Telegram Web Link
የትምህርት ዕድል ያመለጠህ መስሎህ ነው? ገና ሺህ የትምህርት ዕድሎች አሉህ:: ዕድሜህ ያመለጠህ መስሎህ ነው? ነገ የሚጠብቁህ ብሩሕ ዘመናት እኮ ቁጭ ብለው አሉ? የሚረዳኝ ሰው የሚያስብልኝ ሰው አጥቼያለሁ? ብለህ ከሆነም ካልሰሙህ ጥቂቶች በላይ ልንሰማህ የምንሻ "ሁላችን ከዚህ አለንና በራስህ ክፉ ነገር አታድርግ"

መከራ ጸናብኝ ኑሮ ጨለመብኝ የሀገሪቱ ሁኔታ ተስፋ አሳጣኝ ብለህ ይሆን? እኛስ አብረንህ አይደልንም? አብረን ከገባንበት ችግር አብረን ብንወጣ አይሻልም? ከአንተ በባሰ ሁኔታ የታሰርንና የተገረፍን ጳውሎሶችና ሲላሶች "ሁላችን በዚህ አለንና በራስህ ክፉ አታድርግ" ስንልህ ስማን::

ይልቅ አንተም እንደ ወኅኒው ጠባቂ "እድን ዘንድ ምን ላድርግ ብለህ?"ነፍስህን የምታድንበትን መንገድ ወደ መቅደሱ ቀርበህ ጠይቅ::

ወዳጄ ይህንን ጽሑፍ ያነበብኸውም በሕይወት ስላለህ ነው:: የአንተን ዓይን የሚጠብቁ ብዙ ጽሑፎች ፣ የአንተን ጆሮ የሚፈልጉ ብዙ ድምፆች ፣ የአንተን መሐረብ የሚፈልጉ ብዙ ዕንባዎች ፣ የአንተን ሳቅ የሚፈልጉ ብዙ ቀልዶች ... ገና ብዙ ብዙ አሉ::

ስለዚህ ሰይጣንን አሳፍረው:: እንዲህ በለው :-

"ጠላቴ ሆይ፥ ብወድቅ እነሣለሁና፥ በጨለማም ብቀመጥ እግዚአብሔር ብርሃን ይሆንልኛልና በእኔ ላይ ደስ አይበልሽ" ሚክ. 7:8

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 2016 ዓ.ም.
ሜልበርን አውስትራሊያ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ [ዋጋን በምድር የሚያስቀር ውዳሴም ሆነ ሌላ] ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
Audio
ጽጌ አስተርአየ /አበባ ታየ/ 
                                                  
Size:- 60.3MB
Length:-2:53:09
       
     በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
#ጥቅምት_14
አቡነ #_ አረጋዊ የተሰወሩበት፤ ቅዱስ #_ ገብረክርሰቶስ በዓለ እረፍት፤ ቅዱስ #_ ሙሴ_እግዚአብሔር በዓለ ዕረፍታቸው ነው፡፡(ታቦታቸው በቀጨኔ ደብረሰላም ያለ) በጋዛ ምድር ኢትዮጵያዊውን ጃንረባ ባኮስን ያጠመቀው ረድኡ ሐዋርያ ቅዱስ #_ ፊሊጶስ ዕረፍቱ ነው፡፡

ጥቅምት 14 ፤ አቡነ አረጋዊ ( ዘሚካኤል ) ወቅዱስ ሙሴ ብእሴ እግዚአብሔር
#አቡነ_አረጋዊ (#ዘሚካኤል)
፠ ከእንጦንስ ከመቃርስ እና ከጳኵሚስ የምንኵስና ሐረግ አራተኛ ትውልድ ናቸው፣
፠ ደቀ መዛሙርቶቻቸውም 6 ሺህ የደረሱ ናቸው፣
፠ ከቅዱስ ያሬድ ጋር እጅግ ይዋደዱ የነበሩ ፣ ዝማሬውንም ለመስማት ከጐንደር ለመጣ ሲል በጸጋ አይተው ደብረ ዳሞ ላይ ደቀ መዛሙርቶቻቸውን ሰብሰበው ይጠብቁ የነበሩ ፡፤
፠ ታላላቅ የኢትዮጵያ ነገሥታትን ለባረኩ ይመጠላቸው የነበረ ..
፠ አጼ ገብረ መስቀል በተመስጦ የቅዱስ ያሬድን እግር በጦር በወጋው ጊዜ ታለቅ ግብዣን አድርገ የዛኔም አቡነ አረጋዊ ቀድሰዋል፣ ቅዱስ ያሬድም ዘምሯል ፤ ታላቅ ሥርዓትንም አስጀምረዋል፡፡
___________

፠ ትውልዳቸው ሮም ሲሆን እግዚአብሔርን ከሚፈሩ ከአባታቸው #ይስሐቅና ከእናቸው #እድና የተገኙ የቅዱሳን ፍሬ ናቸው ፤ ወንድሞቹም #ቴዎድሮስ እና #ገብረ አምላክ ይባላሉ፡፡
፠ የቀድሞው ስማቸው #ዘሚካኤል ነበር፡፡ “አረጋዊ” የተባሉት ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ነው፡፡ በእድሜ ልጅ ሲሆኑ በመንፈሳዊ ሕይወታቸውና ሥራቸው አዋቂ ስለነበሩ አረጋዊ ብለዋቸዋል፡፡

፠ወላጆቻቸው ቅዱሳት መጻሕፍትን እያስተማሩ አሳደጉት፤ እሱም በመንፈስ ቅዱስ ኀይል እየጸናና እየበረታ ሄደ፡፡ ዕለት ዕለት ጧትና ማታም ወደቤተክርስቲያን እየሄደ ጸሎት ከመጸለይ አያቋርጥም ነበር፡፡እድሜውም ለጋብቻ ሲደርስ አባትና አናቱ ያገባ ዘንድ ሚስት አጩለት፡፡ እሱ ግን ፈጽሞ እምቢ አለ፤ ከሕፃንነቱ ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ እየተቃኘ የምንኵስና ሕይወትን ለመኖር ፈልጓልና፡፡ ከብዙ ዘመንም በኋላ የምንኵንስና ሕይወትን ለመኖር ወደ አባ ጳኵሚስ ዘንድ ሄደ፤ ወደ ገዳሙም በገባ ጊዜ አንድ መነኵሴ አገኙትና ‹‹ልጄ ሆይ ከወዴት መጥተሃል እነሆ አንተ ሕፃን እንደሆንክ እመለከታለሁና›› አሉት፡፡ እሱም አመጣጡ ከሮም እንደሆነና ከአባ ጳኵሚስ ዘንድ የሚፈልገው ነገር እንዳለ ነገራቸው፡፡ እሳቸውም ነገሩን ከሰሙ በኋላ ወደ አባ ጳኩሚስ ዘንድ ወሰዱት፡፡አባ ጳኩሚስም በአየው ጊዜ ከመንበሩ ተነስቶ በፍፁም ፍቅር አቅፎ ሳመው የእግዚአብሔር ጸጋ በእሱ ላይ አድሯልና፡፡ ከዚያም ቀጥሎ ስለምን ጉዳይ ወደ እሱ እንደመጣ ጠየቀው፡፡ አባ ዘሚካኤልም ‹‹እንደአንተ እንደ አባቴ መነኵሴ እሆን ዘንድ መጥቻለሁ›› አለው፡፡ አባ ጳኩሚስም ‹‹ልጄ ሆይ አንተ የንጉሥ ልጅ እንደመሆንህ መጠን የመንግሥቱ ወራሽ ነህና መንኵሰህ ለመኖር እንደምን ይቻልሃል?›› ሲል መለሰለት፡፡ አባ ዘሚካኤል ግን የምድር መንግሥት ኀላፊ ጠፊ እንደሆነ ያውቃልና ከዓለም ንግሥና ይልቅ ዘለዓለማዊ መንግሥትን ይወርስ ዘንድ እንደሚሻ ያመነኵሰውም ዘንድ አጥብቆ ጠየቀው፡፡ አባ ጳኩሚስም ፈተናን ፈትኖት መቋቋም የሚችል ከሆነ እንደሚያስገባው ነግሮ የተለያዩ ፈተናዎችን ፈትነው፡፡ አባ ዘሚካኤልም የተባለውን የታዘዘውን ሁሉ በትጋት ፈጸመ፡፡ አባ ጳኵሚስም ስለሃይማኖቱ ጽናት ስለጠባይና ስለቅንነቱ እጅግ አድርጐ ወደደው፡፡ ከዚያም አስኬማው ወይም ቆቡ ላይ ወደ እግዚአብሔር ጸልዮ አመነኰሰው፤ ስሙንም ዘሚካኤል ብሎ ጠራው፤ በዚህ ጊዜ #እድሜው 14 ዓመት ነበር፡፡

፠አባ ዘሚካኤል አስኬማ ካደረገ በኋላም በታላቅ ትጋቱ በጸሎቱና በጾሙ አባ ጳኵሚስ ተደነቀ፡፡ ስለሱም ዝናው በየሀገሩ ሁሉ እስከ አባቱ አገር ሮም ድረስ ተሰማ፡፡ አባ ዘሚካኤል ገና በሕፃንነቱ የምንኵስና ማዕረግ መቀበሉን ከሰሙ በኋላ ወደ እሱም 8 ቅዱሳን የመጡ ነበሩ፡፡ እነሱም፦ አባ #_ ሊቃኖስ ከቁስጥንጥንያ(ገዳማቸው በአኵሱም የሚገኝ )፣ አባ #_ ይምዓታ (ገዳማቸው በኃውዜን የሚገኝ (ትግራይ) ከሀገረ ቁስያ፣ አባ #_ ገሪማ ከሮም(ገዳማቸው በአኵሱም የሚገኝ ፣ ከአንፆኪያ አባ #_ ድሕማ፣ ከቂልቅያ አባ #_ ጉባ፣ ከእስያ አባ #_ አፍጼ፣ ከሮሚያ አባ #_ ጴንጠሌዎንከሮም(ገዳማቸው በአኵሱም የሚገኝ ) ፣ ከቂሳርያ አባ አሌፍ ነበሩ፡፡ እነሱም አባ ጳኵሚስ የምንኵስናውን አፅፍ አጐናፀፏቸውና አመነኮሷቸው፡፡ ለእያንዳንዳቸውም ስማቸውን ሰየሟቸው፡፡ እኒህም አባቶች ስለትዕግስት፣ አርምሞ፣ ትህትና፣ ስለሥርዐተ ማኀበር አመሠራረት ከአባ ጳኵሚስ ዘንድ ተማሩ፡፡

፠ ከዚህ በኋላ በዚያ ገዳም ለብዙ ዓመታት በፍቅር በአንድነት ከአባ ቴዎድሮስ ጋር ተቀመጡ፡፡ በዚህን ጊዜ ግን አባ ጳኩሚስ አርፈው አባ ቴዎድሮስ ተተክተው ነበር፡፡ እነዚህም አባቶች ወደየሃገራቸው ሄደው ማስተማርና ሃይማኖትንማስፋፋት እንዳለባቸው ተስማምተው ወደየሀገራቸው ተመለሡ፡፡ አባ ዘሚካኤል ግን በዚያው ቆየ፡፡ እሱ ልቡን የነካችዉ ዜናዋንም የሰማላት ሃገር ነበረችና፡፡ ይህቺውም ሃገራችን #ኢትዮጵያ ነበረች፡፡ እሱም ማንም ሰው ሳያውቅና ሳያየው ከሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ጋር ቅዱስ ሚካኤል እየመራቸው መጥተው ጐብኝተዋታል፡፡ ያለመምህራንና ያለአስተማሪ ያመነች የዚህችን ሀገረ እምነቷንና ሥነስርዐቷን ተመልክቶ ተደነቀ፡፡ እነዚያን 8 መነኰሳትም ከያሉበት ስለሃገሪቷ እየነገረ ጠራቸው የሚገርመው ግን እነሱም ስለዚህች ሀገር እንደሰሙ ያለምንም ማመንታት መጥተዋል፡፡ እነሱም ሕዝቡን እንደሰሙት አገኙት፡፡ አባ ዘሚካኤል አቡነ አረጋዊ የሚለውን ስያሜ ያገኙት ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ትህትናቸውና ታዛዥነታቸው እሳቸውሲመነኩሱ ገና ሕፃን ነበሩ ስራቸው ግን የአረጋውያን ነበርና አንተስ ሐፃን አይደለህም የልጅ አዋቂ ነህ ሲሉ #አረጋዊ አሏቸው፡፡ አባታችን አቡነ አረጋዊ ወደ ኢትዮጵያ የገቡበትም ቀን ጥቅምት 11 ነበር ፡፡

አቡነ አረጋዊ በኢትዮጵያ ሲኖሩ በሄዱበት ስፍራ ብቻቸውን የሚፀልዩበትን ቦታ ሁል ጊዜ ይፈልጉ ነበር፡፡ አንድ ቀንም በመንገድ እየሄዱ ሳሉ ትልቅ ተራራን (ደብረ ዳሞን) ተመለከቱ፤ ከሦስተኛው ቀን በኃላም የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መጥቶ ‹‹አንተ እግዚአብሔር ያከበረህ ቅዱስ ሆይ ምን ያስጨንቀሃል›› አለው፡፡ አባታችንም አቡነ አረጋዊም ‹‹ከዚህች ተራራ ላይ ወጥቼ ስለኃጥያቴ እናዘዝና እለማመን ስለበደሌም ይቅርታን እጠይቅ ዘንድ እወዳለሁ›› አለው፡፡ ቅዱስ ሚካኤልም እንዲፀልይና ታላቅ ዘንዶም ወደርሱ እንደሚላክለት ነገረው፡፡ በሦስት ሰዓትም ዘንዶው መጣ፤ አባታችንም የዘንዶውን ጅራት ይዘው ወደ ላይ ወጡ ብቻቸውን አልነበሩም ፡፡ ዘንዶው እንዳያስደነግጣቸውና እንዳይጐዳቸው ሰይፍን ይዞ ቅዱስ ሚካኤል ይጠብቃቸው ነበር እንጂ፡፡ ቢዚያችም ሰዓት ተራራዋ ደብረ ታቦርን መስላ ነበር:: በዚህችም ላይ ንጉሥ አጼ ገብረ መስቀል ቤ/ክ ከአነጹ በኃላ የቅዳሴ ቤቱ ዕለት አቡነ አረጋዊ ቀድስው ንጉሡም ሠራዊትም ሕዝቡም ጳጳሳቱም ጭምር ሥጋ ወደሙን ተቀብለዋል፡፡ ንጉሡም በረከተን ከአባታችን ተቀብሉ ወደ አኵሱም ተመልሷል፡፡ ሲመለስም ሰርቶት የነበረውን ድልድላይ ላፍረሰው ወይ ሲላቸው ዳሕምሞ ብለውታል ትርጕሙም ‹‹የሰራኸውን ደረጃ ናደው ፥ አፍርሰው እንጂ አትተወው›› ፡፡ ከዚ በመነሳት ዳሞ ተብላለች፡፡
እግዚአብሔርም ሰማያዊ ኅብስት ትሁነህ ብሎ ደብረ ዳሞን ስጥቶዋቸዋል ይህም በመንፈስ ለሚወለዱት ልጆቹ እስከ ዘለዓለም ማርፍያ እንድትሆን ነው ፡፡
፠ አባታችን አቡነ አረጋዊም የእርጅና ዘመናቸው በደረሠ ጊዜ እግዚአብሔር ወደ እርሱ በመንፈቀ ሌሊት ተገልጾ ቃልኪዳን ሰጣቸው፡፡ ይኸውም ‹‹መታሰቢያህን ያደርግ በጸሎትህም የተማመነውን ሁሉ እኔ በመላእክት ፊት ሞገስን ቧለሟልነትን እሰጠዋለሁ፤ በእውነተኛ ሀይማኖት ሁሉ የገድልህን መጽሐፍ የጻፈ፤ ያጻፈ፤ የተረጐመ እኔ ስሙን በሕይወት መጽሐፍ እጽፈዋለሁ፤ ይህ ሁሉ ላደረገም እስከ 14 ትውልድ ድረስ እምርልሀለሁ›› አላቸው፡፡ ከዚህም በኋላ አባታችን አልሞተም በዓመቱ "ሞትን የማይቀምሱ አሉ፡፡" ብሎ እንደተናገረው /ማቴ 16 ፥ 28/ ጥቅምት 14 ቀን 558 ዓ/ም #ተሠወረዋል፡፡ ይህም እንዲህ ነው
አባታችን አቡነ አረጋዊ ማትያስ ለተባለው ደቀ መዛሙር ጌታችን ተገልጦ የሰጣቸውን ቃል ኪዳንና ይህ መጽሐፍ ተጽፎ ለልጅ ልጅ መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ነገሩት፤ (መዝ ፻፲፩/፻፲፪፥፮) ወንድሞቹ ደቀ መዛሙርቶቹ በተሰበስቡበትም ሁሉንም ከአስተማሩ በኋላ ‹‹ከዛሬ ጀምሮ በሥጋ አታዩኝም›› አላቸው፡፡ ደቀ መዛሙርቱም በመሪር ኃዘን እግራቸው ሥር ወድቀው አለቀሱ፤ አባታችን አቡነ አረጋዊም አጽኗኗቸው፡፡ ጥቅምት ፲፬ ቀን ቅዱስ አባታችን አቡነ አረጋዊ በ፺፱ (99) ዓመታቸው ተሰወሩ፤ በዚያም #ከመቋሚያና #ከመስቀል በስተቀር ምንም የተገኘ የለም፡፡ ገድላቸውንም ደቀ መዛሙርታቸው ማትያስ እና ዮሴፍ ጽፈዋል፡፡ ከዚያም አባ ማትያስ ደብረ ደሞን ለማስተዳደር ተሾመዋል፡፡
ከጻድቁ አባት በረከት ይክፈለን፤ በቃልኪዳናቸው ይጠብቀን፤ አሜን፡፡

#_ እግዚአብሔር አምላክህ አንተን መርጦሃልና እንደ ኹለቱ ነቢያት ለተከወነ መሠወርህ ሰላምታ የሚገባህ ደግ አገልጋይና የታመንህ መጋቤ ቤቱ ቅዱስ አረጋዊ ሆይ በዐሥሩ አህጉር ተሹመህ ኀምስቱን መካልይ የተቀበልህ አንተ አይደለህምን?፡፡ _#
#መልክአ አቡነ አረጋዊ

#ቅዱስ ሙሴ ብእሴ እግዚአብሔር በዓለ #ዕረፍታቸው_፡፡(ታቦታቸው በቀጨኔ ደብረሰላም ያለ)
ታሪኩ ከሙሽራው ቅዱስ ገብረ ክርስቶስና ከቅዱስ ቶማስ ዘቶርማቅ ጋር ተመሳሳይ የሆነው(ቅዱስ ያሬድ ለእመቤታቸን ( ትዕግሥትኪ ፈድፈደ እምትዕግሥተ ኢዮብ ጻድቅ ፤ወእማርቆስ #ዘቶርማቅ ፤ ወገብረ ክርስቶስ መርዓዊ ተወካፌ ሕማም መጽዕቅ፡፡ ) ብሎ እንደጻፈው ቅዱስ ቶማስ ዘቶማርቅ እንደ ኢዮብ ታጋሽ የሆነ ጻድቅ ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ሰው የተባለ ትዕግሥኛው ቅዱስ ሙሴ ዕረፍቱ ነው፡፡
፠፠ ፠፠፠ ፠፠፠ ፠
/በቀጨኔ ደ.ሰላም መድኀኔዓለምና ደ.ት.ቅ.ገብርኤል ቤ.ክ ፍኖተ ሕይወት ሰ.ት.ቤት የተዘጋጀ
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵
ስርአተ ዋዜማ ዘጥቅምት አቡነ አረጋዊ
🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃🍃
በ፩-
ዝስኩ አረጋዊ አቡክሙ ፥ፃድቅ ወሔር፥በተአምኖ ኤለ፥በተአምኖ  ተጋድለ፤ማ፦ ኤለ ውስተ አድባር ወበአታት

ምልጣን፦
በተአምኖ ኤለ፥በተአምኖ ተጋድለ፤ ኤለ ውስተ አድባር ወበአታት፤ኤለ ውስተ አድባር ወበአታት

አመላለስ፦
ኤለ ውስተ አድባር ወበአታት/፪/
ኤለ ውስተ አድባር ወበአታት/፬/

ለእግዚአብሔር ምድር በምላ፦
አባ ጸሊ በእንቲአነ ጸሎትከ ይብጽዐነ አባ ጸሊ በእንቲአነ

እግዚአብሔር ነግሠ፦
ወረደ ብርሃን ኀበ መቃብሩ ለብእሴ እግዚአብሔር፣ወኮነ መቃብሩ ዘየሐዩ ዱያነ፤ጸሎቱ ለገብረ ክርስቶስ፤ወበረከቱ የሃሉ ምስሌነ

ይትባረክ፦
ኪያከ መሠረት እንተ ብነ አባ ጸሊ በእንቲአነ እስመ ፀሎተ ጻድቅ ይሰምዕ እግዚአብሔር

ሰላም፦
ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ዜና ምግባሩ ትሩፍ ለአረጋዊ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ኮከብ ገዳም ፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ፀጉያን እሙንቱ እምፅጌ ሮማን ወቀ ይሐን እምከላ ገዳም ፤ ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም ደቂቁ ሔራን ልኡላን ክቡር ወስያ፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም እንዘ የአርግ መስዋዕት ሰላም ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም፤ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም

አመላለስ፦
ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም/፪/
ድምፀ ወተሠብከ ውስተ አለም/፬/

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹🌹
ስረዓተ ማኅሌት ዘጥቅምት አቡነ አረጋዊ
🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀🍀
ስቡዕ ከተባለ በኃላ

ገባሬ ኩሉ፦
ሰላም ለአብ ገባሬ ኩሉ ዓለም፤ለወልድ ሰላም ወለመንፈስ ቅዱስ ሰላም፤ለማርያም ሰላም ወለመላእክት ሰላም፤ሰላም ለነቢያት ወለሐዋርያት ሰላም፤ለሰማዕታት ሰላም ወለጻድቃን ሰላም።

ዚቅ፦
ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ሃሌ ሉያ ንፌኑ ስብሐተ፣ ለዘአክበረ ነቢያተ፤ንፌኑ ስብሐተ ወለዘኀረየ ሐዋርያተ፣ንፌኑ ስብሐተ ወለዘአፍቀረ ካህናት፤ንፌኑ ስብሐተ ወለዘአጥብዐ ሰማዕታተ፤ንፌኑ ስብሐተ ወለዘአጽንዐ መነኮሳተ፤ንፌኑ ስብሐተ እለ ዔሉ አድባራተ፤ንፌኑ ስብሐተ ንበሎ ኩልነ፤አቢተነ አንተ

ዘጣዕሙ፦
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ህይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

ዚቅ
በ2 ልዑለ ረሰዮ ለመሠረትኪ፤ዓረፋትኪ ዘመረግድ፤ደቂቅኪ ምሁራን በኀበ እግዚአብሔር፤ቆዓ ትጼኑ ቆዓ ጽጌ ወይን፤ወታፈሪ ለነ አስካለ በረከት፤ጽዮን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ጽጌ ደንጐላት ዘዉስተ ቆላት።

መልክዐ አቡነ አረጋዊ፦
ሰላም ሰላም ለዝክረ ስምከ ቀዋሚ፤ለዓለመ ዓለም ዘይሄሉ ከመ ተብህለ ቀዳሚ፤አረጋዊ የዋህ ተመሳሌ ዳዊት ኢተቀያሚ፤ላዕሌየ በተሀብሎ አመ ተንሥአ ረጋሚ፤በሰዓተ በቀል ይብጽሖ መክፈልቱ ለሳሚ።

ዚቅ
ፃማ ቅዱሳን ዲቤሁ አዕረፈ፤አፈዋተ ወንጌል ጸገየ ዘልፈ፤አባ አረጋዊ ሃይማኖተ ተአጽፈ፤ኀበ ዓምደ ወርቅ ስሙ ተጽሕፈ።

ወረብ፦
ተጽሕፈ"ሃይማኖተ"/፪/ፃማ ቅዱሳን/፪/
ኀበ ዓምደ ወርቅ/፪/ስሙ ስሙ ለአረጋዊ/፪/

መልክዐ አቡነ አረጋዊ፦
ሰላም ለአዕዛኒከ ወለመላትሒከ እቤ፤እንዘ አቀርብ ስብሐተ ወአደምፅ ቀርነ ይባቤ፤ምስለ ገብረ ክርስቶስ አርክከ ዘተሴሰይከ እክለ ምንዳቤ፤አዕርገኒ ሊተ አረጋዊ ኀበ ደብረ ስኂን ወከርቤ፤ወማዕከለ ማኅበር ዓቢይ ሢመኒ መጋቤ።

ወረብ፦
አዕርገኒ ሊተ"አረጋዊ"/፪/ኀበ ደብረ ከርቤ/፪/
ወማዕከለ ማኅበር ሢመኒ መጋቤ ሢመኒ/፪/

ዚቅ
አዓርግ ለልየ ኀበ ደብረ ከርቤ፤ውስተ አውግረ ስሂን፤ወግረ ስሂንስ ሥጋሁ ለአረጋዊ ዘኢይትነገር።

ወረብ
አዓርግ ለልየ ኀበ ደብረ ከርቤ(፪) ውስተ አውግረ ስሂን/፪/
ወግረ ስሂንሰ ዘኢይትነገር ሥጋሁ ለአረጋዊ/፪/

መልክዐ አቡነ አረጋዊ፦
ሰላም ለቃልከ ወለእስትንፋስከ ዕብሎ፤ወለጉርዔከ እምወይን ጣዕመ ፍቅረ ክርስቶስ እንተ አጥለሎ፤አቡቀለምሲስ እለ ትሩፈ ምግባር ወተጋድሎ፤አይድዓኒ እስኩ ዘነጸርከ ኩሎ፤ምሥጢረ ምሥጢራት ኅቡዐ በሰማይ ዘሀሎ

ወረብ፦
አይድዓኒ እስኩ አረጋዊ ዘነጸርከ ኩሎ/፪/
ምሥጢረ ምሥጢራት"ኅቡዐ"/፪/ በሰማይ ዘሀሎ/፪/

ዚቅ-
ዘእምደብረ ደናግል አባ ኤልያስ፤ወትሩፈ ምግባር አርከሌድስ፤ አረጋዊ ዘዉገ ሙሴ ወገብረክርስቶስ፤አማን ዘቀደሶ መንፈስ ቅዱስ።

ወረብ
ዘእምደብረ ደናግል አባ ኤልያስ/፪/
ወትሩፈ ምግባር አረጋዊ ዘዉገ ሙሴ ወገብረክርስቶስ/፪/

መልክዐ አቡነ አረጋዊ፦
ሰላም ለአማዑቲከ እምላህበ ፍቅረ ገድል ዘዉዕየ፤ወለንዋየ ዉስጥከ መዝገብ ዘተመሰለ ባሕርየ፤አረጋዊ ኪያከ ዓቅመ ፈተወ ልብየ፤ማኅሌተ ስምከ ከመ ይዘምር አፋየ፤በምድረ ኅሊናየ ናሁ ፍቅርከ ጸገየ።

ዚቅ
አረጋዊ ምሉዓ ፍቅር ከመ ጽጌ ረዳ፤ዘጥዑም ጼና መዓዛሁ፤አረጋዊ ዓፀደ ወይን ዘጽድቅ ዘይፈራ አስካለ ሕይወት።

ወረብ
አረጋዊ ምሉዓ ፍቅር ከመ ጽጌ ረዳ ጽጌ ረዳ ከመ ጽጌ ረዳ/፪/
ጼና መዓዛሁ ዘጥዑም ጼና መዓዛሁ ለአረጋዊ/፪/

መልክዐ አቡነ አረጋዊ፦
ሰላም ለአካለ ቆምከ ዘኲለንታሁ ፍትው፤ወለመልክእከ ልሑይ በትርሢተ ጽጌ ሥርግዉ፤አረጋዊ እብለከ ውስተ ባሕረ መንሱት ድልው፤አስጥሞሙ ለአጽራርየ ዘመደ አራዊት ዘበድዉ፤ከመ ቀዳሚ ተሰጥሙ አኅርው።

ዚቅ
ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ፤ወበጽጌያት ምድረ አሠርጎከ፤ወስነ ገዳምኒ ምስለ ቅዱሳኒከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ
ወከመ ወሬዛ ኀየል መላትሒሁ፤ጉርዔሁ መዓርዒረ አምሳሉ ዘወይጠል፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ ሰማየ ወምድር ዘአንተ ፈጠርከ ፀሐየ ወወርኃ ዘአስተዋደድከ፤ወመኑ መሐሪ ዘከማከ በከዋክብት ሰማየ ዘከለልከ ወበጽጌያት ምድር አሠርጎከ።

ወረብ
ወከመ ወሬዛ ኀያል(፪)መላትሒሁ/፪/
ጉርዔሁ መዓርዒር ለአረጋዊ/፪/

ሰቆቃወ ድንግል
ብክዩ ኅዙናን ኀልየክሙ ስደታ፤ወላህዉ ፍሡሐን ተዘኪረክሙ ብዙኃ ሠናይታ፤ማርያም ተዓይል ከመ ዖፍ ውስተ አድባረ ግብጽ ባሕቲታ፤ተአወዩ በኃጢኦታ ሀገረ አቡሃ ኤፍራታ፤ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ።

ወረብ፦
ማርያም ከመ ዖፍ ተዓይል ባሕቲታ ውስተ አድባረ ግብጽ/፪/
ወደመ ሕፃናት ይውኅዝ በኵሉ ፍኖታ ይውኅዝ ደመ ሕፃናት/፪/

ዚቅ
አመ አጒየይኪ እምሰይፍ ዕጓለኪ በሐቂፍ፤ አድባራተ ኤልኪ ከመ ዖፍ፤ እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ፤እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ።

ወረብ፦
አመ አመ አጒየይኪ ዕጓለኪ በሐቂፍ/፪/
እንዘ ከመ ዝናም ያንደፈድፍ እምአዕይንትኪ አንብዕ ወእመላትሕኪ ሐፍ/፪/

ማኅሌተ ጽጌ
ለተአምርኪ ማርያም ኃጥእ ውእቱ ዘአስተቶ፤ ከመ ስብሐቲሁ ኢይርአይ እስመ ጽጌኪ አእተቶ፤ ለተአምርኪሰ እንዘ ይነግር ረድኤቶ፤ ቦ ዘፈለሰ ኃዲጎ ብእሲቶ፤ወቦ ገዳመ ዘተግህሠ መኒኖ መንግሥቶ።

ወረብ
ቦ ዘፈለሰ"ኃዲጎ ብእሲቶ"/፪/ ቦ ዘፈለሰ/፪/
ወቦ ገዳመ ዘተግህሠ መኒኖ"መንግሥቶ"/፪/ገብረ ክርስቶስ/፪/

ዚቅ
ትዕግሥትኪ ፈድፈደ እምትዕግሥተ ኢዮብ  ዘቶርማቅ፤ወገብረ ክርስቶስ መርዓዊ ተወካፌ ሕማም መጽዕቅ።

ወረብ
ትዕግሥትኪ ፈድፈደ እምትዕግሥተ ኢዮብ ወእማርቆስ/፪/
ወገብረ ክርስቶስ መርዓዊ(፪)ተወካፌ ሕማም/፪/

ምልጣን
ዘእምደብረ ደናግል አባ ኤልያስ፤
ወትሩፈ ምግባር አርከሌድስ፤አረጋዊ ጻድቅ ዘዉገ ሙሴ ወገብረክርስቶስ፤አማን ዘቀደሶ መንፈስ ቅዱስ።

ወረብ፦
"ዘእምደብረ ደናግል"/፪/አባ ኤልያስ/፪/
ወትሩፈ ምግባር አረጋዊ ክቡር ዘዉገ ሙሴ ወገብረክርስቶስ/፪/

እስመ ለዓለም
ንጉሥኪ ጽዮን አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት፤ ወለሰማይኒ በከዋክብት፤ ውእቱ ክብሮሙ ለቅዱሳን፤ ብርሃኖሙ ለመሐይምናን፤ ዘየአምር እምቅድመ ሕሊና፤ ዘይኄሊ ልብ አርአየ ኃይሎ፤ በላዕሌነ ወጸገወነ ሠናይቶ።

አመላለስ
ዘይኄሊ ልብ አርአየ ኃይሎ/፪/
በላዕሌነ ወጸገወነ ሠናይቶ/፪

ወረብ
ንጉሥኪ ጽዮን አሠርገዋ ለምድር በጽጌያት አሠርገዋ ለምድር/፪/
"ውእቱ ክብሮሙ"/፪/ ለቅዱሳን/፪/

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
19 K Telegram chanal የሚገዛ እውነተኛ ገዢ በውስጥ መስመር ያናግረኝ
👉መሸጫ ዋጋ 15K

@yesadikusitota
ይህ ትልቅ መንፈሳዊ ቻናል ችግር ቢደርስበት መቆያ አልያም መጠባበቂያ የሚሆነን #መዝገበ ሐይማኖት #የተሰኘ ቻናል ከፍቻለሁ! እናም አብሮነታችሁን join በማለት እንድታሳዩኝ በትህትና እጠይቃለሁ🙏🙏

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
mahlete Tsige.pdf
14.1 MB
አባ ጽጌ ድንግል የደረሰ

ማህሌተ ጽጌ
@EotcLibilery
@EotcLibilery
@EotcLibilery
18 K menber yalew መንፈሳዊ Telegram chanal የሚገዛ እውነተኛ ገዢ በውስጥ መስመር ያናግረኝ
👉መሸጫ ዋጋ 15K

@yesadikusitota
ይህ ትልቅ መንፈሳዊ ቻናል ችግር ቢደርስበት መቆያ አልያም መጠባበቂያ የሚሆነን #መዝገበ ሐይማኖት #የተሰኘ ቻናል ከፍቻለሁ! እናም አብሮነታችሁን join በማለት እንድታሳዩኝ በትህትና እጠይቃለሁ🙏🙏

@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
@mezigebekidusan
2024/09/24 22:17:57
Back to Top
HTML Embed Code: