Telegram Web Link
Audio
እውነት ነጻ ታወጣችኋለች 
                                                  
Size:- 54.7MB
Length:-2:37:11
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from Quality move bot
ተዋህዶ ሀይማኖቴ ነው ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ መረዳት መጻህፍትን ማንበብ እፈልጋለው የየእለቱን ስንክሳር ማንበብ እፈልጋለው ያለ ሁሉ ሊቀላቀላቀላቸው ሚገባ ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ቻናል 3 ቻናሎች
👇 ከታች Join በሉ
#የፍቅር_ሥራ_ይህች_ናት

ባልንጀራውን የሚረዳውን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ይረዳዋል፡፡ ለወንድሙ የሚነቀፍበትን ስም የሚያወጣውን ፈታሒ በርትዕ እግዚአብሔር እንዲሰደብ ያደርገዋል፡፡ ክፉ ስለ ሠራ ወንድሙን በቤቱ ለብቻው ሆኖ የሚመክረው ሰው ግን በምክሩ ዐዋቂ ይሆናል፡፡ ወንድሙን በዐደባባይ የነቀፈ ግን ኀዘን ያጸናበታል፡፡ ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች፡፡ ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡ በጎ ነገር ያደርግልኛል ብሎ በጎ የሚሠራ ኋላ ፈጥኖ ይተዋል፡፡

(#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ - በዲ/ን ሞገስ)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
"የማርን ጥፍጥና ማርን ቀምሶ ለማያውቅ ሰው በመቅመስ እንጂ በቃላት ማስተማር እንደማይቻል ሁሉ የእግዚአብሔርን መልካምነት በቃላት በጠራ መልኩ ማስተማር አይቻልም። ራሣችን ወደ እግዚአብሔር መልካምነት ዘልቀን መግባት ይኖርብናል እንጂ።"

ቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
እጅህ ላይ ባለው ነገር ከታመንህ እግዚአብሔር አምላክ በእጁ ውስጥ ያለውን ነገር ይሰጥሃል።

በውስጥህ ያለውን አቅም መጠቅም ከቻልህ እግዚአብሔር የአንተ ያልሆነ ተጨማሪ አቅም ይሰጥሃል።

ከእግረኞች ጋር ሳትደክም እኩል መራመድና መቅደም ከቻልህ እግዚአብሔር ፈረስን ለውድድር ይሰጥሃል። ኤር. 12፥5

የሚታዩ ኃጢአቶችን ለመዋጋት ታምነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር የተሸሸጉና የማይታዩ ኃጢአቶችን ድል እንድትነሣ ይሾምሃል።

በሕፃንነትህ በልጅነትህ ለእግዚአብሔር የታመንህ ሆነህ ከተገኘህ እርሱ በወጣትነትህ በምታደርገው ውጊያ ውስጥ ታማኝነትን ያድልሃል።

ልያን ለመቀበል ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር ራሔልን ሚስት አድርገህ ታገባት ዘንድ ይሰጥሃል። ዘፍ. 29፥27

በሲና ምድረ በዳ ለመቀመጥ ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር አምላክ የተስፋይቱን ምድር ከንዓንን ያወርስሃል።

በዚህ በተወሰነና አጭር ሕይወት ታማኝ ሆነህ ከተገኘህ እግዚአብሔር መጨረሻ የሌለውን ዘላለማዊ ሕይወት ያድልሃል።

ትልቁ ቁም ነገር በእጅህ ውስጥ የገባው ነገር ትንሽም ይሁን ጥቂት በእርሱ መታመን መቻልህ ነው። ስለሆነም ባለህ አንድ መክሊት ታምነህ ስትገኝ እግዚአብሔር አምስት መክሊቶችን በአደራ ይሰጥሃል።

አንተ በሚታዩት ነገሮች ላይ ታማኝ ሆነህ ስትገኝ እርሱ በማይታዩት ነገሮች ላይ ይሾምሃል።በመሆኑም ዓይን ያላየችውን ጆሮ ያልሰማውን በሰው ልብ ያልታሰበውን መንግሥቱን ያወርስሃል። 1ኛ ቆሮ 2፥9

(#አቡነ_ሺኖዳ_ሣልሳዊ - #መንፈሳዊው_መንገድ መጽሐፍ #አያሌው_ዘኢየሱስ እንደተረጎመው።)
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#መጽሐፍ_ቅዱስ

በአንድ ተራራማ ስፍራ እርሻ በማረስ ከልጅ ልጁ ጋር የሚኖር አንድ ሽማግሌ ነበር፡፡ ይህ ሽማግሌ ዘወትር ፀሐይ ብርሃኗን ስትፈነጥቅ እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱስን ያነባል፡፡ የልጅ ልጁ የአያቱን ተግባር ይከታተል ስለነበር እሱም ያያቱን ፈለግ በመከተል ጠዋት ጠዋት እየተነሳ መጽሐፍ ቅዱን ማንበብ ጀመረ፡፡

አንደ ቀን ታድያ አያቱን “አባባ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ እየሞከርኩ ነበር፡፡ ነገር ግን ልረዳው አልቻልኩም ደግሞም አንብቤ እንደጨረስኩ ወዲያውኑ እረሳዋለሁ እናም እንድረዳውና እንዳልረሳው ምን ማደረግ አለብኝ?” ሲል ጠየቀ፡፡

ሽማግሌው ምንም ድምጽ ሳያሰሙ “ከሰሉን ወደ ምድጃው ጨመሩና እንካ ይሄን የከሰል ቅርጫት ይዘህ ወንዝ ውረድና ውሃ ይዘህልኝ ተመለስ” አሉት፡፡ ልጁ ትዛዙን ለመፈጸም ወደወንዝ ወርዶ ውሃውን ይዞ ሊመለስ ቢመክርም ቅርጫቱ ውሃውን እያንጠባጠበ ቤት ከመድረሱ በፊት ፈሶ አለቀበት፡፡ ሽማግሌው የልጁን ሁኔታ እያስተዋሉ “አሁን ለሁለተኛ ጊዜ ይዘህ ስትመጣ ግን ፈጠን ፈጠን ብለህ ተመሰለስ ብለው”
ድጋሜ ላኩት፡፡ አሁንም ልጁ እንደተነገረው በፍጥነት ውሃውን ቀድቶ ሊመለስ ቢሞክርም ቤቱ ሳይደርስ ውሃው ፈሶ አለቀበት፡፡ አያቱንም “በቅርጫት ውሃ ማምጣት ስለማይቻል ሌላ መያዥ ይስጡኝና ላምጣ” ሲል ጠየቀ፡፡ ሽማግሌ አያቱም “እኔ የምፈልገው የቅርጫት ውሃ ነው፡፡ ጠንክረህ ባለመሞከርህ ነው ፈሶ ያለቀብህ” በማለት እንደገና ላኩት፡፡ በዚህ ጊዜ ልጁ በቅርጫት ውሃን ማምጣት እንደማይቻል ቢያውቅም ለአያቱ ታዛዥነቱን ለማሳየት ከበፊቱ ፈጥኖ ለማምጣት ሲሞክር ውሃው ፈሶ ስላለቀበት ባዶውን ቅርጫት እያሳየ “ተመልከት አባባ! እዲሁ ነው የምደክመው እንጅ እኮ ጥቅም የለውም” አለ፡፡

ከዚህ ጊዜ ምልልስ በኋላ ሽማግሌው “እስኪ ቅርጫቱን ተመልከተው” አሉት፡፡ ልጁ ቅርጫቱን ሲመለከት ከዚህ በፊት የማያውቀው ቅርጫት ይመስል ቅርጫቱ የተለየ ሆነበት የከሰል መያዣ እያለ በጅጉ የቆሸሸ ነበር፡፡ አሁን ግን ሙልጭ ብሎ ጸድቷል፡፡ ውስጡን ሲመለከተው ከመንጻቱ የተነሳ የበፊቱ ቅርጫት አልመስለው አለ፡፡

ስለዚህ ልጄ መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ የሚሆነው እደሱ ነው፡፡ ላትረዳው ትችል ይሆናል ወይም ደግሞ ያነበብከውን ሁሉንም ነገር ላታስታውሰው ትችል ይሆናል ዳሩ ግን ባነበብክ ቁጥር ለውጨኛው የሚተርፍ ውስጣዊ ንጽህና እያመጣህ መሆኑን አትዘንጋ የመንፈስ ሥራ እንደዚህ ነው በማለት አስተማሩት፡፡

(ከምስጋናው ግሸን ወልደ አገሬ)

(በድጋሚ የተፖሰተ)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
አንድ ሰው መጥቶ እናንተ የምትለብሱትን አንዲት ቁራጭ ልብስ እንኳ ሳይሰጣችሁና ሰውነታችሁ በብርድና በዋዕየ ፀሐይ እየተቆራመደ ሳለ ቤታችሁን በወርቅና በተንቆጠቆጠ የመጋረጃ ዓይነት ቢያስጌጥላችሁ ምን ጥቅም አለው? እኛስ ነፍሳችን ዕራቁቷን ሳለች ሥጋችንን ወርቅ ብናለብሰው በወርቅ ብናስተኛው ምን ትርጉም አለው? ነፍሳችን በመሬት ላይ እየተንፏቀቀች ሳለ ሥጋችን በከበሩ ሠረገላዎችና የተለያዩ ማጓጓዣዎች ብትንፈላሰስ ምን ጥቅም አለው?

ልጆቼ ! እውነተኛውን ልብስ ልበሱ ብዬ እመክራችኋለሁ። እዚህ የሚቀረውን ሳይኾን ዘለዓማዊውን ልብስ ልበሱ። የሰርጉን ልብስ ልበሱ።

እስኪ በየገዳማቱ ሒዱና ይህን ከቅዱሳን አበው ወእማት ተማሩ። እነዚህ ቅዱሳን በእልፍ ወትእልፊት ዕንቁ የተሽቆጠቆጠ ልብስ ብትሰጥዋቸው አይቀበሏችሁም። ለምን? እነርሱ ጋር ያለው ልብስ እናንተ ይዛችሁት ከሔዳችሁት ይልቅ በእጅጉ እንደሚበልጥ ስለሚያውቁ! ይኸውም የነፍሳቸው ልብስ ማለቴ ነው።

ለእነርሱ ይዛችሁት የሔዳችሁት ልብስ ለአንድ ምድራዊ ንጉሥ ብትሰጡት እጅግ ያመሰግናችኋል። እነርሱ ግን ከዚህ ንጉሥ በላይ በከበረ ልብሱ ያጌጡ ናቸውና አይቀበሏችሁም። ወርቃቸውን ወደሚያስቀምጡበት መዝገብ (ልቡናቸው) ገብታችሁ ስታዩ'ማ ራሳችሁን ስታችሁ ትወድቃላችሁ ። የሀብታቸውን (ምግባር ትሩፋታቸውን) ብዛት የወርቃቸውን ንጻት እንዲህ ነው ተብሎ የሚነገር አይደለም ። እናንተም ከእነርሱ ተማሩና እውነተኛውን ልብስ ለመልበስ ተሽቀዳደሙ ።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

(ሰማዕትነት አያምልጣችሁ መጽሐፍ)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ጴጥሮስን ለታላቅ ንስሓ የቀሰቀሰው የዶሮ ጩኸት ነበር ... ‹የዶሮ ጩኸት ጴጥሮስን ለንስሓ አበቃው› የሚለው ታሪክ ከዶሮ ጩኸት አልፎ እልፍ ሰባኪያን ‹ንስሓ ግቡ› እያሉ ሲጮኹ እየሰማን ምንም ለማይመስለን ለእኛ ለልበ ደንዳኖቹ መልእክቱ ምን ይሆን? የዶሮዎቹን ጩኸት ሰምቶ በመመለስ ፈንታ የዶሮዎቹን የአጯጯህ ስልት እያወዳደርን ሰባኪያን ለምናማርጥ ለእኛ መልእክቱ በእርግጥ ምን ይሆን?

በእርግጥ የዶሮውም እድል የሚያስቀና ነው፡፡ አንድ ጊዜ ጮኾ የወደቀውን ጴጥሮስ እንዲነሣ መቀስቀስ መቻሉ የታደለ ሰባኪ ያደርገዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ስንጮኽ ውለን አንድ ሰው ለንስሓ ማብቃት ላልቻልን ሰባኪያን ይህ ዶሮ ምንኛ የሚያስቀና ነው? ለነገሩ በልማዱ ዶሮ ጮኾ ሌሎቹን ከማስነሣቱ በፊት እሱ ተነሥቶ ክንፉን እያርገበገበ ከፍ ከፍ ይላል፡፡ እኛ ግን ራሳችን በኃጢአት ተኝተን ሌላውን ለንስሓ ለመቀስቀስ የምንሞክር እንቅልፋም ዶሮዎች ስለሆንን በጩኸታችን የረበሽነው እንጂ የቀሰቀስነው ሰው የለም፡፡

(ከዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ - ሕማማት መጽሐፍ የተወሰደ)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
"ኃጢአት ሲሠራ ባየኸው ወንድም ላይ አትፍረድ፥ አንተ ግልጽ የወጣ ኃጢአቱን እንጅ በስውር ለካህን የሚነግረውን ንስሐ አታውቅምና። ስለዚህ የራስህን ድካም ተመልከት።"

#ታላቁ_ቅዱስ_ባስልዮስ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፲ወ፫ ለታኅሣሥ ቅዱስ ሩፋኤል

የታህሳስ ሩፋኤል


ነግሥ (የማንኛውም ወርኃ  በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ)

ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገጽከ እምኔየ፡፡በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኅቤየ፤ሃሌ ሉያ  ሃሌ ሉያእመ ዕለተ አጽውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፡፡ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ለዓለመ ወለዓለመ ዓለም፡፡ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፡፡ንወድሶ ለዘሀሎ እግዚአብሔር ልዑል፡፡ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኵሉ ዓለመ በአሐቲ ቃል፡፡

ለገባሬ ኵሉ፦
ሰላም ለአብ ገባሬ ኵሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዚቅ፦
እስመ ዘይሬእየነ ብነ አብ ብርሃን ምስለ ወልዱ፤ወመላእክቲሁ ቅዱሳን፤እለ ይሔውፁ ቤተክርስቲያን።

መልክአ ሚካኤል
ሰላም ለአዕጋሪከ በክነፈ ነፋስ እለ ይረውፃ፤አብያተ ግፉአን የሐውፃ፤ሚካኤል የዋህ ወኅሩም እምነ ዓመፃ፤ተኖለው አዕጋርየ ለፍኖተ ስህተት እምዳኅፃ፤ወኀበ ምድረ ጽድቅ ምርሐኒ ከመ እብላዕ ሠርፃ።

ዚቅ
ይሔውፅዋ መላእክት አንተ በሰማያት፤ይሔውፅዋ መላእክት እስመ ማኅደረ መለኮተ ዖድክዋ ዖድክዋ ዖድክዋ ወርኢኩ ስነ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምስእል ወምስጋድ፤ወምለት ሥራየ ኀጢአት ይዕቲ ቅድስት ደብተራ።

ነግሥ
ሰላም ለሩፋኤል ለዓይነ ጦቢት ዘፈወሳ፤ዓይኖ ኵሂሎ በሐሞተ ዓሣ፤ለአስማንድዮስ አሠሮ ለመርዓ ጦቢያ ከመ ኢያርኵሳ፤ቤተ ክርስቲያኑ ሜላተ በግዑ ለቢሳ፤በዛቲ ዕለት ቴዎፍሎስ ሐነፃ።

ዚቅ፦
ሃሌ ሃሌ ሉያ ለቤተክርስትያን ቴዎፍሎስ ሐነፃ በጽድቁ ሐወፃ፤እምነ ፀሐይ ይበርህ ገጻ።

መልክአ ሩፋኤል
ሰላም ለዝክረ ስምከ ተጸውዖ ዘቀደመ፤በአፈ አምላክ አዳም እንበለ ይሰመይ ስመ፤ሩፋኤል ምልዓኒ ወወስከኒ ዳግመ፤መንፈስ ቅዱሳዌ አዕምሮ እንተ ይፈሪ ሰላመ፤ወአምላካዌ ጥበበ ዘየአዱ አቅመ፡፡

ዚቅ፦
ሀበነ ጥበበ፤ጥበበ ወምክረ አእምሮ ሠናየ፤ጸግወነ እግዚኦ።

ወረብ
ጥበበ ወምክረ ሀበነ ጥበበ/፪/
አእምሮ ሠናየ ሩፋኤል መልአክ/፪/

መልክአ ሩፋኤል
ሰላም ለቃልከ ዘይደምፅ እመብረቅ፤ለእስትንፋስከኒ እስትንፋሰ መንፈስ ረቂቅ፤ሩፋኤል ሐዋርያ ወመልአከ ጽድቅ፤ይጸንሑከ እግዚኦ ዕሡራነ በዓል በጻሕቅ፤ነዓ ነዓ እምሕላዌከ ምጡቅ፤ውስተ ቤትከ ዛቲ ክርስቶሳዊት ምርፋቅ፡፡

አመላለስ
ሩፋኤል ሐዋርያ/፪/
ወመልአከ ጽድቅ/፪/

ዚቅ
እስመ ለአለም ምሕረቱ ሐውፀነ በበዓልከ፤ሩፋኤል ክቡር አርውየነ እምጣዕመ ቃልከ፤ስፍሐ እዴከ ዲበ ዝንቱ መቅደስ ወካህናት።

ወረብ
እስመ ለአለም ምሕረቱ ሐውፀነ በበዓልከ/፪/
ሊቀ መላእክት ሩፋኤል አርውየነ እምጣዕመ ቃልከ/፪/

መልክአ ሩፋኤል
ተወኪፈከ እግዚኦ ዘንተ አምኃየ፤ዘአቅረብኩ ለከ መጠነ ክሂል ዘብየ፤ሩፋኤል ባዕል እንተ ታብዕል ነዳየ፤ዕስየኒ ለፍቁርከ ዕሤተ ሠናየ፤ዘዕዝነ መዋቲ ኢሰምዐ ወዘዐይን ኢርእየ፡፡

ዚቅ
አንተ ዕሥየነ፤ዕሤተ ሠናየ፤ዘአቅረብኩ ኢርእየ ወዕዝን ኢሰምዓ፤በውስተ ልበ ሰብእ ዘኢተኃለየ፤ዘአስተዳለወ እግዚአብሔር ለእለ ያፈቅርዎ።

ወረብ
አንተ ዕሥየነ ሊቀ መላእክት ዕሤተ ሠናየ ዘአስተዳለወ እግዚአብሔር/፪/
ዘዓይን ኢርእየ ወዕዝን ኢሰምዓ በውስተ ልበ ሰብእ ዘኢተኃለየ/፪/

ወረብ(ዓዲ)
አንተ ዕሥየነ ሊቀ መላእክት/፪/
ዕሤተ ሠናየ ወዕዝን ኢሰምዓ ወዓይን ኢርእየ/፪/

ምልጣን፦
ሃሌ ሉያ ይሰግዱ በብረኪሆሙ ወያሌዕሉ ኅሊናሆሙ በጥንቃቄ ወበሐሢሥ፤ኀበ እግዚኦሙ ንጉሥ፤ቀዋምያን ለነፍሳት፤እሙንቱ ሊቃናት፤ዑራኤል ወሩፋኤል፤ይትፌነዉ ለሣህል፤እምኀበ ልዑል።

አመላለስ፦
ይትፌነዉ ለሣህል/፪/
ለሣህል እምኀበ ልዑል/፬/

ወረብ፦
ይሰግዱ በብረኪሆሙ ወያሌዕሉ ኅሊናሆሙ በጥንቃቄ ወበሐሢሥ/፪/
ኀበ እግዚኦሙ ንጉሥ ቀዋምያን ለነፍሳት እሙንቱ ሊቃናት ዑራኤል ወሩፋኤል/፪/

ቅንዋት
ሰበክዎ በአፈ ኵሎሙ ነቢያት፤ከመ ይመጽእ ወልድ በስብሐት፤ሰበክዎ ነቢያት፤ነቢያት ቀደሙ አእምሮ፤ሐዋርያት ተለዉ አሠሮ፤ሰ:ዕንባቆም ነቢይ ዘአንከረ ግብሮ፤ዕሌኒ ንግሥት ኃሠሠት መስቀሎ፤ሰ:ሚካኤል መልአክ ዘልብሱ መብረቅ፤ወገብርኤል ሐመልማለ ወርቅ፤ሰ:ውእቱሰ ተመሰለ ከመ ሰብእ፤ወአንሶሰወ ውስተ ዓለም፤ሰበክዎ ነቢያት፤ዘዕሩይ ምክሩ ምስለ አብ።
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ቤዛ ኲሉ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ቤዛ ኲሉ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
አንፈርዓጹ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - አንፈርዓጹ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimonot
@mezigebehayimanot
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው 16k
ዝማሬ ዳዊት
ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው

ድንግል ፈጣሪዋን ወለደችው
በመጠቅለያም ጠቀቀለለችው
የለምና ስፍራ ለንግዶች ማረፊአ
ግርግም አስተኛችው በከብቶች ማደርያ /2/
አዝ
ጨነቃት ጠበባት የዳዊት ከተማ
የጌታ መወለድ ታምሩ ሲሰማ
ወረደ መልአኩ ምስራች ሊያወራ
የህፃኑ ክብር በምድር አበራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
አዝ
ሰብአ ሰገል መጡ ከሩቅ ምስራቅ ሀገር
ወርቅ እጣን ከርቤዉን ለርሱ ለመገበር
በእናቱም እቅፍ አገኙት ህፃኑን
ላለም ተናገሩ ንጉስ መወለዱን
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
አዝ
የይሁዳ ምድር ምስጋና ተመላ
ንጉስ መቷልና ከናዝሬት ገሊላ
ታምሩን ትናገር ቤተልሄም ታዉራ
ዝማሬ ሲወጣ ከርስቱ ቆጠራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/
አዝ
የማይታይ ታየ ተዳሰሰ አንደ ሰዉ
በጠባቡ ደረት አዳምን መሰለዉ
ገረማት ጥበቡ ታናሹአን ሙሽራ
ተዋህዳልና ቃል ከ ስጋ ጋራ
ይህ ሚስጢር ግሩም ነው ከቶ የማይነገር
ማርያምም በልቧ ትጠብቀው ነበር /2/

@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ይኸው ተወለደ
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ይኸው ተወለደ

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
ስብሐት ለእግዚአብሔር
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - ስብሐት ለእግዚአብሔር

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
አማን በአማን
ዝማሬ ዳዊት On Telegram
የአእላፋት ዝማሬ መዝሙር ጥናት
ርዕስ - አማን በአማን

ለሁሉም ሼር በማድረግ አዳርሱ!
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
#ቁጣ ድል አይንሣህ

ወንድምህን ከሚገባው ይልቅ ለማክበር ሰውነትህን አትጋት ባገኘህውም ጊዜ እጁን እግሩን ሳመው በጎ አድርግለት አክብረህ ወደህ እየው ሥራው ባይደለ ሥራ አመስግነው ከአንተም በተለየ ጊዜ የእሱን ነገር ተናገር ከበጎ ሥራው ወገን መናገር በሚቻልህ ገንዘብ በጎ በጎ አድርግለት በጎ ነገር በመናገርህ ወደ በጎ ሥራ ትስበዋለህ ታነቃቀዋለህ አንተ ባመሰገንከው ምስጋና አንተ ባከበርከው ክብር የተነሣ ያፍር ዘንድ እንዳመሰገንከው ያልሆነ እንደሆነ ያፍራል እንዲህ የሆነ እንደሆነ ዘርአ ትሩፋትን ትዘራበታለህ፡፡

ነፍስህ ከለመደችው ባልንጀራህን ከማክበር የተነሣ በጎ ነገርን መውደድ በልቡናህ ይቀርጻል ፍጹም ትሕትናን ገንዘብ ታደርጋለህ ሳትጥር ብዙ ሥራ ትሠራልህ የምታከብረው በጎውን ሰው ብቻ አይደለም ነውር ያለበትም ቢሆን አክብረው እንጂ እንዲህ የሆነ እንደሆነ አንተ ካከበርከው ክብር የተነሣ አፍሮ ካንተ ድኅነትን ያገኛል።

ገንዘብህ የምትሆን ይህችን ጥበብ ለሁሉ አድርጋት ጥበብም የተባለች ሰውን ማክበር ለሰው ማዘን መራራት ናት አንዱንስ እንኳን አትቈጣ ተቈጥተህ አታሳዝነው ቍጣ ድል አይንሳህ ስለ ሃይማኖትም ቢሆን ሥራው ክፉ ስለሆነም ቢሆን ሰው እንዳታማ ተጠበቅ እንጂ አትፍረድበት በልዕልና ፊት አይቶ ሳያዳላ የሚፈርድ ዳኛ ክርስቶስ አለንና ወደ በጎ ሥራም ልትመልሰውም ብትወድ እዘንለት እያለቀስህ የለዘበ ነገር ንገረው በቍጣ አትናደድበት ጸብ ያለህ ይመስለዋል ፍቅር ውስጣዊ ቍጣን አይሻምና።

ምክር ወተግሣጽ ዘማር ይስሐቅ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
#ሱባዔ_እንዴት_እንግባ?


1.ሱባዔ መያዝ ስለፈለግንበት ጉዳይ ማሰብ እና መለየት፡- ዓላማ የሌለን ዝርው የሆነ ያልተሰበሰበ አእምሮ ይዘን እንዳንገባ ፤ ከቅዱሳን በረከት ለመሳተፍ፤ወይም የግል ሕይወት ጉዳይ፡- ሥራ፣ትምህርት፤ትዳር…የሀገርና የቤተ ክርስቲያን የመሳሰሉትን ጉዳዮች ለይቶ ማወቅ ያስፈልጋል ፡፡

2. ሱባዔ ከመግባታችን በፊት ስለ ሱባዔ በደንብ ጠንቅቀን ማወቅ ይገባናል፡- መጀመሪያ ከንስሐ አባቶቻችን ጋር መመካከር፤ ቀጥሎም ስለ ሱባዔ ከሚያውቁ መንፈሳውያን አባቶች መጠየቅ ያስፈልጋል፤ ብዙዎችን ሱባዔ ማለት ቀልድ የሚመስላቸው ዝምም ብለው የሚጀምሩት ጉዳይ ሆኗል፤ በዚህም ምክንያት የብዙዎች ሕይወት የሰይጣን መጫወቻ የሆነበት ዘመን ላይ ደርሰናል፡፡

3.ስለምንቆይባቸው የቀናት ብዛት በሚገባ በማሰብ መወሰን፡ -ሱባዔ ማለት ቀጥታ ትርጉሙ ሰባት ማለት ይሁን እንጂ የግድ ግን ሰባት ቀን ወይም ሰባት ዓመት መኖር ማለት አይደለም፤ ይህ ለተሰጣቸውና ከዓለም ሙሉ ሕይወታቸውን ላገለሉ ሰዎች እንጂ ለዓለማውያን የተሰጠ አይደለም፤ ሃያ አራት ሰዓት ወይም 48 ሰዓት ወይም ደግሞ 72 ሰዓት (ሦስት ቀናት) ሊሆን ይችላል፤ ከዚህ ጀምሮ እንደየዓቅማችን 7፣14፣21….ቀናት እያልን ልናሳድገው እንችላለን፡፡ ይህም የሚጠቅመን ምናልባት ባለማወቅ ከጀመርነው በኋላ ፈተናው ሲፀናብን እንዳናቋርጥና ከእግዚአብሔር ጋር እንዳንጣላ ነው፤ይህንንም ጌታችን በምሳሌ እንዲህ ሲል አስተምሮናል "ከእናንተ ግንብ ሊሠራ የሚወድ ለመደምደሚያ የሚበቃ ያለው እንደሆነ አስቀድሞ ተቀምጦ ኪሳራውን የማይቆጥር ማነው? ያለዚያ መሠረቱን ቢመሠርት ሊደመድመውም ቢያቅተው ያዩት ሁሉ፡-ይህ ሰው ሊሠራ ጀምሮ ሊደመድመው አቃተው ብለው ሊዘብቱበት ይጀምራሉ" (ሉቃ 14፡28-30) በማለት አጋንንት፤ የመናፍቃን መሳለቂያ እንዳንሆን ያስጠነቅቀናል፡፡

4. የምንጸልያቸውን ጸሎቶች መለየት፡- በቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓት ብዙ ዓይነት ጸሎት መኖሩ ይታወቃል፤ሁሉንም እንጸልያለን ብንል ዓይናችን ይፈዛል አንደበታችን ይላሻል፤ ስለዚህም በየሰዓቱና በየዕለቱ የምንጸልያቸውን ጸሎቶች በመለየት ሳናስታጉል በትጋት መጸለይ አለብን፤ በጸሎት ጊዜም ሰጊድ(ስግደት)፤አስተብርኮ(መንበርከክ)፤ አንቃዕድዎ(ማንጋጠጥ) ከእንባ ጋር መረሳት የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው፤ እነዚህንም ያስተማረን ራሱ ጌታችን መሆኑን ልብ ይሏል! ማቴ 26፡39፤ሉቃ 22፡42፤ዮሐ 11፡41፡፡

5.የምንመገባቸውን የምግብ ዓይነቶች ለይቶ መወሰንና እናም የመመገቢያ ሰዓትን ማወቅ፡- ምግብ መጠጥ ኃጢአት ምንጮች ናቸው፤ በተለይም አብዝቶ መመገብ ልዩ ልዩ ዓለማዊ ነገሮችን እንድናስብ ከማድረጉ በተጨማሪ እንዳንጸልይና እንዳንሰግድ በማድረግ ይጫነናል፤ ስለዚህ የምንመገበው ለቁመተ ሥጋ ያህል ብቻ እና በሃያ አራት ሰዓት ውስጥ አንድ ጊዜ ወይም ሁለት ጊዜ ብቻ እንዲሆን ያስፈልጋል፡፡ ለዚህም ምሳሌ የሚሆኑን ሠለስቱ ደቂቅ እና ነቢዩ ዳንኤል ናቸው፤ዳን 21 ቀናት) ሳዝን ነበርኩ ማለፊያ እንጀራም አልበላሁም ሥጋና ጠጅም በአፌ አልገባም ሦስቱም ሳምንት እስኪፈጸም ድረስ ዘይት አልተቀባሁም" (ዳን 10፡2-4)፡፡

6. ለሱባዔ በወሰንባቸው ጊዜያት ከማንኛውም ዓለማዊ ጉዳይ ጋር ያለንን ግንኙነት ሙሉ ለሙሉ ለማቋረጥ መወሰን፡- ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሥርዓተ ጸሎትን ሲያስተምረን "አንተ ግን ስትጸልይ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በሥውር ላለው አባትህ ጸልይ በሥውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል“ (ማቴ 6፡6) ብሎ እንደነገረን በሱባዔ ጊዜ መገናኘት ያለብን ከእግዚአብሔር ጋር ብቻ ነው፤ ማንኛውም ጉዳያችን እና ማንነታችንም ሳይቀር በእርሱ እጅ መውደቅ አለበት፡፡

የልብ ሱባዔ እኖዲሆን የልብ ጸሎት እንድንጸልይ እግዚአብሔር ይርዳን!!!!

መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍያለው
ዘመካኒሳ ሚካኤል
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Audio
ሐዋርያት ያስተማሩት እውነተኛ ሀይማኖት 
                                                  
Size:- 60MB
Length:-2:58:02
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
Forwarded from 💎Super📣ፕሮሞሽን
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእናቷ ማህፀን ሳለች ከሞት ያስነሳችው ሰው ማነው?
2024/11/15 17:44:17
Back to Top
HTML Embed Code: