Telegram Web Link
_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፪_
#ግጽው
ትእዛዝ ፲፫ ሕግና ሥርዓትን የማያውቅ ሰው በምእመናን ላይ አይሾም። በምእመናን ላይ ሊሾም የሚገባው በጠባዩ ቸር፣ ታጋሽ፣ በጉዞው ሁሉ ጥሩና ትሑት ይሁን። ይህን ካላደረገ ይሻር። ቃሉንና ትእዛዙንም አይቀበሉት። በአሠራሩ ታማኝ አይደለምና።

ትእዛዝ ፲፬:- ሐሰተኛን እና ሐሜተኛን ሰው ከሹመት ይከልክሉት።

ትእዛዝ ፲፭:- በኮከብ ቆጠራ የሚታመንና በጥንቆላ የሚያምን ሁሉ ከሹመት ይወገድ። ክርስቲያኖችን እግዚአብሔርን ከማያውቁት ጋር የሚያስተካክል ከክህነት ሥልጣን ይሻር።

ትእዛዝ ፲፯:- በዝሙትና በስስት የሚታወቅ እንዲሁም የዚህን ዓለም ጥቅም የሚፈልግ ቄስም ሆነ ዲያቆን ከሹመቱ ይሻር።

ትእዛዝ ፳:- የዚህን ዓለም ሥራ የሚሠራን ሰው በእግዚአብሔር ቤተክርስቲያን ላይ እንዲያዝዝ ሹም አያድርጉት። ጸሎት የያዘ ቄስም ሆነ ዲያቆን ጸሎቱን አቋርጦ ወደሌላ ነገር አይሂድ። እንደዚህ የሚያደርግ ከሆነ ወደቀድሞ ቦታው መመለስ አይሆንለትም (አይገባውም)።

ትእዛዝ ፳፩:- ለቅዱሳን ሰማዕታት በሞቱበት ቀን መታሰቢያ ያድርጉላቸው።

ትእዛዝ ፳፩:- መዝሙረ ዳዊትን ቀንም ሌሊትም ይጸልዩት። መዝሙረ ዳዊት ተአምኖ ኃጣውእ፣ ጸሎት፣ ምስጋና አለበትና። ችግር፣ ሐዘንና፣ መከራ በአጋጠማቸው ጊዜ ከጥፋት ያመልጡ ዘንድ ይጸልዩ።

ትእዛዝ ፳፫:- በቤተመቅደስ ለማገልገል ከሕዝብ የተመረጡ ካህናት ሰባት ይሁኑ።

ትእዛዝ ፳፬:- ዐመፀኛውን ጻድቅ የሚያደርግ፣ ንጹሑን የሚያበሳጭ የተወገዘና ርጉም ይሁን። እንደዚህ የሚያደርገውን ከሹመቱ ይከልክሉት። ስለዐመፀኛነቱም ይመስክሩበት። ዐመፀኛ ከሆነ ጵጵስናው አያስፈራህ። (በእንተ ዐመፃሁ ወኢያፍርህከ ጵጵስናሁ)።

ትእዛዝ ፳፭:- በሰዎች ላይ የሚኩራራና በራሱ የሚታበይ ወደ ሹመት አይቅረብ። ከሌሎች ሰዎች እንደሚበልጥ እንደሚከብርና እንደሚሻል ራሱን የሚያይ፣ የእግዚአብሔርን ሕዝብ በንቀት ዓይን የሚመለከት በሹመት ላይ አይቀመጥ።

ትእዛዝ ፳፮:- በየአውራጃው ባሉ ቀሳውስት ላይ በመካከላቸው ሆኖ የሚያዛቸውና የሚገሥጻቸው ሊቀ ካህናት ይሹሙ።

ትእዛዝ ፳፯:- በጸሎት ጊዜ ንጉሥ በሰው ሁሉ ፊት ከምእመናን ጋር ይሁን። ለቁርባን ወደ መሠውያው ቦታ ይግባ። መቆሚያውም ከሊቃውንትና ከተሾሙ ካህናት ጋር በዚያ ይሁን።

ትእዛዝ ፴:- ቁርባንን በዕለቱ ያቀብሉት እንጂ ለነገ አያሳድሩ።

ሊቃነ ካህናቱ ኒቆዲሞስና ገማልኤል፣ ሐና፣ ቀያፋ፣ ሊቃነ ካህናት ሌሊት ወደክርስቶስ ይመጡ ነበር። በክርስቶስም ያምኑ ነበር። ነገር ግን አይሁድን ፈርተው ይህንን አልገለጹም። ከክርስቶስ ትንሣኤ በኋላ ሁላቸውም አምነዋል።

የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት እርስ በእርሳቸው ይተባበራሉ።

ሐዋርያት ከጠንቋዮች ጋር ይጋደሉ ነበር። ስለ ሃይማኖታቸው ችግር ባጋጠማቸው ጊዜ እኛም የፈጠረንን አስቆጥተነዋልና ይህች የደረሰችብን ችግር ታስታርቀናለች ይሉ ነበር። ከእነርሱ መካከል ብዙ ጊዜ ንብረቱ የተዘረፈበት አለ፣ ከገንዘቡ ከልጆቹና ከቤቱ የራቀም አለ፣ የሰቀሉትም አለ። እስኪሞቱ ድረስ በፈቃዳቸው ይታገሡ ነበር።

ምእመናን ለአማልክት የተሠዋንና በክት የሆነውን ከመብላት፣ ደምን ከመጠጣት፣ ለባዕድ አምላክም ከመሳል እንዲታቀቡ ያዝዟቸው ነበር።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፫
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
_የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፫____
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፩:- ኤጲስ ቆጶስ ሁለት ወይም ሦስት ኤጲስ ቆጶሳት በተገኙበት ይሾም። ቄስ ዲያቆንና የቀሩት ሹማምንት በአንድ ኤጲስ ቆጶስ ሥልጣን ብቻ ይሾሙ።

ትእዛዝ ፪:- ጌታችን ካዘዘው (ስንዴ፣ የወይን ፍሬ፣ መብራት፣ ዘይት፣ ንጹሕ ዕጣን) ውጭ ቁርባን ያሳረገ ይሻር።

ትእዛዝ ፫:- ካህን በአገልግሎት ምክንያት ሚስቱን አይፍታ። ከፈቱ ይለዩ። ካልመለሷት ግን ይሻሩ።

ትእዛዝ ፬:- ካህናት ቀንና ሌሊቱ እኩል ከመሆኑ በፊት ከአይሁድ ጋር ቅድስት ፋሲካ እንድትውል ካደረጉ ይሻሩ።

ትእዛዝ ፭:- ኤጲስ ቆጶስ፣ ቄስና ዲያቆን ከዚህ ዓለም ተግባር ውስጥ አይግቡ። ገብተው ከተገኙ ግን ይለዩ።

ትእዛዝ ፮:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ከካህናት አንዱ ምክንያቱን ሳይናገር በቅዳሴ ግን ቁርባን ባይቀበል የማይገባው ሆኖ ከተገኘ ይቅር ይበሉት። ምክንያቱን ካልተናገረ ግን ይባረር። በአሳረገው መሥዋዕት ላይም በንጽሕና እንዳላሳረገው ሆኖ ለሕዝብ እንቅፋት ሆኗልና።

ትእዛዝ ፯:- ወደ ቤተክርስቲያን የሚገባ አማኝ ሁሉ መጻሕፍትንም የሚሰማ ነገር ግን ጸሎት እስከሚያደርጉ ድረስ የማይቆም ቁርባንም የማይቀበል ከሆነ በላዩ ላይ አይጸልዩለት። ሊባረርም ይገባዋል። በቤተክርስቲያን ክርክርንና ብጥብጥን ፈጥሯልና።

ትእዛዝ ፰:- ከቤተክርስቲያን ከተባረረ ሰው ጋር አይጸልዩ።

ትእዛዝ ፲:- ካህን ከተባረረ ካህን ጋር ቢጸልይ እርሱም ይባረር።

ትእዛዝ ፲፩:- ኤጲስ ቆጶስ የሹመት ቦታውን ትቶ በሌላ ሀገረ ስብከት ሊሾም አይገባም።

ትእዛዝ ፲፪:- ያለ ኤጲስ ቆጶሱ ሥልጣን የሥራ ቦታውን ቢተውና ወደሌላ የሥራ ቦታ ቢሄድ እንዳያገለግል እኛ እናዛለን። በይበልጥም ኤጲስ ቆጶስ ወደቦታው እንዲመለስ ቢልክበትና ባይሰማው ከሹመቱ ይባረር። ባለበት ቦታ እንደ ሕዝባዊ ሆኖ ይቁረብ።

ትእዛዝ ፲፫:- ወደ ተውኔት ቤት የምትሔደውን ያገባ ክህነት ሊሾም አይገባውም።

ትእዛዝ ፲፬:- ዋስ የሚሆን ካህን ይሻር።

ትእዛዝ ፲፭:- በራሱ ፈቃድ ራሱን የሰለበ ክህነት አይሾም።

ትእዛዝ ፲፮:- በዝሙት፣ በሐሰት መማል፣ በመስረቅ የሚገኝ ካህን ይሻር።

ትእዛዝ ፲፯:- ክህነት ወደሚገቡበት ጊዜ አናጉንስጢስና መዘምራን ማግባት ቢፈልጉ ያግቡ። ከተሾሙ በኋላ ግብ ማግባት አይገባቸውም።

ትእዛዝ ፲፰:- ሰዎች ይፈሩት ዘንድ የሚደባደብ ካህን እንዲሻር እናዛለን።

ትእዛዝ ፲፱:- በታወቀ ኃጢአት ምክንያት በትክክል የተሻረ ኤጲስ ቆጶስም ቢሆን ቄስም ቢሆን ዲያቆንም ቢሆን ከተደፋፈረና ሥልጣን ባለው ጊዜ ይሠራውን የነበረውን መሥራት ከጀመረ ፈጽሞ ከቤተክርስቲያን ይራቅ።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፬ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
__የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፬__
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፳:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን መማለጃ በመስጠት የሹመት መዓርግ ቢይዝ ይሻር። የሾመውም ይሻር። ከክህነት ሥርዓትም እስከ መጨረሻው ይባረር።

ትእዛዝ ፳፩:- ኤጲስ ቆጶስ ቤተክርስቲያንን በዚህ ዓለም የአገዛዝ ሥርዓት ለመግዛት የሚፈልግን ሰው ከረዳ ይሻር።

ትእዛዝ ፳፪:- ቄስ ኤጲስ ቆጶስን ቢንቅ ይለይ።

ትእዛዝ ፳፫:- ኤጲስ ቆጶስ ያባረረውን ቄስ ወይም ዲያቆን ራሱ ካልፈቀደ በስተቀር ሌላ ኤጲስ ቆጶስ እንዲመለስ አያድርገው።

ትእዛዝ ፳፬:- ሊቀ ጳጳሳት የሁሉንም ሀገረ ስብከት ኤጲስ ቆጶሳት ያውቅ ዘንድ ይገባል።

ትእዛዝ ፳፭:- ኤጲስ ቆጶስ የሀገረ ስብከቱ ኤጲስ ቆጶስ ካልፈቀደለት የእርሱ ባልሆነ ሀገረ ስብከት ላይ ለመሾም አይደፋፈር። ተደፋፍሮ የተገኘ ካለ እርሱም የሾማቸውም ይሻሩ።

ትእዛዝ ፳፯:- የኤጲስ ቆጶሳት ጉባኤ በዓመት ሁለት ጊዜ ይደረግ። በቤተክርስቲያን ላይ ስለአለ ስሕተትና እንቅፋት ስለሚሆኑ ነገሮችም ይተርጕሙ። የመጀመሪያው ጉባኤ በበዓለ ኃምሳ መካከል ይሁን። ሁለተኛው ጉባኤ ጥቅምት 12 ይሁን።

ትእዛዝ ፳፰:- ኤጲስ ቆጶስ የእግዚአብሔርን ገንዘብ ለዘመዱ ልጆች መስጠት የለበትም።

ትእዛዝ ፳፱:- ከቀሳውስት ወይም ከዲያቆናት ማንም ኤጲስ ቆጶሱን ሳያማክር ምንም አያድርግ።

ትእዛዝ ፴፩ [የጦር ሠራዊት]:- የንጉሥ ሠራዊትም ከጠላት ጋር ጦርነት የሚያደርጉት በራሳቸው ምግብ አይደለም።

ትእዛዝ ፴፪:- ወደ ጭፈራ ቤት የሚሔድና የሚዞር ስካርም የሚያበዛ ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ይተው። አልተውም ካለ ግን ይባረር። ሕዝባውያንም ቢሆኑ እንደዚሁ ይሁኑ።

ትእዛዝ ፴፫:- ወደ ከኃድያን ጥምቀት ወይም ወደ ቁርባናቸው የሚሔድ ካህን ይሻር።

ትእዛዝ ፴፬:- ሥጋ መብላት፣ ጋብቻ፣ ወይን መጠጣት እንደ ርኩስ የሚቆጥር ቢኖር ይህን ሐሳቡን ይተው ዘንድ ይንገሩት። ካልተወ ግን ይሻር። ሕዝባዊ ቢሆንም እንዲሁ ይደረግ።

ትእዛዝ ፴፭:- ከኃጢአት ንስሓ የሚገቡትን አልቀበልም የሚል ካህን ቢኖር ይሻር።

ትእዛዝ ፴፯:- ከካህናት መካከል በገበያ የሚበላ ወይም የሚጠጣ ቢገኝ ከካህናት አንድነት ይለይ። ከካህናት መካከል አንዱ ኤጲስ ቆጶስን ቢሳደብ ይሻር። በሕዝብ ላይ በተሾመ ሰው ላይ መጥፎ ቃል አትናገር ይላልና። ቄስን ዲያቆንን የሚሳደብም ይባረር።

ትእዛዝ ፴፰:- ካህናትን ወይም ሕዝብን የሚንቅና የእግዚአብሔርን መልእክት የማያስተምር ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ይባረር። በንቀቱ ቢቀጥልበት ይሻር።

ትእዛዝ ፴፱:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ከካህናት የተቸገረን አይቶ ቸል ቸል ካለ የሚፈልገውን ነገርም ባይሰጠው ይለይ። በዚሁ በቸልታው ከቀጠለም ወንድሙን እንደገደለ ይቆጠራልና ይሻር።

ትእዛዝ ፵:- ከኃድያን በውሸት የጻፉትን መጽሐፍ ያሳየ ሕዝብንና ካህናትንም ለማጥመድ እንደ ቅዱሳት መጻሕፍት ቆጥሮ ወደ ቤተክርስቲያን ያስገባ ሰው ቢኖር ይሻር።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፭ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
__የሐዋርያት ሲኖዶስ ክፍል ፭__
#ትእዛዝ #ሲኖዶስ
ትእዛዝ ፵፪:- ከካህናት መካከል ከኃድያንን ከመፍራት የተነሣ ቢክድ የካደው የክርስቶስን ስም ከሆነ ይባረር። የካደው ክህነትን ከሆነ ይሻር። ንስሓ ከገባ ይቀበሉት እንደ ሕዝብ ሆኖም ይግባ።

ትእዛዝ ፵፫:- ከካህናት አንዱ ደም ያለው ወይም ያልታረደ ወይም አውሬ የነከሰው ወይም በክት ከበላ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይለይ።

ትእዛዝ ፵፬:- ከቀዳም ስዑር በስተቀር በሰንበትና በዕለተ እሑድ ከካህናት መካከል አንዱ ሲጾም ቢገኝ ይሻር።

ትእዛዝ ፵፭:- ከካህናት መካከል በከኃድያን ቦታ ይጸልይ ዘንድ ቢገባ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነም ይባረር።

ትእዛዝ ፵፮:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ሁለት ጊዜ ተሹሞ ቢገኝ እርሱም የሾመውም ይሻር።

ትእዛዝ ፵፯:- ደዌ ሕመም ካልከለከለው በስተቀር ጾመ አርብዓን፣ ረቡዕና ዓርብን የማይጾም ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ወይም አናጉንስጢስ ወይም መዘምር ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ደግሞ ይባረር።

ትእዛዝ ፵፰:- ከካህናት አንዱ ከአይሁድ ጋር ቢጾም ወይም ፋሲካን ከእነርሱ ጋር ቢያደርግ ወይም ለበዓላቸው ስጦታ ቂጣ ቢቀበል ወይም ይህን የመሰለ ቢያደርግ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ይባረር። ሕዝባዊ ሆኖ ዘይትና መብራት ወደ አይሁድ ምኵራብና ወደ አሕዛብ ምኵራብ ቢወስድ ከምእመንነቱ ይሻር።

ትእዛዝ ፵፱:- የተሾመ ካህን ከቤተክርስቲያን ሠም ወይም ቅባት ቢሰርቅ ይባረር። የሰረቀውንም አምስት እጥፍ አድርጎ ይክፈል።

ትእዛዝ ፶፩:- በኤጲስ ቆጶስ ላይ የከኃድያንን ምስክርነትና የአንድን ኤጲስ ቆጶስ ምስክርነት አይስሙበት። ኤጲስ ቆጶስነትን ይዋረሱ ዘንድ ትክክል አይደለም። ኤጲስ ቆጶስ የቤተክርስቲያንን ሀብት ለፈለገው ሰው አይስጥ። አንድ ዓይኑ የታወረ ወይም አንድ እግሩ አንካሳ የሆነ ሰው ኤጲስ ቆጶስነት የሚገባው ቢሆን ይሾም። ነውረ ነፍስ እንጂ ነውረ ሥጋ አያረክስምና። መስማት የተሳነውና ዐይነ ስውር ኤጲስ ቆጶስ ሆኖ አይሾም።

ትእዛዝ ፶፪:- ጋኔን ያደረበት ካህን ሆኖ አይሾም። ከምእመናን ጋርም አብሮ አይጸልይ።ጌቶቹ እንዳያዝኑ ነጻ ያልወጣ ሰው ካህን ሆኖ ይሾም ዘንድ አናዝም።

ትእዛዝ ፶፫:- ኤጲስ ቆጶስ ወይም ቄስ ወይም ዲያቆን ዓለማዊ ሹመትንና ክህነትን ሁለቱን ለመሥራት ወታደር ሆኖ ማገልገል ቢፈልግ ይሻር። [መንግሥትነት] ንጉሥን ወይም መኮንንን የሚያቃልል ይበቀሉት። ካህን ከሆነ ይሻር። ሕዝባዊ ከሆነ ደግሞ ይባረር።

ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ክፍል ፮ ይቀጥላል
መ/ር በትረማርያም አበባው
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"ዲያብሎስ ልጅነታችንን እናቆሽሽ ዘንድ በእኛ ላይ የሚተናኰለው ተንኰል በጣም ተደጋጋሚና ኃይለኛ ነው፡፡ ስለዚህ ይህን መንቻካ የዲያብሎስን ደባ ድል እንነሣ ዘንድ ዘወትር ንቁዎችና ጠንቃቆች ልንኾን ይገባናል፡፡ እኛ ይህን ማድረግ ሳንችል ቀርተን እጅግ ጥቂት መግቢያ ቀዳዳ የምንተውለት ከኾነ ግን እርሱ ጥቂቷን ቀዳዳ ሰፊ በር ያደርጋታል፡፡ እንዲህ አድርጎም ኃይሉን ኹሉ ተጠቅሞ ወደ እኛ ይገባል፡፡

ስለዚህ ስለ ድኅነታችን የሚገደን ከኾነ እንደዚህ ጥቂትና ቀልድ በሚመስሉ ነገሮች እንኳን አንዘናጋ፤ እርሱ የሚንቀውና ጥቂት የሚለው ኃጢአት የለምና፡፡ እኛ ጥቃቅን የምንላቸውን ነገሮች መነሻ አድርጎ ልጅነታችንን የምናቆሽሽበትን ታላላቅ ኃጢአቶችን እንድንሠራ አድርጎ እጅግ ይተጋልና፡፡"

ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ("የአምር አቡክሙ ሰማያዊ ዘትፈቅዱ ዘእንበለ ትስአልዎ።" ማቴ. ፮፡፰)
መወድስ
●ከዊነ ምንትኑ ይኄይስ እም ከዊነ ሰብእ ከዊነ ዝእብኑ ወሚመ ከዊነ የዋህ በግዕ፥
●ባሕቱ ይኄይስ ከዊነ ተኵላ ሐቅል ኅቡእ፥
●በትምይንቱ ወበጽልሑቱ እም ተኵላ ገዳም እስመ ብእሰ ሰብእ፥
●ዘበኍልቈ ጸጕሩ ኀጣውኢሁ ወእምዘ የሐነክስ ሰብእ ተኵላ ገዳማት ይረትዕ፥
●ዝሰ ከመ ሀሎ ይዘንጋዕ፥
●ሶበ እንዘ ይብለነ ሐዋርያ መብልዕ ኢይበቍዕ፥ (፩ ቆሮ. ፰፡፰)
●በምልኡ ዓለም ለመብልዕ፥
●ላዕለ የዐርግ ወላዕለ ይወፅእ።

👉እም ኀበ መምህር ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ
👉፳፻፬ ዓ.ም
👉ባሕር ዳር ሽንብጥ ፈለገ ፀሓይ ቅዱስ ሚካኤል ገዳም

የዩቲዩብ ድሕረ ገጽ👇
https://www.youtube.com/@yaredzera-buruktube8843

የፌስቡክ ገጽ👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=100063724038968&mibextid=ZbWKwL

የፌስቡክ ገጽ👇
https://www.facebook.com/Yared.ZeraBuruk?mibextid=ZbWKwL

👉የቴሌግራም ቻናል
https://www.tg-me.com/yaredzer

👉ለሌላውም እንዲደርስ share ያድርጉት!!!
Forwarded from የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ("የአምር አቡክሙ ሰማያዊ ዘትፈቅዱ ዘእንበለ ትስአልዎ።" ማቴ. ፮፡፰)
"...ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና..." ሮሜ. 3:28

#ሰው_በእምነት_ብቻ_ይጸድቃልን?
በመ/ር ያሬድ ዘርአ-ቡሩክ = አዲስ አበባ

👉በ16ኛው መቶ ክ/ዘ ለተፈበረኩት ፕሮቴስታንታውያን የተሰጠ የማያዳግም አጥጋቢ መልስ ● Share ይደረግ!

ክፍል ፩. እምነት

ሰው በእምነት ብቻ በጭራሽ ሊድንም ሆነ ሊጸድቅ አይችልም። አንድ ሰው መዳንን ወርሶ ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በትንሹ የሚከተሉት ሰባት መሥፈርቶች ያስፈልጉታል፦ ማመን፣ መጠመቅ፣ መቍረብ፣ መመስከር፣ ሕግን መጠበቅ፣ ሥራን መሥራት እና መጋደል። እነዚህም ሥርዐታት ሳይሆኑ በቀጥታ ከመዳን ጋር የተያያዙ ለመዳን መሟላት ያለባቸው ቀደምት መሣፍርት ናቸው።

እምነት፦ መስማትን፣ ማዳመጥንና ማየትን ተከትሎ የሚመጣ ነው። በቅዱስ መጽሐፍም "እምነት ከመስማት ነው፥ መስማትም በእግዚአብሔር ቃል ነው።" (ሮሜ. 10:17) ተብሏል። ማንኛውም ሰው ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ለመግባት በሥላሴ አንድነትና ሦስትነት፣ በእግዚአብሔር ወልድ ነገረ ሥጋዌ፣ በቅዱሳን መላእክትና ሰዎች ምልጃና ጸሎት ሊያምን ይገባል። በምሥጢረ ሥላሴም ማመን እንዲገባ "እኔ በአብ እንዳለሁ፥ አብም በእኔ እንዳለ እመኑኝ፤ ባይሆንስ ስለ ራሱ ስለ ሥራው እመኑኝ።" (ዮሐ. 14:11፤ 10:38፤ 14:1) ተብሏል። ቅዱስ ጳውሎስም በዕብራውያን መልእክቱ ላይ 3:12 "ወንድሞች ሆይ፥ ምናልባት ሕያው እግዚአብሔርን የሚያስክዳችሁ ክፉና የማያምን ልብ ከእናንተ በአንዳችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ።" በማለት በሕያው እግዚአብሔር (ሥላሴ) የማያምን ልብ እንዳይኖር ያስጠነቅቃል።

ከሦስቱ አካላት አንዱ አካል በሆነው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን በተመለከተም፦ "በልጁ የሚያምን የዘላለም ሕይወት አለው፤ በልጁ የማያምን ግን የእግዚአብሔር ቍጣ በእርሱ ላይ ይኖራል እንጂ ሕይወትን አያይም።" (ዮሐ. 3: 36) ተብሏል። ዳግመኛም "በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን በነፍሱ ምስክር አለው፤ በእግዚአብሔር የማያምን እግዚአብሔር ስለ ልጁ የመሰከረውን ምስክር ስላላመነ ሐሰተኛ አድርጎታል።" (1ኛ ዮሐ. 5: 10) ተብሎ ተተንትኖ ተቀምጧል።

አንድ የወህኒ ቤት ጠባቂም መዳን የሚቻልበትን ፈልጎ በጠየቀ ጊዜ ቅዱስ ጳውሎስና ቅዱስ ሲላስ "በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፥ አንተና ቤተ ሰዎችህ ትድናላችሁ።" በማለት መልሰውለታል። ሐዋ. 16:3። በቅዱሳንም ተራዳኢነት መታመን ለመዳን ምክንያት እንደ ሆነ "በአምላካችሁ በእግዚአብሔር እመኑ፥ ትጸኑማላችሁ፤ #በነቢያቱም እመኑ፥ ነገሩም ይሰላላችኋል።" (2ኛ ዜና. 20:20) ተብሎ ተጽፏል።

እምነት፦ ሕግ ያለው፥ በሕግ የሚጓዙበት ቀጥተኛ መሥመር ነው። ቅዱስ ጳውሎስም "ትምክሕት እንግዲህ ወዴት ነው? እርሱ ቀርቶአል። በየትኛው ሕግ ነው? በሥራ ሕግ ነውን? አይደለም፥ #በእምነት_ሕግ ነው እንጂ።" (ሮሜ. 3:27) በማለት እምነት በሕግ የሚመላሱበት እንጂ በጋጠወጥነት ሥርዐት አልባና ስድ ተሁኖ የሚከተሉት እንዳልሆነ እንቅጩን ቃል ተናግሯል።

እምነት በሥራ ካልታገዘ እምነት ብቻውን በድን ነው። ቅዱስ ያዕቆብ 2:17 "ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።" ሲል ጽፏል። እምነትና ሥራ ድርና ማግ ሆነው ሳይነጣጠሉ በሰዎች ሕይወት ላይ መሰፋት አለባቸው። ቅዱስ ያዕቆብም በዐጭር አገላለጽ "ከነፍስ የተለየ ሥጋ የሞተ እንደ ሆነ እንዲሁ ደግሞ ከሥራ የተለየ እምነት የሞተ ነው።" ያዕ. 2:26 በማለት በእምነት ብቻ እንጸድቃለን ለሚሉ ከንቱዎች የማያዳግም ልብ አርስ መልስ ሰጥቷል።

በእምነት ብቻ መዳን የሚገኝ ቢሆን ኖሮም ከሉተራውያን እጅግ በተሻለ ደረጃ በእግዚአብሔር ፍጹም እምነት ያላቸው አጋንንት ቀድመው መዳንን ይወርሱ ነበር። ነገር ግን በእምነት ብቻ እንዲሁ በቀላሉ መዳንን ማግኘት የሚቻል አይደለም። የመናፍቃን መዶሻ ቅዱስ ያዕቆብ "እግዚአብሔር አንድ እንደ ሆነ አንተ ታምናለህ፤ መልካም ታደርጋለህ፤ #አጋንንት ደግሞ #ያምናሉ ይንቀጠቀጡማል።" (ያዕ. 2:19) በማለት የአጋንንትን እምነት ገልጦ ነገር መጽደቅ እንደማይቻላቸው ጽፏል።

ቅዱስ ጳውሎስም በሮሜ መልእክቱ 3:28 "...ሰው ያለ ሕግ ሥራ በእምነት እንዲጸድቅ እንቆጥራለንና..." ብሎ መናገሩ በሕግ ሥራ ብቻ እንጸድቃለን ይሉ ለነበሩ፥ በሮም ተሰደው ይኖሩ ለነበሩ አይሁድ በሕግ ሥራ ብቻ መጽደቅ እንደማይቻል አስረግጦ ሲያስገነዝባቸው ነው።

የሕግ ሥራ ብሎ የገለጠውም ግዝረትን ነው። ገና ከመጀመሪያው ሲጀምርም "እንግዲህ የአይሁዳዊ ብልጫው ምንድር ነው? ወይስ የመገረዝ ጥቅሙ ምንድር ነው? በሁሉ ነገር ብዙ ነው።" ይልና "እግዚአብሔር የአይሁድ ብቻ አምላክ ነውን? የአሕዛብስ ደግሞ አምላክ አይደለምን? አዎን፥ የተገረዘን ስለ እምነት ያልተገረዘንም በእምነት የሚያጸድቅ አምላክ አንድ ስለ ሆነ የአሕዛብ ደግሞ አምላክ ነው።" ሮሜ. 3:1፣ 29-30 በማለት ያብራራል።

በመቀጠልም "እንግዲህ ሕግን በእምነት እንሽራለንን? አይደለም፤ ሕግን እናጸናለን እንጂ።" ሮሜ. 3:31 በማለት ማንኛውም አማኝ ሕግን እንዲከተል በአጽንዖት ያስገነዝባል።

አስተዋይ ልቡና ያለው ሰው በሮሜ. መልእክቱ 4:1-15 ላይ ቅዱስ ጳውሎስ የጻፈውን፥ የሚከተለውን እንደ ፀሐይ የሚያበራ ግልጽ ዐሳብ በቀላሉ አንብቦ መረዳት ይችላል፦

<<እንግዲህ በሥጋ አባታችን የሆነ አብርሃም ምን አገኘ እንላለን? አብርሃም በሥራ ጸድቆ ቢሆን የሚመካበት አለውና፥ ነገር ግን በእግዚአብሔር ዘንድ አይደለም። መጽሐፍስ ምን አለ? አብርሃምም እግዚአብሔርን አመነ ጽድቅም ሆኖ ተቈጠረለት። ለሚሠራ ደመወዝ እንደ ዕዳ ነው እንጂ እንደ ጸጋ አይቈጠርለትም፤ ነገር ግን ለማይሠራ፥ ኃጢአተኛውንም በሚያጸድቅ ለሚያምን ሰው እምነቱ ጽድቅ ሆኖ ይቈጠርለታል። እንደዚህ ዳዊት ደግሞ እግዚአብሔር ያለ ሥራ ጽድቅን ስለሚቈጥርለት ስለ ሰው ብፅዕና ይናገራል እንዲህ ሲል። ዐመፃቸው የተሰረየላቸው ኀጢአታቸውም የተከደነላቸው ብፁዓን ናቸው፤ ጌታ ኀጢአቱን የማይቈጥርበት ሰው ብፁዕ ነው።

እንግዲህ ይህ ብፅዕና ስለ መገረዝ ተነገረ? ወይስ ደግሞ ስለ አለመገረዝ? እምነቱ ለአብርሃም ጽድቅ ሆኖ ተቈጠረለት እንላለንና። እንዴት ተቈጠረለት? ተገርዞ ሳለ ነውን? ወይስ ሳይገረዝ? ተገርዞስ አይደለም፥ ሳይገረዝ ነበር እንጂ። ሳይገረዝም በነበረው እምነት ያገኘው የጽድቅ ማኅተም የሆነ የመገረዝን ምልክት ተቀበለ፤ ይህም እነርሱ ደግሞ ጻድቃን ሆነው ይቆጠሩ ዘንድ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ አባት እንዲሆን ነው፥ ለተገረዙትም አባት እንዲሆን ነው፤ ይኸውም ለተገረዙት ብቻ አይደለም ነገር ግን አባታችን አብርሃም ሳይገረዝ የነበረውን የእምነቱን ፍለጋ ደግሞ ለሚከተሉ ነው። የዓለምም ወራሽ እንዲሆን ለአብርሃምና ለዘሩ የተሰጠው የተስፋ ቃል በእምነት ጽድቅ ነው እንጂ በሕግ አይደለም። ከሕግ የሆኑትስ ወራሾች ከሆኑ እምነት ከንቱ ሆኖአል የተስፋውም ቃል ተሽሮአል።>>
‹‹ተስፋ ለሕይወታችን አስፈላጊ ነገር ነው:: ሰው ተስፋ ካጣ ሁሉንም ነገር ያጣል። ተስፋ ያጣ ሰው ደግሞ በጭንቀት፣ በስቃይ፣ ግራ በመጋባት፣ ዓላማ በሌለው ጥበቃና በዛለ መንፈስ ውስጥ የወደቀ ስለሚሆን ሰይጣን በመዳፎቹ ውስጥ አስገብቶ መጫወቻ ያደርገዋል፡፡ ይህ በመሆኑም ወደ ተስፋ መቁረጥ የሚመራው ሰይጣን ነው እንላለን፡፡ ይሁን እንጂ የእግዚአብሔር ልጆች ምን ጊዜም ተስፋ ስላላቸው በማንኛውም ሰዓት የሚኖሩት በተስፋ ነው፡፡

በማንኛውም ሰዓት የሚኖሩት በተስፋ ነው፡፡ በመከራ ጊዜ ተስፋ አላቸው፤ ነገሮች ሲወሳሰቡ ተስፋ አላቸው፤ ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔር የዘገየ በሚመስልበት ጊዜና ነገሮች ሁሉ ጨለማ በሚመስሉበት ጊዜም ተስፋ ይኖራቸዋል፡፡››

(ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ተወዳጆች ሆይ! እስኪ ልጠይቃችሁ፦ አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የኾነ ቦታ ላይ ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ? ወደዚያ ቦታ ለመሔድ አስፈላጊ ነው የምትሉትን ኹሉ አታደርጉምን? ቀኑን ሙሉም ቢኾን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁምን?

እግዚአብሔር እሰጣችኋለሁ ያላችሁ ግን አንዲት ወይም ዐሥር ወይም ሃያ ወይም መቶ ወይም አንድ ሺሕ ቅንጣት ወርቅ አይደለም፤ ወይም ምድርን ኹሉ አይደለም፡፡ ከዚህ ኹሉ የምትበልጠው መንግሥተ ሰማያት እንጂ፡፡ ከዚህ የሚበልጥ ስጦታ ታዲያ ምን አለ? ይህንን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ ሰዎችስ እንደምን ያሉ ምስኪናን ናቸው?

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

#ይቀላቀሉ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
አንድን በክፉ ምግባር የተያዘን ሰው ወደ መልካም ነገር ልትመልሰው ብትወድድ መጀመርያ ሰላሙን እንዲያገኝ አድርገው፡፡ በፍቅር ቃል ከፍ ከፍ አድርገው። እንዲህ ያለን ሰው ከክፉ ስራው እንዲመለስ ለማድረግ ከዚህ የተሻለ ዘዴ የለምና። ሰው በተግባር የሚያደርገው ፍቅር ሰዎችን የመለወጥ ፍጹም ሀይል አለውና።

ቀጥለህ በፍቅር አንድ ሁለት ቃልን ንገረው፣ በቁጣ አትንገረው። በእርሱ ላይ አንዳች የጠላትነት ስሜት አታሳይ። ፍቅር ሰዎችን ለመለወጥ መንገዱን እርሱ ያውቅበታል። ብቻ እንተ እድሉን ስጠው። የፍቅር ሰውም ሁን።

(መክስምያኖስ ባህታዊ ዘሶርያ - የበረሃ ፈርጦች)

"ከእውነት የራቀ ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር መንፈስ የራቀ ነው፡ ከእውነት የተለየም ማንኛውም ሰው ከእግዚአብሔር የተለየ ነው።"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

"የሥልጣን ፍቅርን ያኽል ቤተ ክርስቲያንን የሚከፍላት ጽኑ ደዌ  የለም።"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)

“እኔ ክርስቲያን ነኝ፡፡ ለሚጠይቁት እንደዚህ ብሎ የሚመልስ ሰው በአንድ ጊዜ በኹሉም ነገሮቹ ላይ ማወጁ ነው፡፡ ሀገሩ የት እንደ ኾነ፣ ሥራው ምን እንደ ኾነ፣ ቤተሰቡ እነማን እንደ ኾኑ መመስከሩ ነው፡፡ ክርስቲያን የሰማያዊት ኢየሩሳሌም ነዋሪ እንጂ በምድር ላይ ካሉት ከተሞች የአንዲቱም አይደለምና፡፡
                •➢ ሼር // SHARE

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
👉 ሴት በወር አበባዋ ጊዜ መጸለይ ትችላለች?
👉​​ ግለ አውናን / ሴጋ /ማስተርቤሽን/ የፈጸመ ሰው ተክሊል ማግባት ይችላልን?
👉 በሱባኤ ወቅት ህልመ ሌሊት (ዝንየት) ቢመታን ምን እናደርጋለን?
👉 ሕልመ ሌሊት በራሱ ኃጢአት ነውን?
👉 ሕልመ ሌሊት በምን ይከሰታል?
👉 ከዝሙት አጋንንት እና ከዝንየት በተጨማሪ በሕልመ ሌሊት የሚፈትነን አጋንንት የትኛው ነው?
👉 የሕልመ ሌሊት መፍትሔ ምንድን ነው?

ለእነዚህ ሁሉ መልስ ለማግኘት ይቀላቀሉ
Channel link
@tewahdo_haymanotea
++++ ያልተተከሉ ዛፎች +++


አንድ ሩስያዊ የቴዎሎጂ መምህር የተናገሩትን አዝናኝ ወግ ሐበሻዊ ቀለም ሠጥቼ እንዲህ ልተርከው :-

ባልና ሚስት ከተጋቡ ጥቂት ዓመታት ቢያልፋቸውም ልጅ ግን አልወለዱም ነበር:: ወደ አንድ አባት ይሔዱና እባክዎን ልጅ እንዲሠጠን ይጸልዩልን ይሏቸዋል:: አባም ችግሩን ሰምተው የሚከተለውን ምክር ሠጡ

“እዚያ ተራራ ላይ ያለችው ገዳም ትታያችኁዋለች?" አሉአቸው
"አዎ አየናት" አሉ ባልና ሚስቱ
"ነገ በጠዋት እህል ሳትቀምሱ ሒዱና ገዳሙ ውስጥ የወይራ ዛፍ ተክላችሁ ልጅ ሥጠን ብላችሁ ስእለት ተሳሉ"

ባልና ሚስት በማግሥቱ ወደ ገዳሙ ሔደው የወይራ ዛፉን ተከሉ:: ይህ በሆነ በጥቂት ቀናት ልዩነት ውስጥ አባ ወደ ሌላ ሀገረ ስብከት ተመድበው ከዚያች ትንሽ የገጠር ከተማ ተሰናብተው ሔዱ::

ከሃያ ዓመታት ቆይታ በኁዋላ በአንድ አጋጣሚ አባ ወደዚያች ከተማ ተመልሰው መጡ:: ትንሹ ከተማ ትልቅ ሆኖ ብዙ ነገር ተለውጦ ጠበቃቸው:: የመጡበትን ጉዳይ ከፈጸሙ በኁዋላ የእነዚያ ባልና ሚስት ነገር ትዝ አላቸው:: በከተማው መቀየር ትንሽ ቢቸገሩም ቤቱን ፈልገው አገኙትና በር አንኳኩ::

አንድ የሚያምር ሕፃን የታቀፈች ሴት በሩን ከፈተች:: መካኒቱ ሴት ነበረች:: ከታቀፈችው ልጅ ሌላ እግርዋን ተጠምጥመው የያዙ ሁለት ሕጻናት አባን ሽቅብ እያዩ ይቁለጨለጫሉ:: መስቀል አሳልመው ወደ ውስጥ ሲዘልቁ ሶፋ ላይ ቁጭ ብለው ቴሌቪዥን የሚመለከቱ አራት ሕጻናት ተደርድረዋል::

ታላቆቻቸው የሚሆኑ ሁለት ልጆች ደግሞ ጠረጴዛው ላይ ቁጭ ብለው ያጠናሉ:: ይህ እንግዲህ ቡና የምታፈላውን ሴት ልጅና በሕፃን ልጅ አልጋ ላይ የተኛውን አራስ ልጅ ሳይጨምር ነው::

አባ በደስታም በመደነቅም ፈዝዘው ቀሩ::
"እንኩዋን ለዚህ አበቃችሁ ልጄ" አሏት በደስታ
"በእርስዎ ጸሎት ነው አባታችን" አለች እናት
"ለመሆኑ ባለቤትሽ የት ነው?" አሉ በጉጉት
እናት አንገትዋን ደፋች አባ ደነገጡ
"ምነው ሰላም አይደለም?" አሉ በስጋት
"ኸረ ሰላም ነው ... በጠዋት ወደዛች ተራራ ላይ ወዳለችው ገዳም ሔዶአል" አለች እያፈረች
"ምነው? ለምን ጉዳይ ሔደ?"
"ያኔ የተከልነውን የወይራ ዛፍ ሊቆርጥ"

✍🏽 ✍🏽 ✍🏽. ✍🏽. ✍🏽 ✍🏽 ✍🏽

ሊቁ ተርቱሊያን "የሰማዕታት ደም የክርስቲያኖች ዘር ነው" ብሎ ነበር:: "ክርስቲያን መግደል ክርስቲያን እንዲበቅል መዝራት ነው" እንደማለት ነው:: ከዚያ ውጪ ደግሞ ሌላው የክርስቲያን ዘር መውለድ ነው:: ብዙ ምእመናን የመውለድን ጸጋ ተጎናጽፈው ከመውለድ ይሸሻሉ::

ድሆች ሆነው እንኩዋን በፈጣሪ መግቦት አምነው የሚወልዱ እንዳሉ ሁሉ የኢኮኖሚ አቅም እያላቸው የተማሩ በመሆናቸው መውለድን እንደ ኁዋላ ቀርነት ቆጥረው ከመውለድ ወደ ኁዋላ የሚሉም ብዙዎች ናቸው::

ከላይ እንዳየነው ሰው ያህል እንኩዋን ሳይወልዱ ዛፍ ቆረጣ የሚሮጡ ብዙዎች ናቸው:: የሚወልደውን ኸረ በቃህ በቃሽ እያሉ የሚተቹ "ብዙ ተባዙ ምድርንም ሙሉ ሲባል ብቻህን ልትሞላ ነው እንዴ?" ብለው በወለዱ የሚዘብቱ አሉ::

መውለድ ጸጋ በረከት ነው:: የልጅን ጣዕምና ጸጋ የወለዱ ሁሉ ያውቃሉ:: ልጅ መውለድ የወላጆችን መንፈሳዊ ሕይወት ሳይቀር ከፍ ያደርጋል:: ልጅ ፊት አይወራም ሲባል ከሚተው ክፉ ወሬ ጀምሮ አርኣያ ለመሆን ሲባል ከሚደረግ ጥረት ድረስ ልጅ መውለድ ትልቅ በረከት ነው::

ለቤተ ክርስቲያን ደግሞ የልጆች መብዛት በረከት ነው:: አንድ አባትም "በሕፃናት የለቅሶ ጩኸት የማትረበሽ ቤተ ክርስቲያን የነገ ተስፋ የሌላት ቤተ ክርስቲያን ናት" ብለዋል:: ሕፃናት የሚበዙባት ቤተ ክርስቲያን ግን ነገ እንደምትኖር ያረጋገጠች ቤተ ክርስቲያን ናት።

ክርስቲያኖች ሆይ ውለዱ!

(በመምህር ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"እንኳን አንተ እኔም አልገባሁም"
"እንኳን አንተ እኔም አልገባሁም"

ይህን ባየሁ ጊዜ አንድ ያነበብኩት ታሪክ ትዝ አለኝ። ታሪኩ እንዲህ ነው።

ሰውየው ናይጄሪያዊ ነው። በሃይማኖቱም የምስራቅ ኦርቶዶክሳዊት እምነት ተከታይ ነው። ቀን በንግድ ሥራ የሚተዳደር ታታሪም ሠራተኛ ነበር። ከዚህ በላይ መንፈሳዊም ሰው ስለሆነ ሰንበተ ክርስቲያንን ከእግዚአብሔር ውጪ ለማንም አይሰጥም ነበር።

ከሰኞ እስከ አርብ የንግድ ሥራውን ያከናውንና፤ ቀዳሚትን ለተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮች ይጠቀማታል። እሁድን ግን በማለዳ ተነስቶ ያስቀድሳል። ሲዘጋጅ ሥጋ አምላክ ይቀበላል። ሕይወቱን የሚመራው እንዲህ ባለ መንገድ ነው።

ታዲያ አንድ ቀን ሀገሩ የሚሸጠውን ዕቃ ለመጫን ወደ ምዕራባውያኑ ሀገር ይጓዝና አንድ የሚያርፍበት ሆቴል ከተከራየ በኋላ የገበያውን ሁኔታ ለማጥናት ሲዘዋወር፤ አንድ ቤተ መቅደስ ያይና ተደስቶ፤ "በቃ እሁድ አይባክንብኝም። በማለዳ ተነስቼ መጥቼ አስቀድሳለሁ" ብሎ ከራሱ ጋር ቀጠሮ ይይዛል።

ቀኑ ደርሶ ለራሱ ቃል እንደገባው በማለዳ ተነስቶ ወደ ተመለከተው መቅደስ ይገሰግሳል። ሲደርስ ግን እንግዳ ነገር ይገጥመዋል። መቅደሱ በር ላይ የነበረው ዘበኛ "አትገባም" ይለዋል። "ለምን መቅደስ አይደለም?" ብሎ ሲጠይቀው፤ ሰውየው መልሶ "አዎ መቅደስ ነው ነገር ግን ጥቁር አይገባበትም" ብሎ ይመልስለታል።

ይህ አፍሪካዊ ነጋዴ በመልሱ ተደንቆ "ኧረ ግድ የለህም ለጥቁር ሌላ አምላክ የለውም። አንተን ነጭ አድርጎ የእኔን አጥቁሮ የፈጠረ እግዚአብሔርም የለም። እኔ የጠቆርኩት ፀሐይ በሚበረታበት አካባቢ ከሠሃራ በታች ስለምኖር ነው።" ብሎ አስረዳው።

ዘበኛውም በመልሱ በመደነቅ "ኦው እስከ ዛሬ ድረስ የነጭ አፈጣጠር የተለየ አድርጌ አስብ ነበር። ይህን እውነት ነግረህ ምልከታዬን ስላቃናኸው አመሰግናለሁ። ግን አትገባም።" ይለዋል። ይህ ምስኪን አፍሪካዊ ቀጠል አድርጎ "እውነቱ ከገባህ አንተ ልታገኘው ከተዘጋጀህለት አምላክ እኔን ለምን ትለየኛለህ?" ሲለው፦ ዘበኛው በማዘን "የነገርኸኝ እውነት የገባኝ እኔን እንጂ አለቆቼን አይደለምና፤ አዝናለሁ። አለቆቼ ለምን ጥቁር አስገባህ ብለው እኔን መጠየቃቸው አይቀርምና አታድክመኝ።" ብሎ በሩን ዘጋበት።

ይህ አምላኩን የፈለገና እሁድ እንዳይባክንበት የተጨነቀ ምስኪን፥ "ባያስገቡኝ እንኳ ሲቀድሱ ከውጪ ኾኜ ልስማ" ብሎ ጆሮውን ከመቅደሱ ግድግዳ ቢያስጠጋ ድምፅ ወደ ውጪ የማያስተጋባ ግድግዳ ነበር።

ባለመስማቱና ሰው ሀገር በመኾኑ በእግሩ በርከክ ብሎ ስቅስቅ እያለ አለቀሰ። ይህን ጊዜ የናፈቀው አምላክ አዘነለትና ድካም ቢጤ እንዲሰማው አድርጎ እንቅልፍ እንዲጥለው አደረገ። ከዚያም በሕልም ታየውና ምን ኾኖ እንደሚያለቅስ ጠየቀው።

እርሱም ሰው ሀገር በመኾኑና መቅደስ በመከልከሉ እንደኾነ መለሰለት። ያን ጊዜ በሕልም የታየው አምላኩ፦ "ባለመግባትህ አታልቅስ። እንኳን አንተ እኔም አልገባሁም።" ብሎ መለሰለት።

መቅደስን መቅደስ የሚያሰኘውን ታላቁን መቅደስ አውጥቶ ጥሎ፤ በመቅደስ የሚጠሩት አምላክ አይገኝም።

በመጋቤ ሃይማኖት ተስፋዬ ሞሲሳ
Audio
የኃጢአተኞች መንገድ ትጠፋለች

Size:-23.3MB
Length:-1:06:59

   በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/24 20:33:51
Back to Top
HTML Embed Code: