Telegram Web Link
ሳይሆን ሁሉም እኩል ልጆቻችን መሆናቸውን አውቀን በፍቅር በመመልከት ነው፡፡ ሲጋጩብንም የማስታረቅና የማቀራረብ፤ የመምከርና የማሳመን እንጂ ወደ አንዱ ተለጥፎ ሌላውን ዘልፎ መናገር የቆምንለት ቅዱስ ወንጌል አይፈቅድልንም፡፡

ፓለቲከኞችም ባልዋሉበትና ባልተፈቀደላቸው፣ ሌላው ቀርቶ የተቋቋሙበት ሕገ መንግሥቱ እንኳ የማይፈቅድላቸውን በቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ ጣልቃ እየገቡ የግል ፍላጎትና ዓላማ ለማስፈጸም መሞከር ፍጹም ስሕተት ነው፤ ተቀባይነትም የለውም፤ ለቤተ ክርስቲያን ብቻ ሳይሆን ለራሳቸው ለፖለቲከኞቹም አይበጅም፡፡ ሁሉም ድንበሩን ጠብቆ በጋራ ጉዳዮች ላይ በፍቅርና በመከባበር ተመካክሮና ተግባብቶ መስራት ያሻል፤ በዚህ መንፈስ ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት ተናበው ቢሰሩ በሀገር ላይ ሰላም ይሰፍናል፣ ልማት ይፋጠናል፣ ዕድገት ይመዘገባል፤ ስለዚህም በዚህ ዙሪያ ሁላችንም ከምር ልናስብበት ይገባል፤
• ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣
• ክቡራን የበዓሉ ተሳታፊዎች፡-
በዛሬው ዕለት እያከበርነው ያለ በዓለ ሢመተ ክህነት ዓላማው የተሰጠንን ተልእኮ በማሰብ ለተሻለ መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ዕድገት የመነቃቃትና የመነሣሣት መንፈስ ለመፍጠር ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ባለፉት ዓመታት ያጋጠሙንን ፈተናዎች በመለየት፣ በቀጣዩ እንዳይደገሙ ነቅተንና ተግተን መስራት ያስፈልጋል፡፡ ባለፉት ዓመታት እጅግ በጣም አስቀያሚ ነገሮችና ፈተናዎች በቤተ ክርስቲያናችን ላይ ተከሥተዋል፤ አሁንም አልቆሙም፡፡
በየአካባቢው መብቱ ተነፍጎ በቀየው እንዳይኖር በልዩ ልዩ ምክንያት እየተፈናቀለ ያለውን ሕዝባችን ለማጽናናትና ለመደገፍ በአንድነት መቆም ይገባናል፡፡ ቤተ ክርስቲያን ልጆችዋን የመንከባከብ የመጠበቅና ዕንባቸውን በማበስ ፍትሕንና ርትዕን የማንገሥ ኃላፊነት አለባት፤ ይህንን ኃላፊነት በአስተውሎት ልትወጣው ይገባል፡፡ በመሆኑም መጪው ጊዜ ቤተ ክርስቲያን በውስጧ ያለው ውጣ ውረድ በማስተካከል መልክ የምታስይዝበት፣ የተፈናቀሉ ልጆችዋን የምታጽናናበትና የምታግዝበት እንዲሁም ለፈተና የተጋለጡ ልጆቻችን ሁሉ የዜግነት፣ የሃይማኖትና የሰብአዊ መብታቸው እንዲከበር ሰላም ፍቅር፣ ፍትሕ፣ አንድነት በሀገር እንዲነግሥ ሁሉም ድንበሩን ጠብቆ ሕዝቡን የሚያገለግልበት ዓመት እንዲሆን ከመቼውም ጊዜ በላይ በርትተን መሥራት አለብን፡፡ ይህንን ብናደርግ በእውነትም ወደ እግዚአብሔር ተመልሰናል ማለት ነው፤ እኛ ከተመለስን እሱም ወደኛ መመለሱ አይጠረጠርም፤ ስለዚህ አሁንም ወደ እሱ እንመለስ፡፡
በመጨረሻም
በሀገራችን ላይ ይልቁንም በቤተክርስቲያናችን ላይ ያለው ድባብ እጅግ በጣም አሳሳቢ እየሆነ መምጣቱ ለማንኛችንም ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም ካህናትና ምእመናን በሃይማኖት ጸንተው እንዲቆሙ በቤተክርስቲያናችን ላይ እጃቸውን እየዘረጉ የሚገኙ ሁሉ ቤተ ክርስቲያን ጠላታቸው አይደለችምና እጃቸውን እንዲያነሡ፣ መንግሥትም ለቤተክርስቲያን የሕግ ከለላና ጥበቃ እንዲያደርግ በእግዚአብሔር ስም ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡
መልካም በዓለ ሢመት ያድርግልን፤
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!!

አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም
ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
የካቲት ፳፬ ቀን ፳፻፲፮ ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ማዕበሉ ጸጥ ይልላችኋል 
                                                  
Size:- 26.9MB
Length:-1:17:19
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
አመ ፭ሱ ለመጋቢት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥርዓተ ዋዜማ

ሃሌ ሉያ-
አባ አባ ክቡር ገብረ መንፈስ ቅዱስ ክቡር፤ ብእሴ እግዚአብሔር፤ ተሰምዓ ዜናከ ውስተ ኲሉ ምድር፤ ድርገተ ኮንከ እንተ ላዕለ ኃይል፤ አባ፤ ጸሊ በእንቲአነ።

ምልጣን
ተሰምዓ ዜናከ ውስተ ኲሉ ምድር፤ ድርገተ ኮንከ እንተ ላዕለ ኃይል፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።

አመላለስ፦
አባ ጸሊ በእንቲአነ፤(2)
አባ ጸሊ ጸሊ በእንቲአነ፤(4)

💠ለእግዚአብሔር ምድር በምልዓ
አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ ጸሎትከ ወትረ ይብጽሐነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ።

💠እግዚአብሔር ነግሠ፦

ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤ ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ፤ ጸሎቱ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ።

💠ይትባረክ፦
ኪያከ መሠረት አንተ ብነ፤ አባ ጸሊ በእንቲአነ፤ እስመ ጸሎተ ጻድቅ ይሰምዕ እግዚአብሔር።

  💠ሰላም፦
አበው ቅዱሳን እለ ደብር ወገዳም፤ አስተምህሩ ለነ፤ ነሃሉ ወትረ በሰላም።

💠አመላለስ፦
እለ ደብር ወገዳም እለ ደብር ወገዳም/፪/
አስተምህሩ ለነ ነሃሉ ወትረ በሰላም/፬/

ዓዲ (ወይም)
💠ሰላም
አበው ቅዱሳን ዔሉ ውስተ አድባር ወበዓታት፤ አዕረፉ በክብር ወበብዙኅ ሰላም።

💠አመላለስ፦
አበው ቅዱሳን ዔሉ ውስተ አድባር ወበዓታት/፪/
አዕረፉ በክብር ወበብዙኅ ሰላም/፪/

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
አመ ፭ሱ ለመጋቢት ገብረ መንፈስ ቅዱስ ሥርዓተ ማህሌት

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፡ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኃቤየ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፡ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፡ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፡ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፡ በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ፦
ሰላም ለሕፅንክሙ ምርፋቀ ጻድቃን አግብርቲሁ፤ ማያተ ኢያሱ ሥላሴ እለ ትውኅዙ እምሕሊናሁ፤ እንዘ በአፍአሁ አንትሙ ወአንትሙ በውሣጤሁ፤ ኢነጸረ ኀበ ሐይመት ከመ አብርሃም አቡሁ፤ ወመስኮተ ነቢይ ዳንኤል ኢፈቀደ ያርኁ።

ዚቅ
ላህም መግዝዕ ተጠብሐ፤ ጽዋዓ መድኃኒት ተቶስሐ፤ አግብርት አግብርት አግብርት ይረፍቁ፤ ውስተ ሕፅኑ ለመርዓዊ፡፡

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለሕፅንከ እንተ በዲቤሁ ሕቁፍ፤ ጸሎተ ቅዱሳን ውኩፍ፤ ሚካኤል ክቡር መስፍነ ትጉሃን አእላፍ፤ ለረዲኦትየ ከመ ዘይሠርር ዖፍ፤ እንዘ ትሠርር ነዓ በ፪ኤ አክናፍ።

ዚቅ
ወይሁቦ ጸሎቶ ለዘጸለየ፤ ወባረከ ዓመተ ጻድቃኑ፡፡

ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
አመ ኖኅ ይእቲ መድኃኒት፤ እንተ ኮነት አንቀጸ ሕይወት ማርያም ቅድስት።


ዚቅ(ሌላ)
ማርያም ቤዛ ብዙኃን፤ ሕይወተ ኮነት ለኲሉ ዓለም፤ ፍሥሐነ ለእለ አመነ፡፡

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኆኅያቲሁ ቅሩጽ፤ ኀበ ዓምደ ብርሃን ጽዱል ወአኮ ዘዕፅ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኃያል ሠዋቄ ትንቱናን እምዳኅፅ፤ ለዝክረ ስምከ ሠናየ ዜና ወድምፅ፤ ትሴብሕ ኢትዮጵያ ወትዜምር ግብፅ።

ዚቅ
አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሠርር በአክናፍ ከመ አዕዋፍ፤ ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ጽሑፍ፡፡

ወረብ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘይሠርር በአክናፍ/፪/
'ኀበ ዓምደ ወርቅ'/፪/ ስሙ ጽሑፍ/፪/

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለከናፍሪከ ወለአፉከ ሰላም፤ ዓቃቤ ሥርዓት ዘሤመ ወማዕፆ ሕግ ዘዓቅም፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መነኮስ በምግባረ ሠናይ ፍጹም፤ እንበለ መብልዕ ወስቴ እንዘ ትትጋደል በጾም፤ ነጺራ ትዕግሥተከ አንከረት ገዳም፡፡

ዚቅ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በንጹሕ ዘፆመ፤ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ፤ ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመ።

ወረብ
ሃሌ ሃሌ ሉያ በንጹሕ ዘፆመ በከናፍሪሁ ማዕፆ ዘሤመ/፪/
ሐዳስ ይትዋረስ ዓለመ/፬/

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለከርሥከ ዘተሴሰየ ኅብስተ፤ አኮ ኅብስተ ምድራዌ እንተ ያመጽዕ ሐኬተ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኲሉ ይንዕዱከ ከሡተ፤ ብርሃነ ለዕውራን ወለሐንካሣን ፍኖተ፤ ወለበሐማን ቃለ ዘኮንኮሙ አንተ፡፡

ዚቅ
ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ኅብስተ ምድራዌ ዘተሴሰይከ፤ አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት ዘበስለ፤ ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ስቴ ምድራዌ ዘሰተይከ፤ አላ ስቴ ሰማያዌ እምሰማየ  ሰማያት ዘተቀድሐ።

ወረብ
ኦ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አኮ ዘተሴሰይከ ኅብስተ ምድራዌ ኅብስተ/፪/
አላ ኅብስተ ሰማያዌ እምሰማየ ሰማያት/፪/

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለጸአተ ነፍስከ እንተ ረሰየ ህላዌ፤ ኀበ ኢሰማዕ ቦቱ ዜና ሞት ወዝክረ ደዌ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ አንተ ዘገዳማውያን ሠርዌ፤ ወረዱ ጊዜ ሞትከ ዑፁፋነ ፅዱል ሥርጋዌ፤ ከመ ይትቀበሉ ኪያከ መርዓዌ፡፡

ዚቅ
ወወጽአት መንፈሱ ሶቤሃ፤ ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤ እንዘ ይብሉ ሃሌ ሉያ፤ ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ፡፡

ወረብ
ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት/፪/
ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ለገብረ ሕይወት/፪/

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም ለበድነ ሥጋከ ብርሃነ ሰማይ ዘአገቶ፤ እለ ያዕቆብ ወዮሴፍ እስከነ ፈርሁ ቀሪበቶ፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ባዕል ለብዕለ ጸጋከ ዘያስተቶ፤ ኃያል ብእሲ ይንሣእ ሢመቶ፤ ወበዓለ ዕዳ ይበርብር ንዋዮ ወቤቶ፡፡

ዚቅ
ፀሐይ ፀሐይ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፀሐይ፤ ዘያበርህ ስኑ በውስተ ቀላይ፤ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ ዘባረኮ አግዚእ አዶናይ።

መልክአ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
ሰላም መቃብሪከ ዘኢተከሥተ ለባዕድ፤ ከመ መቃብሩ ለሙሴ ወልደ ዮካብድ፤ ዜና መቃብርከሰ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ጸማድ፤ ቦ ዘይቤ በኢየሩሳሌም ዓፀድ፤ ወቦ ዘይቤ ሀለወ በከብድ፡፡

ዚቅ
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤ ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ፤ ጸሎቱ ለገብረ መንፈስ ቅዱስ ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ፡፡

ወረብ፦
ወረደ ብርሃን ወረደ ብርሃን  ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፤
ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ ጸሎቱ ለገብረ ህይወት፤

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ፦
አባ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ዘእግዚአብሔር ገብር በእደ መላእክት ቅቡር፤ በኢየሩሳሌም ሀገር፤ ኀበ ኢይበጽሕ ሰብእ በእግር፤ እንበለ ዳዕሙ ዖፍ ዘይሠርር።

ምልጣን፦
ግሩማን መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል፤ እለ አክናፊሆሙ ነበልባል፤ ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል፤ አማን፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።

አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ገብረ መንፈስ ቅዱስ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል/፬/

ወረብ
'ግሩማን መላእክት'/፪/ ሱራፌል ወኪሩቤል እለ አክናፊሆሙ ነበልባል/፪/
ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል አማን ገብረ ህይወት/፪/

እስመ ለዓለም
ይትፌስሑ በኀበ አልቦቱ ሞት፤ይነሥኡ እሴቶሙ፤እስመ ትዕግሥት ተውህበ ሎሙ ከመ ይንሥኡ፤ብዙኅ ሕማሙ ለጻድቃን፤ ወእምኵሉ ያድኅኖሙ እግዚአብሔር፤ወየዓቅብ ነፍሳቲሆሙ፤እስመ እንዘ ይነብሩ ውስተ ዓለም እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ ፤(ማንሻ-) ከመ ይንሥኡ አስበ ስብሐቶሙ፤ አክሊል ንጹሕ ዲበ ርእሶሙ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5

ስርዓተ ምልጣን ዘመጋቢት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
ከሁሉ አስቀድሞ ጸሎት ከተደረሰ በኃላ ዲያቆን መስቀሉን ይዞ ምስባክ ይስበክ

ምስባክ፡90፡13

ይበል ዲያቆን:
ወትከይድ አንበሳ ወከይሴ፡፡
እስመ ብየ ተወከለ አድኀኖ፡፡
ወእከድኖ እስመ አእመረ ስምየ፡፡
ወንጌል ፡-ሉቃ.21፡33-ፍ.ም

ወንጌል ከተነበበ በኃላ

እስመ ለዓለም #በቅኝት መጀመሪያ ይሉትና ሌሎች በዜማ #ይቀበላሉ

እስመ ለዓለም
ይትፌስሑ በኀበ አልቦቱ ሞት፤ይነሥኡ እሴቶሙ፤እስመ ትዕግሥት ተውህበ ሎሙ ከመ ይንሥኡ፤ብዙኅ ሕማሙ ለጻድቃን፤ ወእምኵሉ ያድኅኖሙ እግዚአብሔር፤ወየዓቅብ ነፍሳቲሆሙ፤እስመ እንዘ ይነብሩ ውስተ ዓለም እለ ሎቱ ተቀንዩ በሕይወቶሙ ፤(ማንሻ-) ከመ ይንሥኡ አስበ ስብሐቶሙ፤ አክሊል ንጹሕ ዲበ ርእሶሙ

መቃኘታቸው -=አይሁድ ጌታን ለመያዝ ይሁዳን አመልካች አድርገው ለመፈለጋቸው ምሳሌ ነው

መቀበላቸው፦የአይሁድ ጭፍሮች ጌታን ከይሁዳ ተረክበው ውሳኔያቸውን የመፈጸማቸው ምሳሌ

🕊🕊
ግሩማን መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል፤ እለ አክናፊሆሙ ነበልባል፤ ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል፤ አማን፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።

ስርአተ ምልጣን፦

መሪ-ሃሌ ሉያ
ተመሪ-ሃሌ ሉያ
መሪ- ግሩማን መላእክት
ተመሪ- ግሩማን መላእክት
መሪ- ሱራፌል ወኪሩቤል
ተመሪ-ሱራፌል ወኪሩቤል
መሪ- እለ አክናፊሆሙ ነበልባል
ተመሪ- እለ አክናፊሆሙ ነበልባል
መሪ- ወረዱ ዮም
ተመሪ- ወረዱ ዮም
መሪ- ይትቀበሉከ በብሂል
ተመሪ- ይትቀበሉከ በብሂል
መሪ-አማን
መሪ-አማን
መሪ- ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።
ተመሪ- ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።

ከዚህ በኃላ "ሃሌ ሉያ" ብሎ ዝማሜውን ይዘምማሉ፤ ንሺው ጋር በመሄድ ለሁለት ረዘም ባለ ዜማ ይመራራሉ

መሪ-ወረዱ ዮም
ተመሪ- ወረዱ ዮም
መሪ- ይትቀበሉከ በብሂል
ተመሪ- ይትቀበሉከ በብሂል
መሪ-አማን
ተመሪ- አማን


በዝማሜ ሁሉም - ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል

መምራት፦ ሊቀ ካህናት ሐና ጌታን እንዲይዙ ጭፍሮችን የመላኩ ምሳሌ

መመራት፦የአይሁድ ጭፍሮች በተሰጣቸው ትዕዛዝ መሠረት ጌታን ይዘው መጀመሪያ ከሊቀ ካህናቱ ሀና ፊት ለማቅረባቸው ምሳሌ

ዝማሜ፦መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሀና ወደ ቀያፋ ፣ከጲላጦስ ወደ ሔሮድስ መመላለሱንና መውደቁን ያመለክታል። በመቋሚያው መሬቱን መምታታቸው አይሁድ የጌታን እራስ በዘንግ መምታታቸውን ያመለክታል።

ሁለተኛ ሰው ከንሺው ጀምሮ ያነሳል

ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል፤ አማን በአማን፤

በዝማሜ ሁሉም - ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።

ሶስተኛ ሰው አሁንም እንዲሁ ንሺውን ያነሳል

በመቀጠል  "አማን በአማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል "  የሚለው በዝማሜ ተብሎ ከጽናጽል ና ከከበሮ ጋር ይቀርባል

አባባሉም፦
በጽፋት የከበሮ አመታት ፩ ጊዜ

አማን በአማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል

ከዚያ በቁርቋሮ እና በጽፋት

አማን በአማን አማን በአማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ አማን በአማን ....     ፩ዴ በቁርቋሮ
አማን በአማን አማን በአማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ አማን በአማን....    ፩ዴ በጽፋት

ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል....     ፩ዴ በቁርቋሮ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል....    ፩ዴ በጽፋት

አመላለስ አባባል ፦

አማን በአማን አማን በአማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ አማን በአማን አማን በአማን/፪ ጊዜ/
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል/፪ ጊዜ/

አመላለሱ ተብሎ እንዳለቀ በጽፋት የከበሮ አመታት

ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል፤ አማን በአማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል

ዝግ አባባል

ወረዱ ዮም ወረዱ ዮም /፪ጊዜ/
ይትቀበሉከ በብሂል ወረዱ ዮም /፪ጊዜ/

አማን በአማን
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል


ከዚ በኃላ በጽፋት ፦
ግሩማን መላእክት ሱራፌል ወኪሩቤል፤ እለ አክናፊሆሙ ነበልባል፤ ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል፤ አማን፤ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል።

ወረቡ እዚጋ ይባላል፦
''ግሩማን መላእክት''/፪/ ሱራፌል ወኪሩቤል እለ አክናፊሆሙ ነበልባል/፪/
ወረዱ ዮም ይትቀበሉከ በብሂል አማን ገብረ ህይወት/፪/

በቁም አባባል፦
አማን በአማን ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገባሬ ኃይል

ቁም- አይሁድ በህጋቸው አርባ ሲገርፉት ረጋ ብለው መጀመራቸውን ያመለክታል

እስመ ለዓለሙን በቁም በመረግድ እንዲሁም በጽፋት ይሉትና ወረቡን አንስተው ስርዓቱን ይፈጽማሉ

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
#እንኳን #ለአቡነ_ገብረ_መንፈስ_ቅዱስ_በዓል_በሰላምና_በጤና_አደረሳችሁ፡፡
መጋቢት ፭ በዓለ ዕረፍት ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ
#share
አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ (አቦ፥ አቡዬ)፤
* እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ብርሃነ ዓለም የኾኑ፤
* እንደ ቅዱስ እስጢፋኖስ ጸጋንና ክብርን የተሞሉ፤
* ኰከበ ገዳም፥ መናኔ ዓለም፥ ምድራዊ መልአክ፤
* ስማቸውን ሊቀ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ያወጣላቸው፤
* በአክናፈ መባርቅት ተጭነው የሚጓዙ፤
* 60 አናብስትና 60አናብርት ይታዘዙላቸው የነበሩ፤ የእግራቸው ትቢያ ለአራዊቶቹ ምግብ የኾነላቸው፤
* ለብዙ አእላፍ ቅዱሳን ወላዴ የኾኑና በረከትን የሰጡ ታላቅ አባት (ለአብነትም፤ ለቅዱስ #ላሊበላ፥ ለአቡነ #ሳሙኤል ዘዋልድባ፥ ለአባ #አንበስ ዘደብረ ሐዘሎ፥ ለአባ ብንያም ዘግብፅ)
፠፠፠ #ምድረ_ከብድ_፤ /ዝ_ምድር_ክቡድ_ውእቱ_/ ፤ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ)
 ምድረ ከብድ ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ያረፉባት ቦታ ናት፤ ቀጥሎ ወደ ደብር ቅዱስ #ዝቋላ (#ዝ_ቆላ) ለጸሎት ሂደው ለሃገራችን ኢትዮጵያና ለዓለማችን ምሕረትና በረከትን ከአምላካችን ለ100 ዓመታት በባሕር ውስጥ ሆነው ለምነዋል፤
*ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው ለ7 ዓመታት ጸልየዋል፤ ቊራም በሰይጣን ተመስሎ መጥቶ ዓይናቸውም ቢያጠፋውም ከ7 ሱባዔያት በኋላ ሊቀ መላእክት ሚካኤልና ገብርኤል ዓይናቸውን መልሰውላቸዋል፡፡
*ወደ ዝቋላ በመመለስም አጋንንትም ከምድረ ዝቋላ አጥፍተዋል፤
፠ እንደገና ወደ ምድረ ከብድ ተመልሰው በነበሩበት ጊዜ ታላላቆቹና በአንበሳ ዘባን ላይ የሚሄዱት #አቡነ_ሳሙኤል_ዘዋልድባ#አባ_አንበስ_ዘደብረ_ሐዘሎ_አፋር)፣ #አባ_ብንያም_ዘግብፅ ከአባታችን ቡራኬ ለመቀበል መጡ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተሰውረው ነበርና፤ የአቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ አናብስት የ3ቱን አባቶች አናብስት በሉባቸው፤ በ7ኛው ቀን አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ ተገልጠው የኾነውን ነገር በማየት የተበሉትን አናብስት እንዲመልሱ የራሳቸውን አናብስት አዘዟቸው መልሰውም እንደነበሩ በተዓምራት አስነስተው ሰጧቸው፤ በደመና ጠቅሰው ቅዱስ ፋኑኤል 3ት ሰማያዊ ኅብስትና 3ት ጽዋዕ ይዞ ለእንግዶቻቸው ይዘው ሠረገላ በሚባለው ዋሻ አመጡላቸውና ሰጥተው ሸኟቸው፤ እነዚህን ቅዱሳን በሸኙ በ7ኛው ቀን ወደ ተለያዩ ሃገራት ሄደው አስተምረዋል፡፡
፠ እድሜያቸው ረዥም እንደመሆኑ፤ ቅዱሱ ንጉሥ አፄ ላሊበላን ጨምሮ ሌሎችም ቅዱሳን ወደ ርሳቸው እየመጡ በረከትን ተቀብለዋል፡፡
#በግብፅ_300_ዓመታት_#በኢትዮጵያ_ምድር_ላይ_262_ዓመታት (በዋነኛነት #በምድረ_ከብድና_በዝቋላ_ ቢኖሩም ሌሎችም የመሠረቷቸውና የኖሩባቸው ገዳማት አሉ፤ ለአብነትም ደቡብ ወሎ የሚገኘውን #ገዘዛ_አቦን_ መጥቀስ ይቻላል)
፠ በድምሩ 562 ዓመታት ከኖሩ በኋላ በንጉሥ ሕዝብናኝ(እንድርያስ) ዘመነ መንግሥት፤ መጋቢት 5 ቀን ቅዳሜ ለእሑድ አጥቢያ ብዙ ቃል ኪዳንን ጌታችን ሰጣቸው፥ 12 አክሊላትንም አቀዳጃቸው፤ የነበሩባት ምድረ ከብድ ገዳም ግን ራደች፥ ተንቀጠቀጠች፥ በብርሃንም ተጥለቀለች፤ ዝቅ እያለችም መንሸራተት ጀመረች፤ ጌታችንም አንቺ መሬት ሆይ ጽኚ ይህንን ኹሉ ስለቻልሽ ምድር ክቡድ /ኋላ ምድረ ከብድ/ ተብለሽ ተጠሪ አላት፤ የጻድቁም ነፍስ ከሥጋቸው ከሌሊቱ 6 ሰዓት ተለየች፡፡
፠ ይህችውም ምድረ ከብድ ጻድቁ የኖሩባትና የቀደሱባት፥ የመሠረቷትና ያነፅዋት፣ ሠራዊተ መላአክት የከተሙባት፣ ታላላቅ አበው መጥተው በረከት ከአባታችን የተቀበሉባት፣ አርምሞና ጸጥታ የማይለያት፤ አጸዷና ቅጥሯ ልቡናን የሚመስጥ፤ ከአ.አ 125 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኝ ናት፡፡

ወተቀበልዎ መላእክት በስብሐት ወበማኅሌት፤
ወአብዕዎ ኢየሩሳሌም ሰማያዊተ አብዕዎ ገብረ ሕይወት፡፡

@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ታላቅ ሀገር 
                                                  
Size:- 34.2MB
Length:-1:38:04
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
ፍቅርና ትሕትና /ዘወረደ/ 
                                                  
Size:- 26.9MB
Length:-24:56
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
Audio
አትጥገቡ /ዐቢይ ጾም/ 
                                                  
Size:- 18.3MB
Length:-52:34
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@Nigatu5
@Nigatu5
@Nigatu5
ቅድስት
2024/09/20 22:59:07
Back to Top
HTML Embed Code: