልግሎት ለመሄድ ቆርጠው ተነሥተው ነበርና ሳልሄድ አላድርም ብለው እምቢ አሉ። በእርግጥ በዚያች የጉዞ ቀን ምን ሊሆኑ እንደሚችሉ ቀድመው ሳይረዱት ቀርተው አይመስልም። ምክንያቱም "ዛሬ ጥሩ ሕልም አላየሁምና አይሂዱ" ላሏቸው አባ ተጠምቀ " እኔስ ብሆን አንዳች ምልክት ያላየሁ ይመስልሃል። ዛሬ ጠዋት ሱሬን ስታጠቅ ሰባት ጊዜ መልሶ ሲፈታብኝ ነበር" ሲሉ መልሰውላቸዋል። ይሁን እንጂ በመቂ የሚገኝ እጅግ ሕመም የጸናበት አንድ የሚያውቁት ክርስቲያን ስለ ነበር ከራሳቸው ሕይወት ይልቅ ለዚያ ሰው ነፍስ ዋጋ ሰጥተው "ኸረ ሳላቆርበው እንዳይሞትብኝ" እያሉ አባ ጎርጎርዮስ ወደ መኪናው ፈጥነው ወጡ። ነገር ግን ከዚያ መኪና በሕይወት አልወረዱም። ከአዲስ አበባ ሕዝብ ጭኖ ከመጣ ተሽከርካሪ ጋር እርሳቸው ያሉበት መኪና ተጋጭቶ እሑድ ኃምሌ 22 ቀን ጠዋት አንድ ሰዓት ገደማ እኛ ደግ እና ባለ ብዙ ራእይ አባት አረፉ።

ብፁዕነታቸው ከማረፋቸው ከ15 ቀናት በፊት በአላጌ ሕፃናት አምባ የልጆች ማሳደጊያ ተገኝተው በዚያ ቦታ ለሚሠራ ቤተ ክርስቲያን መሠረት ካኖሩ በኋላ "ሰው የሚፈልገውን ከሠራ የሚጠብቀው ሞቱን ነው" ብለው ተናግረው ነበር። በውስጣቸውም የነበረው የአገልግሎት እሳት ገና እየተቀጣጠለ ቢሆንም በዚህች ምድር የሚቀራቸው የእንግድነት ዘመን ግን ጥቂት መሆኑን ስለተረዱ በዚያ ለነበሩት መንፈሳዊ ልጆቻቸው እየደጋገሙ "ልጆቼ ከመሸ ተገናኘን" ይሏቸው ነበር። ከዚህች ክፋት ከነገሠባት ዓለም ጠልቀው ፈጣሪያቸው ካለበት መንፈሳዊ አገር የሚወጡበት ጊዜ መቃረቡን ቀድመው የተረዱ አባት ነበሩ።

አቡነ ጎርጎርዮስ ከዘመናቸው ቀድመው የኖሩ፣ ትውልዱ ሃይማኖቱን ያቆዩለትን አባቶች እንዲያውቅና የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ እምነቱንም ታሪክ ከመሠረቱ ተረድቶ ቤተ ክርስቲያኑን እንዲያፈቅር በቃልም በመጽሐፍም የተጉ አባት ናቸው። ቅዱስ አባታችን የነበሩበትን ዘመን አልፎ በሚሄደው ተራማጅ አሳቢነታቸውና ለቤተ ክርስቲያን ሁለንተናዊ ዕድገት ያሳዩት በነበረው ትጋት አሁን ላይ ላሉትና ወደ ፊትም ለሚነሡ በእውነት ለሚደክሙ ቅን አገልጋዮች ሁሉ ትልቅ አርአያ ይሆናሉ።

የአገልግሎት ድካማቸው በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን። እኛንም የአባቶቻችን ልጆች ያድርገን!!!

(*የያኔው አባ ተጠምቀ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ሣልሳይ የምሥራቅ ሸዋ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ናቸው።)

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
ሐምሌ 22፣ 2014 ዓ.ም.
ዝዋይ (ብፁዕነታቸው ብዙ ሥራ በሠሩበት ክፍለ አገር ሆኜ)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/23 14:38:12
Back to Top
HTML Embed Code: