✤እንኳን ለመስከረም 21፤ብዙኃን_ማርያም
#ብዙኃን_ሊቃውንት_ለተሰበሰቡበት_ብዙኃን_ማርያም_፤
#ክቡር_መስቀሉና_ሌሎችም_ንዋያተ_ቅድሳት-በግሸን_ደብረ_ከርቤ_አምባ_ላይ_በክብር_ላረፉበት_ዕለት፤
#ለቅዱስ_ቆጵርያኖስ_(ኃይለኛ ሥራየኛ ጠንቋይ የነበረውና በኋላም አምኖ ለክርስቶስ ምስክር ሆኖ አንገቱን የተሰየፈው )ና ፡ ቆጵርያኖስን ያሳመነችውና ስሟ በተጠራበት ቦታ ሰይጣናት እንደ ትቢያ ሆነው የጠፉት ታላቋ ቅድስት ድንግሊቱ ዮስቴና በሰማዕትነት ላረፉበት ዕለት፤
#ሃይማኖታቸው_ለቀና_ለ318ቱ_አበው_ሊቃውንት (#በ325 ዓ.ም #አርዮስን_አስተምረው_ለመመለስ_#በኒቅያ_የተሰበሰቡባት_ዕለት )፣ /የጉባኤውም ፍጻሜ ኅዳር ዘጠኝ ነው/ እንዲሁም
#ከ72ቱ_አርድእት_አንዱ_ለሆነው_ለሐዋርያው_ቅዱስ_ጢባርዮስ_ዕረፍት በሰላምና በጤና አምላከ አበው መድኀኔዓለም አደረሳችሁ አደረሰን፡፡
✤✤✤✤
የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም በዓሏ መስከረም ፳፩ ቀን መከበሩ ስለ ሁለት ነገር ነው፡፡ ፠1ኛ)
መስከረም ፳፩ የምናከብርበት አንደኛው ምክንያት መስቀልን አስመልክቶ ነው፡፡ መስቀሉ በመስቀልኛ ቦታ በግሸን ደብረ ከርቤ በክብር ያረፈበት ዕለት ነው፡፡
#ግሸን_ደብረ_ከርቤ
ደብረ #ንገሥት ፣ ደብረ #ነጐድጓድ ፣ ደብረ #እግዚአብሔር በሚባሉ ስም ትጠራ ነበር ፡፡
በመጀመርያም የተመሠረትቸው በአፄ ካሌብ ዘመን ነበር ፡፡ሁለት ጽላቶች ከናግርን (አጼ ካሌብ ድል አድርጎ ከተመለሰ በኃላ ) በአባ ፈቃደ ክርስቶስ አማካኝንት (መነኰስ) አምጥተዋል ፤ ከዛም ሲመጡ ወደ ጊሸን ተራራ ሊወጡ ሲሉ በዚያ ንብ ሰፎ ማር ሲንጠባጠብ በማየታቸወው በግእዝና አረብኛ ቋንቋ #አምባ አሰል ብለው ጠሩት ትሩጉሙም የማር አማባ ማት ነው እስካሁንም አካባቢው አምባሰል እየተባለ ይጠራል፡፡ የመጡትንም ጽላቶች በማስገባት የመጀመሪያውን ቤ.ክ ሠረተው ደብሩን መስርተዋል፡፡
በሺህ አንድ መቶ ሃያ ሰባት ዓመት ሰማዕታት ሃይማኖታቸው የቀና የዳግማዊ ዳዊት ልጅ ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከአፄ ይኩኖ አምላክ ከተረፈው የመንግሥት ቅብዓት ተቀብተው ነገሡ፡ ስመ መንግሥታቸውም #ቆስጠንቲኖስ ተባለ፡ በተወለዱም በሃምሣ ዓመት ‹‹ መስቀሌን በመስቀል ላይ አስቀምጥ የሚል ራዕይ አይተው ›› ጠይቀው ሲረዱ አባታቸው የተረከበው መስቀል በመካ መዲናው አሕዛብ ሹም እንዳለ ተረዱ ክተት ሰራዊት ብለው አደሊዋ ድረስ ዘመቱ በዚህ ጊዜ የምስሩ ንጉሥ የአባትህ ገንዘብ እኔጋ ስላለ እባክህ ከእኔ ጋር አተዋጋ መስቀሉን ፣ ሥዕላቱን እና ንዋያተ ቅዱሳቱን እስጥካለሁ አላቸው ( ማብራርያ መስከረም 17 የለጠፋነውን ጽሑፍ ተመልከቱ ) ይህንን ተቀብለው ተመልሰው ለ3 ዓመታት መስቀለኛ ቦታ ፈለጋ በኢትዮጵያ ተራሮች ዞሩ ቅዱስ ዑራኤልም ይራዳቸው ነበር ፡፡ ከሥስት ዓመት ቦኃላም አምባሰል ደርሰው ቦታዋ በመስቀል አምሳል የተቀረጸች መሆኗን አዩ፡፡ መግቢያው ቦታ እጅግ አስቸጋሪ ስለነበር አረፈው በነበሩበት ጊዜ ቅዱስ ዑራኤል ተገልፆ ይህች ደብረ ከዛሬ ጀምሮ ደብረ ከርቤ ትባላለች ፡፡ደብረ ነጐድጓድ ትባለ የነበረውም የካህናትና የነገሥታት መኖርያ ስለሆነች ነው ፡፡ሥላሴን የሚክዱ ሊኖሩባት አይችሉም ፡፡ ወደ ውስጥ ስትገባ ሁለት አብያተ ቤ.ክ ታገኛለህ አንዲቱ #በእግዚአብሔር አብ ስም የተሠራች ናት፡፡ አንዲቱ ደግሞ በእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ስም የታነጸች ናት፡፡
እመቤታቸንም ተገልጻለት #በኢትዮጵያ በተሰደድኩበት ጊዜ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ርስት ትሁንሽ ብሎ ስምሽ እስከ ዕለተ ምጽአት ሲመሰገን ይኑርባት ብሎ ሰጥቶኛል እና ሄድ ብላ ቦታዋን #ጠቆመችው፡፡
በ1446 ዓ.ም መስከረም 21 ወደ ተራረው ገብተው አይተው ተደሰቱ በታዘዙትም መሠረት ቅዱስ መስቀሉን በእግዚአብሔር ስም በተሰራው መቅድስ #አስቀመጠው፡፡
መስከረም 21 ቀንም መስቀሉ የተቀመጠበት የእግዚአብሔር አብ ቤ.ክ ቅዳሴ ቤቱ ሆነ ፡፡ ጌታችን በዘባነ ኪሩቤል ላይ ሆኖ አእላፍ መላእክትን አስከትሎ ከእናቱ ከቅድስት ድንግል ማርያም ጋር መጣ ፡፡ እጅግም ብዙ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ለቦታዋም ታላቅ ክብርን ሰጣት ደብረ ታቦርም ትሁንልህ አለው ፡፡
፠፠፠ #ብዙኃን_ማርያም፤
፠2ኛ) ደግሞ ጉባኤ ኒቅያን ይመለከታል፤ ለ፲፰ኛው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳስ ለተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ካሉት ደቀ መዛሙርት መካከል አርዮስ፣ አኪላስና እለእስክንድሮስ የሚባሉት ዋነኞቹ ነበሩ፡፡ አርዮስ እውቀቱ በመምህሩ የተመሠከረለት ሊቅ ነበር፡፡
ነገር ግን “እጅግ ጥበብ ያደርሳል ከሞት” እንዳለ ሰሎሞን የተጻፈውን ትቶ ባልተጻፈው ላይ ፍልስፍና ጀመረ፡፡ በምሳ. ፰÷፳፪ ላይ ያለውን ቃል በተሳሳተ መንገድ ፈታው፤ ነገር ግን ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ ጠርቶ ቢመክረው ቢገስጸው እንቢ በማለት የክህደት ትምህርቱን ቢቀጥልበት ከሹመቱ አውርዶ አወገዘው፡፡ ተፈጻሜተ ሰማዕት ከደቀመዛሙርቱ መካከል አኪላስን ተክቶ ኅዳር ፲፱ ቀን በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አኪላስም የጓደኝነት ፍቅር አድልቶበት አርዮስን ከውግዘት ቢፈታው በመቅሠፍት ሞት ሞተ፡፡ በመንበሩም እለእስክንድሮስ ተተካ፡፡ በዚህ ጊዜ የአርዮስ የክህደት ትምህርት በሀገሪቱ ሞላ፡፡ ይህ ነገርም እየተባባሰ በመሔዱ በንጉሥ ቈስጠንጢኖስ ዘንድ ተሰማ፡፡ ንጉስ ቈስጠንጢኖስም ይህን ሲሰማ ለአርዮስ ጥያቄ መልስ ይሠጥበት ዘንድ የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ጕባኤ እንዲደረግ ሰኔ ፳፩ ቀን አዋጅ አስነገረ፡፡ ይህንን አዋጅ የሰሙት ሊቃውንት ሁሉ መስከረም ፳፩ ቀን የእመቤታችን እለት ተሰባሰቡ፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞ “ለምን ቈስጠንጢኖስ መልዕክት ከላከበት ጊዜ በኋላ ወዲያውኑ ለምን አልመጡም? ለምን ዘገዩ?” የሚለው ጥያቄ ይነሳል፡፡ ምክንያቱም፤
#አንደኛ መጓጓዣ ችግር ስለነበር፤
#ሁለተኛ ሁሉም ሊቃውንት አስተማሪዎች በመሆናቸው ለምዕመናኑ (ለተማሪዎቻው) ሌላ መምህር ማዘጋጀት ስለነበረባቸው፤
#ሦስተኛ ደግሞ በእድሜ የገፉ ስለነበሩ አንድም ሊቃውንቱ ሲያስተምሩ በአላውያን ነገሥታት ባላመኑ ሰዎች ግፍ ይድርስባቸው ስለነበር ነው፡፡ ለምሳሌ ቶማስ ዘመርዓስ በእነዚህ ሰዎች በግፍ እግሩና እጁ ተቆርጦ ስለነበር ለማስተማር በቅርጫት ይዘውት ነበር የሚጓዘው፡፡ ወደ ጕባኤውም ሲመጣ ደቀ መዛውርቱ ያመጡት #በቅርጫት ይዘውት ነበር ( ማብራርያ የጥቅምት 14 የለጠፍነውን እይ ) ፡፡
ከዚህ በኋላ 2,340 ሊቃውንት መስከረም ፳፩ ቀን ተሠባሰቡ፡፡ ከእነዚህ መካከል ግን 318ቱ ሊቃውንት ‹‹ዘእሩይ ምስለ አብ በመለኮቱ ›› በማለት በሃይማኖታቸው የጸኑ ነበሩ፡፡ ጉባኤውን ከመጀመራቸው በፊት አርባ (፵) ቀን ሱባኤ እስከ ኅዳር ዘጠኝ (፱) ቀን ይዘውና ጕባኤውን አድርገው በአንዲት ቀን ያንን ታላቅ መናፍቅ አርዮስን ድል ነሥተውታል፡፡ ከዚህ ጋር አያይዘውም የኃይማኖታችን መሠረት የሆነውን ጸሎተ ሃይማኖትን አዘጋጅተዋል፡፡
@Nigatu5

ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፳ወ፩ ን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷል።
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።
መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ ለሣሕል፤እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
ዚቅ
ንባርኮ ለአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ስቡሕኒ ውእቱ ወልዑልኒ ውእቱ ለዓለም፤ንፍሑ ቀርነ በጽዮን፤ስብኩ በዓለ ማርያም ወበዓለ መስቀል ዘዮም።
ዘጣዕሙ:-
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
ዚቅ:-
ዓይ ይእቲ ዛቲ መድኃኒት፤እንተ ኃሠሥዋ ወዖድዋ ነቢያት፤ወይቤሎ ለኖኅ አመ አይኅ፤ግበር ታቦተ በዘትድኅን፤እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ፤አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ።
ወረብ
ይቤሎ እግዚእ አመ አይኅ ለኖኅ ግበር ታቦተ በዘትድኅን/፪/
እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ/፪/
መልክአ ማርያም
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምኪ ሐዋዝ፤እምነ ከልበኔ ወቊስጥ ወእምነ ሰንበልት ምዑዝ፤ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ትእዛዝ፤ይስቅየኒ ለለጽባሑ ወይነ ፍቅርኪ አዚዝ፤ከመ ይሰቅዮ ውኂዝ ለሠናይ አርዝ።
ዚቅ
ወይቤልዋ እምነ ጽዮን በሀ፤ወይቤልዋ ደብተራ ፍጽምት በሐ፤ወይቤልዎ ብርሃነ አሕዛብ በሐ፤ረቢ በሀ ወሪዶ ከመስቀሉ ሙቁሐነ ፈትሐ።
ወረብ
ወይቤልዋ[፪]በሐ በሐ ለማርያም[፪]
እምነ ጽዮን[፪]ወይቤልዋ ደብተራ ፍፅምት[፪]
መልክአ ማርያም
ሰላም ለጒርዔኪ ሠናይ እምወይን፤በከመ ይቤ ሰሎሞን፤ማርያም ድንግል ለባሲተ ዓቢይ ብርሃን፤ክድንኒ ገርዜነ ጸጋ ኢያዕጽበኒ ዕርቃን፤ዘኢአነምዎ ጠቢባን በኪን።
ዚቅ
በከመ ይቤ ሰሎሞን በእንተ ማርያም፤ንዑ ንትፈጋዕ ወኢይኅልፈነ ጽጌ ደመና፤መስቀል ዘዮም አብርሃ በስነ ማርያም፤ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን፤ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን፤አጽገዩ ሕዝበ ወመሐይምናን፤በቤተ መርዓ ተመልዑ ክርስቲያን።
ወረብ
ጴጥሮስኒ ሰመያ እመ ብርሃን/፪/
ጳውሎስኒ ይቤላ ደብተራ ግዕዛን/፪/
መልክአ ማርያም
ሰላም ለሐቌኪ በትረ ሌዋዊ ሣዉዕ፤ዘኢሐፀነኪ ጠል ወዘኢሰቀየኪ ነቅዕ፤ማርያም ድንግል እግዚእተ መላእክት ወሰብእ፤ሰድኒ ብሔረ ፍግዕ በትንባሌኪ ባቊዕ፤ምስለ ኅሩያንኪ ደርገ አሀሉ በስንዕ።
ዚቅ
በትረ አሮን እንተ ሠረፀት፤ወባቲ ይገብሩ ተአምረ፤በውስተ አሕዛብ፤እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ።
መልክአ ማርያም
ሰላም ለመልክዕኪ ዘተሠርገወ አሚረ፤ዘያበርሕ ወትረ፤ፍቅርትየ አንቲ እንተ ታበድሪ ፍቅረ፤አርእይኒ ገፀ ዚአኪ ማርያም ምዕረ፤ዘኢይሰምዖ ካልዕ እንግርኪ ነገረ።
ዚቅ
ፍጽመነ ንዕትብ በዕፀ መስቀሉ፤ነግሀ ነቂሐነ እምንዋም በከመ ይቤሉ አዕማደ ሰላም፤ዘዮም መስቀል አሠነየ ዓለመ እንተ በልየ፤በስነ ማርያም አዋከየ፤ለክርስቲያን ኮኖሙ ዕበየ።
ወረብ
ዮም መስቀል አሠነየ እንተ በልየ ዓለመ አሠነየ/፪/
በስነ ማርያም አዋከየ በስነ ማርያም/፪/
መልክአ ማርያም፦
በዝንቱ ቃለ ማኅሌት ወበዝንቱ ይባቤ፤ለዘይስዕለኪ ብእሲ ጊዜ ረከቦ ምንዳቤ፤ብጽሒ ፍጡነ ትሰጠዊዮ ዘይቤ፤ማርያም ዕንቊየ ክርስቲሎቤ፤ወምዕዝተ ምግባር እምከርቤ፤ዘጸገየ ማሕጸንኪ አፈወ ነባቤ።
ዚቅ
ሐፁር የዓዉዳ ወጽጌሬዳ ግብተ በርሃ ገፃ እምፀሐይ በትእምርተ መስቀል ክቡራት ዕንቍ መሠረታ።
ወረብ
ግብተ በርኃ ገፃ እምፀሐይ[፬]
ክቡራት ዕንቁ መሠረታ ሐፁር የዓዉዳ ወጽጌሬዳ[፪]
አንገርጋሪ

ምልጣን
እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ፤አክሊለ ተቀጺላ ታንሶሱ።
ወረብ
ይቤሎ እግዚእ አመ አይኅ ለኖኅ ግበር ታቦተ በዘትድኅን/፪/
እትአመን ባቲ እስመ አርአያ መስቀል ይእቲ/፪/
እስመ ለዓለም ዘበዓታ ዘዘወትር
ማርያም ድንግል ምክሖን ለደናግል፤ይእቲኬ ቤተ ምስአል፤ዘአስተዓፀቡ ታቀልል፤ለኲሉ ፍጥረት ትተነብል፤በአክናፈ መላእክት ትትኬለል፤ይእቲ ተዓቢ እምኪሩቤል፤ወትፈደፍድ እምሱራፌል፤መንክር ወመድምም ዕበያ ወክብራ ለድንግል፤ጽሕፍት ውስተ ወንጌል፤ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል።
አመላለስ
ጽሕፍት ውስተ ወንጌል/፪/
ወዲበ ርእሳኒ አክሊል በትእምርተ መስቀል/፪/
ወረብ
ማርያም ድንግል ምክሖን ለደናግል ይእቲኬ ቤተ ምስአል/፪/
ለኲሉ ፍጥረት ትተነብል ለኲሉ ፍጥረት/፪/
እስመ ለዓለም ዘላይ ቤት(ሰኑይ፤ረቡዕ፤አርብ ሲሆን)
ጸሎትክሙ ጽንእት ሃይማኖትክሙ ርትዕት፤እንተ በኵሉ ትረድዕ፤ሠናያን ወውርዝዋን በምግባረ ጽድቅ፤አግዓዝያን አንትሙ፤እለ መነንክምዎ ለዝንቱ ዓለም ኃላፊ፤ከመ ነግድ ወፈላሲ ሀልዉ አኃውየ ፍቁራንየ፤ምንት ይበቊዓነ ንብረቱ ለዝንቱ ዓለም፤ኢትርሲቱ ለዝንቱ ዓለም ኢወርቅ ሴጡ ለነፍስክሙ፤ሀቡ ናጥብዕ ወንንሣእ መስቀለ ሞቱ ለፍጹም መድኃኒነ፤ኢየሱስሃ ክርስቶስሃ ሰብሕዎ፤ሀቡ አኰቴተ ለስብሐቲሁ፤እንዘ አልብነ ኵሉ ብነ፤እንዘ አልቦ ዘየአምረነ ብዙኀን የአምሩነ፤ንልበስ ልብሰነ ዘድልው ለነ በኃቤሁ ማኅደርነ ዘበሰማያት።
➾✍እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏

#እንኳን #ለፆመ_ጽጌ በሳላም አደረሳቹህ
✤ወርኃ ጽጌ 40 ቀናት ነው፤ መስከረም 26 ተጀምሮ ኅዳር 5 ያልቃል፤ ጾመ ጽጌ የፈቃድ ጾም ነው (ከሰዓትም ቅዳሴ የሚቀደሰስባቸው አካባቢዎች አሉ (ጎንደር )፡፡
በግዕዝ ጸገየ ማለት አበበ ፤ አፈራ ፣ በውበት ተንቆጠቆጠ ማለት ነው፡፡
በማኀሌቱም ወቅትን እመቤታቸንን 3 ዓመት ከ6 ወር እስከ ግብፅ ከዚያም የአሥራት ሀገሯ በሆነችው በኢትዮጵያ የተሰደደችበትን ወቅት በማሰብ በጽጌና በአበባ እመቤታቸንን እና ጌታቸንን በመመሰል ሲያመሰግኗት ፣ ከልጇ ጋር ያየችውን መከራ እያሰቡ እና ምልጃዋን ሲለምኑ ያድራሉ ፡፡
✤እምግብጽ ጸዋዕክዎ ለወልድየ ለክብረ ቅዱሳን፤ ለቅዱሳን ክብር ልጄን ከግብጽ ጠራሁት››
በማለት ነቢዩ ሆሴዕ በምዕራፍ ፲፩ ቍጥር ፩ እና ፪ ላይ አስቀድሞ እንደ ተናገረው ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በልጅነቱ ወደ ምድረ #ግብጽ (ምስር) የተሰደደው የነቢያት ትንቢት ይፈጽም ዘንድ ነው፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ሕፃናትን በመፍጀት ከሚታወቀው ከአረመኔው ንጉሥ ከሄሮድስ ለማምለጥ ነው፡፡ አምላካችን ክርስቶስ ያለጊዜው (ዕለተ ዓርብ) #ደሙ #አይፈስምና፡፡ ስለዚህም ‹‹ሕፃኑንና እናቱን ይዘህ ወደ ምድረ ግብጽ ሽሽ፤ ሄሮድስ ሕፃኑን ለመግደል ይፈልጋልና›› ብሎ መልአኩ ቅዱስ #ገብርኤል ለዮሴፍ በነገረው ቃል መሠረት ሕፃኑንና እናቱን ይዞ በሌሊት ወደ ግብጽ ምድር ተሰደደ፡፡ ይህንን ስደት አስመልክቶ #ሰቆቃወ ድንግል የሚባለውን ቃለ እግዚአብሔር ካህናቱ በሚያሳዝን ዜማ ያደርሳሉ፤ ያቀርባሉ፡፡
#በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሕፃናትን ሄሮድስ አስፈጅቷል፡፡ ‹‹ድምፅ በራማ ተሰማ፤ ለቅሶና ብዙ ዋይታ፡፡ ራሔል ስለ ልጆቿ አለቀሰች፡፡ መጽናናትም አልወደደችም፤ የሉምና›› የሚለው ትንቢትም ተፈጸሟል፡፡
#ከሦስት ዓመት ከመንፈቅ የግብጽ ስደት በኋላ ሊቃውንቱ፡- ‹‹ተመየጢ ማርያም ሀገረኪ ናዝሬተ፣ በላዕሌኪ አልቦ ዘያበጽሕ ሁከተ፣ ወኢትጎንድዪ በግብጽ ከመ ዘአልብኪ ቤተ፣ ዘየኀሥሦ ለወልድኪ ይእዜሰ ሞተ፣ በከመ ነገሮ መልአክ ለዮሴፍ ብሥራተ›› እያሉ ከስደት መመለሷን ያበሥራሉ፡፡ ትርጉሙም፡- ‹‹ማርያም ሆይ! ወደ ሀገርሽ ወደ ናዝሬት ተመለሺ፡፡ በአንቺ ላይ ሁከት የሚያመጣ ማንም የለም፡፡ ቤት እንደሌለሽ ሁሉ በግብጽ አትቆይ፡፡ ለዮሴፍ በሕልሙ መልአክ እንደ ነገረው የሕፃኑን ነፍስ የፈለገው (ጠላት ሄሮድስ) ሞቷልና›› ማለት ነው፡፡ የኢትዮጵያ #ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን በዐርባው ቀን (በዘመነ ጽጌ) ወቅት የማርያምን የሽሽትና የመመለስ (የሚጠት) ታሪክ እያነሡ ውዳሴ የሚያቀርቡትና ማኅሌት የሚቆሙት በዚሁ ምክንያት ነው፡፡ በዚህ ወቅት ለእመቤታችን ክብር ሲባል የፈቃድ ጾም የሚጾሙ ምዕመናንና ምዕመናትም ብዙዎች ናቸው በመሃል ኢትዮጵያ በፈቃድ ጾምነት ሲጾም ; በሰሜኑ አካባቢ ተጹሞ ከሰዓት ይቀደሳል ሌሎች ጋር ግን ጠዋት ያበቃል፡፡
የእመቤታችን ምልጃ ና ጸሎት አይለየን
#ማኅሌተ_ጽጌ
✤የማኅሌተ ጽጌ የሰቈቃወ ድንግል ደራሲ አባ ጽጌ ድንግል ነው ፡፡
ገዳሙም ትልቅና ሰፊ የኾነ የፍልፍል ዋሻ ሲኾን ወሎ ወግዲ ወለቃ ወንዝ አጠገብ በረሃ ላይ (ከጋሥጫ ገዳም የ4 ሰዓት የእግር መንገድ) ይገኛል፡፡
✤✤ በየዓመቱ ሳይመረገዱ ያመይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ፤
እጅጉን በምንወደው የማኅሌተ ጽጌ ቁመት ላይ በየዓመቱ ሳይመረገዱ የማይታለፉ የማይቀሩ፤ ዚቃቸው የማይለወጥ
( ከማኅሌተ ጽጌ፤ ጽጌ አስተርአየ(የመጀመሪያው ሳምንት)፣ በከመ ይቤ መጽሐፍ፣ ትመስል እምኪ ማርያም፣ ዘኒ ስብሐተ ወዘኒ ማኅሌተ፣ ኢየሐፍር ቀዊመ ቅድመ ሥዕልኪ እና ኅብር ሐመልሚል (የመጨረሻው ሳምንት)ናቸው፡፡
✤ ከሰቈቃወ ድንግል፤ በስመ እግዚአብሔር ሥሉስ፣ ብክዩ ኅዙናን፣ እስከ ማዕዜኑ እግዝእትየ እና አብርሂ አብርሂ ናቸው፡፡
✤ከማኅሌተ ጽጌ ውስጥ እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕፃንኪ እና ክበበ ጌራ ወርቅ በየሳምንቱ (በኹሉም ዓመታት) ይመረገዳሉ፤ ዚቁ ግን በዓሉን በተመለከተ ይኾናል፡፡
✤ ከላይ ካየናቸው ውጪ የሚገኙት #የማኅሌተ ጽጌና የሰቈቃወ ድንግል ክፍሎች ግን #በየሰባት ዓመት አንዴ ነው የሚመረገዱት፡፡
( የማኅሌቱ ሥርዐት የላይ ቤት (የጎንደር መካነ ነገሥት ግምጃ ቤት ማርያም አብነት) እና የታች ቤት (የጎንደር ደብረ ኀይል በዓታ ለማርያምን አብነት) የሚያደርግ ሲኾን፤

የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም የመነኮሳትንና የደቀ መዛሙርትን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ፕሮጀክት በመቅረጽ ላይ መሆኑ ተገለጸ !
መስከረም 22 ቀን 2017 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም የመነኮሳትንና የደቀ መዛሙርትን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ፕሮጀክት በመቅረጽ ላይ መሆኑን የገዳሙ የዐራቱ ጉባኤያት የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ ገልጸዋል።
ገዳሙ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሐይቁ ውኃ መሬቱን እየሸረሸረ በመሄዱ ገዳማውያን የእርሻ ቦታ በማጣታቸው እንዲሁም የሀገሪቱ የሰላም እጦት ጎብኝዎች ወደ ገዳሙ እንዳይመጡ ተጽዕኖ በማሳደሩ ገዳማውያን የዕለት ጉርስ በማጣት መቸገራቸውን የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም መጋቢ አባ ገብረ ማርያም ወልደ ቂርቆስ ጠቅሰዋል፡፡
አባ ገብረ ማርያም ወልደ ቂርቆስ አክለውም ከገዳማውያንና ከደቀ መዛሙርት በተጨማሪ ወደ ገዳሙ የሚመጡ እንግዶች በርካታ መሆናቸውን ተከትሎ እነርሱን ለማስተናገድ ተቸግረናል ብለዋል፡፡
የርዕሰ አድባራት ወገዳማት ጣና ቅዱስ ቂርቆስ ገዳም የዐራቱ ጉባኤያት የመጻሕፍት ትርጓሜ መምህር ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ በገዳሙ ውስጥ ያሉ መነኮሳትና ደቀ መዛሙርት የጤና ችግር ትልቅ ፈተና እንደሆነባቸው በማንሳት በቀጣይ ለገዳሙ የራሱ የሆነ ጤና ጣቢያ ለመክፈትና ንጹሕ የመጠጥ ውኃ አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡
ደቀ መዛሙርት እንደ መነኮሳት የዳጉሳ ዳቤ እየተመገቡ መማር ስላልቻሉ ለሕመም እየተዳረጉብን ነው ያሉት አባ ገብረ ኪዳን ማኅበረ ቅዱሳን በየወሩ ለ10 ደቀ መዛሙርት የገንዘብ ድጎማ እያደረገ መሆኑንና ሰሞኑን ለዕለት ምግብ የሚውል ሁለት መቶ ሺህ ብር የሚገመት የጤፍና ዳጉሳ እህል በመግዛት ድጋፍ ማድረጉን ጠቅሰዋል ፡፡
አሁን ላይ የዕለት ቀለብ ብለን ምእመናንን ከማስቸገር ይልቅ ችግሩን በቋሚነት ለመፍታት ፕሮጀክት በመቅረጽ ላይ እንገኛለንም ብለዋል፡፡
አባ ገብረ ኪዳን አክለውም ፕሮጀክቱ እንደ ግብጽና ግሪክ ገዳማት ቤተ ክርስቲያንን የሚያቆም ይሆናል ያሉ ሲሆን ከማኅበረ ቅዱሳንና ከሌሎች አጋር አካላት ጋር በመነጋገር ለመስራት መታቀዱን አብራርተዋል፡፡
በመጨረሻም ሁሉም መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣መንፈሳዊ ማኅበራት እንዲሁም ምእመናን ትኩረት ሰጥተው ገዳሙንና ጉባኤ ቤቱን በመታደግና በማሳደግ ሂደት ውስጥ ትልቅ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡
መረጃው የማኅበረ ቅዱሳን ሰሜን ምዕራብ ማዕከላት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ነው
@Nigatu5
@Niigatu5