Telegram Web Link
#NewsAlert

1ኛ. አባ ሳዊሮስ
2ኛ. አባ ኤዎስጣቴዎስ
3ኛ. አባ ዜና ማርቆስ

ሥልጣነ ክህነታቸውና የማዕረግ ስማቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ውሳኔ መነሳቱ ተገልጿል። ከዛሬ ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በቀድሞ ዓለማዊ ስማቸው እንዲጠሩ መወሰኑን ቅዱስ ሲኖዶስ አሳውቋል።

በቤተ ክርስቲያኗ መንፈሳዊ አገልግሎት ዙርያም በሕይወትም ሆነ በሞት ማናቸውንም መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳያገኙ ቅዱስ ሲኖዶስ አውግዞ ከቤተ ክርስቲያን እንደለያቸው አሳውቋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ አውግዞ በለያቸው ግለሰቦች ይመሯቸው በነበሩ አህጉረ ስብከት መንፈሳዊ አገልግሎት በማከናወን ሀገረ ስብከቱን የሚመሩ ብፁዐን አባቶችን፦
- ለደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት
- ለኬንያ፤ኡጋንዳ፤ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ ሀገረ ስብከት
- ለኢሉ አባቦራ እና በኖ በደሌ ሀገረ ስብከት
- በሰሜን አሜሪካ ለሜኒሶታ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት
- ለጉጂ፤ምዕራብ ጉጂ እና ቦረና ሊበን ዞኖች ሀገረ ስብከት
- ለምስካዬ ኅዙናን መድኃኒዓለም ገዳም በአባትነት የሚመሩ አበው ሊቃነ ጳጳሳት እንዲመደቡ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ወስኗል፡፡

ቅዱስ ሲኖዶስ ፤ " በስም ተጠቅሰው የተወገዙት ግለሰቦች በሠሩት የቀኖና ጥሰት ተጸጽተው ይቅርታን ቢጠይቁ የቅድስት ቤተ ክርስቲያን የምህረት ደጆች ሁል ጊዜ ክፈት መሆናቸውና በቀኖና ቤተ ክርስቲያን መሠረት የምንቀበላቸው " ይሆናል ብሏል።

(ሙሉ መግለጫው ከላይ ተያይዟል)

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#EOTC #አሁን

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በአሁኑ ሰዓት በወቅታዊ ጉዳይ መግለጫ እየሰጠች ነው።

ቤተክርስቲያኗ ፤ ከሃያ (20) ዓመታት በላይ በጅማ የም ኮንታ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን የሚያገለግሉት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ዛሬ በጅማ ዞን  ፖሊስ ታስረው መዋላቸውን ገልጻ ድርጊቱን በፅኑ አውግዛለች።

በአሁኑ ሰዓት ሊቀ ጳጳሱ #በግዳጅ ከጅማ እንዲወጡ መገዳቸውን እና ከሊቀ ትጉሃን ታጋይ ታደለ የኢትዮጵያን የሃይማኖት ተቋማት ጠቅላይ ጸሐፊ ጋር ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ መሆናቸውን ቤተክርስቲያኗ አሳውቃለች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ፤ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ከክልል የተሰጠ ትዕዛዝ ነው በማለት በነገው እለት በጅማ የቅድስት ድንግል ማርያም ሕንጻ ቤተመቅደስ ቡራኬ ቤተክርስቲያን ሳያከናውኑ በፀጥታ ኃይሎች ወደ አዲስ አበባ  እንዲመለሱ የተገደዱት ብሏል።

በተጨማሪ ቤተክርስቲያኗ በሰጠችው መግለጫ " በሕገ ወጥ ከተሾሙ አባቶች መካከል ይቅርታ ጠይቀው የተመለሱትና ቅዱስ ሲኖዶስ ይቅርታቸውን የተቀበለው መጋቤ ሐዲስ አባ ጸጋዘአብ አዱኛ ከመንበረ ፓትርያርክ ማረፊያ ተይዘው ወዳልታወቀ ሥፍራ ተወስደዋል " ስትል ገልፃለች።

በመግለጫው መንግሥት ሕግ የማስከበር ኃላፊነቱን እንዲወጣ የጠየቀች ሲሆን ቅዱስ ፓትርያርኩ በሚገኙበት ግቢ አፈና መፈጸሙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦርቶዶክሳውያንን ያሳዘነ ነው ብላለች።

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ዛሬ ጠዋት 3፡30 ቤተ ክርስቲያኗን ለመመረቅ ብፁዕነታቸው ቢሄዱም ያልተጠበቀና እጅግ አሳዛኝ የሆነ ነገር ተከስቷል፡፡ ከኤርፖርት አስረዋቸው ዞን ፖሊስ አስረዋቸው መዋላቸውንም ተናግረዋል፡፡ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ለብዙ ዓመታት ዘር፣ ቀለም፣ ጎሳ ሳይለዩ የጅማን፣ የየምን ሕዝብ የአገለገሉ የቤተ ክርስቲያናችን እንቁ አባት ናቸው፡፡

በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚደረገው ግፍ ይበቃናል፤ በሀገሪቱ ያለው መንግሥት አንድ ነው ሁሉንም በእኩል ሊመራ ይገባል ብለዋል፡፡

በተጨማሪም የሕገወጥ ሢመቱን አልፈልግም ብለው ይቅርታ የጠየቁትን አባት ከቤተ ክህነት በር ላይ መወሰዳቸውን ተናግረዋል፡፡

እኛ ሃይማኖተኞች እንጂ ጦረኞች አይደለንም፣ እጃችን ላይ ያለው የሰላም ምልክት የሆነው መስቀል ነው ያሉት አባ ወልደ ኢየሱስ የሚመለከተው አካል ይህንን ጉዳይ ሊያስቆም ይገባል ብለዋል፡፡

ቤተ ክርስቲያን ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን ጥሰዋል ያለቻቸው ግለሰቦች በመንግሥት ጥበቃ እየተደረገላቸው እንደሆነ በማኅበራዊ ሚዲያዎች እየተመለከትን ነው፡፡ ነገር ግን ሕጋዊ አካል ያላት ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ አባቶች ግን ታፍነው እንዲያዙ እየተደረገ ነው፡፡ መሳሪያ ያለው አካል የዚችን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መብት ሊያስከብር ይገባል፡፡ የክልሉ መንግሥትም ሆነ የፌደራል መንግሥት ይህንን ጉዳይ አጽንዖት ሰጥቶ ሊመለከተው ይገባል በማለት አሳስበዋል፡፡

በመጨረሻም መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ተከታዮች ሁሉን ማድረግ ወደሚቻለው እግዚአብሔር ተግታቹ ጸልዩ በማለት በእንባ ተማጽነዋል ፡፡
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
“እኛ ሃይማኖተኞች እንጂ ጦረኞች አይደለንም፣ እጃችን ላይ ያለው የሰላም ምልክት የሆነው መስቀል ነው፡፡” መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ

የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የቋሚና ጊዜያዊ ፕሮጀክቶች መምሪያ ኃላፊ የሆኑት መልአከ ሕይወት አባ ወልደ ኢየሱስ ይህንን የተናገሩት በዛሬው ዕለት የተፈጠረውን በአባቶች የደረሰውን ሕገ ወጥ ድርጊት  አስመልክቶ በሰጡት መግለጫ ነው፡፡

በጅማ ብዙ የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን በሀገር ውስጥና በውጭ ከሚኖሩ ምእመናን እርዳታ እጠየቁ ያስከፈቱ፣ ጨለማ የነበረውን ያበሩና ሀገረ ስብከቱን ከ20 ዓመት በላይ ያገለገሉ ታላቁ አባት ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አዲስ ያስገነቧትን የጅማ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለማስመረቅ ከቤተ ክህነት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳትን ጨምሮ 11 የሚሆኑ የቤተ ክህነት አገልጋዮች ለመሄድ ቢነሱም ከዞኑ ተደውሎ ከብፁዕነታቸው ውጪ ማንም መሄድ እንደማይችል እንደተነገራቸው ገልጸውልናል ብለዋል፡፡
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ አዲስ አበባ ገብተዋል።

በዛሬው ዕለት የእመቤታችንን ቅዳሴ ቤቷን እና ነገ በዓለ ንግሥ ለማክበር ወደ ጂማ ቢያቀኑም እንዲመለሱ ተደርገዋል።

ብፁዕነታቸው ከ23 ዓመታት በላይ በጂማ እና አካባቢው ዘር፣ ቀለም፣ ሃይማኖት ሳይለዩ  እያገለገሉ ይገኛሉ።

ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ ሕዝበ ክርስቲያኑን አስተባብረው ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ በመሰብሰብ የሕዝብ ትምህርት ቤት በማሠራት ከወራት በፊት  ለመንግስት ያስረከቡ አባት ናቸው።
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ተመስገን.... አባ ጸጋዘአብም ተለቀዋል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ቅዱስነታቸው በዛሬ ጥር 21 ቀን ዕለት የሰጡት የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ።
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ለሚመለከተው ሁሉ
እሁድ ጥር 14 ቀን 2015 ዓ.ም በሦስት ሊቃነ ጳጳሳት አማካኝነት በተፈጸመው የሕግ ጥሰት 26 ኤጲስ ቆጶሳት በመሾማቸው፣ ይህንን ጉዳይ አስመልክቶ ቋሚ ሲኖዶስ በሀገር ውስጥና በውጭ ሀገር ላሉት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሊቃነ ጳጳሳት አስቸኳይ ጥሪ አስተላልፏል፡፡
ጥሪ የተደረገላቸው አባቶችም በቅጽበት ደርሰው ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም ምልዓተ ጉባኤ አድርገው በቤተ ክርስቲያኒቱ ሕግ መሠረት ከላይ በተጠቀሰው ኢሕጋዊ ድርጊት ላይ ውሳኔ ማሳለፋቸው በዚያው ዕለት ጥር 18 ቀን 2015 ዓ.ም በተላለፈው የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ በሰፊው ተገልጿል፡፡
መግለጫውን ያዳመጡ በውስጥም በውጭም ያሉት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናትና ምእመናን ሁሉ ብርቱ ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡
እንዲሁም የዓለም አብያተ ክርስቲያናት እና መንፈሳውያን ተቋማት ድጋፋቸው ከመግለጻቸው በላይ የታሪካዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነትና ኅብረት ተጠብቆ እንዲኖርም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል፡፡
እኛም ድጋፋቸውንና መልካም ምኞታቸውን ስለገለጹልን የላቀ ምስጋና እናቀርብላቸዋለን፤ ምስጋናችን በያሉበት ይድረሳቸው፡፡
የሃይማኖት ተቋማት የበላይ ጠባቂዎች የክርስትናና የእስልምና መሪዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በደረሰው ድንገተኛ ክስተት ተደናግጠውና ተጨንቀው መጥተው የችግራችን ተካፋይ መሆናቸውን በመንፈሳዊ ስሜት ገልጸውልናልና ምስጋናችን ይድረሳቸው፤ እግዚአብሔርም ያክብራቸው እንላለን።
አሁንም በድጋሚ ለመንግሥትና ለሰፊው ሕዝባችን የምናስተላልፈው የአደራ መልእክት አለን፤ እሱም፡-
1. የታሪካዊቷ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሕግና ሥርዓት (ቀኖና) እንዲከበርልን፤
2. ጸጥታ እንዳይደፈርስና የንጹሐን ክርስቲያን ደም እንዳይፈስ ከወዲሁ ብርቱ ጥንቃቄ የተመላበት ጥበቃ እንዲደረግ በእግዚአብሔር ስም በአጽንዖት እንጠይቃለን፡፡
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን።
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም
ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
ጥር 21 ቀን 2015 ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ

@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/25 04:16:56
Back to Top
HTML Embed Code: