Telegram Web Link
#እረፍታቸው
#ሐዋርያው_ቅዱስ_ጴጥሮስ ከእዚያም እግዚአብሔር በሞቱ እንደሚያከብረው ነግሮት ወደ ሰማይ ዐረገ፡፡ በመጨረሻም ቅዱስ ጴጥሮስ በሮም አደባባይ በጨካኙ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት ቁልቁል (እንደ አምላኬ አልሰቀልም ብሎ) በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት ዐረፈ፡፡
#ሐዋርያው_ቅዱስ ጳውሎስ ለ 2 ዓመት ከ6 ወር በጨለማ ቤት ታሥሮ ከቆየ በኋላ በ74 ዓመት ዕድሜው በሮም ከተማ በኦስትያ መንገድ በኔሮን ቄሳር ዘመነ መንግሥት አንገቱን በሠይፍ ተሠይፎ ሐምሌ 5 ቀን በ67 ዓ.ም. በሰማዕትነት አረፈ፡፡ አምላካችን እግዚአብሔር ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ጳውሎስ ረድኤት በረከታቸው ይክፈለን፤ አሜን፡፡

ቤተ ክርስቲያኖቹ፤
#ብርሃናተ_ዓለም_ጴጥሮስ-ወጳውሎስ፤ ከፒያሳ ወደ አስኮ በሚወስደው መስመር መንገድ ላይ የሚገኝ፡፡
#ሰዋስወ_ብርሃን_ቅዱስ-ጳውሎስ_ገዳም፤ ከ3ቱ መንፈሳውያኝ ኮሌጆች አንዱና ዋነኛው የሚገኝበት፡፡ ከመርካቶ አውቶቡስ ተራ 18ት ማዞሪያ ብላችሁ ስትሄዱ የሚገኝ፡፡
እንካን ለሐዋሪያተ ዓለም ጵጥሮስ ወጳውሎስ የእረፍት በዓል እንካን አደረሳችሁ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
አንደበቱ ተከፈተ ||የሰው ተከታይ አትሁኑ
        
Size:-22.6MB
Length:-1:04:53

በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
የድሬደዋ ሀገረ ስብከት የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ከአጥቢያ የተወጣጡ 16 አባላትን የያዘ የተተኪ መምህራን ቡድን ለ አንድ ወር ለሚቆይ የስልጠና ጊዜ አዲስ አበባ (ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ)ላከ

ሀምሌ 07/2016 ዓ.ም የድሬደዋ ሰ/ት/ ቤቶች አንድነት

በኢትዮጽያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ትምህርትቤቶች ማደራጃ መምሪያ በሀገር ዓቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አዘጋጅነትበየዓመቱ የሚዘጋጀው የተተኪ መምህራን ስልጠና በዘንድሮውም ዓመት ከ16 በላይ ከሚሆኑ አህጉረ ስብከቶች ለተወጣጡ በቁጥር 213 የሚደርሱ ተተኪ መምህራን ስልጠና አዘጋጀ ።
በስልጠናውም ሀገረ ስብከታችንን ወክለው ለመሳተፍ ከአጥቢያ ሰ/ት/ቤቶች የተወጣጡ አስራ ስድስት የሚሆኑ አባላት በዛሬው እለት በስልጠናው ለመሳተፍ ቅድስት ሥላሴ ዩኒቨርሲቲ የገቡ ሲሆን በሚኖራቸውም የአንድ ወር ቆይታ :- .በክህሎታዊ ዘርፍ
.በአስተዳደር ዘርፍ
.በእውቀታዊ ዘርፍ እና
.በመሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ዙሪያ

በአራት የተለያዩ ዘርፎች ስልጠናዎች እንደሚወስዱ እና የሚሰጣቸውንም ስልጠና በአግባቡ ተከታትለው ውጤት ላመጡ መምህራንም እውቅናን እንደሚያገኙ ለዛም ባላቸው አጭር ጊዜ በንቃት መሳተፍ እንዳለባቸው በማንሳት ከስልጠናው በኋላም በሚያገኙት ዕውቀት እና ልምድ የመጡበትን ሀገረ ስብከት ብሎም ሰ/ት/ቤታቸውን በስርዓተ ትምህርት ትግበራ በሚገባ ማገልገል እንደሚገባቸው በሀገር ዓቀፉ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት የስርአተ ትምህርት ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት ዲ/ን ሚኪያስ ግዛቸው አያይዘው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

ምንጭ የድሬደዋ ሰ/ት/ቤቶች አንድነት ጽ/ቤት ነው
Audio
"ጌታችን በመርከብ ውስጥ ሕዝቡ በሐይቅ ውስጥ"

Size:-22.7MB
Length:-1:39:03

💠ርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን 💠

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
2024/09/21 11:55:12
Back to Top
HTML Embed Code: