Telegram Web Link
በትግራይ ክልል የሚገኙ የቀድሞ "ሊቃነ ጳጳሳት" የራሳቸውን ሲኖዶስ ማቋቋማቸውን ገለጹ !


ጥቅምት 15 ቀን 2017 ዓ.ም(ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)


በትግራይ ክልል አህጉረ ስብከትን ሲመመሩ የነበሩት የቀድሞ "ሊቃነ ጳጳሳት" ያቋቋሙት “መንበረ ሰላማ" የተባለው ሕገወጡ "ቤተ ክህነት" ትላንት ባወጣው መግለጫ፣ “የትግራይ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ሲኖዶስ” በሚል መቋቋሙን አስታውቋል።


በትግራይ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናትን እና ገዳማትን በሕገወጥ መልኩ ተቆጣጥሮ የሚገኘው ይኸው ቡድን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ከባድ "የቀኖና" እርምጃ እወስዳለሁ ሲል መዛቱንም ከተሰራጨው የቪዲዮ መረጃ ታውቋል።


የትግራይን ሕዝብ ለፕሮቴስታንታዊ ተሃድሶ ለማስረከብ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ይህ ቡድን አሁንም በጥፋት ሥራዎቹ የቀጠለ ሲሆን በ"ሕገ ቤተ ክርስቲያን" ስም አንድ ሰነድ ማጽደቁ ነው የተገለጸው።

ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ጉዳይ ላይ እስከ አሁን የተባለ ነገር ባይኖርም ቤተ ክርስቲያኒቱ በተለያዩ ጊዜያት ባወጣቻቸው መግለጫዎች እንቅስቃሴው ቀናኖውን የሚፃረር ሕገ ወጥ እንደኾነ አውግዛ፣ “አንድ መንበር አንድ ሲኖዶስ እና አንድ ፓትርያርክ” የሚለውን የቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ እና ቀኖና ሊከበር እንደሚገባው በአጽንዖት አሳስባ ነበር።

ዘገባውን ለማሰናዳት የአሜሪካ ድምጽ ራዲዮን ተጠቅመናል።
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ዘጥቅምት ፲፯፤ ሥርዐተ ማኅሌት ዘወርኀ ጽጌ (‹ዘላይ ወዘታች› ቤት)

(፩ኛ ዙር ዓመት፤  ፬ ሳምንት፥ ዘጥቅምት ፲፯)
በዓለ ሲመቱ ለቅዱስ እስጢፋኖስ ሊቀ ዲያቆናት፤ ወቅዱስ ፊልጶስ ሰማዕት፤ ወዕረፍቱ ለአቡነ ዲዮስቆሮስ ካልዕ፤ ወልደታ ለቅድስት ሐና እመ ሳሙኤል፤ ወዕረፍቱ ለቅዱስ ጎርጎርዮስ እኁኁ ለቅዱስ ባስልዮስ።
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ታርቀን እናስታጉለው!

በአንድ ትልቅ ደብር ላይ የእርስ በርስ የካህናት ቅራኔ ይፈጠርና ጠቡ እየሰፋ ሄዶ ብዙዎቹ ይኮራረፋሉ
ይህን የተረዱት የደብሩ አስተዳዳሪም ካህናቱን በሙሉ ሰብስበው ለማስታረቅ ስብሰባ ያደርጋሉ
የተጣሉበት ነገር ሲነሣ ነገሩ ነገር እየወለደ ለእርቅ የተጠራው ስብሰባ የጠብ እስኪመስል ድረስ ሁሉም ተበደልሁ የሚል ስለሆነ አጀንዳው እየሰፋ ሄዶ የቅዳሴ ሰዓት ይደርሳል

በዚህ ሰዓት የደብሩ ቄሰ ገበዝ ይነሣና አሁን የቅዳሴ ሰዓት ስለደረሰ ምዕመናኑም ወደ ቤተ መቅደስ እየገቡ ስለሆነ የእርቁን ስብሰባ ለሌላ ቀን እናድርገውና አሁን ወደ ቅዳሴው እንግባ የሚል ሐሳብ ያቀርባል

አብዛኞቹም እሺ እንደሱ ይሻላል በማለት ሐሳቡን ደገፉት
አስተዳዳሪው ግን እውነተኛ አስተዋይ አስተዳዳሪ ነበሩና
አይ ሊቃውንት በፍጹም ይህንን የእርቅ ስብሰባ አቋርጠን ቅዳሴ አንገባም እንዲህ ተጣልተን ከምንቀድስ እኛ ታርቀን ቅዳሴውን እናስታጉለው
እኛ ተስማምተንና ተፋቅረን ቅዳሴው ይቅር ምዕመናን ለምን ቅዳሴ ታጎለ ብለው ከጠየቁን ታርቀን ነው በሏቸው ብለው ለእርቅ ያላቸውን የጸና አቋም አቀረቡ

😍ይህ ንግግር የሁሉንም ኅሊና ነካቸውና ያዙኝ ልቀቁኝ ተበድያለሁ የሚል ካህን ሁሉ እየተነሣ አስቀየመኝ ባለው ካህን ፊት እየወደቀ ማረኝ መባባል ጀመረ
5 ሰዓት የፈጀው የእርቅ ጭቅጭቅ በ5 ደቂቃ ብቻ ፍጻሜውን አገኘ ይባላል

አስተዳዳሪው እውነታቸውን ነው ተኮራርፈን ከምንሰብክ ተቀያይመን ከምንፈምር የጎሪጥ እየተያየን ከምንጸልይ እየተፎካከርን ከምንጸነጽል ታርቀን ብናስታጉለው ይሻል ነበር

ቤተ ክርስቲያኗን የፍቅር አውድማ መሆኗ እስኪያጠራጥር ድረስ በመለያየት የተለከፍነው ሁሉ ምነው እንደነዚያ አስተዳዳሪ ሁሉን ከእርቅ ብንጀምረው ምናችን ይጎዳል!

ይቅር በሉን ብንባባል ምን ይቀነስብናል!

የትኛውንም አገልግሎት በእርቅ ካልጀመርነው መሪ እቅድ ተዘረጋ፣ ማኅበር ተቋቋመ፣ የተማረ ሰው ተሾመ፣ በቋንቋ ተሰበከ፣ ወዘተ መዳረሻው ወደ ላይ ሳይሆን ወደ ታች ነው።

ወደ አባቶች የምክር ጠጠር መወርወር ድፍረት ቢሆንብኝም የቅዱስ ሲኖዶስ እቅዶችና አጀንዳዎች ሁሉ በመስማማት አሸናፊና ተሸናፊ ሳይኖር በፍቅርና በመተራረም ካልሆነ በስተቀር ያው ተኮራርፎ መቀደስን እንደመምረጥ ነው የሚሆነውና ከውሳኔዎች ሁሉ በላይ በዚህ ጉዳይ ላንለያይና ላንወቃቀስ ስህተቱንና ክፍተቱን ተረድተን ተዋደንና ተስማምተን በፍቅር ቋጭተነዋል የሚል የምሥራች ከውሳኔዎች ሁሉ በላይ ነው።

ይመስለኛል የሁሉም አማኝና አገልጋይ ምኞት ሲኖዶሳዊ ውሳኔዎችን ከመስማት ሁሉ በላይ የአባቶች አንድነትና ፍቅር ነው የሚያስጨንቀው
ፍቅርና አንድነት፣ ትህትናና መከባበር ከውሳኔዎች ሁሉ በላይ ናቸውና እግዚአብሔር የአንድነትና የፍቅር ዘመንን ያሳየን

እኛም ምዕመናንና አገልጋዮች ሁላችንም አባቶቻችን የሁላችንም እኩል አባት ናቸውና የየትኛውም አባት ክብር የእኛ ክብር ነው የማንም አባት መነቀፍና መዘለፍ የእኛ ውርደት ስለሆነ በአባቶች መካከል አንዱን ከመውቀስና ሌላውን ከማንገሥ በአንዱ ከመፍረድና በሌላው ከመደሰት ተቆጥበን አንድነታቸውን እየናፈቅንና እየተመኘን ስለ አንድነታቸውና ስለ ፍቅራቸው እንጸልይ።
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/11/15 09:48:20
Back to Top
HTML Embed Code: