Telegram Web Link
#Update


ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ አበው ሊቃነ ጳጳሳትን ያካተተ ልኡክ በትናትናው እለት ከመንግሥት ጋር ባደረጉት ውይይት መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም #ሙሉ_በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ እሁድ የካቲት 5 ቀን 2015 ዓ/ም እንዲካሔድ የተወሰነው ሀገር ዓቀፍ እና ዓለም አቀፍ የአደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

Credit : EOTC TV

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
🕊🕊 ㅤ ❍ㅤ YAHWEH NSi ♡ ㅤ 🕊 ❍ㅤ 🕊

📡 "ያህዌህ ንሲ" የሚለው ቃል የዕብራይስጥ ቃል ሆኖ ትርጉሙ "እግዚአብሔር አላማዬ ነው" ማለት ነው !! እግዚአብሔር ዓላማህን በማድርግ የእግዚአብሄርን ቃል ፣መንፈሳዊ ትምህርት ፣ የቤተክርስትያን ታሪክ ትውፊት እና ሥርዓት ለምእመናን ማድረስ መባረክ ነው።

እንዲሁም እግዚአብሄር ዓላማችሁ አድርጋችሁ መንፈሳዊ ትምህርት ለምታስትላልፉ ሁላችሁ መምህራን፣ምእመናን በየቻናሎቻችሁ የተለያዩ አገልግሎቶችን የምታቀርቡ  ሰዎች በሙሉ በመጀመርያ ምስጋና ይገባችኋል።
ያህዌህ ፕሮሞሽንም እግዚአብሔር ዓላማው በማድረግ በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ቻናሎች መዝግቦ ለምእመናን  እንዲዳረሱ  ፕሮሞት እያደርገ ይገኛል ።  500 members ካለው 5ሺ members ያሉ በጣም ብዙ ናቸው ። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ #ከ5ሺ እስከ 50ሺ members የያዙ እና ከዛ በላይ  አባሎች የያዙ ቻናሎችን እያሳደግን እንገኛለን እና ያለን ቦታ የተወሰነ ሰለሆነ ሁላችሁም የቻናል ባሌቤቶች (Owners ) በተሎ እንድትመዘገቡ በትሕትና እናሳውቃለን ።

  በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ያስመዝግቡ
                =  @YEmeAmlak_DnglMaryam_Ljoch_Bot         
                =  ♡@Azaheill
Tel      :-  +251943686155 📞 ያገኙናል !!
 
          የፕሮሞሽኑ ሰዓት የተመለከተ

የሳምንት ፕሮግራም  
                 ➱ ማክሰኞ
                   ➱ ሀሙስ                   
                     ➱ ቅዳሜ     
                        ➱ እሁድ                    

🔘 ሰአት ፦ ከምሽቱ 12:00 - ጧት 2:00

🔘 Resend ፦ ከምሽቱ 2:00 ላይ ይደርጋል !!

   የፕሮሞሽን ማስታወቅያዎች  በሰዓቱ እንለቃለን እንዲሁም
በሰዓቱ እንሰርዛለን !!
               
#Update

ቅዱስ ሲኖዶስ በዛሬ መግለጫው ትላንት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ እና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር በነበረው ውይይት ስለተደረሰበት ስምምነት አሳውቋል።

በዚህም ከመንግስት ጋር፦

- የጉዳት ሰለባ ለሆኑቱ መንግሥት የድርጊቱን ፈጻሚዎች ለይቶ በሕግ አግባብ ተጠያቂ እንዲያደርግ፤

- አሁን ላይ እስር፤ ወከባ፤
እንግልት እየተፈጸመባቸው ያለት ብፁዓን ሉቃነ ጳጳሳት፤ የሀገረ ስብከት ሠራተኞች፤ አገልጋይ ካህናት እና በተለያዩ አደረጃጀቶች የሚገኙ የቤተ ክርስቲያኒቱን ልጆች ችግሩ በአስቸኳይ እንዲቆምና የታሠሩትም እንዲፈቱ አገልግልታቸውን በሰላምና በነጻነት መስጠት እንዲችሉ
#ስምምነት ላይ መደረሱ ተገልጿል።

መንግሥት የቤተ ክርስቲያኒቱን አቋም ሙሉ በሙሉ የተቀበለ ቢሆንም ይህንን ለማስፈጸም የሚያስችል የአፈጻጸም የድርጊት ጊዜ የሚያስፈልግ በመሆኑ ለነገ እሁድ የተጠራው ሰልፍ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።

በዚሁ እለትም ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁለም በየአጥቢያው በሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት ዓውደ ምሕረት ላይ ባለመቅረት የተለመደውን የእለተ ሰንበት የሥርዓተ ቅዳሴ፤ የጸሎት፣ የምሕላ እና የትምህርተ ወንጌል ከወትሮው በተለየ የመንፈሳዊ ሥርዓት በማከናወን እንዲያሳልፍ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ሰላማዊ ሰልፉ ለተወሰኑ ቀናት እንዲተላለፍ የተደረገው የአቋም ለውጥ ተደርጎ አለመሆን በመግለፅ አስቀድማ ቤተ ክርስቲያኗ በሮቿን ለሰላም ክፍት በማድረግ ባስተላለፈችው ጥሪ እና በአስቀመጠችው ቀነ ገደብ መሠረት
በመንግሥት በኩል ወዲያውኑ ችግሩን ለመፍታት ፍላጎት
በማሳየቱ ምክንያት መሆኑን አስገንዝቧል።

ቅዱስ ሲኖዶስ፤ " መንግሥት የገባውን ቃል እና የወሰነውን ውሳኔ የማይፈጽም ከሆነ መንፈሳዊ ተጋድሏችን የሚቀጥል ይሆናል " ብሏል።

@tikvahethiopia
Audio
የክርስቲያን ደም ዘር ነው
                         
Size 10.6MB
Length 30:26

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሰበር ዜና
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በሕገ ወጡ ቡድን የጵጵስና ልብስ አልብሶ ሾሜዎታለሁ ካላቸው መነኮሳት መካከል ከኢየሩሳሌም የመጡት "አባ" ንዋየሥላሴ አክሊሉ ቅዱስ ሲኖዶስ የሰጠውን ዕድል በመጠቀም በመንበረ ፓትርያርክ በመገኘት አስኬማቸውንና አርዌ በትሩን ለሕጋዊዋ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በማስረከብ ቤተክርስቲያንንና ምእመናንን ይቅርታ ጠይቀዋል።
በይቅርታ ደብዳቤያቸውም ሰሞኑን በቅድስት ቤተክርስቲያናችን ከቅዱስ ሲኖዶሱ እውቅና ውጪ አዲስ ኤጲስ ቆጶሳት ሹመት ሲካኼድ ከኢየሩሳሌም መጥቼ ከተሾሙት አንዱ ነበርኩ።

በዚህ ምእመናንን ባሳዘነ ቅዱስ ሲኖዶስ ቃለ ውግዘት ባስተላለፈበት ሕገ ወጥ ሢመት ውስጥ ባለማወቅና ነገሩን ሳላጣራ የገባሁበት በመሆኑ በእጅጉ የተጸጸትኩና በዚህም ተግባር ያዘንኩ መሆኔን በይቅርታ ልብ ለመግለጥ እወዳለሁ። በመሆኑም በዛሬው ዕለት ቅዱስ ሲኖዶስ በሠየመው አቀራራቢና በይቅርታ ኮሚቴ አማካኝነት በቅዱስ ሲኖዶሱ ውሳኔ መሠረት በተከፈተው የይቅርታና የምሕረት በር ወደ እናት ቤተክርስቲያኔ እና የመንፈስ ቅዱስ አባቶቼ እንዲሁም ምእመናን ለይቅርታ የቀረብኩ ስለሆነ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልዓተ ጉባኤው ውሳኔ መሠረት ይቅርታዬን በአባትነት መንፈስ ይቀበለኝ ዘንድ በታላቅ ትህትና እጠይቃለሁ ብለዋል።

"መከራውን ቤቴ ሁኜ ልቀበል ብለው ስለመጡ ቤተ ክርስቲያን ደስ ይላታል ፤ ሌሎችም ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ከእኛ ጋ ናቸው ተብላችሁ ተታላችሁ የሄዳችሁ፤ ፀፀት ውስጥ እንዳላችሁ እናውቃለን። ሌሎች ለመምጣት እየፈለጉ ቁልፍ ተይዞባቸው እንደተቸገሩም ሰምተናል::"
ብፁዕ አቡነ አብርሃም ይህንን የተናገሩት በሕገ ወጥ መንገድ ከተሾሙት "ኤጲስ ቆጶሳት" መካከል በቀድሞ ስማቸው አባ ንዋየ ሥላሴ አካሉ የይቅርታ ደብዳቤ በአስገቡ ሰዓት ነው፡
@EotcLibilery
‼️ቱርካዊው ወጣት ህይወትን እና ጊዜያዊ ደስታን ጠቅለል አድርጎ እንዲ ገልጿል..!

‼️ከቀናት በፊት ቤት ያከራየኝ ሰው ኪራይ ከሚገባው በላይ ጨምሮብኛ መክፈል ስላልቻልኩ ከቤቱ አባረረኝ፣ ካባረረኝ ከጥቂት ቀናት በኋላ የመሬት መንቀጥቀጡ ተከሰተ ታዲያ ዛሬ በመጠለያ ድንኳን ውስጥ አብረን እሳት እየሞቅን ነው ይላል ..!

Via Hijra Tube

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ሰላም የ EOTC ቤተ መጻሕፍት chanal ቤተሰቦች
እንኳን ለታላቁ አብይ ፆም አደረሳችሁ እያልቁ 1 ትልቅ የበረከት ስራ ልንሰራ አስበናል እሱም
ለድሬደዋ መካነ ሕይወት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ለሰሞነ ሕማማት መገልገያ የሚሆን ጥቁር ልብሰ ተክኖ ስለሌለው በዘሁ chanal አባላት አስተባብረን አሰፍተን ልንሰጥ ስላሰብን ይሕን የበረከት ስራ ላይ መሳተፍ ምትፈልጉ በውስጥ መስመር @yesadikusitota ላይ ያናግሩን አልያም በስልክ ቁጥር 0943896021 ላይ ያናግሩን
ለምታደርጉት ሁሉ እግዚአብሔር ይስጥልኝ
2024/09/24 14:30:12
Back to Top
HTML Embed Code: