Telegram Web Link
7ኛ ዙር ዓመት 4ኛ ሳምንት ማሕሌተ ጽጌ
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ሥርዓተ ማኅሌት ዘዘመነ ጽጌ "፬ኛ ሳምንት" "በዓለ ቅዱስ ቴዎፍሎስ ሊቀ ጳጳሳት፣ ወሮማኖስ ሰማዕት" "ጥቅምት ፲፰"

የማን ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።

መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለአፉክሙ ዘማዕጾሁ ሰላም፤ጽጌያቲሁ ሥላሴ ለተዋህዶ ገዳም፤መንገለ አሐዱ አምላክ ንዋየ መጻኢት ዓለም፤ወልጡ አምልኮትየ በጸጋክሙ ፍጹም፤እምአምልኮ ጣኦት ግሉፍ አሐዱ ድርኅም።

ዚቅ
መዓዛሆሙ ለቅዱሳን ከመ ጽጌ ደንጐላት፤ወከመ ሮማን ዘውስተ ገነት፤ይትፌሥሑ ጻድቃን የውሃን ውሉደ ብርሃን፤በትፍሥሕት ዔሉ ውስተ
ማኅሌተ ጽጌ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ ጽጌ ፀዓዳ ወቀይሕ፤አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ በዕለተ ተአምር ወንጽሕ፤ንዒ ርግብየ ትናዝዝኒ እምላህ፤ወንዒ ሠናይትየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ፤ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩሕ፡፡

ወረብ
እንዘ ተሐቅፊዮ ለሕጻንኪ እንዘ ተሐቅፊዮ አመ ቤተ መቅደስ ቦእኪ/፪/
ንዒ ርግብየ ምስለ ገብርኤል ፍሡሕ ወሚካኤል ከማኪ ርኅሩኅ/፪/

ዚቅ
ንዒ ርግብየ አግዓዚት ከመ ጎኅ ሠናይት፤ታቦተ መቅደስ ቅድስተ ቅዱሳን፤ዕፀ ጳጦስ ደብተራ ፍጽምት ማኅደረ መለኮት።

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ ዘየኃቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኵሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ፡፡

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቈ ባሕርይ/፪/
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ/፪/

ዚቅ
ሰአሊ ለነ ማርያም፤አክሊለ ንጹሐን፤ብርሃነ ቅዱስ
ማኅሌተ ጽጌ
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ፤ወፈድፋደሰ በላዕለ ኃጥአን ነግሠ፤እስመ አንሥአ (አሕየወ) ሙታነ ወሕሙማነ ፈወሰ፤ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ፤ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ፡፡

ወረብ
ተአምረ ፍቅርኪ ማርያም በማኅበረ ጻድቃን ተወደሰ ተአምረ ፍቅርኪ/፪/
ቦ ዘይቤ አጽገየ ዘየብሰ ወቦ ዘይቤ አድባረ አፍለሰ/፪/

ዚቅ፡
ይዌድስዋ ኲሎሙ ወይብልዋ፤እኅትነ ነያ፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤በሰማያት ኲሎሙ መላእክት ይኬልልዋ፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ፤ወበምድር ኲሎሙ ቅዱሳን ይቄድስዋ፤ካዕበ ይብልዋ ሐዳስዩ ጣዕዋ።

ማኅሌተ ጽጌ
ለምንት ሊተ ኢትበሊ እምአፈ ኃጥእ ውዳሴ፤ይበቍዓኒ ዘብየ እምአፈ ጻድቃን ቅዳሴ፤ጽጌ መድኃኒት ማርያም ዘሠረፅኪ እምሥርወ እሴ፤እመ ተወከፍኪ ኪያየ አባሴ፤ተአምረኪ
ወረብ
ለምንት ሊተ ኢትበሊ ድንግል ውዳሴ እምአፈ ኃጥእ/፪/
ይበቊዓኒ ዘብየ ቅዳሴ እምአፈ
ዚቅ
አዘክሪ ለኃጥአን ወአኮ ለጻድቃን፤አዘክሪ ለርሱሐን ወአኮ ለንጹሐን።

ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ሐልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሓን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኲሉ ፍኖታ፡፡

ወረብ
ብክዩ ኅዙናን ሐልየክሙ ስደታ ለማርያም/፪/
ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ተዓይል/፪/

ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤አድባራተ ዔልኪ ከመ ዖፍ፤እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጽፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ።

ወረብ
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/፪/
እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጽፍ እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/፪/


🌻መዝሙር🌻

ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት ቆመ በረከት፤ናሁ ጸገዩ ጽጌያት፤ናርዶስ ፈረየ በውስተ ገነት፤ቀንሞስ ቀናንሞስ ከርካዕ፤ምስለ ዕንጐታት ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ፤ነአኵቶ ለዘጸገወነ ሠናይቶ፡፡

አመላለስ
ቀንሞስ ቀናንሞስ ከርካዕ ምስለ ዕንጐታት ክርስቶስ ሠርዓ ሰንበተ/፪/
ነአኵቶ ለዘጸገወነ ሠናይቶ/፪/

ዓራራት
በጊዜሁ ኀለፈ ክረምት፤በጊዜሁ ቆመ በረከት፤እግዚአ ለሰንበት አኰቴተ ነዐርግ ለመንግሥትከ፤ምድረ በጽጌ አሠርጎከ።

ዕዝል
ስብሐት ለአብ ለአኃዜ ኵሉ ዓለም፤ስብሐት ለወልድ ለዘቀደሳ ለሰንበት፤ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ ለዘአሠርገዋ ለምድር በጽጌያት።

ሰላም
ተሣሐልከ እግዚኦ ምድረከ፤ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሃሌ ሃሌ ሉያ ሐረገ ወይን፤እንተ በምድር ሥረዊሃ ወበሰማይ አዕፁቂሃ ሐረገ ወይን፤እንተ በሥሉስ ትትገመድ፤ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት ሐረገ ወይን፤ሲሳዮሙ ለቅዱሳን ሐረገ ወይን፤ሠርዓ ሰንበተ በቃሉ፤ወጸገወ ሰላመ ለኵሉ።

የዕለቱ ምንባባት
ሮሜ ፯፥፩-፲፬
ራእየ ዮ ፳፩፥፳፩-ፍ:ም
ግብ:ሐዋ፳፪፥፩-፮

የዕለቱ ምስባክ
አንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ፤
ወአንተ ገበርከ አድባረ ምድር ኵሉ፤
ክረምተ ወሐጋየ ዘአንተ ፈጠርከ።መዝ ፸፫፥፲፯

የዕለቱ ወንጌል
ማቴዎስ ፮፥፳፭-ፍ:ም
ቅዳሴ ዘእግዚእትነ

➾ሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)🙏🙏🙏
 @EotcLibilery @EotcLibilery @EotcLibilery
"በሰማዕታት ሞት ሃይማኖት ትጠበቃለች፣ እምነት ታድጋለች፣ ቤተ ክርስቲያን ትጠነክራለች። የሞቱት ሲያሸንፉ አሳዳጆቹ ደግሞ ተሸናፊዎች ይሆናሉ...የሰማዕታት ሞት በራሱ ለሕይወታቸው ሽልማት ነው።"

ቅዱስ አምብሮስ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
ከምን ዓይነት ነገር መላቀቅ እንዳለብህ ታዉቃለህ ??

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ ምድራዊ ምኞት ምን ያህል አስከፊ እንደሆነና እንዴት ከዚህ ነገር ነፃ መውጣት እንዳለብን እንዲህ በማለት ይመክሩናል፦

"ወዳጄ ከምድራዊ ምኞትህ ተላቀቅ ከምን አይነት ነገር መራቅ እንዳለብህ ታውቃለህ? ከምድራዊ ፍላጎት ከመሳሰሉት ራቅ ፍፁም የመንፈስ ነፃነት እንዲኖርህ ከፈለክ ከምድራዊ ምኞቶችህ ተላቀቅ።

በእርጋታና በግልጽነት ላውጋህ እጅግ አብዝተህ የምትጨነቅባቸው ልብህን የተቆጣጠሩት ታላላቅ ምድራዊ ተስፋዎች አሉህ።

እነኚህም ሃሳብህን ሁሉ ይቆጣጠሩታል ብቻህን በምቶንበት ጊዜ በምናብ ይመጡብሃል በምትተኛ ጊዜ ህልምህ ሁሉ ይህ ይሆናል ልትክዳቸው የማትችለው ነገር ግን የምታውቃቸው ምድራዊ አላማዎች አሉህ። ተፈላጊነት እንዲኖርህ ትመኛለህ፣ ስልጣን እንዲኖርህና፣ ኃያል እንድትሆን፣ ዕውቅና እንዲኖርህና ስምህ ከጽንፍ እስከ አጽናፍ እንዲናኝ ትፈልጋለህ።

በሀብት፣ በምድራዊ ስልጣን፣ በዕውቀት በማዕረግና በመልክ ዝነኛ የመሆን ተስፋ አለህ ፣ በመኖሪያ ቤት፣ በምግብ፣ በልብስና በሰውነት ደስታን በሚሰጡ ነገሮችም ተስፋ አለህ።

ዓለም በአንተ እንጂ አንተ በዓለም እየኖርክ አይደለም። ስለዚህ አንተነትህ በዚህ ምድራዊ ተስፋ የታጠረ ነው። መንፈስህም ከስጋ ፍላጎቶች መራቅን ትመኛለች ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስ በሥጋ ላይ ይመኛልና። (ገላ.5፥17) እነዚህ ሥጋዊ ተስፋዎችና ፍላጎቶች ስኬታማ ስለማይሆኑ ግራ ትጋባለህ።

ይህን በእርግጥ ቅሬታን ያመጣብሃል።
እነዚህን ነገሮች ሁሉ ትናፍቃለህ ነገር ግን ናፍቆትህ አያስደስትህም። ስለዚህ ለምኞትህ ሁሉ ማስተካከያ ታበጅለት ይሆናል ምናልባትም ይጠቅሙኛል የምትላቸውን ሰዎች ማግኘት፣ በምኞትህ ዙሪያ የተጻፈ መዛግብት ማገላበጥ ትፈልግ ይሆናል በዚህም ላይ ታች ስትል ምኞትህን ለማሳካት ትታገላለህ እንዲሆን ሌላ ዘዴ ልትፈጥር ትችላለህ ይሁን እንጂ ሳይሳካልህ ቀርቶ በሃሳብና በጥረት ትታክታለህ ከዚያም ትበሳጫለህ። ከዚህ የከፋው ነገር በእነዚህ ምኞቶችና ተስፋዎች ስኬታማ አለመሆን ምክንያት ለከፋ ሕይወት መዳረግህ ነው።

እንደምትሰለች አውቃለሁ አዘንኩልህ እስከመቼ ድርስ በምኞት ማዕበል ውስጥ ትኖራለህ? የምትመኘውን ባገኘህ ጊዜ ደስተኛ ትሆናለህ ይህ ደስታ ስለማያረካህ ሌላ አዲስ ደስታን እንድትመኝ ያደርግሃል። ልክ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ "ከዚህ ውሃ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል" (ዮሐ.4፥13 ) እንዳለው እርካታ አይኖርህም።

ስለዚህ ውድ ወንድሜ ነገሩን በእርጋታ ከአንተ ጋር ለመነጋገር እፈልጋለሁ። "አለሙም ምኞቱም ያልፋል" (1ኛ ዮሐ.2፥17) ታዲያ ይህን ቃል ካወክ ለምን አለማዊ ፍላጎቶችን ለማግኘት ትታክታለህ? አንተ ልክ እንደ እኔ ለመሬት እንግዳ ነህ። ዓለም የሚያልፍበት አንተም የምትጠፋበት ጊዜ ይመጣል ልክ ከእናትህ ማህጸን ራቁትህን እንደመጣህ እንደዚሁ ራቁትህን ትመለሳለህ።(ኢዮ. 1፥21)

ዓለምን ከነክብሯ ከነሀብቷና ከነስሟ ለቀሃት እንድትሄድ በመገደድ እንደ ማንኛውም ሰው ወደ መሬት ትወርዳለህ። ከዚያም ከዓለም ያገኘኽውን ደስታ ታወቂነት ወይም ምንም ይሁን ምን ሥጋህን ከሞት ሊከላከልልህ አልያም ሥጋን ከሚበሉት ትል ሊከላከልልህ አይችልም። በፍርድ ቀን ከዓለም ሀብትና ንብረት ውጭ በእግዚአብሔር ፊት ትቆማለህ። መልካም ይሁን ክፉ የሰራኸው ሥራ እንጂ የዓለም ቁሳዊ ነገር አይከተልህም።

ስለዚህ ውድ ወንድሜ ምኞትህንና ተስፋህን በዓለም ላይ በማድረግ መታወክህ ለአንተ ጥሩ አይደለም ይህችን ምድር እሾህንና አሜኬላን እንዳበቀለችልህ ትዘነጋለህን!!! ከእኛ በፊት የነበሩና ምድርን ሊረግጧት የማይገባት የቅዳሳን አባቶችና እናቶች አሠራርና ፈለግ ተከተል ቅድስናቸውን ያገኙት ይህችን ዓለም በመውደድ ሳይሆን በመናቅ ነበር ሁኔታዎች ሁሉ ተመቻችተውላቸው ሳለ በዓለም ስላሉ ነገሮች ለማንኛውም ጉጉት አልነበራቸውም ።

ውድ ወንድሜ አሁንም ምኞት አሉህ መዝገብህ ባለበት ልብህ ደግሞ በዚያ ይሆናልና (ማቴ.6፥21) የሥጋን ምኞቶችን ስለተቆራኘ መንፈሳዊ ነገሮች በአንተ አመለካከት ዋጋቸውን ያጣሉ ይህ የክብር ጌታ እንደተፈተነው ዓይነት ፈተና ነው። (ማቴ.4፥8-9)

አሁን አስተውል እነዚህን ነገሮችን ብትይዝ በጥሩ ምኞት ያላሰርካት ነፍስህን ብታጣ ጥቅሙ ምንድን ነው? ነፍስህ ነጻነትን ትሻለች።

ከስጋ ምኞት ተላቀን የመንፈስ ፍሬ የሆኑትን " የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣  እምነት፣ የውሃት፣ ራስን መግዛት ነው።"(ገላ.5፥22) እንዳለው ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ እነዚህን ገንዘብ አድርገን እንድንኖር እግዚአብሔር አምላክ ይርዳን!!

(የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ "የመንፈስ ነጻነት "ከሚለውና በዲ/ን ደስታ ፍፁም ከተተረጎመው መጽሐፍ ላይ የተወሰደ። ምክር ወተግሳፅ እንዳቀረበው)
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
የቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ
*
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን 
ቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ መደበኛ ስብሰባ በዓመት ሁለት ጊዜ እንዲሆን በፍትሕ መንፈሳዊ አንቀጽ 5 ቁጥር 164 ላይ በተደነገገው መሠረት ምልዓተ ጉባኤው የመክፈቻውን ሥርዓተ ጸሎት ከፈጸመበት ከጥቅምት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን ሲያካሂድ ሰንብቷል፡፡
በመሆኑም ምልዓተ ጉባኤው ስለ ቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እድገት፣ እየተከሰቱ ስላሉት ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎች እንዲሁም ስለ ሀገር ሰላምና አንድነት በስፋት በመወያየት ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን ጠቃሚ የሆኑ ውሳኔዎችን አሳልፏል፡፡
በዚሁ መሠረት፡- 
1. የ2016 ዓ.ም. የመንበረ ፓትርያርክ ዓለም አቀፍ አጠቃላይ መንፈሳዊ ጉባኤ ያሳለፈውን የጋራ የአቋም መግለጫ በመመርመርና አስፈላጊውን ማሻሻያዎች በማድረግ የበጀት ዓመቱ የቤተ ክርስቲያናችን የሥራ መመሪያ እንዲሆን ጉባኤው አጽድቆታል፡፡

2. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን መዋቅራዊ አደረጃጀቱን የበለጠ ተደራሽ በማድረግ ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን መወጣት ትችል ዘንድ በአዲስ እንዲደራጁ ተጠንተው የቀረቡትን የአህጉረ ስብከት ይደራጅልን ጥያቄዎችን በመመርመር፡-
ሀ. የሸገር ከተማ ሀገረ ስብከት፣ 
ለ. የሰሜን ጎጃም ዞን ሀገረ ስብከት 
ሐ. የጎፋና ባስኬቶ ዞን ሀገረ ስብከት 
መ. የምሥራቅ ጉራጌ ዞን ሀገረ ስብከት እራሳቸውን ችለው ሀገረ ስብከት ሆነው ተደራጅተው እንዲቀጥሉ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡  

3. ቤተ ክርስቲያናችን የመንፈሳዊ ኮሌጆቿን ቁጥር ከፍ በማድረግ የአገልጋይ መምህራንን ቁጥር ለማሳደግ ባላት እቅድ መሠረት ተጠንተው ከቀረቡት መካከል በ2016 ዓ.ም. የበጀት ዓመት በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ደብረ ብርሃን ከተማ ላይ፣ በደቡብ ጎንደር ሀገረ ስብከት ደብረ ታቦር ከተማ ላይ ሁለት መንፈሳዊ ኮሌጆች እንዲቋቋሙ፣ በማዕከላዊ ጐንደር ሀገረ ስብከት ርእሰ ከተማ ውስጥ ለሚገኙት የምስክር ጉባኤ ቤቶች በኮሌጅ ደረጃ በጀት እንዲመደብላቸው እና በከንባታ ሐድያ ስልጤ ሀገረ ስብከት ሆሣዕና ከተማ ላይ አንድ የካህናት ማሠልጠኛ እንዲከፈት ጉባኤው ወስኗል፡፡ 
 
4. ቤተ ክርስቲያናችን ከውስጥና ከውጭ እየደረሱባት ያሉት ከፍተኛ የሆኑ ፈተናዎችን ተቋቁማ ሕልውናዋን አስከብራ መቀጠል ትችል ዘንድ ፡-

ሀ. ውስጣዊ ችግሮቻችን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በጠበቀ በውይይት እንዲፈቱ፣

ለ. ውጫዊ ችግሮችንና የመብት ጥሰቶችን በተመለከተ በችግሮቹ ዙሪያ ከሚመለከታቸው መንግስታዊ ተቋማት ጋር በመነጋገር ችግሮቹ እንዲፈቱ እና የቤተ ክርስቲያናችን መብትና ሕልውና ተጠብቆ እንዲቀጥል እንዲደረግ፣

ሐ. ለቤተ ክርስቲያናችን ሕልውና አደጋ የሆኑና ሊሆኑ የሚችሉ ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን አስመልክቶ በአግባቡ ተጠንተውናበማስረጃ ተተንትነው ከመፍትሔ ሐሳብ ጋር እንዲቀርብ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
  
5. ትላንት በሰሜኑ ኢትዮጵያ የሀገራችን ክፍል በተካሄደው ጦርነት በጠፋው የሰው ሕይወትና በወደመው ንብረት ከደረሰብን ሐዘን እኛ ኢትዮጵያውያን ገና ሳንጽናና ዛሬም በሀገራችን ኢትዮጵያ በበርካታ አካባቢዎች የተከሰቱት ጦርነቶች፣ ግጭቶችና አለመግባባቶች እያስከተሉት ያለው የንጹሐን የሰው ሕይወት መጥፍትና የንብረት ውድመት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤን በእጅጉ አሳዝኖታል፡፡ በመሆኑም ችግሩ በውይይትና በስምምነት እንዲፈታ የፌዴራልን የክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም በግጭቱ ተሳትፎና ድርሻ ያላችሁ በሁሉም አካባቢ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን በሙሉ የበኩላችሁን ሚና በመወጣት እናት አገራችን ኢትዮጵያ ሰላሟና አንድነቷ ተጠብቆ ይቀጥል ዘንድ ቅዱስ ሲኖዶስ ከአደራ ጭምር በድጋሚ ጥሪውን ያቀርባል፡፡   

6. በሀገራችንና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየተከሠተ ያለው ችግርና ፈተና የሚወገደው ሁሉም ኢትዮጵያዊያን በአንድነትና በሕብረት ለችግሮቹ መፈታት ድርሻ እንዳለን አውቀን እንደየእምነታችን አስተምህሮ በጸሎትና በምሕላ ወደ አምላካችን ወደ እግዚአብሔር በንስሓ መመለስ መሆኑን ቅዱስ ሲኖዶስ በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም ስለ ሀገራችን ሰላምና ስለ ቤተ ክርስቲያናችን አንድነት በመላው ዓለም በሚገኙት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት በሙሉ ከህዳር 15 ቀን 2016 እስከ ታህሣሥ 27 ቀን 2016 ዓ.ም. ድረስ ጸሎትና ምሕላ እንዲፈጸምና መላው ሕዝበ ክርስቲያንም በአንድነትን በሕብረት ከላይ በተጠቀሱት ዕለታት በቤተ ክርስቲያን በመገኘት የበረከቱና የሥርዓተ ጸሎቱ ተሳታፊ እንዲሆኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኖ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡  

7. የቤተ ክርስቲያናችንን ታሪክና ለሀገረ መንግስት ምሥረታና እድገት ያበረከተችውን አስተዋጽኦ በማዕከል ደረጃ በማስረጃ አስደግፎ በመጻፍና በማደራጀት ትውልዱ እንዲረዳው በማድረግ ለቤተ ክርስቲያናችንና ለሀገራችን የሕልውና አደጋ የሆነውን የሐሰት ትርክት መከላከል ይቻል ዘንድ የዝግጅት ሥራው በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል በሊቃውንት ጉባኤ የበላይ ተቆጣጣሪነት ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንንና የታሪክ ተመራማሪዎችን በማሳተፍ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡

8. ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን በሀገራዊ የምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖራት ተሳትፎና ሚና በተመለከተ ጉባኤው በስፋት የተወያየ ሲሆን ሀገራዊ ምክክሩ ሀገራዊ ችግራችንን እንደሚፈታና በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚነገሩትን የሐሰት ትርክቶች ሁሉ የሚታረሙበት እንደሚሆን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በምክክር ሂደቱ ላይ ስለሚኖረን ተሳትፎና ሚና በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ እንዲፈጸም ሆኖ የምክክር ኮሚሽኑም ይህን የቤተ ክርስቲያናችን እቅድ በመርሐግብሩ በማካተት ቤተ ክርስቲያናችን የድርሻዋን እንድትወጣ እድሉን እንዲያመቻችልን ጉባኤው ጥሪውን ያቀርባል፡፡

9. የመረጃ ቋት መዋቅራዊ አደረጃጀትን በሁሉም ክልል አህጉረ ስብከት ደረጃ በማቋቋም እና እለት እለት በቤተ ክርስቲያናችን ላይ የሚከሰቱትን ችግሮችና የመብት ጥሰቶች በመረጃና ማስረጃ አስደግፎ ለዋናው ማዕከል የመረጃ ቋት በፍጥነት ተደራሽ በማድረግ በአንዱ ቦታ ችግር ሲደርስ በመላ ሀገሪቱ እና በውጭው ክፍለ ዓለማት ባሉት አህጉረ ስብከት በአንድነት ድምፅ መሆን ይቻል ዘንድ ተጠሪነታቸው ለዋናው ማዕከል የሆኑ የመረጃ ቋት ማዕከላት በሁሉም አህጉረ ስብከት ተቋቁመው ወደሥራ እንዲገቡ ጉባኤው ወስኗል፡፡ 

10. የቤተ ክርስቲያናችን ሀብትና ንብረት የሆኑት ቅዱሳት መጻሕፍትን፣ የሚዳሰሱና እና የማይዳሰሱ ቅርሶችንና በአጠቃላይ ንዋየ ቅድሳቶቻችን ግለሰቦች እና ተቋማት በሕገወጥ መንገድ አትመውና አሳትመው በማሠራጨትና ትክክለኛ ቅጅውን አዛብቶ በማተም ቤተ ክርስቲያናችን ለሐሰተኛ ትርክት እንድትዳረግ በማድረግ ከፍተኛ የሆነ በደል እየተፈጸመባት መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ በመሆኑም በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤቱ በኩል የተጀመረው የአዕምሯዊ ንብረት ምዝገባ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እና የቤተ ክርስቲያኒቱ መብትና ጥቅም እንዲከበር ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
11. በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት አህጉረ ስብከት ሥር የተቋቋሙት አብያተ ክርስቲያናት የሚተዳደሩበት እራሱን የቻለ ሕግና ደንብ ባለመኖሩ በመዋቅራዊ አስተዳደራችን ላይ ከፍተኛ ክፍተት ሲፈጥር የቆየ መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ ለውጭው ክፍለ ዓለማት አህጉረ ስብከት እና አብያተ ክርስቲያናት እራሱን የቻለ መተዳደሪያ ደንብ ተዘጋጅቶ የፀደቀ በመሆኑ በውጭው ክፍለ ዓለማት በሚገኙት ሁሉም አህጉረ ስብከትና አብያተ ክርስቲያናት በጸደቀው መተዳደሪያ ደንብ ብቻ ሥራቸውንና አገልግሎታቸውን እንዲያከናውኑ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡ 

12. የቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ ኮሌጆች ወጥ የሆነ የጋራ መተዳደሪያ ደንብ እንዲኖራቸው በማሰብ ጉባኤው አስቀድሞ ተዘጋጅ እንዲቀርብ ባዘዘው መሠረት ተዘጋጅቶ የቀረበውን ረቂቅ መተዳደሪያ ደንብ መርምሮ በማጽደቅ በሁሉም በተቋቋሙትም ሆነ ወደፊት በሚቋቋሙት  ኮሌጆች ሥራ ላይ እንዲውል ጉባኤው ወስኗል፡፡
13. ገዳማትና ገዳማዊ ሕይወት፣ የአብነት መምህራን እና ትምህርት ቤቶች እንዲሁም በአጠቃላይ ክብረ ክህነት እና ትምህርተ ኖሎት ተጠናክሮ እንዲቀጥል በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል እየተጠና አስፈላጊው ሁሉ ድጋፍና ክትትል እንዲደረግ ጉባኤው ወስኗል፡፡

14. የቤተ ክርስቲያናችን ሕጋዊ፣ ተቋማዊ፣ ሃይማኖታዊና ማህበራዊ መብቶች መከበርና የእምነት ነጻነታችንን እና የምእመናንን ደኅንነት በሕግ አግባብ ማስከበር ይቻል ዘንድ ልክ እንደ ዋናው መሥሪያ ቤት በሁሉም ክልሎች ውስጥ ባሉት አህጉረ ስብከት የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ሥራ እንዲገባ ጉባኤው ወስኗል፡፡

15. ወጣቱ ትውልድ በእምነቱ ጸንቶና በቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምህሮ በእውቀትና በሥነምግባር ይታነጽ ዘንድ በሰ/ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ተዘጋጅቶ የቀረበው ሥርዓተ ትምህርት በሁሉም የቤተ ክርስቲያኒቱ መዋቅር እና አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ተግባራዊ እንዲሆን ጉባኤው ወስኗል፡፡

16. የ2016 ዓ.ም. ዓመታዊ በጀትን አስመልክቶ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በኩል ተዘጋጅቶ የቀረበውን የበጀት ድልድል ጉባኤው መርምሮ በማጽደቅ ሥራ ላይ እንዲውል ወስኗል፡፡

17. የቤተ ክርስቲያናችን የመልካም አስተዳደር ችግሮች የሚፈቱት እና የልማት ተቋማት የሚጠናከሩት ዘመኑን የዋጀ መዋቅራዊ አደረጃጀት በመፍጠር እና በእቅድ ተደግፎ በእውቀት ላይ የተመሠረተ የሀብትና የንብረት አስተዳደር ማስፈን ሲችል መሆኑን ጉባኤው በጽኑ ያምናል፡፡ 

በመሆኑም በባለፈው ጉባኤ የጸደቀው የ10 ዓመት የመሪ እቅድ  በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አስፈላጊው ድጋፍና ክትትል እየተደረገለት የመሪ ዕቅዱ አፈጻጸም እንዲቀጥል ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን


             አባ ማትያስ ቀዳማዊ 
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ
ጳጳስ ዘአክሱም  ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ጥቅምት ፲፱ ቀን !)0፮ ዓ.ም.
  ኢትዮጵያ አዲስ አበባ
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
ከሰው ለተለዩት
✍🏽 ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ እንደጻፉት

የአንቀጸ ብፁዓን ተራራ፥ ወንጌል የተጀመረችበት፣ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ መምህርነቱን ለቤተ ክርስቲያን የገለጠበት ስፍራ ነው። ዘጠኙን ብፁዓን በስብከቱ የገለጣቸው በዚህ ተራራ ላይ ነው። ትምህርቱን ለመስማት በጉባኤው ለመገኘት ወደ ተራራው የወጡ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም ደቀ መዛሙርቱ ደግሞ ከሁሉ ይልቅ ቀርበው ይሰሙት ነበር። “ሕዝቡንም አይቶ ወደ ተራራ ወጣ በተቀመጠም ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደ እርሱ ቀረቡ” ማቴ 5፥1 እንዲል። እሱ ከተራራ ላይ ወጥቶ ከተቀመጠ ማን ከተራራው በታች ይቀራል ብለው እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚነሱ ደቀ መዛሙርቱ ሁሉ ወደ ተራራ ወጥተው በተቀመጠበት ስፍራ ሲፈልጉት ይኖራሉ።

ኢትዮጵያ ሀገራችን ፍጹማን የክርስቶስ ደቀ መዛሙርት የበዙባት አገር ናት። ብዙዎቹ ዓለምን ንቀው ስብከቱን እየሰሙ ለመኖር ወደ ተራራው ይወጣሉ። እሱ ከፍ ካለው ቦታ ላይ ይቀመጣል። እነሱ ቃሉን ለመስማት እንዲመቻቸው ዝቅ ብለው ተቀምጠው “በመንፈስ ድሆች የሆኑ ብፁዓን ናቸው” ሲል ይሰሙታል። ጠቢባን ጥበባቸውን፣ ባለጠጎች ሀብታቸውን፣ የሕዝብ አለቆች ሹመታቸውን ትተው ይከተሉታል። በዚያ ዘመን ከክርስቶስ ጋር ወደ ተራራው ወጥቶ፣ ስብከቱን ሰምቶ ከአይሁድና ከአጋንንት በቀር ወደ ኋላ የተመለሰ የለም ማቴ 4፥10፣ ዮሐ 6፥66።

ከተራራ ወደ ተራራ ያመላልሳቸዋል፤ በትንሹ ተራራ ያስጀመራቸውን ትምህርት ወደ ረዥም ተራራ አውጥቶ ምሥጢሩን ያብራራላቸዋል። በመጀመሪያው ተራራ ላይ ደቀ መዝሙርነትን ያስጀምራቸዋል፤ በመጨረሻ የሚገናኙበት ተራራ ላይ አካሉ ባደረጋት ቤተ ክርስቲያን ላይ ይሾማቸዋል። ትንሹ ተራራ ያልኋችሁ የአንቀጸ ብፁዓን ተራራ ነው። ረዥሙም ተራራ ደብረ ታቦር ነው። የመጨረሻ ክከርስቶስ ጋር የተለያዩበት ተራራም ደብረ ዘይት ነው። በትንሹ ተራራ በአንቀጸ ብፁዓን በቃል የነገራቸውን ወንጌል ምሥጢሩን በዐይናቸው እንዲያዩት ያደረገው በደብረ ታቦር ተራራ ላይ ነው። በቤተ ክርስቲያን ላይ ካህናት አድርጎ በአንብሮተ እድ የሾማቸውም በደብረ ዘይት ነው ሉቃ 24፥50።
የቤተ ክርስቲያን ደቀ መዝሙርነቷ ዛሬም ልክ እንደ መጀመሪያው ነው። አንዳንዶቹ በልባቸው፤ አንዳንዶቹም በእግራቸውም በልባቸውም ከተራራ ወደ ተራራ እየተዘዋወሩ በዕዝነ ነፍሳቸው ትምህርቱን ይሰማሉ። በዚህ ሰሙን መታሰቢያቸውን ያከበርንላቸው አቡነ አረጋዊ ደብረ ዳሞ ወጥተው መኖር የፈለጉት በተራራ ላይ የሰበካትን ወንጌል በልባቸው እያመላለሱ ለመኖር ነው። ከተራራው ጫፍ ወጥተው በተቀመጡ ጊዜ ደቀ መዛሙርቱ ወደርሱ ቀርበው ስብከቱን ሲሰሙ ያገኟቸዋል። ቀርበው ሲሰሙ ይውላሉ። በሌላ ጊዜ ደግሞ ደብረ ዳሞ ደብረ ታቦርን ይሆንላቸዋል፤ ጌታ ልብሱ ነጭ ሆኖ፣ ሙሴና ኤልያስም ከሱ ጋር ሲነጋገሩ፣ አብ በደመና ሁኖ “የምወደው ልጄ” ብሎ ሲመሰክርለት ይሰማሉ። በተመስጦ ይዋጣሉ። ለሰው ከተደረገው የእግዚአብሔር ፍቅር የተነሣ ደንግጠው ዝም ይላሉ።

በነገራችን ላይ በቅዱስ ወንጌል ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የነበረባቸውን ቦታዎችና ታሪኩን ሊያስታውሱን የሚችሉ ኩነቶችን ሊገልጡልን የሚችሉ ምሳሌዎችን ማድረግ ለአንዳንዶቹ እንደሚመስላቸው ግብዝነት አይደለም። ራሱ ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ አንዳንድ ነገሮችን ያደረገው ነቢያት ያደርጉት በነበረበት መንገድና ቦታ ነው። ሙሴ ወደ ተራራ ወጥቶ እንደጸለየ እሱም ይህንኑ አደረገ ዘዳ 9፥9፣ ማቴ 4፥1። ኤልያስ በኮሬብ ፈፋ ውስጥ ያድር እንደነበረ እሱም በኤሌዎን ዋሻ ውስጥ ያድር ነበረ።

ከሁሉም ይልቅ የሚደንቀኝ ጌታ የሞት ፍርሃት በያዘው ሰው አምሳል የጸለየባት የጌቴሴማኒ ምሥጢር ነው። ከረዥም ዓመት በፊት በዚህ ስፍራ ይስሐቅ “አባቴ ሆይ በጉ ወዴት አለ?” ዘፍ 22፥7 ብሎ አብርሃምን የጠየቀው በዚህ ስፍራ ነበር። ተመልከቱ ይስሐቅ የአባቱን ፈቃድ መፈጸሙ አይቀርም፤ ነገር ግን ሞት እንዲቀርለት የፈለገ ይመስላል። ኢየሱስ ክርስቶስም መሥዋዕትነቱ የሚያስፈልገን ስለሆነ እንዳይቀር የሱም የባሕርይ አባቱ የአብም ፈቃድ ነው። ነገር ግን “አባት ሆይ ይህች ጽዋዕ ከኔ ትለፍ” ብሎ ይጣራል። እንዴት ያለ ነገር ነው?

ለማንኛውም የቦታና የሁኔታዎች መመሳሰል የሰውን ልብ በጊዜውና በቦታው እንዳለ ሆኖ እንዲረዳው ስለሚያደርግ ቅዱሳን ወደ ተራራ ወጥተው ገዳም አቅንተው በዐት ሠርተው የሚኖሩበት አንዱ ምክንያት ይህ ነው። ከዓለም ተለይተው ወደ ተራራው በወጡ ጊዜ በቀራንዮ ተራራ ላይ ሊቀ ካህናት ሆኖ ያገኙታል። በደብረ ዘይት ተራራ ላይ ሠያሜ ካህናት ሆኖ በካህናት በጳጳሳት ላይ እጁን እየጫነ ሲሾማቸው ይመለከቱታል። ከዚህ መውረድ አይሆንላቸውም።

ቅዱስ ጴጥሮስ “በዚህ መሆን ለኛ መልካም ነው” ብሎ የጠየቀው ጥያቄ ለነሱ ተፈጽሞላቸው ከተራራው ሳይወርዱ እንደ አባ አረጋዊ ያሉት በዚያው ጌታ እስኪመጣ ድረስ ሊኖሩ ከሞት ተሸሽገው የሚቀመጡበት መኖሪያቸው ያደርግላቸዋል። ከሰው ለተለዩት ከሰው የተለየ ነገር ያደርግላቸዋል። በዓለም ሳሉ ሞት እንዳያያቸው ይሸሽጋቸዋል። ሄኖክ ከሰዎች ተለይቶ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር አደረገ እግዚአብሔርም ስለወሰደ አልተገኘም ዘፍ 5፥24። ኢልያስን በእሳት ሠረገላ ቢጭነው፤ ጠላቶቹን እሳት ከሰማይ አውርዶ እንዲያስበላቸው ለማድረግ ሥልጣን ቢሰጠው ከሰው የተለየ ነገር አደረገ ብሎ እግዚአብሔርን ሊወቅሰው የሚፈልግ ማነው? ከሰው ተለይቶ ቢለምኑት እግዚአብሔር ከሰው የተለየ ጸጋን ይሰጣል።
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
#አበው_ስለ_እመቤታችን_እንዲህ_አሉ

"አምላክ ከንጉሥ ሔሮድስ ሴት ልጅ ቢወለድ ኖሮ አልጋ ወራሽ በሆነና ባልተሰደደ ነበር። እርሱ ግን የድሆች ልጅ የሆነችውን ድንግል መረጠ"
#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

"ታላቁ ተራራ ሆይ ታናሽዋ ብላቴና የተሸከመችህ ራስህን በሚቻላት መጠን አድርገህላት ነው ፣ ታላቁ እሳት ሆይ ታናሽዋ ብላቴና ተሸክማህ ያልተቃጠለችው ኃይልን ትችል ዘንድ አጽንተሃት ነው "
#ቅዱስ_ኤፍሬም_ሶርያዊ

"ይህ ዓለም የእግዚአብሔርን ልጅ በቀጥታ ከእግዚአብሔር አብ እጅ ለመቀበል የተገባ ሆኖ ስላልተገኘ ፣ ዓለም ከእርስዋ ይቀበል ዘንድ አንድያ ልጁን ለድንግል ማርያም እናት ትሆነው ዘንድ ሠጣት"
#ቅዱስ_አውግስጢኖስ

"ሔሮድስ የማይያዘውን ይይዝ ዘንድ ተነሣ ፣ ዓውሎ ነፋስንም በቤቱ አስገብቶ ሊዘጋ ታገለ"
#አባ_ጊዮርጊስ_ዘጋስጫ

"ጌታ ሆይ እናትህን ማን ብለን እንጥራት? እናት ብቻ እንዳንላት ድንግል ሆና አገኘናት ፣ ድንግል እንዳንላት ልጅ ታቅፋ አየናት። ጌታ ሆይ እናትህን ለመጥራት እንዲህ የሚያስቸግር ከሆነ አንተን ከቶ ምን ብለን እንጠራሃለን??"
#ቅዱስ_ኤፍሬም

(በ Deacon Henok Haile የተሰባሰበ)


@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
  [       ትእግስትን በተመለከተ  !    ]

ሥቃዩን ሁሉ ታግሠው ኖሩ  !

" የቀደሙ አባቶቻችን ጻድቃን ቅዱሳን በእምነታቸው የእሳቱን እቶን አቀዘቀዙት በዚያም በባዕድ ሀገር ባርነቱን መከራውን ሥቃዩን ሁሉ ታግሠው ኖሩ
እኛ ጥቂቱን መከራ እንኳ ያለመታገሣችን ምክንያቱ እምነታችን ጎዶሎ ስለሆነ ነው በዚህም ምክንያት ትዕግሥት ከእኛ ዘንድ የራቀ ሆነ አንተ የሰውን ገንዘብ ብታጠፋ እምነትንም ብታጎድል ወደ ወኅኒ ቤት ትጣላለህ በዚያም መከራን ትቀበላለህ እንዲሁ በእግዚአብሔር ባትታመንና ወደ ድፍረት ኃጢአት ብትገባ በነፍስህ ጽኑ መከራን ትቀበላለህ፡፡

ስለዚህ በእግዚአብሔር አምላክህ ዘንድ ዋጋ እንዳታጣ ትዕግሥትን ገንዘብህ አድርገህ ተመላለስ አስቀድመህ የፈጸምከውም የጽድቅ ሥራ ዋጋ እንዳያጣ ወደ ኋላ አትመልከት በሕይወትህም ለእግዚአብሔር የምትቀና በሰው ዘንድ የታመንህ ሁን"

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ  
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
በበረሓው ጉያ ውስጥ ከሚለው መጽሐፍ የተወሰደ ፦

አንድ ጊዜ  አባ መቃርዮስ  ከወንድሞች ጋር ወደ ግብጽ  ሲሔድ አንድ ልጅ ለእናቱ  << አንድ ሀብታም  አለ እርሱ ይወደኛል  እኔ እጠላዋለሁ ፤ አንድ ምስኪን አለ እርሱ ይጠላኛል እኔ እወደዋለሁ >> ብሎ ሲነግራት ሰማ ። ይህን ጊዜ  አባ መቃሪዎስ እጅግ ተደነቀ ። አብረውት የነበሩ ወንድሞችም  ምን እንዳስደነቀው ጠየቁት ። እርሱም ።<<በእውነት ባለጸጋ የተባለው ጌታችን ነው ። ነገር ግን እኛ አንወደዉም ።ምስኪን የተባለው ዲያብሎስ  ግን እኛን ይጠላናል እኛ ግን ክፋቱን እንወድለታለን ብሎ ነገራቸው ።
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ሥርዓተ ማኅሌት አመ ፳ወ፫ ለጥቅምት ጊዮርጊስ

የጥቅምት ጊዮርጊስ #ሥርዓተ_ማኅሌት ከሊቃውንቱ ጋራ አብረን ለማመስገን ይረዳን ዘንድ እንደሚከተለው ተዘጋጅቷ


የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ (ሥርዓተ ነግሥ)
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወይብጻሕ ቅድሜከ ገአርየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ወኢትሚጥ ገጸከ እምኔየ፤በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ እዝነከ ኀቤየ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ፤ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ፤ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤በአሐቲ ቃል።

መልክዐ ሥላሴ
ሰላም ዕብል ለንዋየ ውስጥ ምሕረትክሙ፤ትሩፋተ ገድል ኩኑኒ ሥላሴ አምጣነ ትሩፋት አንትሙ፤ሶበ ሖርኩሰ ከመ እሳተፍ ገድሎሙ፤ጊዮርጊስ ኢወሀበኒ መጠነ ነጥበ ጠል እምደሙ፤ወተክለሃይማኖት ከልአኒ ስባረ እምዓጽሙ።

ዚቅ
ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ወከመ ወሬዛ ኀየል መላትሒሁ፤ጒርዔሁ መዓርዒር አምሳሉ ዘወይጠል፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ሰማየ ወምድረ ዘአንተ ፈጠርከ፤ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ፤ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ቀደሳ ወአክበራ አዕበያ ለሰንበት፤ወአልዓላ እምኲሉ ዕለት፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ወኲሉ ይሴፎ ኪያከ።

አመላለስ
ወመኑ መሐሪ ዘከማከ/፪/
ወኲሉ ይሴፎ ኪያከ/፬/

ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
በ፪ ልዑለ ረሰዮ ለመሠረትኪ፤ዓረፋትኪ ዘመረግድ፤ደቂቅኪ ምሁራን በኀበ እግዚአብሔር፤ቆዓ ትጼኑ ቆዓ ጽጌ ወይን፤ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት፤ጽዮን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ጽጌ ደንጐላት ዘውስተ ቆላት።

መልክአ ጊዮርጊስ
ሰላም ለዘባንከ ዘተሞጥሐ ምንዳቤ፤ጊዜያተ ምዕተ መቅሰፍተ ጥብጣቤ፤ጊዮርጊስ ምዑዝ እምጼና ሐንክሶ ወከርቤ፤ኅሊናየ ዘተመነየ ወልሳንየ ዘይቤ፤እንበለ አጽርኦ ፍጡነ ኩነኒ ወሀቤ።

ዚቅ
ጊዮርጊስ ምሉዓ ፍቅር ከመ ጽጌ ረዳ፤ዘጥዑም ጼና መዓዛሁ፤አረጋዊ ዓፀደ ወይን ዘጽድቅ ዘይፈራ አስካለ ሕይወት።

ወረብ
ጊዮርጊስ ምሉዓ ፍቅር ከመ ጽጌ ረዳ ዘይወጽእ እምአፉሁ ዕጣነ ቅድስና/፪/
ለገቢረ ሠናይ ዘይውኅዝ ከመ ማይ ምስለ ገብረ ክርስቶስ/፪/

መልክአ ጊዮርጊስ
ሰላም ዕብል አፃብአ እዴከ የውጣ፤ወለአጽፋሪሆን ዓዲ ዲበ ከተማሆን ዘተለብጣ፤ጊዮርጊስ ኩኑን ለዓራተ ሐጺን በዉስጣ፤ቅዱሳት አብዒከ ዲበ ርእስየ ይሱጣ፤ቅብዐ ቅድስና ዕፍረተ ዘዕፁብ ሤጣ።

ዚቅ
ብፁዕ ጊዮርጊስ በጽጌ ሃይማኖት ሥርግው፤ከመ ርኄ አፈዉ ዜናሁ ፍትዉ።

ዓዲ ዚቅ
ሃሌ ሉያ አጻብኢሁ ፍሁቃት፤ከናፍሪሁ ጽጌ ዘወልድ እኁየ፤እለ ያዉኅዛ ከርቤ።

መልክአ ጊዮርጊስ
ሰላም ለመቃብርከ ምክሐ እድያሚሃ ወዓጸዳ፤ለምድረ ሙላድከ ልዳ፤ጊዮርጊስ ዘልፈ ሀብተ በረከት ዘእፈቅዳ፤ከመ ትጸጊ ሕንባበ ረዳ ለኢያሪኮ በዓዉዳ፤በዲበ ድማኅየ ትጽጊ እምሰማይ ወሪዳ።

ዚቅ
ዘይጸጊ ወይፈሪ እስከ አድያሚሃ ለዮርዳኖስ፤እስመ ስብሐተ ሊባኖስ ተዉህበ ሎቱ ለክብር ወለቀናንሞስ።

ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።

ወረብ
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ ለማርያም[፪]
ማርያም ተዓይል ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ ከመ ዖፍ[፪]

ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤እንዘ ከመ ዝናም ያንጸፈጽፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ።

ማኅሌተ ጽጌ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ ዘይኀቱ፤ዘተጽሕፈ ብኪ ትእምርተ ስሙ ወተዝካረ ሞቱ፤አክሊለ ጽጌ ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግሥቱ፤አንቲ ኩሎ ታሰግዲ ሎቱ፤ወለኪኒ ይሰግድ ውእቱ።

ወረብ
ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ ክበበ ጌራ ወርቅ ጽሩይ እምዕንቄ ባሕርይ[፪]
አክሊለ ጽጌ ማርያም ቀጸላ መንግሥቱ ለጊዮርጊስ[፪]

ዚቅ
ሰዓሊ ለነ ማርያም፤አክሊለ ንጹሐን ብርሃነ ቅዱሳን።

ምልጣን
ዝንቱሰ ብእሲ ኮከበ ክብር ዘዓቢየ ኃይለ ይገብር፤ጊዮርጊስ ኃያል መስተጋድል ስምዓ ጽድቆሙ ለቅዱሳን፤አማን ብርሃን ሰምዓ ብርሃን።

እስመ ለዓለም
አግዓዝያን አንትሙ፤ከመ ፀሐይ ይበርህ ገጾሙ፤አክሊለ ስምዕ ዲበ ርእሶሙ ከመ ኮል መዓዛ አፉሆሙ፤ሠረገላሆሙ ጽኑዕ፤ምስለ መላእክት የኃድራ ነፍሳቲሆሙ።

እመሒ ስሕተኩ አንትሙ እለ በመንፈስ አርትዕ(የተሳሳትኩት ቢኖር እናንተ በመንፈስ ያላችሁ አቃኑት)
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
. የ አ ሚ ና ዳ ብ ፡ ሠ ረ ገ ላ ፡ አ ን ቺ ፡ ነ ሽ
༺◉❖═───◉●◉🌹🌹🌹◉●◉────═❖◉༻
#አባ_ሕርያቆስ ❝ የአሚናዳብ ሠረገላ አንቺ ነሽ በማለት አመስግኗታል መተርጉማኑ እመቤታችን በአሚናደብ ሠረገላ የተመሰለችበትን ምሥጢራዊ ምክንያት ሲናገሩ እንዲህ ይላሉ የአሚናደብ ሠረገላ ልዝብና ፈጣን ምቹ ነበረች እመቤታችንም ለነፍስ ለሥጋ የምትመች በንጽሕና በቅድስና የለዘበች ለምሕረት የፈጠነች አፍጣኒተ ረድኤት ሰአሊተ ምሕረት ምዕራገ ጸሎት ናትና።

#አባ_ጊዮርጊስ_በሰዓታቱ ደግሞ ❝ በጭንቅ ጊዜ ረድኤትን የምታፋጥኚ ማርያም ሆይ ! እንደ ዐይን ጥቅሻ በላባ ቤት ያዕቆብን የረዳሽው አንቺ ነሽ በሁሉ ሐሳቧ በሁሉ ልቡናዋ አንቺን የማትወድ ነፍስ ከወገኗ ተለይታ ትጥፋ ። ❞ በማለት የአምላኳን እናት ሰማያዊቷን ንግሥት የዓለምን ሁሉ እመቤት ድንግል ማርያምን የማትወድ ነፍስ እድል ፈንታዋ ጽዋ ተርታዋ ሲኦል መሆኑን ተናግሯል ።

#ቅዱስ_ያሬድም እመቤታችን አደፍ ጉድፍ የሌለባቸው ቅዱሳት ሕዋሳቶቿ በንጽሕና በቅድስና ያጌጡ ልብሶቿ እንደ ስሂን ሽቶ የጣፈጡ የቃሏ ንግግር ከወይን ይልቅ እንደሚጥም ሲዘምር እንዲህ አለ ፦

❝ እንደ ሮማን ቅርፊት ቀይ ናቸው የልብሶቿ መዐዛ ስሂን እንደሚባል ሽቱ መዐዛ ነው የአማኑኤል እናት ድንግል ማርያም በእሾህ መሐል ያበበች በእውነት #የሃይማኖት_አበባ_ናት የቃሏ ጥፍጥና ከወይን ይልቅ ያማረ የጣፈጠ ነው የቅዱስ ቃል መዝገቡ የሆንሽ ፈጣን ደመና ሆይ ! ከከናፍርሽ የማር ወለላ ይፈሳል ። ❞ በማለት የእመቤታችን ፍቅሯ ፣ ቃል ኪዳንዋን ፣ ንግግሯና ቃሏ እንደ ማር የሚጣፍጥ ለነፍስና ለሥጋ የሚመስጥ መሆኑን ዘምሯል ።

#ቅዱስ_ኤፍሬምም ❝ ሳይተክሏት ተተክላ ውኃ ሳያጠጧት ለምልማ አብባ አፍርታ የተገኘች የአሮን በትር ነበረች ያለዘርአ ብእሲ ሰው ሆኖ ያዳነን አምላክን የወለድሽ እመቤታችን ሆይ ! አንቺም እንደ እሷ ነሽ ❞ በማለት በንጽጽር መስሎ አመሰግኗታል

#አባ_ሕርያቆስ በቅዳሴው የእመቤታችን ውበት አፍአዊ ብቻ ሳይሆን ውሳጣዊ ፣ ሥጋዊ ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ፣ ጊዜዊ ሳይሆን ዘለዓለማዊ በመሆኑ ውበቷ አምላክን ከዙፋኑ እንደሳበው ሲነግረን እንዲህ አለ ፦

❝ እግዚአብሔር አብ ከሰማይ ሆኖ በእውነት በአራቱ ማዕዘን ተመለከተ መረመረ ፤ በንጽሕና በቅድስና የተዘጋጀ እንደ አንቺ ያለ አላገኘም ፤ ስላላገኘ መዐዛ ሃይማኖትሽን መዐዛ ምግባርሽን ንጽሕናሽን ቅድስናሽን ወደደ #ሥጋሽን_ለልጁ_ተዋሕዶና_ለልጁ_እናትነት_መረጠ ቢመርጥሽ የሚወደውን የሚወልደውን ፤ ተቀዳሚ ተከታይ የሌለው ልጁን ውረድ ተወለድ ሙት ተሰቀል ብሎ ወደ አንቺ ሰደደ ❞ አለ ።

#አንቀጸ_ሰላማዊትሆይ_ሰላም_ላንቺ_ይሁን_ያንቺ_ሰላም_ከሁላችን_ጋር_ይሁን
#የጌታችን_እናት_እናታችን_ማርያም_ሆይ_ለምኚልን_ከደጅ_እንዳንቆም_አማልጂን

#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘን_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
፯ኛ ዙር ዓመት ፭ኛ ሳምንት
ማሕሌተ ጽጌ
ጥቅምት ፳፭
በዓለ አቡነ አቢብ ወመርቆሬዎስ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
2024/09/22 16:23:02
Back to Top
HTML Embed Code: